Friday, March 14, 2014

ፍርድ ቤት ችሎት ላይ አይደለም የተቀመጠው “አሜን!” የማይለው፡፡ምንጭ፡-http://awdemihreet.blogspot.com/
        ከዲ/ን ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
(መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ወደ አውደ ምህረት ከተመለሰ በኃላ እርር ያሉት የማቅ ብሎጎች እሱን “መናፍቅ” ለማለት የሚያስችለን ነው ብለው ያመኑበትን ስድ ስድብ እየደረደሩ ይውጣልን ይጥፋልን የሚያሰኝ ዛር ነግሶባቸው እየተክለፈለፉ ይገኛሉ፡፡ መቸም ለዲያቢሎስ ጭንቀቱ የሚድነው መብዛቱ እና የሱ መንግስት ጠላቶች የመንግስቱን ሀሳብ ሲያፈርሱ ማየት ነው፡፡ ተከታዮቹም በጌታቸው መንግስት ላይ የተቃውሞ ሀሳብ ያለውን ክርስቲያን ሁሉ ማሳደድን እምቢኝ ብለው አያውቁም፡፡
ለማኅበረ ቅዱሳን መሪዎች የዲያቢሎስን አሰራር ለማፍረስ በተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅ አምኖ የዲያቢሎስን አሰራር ለማፍረስ የሚንቀሳቀስ ክርስቲያን ሁሉ ጠላታቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው ሰሞኑን በሁሉም ብሎጎቻቸው እንደገና መጋቤ ሐዲስ በጋሻው ላይ መዝመት የጀመሩት፡፡ የወላይታ ሶዶው ጉባኤ እንዳይካሄድ ያደረጉት ጥረት ሁሉ  ከሽፎ ጉባኤው ከፍተኛ ህዝብ በተገኘበት መካሄዱ ቢያቃጥላቸው “ስህተት” ብለው ያገኙትን ነገር ነቅሰው አወጡ፡፡ ታዲያ በማቅ መመዘኛ ትልቁ ምንፍቅና በ10 ደቂቃ 20 ጊዜ አሜን ማለት ሆኖ ተገኘ፡፡ ከታወሩ አይቀር እንዲህ ነው እንጂ!!!
ዲ/ን ሙሉጌታ ወልደ ገብርኤል አሜን ለምን ይባላል አሜን ማለት የሊቅነት ማነስ ውጤት ነው የሚለውን የአንድ አድርገን ዘገባ እንዲህ ይተቻል፡፡ መልካም ንባብ!! )
ነዋሪነታቸው ጀርመን ፍራንክፈርት  የሆነ አንድ በአካባቢው የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ ምእመን ባሳለፍነው ሳምንት በኢሜይል አድራሻዬ “ … እርስዎስ ምን ይላሉ?” ሲሉ ነበር የጠየቁኝ። አያይዘው ከላኩልኝ ሊንክ በተጨማሪ ለይተው አውጥተው አስተያየቴን የጠየቁበት ጽሑፍ እንደሚከተለው ይነበባል።
ሊቃውንቱ ሲሰብኩ ሰው ወደ ውስጡ እንዲመለከትና በጥሞና እና በአስተውሎ የእግዚአብሔር ቃል እንዲያደምጥ ሲያደርጉ ነበር እኛ የምናውቀው፤ አሁን አሁን በአስር ደቂቃ ጊዜ ውስጥ 20 ጊዜ በላይ ‹‹አሜን›› የሚያስብለውን ሆነ ‹‹አሜን›› በማያስብለው ምዕመኑን ጮኻሂ የማድረግ አዝማሚያ እየታየ ነው፤ መናፍቃን ቤት የሚገኝው ጩኽት እኛ ቤትም ለመግባት ደጃፍ ላይ እያኮበኮበ ይገኛል፡፡[http://www.andadirgen.org/2014/02/blog-ost_5495.html]
እኚህ ወንድም አያይዘው በላክሉኝ መልዕክት የእግዚአብሔር መንጋ ለመበተን የሌሊት እንቅልፍ የማያውቀው ራሱንማኅበረ ቅዱሳንበማለት በሚጠራው ቡድን የሚዘወርአንድ አድርገንየተባለ መካነ ድር ነበርና ከዚህ የሽፍታ ድረ ገጽ ያነበቡትን ጽሑፍ ተንተርሰው የተፈጠረባቸው ጥያቄ ሲጨመቅ ፍሬ ነገሩ እንደሚከተለው አቅርቤዋለሁ።

የመጀመሪያ ጥያቄአቸው በደረቁ በስብከት ጊዜ አሜን ማለት ይቻላል አይቻልም?” አክሎውም የሚቻል ከሆነስ በአንድ ስብከት ውስጥ ስንት ጊዜ ነው አሜን ማለት የሚቻለው?” ባነበቡት እንግዳ ትምህርት የተደናገጡ ስለሆነም ለመሆኑ አሜን ማለት ምን ማለት ነው? አሜን የአማርኛ/የግዕዝ ቋንቋ ነው ወይስ ከሌላ ቋንቋ የተገኘ ቃል?” በማለት በአሜን “… ዙሪያ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ትምህርት ያካፍሉን ዘንድ በትህትና እጠይቃለሁ። እግዚአብሔር አገልግሎትዎን ይባርክ።ስም አለው።!

በስብከት ጊዜ አሜን ማለት ይቻላል አይቻልም?”

መልሱ ግልጽና አጭር ነው። የእግዚአብሔር ቃል ተገልጦ በሚነገርበት ስፍራ፣ የህይወት ቃል በሚሰበክበት ጊዜ ሰሚ ከመባረኩ የተነሳ ደስ እያለው ይሁንታውን በእልልታ ከፍ ባለ በታላቅም ድምጽ አምላኩን ያመሰግን ዘንድ የተገባ ነው። ምነው ቢሉ ምዕመኑ በአምላኩ ፊት አንጂ ፍርድ ቤት ችሎት ላይ አይደለም እና የተቀመጠው። እየተነገረ ያለው ቃል ሕያው፣ የሚሠራ፣ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ፣ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ የሚወጋ፣ የልብንም ስሜትና አሳብ የሚመረምር የእግዚአብሔር ቃል ነው።
የተደረገለት፣ የገባው፣ የምህረት እጁ የዳሰሰችው ከመንፈስ ቅዱስ በሆነ በደስታ በእግዚአብሔር ፊት ይቅለጥ። ዳኛው እግዚአብሔር ነው። ታድያ ጭብጨባ፣ አምልኮ፣ ዕልልታና ውዳሴ ከሰማይ ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም ተብሎ ማንነቱ የተመሰከረለት ለእግዚአብሔር ልጅ ለኢየሱስ ብቻ ነው። በታላቅ ጭኸትና በደስታ በጭብጨባ ከማምለክና የምስጋና መስዋዕት ካቀረብክ አይቀር ዋጋ ለሚያሰጥ ለእግዚአብሔር ልጅ ለኢየሱስ ክብር አድርገው። ቅድሳት መጻህፍትም የሚመሰክሩት ይህንኑ ሐቅ ነው።

አህያይቱንና ውርንጫዋንም አመጡለት፥ ልብሳቸውንም በእነርሱ ላይ ጫኑ፥ ተቀመጠባቸውም። ከሕዝቡም እጅግ ብዙዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፥ ሌሎችም ከዛፍ ጫፍ ጫፉን እየቈረጡ በመንገድ ላይ ያነጥፉ ነበር። የሚቀድሙትም ሕዝብ የሚከተሉትም። ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር። ወደ ኢየሩሳሌምም በገባ ጊዜ መላው ከተማ። ይህ ማን ነው? ብሎ ተናወጠ። ሕዝቡም ይህ ከገሊላ ናዝሬት የመጣ ነቢዩ ኢየሱስ ነው አሉ።(የማቴዎስ ወንጌል 21 7-11)

መጽሐፍ ቅዱስመጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ 1529 “የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰ ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች ንጉሡም ዳዊት ሲዘፍንና ሲጫወት አይታ በልቧ ናቀችውካለ እና ሊናቁ የሚገባቸው ናቁ ብሎ ከነገረን ማኅበረ ቅዱሳንደግሞ ‹‹አሜን›› ‹‹አሜን›› ማለትየመናፍቃን ነው!” ቢል ምን ይደንቃል? “ማኅበረ ቅዱሳንእንደሆነ የቅዱሳን ደም ለማፍሰስ ካልሆነ በስተቀር የእግዚአብሔር ስም አንስቶ እግዚአብሔርን ለመባረክና ለማመስን አሜን አይልም። በየት አልፎ? የኢየሱስ ጌትነትና አምላክነት ለማወጅ የኮሌጅ ዲግሪ ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ነው የሚጠይቀው። ማኅበረ ቅዱሳንደግሞ ይህችን ኬላ ማለፍ አይችልም።

ሊቃውንቱተብሎ የሰፈረው ቃል ይመልከቱልኝማ። አይተውልኛል? ለመሆኑ እነዚህ ሊቃውንት እነማን ናቸው? ግዕዝና አግአዚ የማይለዩ እንደ እነ ዳንኤል ክብረት የመሳሰሉ የማኅበሩ ግሳንግስ ግለሰቦችን እንደሚሉን አምናለሁ።! እንዲህም አርጎ ሊቅነት የለ!!

አሜን ማለት ምን ማለት ነው?”

እውነት ነውአሜንየሚለው ቃል የአማርኛ ወይም የግዕዝ ቋንቋ አይደለም።አሜንየሚለው የግሪክ፣ የግዕዝ ሆነ የአማርኛ ቃል መሰረቱየተረጋገጠና የታመነከሚል ከዕብራይስጡ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውምይሁን”“መልካምየሚል ነው። አሜን በረከት፣ እርግማን፣ ጸሎትወዘተ ከቀረበ ወይም ከተነገረ በኋላ ተደጋግሞ አገልግሎት ላይ የሚውል ቃልም ነው። በተጨማሪም አሜን የሚለው ቃል በተነገረው ቃል ላይ መስማማትን የሚያመላክት ነው። ለምሳሌ ያህል በሐዲስ ኪዳን (ዮሐንስ 1 51 ይመልከቱ) ኢየሱስ በተደጋጋሚአሜንየሚለውን ቃልእውነት እውነትበሚል ተተክቶ ወይም ተተርጉሞ እናገኘዋለን።!

ስንት ጊዜ ነው አሜን ማለት የሚቻለው?”

እንደማኅበረ ቅዱሳንደርቆ የሚያደርቅ የልምድ አዋላጅ በፊትዎ እስካልተገተረ በስተቀር በሰሙት ቃል የተባረኩ ያህል አሜን የማለት የልጅነት ሥልጣን ተሰጥቶታል። እዚህ ላይ በቁጥር የሚወሰን ነገር የለም። ከመንፈስ ቅዱስ በሆነ ሙላት፣ ደስታና በአምልኮ የተነሳ ሰባት ጊዜ ሰባ ሰባት አሜን ቢሉ እርር ድብን ቅጥል የሚለው የሰው ልጅ መልካም ነገር ማየት የማይሆንለትና የማይወድ የወንድሞች ከሳሽ ሰይጣንና ጭፍሮቹ ናቸው።ማኅበረ ቅዱሳንእንደሆነ በር ዘግቶ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሲራገምና ደማቸውንም ለማፍሰስ ሲማማል አንጀቱ እስኪሳብ ምላሱም እስኪደርቅ ድረስ ማቆሚያ በሌለው ሁኔታ አሜን ሲል ነው ጸሐይ የምትጠልቅበት።! እናንተ ሰው ለማጥፋት አሜን በሉ የእግዚአብሔር ቅዱሳን ግን ለጌታቸው ክብር ልባቸው በተነካ ቁጥር አሜን ይላሉ፡፡ ለተረፈ ሚልኮሎች እድል መስጠት አይገባም፡፡ የእነርሱ ድርሻ  በጌታ ፊት የሚሆኑትን በአምላካቸው የሚደሰቱትን መናቅ ነው ነው፡፡ ምላሹ ደግሞ በትልቁ ጌታ በእግዚአብሔር መተው መረሳት ነው፡፡ ለወደዳችሁ ከኃጢአትም በደሙ ለዋጃችሁ ጌታ እልል በሉለት፡፡ አሜን!!!!!
/ ሙሉጌታ ወልደገብርኤል
Email: yetdgnayalehe@gmail.com

22 comments:

 1. አይ አባ ሰላማዎች የህ የምንፍቅና ጉዟችሁ በቅርቡ እዘው አዳራሻችሁ ውስጥ አሁን ቤተክርስቲን ውስጥ የተደቡትን ጨምሮ እንደምናያችሁ ስለምናውቅ አዟቸሁ ተሰባሰቡ….እኛ ግን የአባቶቻችንን ሥርዓት አንለቅም….

  ReplyDelete
 2. ተባረከ ሙሉዬ ይህን የሰይጣን ማህበር አሜንን አይወድም

  ReplyDelete
 3. dink new sehufu. amen belenal

  ReplyDelete
 4. አሜን!!!!!
  አሜን!!!!!
  አሜን!!!!!
  አሜን!!!!!
  አሜን!!!!!

  ReplyDelete
 5. ሙሉጌታ እውነተኛ መጠሪያህ ነው ወይስ እንዲሁ ሥራ ፈተህ አሉባልታ የምትጽፍበት መለያ ስምህ ነው? በጣም የምትገርም ፍጡር ነህ። ሌባ ለዓመሉ ዳቦ ይልሳል እንዲሉ በጋሻው እንዲህ እንደትልቅ ነገር መነገሩ ለቤተ ክርስቲያን ንቀት ነው። ይህን ስል ከአሉት ሊቃውንት አንጻር ነው። በሙሉጌታ ስም የምትጽፈውን ሁለት ያህሉን ተመልክቼአለሁ አንድም የሚጠቅም ነገር ያለው ነገር አላየሁም። ለምን ማኅበሩን እንደምትጠሉት በሚገባ ስለማውቀውና እንቅስቃሴውም አገር አቀፍ ብቻ ሳይሆን የውጪውም ዓለም እጅ ስለአለበት ቤተ ክርስቲያኗን በማዳከም ሀገርንም በሌሎች መዘውር እንድትወድቅ የሚደረግ ከፍተኛ ጉዞ ላይ ስለመሆኑ አያጠራጥርም። የጸሐፊ ዋና መልእክት እንደሚያመልክተው በጥላቻ ወይም በጥቅማ ጥቅም እንደሆነ እንጂ የማኅበሩን ዓላማና ሥራዎች በቅርቡ ስለማውቀው አንተም እንደምትለውም አይደለም። አንዴ ለዚሁ ዓላማ የተሰለፍክ ስለሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም። በጋሻውም ቢሆን ሌላውን ነገር ትቶ በአባቶች እግር ስር ሆኖ ቢማር ይጠቅመዋልና በዚህ ላይ ቢያተኩር መልካም ይሆናል አለበለዚያ ግን ወደፊትም ቢሆን በዚህ አካሄዱ የትም የሚደርስ አይመስለኝም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሁለት ነገር። 1፥ ሙሉጌታ የታወቀ በማቅ ጦር ተወግቶ እንዳይሞት ጌታችን ያተረፈዉ ትክክለኛ ስሙ ነዉ፥ ማሀበረ ሰይጣን የሚለዉን መጻፍ የጻፈ የሐዋሪያት ወንድም ነዉ 2፥ በጋሻዉ የትኛዉ አባትህ እግር ስር ተቀምጦ እንደማር ትጠቁመዋለህ እሱ የሚያስተምሩት ካገኘ ምንጊዜም ለመማር ዝግጁ ነዉ፥ ወንጌልን ግን ከሆነ የምትለዉ መንፈስ ቅዱስ በበቂ እያስተማረዉና እያናገረዉ ስለሆነ ሳትሰማዉ መናገር ጥሩ አይደለም። የጌታ ስም የተባረከ ይሁን!! አሜን!አሜን!አሜን!አሜን! አሜን!አሜን!!!!

   Delete
  2. Mulugeta simeh lihone yichilal but dicon yemilew gin ke-eraseh lay aurdew..Aurtodox has no diacone like you...go to pente adarash and they will give you somename...nigid yibekah

   Delete
  3. ቆይ ልጠይቅህ አቶ አኖኒመስ አሁን ሙሉጌታ ያነሳቸዉ ነገሮች ምን አጥፍተዉ ነዉ ከቤተከርስቲያን አንተ ደገሞ ልታወጣዉ የፈለገህ እርግጥ ስህተት የሆነ ነገር ተናግሮ ከሆነ እኛም ሊገባነ ይገባልና አካፈለን አለዚያ ወንደምን በባዶ ሜዳ መክሰስ ክርስቲያንነት ሳይሆን እንዴተ ተደፈርኩ የሚል የፊወዳል ወኔ ነዉ

   Delete
 6. Amennnnnnnnnnnnnnnnnnnnn

  ReplyDelete
 7. Amen.keber hulu legeta yehun.

  ReplyDelete
 8. Yemehaym tirekim hulu begashaw andu mehayme meriachehu new kezih hulu esu rasu megemerya yemar ena amen yebel MK is mk

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጤና ይስጥልኝ ሊቀ ሊቃውንት!!!!!!!
   አፍ ሲከፈት ጭንቅላት ይታያል አሉ!!!!
   ስድብህን ለሚመጥንህና ለሚገልጥህ ላንተ አቆየው

   Delete
 9. Replies
  1. ተሃድሶ ተጋለጠ
   ቅድስት ማሪያም የመዳን ምክንያት ያደረጋት ጌታ ኢየሱስ ነው፣ ፃድቃንን ሐዋሪያትን መርጦ ያከበራቸው ጌታ ኢየሱስ ነው
   ለሐዋሪው ዮሐንስ እና ለመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የመሰከረው ጌታ እየሱስ ነው ፣ በመፀሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ፃድቃን ካሉ ለእንርሱ ስል ለሕዝቡ ምህረት እሰጣለሁ ያለው ጌታ እየሱስ ነው፣ በፃድቀን ሥም የሚደረግ በጎነገር ዋጋ እንዳለው የተናገረው ጌታ እየሱስ ነው፣ ቅዱሳን መላዕክት ከፈጣሪ በተሰጣቸው ፀጋ የሰውን ልጅ ከመከራ እንደሚታደጉ በመፀሃፍ ቅዱስ ተመስክሯል
   ታዲያ ይህቺ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በዕውቀት የተሞላች ምንጎሎባት ነው መታደስ አለባት የሚባለው ቅዳሤው እረዘመ፣ ፆሙ በዛብን፣ ፃድቃንን ፣ ቅድስት ማሪያምን ማመስገን አያስፈልግም ፣ እንደፈለግን እንብላ እንጠጣ፣ እንጨፍር እንዝናና ፣ ፃድቃንን ማክበር አያስፈልግም፣ ስንቱን ፆርና ተጋድሎ በድል የተወጡትን በምድር ላይ እራሳቸውን የካዱትን ፃድቃን ሰማዕታት ከእራሳቸው ሕይወት ጋር የሚያወዳድሩ ነውረኞች ፋሽን ቲሸርት ቀበቶና መነፅር ለመግዛት በየሱቁ ሲሻሙ የሚውሉ የስጋቸውን ፍላጎት መግታት የተሳናቸው አቅመቢሶች ቢያንስ አስከ 6 ሰአት እንኮን መፆም የማይችሉና አብዝቶ መስገድን የሚፈሩ በየካፍቴሪው በርገር እንደ አሳማ ሲሰለቅጡ የሚውሉ ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑ ተሃድሶ መናፍቃን ከቤተክርስቲያን ይመነጠራሉ በቤተክርስቲናችን እድል ፋንታ የላቸውም በተጨማሪም ከላይ ከሰማይ ተሰጥኦ ሳይታደሉ ለቢዝነስ/ ለሆዳቸው መሙያ ስባሪ ሳንቲም ለማግ ኘት/ በኦርቶዶክስ ስም የሚዘምሩ ሐያሉን እግዚሃቤር አቃለው በማይገባ ቃል የሚጠሩ/ ፍቅሬ፣ውዴ፣…../ መዝሙራቸው ዜማው ከአለማዊ ዘፋኞች የተሰረቀ እና ተራ ምንም መልዕክት የሌለው ሕይወታቸው በምሳሌነት የማይቀርብና የማያስተምር፣ የሰውን ብሶት መሰረት ያደረገ ስብከት አይሉት ፉከራ በመንዛት ሲደ በማሳተም ሆዳቸውን የሚሞሉ ማፈሪያዎች በምድራዊ ሕይወታቸው ሰነፎችና ታካቾች በመሆናቸው ዘለግ ያለ የትምህርት ደረጃ የሌላቸው ለመኖር ሆዳቸውን ለመሙላት አማራጭ ስለሌላቸው ይህችው ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው የሚቃትቱ ሰነፎች በእግዚአብሄር እገዛና በእራሳቸው ጥረት በሁለት ወገን የተሳለ ቢላዋ ሆነው/በምድራዊ ትምህርታቸው የመጠቁና የላቁ ዶክተሮች፣ ዳኞች፣ መምህራን፣ ኢንጂነሮች፣ሳንቲስቶች እንዲሁም በመንፈሳዊ ህይወታቸው በማይታመን ሁኔታ የላቁ አስከ ቅስና ድረስ የዘለቁ / ወንድሞች የመሰረቱትን ማህበር የመናፍቃንና የተሃዱሶዊያን ጠላት የሆነውን ማህበረ ቅዱሳን መናፍቃን በብሎጋቸው ስሙን ጥላሸት ለመቀባት ሲፍጨረጨሩ ይውላሉ ሆኖም ማህበሩ እውነተኛው ዳኛ እግዚሃብሄር የመሰረተውና በሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን ልብ ውስጥ ሰርፆ የገባ በመሆኑ ምንም ማምጣት አይቻላቸውም እኛም/የኦርቶዶክስ ልጆች/ በፀሎት፣ በዕውቀት፣ በገንዘባችን ማህበሩን መርዳት አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡መስቀል መሳለም፣ የንስሃ አባት፣ የቃልኪዳኑ ታቦት፣ እጣኑ የቅዱሳንን ስም መጥራትና ማመስገን ኤስፈልግም የምትሉ እንዲሁም ስግደትን፣ ፆምን፣ ቅዳሴን የምትፈሩ ሰነፎች እና ሆዳም ተሃድሶዊያን አርብና እሮብ ሳገለግል ይርበናል ስለዚህ አልፆምም መብላት ያስፈልገኛል የምትሉ አጉራ ዘለል ሰባኪያን ከቤተክርስታኒያችን ውጡ ልቀቁ ምክንያቱም ቤተክርስታኒያችን ለሰነፎችና ለሆዳሞች ቦታ የላትም አትመችም ፣ በመዝሙር ሥም ጭፈራ እና የስጋ ድሎት ወደሚፈቀድለት በአዳራሽ ውስጥ ሴሰኝነት ወደ ነገሰበት የዘመኑ መናፍቃን መሰባሰቢያ ሂዱ እንደወደዳችሁም የሥጋችሁን ፈቃድ ፈፅሙ አታለቃቅሱ የፃድቃንን ተጋድሎ በምን አቅማችሁ ትችላላችሁ ወዝ የሌላችሁ ሀሰተኞች አስመሳዮች ጌታ ያከበራቸውን ከእኛ በምን ይበልጣሉ የምትሉ ማፈሪዎች ቅዱሳን ከመወለዳቸው በፊት በእግዚያብሄር እንደሚመረጡ እንኮን የማታስተውሉ ሰነፎች ሀሳባችሁ ምድራዊ የሆነ "መዝሙርና "ስብከታችሁ" ሰውን የማይለውጥ ባዶ የቆርቆሮ ጩኽት አሁንማ ተነቃባችሁ ሲዲ መቸብቸብ ቀረ በመዝሙር ስም ትዝታ፣ አምባሰል ……… እየዘፈናችሁ፣ ሁሉም ነቃ ትንሽ ትልቁ …. ቡዝነስ ቐረ ቦሌ ካፍቴሪያ እያማረጡ ሆድ መሙላት ቀረ ገና እውነተኛ ጌት እየሱስ ክርስቶስ በስሙ የሚነግዱትን ያዋርዳቸዋል፣

   Delete
 10. አሜን ማለቴን አላቈርጥም
  ጠላት ዐይኑን ቢያፈጥም

  ሀያ አራቱም ሽማግሌዎችና አራቱ እንስሶች በፊታቸው ተደፍተው በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ለእግዚአብሔር። አሜን፥ ሃሌ ሉያ እያሉ ሰገዱለት።
  ዮሐንስ ራእይ 19:4

  እኔስ አሜን ብል ያሣፍራል ወይስ...?

  አራቱም እንስሶች። አሜን አሉ፥ ሽማግሌዎቹም ወድቀው ሰገዱ።
  ዮሐንስ ራእይ 5:14

  እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኃይል ይሁን፤ አሜን።
  1ኛ ጢሞቴዎስ 6:16

  የሚነገረው አሜን በእርሱ

  እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነውና፥ ስለዚህ ለእግዚአብሔር ስለ ክብሩ በእኛ የሚነገረው አሜን በእርሱ ደግሞ ነው።
  2ኛ ቆሮንቶስ 1:20

  አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው

  በሎዶቅያም ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ። አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ በእግዚአብሔርም ፍጥረት መጀመሪያ የነበረው እንዲህ ይላል።"
  ዮሐንስ ራእይ 3:14

  ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
  2ኛ የጴጥሮስ 3:18

  ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።
  የይሁዳ መልእክት 1:25

  የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።
  2ኛ ቆሮንቶስ 13:14

  አሜን የሆነው፥ አያውቁምና ይቅር በላቸው

  ኢየሱስም። አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ።
  ሉቃስ 23:34

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሁንም አሜን!! አሁንም አሜን!! ሰይጣን የሚጠላዉ እኛ ግን የምንባረክበት ትልቅ የተሰጠን ቃል ነዉ

   Delete
 11. amen alebotawna alegizew kchuhet yalefe aydelem. enante meredat silematichilu yalhone tirgum setachihut

  ReplyDelete
  Replies
  1. እርግጥ ዉስኪ ጠጣ ቁርጥ ብላ ሲሉኝ አሜን ማለት የለብኝም። ነገር ግን ስለጌታዬ ምስጋና ድንቅ ነገሮች በረከቶች፥ ሊያረግልን ቃል ስለገባበትና ሌሎችም ትንቢቶቸ ስሰማ አሜን!!! አሜን!! እላለሁ። ስንት ጊዜ ብትለኝ፥ 10000000000 ጊዜ ሊሆን ይችላል። ስለዚህም አለጊዜና አለቦታዉ የምትለዉን እስካለየህ ድረስህ መልዕክትህ እንዳልደረሰኝ እወቅ። ልቦናህን ያበራልህ።

   Delete
 12. አሜን የሆነው የክርስቶስ እውነት ገና ይገለጣል አሜን እንላለን ሁሉ ጊዜ የሰይጣን መልክተኞቸ ማህበረ ቅዱሳን እባካችሁ አሜን በሉ ጠላት ይፈር አልያ ተለዩና ለአባታችሁ ለሰይጣን ተገዙ፡፡ በቤ/ክ ለእኛ ተውሉን የቀደመችውን ኦርቶዶክስ እውነቷ አሜን የሆነው ክርስቶስ ነው፡፡ ማስተዋልን ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 13. Ehi? Begashaw Vs Abaselama Blog?

  ReplyDelete
 14. Amen Amen yehun yedergelen !

  ReplyDelete
 15. sint gize tinoralachihu yemitinorut lehodachihu kehone pls kemenifesawinet wotitachihu yealemin nuro mekelakeli

  ReplyDelete