Thursday, March 27, 2014

ነገረ ማርያም የተባለው መጽሐፍ “ልዩ ወንጌል” በመሆኑ በሐዋርያት ሥልጣን የተወገዘ ነው                                                          ከመምህር አዲስ
ነገረ ማርያም ስለ ቅድስት ማርያም የሚናገር መጽሐፍ ነው። ስለማርያም የሚናገረውም በመጽሐፍ ቅዱስ ስለእርስዋ ከተጻፈውም በመጽሐፍ ቅዱስ ከማይታወቀውም ታሪክ እያመጣ ነው። አሁን አሁንማ ይህ መጽሐፍ እንደጸሎት እንዲደገም በመዝገበ ጸሎት ውስጥ ተካቶ ታትሟል። ብዙ ምእመናንም እንደ ጸሎት ያነበንቡታል። ምን ያህሉ ግን በውስጡ የያዘውን “ልዩ ወንጌል” አስተውሎ ይሆን? የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው፡፡  
 በቅድሚያ “ልዩ ወንጌል” (another gospel) የተባለው ምንድነው? ስለ ልዩ ወንጌል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በገላትያ 1፡6 ላይ “በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤” ተብሎ ተጽፏል፡፡ እንደዚሁም በ2ኛ ቆሮንቶስ 11፡4 ላይ “የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥ በመልካም ትታገሡታላችሁ።” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ከእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የምንረዳው ልዩ ወንጌል ተብሎ የተገለጸው ከእውነተኛውና የሚያድነውን የምሥራች ከያዘው ወንጌል በተቃራኒ የሚገኝና እውነተኛውን ወንጌል ለማስተባበል የሚሰበክና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እውነተኛውን ወንጌል የሚቃወም መልእክት ነው፡፡ እንዲህ ያለው የተሳሳተ “ልዩ ወንጌል” በሚያጋጥመን ጊዜ እንዳንቀበለውና በመልካም እንድንታገው ሐዋርያው ጳውሎስ በሁለቱም ጥቅሶች ውስጥ አስተምሮናል፡፡

Tuesday, March 25, 2014

በቨርጂንያ እስቴት በምትገኘው በአሌክሳንድርያ የሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት አስተዳዳሪ ጉዳይ እነቀሲስ አስተርአየ እና አቡነ ፋኑኤል እየተወዛገቡ ነውየቀድሞው ቄስ በቨርጂኒያ ሰቴት በአሌከሳድርያ ከተማ የምትገኘው የሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት አስተዳዳሪ የሆኑት ግለሰብ አሳይተዋል ባሉትና አገር ባወቀውና ፀሐይ በሞቀው የቅድስና ችግር ሳቢያ ተገቢውን መንፈሳዊ አካሄድ ተከትለው ችግሩን ለመፍታት ያደረጉት ጥረት ባለመሳካቱ ግለሰቡን ማውገዛቸውን ሊቀ ማእምራን ዶ/ር አማረ ካሳዬ ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ እና አባ ኃይለሚካኤል ተክለሃይማኖት ባስተላላፉት ቃለ ወግዘት አስታወቁ፡፡ በ4 ገጽ በተላለፈው ቃለ ውግዘት ላይ የግለሰቡ ችግሮች የተዘረዘሩ ሲሆን አንዳንዱ ችግር በይቅርተ የማይፈታና ከመቀደስ ውጪ የሚያደርጋቸው ወይም ሥልጣነ ክህነታቸውን የሚያስወሰድ ነው፡፡ የግለሰቡን ችግር ተበዳይ የሆኑና ሚስታቸውን በቄሱ የተቀሙት ግለሰብ ለክፍሉ ጳጳስ ለአቡነ ፋኑኤል ጉዳያቸውን ቢያቀርቡም ጳጳሱ ግን “ካቅሜ በላይ ስለሆነ ወደሕግ አቅርበው” ማለታቸው በቃለ ውግዘቱ ላይ ተመልክቷል፡፡

Saturday, March 22, 2014

የደብር አስተዳዳሪዎች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተቃውሞ መግለጫ ሊያወጡ ነውምንጭ፡-http://www.addisadmassnews.com/
(ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ውጭ በመሆን የማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት ሆኖ የነበረው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ሚዛናዊ ዘገባ ለማቅረብ ሞክሯል። ብዙዎቹ “ጋዜጠኞቻችን” ከሀራው አሉላ ጋር ያላቸውን ጓደኝነት ለእውነት ሳይሆን በእውነት ላይ እንዲቆሙ አድርጎዋቸዋል። በቤተክርስቲያን ጉዳይ የሚሰሩት ዜና ሁሉ የማኅበረ ቅዱሳንን ሀሳብ ብቻ የሚያንጸባርቅ እና ፍጹም ሚዛናዊነት የጎደለው ሆኖ ይስተዋላል። ለዚህ ደግሞ ሚናውን እየወሰዱ ያሉት አዲስ አድማስ ሰንደቅና ፋክት ናቸው። ጋዜጠኝነት ግን እነሱ እየሆኑ እንዳሉት በአንድ ጥግ ቆሞ መጮህ አይደለም። እሱ የጠበቆች ሥራ ነው። ጋዜጠኞች ግን እንኳን በቅጡ በማያውቁት በቤተክህነት ጉዳይ አይደለም በማንኛውም ጉዳይ ቢሆን የእነርሱ ድርሻ ሁሉንም ያማከለ ሚዛናዊ ዘገባ ማቅረብ ነው።
ከዚህ አንጻር በዛሬው ዕለት የወጣው የአዲስ አድማስ አገባ በአንጻራዊነት ሚዛናዊ ሆኖ ተገኝቷል። የጋዜጣውን ዘገባ እንድታነቡት አቅርበነዋል።)
   ማኅበረ ቅዱሳን የተዘጋጀውን የአስተዳደር መዋቅር ተቆጣጥሮ ለፖለቲካ ጥቅም ሊያውል ይፈልጋል በማለት የሚቃወሙ የአዲስ አበባ የደብር አስተዳዳሪዎች ዛሬ ስብሰባ የሚያካሂዱ ሲሆን፤ የማህበረ ቅዱሳን አባላት በበኩላቸው ዘመቻ ተከፍቶብናል ይላሉ፡፡ 
የአዲስ አበባ አድባራት አስተዳዳሪዎች ማኅበሩ ሀብቱንና ንብረቱን እንዲያስረክብ ሊያስገድዱት ተዘጋጅተዋል ይላሉ የማህበሩ አባላት፡፡ ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር በመጣስ እንደሚንቀሳቀስ የሚጠቅሱት አስተዳዳሪዎቹ በበኩላቸው፤ ገንዘቡንና ንብረቱን የሚያንቀሳቅሰው ከጠቅላይ ቤተ ክህነት አሰራር ውጭ ስለሆነ   የሀብቱና ንብረቱ መጠን አይታወቅም ይላሉ፡፡ 

Tuesday, March 18, 2014

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ ማቅ ለፈጸመው ስሕተት ባለው የሚዲያ ሽፋን ሁሉ ይቅርታ እንዲጠይቅ ወሰነ

Read in PDFየመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ በቀን 13/6/2006 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ በትምህርትና ሥልጠና መምሪያ በቀረበው የ5 ዓመት መሪ ዕቅድና የ1 ዓመት የሥራ ዕቅድ ላይ ውይይትና ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት መዋቅርን ጠብቆ ሳይሆን እንዳሻው መስራት የለመደው ማኅበረ ቅዱሳን የአሠራር መዋቅርን ሳይከተል በፈጠረው የመዋቅር ጥሰት ምክንያት ማኅበሩ ባለው የሚዲያ ሽፋን ሁሉ ይቅርታ እንዲጠይቅ ውሳኔ አሳለፈ።
የውሳኔው ደብዳቤ ለማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማእከል ጽ/ቤት የተላለፈው በጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ፊርማና ቲተር መሆኑም ተመልክቷል፡፡ ደብዳቤው ራሱን “ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ወጥቻለሁ፤ አሁን በሲኖዶስ ስር ነኝ” እያለ ለሚጠራው ማቅ ይህን እውቅና የነፈገው ሲሆን፣ የደብዳቤው አድራሻው በቀጥታ “ለማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማዕከል ጽ/ቤት” ነው የሚለው፡፡
በደብዳቤው እንደታተተው ቤተ ክርስቲያኒቱ ራሱን የቻለ ሕግና ደንብ ያላት ከመሆኑም በላይ ይህንኑ ጠብቃና የእዝ ሰንሰለትን አክብራ እየሰራች ባለችበት ወቅት ማንአለብኝ ባዩ ማቅ እያደረገው ያለው የመዋቅር ጥሰት ተገቢ አለመሆኑን ገልጾ ማኅበሩ ለፈጸመው የመዋቅር ጥሰት በይፋ ቤተክርስቲያኗን ይቅርታ እንዲጠይቅ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ይህም የሚያሳየው ማቅ ቤተክርስቲያኗን እንደበደለ ነው፡፡ እንዲያ ባይሆን ኖሮ ቤተክርስቲያኗን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ ባልተደረገም፡፡ 

Sunday, March 16, 2014

የቤተክርስቲያን ልሳን የሆነው ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ማኅበረ ቅዱሳን አዘጋጅቶት የነበረው የአብነት መምሕራን የምክክር ጉባኤ የታገደው ሕገወጥ በመሆኑ ነው አለ

Read in PDF


በማንአለብኝነት እየተንቀሳቀሰ ያለውና በሕገወጥ መንገድና በቤተክርስቲያን ስም የግል ጥቅሙን እያካባተ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን እንደትልቅ የገቢ ምንጭ የሚጠቀምበትን የአብነት ትምህርት ቤት ከእስካሁኑ በበለጠ ሊጠቀምበት በማሰብ ጠርቶት የነበረው የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ መታገዱን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይህንኑ እግድ አስመልከቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልሳን የሆነው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በየካቲት 2006 ዓ.ም. እትሙ ጉባኤው ሕገወጥ በመሆኑ መታገዱን ገልጿል፡፡ 
እንደጋዜጣው ዘገባ ከሆነ ጉባኤው የታገደው የሥልጣን ተዋረድ ማእከሉን ያልጠበቀና ቤተክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት እንደሌላት የሚያስቆጥር ሕገ ወጥ አሠራር በመሆኑ ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው በማኅበረ ቅዱሳን አካሄድ ሕገወጥነት በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ እየተስፋፋ መሆኑን ነው፡፡ለዚህም አንዱ ማሳያ በግዮን ሆቴል ሊደረግ የታሰበው ጉባኤ ቢታገድም ሕገወጡ ማቅ ግን “የቅዱስነታቸውን ትእዛዝ ተግባራዊ ባለማድረግ በራሱ ጽሕፈት ቤት የምስክር ጉባኤውን ማካሄዱ ነው፡፡” ሲል የማቅን ሕገወጥነት ጋዜጣው አጋልጧል፡፡ 

Friday, March 14, 2014

ፍርድ ቤት ችሎት ላይ አይደለም የተቀመጠው “አሜን!” የማይለው፡፡ምንጭ፡-http://awdemihreet.blogspot.com/
        ከዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
(መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ወደ አውደ ምህረት ከተመለሰ በኃላ እርር ያሉት የማቅ ብሎጎች እሱን “መናፍቅ” ለማለት የሚያስችለን ነው ብለው ያመኑበትን ስድ ስድብ እየደረደሩ ይውጣልን ይጥፋልን የሚያሰኝ ዛር ነግሶባቸው እየተክለፈለፉ ይገኛሉ፡፡ መቸም ለዲያቢሎስ ጭንቀቱ የሚድነው መብዛቱ እና የሱ መንግስት ጠላቶች የመንግስቱን ሀሳብ ሲያፈርሱ ማየት ነው፡፡ ተከታዮቹም በጌታቸው መንግስት ላይ የተቃውሞ ሀሳብ ያለውን ክርስቲያን ሁሉ ማሳደድን እምቢኝ ብለው አያውቁም፡፡
ለማኅበረ ቅዱሳን መሪዎች የዲያቢሎስን አሰራር ለማፍረስ በተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅ አምኖ የዲያቢሎስን አሰራር ለማፍረስ የሚንቀሳቀስ ክርስቲያን ሁሉ ጠላታቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው ሰሞኑን በሁሉም ብሎጎቻቸው እንደገና መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ላይ መዝመት የጀመሩት፡፡ የወላይታ ሶዶው ጉባኤ እንዳይካሄድ ያደረጉት ጥረት ሁሉ  ከሽፎ ጉባኤው ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት መካሄዱ ቢያቃጥላቸው “ስህተት” ብለው ያገኙትን ነገር ነቅሰው አወጡ፡፡ ታዲያ በማቅ መመዘኛ ትልቁ ምንፍቅና በ10 ደቂቃ 20 ጊዜ አሜን ማለት ሆኖ ተገኘ፡፡ ከታወሩ አይቀር እንዲህ ነው እንጂ!!!
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል አሜን ለምን ይባላል አሜን ማለት የሊቅነት ማነስ ውጤት ነው የሚለውን የአንድ አድርገን ዘገባ እንዲህ ይተቻል፡፡ መልካም ንባብ!! )
ነዋሪነታቸው ጀርመን ፍራንክፈርት  የሆነ አንድ በአካባቢው የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ ምእመን ባሳለፍነው ሳምንት በኢሜይል አድራሻዬ “ … እርስዎስ ምን ይላሉ?” ሲሉ ነበር የጠየቁኝ። አያይዘው ከላኩልኝ ሊንክ በተጨማሪ ለይተው አውጥተው አስተያየቴን የጠየቁበት ጽሑፍ እንደሚከተለው ይነበባል።
ሊቃውንቱ ሲሰብኩ ሰው ወደ ውስጡ እንዲመለከትና በጥሞና እና በአስተውሎ የእግዚአብሔር ቃል እንዲያደምጥ ሲያደርጉ ነበር እኛ የምናውቀው፤ አሁን አሁን በአስር ደቂቃ ጊዜ ውስጥ 20 ጊዜ በላይ ‹‹አሜን›› የሚያስብለውን ሆነ ‹‹አሜን›› በማያስብለው ምዕመኑን ጮኻሂ የማድረግ አዝማሚያ እየታየ ነው፤ መናፍቃን ቤት የሚገኝው ጩኽት እኛ ቤትም ለመግባት ደጃፍ ላይ እያኮበኮበ ይገኛል፡፡[http://www.andadirgen.org/2014/02/blog-ost_5495.html]
እኚህ ወንድም አያይዘው በላክሉኝ መልዕክት የእግዚአብሔር መንጋ ለመበተን የሌሊት እንቅልፍ የማያውቀው ራሱንማኅበረ ቅዱሳንበማለት በሚጠራው ቡድን የሚዘወርአንድ አድርገንየተባለ መካነ ድር ነበርና ከዚህ የሽፍታ ድረ ገጽ ያነበቡትን ጽሑፍ ተንተርሰው የተፈጠረባቸው ጥያቄ ሲጨመቅ ፍሬ ነገሩ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።

Thursday, March 13, 2014

“ኦርቶዶክስ መልስ ካላት እኛም ጥያቄ አለን” የሚለው ቪሲዲ ብዙዎችን እያነቃቃ ነው

Read in PDF


በመምህር ጽጌ ስጦታውና በመሪጌታ ሙሴ የተዘጋጀውና ከወራት በፊት የተሠራጨው ቪሲዲ ብዙዎችን እያነቃቃና የብዙዎችን ዓይን እየገለጠ ነው፡፡ ቪሲዲው የተዘጋጀው ሃይማኖት የለሹና ስም አጥፊው ዘሪሁን ሙላቱ ከእነ ጽጌ ጋር ለመወያየት ከተስማማና ውይይቱ በቪዲዮ ከተቀረጸ በኋላ ስምምነቱን ወደጎን ብሎ ዳጎስ ያለ ትርፍ ለማጋበስ በማሰብ እንደሚፈልገው ቆርጦና ቀጥሎ ማሰራጨቱን ተከትሎ የተዘጋጀ ነው፡፡ 

ዘሪሁን እነመምህር ጽጌን አሸነፍኳቸው ለማለት ቆርጦና ቀጥሎ ያሰራጨው ቪሲዲ እስኪነጋ ድረስ አንዳንዶችን ያሳሳተ ቢመስልም፣ ሲነጋ ግን ውሸቱ እርቃኑን ቀርቷል፡፡ እንዲያውም “ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ አያማልዱም” ብሎ ሲል የማያምንበትን እውነት መንፈስ ቅዱስ ፊቱን ጸፍቶ አፉን ከፍቶ አናግሮታል፡፡

Sunday, March 9, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን የፓትርያርኩን እጅ የመጠምዘዝ፤ እምቢ ካሉም የማስወገድ ትግሉን አጠናክሮ ቀጥሏል!! (ከማን ጋር ሊሰሩ ነው? » አባ ኤልሳዕ

  • የአሀዳዊ መዋቅር ምንጭ በሆነው ሲኖዶስ የምትተዳደር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን ምኗ ነው? 

በአንድ ወቅት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ «በመንግሥት ሌቦች እጃችን ታስሯል» ማለታቸው አይዘነጋም። ከትንሹ በቀቀን ካድሬ አንስቶ እስከ ትልቁ ዓሳ ነባሪ/አንበሪ/ ሹመኛ ድረስ የመዋጥ፤ የመሰልቀጥ ተግባሩን ተመልክተው «የመንግሥት ሌባ እጃችንን አስሯል» ማለታቸው ይህንን ሁሉ በአንዴ ለማስቆም አለመቻላቸውን መግለጻቸው ብቻ ሳይሆን ከስፋቱ አንጻር ለማስቆም መሞከር ውጤቱ አደገኛ ሊሆን መቻሉን ለማመልከት« እጃችን ታስሯል» በማለት የችግሩን ስር መስደድ በአጭር ዐረፍተ ነገር ለመግለጽ ሞክረዋል። እዚያ አደገኛ ደረጃ ላይ የተደረሰው ግን በአንድ ጀምበር ሳይሆን ቀስ በቀስ አንዱ አንዱን እየዋጠና እየፋፋ እንደመሆኑ መጠን እጅ ከመታሰሩ በፊት አስቀድሞ ትንሽ በትንሹ እርምጃ ቢወሰድ ኖሮ አስጊነቱ ያን ያህል ባላሳሰበ ነበር።  ስርቆት ምንጊዜም ከክፉ ሰዎች ልቡና በሚመነጭ ሃሳብ የሚፈጸም ተግባር ነው። ክፉ ሰዎች ደግሞ ሰውን ከመግደል ወደኋላ አይመለሱም። እግዚአብሔርን ማወቅ ከሰዎች ኅሊና ውስጥ ሲጠፋ ጭካኔ ይስፋፋል። እርግማን፤ ግዳይ፣ ስርቆት፤ ደም ማፍሰስ ይበዛል።
በአንድ ወቅት የእስራኤል ልጆች ኃጢአት በመብዛቱና የካህናቱ ርኩሰት መጠን ከማጣቱ የተነሳ እግዚአብሔር አዝኖ የሥራቸውን ዋጋ ይቀበሉ ዘንድ ጥፋት እንደተዘጋጀባቸው መጽሐፍ ቅዱሳችን ይነግረናል።( ሆሴዕ ምዕ 4 እና 5) ሌብነትን መዋጋት ህግን እንደማስከበር ብቻ ሳይሆን መታየት ያለበት ደም ለማፍሰስ የማይመለሱ ሰዎችን ከኅብረተሰቡ ውስጥ እንደማውጣት ይቆጠራል።

Thursday, March 6, 2014

እምነት በአዋጅ ወይስ በእግዚአብሔር ቃል?

    Read in PDF
     
“እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው” ይላል ጳውሎስ በሮሜ 10፥17፡፡ እምነት በሰው አመለካከት ሊሆን አይችልም፣ እምነት ከተባለ እንደ እግዚአብሔር ቃል መሆን አለበት። ቤተ ክርስቲያን የምትባለው የክርስቶስ አካል ስትሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል አምነው የዳኑ ከነገድ ከቋንቋና ከሕዝብ ተዋጅተው አንድ የሆኑባት ጉባኤ ናት።

   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም በመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አማካይነት በትንቢተ ኢሳይያስ ም 53 ትርጉም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ ብላ በመጠመቅ የተመሠረተች ነበረች የሐዋ 8፥ 27-40። ከዚያም ቀስ በቀስ እየሰፋች መጥታ በቅዱስ ፍሬምናጦስ አማካይነት በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ህዳር 21 ቀን ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ተብላ በአክሱም ተመሠረተች። አጼ ዘርዐ ያዕቆብ ህዳር 21ን የማርያም በዓል አድርጎ በታምረ ማርያም እስኪያውጅ ድረስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ማህበረ ጽዮን ሰማያዊት ተብላ የተመሠረተችበት ቀን በአል ነበር። ህዳር 21ን በተመለከተ የሚዘመረውን የያሬድ ቀለም (ዜማ) ድጓውን ብንመለከተው በአክሱም ስለተመሠረተችው ቤተ ክርስቲያን (ማኅበረ ጽዮን)የሚናገር እንጂ ስለ ድንግል ማርያም አይናገርም።

Sunday, March 2, 2014

አባ እስጢፋኖስ ዘጉንዳጉንዲና ተከታዮቹ ስለ ማርያም የሚያምኑት ምን ነበረ?

ከመምህር አዲስ
አባ እስጢፋኖስና ተከታዮቹ እስካሁን ድረስ መነጋገሪያ ሆነው እንደቀጠሉ ነው፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ምናልባትም በፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ የተተረጐመው በሕግ አምላክ መጽሐፍ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ ፀረ ማርያም እየተባሉ ይጠሩ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡ ለዚህም በአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመን በተደረሰው ተአምረ ማርያምና እርሱን በመሰሉ እንደማህሌተ ጽጌ ባሉ የዚያ ዘመን ድርሰቶች የእነዚህ ቅዱሳን ስም እንዲጠፋ ተደርጓል፡፡ ከዚህ የተነሣ ለደቂቀ እስጢፋኖስ በአብዛኛው ሕዝብ ዘንድ የነበረው አመለካከት በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ አስተምህሮ የተቃኘ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የእነዚህ ቅዱሳን ገድል ታትሞ ሲወጣ የአፄ ዘርዓ ያዕቆብ አስተምህሮ ብቻ ሲናኝበት የነበረው መድረክ መልእክቱን እንዲቀይር ተገድዷል፡፡ በዚህ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙ አንዳንዶች ደቂቀ እስጢፋኖስ ለማርያም የነበራቸው አመለካከት አሁን በኦርቶዶክስ እንዳለው ነው በማለት የእነርሱ እንቅስቃሴ የተሐድሶ እንቅስቃሴ አይደለም ለማለት እየጣሩ ይገኛሉ፡፡ ለዚህም ከደቂቀ እስጢፋኖስ ገድሎች ውስጥ አንዳንድ ነጥቦችን እየነቀሱ በማውጣት ፀረ ማርያም አለመሆናቸውን ለማሳየት ይሞክራሉ፡፡ ይሁን እንጂ ደቂቀ እስጢፋኖስ ስለማርያም ያምኑ የነበረው ምን እንደሆነ እነዚህ ወገኖች ቆንጽለው የሚጠቅሱትን ብቻ ሳይሆን ሳይጠቅሱ የሚያልፉትንና በገድላቸው የተጻፈውን ሁሉ መመርመር ያስፈልጋል፡፡

        በቅድሚያ ደቂቀ እስጢፋኖስ በአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘንድ “ፀረ ማርያም” ተብለው መፈረጃቸውን ማስታወስ አስፈላጊ ነው፡፡ ይህም የሆነው ተኣምረ ማርያምን ወደ ገዳማቸው ስላላስገቡና ለማርያም ሥዕል አንሰግድም ስላሉ ነው፡፡ ተአምረ ማርያምን ወደገዳማችን አናስገባም ያሉትም መጽሐፉ ብዙ ኃጢአት የሰሩትን ማርያም አማልዳ አስማረቻቸው ስለሚል መነኮሳቶቻችን ይህን ካነበቡ በቀና ምግባር መኖራቸውን ትተው ንዝህላል ይሆናሉ ብለው ስለሰጉ ነው፡፡ (ደቂቀ እስጢፋኖስ በሕግ አምላክ ገጽ 128)፡፡ እንደተባለውም ሰው እንደፈለገው ኖሮ ተአምረ ማርያም እንደሚሰብከው ለድሃ በማርያም ስም በመመጽወትና በመሳሰሉት ስራዎች ሁሉ በማርያም ምልጃ የሚድን ከሆነ በወንጌል ማመን፣ እንደወንጌሉ ቃል መኖር ወይም ሰፊውን የኃጢአት መንገድ ትቶ በጠባቡ የጽድቅ መንገድ መጓዝ ቦታ ስለሌላቸው መንግስተ ሰማያት የድል ነሺዎች ስፍራ ሳይሆን የቀልድ ቦታ ነው የሚሆነው፡፡ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የቤዛነት ሥራም ከንቱ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ተአምረ ማርያም በደቂቀ እስጢፋኖስ ዘንድ ተቀባይነት ማጣቱ ትክክለኛ ክርስቲያናዊ እርምጃ ነው፡፡ ለዚህም ነው “ዘሰይብል አፈቅረኪ ወኢያፈቅር  ተአምረኪ ክርስቲያናዊ ኢክርስቱን ውእቱ አይሁዳዊ ወሰርጸ እስጢፋ ሐሳዊ” ትርጉም “አንቺን እወድሻለሁ እያለ ክርስቲያናዊ የሆነ ተአምርሽን የሚጠላ እርሱ ክርስቲያን ሳይሆን አይሁዳዊና የዚያ የእስጢፋኖስ  ተከታይ ነው፡፡” ተብሎ አባ እስጢፋኖስ በማሕሌተ ጽጌ የተወቀሰው፡፡