Thursday, March 13, 2014

“ኦርቶዶክስ መልስ ካላት እኛም ጥያቄ አለን” የሚለው ቪሲዲ ብዙዎችን እያነቃቃ ነው

Read in PDF


በመምህር ጽጌ ስጦታውና በመሪጌታ ሙሴ የተዘጋጀውና ከወራት በፊት የተሠራጨው ቪሲዲ ብዙዎችን እያነቃቃና የብዙዎችን ዓይን እየገለጠ ነው፡፡ ቪሲዲው የተዘጋጀው ሃይማኖት የለሹና ስም አጥፊው ዘሪሁን ሙላቱ ከእነ ጽጌ ጋር ለመወያየት ከተስማማና ውይይቱ በቪዲዮ ከተቀረጸ በኋላ ስምምነቱን ወደጎን ብሎ ዳጎስ ያለ ትርፍ ለማጋበስ በማሰብ እንደሚፈልገው ቆርጦና ቀጥሎ ማሰራጨቱን ተከትሎ የተዘጋጀ ነው፡፡ 

ዘሪሁን እነመምህር ጽጌን አሸነፍኳቸው ለማለት ቆርጦና ቀጥሎ ያሰራጨው ቪሲዲ እስኪነጋ ድረስ አንዳንዶችን ያሳሳተ ቢመስልም፣ ሲነጋ ግን ውሸቱ እርቃኑን ቀርቷል፡፡ እንዲያውም “ቅዱሳን በአጸደ ነፍስ አያማልዱም” ብሎ ሲል የማያምንበትን እውነት መንፈስ ቅዱስ ፊቱን ጸፍቶ አፉን ከፍቶ አናግሮታል፡፡

“ኦርቶዶክስ መልስ አላት” የሚለውን ባዶ ቀረርቶ ከዘሪሁን በፊት ዳንኤል ክብረት ርእስ አድርጎ መጽሐፍ የጻፈበት ሲሆን ብዙዎች መልስ ሊያገኙ ቀርቶ ብዙ ጥያቄ እንዲፈጠርባቸው አድርጎ ማለፉ የሚታወስ ነው፡፡ ያንኑ ርእስ አስፈቅዶ ይሆን ቀስጦ ባይታወቅም ዘሪሁን አትራፊ ርእስ ነው ብሎ አስልቶ ሊበላበት ርእሱን የተጠቀመበት ቢሆንም እርሱም መልስ በመሆን ፋንታ በርካታ ጥያቄች እንዲቀርቡ ምክንያት ሆኗል፡፡ ለዚህም ነው እነመምህር ጽጌ “ኦርቶዶክስ መልስ ካላት እኛም ጥያቄ አለን” የሚል ርእስ ለቪሲዲያቸው የሰጡት፡፡ በቪሲዲውም ብዙዎች እየተነቃቁ ሲሆን እርስዎም ቪሲዲውን እንዲ እንጋብዛለን፡፡


55 comments:

 1. ይሁና ብለናል!!!

  ReplyDelete
 2. thank you, great job. more you listen more you know. Truth is never die!!!

  ReplyDelete
 3. ከሁሉም ጥምጣማቸው 'ማማሩ' .... ሂ.ሂ.ሂ..

  ዳላስ ቴክሳስ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ ማህበረ ቅዱሳን ከውስጥ ይልቅ ላይን የምታዬ የመቃብር ውስጥ ምስኪኖች፡፡ ጽጌ ማለት እኮ እንዳንተ ወይም እንደ አንቺ የደለላው በውጭ ሀገር የሚሞላቀቅ አይለም ለጌታው ክብር ሁሉን የተዎ ነው፡፡ ስለዚህ ልቡ ለጌታው ነው ላዬ እንዳያምርም ደሀ ነው ግን በጌታ ክብር ባለጸጋ ነው፡፡ እናንተ ከጥምጥሙ እርሱ ከልቡ ከጌታው አናንተ ከነጠላ እንርሱ ጌታቸውን ለብሰውታል፡፡ማስተዋልን ይስጥህ

   Delete
 4. 1. ምስኪኖቹ ጽጌ ስጦታውና ሙሴ ቪሲዲው አልሸጥ ሲላቸው በነጻ ለቀቁት!!አይ ጽጌ …እኔ አሁንም ኦርቶዶክስ ነኝ… ስትል ከርመህ አሁን ደግሞ ማሊያ ቀይረህ …ኦርቶዶክስ መልስ ካላት ጥያቄ አለኝ… ትላለህ!!እንደው እዛ እና እዚህ መርገጥ ከቆሎ ተማሪነታቸው ሳይበስሉ የተጠለፉ ወንድሞቻችን መለያ ሆኖ ይቅር!!ጎፋ ገብርኤል ሰባኪ እያለህ ነው የማውቅህ!!ከበፊቱም የተምታታብህ ጥራዝ ነጠቅ ስለመሆንህ ለማወቅ አልተቸገርኩም!!ጉባኤ ቤት መቀመጥ ብቻ ምስጢር አደላድሎ ለማወቅ እንደማይረዳ ካንተ ተረድቻለሁ!!
  2. ቅ/ያሬድንም፣የሃይማኖተ አበው ሊቃውንትንም ጥቅሶች ላንተ በሚመች መልኩ ስትቆነጽል በትሪኒቲ መጽሄት በ2003 ዓ.ም አንብቤህ በጣም አሳዘንከኝ!!በዛ መጽሄት ላይ ተለይተህ የወጣኸው በማኅበረቅዱሳን እልህ መሆኑን ተናግረህ አንብቤ ነገ ደግሞ ከፓስተሮቹ ስትጣላ ወደ እስልምና እንዳትሄድ ብየ ነበር!!ተመስገን!!እስካሁን አልሄድክም!!
  3. ፉክክር የበዛበት የፓስተርነት ሕይወት ከቆሎ ተማሪ ቤት ለወጡ እግረ ተማሪዎች(ተልሚድ) ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ስለሚገባኝ ታሳዝኑኛላችሁ!!አይ!! ሰዎቹ እኮ ኦርቶዶክስ…ኦርቶዶክስ የሚሸት ነገር መስማትም ማየትም አይፈልጉም!!በዚህ ላይ የገጠር ላህይ እና የግእዝ ቁዋንቁዋ መስማት ይነስራቸዋል!!ስለዚህ እናንተም ብዙ ያልደከማችሁበትን ግእዝ ከመቆንጸል፡ ሱፍ በከረባት አድርጉና መሀረባችሁን ይዛችሁ ….ጌታ ምስክሬ….እያላችሁ የትንቢት እና የፈውስ ኮንፈረንስ/ኮንሰርት አዘጋጁ!!ወይ አንድ ናይጄሪያዊ ፓስተር ፈልጉና ቅርናጫፉን ኢ/ያ ውስጥ ከፍቶ ውክልናውን እንዲሰጣችሁ ተማጸኑ!!ያለበለዚያ አሁን እንደማያችሁ ከእኛም፣ ከእነሱም፣ ከራሳችሁም ሳትሆኑ መቅረታችሁ ነው!!እንግዲህ ለጊዜው የሰላማ ብሎግ ማስታወቂያ ከረዳችሁ ጥሩ ነው!!ጊዜ ካገኘሁ ቶክሾውን አይቸ እመለሳለሁ!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሁን ከዚህ ዉይይት በመነሳት መልስ ካላችሁ መልስ መስጠት እንጂ ዝም ብሎ ስድብ ምንድርነዉ እኔ መቼም እስከ ዛሬ ምን ያህል እንደተጫወታችሁብኝ ነዉ የገባኝ፣ የጌታችን ትዕግስቱ ይገርማል
   ይልቁኑ ይህንን ቃል በቃል ማስተባበል እስከቻላችሁ ድረስ ብቻ ነዉ መነጋገር የምትቸሉት

   Delete
  2. Please don't reply hopeless answer!!!!!

   Delete
 5. ሀሀሀሀሀ...

  ReplyDelete
 6. "ሊቃውንተ" መናፍቃን ለሆናችሁ
  1. ለዚህ ብሎግ ባለ ቤት ለሆናችሁ ማኅበረ ሰላማዎች፦ በመጀመርያ እንኳን መናፍቅነታችሁ በብሎጋችሁ ለመግለፅ አደረሳችሁ! እርግጥ ነው መግለፅ ከጀመራችሁ እንኳ ሰንበትበት ብላቹኋል አሁን ግን ባሰ...። እኔ እንኳ እስከ ዛሬ ዝምታን መርጬ ነበርኩኝ አሁን ግን እስኪ ስለ መናፍቅነታችሁ ትንሽ ልጨምርላችሁ... ግን ለምንፍቅና ምን ይጨመረዋል? እኔ በጣም የሚገርመኝ ድሮ ድሮ እኮ ስትሸውዱን የነበረው በዘር እየከፋፈላችሁ ነበር። ለምሳሌ ማኅበረ ቅዱሳን የአማራ ነው እኛ ግን የትግራይ ነን ስለዚ ኑ ውደ እኛ እያላችሁ ስንቶቻችን ውደ ጥፋት ከትታችሁን ነበር? ከዚህ መንገዳችሁ ላወጣኝ አምላኬ አመሰግነዋሎህ። ታድያ ዛሬ መናፍቅነታችሁ ራሳችሁን እንድትገልፁ ምን አነሳሳችሁ? የዲያብሎስ ፈረሶችና የመናፍቃን ተላላኪዎች መሆናችሁ ተረድቼአሎህ።
  ይድረስ እንደኔ በየዋህነት ለቤተ ክርስቲያን ካላችሁ ፍቅር የተነሳ መደዚህ ማህበር ለተቀላቀላችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ ከእነዚህ ተኩላዎች ፈጥናችሁ እንድትለዩ አደራ እላሎህ።
  2. ለመናፍቃኑ ጽጌስጦታውና ሙሴ፦ የእናት ጡት ነካሾች እንዳልላችሁ ከመጀመርያው የአምልኮ መልእንጂ እምነት ስላልነበራችሁ ወንበዴዎችና ዘራፊዎች ነበራችሁ? አሁንም ለሆዳችህ ብቻ የምትኖሩ ሆዳሞች የበግ ለምድ የለበሳችሁ ተኩላዎች ናችሁ። ትምህርታችሁና ጥያቄዎቻችሁ ሰማሁላችህ...? ለመሆኑ እናንተ ምድባችሁ የት ነው? በየትኛው መንገድ ሁናችሁ ነው ጥያቄውን የምትጠይቁት? ለነገሩ ፕሮቲስታንት/መናፍቃን መሆናችሁ ንግግራችሁ ስለሚገልጥባችሁ ትቼዋሎህ። እናንተ ሆዳሞችና ተኩላዎች መብላቱስ ብሉ፤ መካዱም ካዱ ለራሳችሁ አትበሉ እኛን ግን ቀድመን ነቅተናልና አንሰማችሁም ሃይማኖታችን ጠንቅቀን እናውቃለን
  እግዚአብሔር እምነታችን ይጠብቅልን!

  ReplyDelete
  Replies
  1. please don't replay hopeless answer!!
   God bess you....Merigeta Tsigie and Mussie!!!

   Delete
 7. "Wey merigeta" Merigeta kelid hone ende enante meri geta satihonu Meri Satinael nachihu gibrachihu simachihun geletew.....

  ReplyDelete
 8. ከዝዋይ ጓደኞቹMarch 14, 2014 at 8:23 AM

  ዘሪሁን በእግዚአብሄር አያምንም በተጨመሪም ከርኩሳን መናፍስት ጋር ባለው ቁርኝት
  ማነኛውንም ደም ካየ ሁከት ሁከት እያለ :ለዚህ ማርከሻ በኪሱ እና በእጁ የያዘውን ገንዘብ እያበተነ እየሮጠ ይሄዳል :: የሴት ነገርማ አይወራም ያያትን ሴት ግብረ ስጋ ሳይገናኛት አይመለስም : በመንገድ ላይ ሴት እየሰመ በመሄድ የሚተካከለው የለም::
  ስለዚህ መልስ ለመስጠት ብቁ አይደለም
  ሊቀ ጠበብት ዘሪሁን
  ሊቀ ጠበብት ማለት የጥንቌዬች አለቃ ማለት ስሙ ከግብሩ ጋር ተሰማምቷል ይበል ነው :
  ዘሪሁን ግን እምነት የለሽ ነውና እንደ ሰባኪ አትዩት

  ReplyDelete
 9. እንዲህ ነው እንጂ መልስ መስጠት እንደ ዘሪሁን ከመንቋቋት እንዲህ በመጽሀፍ የተደገፈ መልስ መስጠት ያረካል።
  እናመሰግናለን

  ReplyDelete
 10. Guys,

  Someone needs to answer their questions properly. We don't have to insult them for raising questions. One of the biggest weaknesses of the EOTC folks is they insult and call names when they are asked questions or challenged.

  The people in the video have raised a very legitimate question, the EOTC's job is to answer them properly. Why resort to name calling? I am EOTC faith follower, but I am happy that such folks are challenging the church because I believe that it helps sift the grain from the chaff and eventually strengthen the EOTC.

  Furthermore, I have read the 2000 new revised version of the 81 Bible to find a lot of distortions. The EOTC Lqawints have made mistakes by re-translating the Holy Bible in a very distorted way. To be fair, there are areas where they made some corrections, but most of the changes are distortions.

  In an attempt to undermine the primacy of Ethiopia, some Westerners replaced the name Ethiopia with the Sudan or Nubia in some English Bible translations, basically defying the Word of God. The 2000 Bible EOTC Liqawint translators made the same mistake as the Westerners did. This shows humans are humans; they always defy God in all places, be it in Ethiopia, USA or Europe, to promote their own agenda, instead of those of God's.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Good assessment & I concur!

   Delete
  2. they did not have a single question. they just want to make arguments. Besides, they are liar by making claim that they are orthodox. liars and lairs.

   Delete
 11. አሜን በል ኦርቶዶክስ

  ReplyDelete
 12. I don't see any difference from the "protestant" teaching except this one is preresented by the title so called "merigeta" and "memihir". It make sense if this was presented by paster. I heard those points many times by those "new christians" every corner of the road. I don't understand why you need to ask this question to Orthodox Tewahido Church, which has different ideology from what you have. This is protestants' teaching. You know the word protestand derived from "Protest", ...

  ReplyDelete
  Replies
  1. የኔ ልጅ እኔ አንተን ብሆን ይህ የፓስተር ጥያቄ ነዉ ከማለት መጀመሪያ መልሱን ስጡኝና ለፓስተሩ ልመልስ እል ነበር አንተም መለሱ ቢኖርህ ኖሮ አሁኑኑ ተመልስልን ነበር ቶሎ በሎ የእከሌ ጥያቄ ነዉ ማለት መልስ ሲያጡ በቀረርቶ የሚገቡት አይነት ነዉና አርፈህ ተቀመጥ

   Delete
  2. AnonymousMarch 17, 2014 at 3:09 AM

   What i said is we don't need to argue!! Believe what you believe, but don't come to my house and try to tell me what I should believe. There are people who believe in different things. RasTafarian believe Atse Haile Sellassie as a mesih. They even requested to be babtized in the name of Haile Sellassie.

   Again, go to your place and worship what you believe in. Leave my orthodox church alone, which have her own doctrine. I don't understand the point of argument. I know what I have to believe in!!!! don't "protest" on church, protest against devil and sin.

   Delete
  3. Jesus said ''Go into all the world and preach the gospel to ALL CREATION'' but yet you come out here and contradict his teaching by saying '' Believe what you believe, but don't come to my house and try to tell me what I should believe''. You have fallen victim to modern age philosophy conceived by atheist & alike to restrict the message of the gospel from spreading. You say ''haymanot yegel new'' but we mimic our Lord and reply ''haymanot lehulum new!!''

   Delete
 13. ጽጌ ማለት እኮ እንዳእናንተ አይዳለም እንደ እውነተኞቹ ሀዋርያት በጌታው ስም ብዙ መከራ የተቀበለ ነው፡፡ የሰይጣን ቅጥረኞቹ በሆኑ የማህበረ ቅዱስን ተብየዎች፡፡ እሱ ግን ክብሩና ዋጋው ከላይ ነው፡፡ ጌታ ሲማጣ የሚገባውን ክብር ከአባቱ ዘንድ ይቀበላል፡፡ አሁን የእርሱ ስራ ጌታውን በእውነት መግለጥ ነው፡፡ እንደ እናንተ በደላቀቀ ኑኖ የማይኖር ለጌታው ሲል ሁሉን የተዎ ነው፡፡ አዎ ለዚህ አለም ደሀ ሆኖ በኋላ ሊከብር ብድራቱን ትኩር ብሎ ተመልክቷልና እንደ አብርሃም፡፡ ጽጌ የተለየህለትተ ጌታ ጸጋውን በእምነት ያብዛል ሀይሉን ከቀደመው ይልቅ ያስታጥቅህ፡፡ ተባረክልኝ ወንድሜ ጽጌ በርቴ ሰልፍ የእግዚአብሔር ነውና፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. the lord will not stand for liars. it is one of the five sins that he mentioned in the revelation. this the so called mergetas are liars. why did they claim they are orthodox while they are clearly and loudly protestant. Liars liars liars

   Delete
 14. ኦ ጌታ ሆይ ተባረክ ቅሬታ ስላለህ ማንም የለም ብለው በጌታ እውነትና በህዝቡ ላይ ለሚቀልደው ገንዘብ ለመሰብሰብ ብሎው ህዝቡን ለሚያደናግሩ ማህበረ ቅዱሳን እን ጽጌን ስላስነሳህ ተመስገን፡፡ ጽጌ ተባረክልኝ ጌታ ይርዳህ ፀጋው ይብዛልህ፡፡

  ReplyDelete
 15. ይሄን ቪዲዮ ለማየት አልጉዋጉዋሁም!!ግን ብዙ ሰዎች በአስተያየት ስም ሲንጫጩ አየሁና ምሳየን ስበላ ጎን ለጎን ከምግቡ ጋር ተመለከትኩት!!እንደ እውነቱ ያን ያህል አዲስ ነገር የለውም!!ለዘመናት ነባር ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን የሚሰብኩትን ከመደጋገም በቀር!!እንዲያውም ለእኔ ኑፋቄን ከኑፋቄ ማወዳደር ባይሆንብኝ በጥልቀት ደረጃ ቀደም ሲል በሰላማ ብሎግ ከወጡ ጽሑፎችም ያነሰ ነው!!ለማንኛውም ትንሽ ልበል…
  1. ስለ 81ዱ መጻህፍት ብዙ ደስኩረዋል!!ልክ መጽሐፉ ድንገት ፕሮቴስታንቶች ሲመጡ የተጨመረ እንደሆነና ትርጉሙም እነ ጽጌ ጥያቄ እያነሱ ስላስቸገሩ ሆን ተብሎ እንደተቀየረ!!በዚህም ኦርቶዶክስ ከዓለም ተለይታ ከ66ቱ የመ/ቅዱስ ክፍሎች ውጭ ያላት ብቸኛ ቤ/ክ ሆና እንዳገኙዋት ጥናታቸውን አቀረቡ!!ድንቄም ጥናት!!ወትሮም ወድጄ አልነበረም ጥራዝ ነጠቅ ያልኩት!!ስህተታቸው እንዲህ ነው….
  2. ለእነሱ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ማለት ፕሮቴስታንት ብቻ ነው!!ባይሆንማ ቢያንስ የካቶሊኮች መ/ቅዱስ 72 እንደሆነ፣የምስራቅ ኦርቶዶክሳውያንም ከ72 የሚልቁ መጻህፍትን በመ/ቅዱሳቸው ክፍል እንዳካተቱ፣አንግሊካኖችም ከ66 መጻህፍት በላይ ቅዱስ ብለው እንደሚቀበሉ፣የኢኦተቤክ በዓለም ላይ ብቸኛ ጥንታዊ ቅጃቸው ግዕዝ የሆኑትን ኄኖክንና ኩፋሌን ጨምሮ 81 መጻህፍትን ቅዱሳት መጻህፍት ብላ ስለምትጠራ በዓለም ላይ መ/ቅዱስ 66 ብቻ ነው የሚል አስገዳጅ ድንጋጌ እንደሌለ ይረዱ ነበር!!ለመሆኑ መ/ቅዱስ ከ66 በላይ የለም የሚል አስገዳጅ ጽሁፍ አለ??እነ ጽጌ እባካችሁ እንግሊዝኛ ተማሩና ጎግል አድርጉ!!ያለበለዚያ የማታውቁትን ዓለም እየጠቀሳችሁ ዓለም የሚመራበት ማለት ጥራዝ ነጠቅ መሆን ነው!!
  3. እኛ ስላስቸገርን ኦርቶዶክስ ትርጉም ማጣመም ጀመረች የሚለው ድንፋታ ያስቃል!!ወይ አቅምን አለማወቅ ያሰኛል!!ለማንኛውም ግዕዝ የእንግሊዝኛ ልጅ አይደለም!!ቅድምና አለን!!እንግሊዞች ዋሻ ውስጥ እያሉ የእኛ ጃንደረባ ትንቢተ ኢሳይያስን አንባቢ የነበረ ስለመሆኑ ተጽፎልሃል!!ብሉይ ኪዳንም ሆነ ሐዲስ ኪዳን ወደ ግእዝ ሲተረጎም እንግሊዝኛ ቃለ እግዚአብሄር የሚነገርበት ቁዋንቁዋ ወደ መሆን አልደረሰም!!ታዲያ ይሄን ያህል እድሜ ጠገብ ቁዋንቁዋ እያለን ቨርዢኑን በየዘመኑ ከሚለዋወጠው እንግሊዝኛ መጽሐፋችሁን ከላጣጣማችሁ ትክክል አይደላችሁም ማለት ሳይቸገር ጤፍ ብድር የሚያስተርት ነው!!ብሉይ ኪዳንም ሆነ ሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ ሲጻፉ በእንግሊዝኛ ቢጻፉ ምን አልባት እንገደድ ነበር!!ለማንኛውም አዲሱ የአማርኛ 81ዱ መጽሐፍ ከአመታት ጥናት በሁዋላ ከግእዙ ጋር እንዲጣጣም ሆኖ የወጣው በ2000 ዓ.ም ማለትም እናንተ ተወግዛችሁ ከምዕመናን ኅብረት ከመነጠላችሁ 4 አመት ቀድሞ ስለሆነ በአጉል ጉራ አቡዋራ ለማስነሳት አትሞክሩ!!እሱ አጉል መታበይ ነው!!
  4. መቃብያንንም፣ኄኖክንም፣ኩፋሌንም እንዳሻችሁ እየተረጎማችሁ ለማጣረስ ሞክራችሁዋል!!ወደ ዝርዝሩ አልገባም!!ለማንኛውም የሚጣረስ አድርጎ ለማቅረብ ከተፈለገ እኮ ከ66ቱም ሳንወጣ በሐዋ ስራ 1 ቁ 18 ይሁዳ አንጀቱ ተዘርግፎ እንደሞተ የሚገልጸውን ቃል በማቴ 27 ቁ 5 ታንቆ እንደሞተ ከሚገልጸው ጋር እንደሚጣረስ አድርጎ መናገርም ይቻላል!!በማቴ 4 ለአምላክህ ስገድ ተብሎ ተጽፉዋል በሚል የተነገረውና በማቴ 27 ቁ 9 ኤርምያስ ተናገረው የተባለው ትንቢት በየትኞቹ የ66መጻህፍት እንደሚገኙ ብትነግሩን መልካም ነበር!!አትልፉ!!ጽሁፎቹን በ66ቱ ውስጥ አታገኙአቸውም - ወደ 81ዱ ካላማተራችሁ በቀር!!ስለዚህ እንዳሻችሁ ቃል ለመሰንጠቅ አትሞክሩ!!
  5. ስለድርሳናትና ገድላት አላስፈላጊነትና እነዚህ ጽሁፎች የጌታን ክብር የሚከልሉ ስለመሆናቸው ያችኑ እነ መሰረት ስብሐትለአብ ያቆዩአትን ነጥብ እየደጋገማችሁ ከሀንድ አውታችሁ ትጠቅሳላችሁ!!የሐዋርያት ስራ በራሱ የሐዋርያትን ገድል የሚተርክ መሆኑ እየታወቀ የእነሱ ተከታይ የሆኑ ቅዱሳን ታሪክ ሲነሳ ግን ደርሶ ማጣጣል ክርስትና ከሐዋርያት በሁዋላ ታሪክ እንደሌለው ለማሳመን መጣር ነው!!እሱ ደግሞ ከእውነታም ፣ከእ/ርም፣ ከታሪክም ጋር ያቃቅራል!!እ/ር እስከዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ ሲል ጴጥሮስና ጳውሎስ እስከዓለም ፍጻሜ እንደሚኖሩ ሊነግረን ፈልጎ አይደለም!!እንደዛማ እንዳንል የእኛ ይቅር እናንተም በየቸርቻችሁ እ/ር ድንቅ ስራ ሰራ እያላችሁን ነው!!
  6. ሩቅ ሳንሄድ በግራኝ እና በጣሊያን ወረራ ወቅት በአባቶቻችን የተፈጸመውን ገድል ማየት ቀላል እኮ ነው!!እና ይሄን ሁሉ ካዱት ተረት ነው ስትሉን ዐይናችሁን ጨፍኑና እናሞኛችሁ እንደማለት ሆኖ ይታየናል!!ቢያንስ አንዳንድ በድርሳናት እና በገድላት ላይ ያሉ ታሪኮች ለመቀበል ከከበዱዋችሁ እነሱ ላይ ጥያቄያችሁን አጠንክራችሁ ሌላውን ሙሉ ታሪክ ብትቀበሉ መልካም!!እናንተ ግን በቃ አንዱ አንቀጽ ስላልተመቸኝ ሁሉም ተቀዶ ይጣል ስትሉ ሳይ ጉዳዩ የእልህና የጥላቻ ሆኖ ነው የሚታየኝ!!በዚህ ላይ ተአምርን እንደ ተአምር ከመቀበል ይልቅ በሎጂክ ለመተንተን ስትንደረደሩ ስመለከት የነገረ ሃይማኖት እውቀታችሁን ቁንጽልነት እታዘበዋለሁ!!
  7. ለማንኛውም፤ፕሮቴስታንት መልስ ካላት እኝም እንጠይቅ…
  ሀ-ኢየሱስን የግል አዳኝ አድርገህ ተቀበል ብሎ ያሳመነ ሐዋርያ ካለ ከነጥቅሱ ንገሩን፣
  ለ-ያለጥምቀት ጌታን በመቀበል ክርስቲያን ስለመባባላችሁ አስረዱን፣
  ሐ-ሃይማኖት ያለምግባር ሙት ነው የሚለውን የያዕቆብ ቃል ተርጉሙልን፣
  መ-በ1ኛ ቆሮ 11 ቁ 4 ሴት ራሱዋን ሳትሸፍን እንዳትጸልይና ትንቢት እንዳትናገር የሚገልጸውን ቃል ከባለ ሚኒ እና ታይት ሴት ፓስተሮቻችሁ ድርጊት አንጻር ተንትኑልን፣
  ሠ-የነቢያቶቻችሁ ቁጥር ለስታቲስቲክስ መ/ቤትም ከማስቸገሩ በፊት ነቢይነትን ብታብራሩት፣
  ረ-የልሳንና የፈውስ ነገር ከዑቃቢ እያምታታን ነውና አንድ በሉት፣
  ሰ-ከባለ 2 ባህርይ ካቶሊኮች የተገኙት ፕሮቴስታንቶች ከእኛ ባለ 1 ባህርይ አማኞች ከወጡት መስማማታቸው ስለምስጢረ ስጋዌ ካለመረዳት ስለመሰለን አንድ በሉን፣
  ሸ-እመቤታችንን ወላዲተ አምላክ ለማለት የማትደፍሩበትን ም/ት አሳውቁን፣
  ቀ-በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ የሚለውን ቃል ሽሽት ም/ት አስረዱን፣
  በ-እኛ ኢየሱስ ጌታ ነው ስንል የባህርይ አምላክ ማለታችን ነው እስኪ የእናንተን የኢየሱስ ጌታ ትርጉዋሜ ግለጹልን፣

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hiruy, I have read in multiple sources that the Book of Enoch was considered uncanonical by church fathers in the early centuries and was rejected from the canon. What's your take on this? (they had many other manuscripts other than the geez so the geez translation was not the only translation left)

   Also in your opinion, which language is more reliable the Geez or the ancient Greek? (As it pertains to the scripture, more specifically the New Testament). If a passage in the Greek New Testament read differently than that of the geez, in your opinion which one is more reliable?

   Delete
  2. The presence of believing other than 66 books in one bible doesn't correct Ethiopian Orthodoxy's mistake ....The only truth bible is the one which has 66 books!!

   Delete
 16. ከመጠምጠም ትምህርት ይቅደም!!
  1. መጽሐፈ ኄኖክን የጠቀስክልኝ ወዳጄ ትክክል ነህ መጽሐፉ በሌሎች አብ/ክርስቲያናት የለም!!ብቸኛ ቅጅውም ያለው ኢ/ያ ውስጥ ብቻ ነው!!ይኄ ያኮራል እንጅ አያሸማቅቅም!!ምነው ቢባል (ሀ)መጽሐፉ በይዘቱ ከሌሎች ቅዱሳት መጻህፍት አይጋጭም፣(ለ)ሐዋርያው ይሁዳም ከ66ቱ ገብቶ በሚደመር መልእክቱ ቁ 14 ላይ ኄኖክ ም 1 ቁ 9ን ጠቅሶታል!!ልጥቀስልህ!!....ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ኄኖክ፡ እነሆ…..ኀጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፍ ቅዱሳኑ ጋራ መጥቱዋል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ….ሲል ተናገሮለታል!!እንግዲህ ዓለም በስንት ጦርነት ስታልፍ ቅርሶቹዋን ሁሉ አውድማለችና እኛ በስንት ትግል በብራና ገልብጠን ያስቀረነውን መጽሐፍ ካልጣላችሁ አንባልም፣(ሐ)ስለ መጽሐፈ ኄኖክ ከአኃት አብ/ክርስቲያናትም ሆነ ለዘመናት ከግብጽ ሲላኩልን በኖሩት ብጹአን አባቶች ወቀሳ ደርሶብን አያውቅም፣(መ)ከጥንት ጀምሮ በየጉባኤ ቤቶቻችን ሲሰጥ ነው የኖረው፣(ሠ)ቅ/ሲኖዶስ ቅዱስ የሆኑ መጻህፍትን በቀኖና የመደንገግ ስልጣን አለው፣(ረ)በፍ/ነገስትም ከቅ/መጻህፍት ጋር ተቆጥሩዋል!!ስለሆነም ስለ መጽሐፈ ኄኖክ ቤ/ክ ትወደስበታለች እንጅ አትወቀስበትም!!
  2. ከጥንታዊው ግሪክና ከግእዙ የትኛው ነው ለመ/ቅዱስ ትርጉዋሜ የሚያገለግለው ላልከው፡ጥንታዊው ግሪክ ለሐዲስ ኪዳን መጻህፍት ትርጉዋሜ ማመሳከሪያ ይረዳል፣ለብሉይ ኪዳን ደግሞ እብራይስጡ ይሻላል!!ለግእዙ መ/ቅዱስ ትርጉም ምንጮች በዋናነት ሁለቱ ናቸው!!እርግጥ ነው ከሶርያ እና ከጥንቱ ዐረብኛም ቀደምት ሊቃውንት ተጠቅመዋል የሚል እይታ አለ!!ዋናው ነገር እንግሊዝኛ ለግእዝ ትርጉም ምንጭ ሆኖ አያውቅም!!እነ ጽጌም እያወሩ ያሉት በግሪክ የተጻፈ ሐ/ ኪዳንና በእብራይስጥ የተጻፈ ብሉይ ይዘው አይደለም!!
  3. ስለ ግእዝና አማርኛ መ/ቅዱስ ለጠቅላላ እውቀት ያህል እንጠቁም….
  -ኢትዮጵያዊ ቤተ አይሁዶች በተለምዶ ፈላሾች ያላቸው መጽሐፍ በግእዝ ብቻ የተጻፈ መሆኑን ስናስተውልና በ14ኛው ክ/ዘመን የተነሱት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም በመጽሐፈ ምስጢር ብሉይ በዘመነ ኦሪት ወደ ግእዝ መመለሱን መጻፋቸውን ስናነብ ግእዝ ብ/ኪዳን አስቀድሞ ከተተረጎመባቸው ልሳናት ውስጥ መሆኑን እንረዳለን፣
  -ሐዲስ ኪዳንም እንዲሁ ከጉባኤ ኬልቄዶን(431) በፊት በነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን እና 9ቱ ቅዱሳንን ጨምሮ በሊቃውንት ከግሪክ፣ከጠንታዊ ሶርያ እና አረብኛ ቅጅዎች ወደ ግእዝ እንደተተረጎመ መዛግብቶቻችን ያስረዳሉ፣
  -አማርኛ መ/ቅዱስ በየብራናው ለየብቻው ተጽፎ ሲነበብና ከግእዙ ሲተረጎም ከኖረ በሁዋላ አንዳንድ የካቶሊክ ሚሲዮናውያን ከ16ኛው ክ/ዘመን ጀምሮ በራሳቸው መንገድ ለማሳተም መሞከራቸው ባይካድም ኢኦተቤክ በተሳተፈችበት መልኩ 66ቱ የታተመው በ1953 ዓ.ም ሲሆን በ1980 ዓ.ም ደግሞ የቀኖና(በተለምዶ አዋልድ)ተካተው 81ዱ ታትሞአል!!የ1980ው እትም ከግእዙ ጋር ለማጣጣም መሞከሩን በመግቢያው ገልጾ ዳግመኛም ሊታይ እንደሚችል ለሲኖዶስ ስልጣን ሰጥቶ ስለነበር እንደገና ሊቃውንት ተሰብስበው ግሪኩን፣እብራይስጡንና ሌሎቹን ጥንታዊ የመ/ቅዱስ መጻፊያ ቁዋንቁዋዎች ባገናዘበ መልኩ በ2000 ዓ.ም ተርጉመውታል!!እነ ፅጌና ሙሴ በኢ/ያ መ/ቅዱስ ማኅበር ድጋፍ የታተመውን የ1980ውን መ/ቅዱስ መግቢያ በደንብ አንብቡት!!ከመጠምጠም ንባብ ይቅደም!!ልምከራችሁ!!ኦርቶዶክስን በማብጠልጠል እንጀራ ማብሰል እነ ፓ/ር እንትናን ባለሀብት አድርጎ አልፎበታል!!ፕሮቴስታንቶቹም ሰልቸተውታል!!ይልቅስ ስለ ክርስቶስ ምትናገሩት ካለ ተናገሩ!!ከዚያኛው ከፕሮቴስታንቱ ወገንም የራሳችሁ አድማጭ ትፈጥራላችሁ!!ስጋችሁንም ትጠቅማላችሁ!!ጾም መጾም አቁማችሁ እንኩዋ ያልተመለሰው ሰውነታችሁም ያገግማል!!ያላችሁ እውቀት ማብጠልጠል ብቻ ከሆነ ግን በዚሁ ቢበቃችሁ ጥሩ ነው!!ያለበለዚያ የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባየ በሚለው ተረት እናልፋችሁዋለን!!
  4. መ/ቅዱስ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው ከ14ኛው እስከ 16ኛው ባለው ጊዜ ውስጥ ነው!!በዚህ ጊዜ ውስጥ ደግሞ እኛ መ/ቅዱሱን ከትርጉም ተሻግረን፣ ወደ ተግባር ቀይረን፣ ዮዲት ጉዲትን አልፈን ፣ከግራኝ መሐመድ ሰማዕትነት እየተቀበልን ነበር!! እናም ዛሬ ከእንግሊዝኛ ካልተጣጣማችሁ መጽሐፋችሁም ቅዱስ አይደለም እናንተም ክርስቲያን አይደላችሁም የሚሉን ሰዎች ሲገጥሙን እናዝናለን!!ካለማንበብ፣ከጥላቻ፣የራስን ከመናቅ፣ፈረንጅን ከማመን ብዙ ሲስቱ ስለምንመለከት!!ቢያስተውሉማ እነሱ ተረት የሚሉዋቸው ገድላት በስንትና ስንት ዶላር ተገዝተው ሂደው ዛሬ የአውሮፓ ላይብረሪዎች የእውቀትና የገንዘብ ምንጭ ሆነዋል!!ከፖርቱጋል ወታደሮች ጋር የመጡ የካቶሊክ ሚሲዮናውያንን ተከራክረን ስንረታ መ/ቅዱሳችሁ ከላቲኑ ትርጉም አይስማማም አልተባልንም!!
  5. ችግር የለም!!ትርጉሙ ያን ያህል የተለየ አዲስ ነገር የለውም!!አለው ካላችሁም ለንግግራችን የ1953ቱን ቅጂ መጠቀም ስለምንችል ወደ ሜዳችሁ እየወረድን እንነጋገራለን!!ጥራዝ ነጠቅ መናፍቅ በተነሳ ቁጥር ቅ/ሲኖዶስ ይጠራና እንከራከር ማለት ግን አጉል ድፍረት ነው!!የእናንተ ሃይማኖት በየቀኑ ይራባልና ሲኖዶስ ስራ ፈትቶ እናንተ ጋር ሲወጋገዝ አይኖርም!! በቀደመ ኑፋቄ የሚራመድ ካህን ካለና ይህ ካህን ወይም ሰባኪ በቤ/ክ ሆኖ ኑፋቄውን በማራመዱ ተገስጾ ካልተመለሰ መለየት ነው!!ሲኖዶስ በአማላጅነት የማያምን ትውልድ በመጣ ቁጥር አይሰበሰብም!!በዚህ ጉዳይ ላይ እንደ ሃይማኖት ተቁዋም አቁዋማችን ግልጽ ነው!!የለም በዓውደምሕረቱ እቀጥላለሁ የሚል ቢኖር እጣው ሰማዕት ዘበከንቱ መሆን ነው - እዚህ ጋ ዓለማዊው ህግም ለጸጥታ ሲል ከእኛ ጋር ይቆማል!!

  እኛም እንደ እናንተ በጉባኤ ቃና እንዝጋው…ተቀበል…
  ሙሴ ህጻን ዘበፅጌ ፈለግ ተገድፈ፣
  ምድረ-ርስት አሚነ እንዘ ኢይሬኢ ሀለፈ!!

  ዐይነልቡናችንን ያብራልን!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Way way before "fiteha negest" even existed, in the year 325 A.D. there was much discussion as to which scriptures and gospels to be included in the Holy Bible and which ones to be excluded. The Book of Enoch was disfavored because of its controversial statements on the nature and deeds of the fallen angels. This is not my decision. These are St. Athanasius and the 318 fathers of the church that made the decision by the guidance of the Holy Spirit; the same fathers that denounce Arius and his heretical teachings. I just wanted to know your opinion but it seems you resorted to name calling.

   Good day

   Delete
  2. TO: Dear Anonymous March 20, 2014 at 10:01AM
   No fear or favor!! I wrote what I believe and what I know!! I'm ready 2 accept any evidence that rebut my argument!! SO, please forward ur evidence/reference be it in website or hard books which support ur position!! Especially; I will be happy if u quotes a condemnation from St. Athanasius on EOTC for its use of Book of Enoch with other canonized Holy Books!! As u knows St. Athanasius was also the patriarch of EOTC, he was and is our father!!
   ስለ ወደቁ መላእከት ባህሪ ጥቂት ተናግረን እንለፍ፡፡አንዳንድ ሰዎች መጽሐፈ ኄኖክን ስለወደቁ መላእክት ያልተገባ ነገር አለው ብለው ይተቻሉ፡፡አባቶች ለንባቡ የሚሰጡት ትርጉዋሜ እንዳለ ሆኖ ለእኔ ያልተገባ የሚባል ንባብ የለውም፡፡አለው ከተባለም ከ81ዱ በመደመሩ የመጣ አይደለም፡፡እንዲህ አይነት አመለካከት በቀደምት ሊቃውንትም ተንጸባርቁዋል፡፡አጨቃጭቋል፡፡ለጊዜው ሊቃውንቱንም ሆነ 81ዱውን እናቆያቸው፡፡ወደ ሜዳው እንውረድ!!ከ66ቱ መ/ቅዱስ የይሁዳ መልእክት ስለጉዳዩ የሚለውን እናንብብ፡፡የይሁዳ መልእክት ቁ 6 እስከ 7 እንዲህ ይላል…
   "6፤መኖሪያቸውንም፡የተዉትን፡እንጂ፡የራሳቸውን፡አለቅነት፡ያልጠበቁትን፡መላእክት፡በዘለዓለም፡እስራት፡ከጨ ለማ፡በታች፡እስከታላቁ፡ቀን፡ፍርድ፡ድረስ፡ጠብቋቸዋል።
   7፤እንዲሁም፡እንደ፡እነርሱ፡ዝሙትን፡ያደረጉና፡ሌላን፡ሥጋ፡የተከተሉ፡ሰዶምና፡ገሞራ፡በዙሪያቸውም፡የነበሩ ፡ከተማዎች፡በዘለዓለም፡እሳት፡እየተቀጡ፡ምሳሌ፡ኾነዋል።"
   እንግዲህ ከላይ “እንዲሁም እንደነእርሱ” ተብለው ለሶምና ገሞራ ሰዶማዊ የዝሙት ድርጊት ማንጸሪያ የሆኑት የወደቁ መላእክት ናቸው፡፡ስለዚህ ስለወደቁ መላእክት የዝሙት ባህሪ የሚያወራው መጽሐፈ ኄኖክ ብቻ ሳይሆን ቁጥሩ በማቴ 19 ቁ 28 በ12ቱ ነገደ እስራኤል ላይ ትፈርዳላችሁ ከተባሉት ወገን የሆነው ሐዋርያው ይሁዳም ጭምር ስለሆነ መፍትሄው ጉዳዩን ማጥራት እንጅ መጻሕፍትን መቆንጸል ሊሆን አይችልም፡፡
   ወዳጄ ስለ አስተያየትህ ያለኝ ክብር አይጉዋደለም!!ሙሉ ነው!! “…but it seems you resorted to name calling!” ያልካት ነገር አንዳንዴ ሰዎችን በሰውነታቸው ብቻ ሳይሆን በድርጊታቸውም መግለጽ ስለሚገባ ነው ያደረኩት፡፡as a result I have no regret for doing that!!
   Stay blessed my brother!!

   Delete
  3. በሉተር አምበልነት የምትመሩት ቡድን 66ቶች ግዴለም ኄኖክን ተውት ይቺን ጥቅስ አንብቧትማ!!ታዲያ….ይሄማ እንዲህ ለማለት ተፈልጎ ነው…ብትሉን አንሰማም!!ራሳችሁ አንድምታ ትርጉዋሜ አያስፈልግም ሁሉም አማኝ እንደመሰለው መ/ቅዱስን መረዳት ይችላል ብላችሁዋል!!በህጋችሁ ተዳኙ!!

   _______________ኦሪት፡ዘፍጥረት፥ምዕራፍ፡6።______________
   ምዕራፍ፡6።
   1፤እንዲህም፡ኾነ፤ሰዎች፡በምድር፡ላይ፡መብዛት፡በጀመሩ፡ጊዜ፡ሴቶች፡ልጆች፡ተወለዱላቸው፤
   2፤የእግዚአብሔር፡ልጆችም፡የሰውን፡ሴቶች፡ልጆች፡መልካሞች፡እንደ፡ኾኑ፡አዩ፤ከመረጧቸውም፡ዅ ሉ፡ሚስቶችን፡ለራሳቸው፡ወሰዱ።
   3፤እግዚአብሔርም፦መንፈሴ፡በሰው፡ላይ፡ለዘለዓለም፡አይኖርም፥ርሱ፡ሥጋ፡ነውና፤ዘመኖቹም፡መቶ ፡ኻያ፡ዓመት፡ይኾናሉ፡አለ።
   4፤በእነዚያ፡ወራት፡ኔፊሊም፡በምድር፡ላይ፡ነበሩ፤ደግሞም፡ከዚያ፡በዃላ፡የእግዚአብሔር፡ልጆች ፡የሰውን፡ሴቶች፡ልጆች፡ባገቡ፡ጊዜ፡ልጆችን፡ወለዱላቸው፤እነርሱም፡በዱሮ፡ዘመን፡ስማቸው፡የታ ወቀ፡ኀያላን፡ኾኑ::

   Delete
 17. አይ ህሩይ በጥምጥም የምታምኑትማ እናንተ ናችሁ አረ አስተውል እስቲ አንተ አውነት የጌታ ቃል የገባህ ከሆንክ ለምን ለየጠየቁህ ነገር መልስ አስተጥም፡፡በነጣላና በስርዓት የምታምኑ አዲስ ኪዳን መጥቶ ገና ብሎይ ላይ ያላችሁ እናንተ ናችሁ፡፡ እነሱም ወንጌሉን የቤ/ክ መጽሐፍትን በደንብ የተረዱ ናቸው፡፡ ለዚህ እኮ ነው ድፍረት ስላጣህ ቢሎግ ላይ በመጻፍ ሰውን የምታደናግረው፡፡ ለማንኛው ጌታ ሲመጣ እንደዚህ እንደፈለጉ ማውራት የለም ፊቱ አስፈሪ ነውና፡፡ እውነትን ብትይዝ ይሻልሀል ወንድሜ፡፡ ጌታ ማስተዋልን ይስጥህ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. 1. አንቺ ሴት አንዴ ሰላም፣አንዴ ሄለን፣ሌላ ጊዜ ሳምራዊት እያልሽ የስድብ ሜኑ ከመደርደር ውጭ ቃለ እግዚአብሄር ስትናገሪ አላይሽም፡፡ከላይ የተቀመጠውን ቪዲዮም እንደ ብዙኀኑ አስተያየት ሰጭዎች ሁሉ ያየሽው አልመሰለኝም፡፡ይሄውልሽ ካለወቅሽ ዝም በይ!!ካወቅሽ ያስቀመጥነውን መልስ ተመልከችና ያልተመለሰልሽ ጥያቄ ካለ የምትይውን በይ!!ከዚህ ውጭ በቲፎዞነት ብቻ መጮህ አግባብ አይደለም፡፡ብሎጉንም ረከቦት አናድርገው!!ብሎጉ ለእኔም ላንችም ክፍት ነው፡፡… ድፍረት ስላጣህ ማደናገር… ማለት አልገባኝም!!እንደ አንቺ አይነት ከወጡ በኋላ ወደኋላ እየተመለሱ ለሚደናገሩ የጠፉ በጎች እኔ አልጠየቅም!!ለድፍረቱማ እንግዲህ ከጦርና ጎራዴ ውጭ እነሱ በተጠቀሙበት ቋንቋ ሁሉ እየተጠቀምን እንደ ኦርቶዶክሳዊ አቋምችንን እየገለጽን ነው!!ከመጠምጠም ትምህርት ይቅደም ያልነውም እነሱ የሳቱትን እያመለከትን ነው!!
   2. ይሁውልሽ እህቴ የብሉይ ኪዳን አለባበስ በሐዲስ ኪዳን ተቀይሯል የሚል ጥቅስ የለም፡፡ይልቅስ ይቺን ጥቅስ አንብቢያት 1ኛቆሮ 11ቁ4….ራሷን፡ሳትሸፍን፡ግን፡የምትጸልይ፡ወይም፡ትንቢት፡የምትናገር፡ሴት፡ዅሉ፡ራሷን፡ታዋርዳለች፤እንደ፡ተላጨች፡ያኽል፡አንድ፡ነውና።
   ፤ሴትም፡ራሷን፡ባትሸፍን፡ጠጕሯን፡ደግሞ፡ትቈረጥ፤ለሴት፡ግን፡ጠጕሯን፡መቈረጥ፡ወይም፡መላጨት፡የሚያሳፍር ፡ከኾነ፡ራሷን፡ትሸፍን።
   3. ይሄ የሐዲስ ኪዳን ሕግ ነው፡፡አንቺ ወደ ቸርች ስትሄጅ ልክ እንደዚህ የሐዲስ ኪዳን ሕግ እየተራመድሽ ከሆነ እኛን ኦሪታዊ የምትይው ደስ ይላል፡፡ለማንኛውም ስለ እኛ አለባበስ መ/ቅዱሳዊነት ማወቅ ከፈለግሽ ዘሌዋውያን 8ን አንብቢው፡፡እሱ የአለባበስ ህግ በሐዲሱም አልተሻረም፡፡በተረፈ ኦርቶዶክስ የሚል ቃል በሰማሽ ቁጥር እንደ በለዓም ስራሽ መራገም ከሆነም ቀጥይበት፡፡በነገርሽ ላይ ነጠላ ለብሶ በሥርዐት እየተራመዱ በቤ/መቅደስ ማገልገልን ነቅፎ በሚኒ እና በታይት ያለስርዐት መራመድን የሚፈቅደው ሃይማኖትሽ አስቀንቶኛል!!ፐፐፐ…ለካ እነ ሰሎሜ፣እነ ሊዲያ፣እነ ማርያም መግደላዊት እንዲህ ነበር የሚለብሱት!!ወይ አለማወቄ!!
   እንግዲህ የጌታን ምጽአት በጉልህ የምንዘክርባት ደ/ዘይት የፊታችን እሐድ ናትና ለእሱ የአገልግሎት ዝግጅት ስላለብኝ ለጊዜው ከዚህ በላይ የምልሽ የለም!!

   Delete
  2. ህሩይ አሁንም መልሰ አልሰጠህም እነ ጽጌ ያሉት ብዙ ነዉ አንተ ግን አንዱንም አልነካህም ለመሆኑ የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተቅማጥ በምን መስፈርት ከጌታ ስቅለት ጋር ይመዛዘናል ደግሞስ እመቤታችን የወደደችዉ ሰዉዬ በማግባቱ የምትቀና ተራ ሴት አድርጋቸዉ ታምራተ የምትሉትስ ፍጥረተ ሁሉ እርስዋነ ለማመስገን ተፈጠረ የምትሉትስ ይህንን ሁሉ አይተህና ሰምተህ አዉቀህ ከሆነ ስለ አሁንዋ ኦሮቶዶክስ የምትከራከረዉ ከእንግዲህ አልሰማህም

   Delete
  3. asnaku....lemehonu hiruy kelay yesetewn mels anbibeshal wey?

   Delete
  4. በሚገባ አንብቤአለሁ!! እኔ ጉዳዬ ከሥርዐት ጋር ሳይሆን ከጌታችንን የማዳን ሥራን ከሚያክፋፋዉ የገድሎች እምነት ጋር ነዉ፡፡ አሁንም እኔ ቤተክርስቲያን መሄዴን አልተዉም፡፡ ግን ፀሎቱንና ቅዳሴዉን edit አድርጌ ነዉ ጌታዬን ብቻ የማመልከዉ፡፡ እማዝነዉ ለልጆቼና ለልጅ ልጆቼ አፌን ሞልቼ ስለሚነግሱት ቅዱሳንና መላዕክት መናገር አለመቻሌና መሸማቀቄ ነዉ፡፡ ወላ ሂሩይ ወላ ማቅ እንደኛ ላሉት በቅንነት ለማወቅ ለሚፈልጉት መልስ አልሰጡም፡፡ በመጠየቃችን የተረፈን ስድብ ብቻ ነዉ፡፡ እሱን ደግሞ ለልጆቼ አላስተምርም፡፡

   Delete
  5. Asnaqu ...gedl le haymanot kirkir yeminteqembet aydelem. betechemarim gedl ye telewawachu sew dirset new...yihun enji qidusan sertewtal yetebalewn hulu alserum malet aychalim...Be Egiziabher hayl yemaydereg yelemna!... sihtet ale ketebalem yesew dirset silehone sihtet yelelew new malet aychalim..sihtetun yemiarmew gin yebetekirstian abatoch enji tsigie weym musie weym enie weym degmo asnaqu anhonim...yegna halafinet abotachahinin meteyeq ena mabrariya mesmat new...Hiruy betam yeteleqe ewqet yalew wendim new..yilqis ke elhina ke tilacha be melaqeq ke hiruy binimar yiteqmal enji aygodam.... lemehonu ye Ethiopia Orthodox Tewahdo Church teketay lemehonachin ye emnet maregagechachin mindnew? ke betekirstianua emnet ena sirat wust masaterna masrezem endihum meqenesna mechemer yemichlew manew? le lijochish masebish tiru new..gin welaj kaldane ena yeterawn emnet kalyaze yelij eta fenta gilts new....

   Delete
  6. Dear አስናቀች የሉቃስ ወንጌል
   7፥28 እላችኋለሁ፥ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም: Do you think Jesus is great than John? I hope you don't say Jesus is not born form a woman. After reading this why you are a Protestant?

   Delete
  7. ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል which means ፍጥረተ ሁሉ (ትውልድ ሁሉ) ያመሰግንኛል ማለት ነው

   Delete
  8. አስናቀች- Have ever read this vers "ወንድሞች ሆይ፥ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።"

   Delete
  9. Sister አስናቀች This one of our የገድሎች - የሐዋርያት ሥራ
   5፥15 ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር። I hope you don't say to ጴጥሮስ ከጌታችንን የማዳን ሥራን ይከፋፍላል

   Delete
  10. ታዲያ ሕዝቡ ሲሰግድላቸዉ የመለሱትን ምነዉ ተዉከዉ፡፡ እኛ እኮ ያዉም አሁን በገድላቸዉ ብቻ ለምናዉቃቸዉ ነዉ ግንባራችን እስኪላጥ ተደፍተን የምንሰግደዉ፡፡ ጌታ ይህንን በማድረጋችን ይቅር የሚለን ይመስላችሁዋል እንጸልይ ንሰሐ እንግባ

   Delete
  11. Asenakech. what are you talking about? you are practicing what you dont believe? shame on you. you are a disgrace for your kids. YOU ARE JUST ONE BIG LIAR.

   Delete
 18. Am with you Asnaku some times yemebetachen tamerat eyalu yemiyanebut neger betam new yemigermgne...bizu bejesus timeless Yalhon negeroch yinebebalu .

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ante belibih hasab bicha yemitkor yegeta teamirat bicha newu inde metshaf kidus wust yetesafe.yeimebetachin teamirim ale iko lemina wuhawu wed weyn sitaskeyir,Petros betilawu sifewus,Yohannis getan siyatemk.gebriel zekariyasn silegum,Mikael israeln simera.indiyawum atasmerirut yikir aylimina yetebalelet.Geta inanen yetekebele inen tekebele,inen yetekebele yelakegn tekebel(mat:!0)bilwal.Birsu yemiyami kirsu belay teamiratin indemiyareg irasu iyesus kirstos ttenagrual.kimnetachin sihtet yelem kenantewu astesaseb newu inji

   Delete
 19. እረ አስተውሉ አስናቀች እያለች ያለችውን ነገር አላሽተዋልችሁም እኮ የነጰውሎትን አምላክ አምልኩ ቅድስናና ፀጋን ለእነሱ የሰጠውን የጌቶች ጌታ የሆነውን አምልኩ ጸጋ ሰጭውን እንጁ ፀጋን አታምልኩ ነው ያለችው ይህ ደግሞ የዘላለም እውነት ነው ይህንን ካላደረግን አንድንም፡፡ ከዋናው ምንጭ ጋር ሁኑ ወራጁን አትቅዱ ያ ወደ እውነትና መዳን አይደርስም እውነተኛ የወይን ግንድ እኔኝ ብሏል ጌታ፡፡ ጌታ እኮ የነ ጴጥሮስ አምላክ ነው እነሱም እርሱ እንዲከበር ነው በዘመናቸው ሁሉ የሰሩት ይህንን እናንተ የምትሉትን ለማወቅ አሁን አይችሉም እንጂ ይታዘቧችሁ ነበር፡፡ እነሱም ተናግረዋል አሁን ከእውቀት ከፍለን እናውቃለን ብለዋል፡፡ ሙሉ እውቀትና በሁሉ ያለ እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ወገኖች ሆይ ትድኑ ዘንድ ማሰማት ያለባችሁን በማስተዋል ስሙ ሁሉ በቃሉ መዝኑ ለቁጣ አትቸኩሉ ማስተዋልን ይስጠልን፡፡ አባ ሰላማ ተባረኩ የዚች ቤ/ክ ትንሳኤ ማርሷልና፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከአስናቀች፤
   እደግመዋለሁ።እኔ ያልኩት ብዙ የኛ ቤተክርስቲያን አማኞች በልባቸዉ የሚያነግሱት ጸጋዉን የተቀበሉትን ነዉ እንጂ ጸጋ ሰጪዉን አይደለም። ይህም የሚገለጸዉ፤ አቡዬ፣ እመቤቴ፣ ገብርኤል፣ ሚካኤል እንዲህና እንደዚያ አደረጉልኝ፤ አመስግኑልኝ፤ ምሥጋና ይገባቸዋል፤ የሚሉ ለቁጥር የሚያታክቱ ምዕምናን ስላሉ ጌታችንን እያስቀኑ ስለሆነ የባዕድ አምልኮ ነዉ እያልኩ ነዉ። ጌታ ትናንት በሐዋሪያት ላይ የሰራዉን ዛሬ አይሰራም አላልኩም፤ ደግሞ በየገድላቱ የተጻፋት ሁሉ ልክ አይደለም አላልኩም፤ ግን በመጽሐፍ ቅዱሳችን መለካትና ጥፋት ያለባቸዉ ከቤተክርስቲያን መወገድ አለባቸዉ ማለቴ ነዉ። እነ ጴጥሮስ ተአምር በመሥራታቸዉ ሕዝቡ ቢሰግድላቸዉ ልብሳቸዉን እየቀደዱ እኛ ደግሞ እንደናንተ ሰዎች ነን ብለዉ መጮሃቸዉስ ክብር ሁሉ ለባለጸጋዉ ጌታ ብቻ መሆኑን ለመመስከር አየደለምን? እኛ ዛሬ ምን እያደረግን ነዉ ኩክ የለሽ፤ተአምረኛዉ ገብርኤል፤ ታምረኛዉ ኡራኤል ወዘተ በማለት ዝማሬ፣ ምስጋናና ዕልልታ ለነዚህ ፍጡራን እያደረስን አይደለም? ምነዉ እነሱን ለፈጠራቸዉ ጌታ ሩቡ እንዲደርስ የማትከራከሩለት? ጌታ እኮ ለምድራዊ ቁሳቁስ ሳይሆነ ራሱን ሰዉቶ በደሙ ያደነን ንጉሰ ነገስት ለየትኛዉ ልመናችን ጆሮ ዳባ ልበስ ለማለት ሞከረና ነዉ ፍጡራን ናቸዉ ያደረጉልን ብለን የምናሳዝነዉ?ደግሞስ ገና ለገና «የዓይኑ ቀለም አላማረንም» እየተባለ ብዙ ሰባክያነ ወንጌል ተወግዘዉ ተባርረዉ የለም? ይህንን እነ ህሩይ አያዉቁትምና ነዉ ኢ-ክርስቶሳዊ ለሆኑ ገድላትና የአምልኮ ሥርዐት የሚሟገቱት?
   እኔ በሐቅ ላይ የተመሰረተ መልስ እንጂ የተቆነጻጸለ ጥቅስና የእጅ አዙር መልስ አልፈልግም፡፡ አሁን ለጠየቅሁት ህሩይ ትሆን ሌላ ሰዉ ግልጽ መልስ እፈልጋለሁ፡፡

   Delete
  2. iyitachin Asnakech ? lojiksh tiru newu neger gin behaymanot bota lojik ayseram.Bemetshaf kidus kidusan malet Igziabiher malet newu.Irasu kidus hono kidus aderegen,Irsu lij hono,lijoch aderegen.yekidusan madan yesitota siyon,yeigziabiher madan degmo yebhiriyi newu.Betekiristiyan ferwan yemitisit aydelechim.Gbriel sinil meliak bilen inerawalen inji getachin medhanitachin iyesus kiristos anilim,atsaachi.
   asrejiwoch
   1.Daniel.kemikael beker yemiyasnany yelem maletu igziabiher ayatsenam malet newu?
   2.Yohanis lemelaku yesegedwu sayawuk kerto newu?wengelawi,balemelikt,baleraiyi yenebere newu iko.meskelu sir bichawun yetegegn iko newu.Irsu sigdet yigebal bilo kesegede manewu aygebaam malet yemichleu
   3.Leabrham silase besost sewoch amsal tegeletu,wedelot sihedu degmo bemelaikt honu lotim segedelachewu
   4.geta lehawariyat bemidir yaseracchihut besemay yetasere yihonal bemidir yefetachihut besemay yetefeta yihonal yilal
   5.Matewos wengel lay nebiyin benebiy sim yetekebele yenebiyun waga yagegnal yilal.Ignam indezihu nen(10:
   6.Kidus pawulos kidusan indemiyamalidu bekorontos meliku 9:13-15 lay tsfal.indiyawum silemayneger sitotawu igziabiher yimesgen bilo newu yezegawu.
   Beachiru betekiristiyan kemetshaf kidus befit yeneberech na yemitnor nat.lematakesha kidmiya betekiristiyan inji pirotestantot b16 kiflezemen yatsfut,yebrezut metshaf mehon yelebetm.mesthaf kidus kelay balut tiksoch aykawemen.Atilfi ishi?

   Delete
 20. በመጀመሪያ መታወቅ ያለበተ ነገር ለእገዚአበሔር ማንም ጠበቃ ሊሆን እንደማይችል ነው!!! ስለዚህ እንደተጠያቂ ከቡድን መንፈስ ወተን እናውራ!!!!! ክርስትናችን ያስከፈለው የክርስቶስን ደም እንደሆነ ሁላችንም እናምናለን ኣይደል? ስለዚህ ለወንጌል የተገባ ኑሮ እንኑር ካለበለዚያ ግን ጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጠራላቹ ውስጣቹ ግን ክፋትሞልቶበታል ከተባለላቸው ፈሪሳውያን ምንም አንለይም፣፣ እርስ ብእርስ ስንካሰስ እስልምና በቁማችን እንዳይወርሰን የዘውትር ስጋቴ ነው!!!!!

  ReplyDelete
 21. who is the owner of this blog we know your aim

  ReplyDelete
 22. ሰላም መጠየቅ ይቻላል?

  ReplyDelete