Sunday, March 16, 2014

የቤተክርስቲያን ልሳን የሆነው ዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ማኅበረ ቅዱሳን አዘጋጅቶት የነበረው የአብነት መምሕራን የምክክር ጉባኤ የታገደው ሕገወጥ በመሆኑ ነው አለ

Read in PDF


በማንአለብኝነት እየተንቀሳቀሰ ያለውና በሕገወጥ መንገድና በቤተክርስቲያን ስም የግል ጥቅሙን እያካባተ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን እንደትልቅ የገቢ ምንጭ የሚጠቀምበትን የአብነት ትምህርት ቤት ከእስካሁኑ በበለጠ ሊጠቀምበት በማሰብ ጠርቶት የነበረው የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ መታገዱን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይህንኑ እግድ አስመልከቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልሳን የሆነው ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በየካቲት 2006 ዓ.ም. እትሙ ጉባኤው ሕገወጥ በመሆኑ መታገዱን ገልጿል፡፡ 
እንደጋዜጣው ዘገባ ከሆነ ጉባኤው የታገደው የሥልጣን ተዋረድ ማእከሉን ያልጠበቀና ቤተክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት እንደሌላት የሚያስቆጥር ሕገ ወጥ አሠራር በመሆኑ ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው በማኅበረ ቅዱሳን አካሄድ ሕገወጥነት በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ እየተስፋፋ መሆኑን ነው፡፡ለዚህም አንዱ ማሳያ በግዮን ሆቴል ሊደረግ የታሰበው ጉባኤ ቢታገድም ሕገወጡ ማቅ ግን “የቅዱስነታቸውን ትእዛዝ ተግባራዊ ባለማድረግ በራሱ ጽሕፈት ቤት የምስክር ጉባኤውን ማካሄዱ ነው፡፡” ሲል የማቅን ሕገወጥነት ጋዜጣው አጋልጧል፡፡ 

ጋዜጣው አክሎም ማኅበረ ቅዱሳን “ይባስ ብሎ የምክክር ጉባኤውን መታገድ እንደተጽእኖ በመቁጠር ዜናውን ወቅት ባፈራቸው የተለያዩ ድህረ ገጾች በመላው ዓለም እንዲሰራጭ አድርጓል፡፡” በማለት ማቅ በከፈታቸው ስውር ብሎጎቹ የቤተክርስቲያንን ክብርና ልዕልና የሚያጎድፉ መልእክቶችን ለዓመታት ሲያስተላልፍ የቆየ መሆኑንና ይህም በቤተክርስቲያኒቱ ስር ነኝ ከሚል አንድ ማኅበር የማይጠበቅ ድርጊት ሆኖ መገኘቱን አመልክቶ፣ ማህበሩ ከስህተቱ ተምሮ ይቅርታ መጠየቅና ከሕገወጥ ድርጊቱ መታቀብ እንዳለበት የጠቆመ ሲሆን ማኅበሩ ከዚህ ድርጊቱ ካልታቀበ ግን በተክርስቲያኒቱ ቀኖናዋ በሚፈቅደው መሠረት ሕጋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ጠቁሟል፡፡
ከዚህ ሌላም ማቅ ጭሰኞቹ ያደረጋቸው አንዳንድ የአብነት መምህራንም ከሀገረ ስብከታቸው ዕውቅና ውጪ በማቅ ጥሪ ብቻ መንቀሳቀስ የሌላባቸው መሆኑንና በማቅ እዝ ሥር የዋሉ አንዳንድ ሀገረ ስብከቶች ካሉም በጠቅላይ ቤተክህነት ተጠያቂነት እንዳለባቸው አስገንዝቧል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የዜና ቤተክርስቲያን ዋና አዘጋጅ የሆኑትን መጋቤ ምስጢር ወልደሩፋኤልን የማቅ ሰዎች በስልክ “እንገድልሃለን” ሲሉ ማስፈራራታቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡ እርሳቸውም ለማቅ ዛቻ ቦታ ሳይሰጡ እናንተ እኔን ለመግደል ያልዛታችሁበት ጊዜ አለ ወይ? ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ የጋዜጣውን ሙሉ ቃል ከዚህ የሚከተለው ነው፡፡
  
ማኅበረ ቅዱሳን አዘጋጅቶት የነበረው ሀገር አቀፍ የአብነት መምሕራን የምክክር ጉባኤ ሕገ ወጥ በመሆኑ ታገደ
ማህበረ ቅዱሳን ከየካቲት 3 እስከ የካቲት 9 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም. በግዮን ሆቴል በሌሎች ስፍራዎች ሊያካሄደው አስቦት የነበረው የመላው ኢትዮጵያዊ የአብነት መምሕራን የምክክር ጉባኤ ሕገ ወጥ ሆኖ በመገኘቱ መታገዱን በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ከተጻፈው ደብዳቤ ለመረዳት ተችሎአል፡፡
ቀደም ሲልም በቊጥር 497/2ዐዐ6 የካቲት 4/6/ዐ6 ዓ.ም. በጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ በተጻፈ ደብዳቤ ስብስባው እንዳይደረግ መከልከሉ ተገቢ እንደነበር በቅዱስነታቸው የተላለፈው የጽሑፍ ትእዛዝ አስታውሶ ጉባኤው የሥልጣን ተዋረድ ማእከሉን ያልጠበቀ ከመሆኑም በላይ ቤተክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት እንደሌላት የሚያስቆጥር ሕገ ወጥ አሠራር በመሆኑ ነው፡፡
ይሁን እንጂ በግዮን ሆቴልና በሌሎችም ቦታዎች ሊደረግ የነበረው ስብሰባ ቢታገድም ማህበሩ ግን የቅዱስነታቸውን ትእዛዝ ተግባራዊ ባለማድረግ በራሱ ጽሕፈት ቤት የምስክር ጉባኤውን ማካሄዱ ታውቆአል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ይባስ ብሎ የምክክር ጉባኤውን መታገድ እንደተጽእኖ በመቊጠር ዜናውን ወቅት ባፈራቸው የተለያዩ ድህረ ገጾች በመላው ዓለም እንዲሰራጭ አድርጓል፡፡
          ማህበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብርና ልዕልና ያልጠበቁ፣ ስምዋንም በከንቱ የሚያጐድፉ የተሳሳቱ መልእክቶችን በተለያዩ ድህረ ገጾች በየጊዜው ሲያስተላልፍ መኖሩ ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም እንዲህ ዓይነቱ ሕገ ወጥ ድርጊት በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር ነኝ እያለ በስምዋ ከሚጠቀም ማህበር የሚጠበቅ ድርጊት ሆኖ አልተገኘም፡፡
          ስለዚህ ማህበሩ ካለፈው ስህተቱ ተምሮ ይቅርታ በመጠየቅ ወደፊት እንዲህ ዓይነቱን ሕገ ወጥ ድርጊት ከመፈፀም የማይቆጠብና ማንኛውንም እንቅስቃሴውን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ፈቃድ ውጭ የሚያደርግ ከሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናዋ በሚፈቅደው መሠረት አስፈላጊውን ሕጋዊ ርምጃ ለመውሰድ የምትገደድ መሆኑዋ ሊታወቅ ይገባል፡፡
          ከዚህም ሌላ የአብነት መምህራኑ ከያሉበት ሀገረ ስብከት ፈቃድ ሳይሰጣቸው  በቀጥታ በማህበሩ ጥሪ ብቻ የመጡ ከሆነ አህጉረ ስብከት በአብነት መምህራኑ የማስጠንቀቂያ ርምጃ የመውሰድ ግዴታ አለባቸው፡፡ ከሀገረ ስብከታቸው ፈቃድ ተሰጥቶአቸው የመጡ ከሆነ ግን ጠቅላይ ቤተ ክህነት በአህጉረ ስብከት ላይ ርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል፡፡  

15 comments:

 1. it seems that you as anti church has managed to infiltrate the Church Media outlet!! why you are so happy because of this news??

  ReplyDelete
  Replies
  1. What? you kidding ya? is there any one who is better than mk labeled us anti church in EOTC. you should know that mk is tho one who stands against the will of God.

   Delete
 2. mk where are you??????????????are you dead or alive?

  ReplyDelete
 3. mk where are you??????????????are you dead or alive?

  ReplyDelete
 4. Elelelelelellellele

  ReplyDelete
 5. yenante terfi tehadsowoch were mk serawen aykurtewm

  ReplyDelete
 6. ከ60 በላይ ማህበራት ተወካዮች የተገኑበት መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ርእሰ አድባራት ወገዳማት አዲስ ዓለም ገዳም መጋቢት 7 ቀን 2006 ዓ.ም ያደረገው ህብረቱ በፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አቅራቢነት ከቋሚ ሲኖዶስ እውቅናን አግኝቷል፡፡ ወጣቶቹ የሚታወቁት በተለይ በጥምቀት በዓል ለታቦታቱ ምንጣፍ በማንጠፍ አስፋልቱን በማጽዳት ቄጠማ በመጎዝጎዝ ከመታወቃቸውም በተጨማሪ የተሃድሶን እንቅስቃሴን በመግታት ረገድ ከፍተኛውን ድርሻ የተወጡ ናቸው፡፡ እነዚህን ወጣቶች ማንም ሳያነሳሳቸው በራሳቸው ተነሳሽነት የተነሱ ስለሆነ መሰልቸትና ወደኋላ ማፈግፈግ የሚባል ነገር አይታይባቸውም፡፡ የወጣቱን ከፍተኛ መንፈሳዊ እንቅስቃሴ የተመለከተችዋ ቤተ ክርስቲያናችንም ለወጣቶቹ እውቅና ሰጥታለች፡፡ መጋቢት 7 በተደረገው መንፈሳዊ ጉዞ ላይ በአሁን ሰዓት የተሃድሶ ፕሮቴስታንትን የውስጥ አርበኞችን በቤተክርስቲያን ላይ እያሴሩ ያለውን ድብቅና ግልጥ አጀንዳቸውን በተመለከተ መረጃ የቀረበ ሲሆን ወጣቶቹም ከዚህ በፊት ለቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበውና ጉዳያቸው በይደር የተያዘውን ጉዳይ ከፍጻሜ እንዲያደርስና አፋጣኝ መልስ ለህዝበ ክርስቲያኑ እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ በተለይ በቅርቡ ጉዳያቸው በይደር የተያዘላቸው ግለሰቦች ሾልከው ወደ ቤተክርስቲያን መግባታቸውን የገለጹት ወጣቶቹ ቤተክርስቲያናችንን አናስደፍርም፤ ነቅተን እንጠብቃለን ተሀድሶ አራማጆች ግለሰቦችን ወደ ቤተክርስቲያን በማስገባት የሚሯሯጡትን አባቶችም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አሳስበዋል፡፡ ቤተክርስቲያን የሁላችንም ናት ያሉት ወጣቶቹ ጥቂት አባቶች የቅዱስ ሲኖዶሱን /ምለዓተ ጉባኤ/ አጀንዳ ወደ ጎን በመተው የሚወሰነው ውሳኔ ትክክል አለመሆኑን የገለጹት ወጣቶቹ ወደፊትም በየደብራችን ቤተክርስቲያናችንን ነቅተን መጠበቅ አለብን በማለት ተስማምተዋል፡፡ ከ6000/ ከስድስት ሺህ በላይ አባላት ያሉት ህብረቱ ወደፊትም ከሰንበት ት/ቤቶች ከሰበካ ጉባኤ አባላት ከምእመናንና ከሌሎች ማህበራት ጋር በጋራ መበሆን የተሀድሶ እንቅስቃሴ ከመሰረቱ ነቅሎ እንደሚጥልም አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን ማንኛውም ተባባሪ አካላትም ከጎናችን እንዲቆም ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም ይህንኑ የወጣቱን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በመደገፍ ና ወጣቱን ሰብስቦ በማወያየት አባታዊ ምክርና ትምህርት በመስጠት ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጀምሮ የአባትነት ድርሻቸውን በሚገባ እንዲወጡም አሳስበዋል፡፡

  ReplyDelete
 7. the newsletter can say the fact but the way of expressing the issues is like jebdu and crime with out sprituality opinion rather political opinion

  ReplyDelete
 8. Esey min yitebes ena... Aras wusha bicha... Were lemanafes tirotalachihu.

  ReplyDelete
 9. abatochin kemisedib azegaji lela min yitebekal? anid ken enkuan sileselam tsifo ayawikim.aiy welde rofaeal fetaye

  ReplyDelete
 10. Naive fulish priest called him self as highest in the fact he seems block head Erget kale fired. from Texas related multi sexual partener. His x wife Wro Workantefu from his nativ gojam will be speak in the public regarding to his children.

  ReplyDelete
 11. Now is spring mk are relax with cheeky. Where are u mk answer

  ReplyDelete
 12. You are Devil's mouth. Whatever you try to you write about MK no one accept your false information. You know that the author of this magazine is your member. He always write against the church. What he write is the mission given by YOUR GROUP!!!

  ReplyDelete
 13. Hi you guys practing the religious or you got another plane? For me you just look like street people to be honest with you.

  ReplyDelete
 14. I KNOW THE CHIEF EDITOR OF THE MAGAZINE HE HAS NOW BELIEF AND HE IS ALWAYS LIVING FOR MONEY.
  THE BETA KIN ATE IS FULL OF CORRUPTED AND SELFISH SO ''CALLED'' FATHERS THEY AFRAID GOVERNMENT OFFICIALS THAN GOD.
  SO I DIDN'T EXPECT TRUTH AND AUNASITY FROM THEM.

  ReplyDelete