Tuesday, February 25, 2014

ይድረስ ለፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ፡- በኢትዮጵያ ታሪክ ተወቃሾቹ የኦሮሞ ሕዝብና ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ብቻ ነውን እንዴ?!


Read in PDF
በዲ/ን ኒቆዲሞስ ዕርቅ ይሁን  ~ nikodimos.wise7@gmail.com
‹‹ዕርቅና ሰላም የሕይወት ቅመም፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደውለታ ቢስ ለሚቆጥሩ ወገኛ ሁሉ የሚሆን መልስ እነሆ!›› በሚል ርእስ የጻፉትን ጦማር እጅግ የማክበርዎና ኢትዮጵያዊው የምሆን ወንድምዎ ደጋግሜ አነብበኩት፡፡ ፕሮፌሰር በትክክል ተረድቼዎት ከሆነ እርስዎ በጽሑፍዎ ለማስተላለፍ የፈለጉት ዋንኛ መልእክትዎ፣ አንድም ‹‹ዕርቅንና ሰላም መስበክ›› ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ጠላት ወይም ውለታ ቢስ አድርገው ለሚቆጥሩ ወገኛ ሁሉ መልስ ይሆናል በሚል እነሆ ያሉት ጦማር እንደሆነ ነው፡፡
ፕሮፌሰር ለረጅም ዓመት ካካበቱት ዕውቀትዎ፣ በትምህርት ዓለም በሥራ፣ በምርምርና ጥናትዎ ከሕይወት ተሞክሮዎና ልምድዎ በመነሳትና እንዲሁም ዕድሜዎን ሙሉ ከመረመሯቸውና በአካዳሚያው ዓለም አንቱ ከተሰኙባቸው፣ ከበሬታን ካተረፉባቸውና ጥንታዊ የኾኑ መዛግብቶቻችንን በመመርመር እስካሁን ድረስ እያካፈሉን ስላለው ሰፊ የሆነ እውቀትዎ ከምስጋና ጋር ዝቅ ብዬ እጅ እነሳለሁ፡፡ ከገለታዬ አስከትዬ ግን በተለያዩ ድረ ገጾች ከሰሞኑን ባስነበቡን ጽሑፍዎ ማዘኔን ልገልጽልዎ እወዳለሁ፡፡

ይህ ጽሑፍዎ ከዕርቅና ሰላም ይልቅ ጠብንና ኹከትን፣ ከፍቅርና አንድነት ይልቅ መለያየትን የሚዘራ መስሎ ነው የታየኝ፡፡ መቼም ለእንደ እርስዎ ዓይነት ዘመኑን ሙሉ የኢትዮጵያን ጥንታዊ የሆኑ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች ሲመረምር ለነበረ ሊቅ/ምሁር ስለ ኢትዮጵያም ሆነ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን  ታሪከ ማስረዳት ‹‹ለቀባሪው አረዱት›› አሊያም ደግሞ ‹‹ልጅ ለአናቷ ምጥ አስተማረች›› እንዳይሆንብኝ እሠጋለሁ፡፡ ቢሆንም ግን ፕሮፌሰር በዚህ ጽሑፍዎ ለዕርቅና ሰላም ይሆናል ብለው ባቀረቧቸው መፍትሔዎች ዙሪያ ጥቂት ሙግቶችን እንዳቀርብልዎ አስገድዶኛል፡
በሙያዬ የታሪክ ተመራማሪ፣ የአርኮዮሊጂና የቅርስ ባለሙያ ነኝ፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወት ረገድም ጥንታዊትና ሐዋርያዊት በምትሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ካሉ ሊቃውንት አባቶቼ እግር ስር ከማያልቀው ዕውቀት ምንጫቸው እጅግ በጥቂቱ ለመጥለቅ ሞክሬያለኹ፤ እስከ ሕይወት ፍጻሜዬም ከእነዚህ አባቶቼ የማያልቀውን ሰማያዊ ዕውቀታቸውንና ጥበባቸውን መጥለቄን እቀጥላለኹ ብዬ አስባለኹ፡፡ እናም ክቡር ፕሮፌሰር በአንዲት ቤ/ን ጥላ ስር መገኘታችንና ሁለታችንም የኢትዮጵያን ረጅም ዘመናት ታሪክ፣ የሕዝቦቿን ገናና ሥልጣኔ፣ መንፈሳዊና ቁሳዊ ቅርሶቿን ለመመርመር ምንተጋ ከመሆናችን የተነሣ በዚህ ጦማሬ ቋንቋ ለቋንቋ፣ አሳብ ለአሳብ እንግባባለን ብዬ እገምታለኹ፡፡
ፕሮፌሰር ‹‹ዕርቅና ሰላም ለሕይወት ቅመም›› ብለው የጻፉት ጽሑፍዎ እንደሚመስለኝ መነሻ ያደረገው ባለፈው ሰሞን በአሜሪካ ሚቺጋን ስቴት የሚኖረው ወጣቱ የፖለቲካ ተንታኝ ጀዋር መሐመድ፣ አንዳንድ በውጭ አገርና በኢትዮጵያ ያሉ የኦሮሞ ልሂቃንና የብሔረሰቡ ተወላጆች ዘንድ ዳግመኛ እንደ አዲስ በሰፊው መከራከሪያ ሆኖ በዘለቀው የኦሮሞ ታሪክ ትንታኔ፣ የሕዝቡ የነጻነት ጥያቄ፣ የኢትዮጵያ ቤ/ን ለአቢሲኒያ/ለነፍጠኛ ገዢዎች ቅኝ ግዛት ዘመቻ ዋንኛዋ አጋር ነበረች በሚሉትና በመሳሰሉት ታሪካዊና ፖለቲካዊ ትኩሳቶች ዙሪያ ሲንሸራሸሩ የነበሩና አሁንም ያሉ አሳቦች ይመስሉኛል፡፡
እርስዎም በዚህ ክርክር መነሻነት ተስበው ይመስለኛል ለዕርቅና ለሰላም መፍትሔ ይሆናል ባሉት ጽሑፍዎ የኦሮሞ ሕዝብ አውዳሚ፣ አረመኔና ጨካኝ እንደሆነ የነገሩን፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን የኦሮሞ ሕዝብ ‹‹ጋዳ›› የሚለው ሥርዓት አንዳንዶች እንደሚሉት አፍሪካ በቀል የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ሣይሆን ሕግ አልባ፣ በጭፍን የሚጓዝ የማፊያዎች ጥርቅም እንደሆነም አስረግጠው ነገሩን፡፡ እነ ጃዋርና ተከታዮቻቸውም በሸሪያ ሕግ ሊገዙንና ሊዳኙን እያቆበቆቡ ያሉ ጠባብ ብሔርተኞች፣ የኢትዮጵዊነት/የአንድነት መንፈስ ነቀርሳና የሰይጣን መልእክተኛ ናቸው ሲሉም ፈረጇቸው፡፡
አስከትለውም የኦሮሞ ሕዝብና ኢትዮጵውያን ሙስሊሞችም አባቶቻቸው በኢትዮጵያ ታሪክ፣ ቅርስና ሥልጣኔ ላይ ላደረሱት ውድመትና ጥፋት ይቅርታ መጠየቅ እንደሚገባቸው ለማሳሰብ ሞከሩ፡፡
ስለ ኦሮሞ ሕዝብ ጭካኔና አረመኔነትም ከአገር ውስጥ ካሉ ጸሐፊዎች እስከ ውጭ አገር የታሪክ ጸሐፊዎችና ተመራማሪዎች ድረስ የመሰከሩት ስለሆነ፣ ‹‹ጩኸቴን ቀሙኝ›› አሊያም ‹‹ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮኻል›› እንዲሉ ካልሆነ በስተቀር ኦሮሞዎች በኢትዮጵያና በክርስቲያኑ ሕዝብ ላይ ላደረሱት አሰቃቂ ግፍና በደል፣ እንዲሁም ወደ አንድነትና ኅብረት እንዲመጡ ላደረጓቸው ንጉሥ ምኒልክ በሀውልታቸው ስር የይቅርታ ጉንጉን አበባ በማኖር ዕርቀ ሰላም እንዲያወርዱና ለባለውለታቸው ለምድራቸው/ለአፈራቸው ልጅ ለጎበና ዳጬም ሀውልት እንዲያቆሙላቸው ምክርዎን ለግሰዋል፡፡
 ፕሮፌሰር ጌታቸውን ያህል ታላቅ ምሁርና ላለፉት በርካታ ዓመታት የኢትዮጵያን ታሪክ የመረመሩ ሰው እንዴት የኦሮሞ ሕዝብንና ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን ብቻ ነጥለው በአገሪቱ ላይ ለደረሰው ውድመትና ጥፋት ተወቃሽና ይቅርታ ጠያቂዎች እንዳደረጓቸው ሊገባኝ አልቻለም፡፡ መቼም ፕሮፌሰር ኢትዮጵያ በምትባል ግዛት ይኖሩ የነበሩ የተለያዩ ሕዝቦች በተለያዩ ዘመናት ባደረጉት ጦርነትና የግዛት ማስፋፋት ወረራ የየበኩላቸውን ጥፋትና ውድመት እንዳደረሱ ይስቱታል ብዬ አልገምትም፡፡
ሌላው ቀርቶ በቅርቡ ታሪካችን ዘመን፣ በታሪክ ምሁራን ዘንድ ‹‹ዘመነ መሳፍንት›› ተብሎ በሚጠራው ዘመን በአማራነት ስም የሚጠሩ ገዢዎች፣ መሳፍንትና መኳንንት፣ የጎንደሩ በወሎ፣ የጎጃሙ በሸዋ፣ በትግራይ የእንደርታው፣ በአጋሜ፣ የአድዋው በአክሱም፣ በኦሮሞው ግዛትም የአርሲ፣ የባሌ፣ የሸዋና ወለጋ እያለ እርስ በርሱ እንዳልተላለቀና የአገሪቱን ለከፋ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ቀውሶች እንዳልዳረጉ ለምን የኦሮሞን ሕዝብ ብቻ ነጥለው ወራሪ፣ አውዳሚና ብቻ አድርገው እንደሳሉት በእጅጉ ግራ የሚያጋባ ብቻ ሳይሆን የሚያስተዛዝብም ጭምር ነው፡፡
ፕሮፌሰር በእንዲህ ዓይነት የአንድ ወገን ብቻ የታሪክ አተያይና ትንታኔና እንዲሁም ፍረጃ ዕርቅንና ሰላምን ማውረድ ይቻላል ብለው አስበው ከሆነ ይህንን ጽሑፍ እንካችሁ ያሉት ትክክል አይመስለኝም፡፡ በእኔ እሳቤ በአብዛኛው በአገራችን ታሪክ አንድን ብሔር ወይም ሕዝብ ሆን ብሎ ለማጥፋት ወይም ለመፍጀት የተደረጉ ዘመቻዎች ነበሩ ብዬ ለመውሰድ እቸገራለኹ፡፡ አብዛኛው የታሪካችን ገጽ የሚሳየን ገዢዎች ለሥልጣን፣ በገብርልኝ አልገብርህም ሰበብ የኢኮኖሚ ጥቅምንና የፖለቲካ የበላይነትን ለመውሰድ በነበረ ውድድርና ፍጥጫ በተደረጉ ጦርነቶችና ወረራዎች ብዙዎች ምስኪኖች አምነውበትም ሆነ ሳያምኑበት ጭዳ እንደሆኑ ነው የማስበው፡፡
በተመሳሳይም በአገራችን በአብዛኛው በሙስሊሙና በክርስቲያኑ መካከል ተደረጉ ጦርነቶች ውስጥም ቢሆን ሃይማኖት መሳሪያ ወይም ሽፋን እንጂ ሃይማኖትን ሰበብ አድርገው በተነሱ ተፋላሚዎች የተደረጉት ጦርነቶች ዋና ምክንያት አልነበረም፡፡ ሃይማኖት ሽፋን ነው፡፡ ጠቡና መሠረታዊው ቅራኔ የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑትን የኅብረተሰብ ክፍሎች እንመራሃለን ወይም እናስተዳድርሃለን በሚሉት ገዢ መደቦች የሚነሳ የሥልጣንና የኢኮኖሚ ጥቅም ጥያቄ ነበር፣ ነውም፡፡
እናም የአገራችን የፖለቲካ ታሪክ ሂደት ውስጥ የኦሮሞ ሕዝብ እንደማንኛውም የኢትዮጵያም ሆነ የዓለም ሕዝብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በበጎም ሆነ በክፉ ጎኑ የሚነሳበት ታሪክ ያለው ሕዝብ እንደሆነ ነው የማምነው፡፡ ፕሮፌሰር የኦሮሞ ሕዝብን ብቻ ነጥለው አውዳሚና የጥፋት ልጅ እንደሆነ በጻፉበት ብዕራቸውና ለዚህም መከራከሪያቸው ከጠቀሷቸው የአገር ውስጥና የውጭ አገር ጸሐፍት መካከል ለምን እነዚሁ ጸሐፊዎች በአንጻሩ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የደረሰውን በደልና ግፍ በተመለከተ የተዉትን ምስክርነታቸውን ለመጥቀስ/ለመጻፍ እንዳልደፈሩ ግን ግልጽ አይደለም፡፡
እስቲ ለአብነት ያህል አፅሜ ጊዮርጊስ የተባሉ ጸሐፊ ‹‹የኦሮሞ ታሪክ›› በሚል በተዉልን የታሪክ ማስታወሻቸው ዐፄ ምኒልክና ሠራዊታቸው በኦሮሚያና በደቡብ የአገራችን ክፍሎች ባደረጉት የማቅናት ዘመቻ ወቅት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ስለደረሰው በደልና ግፍ የከተቡትን በጥቂቱ እንመልከት፡፡
በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን ኦሮሞ ሁሉ ተገዛ፣ በአማራ ሕግና ሥርዓት ሔደ፣ ካህናቱ አንድ ኦሮሞ አስተምረው አላጠመቁም፡፡ ይልቅስ ተፊተኛው ቂም የበለጠ ቂም በልቡ አኑረውበት መሬቱን በቀላድ ወሰዱበት፡፡ አንድ ቀላድ የቅስና አንድ ቀላድ የአወዳሽ እያሉ በዚሁ ስብከት ንጉሡን አሳመኑ፡፡ ስለ መንግሥት ያሰቡ መስለው ለንጉሡም አንድ ቀላድ፣ ለወታደር አንድ ቀላድ … መሬቱን ተካፍለው ኦሮሞን እንደ ባሪያ አድርገው ይገዙታል እንጂ የክርስቶስን መንገድ አላሳዩትም፡፡ እነርሱም የእግዝሔርን መንገድ በሚገባ አልተማሩም፣ አስተማሪም ቢመጣም ይከለክላሉ …፡፡
ፕሮፌሰር ጌታቸው የኦሮሞ ወራሪ ኃይል በአማራውና በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ላይ ያደረሰውን ግፍና በደል ዘርዝረው የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባዋል ባሉበት ብዕራቸው ለምን ይህንም የኦሮሞ ሕዝብን በደል ወይም የታሪካችንን ሌላውን ገጽ ቦታ አንዳልሰጡት፣ ሊያነሡት ወይም ሊነግሩን እንዳልደፈሩ ግልጽ አይደለም፡፡ ፕሮፌሰሩ መልእክቴ በኢትዮጵያ ምድር ዕርቅና ሰላም ለማውረድ ነው ካሉን ዘንድ ሚዛናዊ በመሆን አንዱን ብቻ ሳይሆን ሌላውንም የታሪካችንን ገጽ ሊያሳዩን በተገባቸው ነበር፡፡ እንዲህ ዓይነቱ የአንድ ወገን ብቻ የሆነ የታሪክ ትንታኔና ዕይታ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ወዴየትኛው የጥፋት መንገድ ይዞን እንደነጎደ በተግባርም ጭምር ዐይተነዋል፡፡
በሌላም በኩል እስቲ እስካሁንም ድረስ ሳስበው ግርም የሚለኝን ከዚሁ ካነሳሁት ርእሰ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ አንድ ገጠመኜን እዚህ ላይ ጨምሬ ለማንሳት እወዳለኹ፡፡ ታሪኩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበርንበት ሰዓት የኾነ ነው፡፡ በዩኒቨርስቲው ካሉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ዘንድ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ጥላ ስር አብረን ያለን ጓደኛዬ በአንድ ወቅት ‹‹ራእይ ማርያም›› ከሚል የጸሎት መጽሐፍ ኮፒ የተደረገ ጽሑፍ ከአንድ ከሌላ ኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ጓደኛው ጋር ይዞ በመምጣት እንዲህ አለኝ፡፡
‹‹ይቅርታ፣ ከልቤ አዝናለሁ … በክርስቶስ ኢየሱስ፣ በጌታችንና በመድኃኒታችን ክቡር ደም ፈሳሽነት/ቤዛነት ሁላችንም በአንድ መንፈስ፣ ሰማያዊ ዜጋ ሆነን የእግዚአብሔርን መንግሥት እንወርሳለን ብላ በምታስተምር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሕዝቦችን የሚለያይና የሚከፋፍል መጽሐፍ መኖሩን እስከዛሬ አላውቅም ነበር፡፡›› በጓደኛዬ ንግግር ውስጥ እልክና ብርቱ የሆነ አንዳንች የቁጭት መንፈስ ነበር የሚነበብበት፡፡ ‹‹… ለመሆኑ ይህን መጽሐፍ አይተኸው ወይም አንብበኸው ታውቃለህ በማለት ‹‹የራእይ ማርያም›› መጽሐፍን አንድ ገጽ ኮፒ እንዳነበው በእጄ ሰጠኝ፡፡ እንዲህ ይላል፡-
… ከስር እስከ ጫፍ፣ ከጫፍ እስከ ስር ድረስ በአምስት ሺሕ ዓመት የማይደረስበት ትልቅ ገደል አሳየኝ፡፡ ያንዱ ነፍስ በአንዱ ላይ ሲወድቅ ዐየኹ፡፡ እኔም ምንድናቸው ብዬ ልጄን (ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ኢየሱስን መኾኑን ልብ ይሏል) ጠየቅኹት፡፡ እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላት፡- … አራስ፣ መርገም፣ ደንቆሮ፣ ‹‹እስላም››፣ ‹‹ጋላ››፣ ‹‹ሻንቅላ››፣ ‹‹ፈላሻ›› ጋር የተኙ፣ ፈረስ፣ አህያ፣ ግመል በግብረ ስጋ የሚገናኙ፣ ወንዱም ግብረ ሰዶም ወገሞራ የሚዳረጉ… እነዚህ ሁሉ ኩነኔያቸው ይህ ነው አለኝ …፡፡
በጊዜው ይህን ጉድ ካነበብኩ በኋላ እንዲህ ዓይነቱን ክፋትና እርግማን የሞላበት መጽሐፍ ቤተ ክርስቲያኒቱንና እውነተኞቹን የወንጌል መምህራን የሆኑትን አባቶቻችንን እንደማይወክል ባውቅም ይህ የጸሎት መጽሐፍ ተብዬ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ታትሟልና በጊዜው የመከራከሪያ አሳብም ሆነ የምሰጠው ምላሽ አልነበረኝም፡፡ ግና ስለ ስለዚሁ የጸሎት መጽሐፍ የኩነኔ ፍርድ ጥቂት ነገሮችን ለማለት ያህል፤ መቼም ሌላ ስምና መልክ እስካልተሰጠው ድረስ በመንፈሳዊው ዓለም አስተምህሮ/ሕግ ካልተፈቀደልንና የእኛ ከሆነችው ሴትም ኾነ ወንድ ውጭ መሔድ ዝሙት ነው፡፡
‹‹ከጋላ›› ወይም ‹‹ከሻንቅላ›› ‹‹ከእስላም›› ወይም ‹‹ከፈላሻ›› ጋር ስለተኛን ወይም ስለዘሞትን የተለየ ነገር ሊሆንም ሊደርስም አይችልም፣ በአምስት ሺሕ ዘመንን በሚያስኬድ ገደል ውስጥም ልንጣልም አንችልም፡፡ ደግሞስ ምን ዓይነት ሕሊና ያለው ሰው ነው ሰውንና እንሰሳን በእኩል ሚዛን አስቀምጦ ፈረስም ተገናኘህ ‹‹ሻንቅላ›› ወይም ‹‹ፈላሻ›› ምንም ልዩነት የለውም ያው ነው በሚል የሚጽፍ፡፡
አንድን ጎሳና ብሔር ለይቶ ከእነርሱ ጋር ከተኛህ እንዲህ ዓይነት ቅጣት ይደርስብሃል/ያገኝሃል ብሎ እንዲህ ዓይነቱን መርገምን፣ ጥላቻንና ክፋትን የተሸከመ ድርሳን ቅድስት፣ ንፅሕትና ርትዕት በኾነች በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም አሳትሞ በማቅረብ፣ ‹‹ፈላሻነቱንም›› ኾነ ‹‹ሻንቅላነቱን›› ወዶና ፈቅዶ ባላመጣው ሰው ሕሊና ውስጥ የጥላቻ መርዝ እንዲረጭና ልቦናው ክፉኛ እንዲቆስል ምክንያት ኾኗል፡፡
ይህ ትናንትና እንደ ዘበትና ቀልድ ያየነውና በጊዜው በይቅርታ መፍትሔ ያላበጀንለት ነገር ይኸው ዛሬ ከታሪካችን ማኅደር እየተመዠረጠ የብዙዎችን ቁስል እያመረቀዘ ቤተ ክርስቲያኒቱንም ኾነ ተከታዮቿን በጥላቻ ዓይን እንዲታዩ ምክንያት ከኾነ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ እነዚህና ሌሎች መሰል ታሪኮችን ዕድሉ ያጋጠመን ሁሉ ደጋግመን ሰምተናቸዋል፡፡ መፍትሔው ምን ይሁን፣ ምን መላ እንፍጠር ከማለት ይልቅ ያለፈ ታሪክን ማንሳት ምን ይጠቅማል በሚል በማድበስበስ የተውናቸው ክስተቶች እያመረቀዙ በመካከላችን መፈራራትንና ጥላቻን አነገሡብን/አባባሱብን እንጂ መፍትሔ አልሆኑንም፡፡
ብዙዎቻችንን እያከራከረን ስላለው የትናንትና ታሪካችን ርእሰ ጉዳይ ስንመለስም አንድ ማስተዋል ያለብን ነገር ያለ ይመስለኛል፤ ይኸውም አብዛኛው የአገራችን የፖለቲካ ታሪክ በጦርነትና በወረራ፣ በገብር አልገብርም፣ በልግዛህ አልገዛም በተደረገ ግብግብና ጭፍጨፋ በደም የቀላ ታሪክ ነው ያለን መሆኑን፡፡
አንዱ የገዢ መደብ ሌላውን፣ ክርስቲያኑ ሙስሊሙን፣ ሙስሊሙ ክርስቲያኑን ያጠቃበት የጨፈጨፈበት በርካታ ዘመናቶች የታሪካችን አካል ኾነው አብረውን አሉ፡፡ አንዱ አገር የሌላውን አገር በጦርነት በመግጠም ሀብት ንብረቱን በመዝረፍ፣ መሬቱን በመቀማት፣ በምርኮና በባርነት በማጋዝ ያሳለፍናቸው የታሪካችን ቁስሎች በፍቅር ዘይት ለስልሰውና በዕርቀ ሰላም ፈውስ አግኝተው መፍትሔ ካላገኘን አንድ ብሔርን/ሕዝብን ወይም ሃይማኖትን ብቻ ነጥሎ እንደ ጥፋተኛና አውዳሚ አድርጎ ማቅረብ ወደምንናፍቀው የዕርቅና የሰላም ምንገድ ያመጣናል ብዬ አላስብም፡፡
ደግሞስ አማራው ከኦሮሞው፣ ኦሮሞው ከትግሬ፣ ወላይታው፣ ከጉራጌው፣ ሐረሪው፣ ከአፋር በደም፣ በአጥንት በተዛመደ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በጋራ ታሪክ  በተሳሰረ ሕዝብ መካከል ብሔርና ጎሳ ለይይቶ መወቃቀሱ ጥቅሙ ምንድን ነው፡፡ ትርፉስ ለማን ነው?! በእርግጥም ለእውነተኛው ዕርቀ ሰላም ቀናውን መንገድ ካላመቻቸን ላለፉት ሃያ ዓመታት ታሪክንና ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው እየተካሔዱ ያሉ የቂም በቀል ዘመቻዎች ፍፃሜያቸው እጅግ አስፈሪና አሳፋሪ እንደኾኑ ነው የታዘብነው፡፡
በሃይማኖትና በብሔርተኝነት ስም በአዲስ አበባና በሌሎች ክልል ከተሞች ቦግ እልም እያለ ያለውና ተዳፈኖ ያለው የረመጥ እሳት ሊያስከትለው የሚችለውን አደጋ ከወዲሁ መፍትሔ ካላበጀንለት (ያው እስከ ዛሬ ድረስ በአርባ ጉጉ፣ በበደኖ፣ በአርሲ ነገሌ፣ በወተር፣ በቤሻንጉል ጉሙዝ፣ በጅማ … የደረሰው አሰቃቂ እልቂት፣ ጥፋትና ውድመት ሳይዘነጋ) ይህ ዓለም ሁሉ የሚያደንቀውና የምንኮራበት፣ በቋፍ ያለው ለዘመናት አብረን በፍቅርና በወዳጅነት የቆየንበት አኩሪ ታሪካችን በነበር ልናወሳ የምንገደድባቸው ጊዜያቶች ሩቅ ሊኾኑ እንደማይችሉ በርካታ ማሳያዎችን መጥቀስ የሚቻል ይመስለኛል፡፡
ያለፈው ሰሞን የእነ ጃዋር መሐመድና የኦሮሞ ወንድሞቻችን ኦሮሞነትን ከኢትዮጵያዊነት ነጥለው ያቀረቡበት ትርክትና የትናንትና ክፉ የታሪክ ጠባሳችን፣ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸውና እያንጸባረቁት ያለው ቁጣ፣ ቅያሜና ዛቻ የነገይቱ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ፣ የቤተ ክርስቲያኒቱስ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል ብለን እንድንጠይቅ፣ እንድንሰጋ ያስገድደናል ብዬ ለማለት እደፍራለኹ፡፡
አገሪቱን እያሥተዳደረ ያለው መንግሥትም ለጉዳዩ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ያለ ቅጥ ያራገበው የብሔር ፖለቲካ ወላፈኑ እራሱንም ጭምር እየለበለበው እንደሆነ እያየን ነው፡፡ ‹‹ካፈርኩ አይመልሰኝ›› በሚል ግትርነትና ዕድሜዬን ያራዝምልኛል በሚል እንዲሁ በአገም ጠቀም የተወው የጎሰኝነት/የዘረኝነት ጉዳይ ነገ መዘዙ ከየት እስከ የት ሊመዘዝ እንደሚችል መገመት የሚያዳግት አይመስለኝም፡፡ ትናንትና በሆነው በሚያኮራው ታሪካችን ተከባብረንና ተዋደን፣ አሳፋሪና ክፉ ጠባሳ የተዉብንን የታሪካችንን ምዕራፍ ደግሞ በይቅርታ ዘግተን በፍቅርና በመቀባበል መኖር ካልተቻለን የሚጠብቀን ዕድል ጥላቻ፣ መከፋፋት፣ ጠላትነት፣ መለያየት … ብቻ ነው ሚሆነው፡፡
ይህ እንዳይሆንብን፣ ይህ ክፉ ነገር እንዳይደርስብን ቆም ብለን ማሰብ ያለብን ጊዜ ላይ ያለን ይመስለኛል፡፡ እንደ ፕሮፌሰር ጌታቸው ያሉ የዕድሜ ባለፀጋዎችና ምሁራን፣ የታሪክ ተመራማሪ ምሁራኖቻችንና የፖለቲካ መሪዎችም ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ወደ ፍቅር፣ ሰላምና አንድነት የሚመጡበትን ቀና የሆነ መንገድ በማመቻቸት አገሪቷን ከተደቀነባትና ካዣንበባት ጥፋት ሊታደጓት የትውልዱንም ልብ በፍቅር ዘይት አልስልሰው ለይቅርታ/ለዕርቀ ሰላም ሊያዘጋጁት ጊዜው አሁን ይመስለኛል፡፡
ከሁሉም በላይ ደግሞ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች ከእኔ ይበልጥ ከእኔ ይበልጥ የፉክክር መንፈስ ወጥተው ለአገርና ለሕዝብ የሚሆን የዕርቀ ሰላም መልእክት ይዘውልን ሊመጡ ይገባቸዋል፡፡
ነገሥታትን/መንግሥታትንና ክፉ መሪዎችን በመገሠጽ፣ በሕዝቦች መካከል ፍቅርንና ሰላምን፣ በአገራችንም ብሔራዊ ዕርቅን በማስፈን ሐዋርያዊ ተልዕኮአቸውንና መንፈሳዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ጊዜው አሁን ነው፡፡ አሊያ ግን ዕርቅንና ሰላምን ያወርዳሉ ያልናቸው አባቶቻችንም እርስ በርሳቸው ተለያይተውና ተወጋግዘው፣ ለነገ ህልውናችን በሚል ሰበብ የፖለቲከኞችን ጉያ የሚመርጡ ከሆኑ፣ ከእውነትና ከፍትሕ ጎን ለመቆም መንፈሳዊ ድፍረትና ወኔ ከተለያቸው እንዴት ባለ መንገድ ነው ፍቅርንና ዕርቅን ሰብከው አገሪቱንም ሆነ ትውልዱን ከጥፋትና ከሞት መንገድ ሊታደጉት የሚችሉት?!
በታሪካችን ለኾኑት ስህተቶች በግልፅ ይቅርታ ተጠያይቀን ዕርቅ ማውድ ካልቻልን አስቸጋሪ ነው፡፡ የሚሻለው መነጋገርና መግባባት ነው፡፡ እንደ እውነቱም ከኾነ ትናንትና ለኾነው በደል እውቅና መስጠት ሳይቻል ዕርቅ ዕርቅ የሚለው ነገር ከጉንጭ አልፋ ወሬነት የሚያልፍ ፋይዳ ይኖረዋል ብዬ አላስብም፡፡ ዛሬ እንደገና ከበርካታ ዓመታትም በኋላ ተመልሶ እነ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ እነ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ የምኒልክ ጦር በአያቶቻችን ላይ ያደረሰውን በደል አንረሳውም ወደሚል አዙሪት መልሶ እየከተታቸው ያለው ይኸው በይቅርታ ያልተወራረደው ታሪካችን ጥሎብን የሔደው ክፉ አበሳና ጠባሳ ይመስለኛል፡፡
እናም እንደ ፕ/ር ጌታቸው ያሉ ምሁራንና የዕድሜ ባለጠጋዎች የአንድ ወገን ታሪክን ብቻ በማጉላት ሳይሆን ሚዛናዊነት ባለው መልኩ ታሪካችንን በማቅረብ የሁላችንም የጋራ ቤታችን በሆነች ኢትዮጵያችን ተስማምተን፣ ተዋደን፣ ተፋቀርንና ተከባብረን የምንኖርባት አገር እንድትኖረን የታላቁን የሰላምና የይቅርታ አባት የኔልሰን ማንዴላን ዓይነት ሚና በመጫወት የትውልድ ባለውለታ ይሆኑ ዘንድ በእኔና በትውልዴ ስም አደራ እላለሁ፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!! 


64 comments:

 1. A very good and interesting points

  ReplyDelete
 2. Abet abselam des alchihu adel, ke Andu website zerfachihut. Ye nikodoms hasb lanate yemihon adelm

  ReplyDelete
  Replies
  1. የምትናገረው ከሌለህ ምነው ዝም ብትል?

   Delete
 3. thank you brother, it is really Astonishing.

  ReplyDelete
 4. girum sehuf new. sehafiw betam temesegenalehe. endihe yale chewana besal hasab makerebehe dinkhe new. tebareke

  ReplyDelete
 5. I am half Oromo, I didn't know about this tert tert book ‹‹የራእይ ማርያም›› written by Debetera? the writer wasn't a believer (not by Jesus) so I am not mad.

  ReplyDelete
 6. ፕሮፌሰር ተብዬዉ ጭንቀት ነው ወይስ ጭንቅላቶ ነቅዘ?
  Are you real Professor? OR...????????????????????????????????????????????????????

  ReplyDelete
 7. ወንድሜ ኒቆዲሞስ ያነሳሀው ሀሳብ ሸጋ ነው!!ፍሰት አለው!!ከሁለቱ ሊቃውንት ጫፍ የወጣ አስተሳሰብ ያንተ ተሸሎኛል!!የጃዋር እና የፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ጽንፍ እና ጽንፍ የቆሙ ሀሳቦች የልሂቃኑን እውቀትን የጥላቻ ባሪያ አድርጎ ከመራመድ የሚመነጭ ይመስለኛል!!ስለዚህ ሁለቱም ሀሳቦች የየራሳቸው ጠርዘኛ ተከታይ ከመፍጠር በቀር ሁለቱም እንድትኖር ለሚፈልጉዋት ኢትዮጵያ ጠቃሚ ሆኖ አይታየኝም!!
  እውነቱ ያለው በመሀል ነው!!የሀገሪቱ አንድነትም ሆነ የህዝቡ በየግዛቱ መስፋፋት በሪፈረንደምና በመሬት ምሪት አልተካሄደም!!በብዙ መስዋእትነት እንጅ!!በሂደቱ ሁሉም ወገን ገድሉዋል!!አንዱ አንዱን እየገደለ መሬት በየተራ ይዙዋል!!!!ወደሁዋላ ብዙ ሀይል ኖሮት ብዙ የገደለው በየጊዜው ስልጣኑን ያዘ !!እናስተውል!!የሙዋችም አላማ ቀድሞ ባይገደል ኖሮ በመግደል አሸንፎ መግዛትና ግዛት ማስፋፋት ነው!!ስለሆነም በስኬት ካልሆነ በቀር ሙዋችና ገዳይ በዓላማ አንድ ናቸው!!ክፉ ስለሆኑ አይደለም!!በቃ የጊዜው የኑሮ ዘይቤ የሚፈቅደው ይሄን ነበር!!ስለዚህ የሚዳኙት በነቡበት ጊዜ በነበረው ህግ እንጅ በ1996ቱ የኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አይደለም!!
  አሁንም መፍትሄው በታሪክ ሂደት ለተፈጠረው ሁሉ እውቅና መስጠት እንጅ በይቅርታ ስም ከ15ኛው መቶ ክ/ዘመን ጀምሮ በሃይማኖትና በመስፋፋት ስም በ2ቱም ወገኖች ለተፈጸሙት በደሎች በይቅርታ ስም ሂሳብ የማወራረድ ተልእኮ ያላቸውን በአዋቂነት ስም የተጀቦኑ ጥላቻዎች በቀለም እየኩዋሉ በመዝራት አይደለም!!በተለይ ከፍረጃ መውጣት አለብን!!
  ወንድሜ!!በቤተክርስቲያን ስም ታተሙ ብለህ የጠቀስካቸው ጽሁፎች ላይ ጥንቃቄ አድርግ!!በግእዝ የተጻፈ ሁሉ የቤተክርስቲያን ነው ማለት አይደለም!!የቤተክርስቲያን ነው ለማለት ጽሁፉ በሊቃውንት ጉባኤ ተመርምሮ የታተመ መሆን አለበት፣ወይም በእለት ከእለትም ሆነ በአመታዊ የቤ/ክ መንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ገብቶ ግልጋሎት መስጠት አለበት፣ያለበለዚያም በጠቅላይ ቤተክህነት ወይም ስልጣን ባለው የቤ/ክ አካል ፈቃድ በትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት መታተም አለበት!!ከዚህ ውጭ ያሉ መጻህፍት ላይ የየራሳችንን ጥንቃቄ አድርጎ ማንበብ የእኛ የአንባብያኑም ድርሻ ስለሆነ የቤ/ክ ስም ባጉል ቦታ ላለማንሳት ጥንቃቄ ማድረጉ አይከፋም!!


  ReplyDelete
  Replies
  1. አቶ/ዲያቆን ህሩይ፤ እርስዎ ስለቤተክርስቲያን ብዙ እንደሚያዉቁ ከሚጽፉት መልሶች ተረድቻለሁ። ስለዚህም ይህችን ራዕየ ማርያም አላነበቡም ብዬ ማሰብ አልፈልግም። አላወቁትም ብንል ደግሞ የቤተክርስተያኒቷን ገጽታ የሚያጎድፍ በመሆኑ እርስዎ አድበስብሰዉ ለምን አለፉት። አንድም ዉሸት ነዉ፤ እንዲዚህ ዓይነት መፅሐፍ የለም ማለት፤ አለዚያ ደግሞ ይህንን ከባድ ጥፋት ከሌሎቹ ጋር ማዉገዝ አለብዎት እንጂ አሁን የያዙት አቋም የሚያዋጣ አይደለም። ክርስቲያንነትም አይደለም። በዚህ የአብይ ፆም እንደዚህ ዓይነት የተረት ትምህርትና እመቤታችንን ተራ ኃጢአተኛ ከሚያደርግ የመሰሪዎች ሥራ እንዲሰዉረን መፀለይ አለብን።

   Delete
 8. Man you are good, you have a better idea and a reconciliation concept than most of Ethiopian intellectual and politicians. this is what we want for this country.
  be blessed

  ReplyDelete
 9. tadiya ende raeye mariyam yalu kotetocin yezo kerestina ale ende? yihen mesehaf betekerestian beawage awgeza metal alebat.

  ReplyDelete
 10. አሁን ታድያ እንደ ራዕየ ማርያም ያለ መጽሐፍ ያለባት ቤተክርሲቲያን ተሃድሶ አያስፈልጋትም? ወይ ታደሱ ወይ ደግሞ የክርስቲያንነትን ትርጉም ቀይሩ።

  ReplyDelete
 11. ራዕየ ማርያምን የያዝሽ ቤተክርስቲያን ሆ!!!!!!!!
  ወይ በይፋ እነዚህን መጽሐፍት አውግዘሽ ታደሺ አሊያም ደግሞ ፍረሺ

  ReplyDelete
 12. ‹‹የራእይ ማርያም›› መጽሐፍን አንድ ገጽ ኮፒ እንዳነበው በእጄ ሰጠኝ፡፡ እንዲህ ይላል፡-
  … ከስር እስከ ጫፍ፣ ከጫፍ እስከ ስር ድረስ በአምስት ሺሕ ዓመት የማይደረስበት ትልቅ ገደል አሳየኝ፡፡ ያንዱ ነፍስ በአንዱ ላይ ሲወድቅ ዐየኹ፡፡ እኔም ምንድናቸው ብዬ ልጄን (ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ኢየሱስን መኾኑን ልብ ይሏል) ጠየቅኹት፡፡ እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላት፡- … አራስ፣ መርገም፣ ደንቆሮ፣ ‹‹እስላም››፣ ‹‹ጋላ››፣ ‹‹ሻንቅላ››፣ ‹‹ፈላሻ›› ጋር የተኙ፣ ፈረስ፣ አህያ፣ ግመል በግብረ ስጋ የሚገናኙ፣ ወንዱም ግብረ ሰዶም ወገሞራ የሚዳረጉ… እነዚህ ሁሉ ኩነኔያቸው ይህ ነው አለኝ …፡፡
  ይሔ ነው ኦርቶዶክሳዊነት ማለት ነው? እንዴት እንደጠላሁት ኦርቶዶክሳዊነቴን። እንዲህ ያለውን ከንቱ መጽሀፍ ይዘን ነው። ክርስቲያኖች ነን የምንለው? እንዴት ያሳፍራል። ይቺ ቤተክርስቲያን የእውነት መጽሐፎችዋን መርምራ ለፈጸመችው ስህተት በይፋ ይቅርታ መጠየቅ አለባት።

  ReplyDelete
 13. አቶ/ዲያቆን ህሩይ፤ እርስዎ ስለቤተክርስቲያን ብዙ እንደሚያዉቁ ከሚጽፉት መልሶች ተረድቻለሁ። ስለዚህም ይህችን ራዕየ ማርያም አላነበቡም ብዬ ማሰብ አልፈልግም። አላወቁትም ብንል ደግሞ የቤተክርስተያኒቷን ገጽታ የሚያጎድፍ በመሆኑ እርስዎ አድበስብሰዉ ለምን አለፉት። አንድም ዉሸት ነዉ፤ እንዲዚህ ዓይነት መፅሐፍ የለም ማለት፤ አለዚያ ደግሞ ይህንን ከባድ ጥፋት ከሌሎቹ ጋር ማዉገዝ አለብዎት እንጂ አሁን የያዙት አቋም የሚያዋጣ አይደለም። ክርስቲያንነትም አይደለም። በዚህ የአብይ ፆም እንደዚህ ዓይነት የተረት ትምህርትና እመቤታችንን ተራ ኃጢአተኛ ከሚያደርግ የመሰሪዎች ሥራ እንዲሰዉረን መፀለይ አለብን።

  ReplyDelete
 14. አባ ሰላማዎች በነጋ ጠባ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን›› የተባሉ ከሚል ብሶት፣ አሉባልታ፣ እርግማንና ውርጅብኝ ወጣ ብላችሁ እንዲህ ያለውን ትልቅ ቁም ያነሳ ጽሑፍ ቦታ ሰጥታችሁ ማስተናግዳችሁ ይበል የሚያሰኝ ነው፡፡


  ወንድማችን ዲ/ን ኒቆዲሞስ ዕርቅ ይሁን የፕ/ር ጌታቸው ኃይሌን ጽሑፍ መሠረት አድርጎ ያነሳው አሳብ በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ መሪዎችና አባቶች፣ አገልጋዮችም ሆኑ በልሂቃኑ ዘንድ አይነኬ የሚመስሉና ብዙም ጊዜ አደገኛ ናቸው በሚል ሰብብ የተገፉ የታሪክ እውነታዎች ናቸው፡፡ በፍርሃት፣ በይሉኝታና በግብዝነት ሰበብ በዝምታ ተሸብበው ከእውነትና ከሕሊናቸው ጋር ማዶ ለማዶ የቆሙ እነዚህ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሊቃውንትና ምሁራን ‹‹የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ›› በሚል ሰበብ የተዉት ይህ ሐቅ ጊዜውን ጠብቆ እንደ ተዳፈነ እሳት ቦግ እልም ማለቱን አላቆመም፡፡
  ፕሮፌሰሩም ሆኑ ዲያቆኑ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታሪክና ይህንም ተከትሎ በኦሮሞ ሕዝብ፣ በደቡብ፣ በምዕራብና በደቡብ ምዕራብ ያሉ ሕዝቦች ስለሚያነሷቸው አንዳንድ ብሶቶችና ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲያም ሲል ሃይማኖታዊ ጥያቄዎች ዙሪያ በሰከነ መንፈስ መነጋገሩ ጠቃሚ እንደሆነ አስባለኹ፡፡ እናም እኔም በበኩሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ዙሪያ ከትናንት ታሪካችን በመነሣት በጣም መሠረታዊ ሊባሉ የሚችሉ ጥቂት ነገሮች ላንሳ፡፡
  ከአክሱማውያን አንስቶ በዛጉዌዎች በኩል አቋርጦ ሸዋ ላይ የደረሰው ስርወ-መንግሥት በታሪክ የገጠሙትን ከመጥፋት ጠርዝ አፋፍ መልሶ የተንሰራራባቸውን የተለያዩ የታሪክ ምእራፎች እያለፈ፣ ራሱን በሺህ የሚቆጠሩ የዘመናት ዕድሜ ያለው መንግሥትና ሀገር ቅጥልጥሎሽ አድርጎ ማየት የቻለው የክርስትና እምነት ከሰጠው ያልተቋረጠ ውስጣዊ ጥንካሬ ነው፡፡ ቤተ ክህነቱ ለነገሥታቱና ለገዢዎችም በፈጣሪ መመረጥን ከሌሎች መመዘኛዎች ቅድሚያ በመስጠት የዘርን፣ የጎሳንና የጎጥን ትርጉም በማሳነስ የፈጠረችው ርእዮት ነገሥታቱ የነገሡበትን ጎጥ ብቻ ሳይሆን ምድረ-ክርስቲያኑን በሙሉ እንደ ግዛታቸው እንዲያዩ የሚያስገድድ አመለካከት እንዲኖራቸው አድርጋለች፡፡
  ቤተ ከህነት በክርስትና እምነት አማካይነት የአካባቢውን ሕዝቦች በክርስትና ቤተሰብነት፣ መኖሪያቸውንም በአንድ የክርስቶስ ግዛትነት እንዲታይ በማድረግ ያሠራጨችው፣ የጎሳንና የጎጥን ልዩነት የቀበረ አድማሳዊ ርእዮት ዋነኛ ተሸካሚዎች ደግሞ ነገሥታቱና መሳፍንቱ እንደሚሆኑ ግምት ውስጥ ስናስገባ ደግሞ ይህ ርእዮት ሰፊና ጥልቅ መዘዞችን መሸከሙን እንረዳለን፡፡
  ከእነዚህ መዘዞች ውስጥ ዋንኛው በታሪክ ቅጥልጥሎሽ የእዚህ እምነት ተሸካሚ በሆኑ ነገሥታትና ገዢዎች የተመራው የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ አገርና መንግሥት ግንባታ ጥረት ወለደው አቅጣጫ ነው፡፡ ይህን የታሪክ ሂደት ነው የትናንትናዎቹም ሆኑ የዛሬዎቹ ኦሮሞ፣ የደቡብ፣ የምዕራብና ደቡብ ምዕራብ ሕዝቦች ብሶት፣ ክስና የጭቆና ታሪክ ትርክትም ከዚሁ ታሪካዊ ኩነቶች ጋር የሚያያዙት፡፡
  ይሁን እንጂ በጊዜው ገዢዎቹም ሆኑ ቤተ ክህነት የአገር ግንባታ ሂደቱ በፊት ለፊታቸው የተቀመጠላቸውና ያለውም ብቸኛ አማራጭ ይኸውና ይኸው ብቻ ነበር፡፡ ይህ አቅጣጫም ከክርስትና/ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ጋር በተያያዙ ታሪካዊ ጫናዎች የተነሣ ሀገራዊነትን ወይም የግዛት አንድነትን ከማስቀደም ውጭ ሌላ መሔጂያም ሆነ አማራጭ ያልነበረው መሆኑን ልብ ልንል ይገባል፡፡
  የዐፄ ምኒልክና የቤተ ክህነቱ የተባበረ ኦሮሚያንና ደቡብን የማቅናት ዘመቻም ከላይ የገለጽነውን ታሪካዊ እውነታ ከግምት ባስገባ መልኩ የተካሔደ ነው፡፡ በዚህ ሂደት ብዙ ነገሮች ኾነዋል፡፡ ይህ ደግሞ በዐፄ ምኒልክ ዘመን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በፊት የክርስትናንም ሆነ የእስልምናን ሃይማኖት በሚያራምዱ ገዢዎችና ተስፋፊዎች ዘንድ በተደረጉ ወረራዎች በርካታ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውሶች እንዲከሰቱ መንሥኤ ሆነዋል፡፡ ሕዝቦች በባርነት ተግዘዋል፣ ተጨፍጭፈዋል፣ ታርደዋል፣ አሰቃቂ ለሆነ መከራና ስደትም ተዳርገዋል፡፡
  በእርግጥም ጸሐፊው እንዳሉት የሚጠቅመንና የሚበጀን እውነቱን መነጋገር ነው፡፡ ከታሪካችን ስህተት ተምረን ለይቅርታ፣ ለምሕረት፣ በሰላምና በፍቅር፣ ተዋዶና ተከባብሮ ለመኖር በሚያስችሉን ቁም ነገሮች ላይ ሰከን ብለን ለመነጋገር ብንጀምር መልካም ይመስለኛል፡፡
  አመሰግናለሁ!!

  ReplyDelete

 15. አባ ሰላማዎች ይህን ጽሑፍ እንዳነበው የጋበዘኝ አንድ ጓደኛዬ ነው፣ አባ ሰላማ የሚባል ብሎግ ስለመኖሩም አላውቅም ነበር፡፡ በእናንተ ድረ ገጽ የተስተናገደውን የዲያቆኑን ጽሑፍ ካነበብኩ በኋላ የፕሮፌሰሩን ጽሑፍ ከኢትዮ ሚዲያ ድረ ገጽ ላይ አነበብኩት፡፡ የፕሮፌሰሩ አጻጻፍ በእጅጉ ይሰቀጥጣል፣ ከአንድ ታሪክን ከሚመረምር ምሁርም የሚጠበቅ አይደለም፡፡ አያቶቻችንና አባቶቻችን ያቆዩልንን የገዳ ሥርዓት ‹‹የማፋያዎች ስብስብ ነው፡፡›› ሲሉ አጣጣሉት፡፡
  ኢትዮጵያ በምትባል አገር ውስጥም ለደረሰው ውድመትና ቀውስ የኦሮሞ ሕዝብ ይቅርታ ይጠይቀን አሉን፡፡ ቤተ ክህነትም ያደረግችህላችሁን ውለታ አስቡ፣ ለልጅ ልጆቻችሁም አሳስቡ ሲሉ መከሩን፡፡ እንደው ፕ/ር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እርሳቸው በሚገኙበት የቤተ ክህነት ተቋም በሚገኙ አገልጋዮችና ምእምናን ዘንድ ‹‹ለኦሮሞ ነፍስ የዲያቆን ንስኃ አባት አነሰው እንዴ!›› የሚለውን ንቀትና ጥላቻ የተሞላ ተረት/ስላቅ ትዝ አይልዎትም ማለት ነው፡፡
  እውነት እንነጋር ከተባለ እኮ በዚህች አገር ገና ያልተገለጸ ብዙ ጉድ አለ፡፡ ይህ በይቅርታና በንስኃ ያልተወራረደ በእግዚአብሔር አምሳል በተፈጠሩ ሰዎች ላይ የተደረገው ግፍ፣ በደል፣ ንቀትና ጥላቻ ይኸው እስከዛሬም ለአገሪቱ ዕርግማንና መርገምትን እንዳሸከማት ዘልቋል፡፡ ለአገሪቱ ድህነት፣ ለሕዝባችንም ጉስቁልና መፍትሔው እውነታውን አውጥተን መነጋገርና ዕርቀ ሰላም ማውረድ ነው፡፡
  ለአገራችንም ሆነ ለሕዝባችን የምናስብ ከሆነ፣ ለእኛ ከጌታ ዘንድ የምሕረትና የመጎብኘት ዘመን እንዲመጣልን የምንሻ ከሆነ እውነተኛ የሆነ ብሔራዊ ንስሐና ዕርቅ ያስፈልገናል፡፡
  ዋቅጅራ ነኝ፡፡ ከወለጋ/ነቀምት

  ReplyDelete
 16. Here we go … the Ethiopians and the Ethiopian Orthodox Church Followers here is the bare fact deal with it…!!!

  ReplyDelete
 17. አንጋፋው የወያኔ ታጋይ የሆኑት አቦይ ስብሐት ደጋግመው እንደሚናገሩት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን መሪዎችና ሊቃውንት ነን በሚሉ ሰዎች ልብ ውስጥ ለዘመናት ስር ሰዶ የቆየው ትምክህተኝነት፣ አጎብዳጅነት፣ አድር ባይነት፣ ግትርነት… ወዘተ. በአገሪቱ ፖለቲካ ታሪክ ላይ ይህን ነው የማይባል ከፍተኛ የሆነ ጠባሳ ጥሎ አልፏል፡፡ በ60ዎቹ በአገሪቱ የተቀጣጠለው የለውጥ እንቅስቃሴም ይህን ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፖለቲካው ጋር ያደረገችውን ያለአቻ ጋብቻ ለማፍረስ ጭምር የተካሔድ እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡
  በቀደመው ዘመንም ቤተ ክርስቲያኒቱ ነገሥታትን በማንገሥና በማውረድ ከነበራት ሥልጣን እንዲሁም ደግሞ ከፖለቲካው ጋር ከነበራት የጠበቀ ግንኙነት የተነሣን በጎ ክፉም ሊባሉ የሚችሉ ተጽዕኖዎችን ለመዘርዘር አዳጋች ቢሆንም፣ በእርግጠኝነት ሊባል የሚቻለው ቤተ ክርስቲያኒቱ ከመጡት መንግሥታት ሁሉ ጋር እጅና ጓንት በመሆን ለሆነው ጥፋትና ውድመት የቅርታ ልትጠይቅም ሌሎችንም ይቅርታ ለማስተማር ዕርምጃዎችን ልትወስድ ይገባታል፡፡

  ReplyDelete
 18. ብፁዓን ገባርያነ ሰላም! እንዲል አምላካችን፣ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እናንተም አባ ሰላማዎች ፍቅርን፣ ዕርቅንና ሰላምን የሚሰብክ እንዲህ ዓይነት ድንቅ የኾነ ጽሑፍ ስላስነበባችሁን የአባቶቻችን አምላክ አብዝቶ ጸጋውን፣ ማስተዋሉንና ጥበቡን ያድላችኹ፡፡ በወርኻ ጾም እንዲህ ዓይነት ፍሬ ያለው ቁም ነገር ግሩም ድንቅ ነው፣ ይበል፣ ይበል የሚያሰኝ፡፡
  በዘር፣ በጎሳ፣ በሥልጣንና በጥቅም የተለያዩትን አባቶቻችንም እነርሱ አንድ ኾነው መንጋውን አንድ የሚያደርጉበትንም ዘመን አምላከ እስራኤል ያቅርብልን፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ጥበብንና ማስተዋልን የተሞሉ ጸሐፍያንንም ያብዛልን፡፡ እናንተ አባ ሰላማዎች በነጋ ጠባ ጆሮአችንን በጥላቻ፣ በአሉባልታና በሐሜት ከሚሞሉ ጽሑፎች ተጠበቁ፡፡ እንደ ስማችሁ የሰላም ሐዋርያዎች ኹኑ፡፡
  ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!
  አባ ፍቅረ ማርያመ፡፡

  ReplyDelete
 19. ብፁዓን ገባርያነ ሰላም! እንዲል አምላካችን፣ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እናንተም አባ ሰላማዎች ፍቅርን፣ ዕርቅንና ሰላምን የሚሰብክ እንዲህ ዓይነት ድንቅ የኾነ ጽሑፍ ስላስነበባችሁን የአባቶቻችን አምላክ አብዝቶ ጸጋውን፣ ማስተዋሉንና ጥበቡን ያድላችኹ፡፡ በወርኻ ጾም እንዲህ ዓይነት ፍሬ ያለው ቁም ነገር ግሩም ድንቅ ነው፣ ይበል፣ ይበል የሚያሰኝ፡፡
  በዘር፣ በጎሳ፣ በሥልጣንና በጥቅም የተለያዩትን አባቶቻችንም እነርሱ አንድ ኾነው መንጋውን አንድ የሚያደርጉበትንም ዘመን አምላከ እስራኤል ያቅርብልን፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ጥበብንና ማስተዋልን የተሞሉ ጸሐፍያንንም ያብዛልን፡፡ እናንተ አባ ሰላማዎች በነጋ ጠባ ጆሮአችንን በጥላቻ፣ በአሉባልታና በሐሜት ከሚሞሉ ጽሑፎች ተጠበቁ፡፡ እንደ ስማችሁ የሰላም ሐዋርያዎች ኹኑ፡፡
  ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!
  አባ ፍቅረ ማርያም

  ReplyDelete
 20. I’ve gone through the short article of Prof. Getachew Haile called ‘Peace and Reconciliation a cure for Life’ and found it a bit bitter. First and foremost, Im not clear why Prof. Getachew used some inflammatory and provocative words and phrase against the Oromo and the Ethiopian Muslims. Such as ‘Gada System is a group of Gangsters/Mafia’, ‘The Oromos were destructive and unlawful people’ and ‘The Oromo people were caused a political, economic and social chaos/crisis in the country, and so on.

  In fact, Prof. also pointed at the Ethiopia Muslims did play the same role as the Oromo. Prof. has mentioned few scholars and writers who had written those bare facts. Anyhow, I have never ever come across scholars (both Ethiopians and foreigners) who labeled the Gada System as ‘a group of Gangsters’.

  Im quite sure that Prof. has already read the book by Prof. Asmerom Legesse. If so how he dared to say like that it’s really shocking. I didn’t expect such pejorative terms from the renowned academician, like Prof. Getachew.

  The Prof. might have a hidden agenda against the Oromo people and to add some fuel on the already going on, the Oromo Freedom Question discourses, such as by Jawar Mohammad and his friends. In fact, his article is mainly grounded on the lately Jawar’s debates. But he absolutely failed to address the bare bones of the matter.

  It is quite obvious that we need to rebrand our way of narration of the Ethiopian history or Past. Unless Prof. Getachew’s way of narrating or approaching will definitely lead us to hatred and destruction. Ethiopia desperately needs sons and daughters, who are dedicate their time, knowledge, power and even life to rescue her from division and hatred.

  Where are the Beautiful ones for Ethiopia? They are not yet born or …???

  ReplyDelete
 21. ጸሐፊው ዲያቆን ተብዬ፣ የራእይ ማርያም ተረት ተረትንና ዕርግማንን በስሟ ታትሞ እርሷም በጉያዋ ይዛ ምእመኖቿም ለዘመናት ለጸሎት እንዲጠቀሙበት ያደረገችውን ቤ/ን ንጽሕት፣ ርትዕት፣ ሐዋርያዊትና ጥንታዊት ብሎ ሲጠቅሳት ያው የማኅበረ ቅዱሳን ግርፍ መሆናቸውን አስመስክረዋል፡፡ መቼም ይህ ዕርግምንና ሌሎችንም ጉዶች ተሸክማ ያለች ቤ/ን በምን ሂሳብ ሐዋርያዊትና ርትዕት ልትባል እንደምትችል እግዚአብሔር ያሳያችሁ፡፡


  ጸሐፊው ያነሡት አሳብ ድንቅና ግሩም፣ የፖለቲካ ታሪክ እውቀታቸውና ትንታኔያቸውም ሚዛናዊና አስተውሎት ያለው ቢሆንም በመንፈሳዊ ሕይወታቸው ረገድ ግን ገና የማኅበረ ቅዱሳን የአሮጊቶች ተረት ተረትና ዘመን የጣለው ድርሰቶቻቸው ምርኮኛ መሆናቸው ግን ግልጽ ነው፡፡ እናም ጸሐፊው ራሳቸውን ከማኅበረ ቅዱሳን የግብዝነት ሰንሰለትን አውጥተው ከጨለማ ወይም ከግዞት ወደ ብርሃን ይመጡ ዘንድ ልናግዛቸው ይገባል፡፡ መዳን በሌላ በማንም የለም፣ እንድንበት ዘንድ ከሰማይ በታች የተሰጠ ሌላ ስም የለምና፣ እርሱም የእግዚአብሄር ሕያው ልጅ የሆነው ኢየሱስ ነው!!!

  ReplyDelete
 22. Thank you Jesus you bring us together to open our eyes and to see it and to correct our mistake. We Ethiopian Orthodox we are not blind anymore we have to correct our mistake we are not lead by blind anymore. We can read the Bible. The Bible is the only truth words of God nothing else. May God open our EYS?

  ReplyDelete
 23. I’ve gone through the short article of Prof. Getachew Haile called ‘Peace and Reconciliation a cure for Life’ and found it a bit bitter. First and foremost, Im not clear why Prof. Getachew used some inflammatory and provocative words and phrase against the Oromo and the Ethiopian Muslims. Such as ‘Gada System is a group of Gangsters/Mafia’, ‘The Oromos were destructive and unlawful people’ and ‘The Oromo people were caused a political, economic and social chaos/crisis in the country, and so on.
  In fact, Prof. also pointed at the Ethiopia Muslims did play the same role as the Oromo. Prof. has mentioned few scholars and writers who had written those bare facts. Anyhow, I have never ever come across scholars (both Ethiopians and foreigners) who labeled the Gada System as ‘a group of Gangsters’. Im quite sure that Prof. has already read the book by Prof. Asmerom Legesse. If so how he dared to say like that it’s really shocking. I didn’t expect such pejorative terms from the renowned academician, like Prof. Getachew.
  The Prof. might have a hidden agenda against the Oromo people and to add some fuel on the already going on, the Oromo Freedom Question discourses, such as by Jawar Mohammad and his friends. In fact, his article is mainly grounded on the lately Jawar’s debates. But he absolutely failed to address the bare bones of the matter.
  It is quite obvious that we need to rebrand our way of narration of the Ethiopian history or Past. Unless Prof. Getachew’s way of narrating or approaching will definitely lead us to hatred and destruction. Ethiopia desperately needs sons and daughters, who are dedicate their time, knowledge, power and even life to rescue her from division and hatred.
  Where are the Beautiful ones for Ethiopia? They are not yet born or …???

  ReplyDelete
 24. what a lier are you aba selama...i have read 6 times there is no anything related to you lie.shame on you.please aba selama commenters read mezgebe tselot book and find raeye maryam...hiruy....how did you believe them..havent you read this book befor.....shame on you

  ReplyDelete
 25. I read ‹‹የራእይ ማርያም›› just finished it minutes ago. I didn’t find the bad mouthing words (gala, shankla, etc). I wonder why the writer created fake stories. Many people may believe the content of the article. Please read ‹‹የራእይ ማርያም›› before reaching to conclusion.

  ReplyDelete
 26. Raeye maryam mierafna kutir yelewm?

  ReplyDelete
 27. በመጀመር ያው ዉሽት ለማውራት የማይታክታችሁ የዲያቢሎስ ልጆች መሆናችሁ አሳይታችሁናል ራእየ ማፘም የተባለው መስሃፍ ውዳሴ ማፘምን የሚያክል ትንሽ ምጽሃፍ ማንም በ5ብር ገዝቶ ማንበብ ይችላል እውነታውን ማየት ከፍለ ሰለ ብሄር ሆነ ስለ እስልምና አያነሳም ወይም መዝገበ ጸሎት ካላችሁ እርሱ ጋር አብሮ ተተርዟልና ተመልከቱ እና የአባ ሰላማን ዉሸታምነት እወቁplease dont jugje without reading the book....another thing i surprised was...hiruy

  ReplyDelete
  Replies
  1. በመጀመር ያው ዉሽት ለማውራት የማይታክታችሁ የዲያቢሎስ ልጆች መሆናችሁ አሳይታችሁናል ራእየ ማፘም የተባለው መስሃፍ ውዳሴ ማፘምን የሚያክል ትንሽ ምጽሃፍ ማንም በ5ብር ገዝቶ ማንበብ ይችላል እውነታውን ማየት ከፍለ ሰለ ብሄር ሆነ ስለ እስልምና አያነሳም ወይም መዝገበ ጸሎት ካላችሁ እርሱ ጋር አብሮ ተተርዟልና ተመልከቱ እና የአባ ሰላማን ዉሸታምነት እወቁ

   Delete
 28. Hello!!

  Where did you get "...‹‹ እስላም››፣ ‹‹ጋላ››፣ ‹‹ሻንቅላ››፣ ‹‹ፈላሻ›› ጋር የተኙ...." from???? of course it says "..አራስ፣ መርገም፣ .." and animals. I have it on my hand it doesn't say like that. The writer never read "raeye Mariam" or think people never read it. Shame on you and everyone who believe you without reading the book. Don't be such foolish lier!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አንተ ያነበብከው ኢዲት ተደርጎ የታተመመውን ነው። ኦርጂናሉ የአማርኛ ቅጂ እና ግዕዙ ግን የሚለው የተጻፈውን ነው። ጸሐፊው ያነሳው ዋናውን ኦርጂናል ቅጂውን ነው። የተባለው ሁሉ መኖሩ የማይካድ እውነት ነው።

   Delete
  2. ጸሐፊው ዲ/ን ኒቆዲሞስ የጠቀሱት የራእይ ማርያምን የጥነቱን እትም ነው፡፡ በ1960 ዓ.ም. የታተመው የራእይ ማርያም መጽኸፍ አለኝ፡፡ ያንኑ ነው የሚለው ያው ተስፋ ዘገብረ ሥላሴ ዘብሔር ቡልጋ በዘመነ ኢህአዴግ እንዲህ ዓይነቱ ሕዝብን ጎሳ ለይቶ ማዋረድ የሚያመጣውን ጣጣ ስለሚያውቁ እነዚህን ለዘመናት በመጽሐፉ ውስጥ የነበሩትን ጉዶች አውጥተው አሳትመውታል፡፡

   አሳዛኙ ነገር በሀዚህ የጸሎት መጽሐፍ ሕሊናቸው የቆሰሉ ሰዎች ግን እስካሁንም ቁስላቸውን እያስታመሙ ያሉ መሆናቸው ነው፡፡ መቼም ምናልባት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ነገሮች የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተምህሮ አይወክልም ብለው ሊናገሩ የሚችሉ ይኖራሉ፡፡ ግና ራእይ ማርያም በጸሎት መጻሕፍቶች/በመዝገብ ጸለኮት ውስጥ ተካቶ ለምእመናኑ እየተሸጠ ነው፡፡

   እስከ ዘመነ ኢህአዴግ ድረስም ያ ጉድ እዚህ መጻሕፍ ውስጥ ነበር፡፡ ብዙዎችም ከዚሁ መርገምና ክፋት ጋር አብረውት ሲያነቡት ነበር፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ላሉት ስህተቶች ኃላፊነት ወስዶ ይቅርታ የጠየቀ አካልም ሆነ አሳታሚ የለም፡፡ እናም ይህን ያነበቡ ሁሉ ከቁስላቸው ጋር አሁንም ድረስ አብረው አሉ፡፡ የሚያስከትለውን መዘዝ የተረዱት ቀኛዝማች ተስፋ ገ/ሥላሴ ይሄን ጉድ ገድፈው አውጥተው አሳትመውታል፡፡ ግና በሥላሴ አምሳል የተፈጠረው ክቡር ሕዝብ ይቅርታ አልተጠየቀም፣ መጽሐፉም በይፋ አልተወገዘም፡፡ ታዲያ በእነዚህ ሰዎች ላይ ማን ሊፈርድ ይችላል፡፡

   አሳዛኙ ነገር አሁንም ድረስ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ለተጠቀሱት ሕዝቦች ንቀትና ጥላቻ ያላቸው የሃይማኖት አባቶችና አገልጋዮች መኖራቸው የአደባባይ ምሥጢር የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ እናም እውነቱን ተነጋግረን የሚሻለን ይቅር መባባል፣ ዕርቀ ሰላም ማውረድ ነው፡፡

   በተረፈ የቆየውን የራእይ ማርያምን መጽሐፍ ከፓትርያርክ ግቢ ቤተ መጻሕፍት አሊያም ከቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ወይም የጥንቱ እትም ካላቸው ሰዎች ፈልጋችሁ አንብቡት፣ እውነታውን የዛን ጊዜ ታገኙታላችሁ፡፡ በጽንፈኘነት፣ በዐርበኝነት፣ በነፍጠኝነት፣ በንቀት፣ በማንአለብኝነት፣ በጥላቻና በተገዳሪነት መንፈስ ያሉ ሁሉ ሁሌም የሚታያቸው የክርስቶስ የፍቅር፣ የይቅርታ ልብ ሳይሆን እልከኝነትና ቁጣና እንዴት ተደፈርን ባይነት ነው፡፡


   የኦሮሞ ሕዝብና ሌሎች በደቡብ ክፍል የሚገኙ ሕዝቦች ተንቀዋል፣ ተጨፍጭፈዋል፣ ተረግጠዋል፣ ተግዘዋል ... ለዚህ እኩይ ዘመቻ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንወክላን የሚሉ በልቶ አደሮችና አስመሳይ ግብዞች ድጋፋቸውንና የይለፍ ማረጋጋጫቸውን ሰጥተዋል፡፡

   ይህ የቤተ ክህነቱንና የቤተ መንግሥቱ ጋብቻ የፈጠረውን ቀውስ ለመረዳት የሚፈልግ የአዲስ አለማየሁን ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር ቢያነብ እውነታው ይገለጽለታል፡፡ ቤተ ክህነቱን የሚወክሉት እንደ እነ አባ ሞገሴ ያሉ በልቶ አደሮች በዛብህ ከሰብለ መጋር የጀመርውን ንጹሕ ፍቅር ከፊታውራሪ ጋር ሆነው የሰውን ደምና አጥንት ቆጠራ ውስጥ ገብተው ግብዝነታቸውን አለኝ በሚሉት መንፈሳዊ ሥልጣን ማረጋገጫ ሲሰጡት እናያለን፡፡

   እናም ወገን የተበደሉ ይቅርታ ሊጠየቁና ሊካሱ ይገባል፡፡ ይህ ጸሐፊው የገለጸው ትንሹና ጥቂቱ ነው፡፡ ገና ብዙ ጭንቅላትን አስይዞ ኡ ኡ የሚያሰኙ ጉዶች አሉን እኮ ... እረ በወላዲቱ፣ ስለ ማርያም ብላችሁ ወገን እንደ ባለ ሕሊና ሰው እናስብ፣ እንመላለስ ... እንጂ ... እረ ጉድ ነው...!!!

   Delete
  3. ena antena zer manzeroche edit adergacheu safachu malet geezu aylem malet new? yihen lega lebalemuyawochu tewelne. raeye mariyam gala minamin bedenbe yilal. seheteten kemeshefafene mamene yetelekenete milikit new.

   Delete
  4. Ye yiketa lib yinuren!

   Delete
  5. What are you talking about? "...የማይካድ እውነት ነው?" Why don't you scan and post it if you have that copy. Don't try to read which never written. I have the book which is bundled with 'mezgebe tselot' I also have the old individual copy. I never see any thing like that. OK, you may not agree what is written there, you may say that St. Mariam didn't see this raey or some thing like that as usual. But all written there is "siners, those who don't help others, who don't fast, who don't pray...." no ethic or specific group of people there.

   You guys went too much.

   Delete
  6. Stop Hate politics against EOTC!!! This is part of the hate politics going on right now. EOTC is the true way that is why all these internal and external challenges going on.

   Delete
 29. 1. አንዳንድ ወንድሞቼና እህቶቼ የሰጣችሁኝን ትችት እቀበላለሁ!!አስቀድሞ ራዕየማርያምን ሳላመሳክር መናገር አልነበረብኝም!!ትክክል ናችሁ!!ዋናው ነገር ግን እኔ ጸሀፊው ያነሱት ነገር በራዕየማርያም ይገኛል ብየ በጽሁፌ ምስክርነት አልሰጠሁም!!ስላላነበብኩት!
  2. ከተግባባን ያልኩት በግዕዝ የተጻፈ ሁሉ ሃይማኖታዊና በተለይም ኦርቶዶክሳዊ ነው ማለት አይደለም ነው!!ይህን ስልም ብዙ የተማሪ ኩሸት የያዙ በግእዝ የተጻፉ ኢ-መንፈሳዊ ጽሁፎችን ስለማውቅ ነው!!ለምሳሌ፡ ዐውደነገስት በግእዝ ከመጻፉ በቀር በብዙ ይዘቱ ኦርቶዶክሳዊ ሊሰኝ አይችልም!!እኔ ለኦርቶዶክሳዊ መጻህፍት መመዘኛ ቢሆኑ ብየ የጠቀስኩዋቸውን መመዘኛዎችም የሚያልፍ አይመስለኝም!!ቤ/ክ የእኔ ነው ስትል ሰምቸ አላውቅም!!መቸም ግዕዝ ሰፊ ቁዋንቁዋ ነው!! ለረጅም ጊዜ የቤ/መንግስት ቁዋንቁዋ ሆኖ በእለት ተእለት ኑሮ አገልግሉዋል!! በስነጽሁፉም የበለጸገ ነው!!ስለሆነም በግዕዝ የተጻፉ ሁሉ ሃይማኖታዊ ጽሁፎች ብቻ ናቸው ብሎ መደምደም ትክክል አይመስለኝም!!ሃሳቤን በዚህ መልኩ ብትረዱኝ ደስ ይለኛል!!ለበለጠ ማብራሪያ የሰሞኑን የዲ/ዳንኤል ክብረትን የጠቅል አሽከር የሚል ጽሁፍ እዩ!!የእኔን ሃሳብ የሚደግፍ ትንታኔ ይዙዋል!!
  3. ለማንኛውም እናንተም(dear commentators) እንደአንድ ትጉህ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን እኔ የሳትኩትን በመሙላት ስህተቱን ስላረማችሁ ላመስግናችሁ!!ሁላችንም ስለምንወዳት ርእትእት ሃይማኖት ያገባኛል ብለን በድርሻችን መጠን የምንችለውን ስናደርግ ሃሴት አደርጋለሁ!!በተለይ…በተለይ የሁሉም የሀገራችን ሃይማኖቶች ምንጭ ሀገራዊ ሳይሆን አንድም ከቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም፣አንድም ከመካ፣አንድm ከምዕራቡ ዓለም መሆኑ እየታወቀ የተለየን ብሄር ከተለየ ሃይማኖት ጋር በማያያዝ የሚደረግ ጸያፍ የፖለቲካ ዘመቻን እንዳላዩ ማለፍ ቸልተኝነት ሆኖ ይታየኛል!!ድርጊቱ ጸያፍ ነው!!ትርፍም አያስገኝም!!ይቅርብን!!
  4. “አብዝሆ ነገር(መጻህፍት) ያዘነግዕ ልበ” ይላሉ አባቶች!! ብዙ በመናገር ነገረ-ዘርቅ ውስጥ እንዳልገባ ላልተወሰነ ጊዜ ወደ አርምሞ መመለስ እንዳለብኝ ተሰምቶኛል!! “እምተናግሮ ይኄይስ አርምሞ” ይል የለ ሊቁ ቅ/ያሬድስ!!በአግባቡ ሲሆን “አርምሞ ተዐቅብ ሃይማኖተ” የሚለውን መከተል መልካም ነው!!በተለይ በጾም ወራት!!
  እስካሁን ያልነውን ሁሉ ለማለት የረዳንን አምላክ እያመሰገንን ወደ አርምሞ ተመልሰናል!!

  ReplyDelete
 30. ጸሐፊው ዲ/ን ኒቆዲሞስ የጠቀሱት የራእይ ማርያምን የጥነቱን እትም ነው፡፡ በ1960 ዓ.ም. የታተመው የራእይ ማርያም መጽኸፍ አለኝ፡፡ ያንኑ ነው የሚለው ያው ተስፋ ዘገብረ ሥላሴ ዘብሔር ቡልጋ በዘመነ ኢህአዴግ እንዲህ ዓይነቱ ሕዝብን ጎሳ ለይቶ ማዋረድ የሚያመጣውን ጣጣ ስለሚያውቁ እነዚህን ለዘመናት በመጽሐፉ ውስጥ የነበሩትን ጉዶች አውጥተው አሳትመውታል፡፡

  አሳዛኙ ነገር በሀዚህ የጸሎት መጽሐፍ ሕሊናቸው የቆሰሉ ሰዎች ግን እስካሁንም ቁስላቸውን እያስታመሙ ያሉ መሆናቸው ነው፡፡ መቼም ምናልባት በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ያሉ ነገሮች የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተምህሮ አይወክልም ብለው ሊናገሩ የሚችሉ ይኖራሉ፡፡ ግና ራእይ ማርያም በጸሎት መጻሕፍቶች/በመዝገብ ጸለኮት ውስጥ ተካቶ ለምእመናኑ እየተሸጠ ነው፡፡

  እስከ ዘመነ ኢህአዴግ ድረስም ያ ጉድ እዚህ መጻሕፍ ውስጥ ነበር፡፡ ብዙዎችም ከዚሁ መርገምና ክፋት ጋር አብረውት ሲያነቡት ነበር፡፡ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ላሉት ስህተቶች ኃላፊነት ወስዶ ይቅርታ የጠየቀ አካልም ሆነ አሳታሚ የለም፡፡ እናም ይህን ያነበቡ ሁሉ ከቁስላቸው ጋር አሁንም ድረስ አብረው አሉ፡፡ የሚያስከትለውን መዘዝ የተረዱት ቀኛዝማች ተስፋ ገ/ሥላሴ ይሄን ጉድ ገድፈው አውጥተው አሳትመውታል፡፡ ግና በሥላሴ አምሳል የተፈጠረው ክቡር ሕዝብ ይቅርታ አልተጠየቀም፣ መጽሐፉም በይፋ አልተወገዘም፡፡ ታዲያ በእነዚህ ሰዎች ላይ ማን ሊፈርድ ይችላል፡፡

  አሳዛኙ ነገር አሁንም ድረስ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ለተጠቀሱት ሕዝቦች ንቀትና ጥላቻ ያላቸው የሃይማኖት አባቶችና አገልጋዮች መኖራቸው የአደባባይ ምሥጢር የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡ እናም እውነቱን ተነጋግረን የሚሻለን ይቅር መባባል፣ ዕርቀ ሰላም ማውረድ ነው፡፡

  በተረፈ የቆየውን የራእይ ማርያምን መጽሐፍ ከፓትርያርክ ግቢ ቤተ መጻሕፍት አሊያም ከቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ወይም የጥንቱ እትም ካላቸው ሰዎች ፈልጋችሁ አንብቡት፣ እውነታውን የዛን ጊዜ ታገኙታላችሁ፡፡ በጽንፈኘነት፣ በዐርበኝነት፣ በነፍጠኝነት፣ በንቀት፣ በማንአለብኝነት፣ በጥላቻና በተገዳሪነት መንፈስ ያሉ ሁሉ ሁሌም የሚታያቸው የክርስቶስ የፍቅር፣ የይቅርታ ልብ ሳይሆን እልከኝነትና ቁጣና እንዴት ተደፈርን ባይነት ነው፡፡


  የኦሮሞ ሕዝብና ሌሎች በደቡብ ክፍል የሚገኙ ሕዝቦች ተንቀዋል፣ ተጨፍጭፈዋል፣ ተረግጠዋል፣ ተግዘዋል ... ለዚህ እኩይ ዘመቻ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንወክላን የሚሉ በልቶ አደሮችና አስመሳይ ግብዞች ድጋፋቸውንና የይለፍ ማረጋጋጫቸውን ሰጥተዋል፡፡

  ይህ የቤተ ክህነቱንና የቤተ መንግሥቱ ጋብቻ የፈጠረውን ቀውስ ለመረዳት የሚፈልግ የአዲስ አለማየሁን ‹‹ፍቅር እስከ መቃብር ቢያነብ እውነታው ይገለጽለታል፡፡ ቤተ ክህነቱን የሚወክሉት እንደ እነ አባ ሞገሴ ያሉ በልቶ አደሮች በዛብህ ከሰብለ መጋር የጀመርውን ንጹሕ ፍቅር ከፊታውራሪ ጋር ሆነው የሰውን ደምና አጥንት ቆጠራ ውስጥ ገብተው ግብዝነታቸውን አለኝ በሚሉት መንፈሳዊ ሥልጣን ማረጋገጫ ሲሰጡት እናያለን፡፡

  እናም ወገን የተበደሉ ይቅርታ ሊጠየቁና ሊካሱ ይገባል፡፡ ይህ ጸሐፊው የገለጸው ትንሹና ጥቂቱ ነው፡፡ ገና ብዙ ጭንቅላትን አስይዞ ኡ ኡ የሚያሰኙ ጉዶች አሉን እኮ ... እረ በወላዲቱ፣ ስለ ማርያም ብላችሁ ወገን እንደ ባለ ሕሊና ሰው እናስብ፣ እንመላለስ ... እንጂ ... እረ ጉድ ነው...!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. 100 በ 100 እውነት ነው::

   Delete
  2. እውነትን እውነት ለማለት ድፍረት ስላለህ ጎበዝ ሰው ነህ

   Delete
 31. my friends great and wonderful articles . Good job////////some many things wrong books in our church.........most of new written book are fine but when we look the all oldest book in our church was wrong message obtain books kept......in the hiding place. that wise our God brought this kind of good articles against of Professor Getachew.revealed All Orthodox Christian are equal and good peoples, it doesn't matter where you came from.........some stupid racist tribes members but still thinking bad ideas...not good for anybody....... .

  ReplyDelete
 32. Hi Aba Selama's editor: Please kindly post Prof. Getachew Haile's article as well.

  ReplyDelete
 33. ቀወጥሽው ብራዘር ፒፕሉን አነቃነቅሸው እኮ። አሪፍ ነው ይመችሽ

  ReplyDelete
 34. ውድ ዲ/ን ኒቆዲሞስ ዕርቅ ይሁን፣
  የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ጽሑፍ በጣም እንደከነከነኽ በረዥሙ ከደረደርከው ጽሑፍ ለመርዳት ይቻላል፡ እንደምትለው፣የቤተክርስቲያን ምሑር እና የታሪክ ተመራማሪ ያውም የቅርስ ባለሙያ ሆነህ እያለ እንዴት ባኦሮሞ ወረራ የወደሙ ቅርስና አብያተክርስቲያናትን አታውቅም? እኔ እንደሚመስለኝ፣ ከነጃዋር ሙሀመድ አባላት አንዱ እንደሆንክ ነው የማምነው፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን እና የአማራ ሕብረተሰብ እኮ እንኳን ከመቶ ዓመት በፊት የተፈጸመ ታሪክ ቀርቶ ከዛሬ ሃያ ሁለት ዓመት በፊት በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ግፍና ጭፍጨፋ እንኳ ዝም ብሎ ታግሷል፡ እና፣ አንተ ዲያቆን?! ከአነጋገር ይፈረዳል፥ ከአያያዝ ይቀደዳል ይባላል።

  ReplyDelete
 35. Mr. Getachew Haile is one of undercover writer of mk element. Working hard to return Amahara superior complex. Oromo major population in Ethiopia will be respect as citizen.

  ReplyDelete
 36. I don't think terms Shankila,Galla and Felasha represent any tribe in Ethiopia.This terms have been drawn out from the mentioned article to different tribes who had their own name before.This was to easily Concur them.I don't accept Oromo is Galla. Oromo is Oromo .In history of Ethiopia there were many other names attached to different tribes like Gurage,Welamo,Agame,Kullo,Gimira etc to denounce them as inferior to the Amharas for concurring purpose unrelated to the churches mission and objectives.Before writing any comment,please think as much as you understand.Hasty generalizations leads to unnecessary disputes among brothers

  ReplyDelete
 37. Oromia shall be Free!
  Oromia shall be Free!
  Oromia shall be Free!
  Oromia shall be Free!
  Oromia shall be Free!
  Oromia shall be Free!
  Oromia shall be Free!

  ReplyDelete
  Replies
  1. For What Puropse

   Delete
  2. "Oromia shall be Free!"? From what????

   Delete
  3. "Oromia shall be Free!"? From What????

   Delete
 38. ‹እስላም››፣ ‹‹ጋላ››፣ ‹‹ሻንቅላ››፣ ‹‹ፈላሻ›› ጋር የተኙ፣ ፈረስ፣ አህያ፣ ግመል በግብረ ስጋ የሚገናኙ፣ ወንዱም ግብረ ሰዶም ወገሞራ የሚዳረጉ… እነዚህ ሁሉ ኩነኔያቸው ይህ ነው አለኝ …፡፡ RASUN GALA SHANKILA BILO YEMITERA AKAL YITEYIK AHZAB HULA TSEHAFIW CHIMER

  ReplyDelete
 39. የተጻፈውን አስነዋሪ ሁሉ ጽሑፍ በኦርቶዶክስ ቤ/ክ አናሳብብ ግለሰቦች እንደፈለጉ ለቅልቀው በቤ/ክ ስም ያስገቡትን ሁሉ ቤ/ክ እንዳደረገችው ተቆጥሮ በቤ/ክርስቲያኒቷ ላይ የቀረበ ዘለፋ ንስሃ ያስገባል ለምሳሌ በፕሮቴስታንቶች የተለያዩ ሰዎች የሚጽፏቸው አስተሳብ የያዘ ትምህርት አለ< ስለ ብልጽግና ወንጌል>ታዲያ ይህ ጽሑፍ ሁሉን አይወክልም አንድ ግለሰብ ታየኘ ያለው ጻፈ የፈለገ ይቀበለዋል ያልፈለገ ይተወዋል ልክ እንደዚያ ማለት ነው ግን በዚህ ትምህርት እርስ በርስ ሲወጋገዙ አንብበናል።እና ታዲያ ይህ ፕሮቴስታንትን ሁሉ ይወክላልን?በኦርቶዶክስ ቤ/ክ መሰረታዊ ትምህርት እንዳለ እናውቃለን ያንን በተመለከተ ማስተማር ይሻላችኋል!
  የአርማትያሱ ዮሴፍ

  ReplyDelete
 40. እስላም››፣ ‹‹ጋላ››፣ ‹‹ሻንቅላ››፣ ‹‹ፈላሻ› means muslims, pagans and jew. Nothing else. Galla and shangalla(shanqila) andi newu. Shanqila agewoch ena oromowoch galla lemalet yemiteqemut qal newu.

  ReplyDelete
 41. Atakabdu እስላም››፣ ‹‹ጋላ››፣ ‹‹ሻንቅላ››፣ ‹‹ፈላሻ› means Muslims Pagans and Jew. ጋላ›› amaroch non christian barbaric lemalet ke arebigna yeweresut qal ፣ ‹‹ሻን ጋላ> Agewoch ena oromowoch non christian barbaric Christian malet newu bediro gize. Galla can be from any ethnic or tribe, not Oromo.

  ReplyDelete
 42. Oromona Gumuz wendimochachinin kebetekiristiyan bemasiwetat protestant lemadireg qdemit geez yemichilu kebetekiristian yekobelelu protestantoch bebetekristianitu sim asegebitewu endasatemut eyetaweke yihen yakil ggirigir "wusha bekededewu jib yigebal" ayinet ayin awutanet yimesilegnal. Yihunina hulachinim melikamunina yemibejewun meyaz yigebanal.

  ReplyDelete