Tuesday, March 18, 2014

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ ማቅ ለፈጸመው ስሕተት ባለው የሚዲያ ሽፋን ሁሉ ይቅርታ እንዲጠይቅ ወሰነ

Read in PDFየመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ በቀን 13/6/2006 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ በትምህርትና ሥልጠና መምሪያ በቀረበው የ5 ዓመት መሪ ዕቅድና የ1 ዓመት የሥራ ዕቅድ ላይ ውይይትና ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት መዋቅርን ጠብቆ ሳይሆን እንዳሻው መስራት የለመደው ማኅበረ ቅዱሳን የአሠራር መዋቅርን ሳይከተል በፈጠረው የመዋቅር ጥሰት ምክንያት ማኅበሩ ባለው የሚዲያ ሽፋን ሁሉ ይቅርታ እንዲጠይቅ ውሳኔ አሳለፈ።
የውሳኔው ደብዳቤ ለማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማእከል ጽ/ቤት የተላለፈው በጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ፊርማና ቲተር መሆኑም ተመልክቷል፡፡ ደብዳቤው ራሱን “ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ወጥቻለሁ፤ አሁን በሲኖዶስ ስር ነኝ” እያለ ለሚጠራው ማቅ ይህን እውቅና የነፈገው ሲሆን፣ የደብዳቤው አድራሻው በቀጥታ “ለማኅበረ ቅዱሳን ዋና ማዕከል ጽ/ቤት” ነው የሚለው፡፡
በደብዳቤው እንደታተተው ቤተ ክርስቲያኒቱ ራሱን የቻለ ሕግና ደንብ ያላት ከመሆኑም በላይ ይህንኑ ጠብቃና የእዝ ሰንሰለትን አክብራ እየሰራች ባለችበት ወቅት ማንአለብኝ ባዩ ማቅ እያደረገው ያለው የመዋቅር ጥሰት ተገቢ አለመሆኑን ገልጾ ማኅበሩ ለፈጸመው የመዋቅር ጥሰት በይፋ ቤተክርስቲያኗን ይቅርታ እንዲጠይቅ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ ይህም የሚያሳየው ማቅ ቤተክርስቲያኗን እንደበደለ ነው፡፡ እንዲያ ባይሆን ኖሮ ቤተክርስቲያኗን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ ባልተደረገም፡፡ 

ጽ/ቤቱ ለማኅበሩ ከጻፈው ደብዳቤ በተጨማሪ ለ50 ሀገረ ስብከት ጽ/ቤቶች በላከው ደብዳቤ ላይ እንደ ገለጸው፣ በማኅበረ ቅዱሳን የሚሠሩት ሥራዎች ሁሉ የሚመለከታቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያዎች ተመርምሮና ተገምግሞ ይሁንታ ሳያገኝ ስብሰባዎች እንዳይካሄዱና ጥሪም እንዳይተላለፍ ጥብቅ መመሪያ እንዲሰጥ በሌላ አካል ጥሪ ቢተላለፍ ተቀባይነት እንዳይኖር የሚል ውሳኔ ነው፡፡  ይህ ማኅበሩ የአንዳንድ ሀገረ ስብከቶች ሹማምንትን ደልሎና አታሎ የተለመደ ቅሰጣውን እንዳያካሂድ በር የሚዘጋና እንዲህ አድርገው የሚገኙ የሀገረ ሰብከቶች ሹማምንት ቢኖሩ ተጠያቂ የሚያደርግ መሆኑን ከደብዳቤው መንፈስ መረዳት ይቻላል፡፡ በራሱ ጊዜ ችግር ውስጥ እየገባ ካለ ማኅበር ጎን የሚቆም ቢኖር አላስፈላጊ ዋጋ ለመክፈል የተዘጋጀ “ሰማዕት ዘበከንቱ” መሆኑ አይቀርም፡፡
በዚሁ ርዕስ ላይ ዜና ቤተክርስቲያን ያወጣውን ዘገባ ያስነበበብን መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ጋዜጣው የማቅን አካሄድ ጠንከር ባለ ሁኔታ የተቸው፤ ማቅ ጉባኤውን በሆቴል እንዳያደርግ ሲከለከል በጽ/ቤቱ  ማካሄዱ “የቅዱስነታቸውን ውሳኔ ተግባራዊ” አለማድረግ ነው በማለት ነበር። ከጋዜጣው ዘገባ በኋላም የጠቅላይ ቤተክህነት ሰራተኞች የጋዜጣውን ዘገባ አድንቀው ሲናገሩ የነበረ መሆኑ ሲታወቅ የብጹዕ ዋና ሥራ አስኪያጁም ደብዳቤም ማኅበሩ የቅዱስነታቸውን ውሳኔ ተግባራዊ ላለማድረግ ያሳየውን ንቅት በይቅርታ እንዲያወራርድ የሚያስገድድ መሆኑ በራሱ ለማኅበሩ ወጣራ እና “ኩሩ” መንፈስ ትልቅ ራስ ምታት እንደሆነበት በግልጽ የሚታይ ሆኗል።
ከሁለቱም ደብዳቤዎች መረዳት እንሚቻለው ለዚህ ውሳኔ መነሻ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን በቅርቡ በሀገሪቱ ያሉትን የአብነት መምህራን ጠርቶ በሆቴል ስብሰባ በማድረግ ሊያካሂድ ያሰበው በማይመለከተው ጉዳይ በጠቅላይ ቤተክህነትና በመምሪያው የሥራ ኃላፊነት ላይ ጣልቃ በመግባቱ እንደሆነና በጠቅላይ ቤተክህነት እገዳ ተደርጎበት እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ ይህ ሕገወጥ እንቅስቃሴ እዚሁ ላይ መቆም ካልቻለ በቤተክርስቲያኒቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ስለሚኖረው ከወዲሁ መገታት እንዳለበት ደብዳቤው አመልክቷል። በዚሁ መሠረት በጠቅላይ ቤተክህነትና በሚመለከታቸው መምሪያዎች ይሁንታ ሳያገኝ በማኅበሩ ስም በቀጥታ  የሚተላለፉ የስብሰባ ጥሪዎች ተቀባይነት እንደሌላቸውና ምንም ዓይነት ስብሰባ እንዳይካሄድና ሁሉም አህጉረ ስብከቶች ይህንኑ እንዲያስፈጽሙ ደብዳቤው አስታወቋል፡፡
በውሳኔው መሠረት ይቅርታ መጠየቅ ለማቅ ትልቅ ፈተና እንደሚሆንበትና ይቅርታ የሚጠይቅ ማንነት የሌለው ከመሆኑ አንጻር ጉዳዩን ወደማያዋጣው ክርክር እንደሚወስደው ከወዲሁ ተገምቷል፡፡  በተጨማሪም ማቅ ራሱን የሚያየው እንደአንድ ማኅበር ሳይሆን እንደአንድ መንግሥት በመሆኑ ይህን ማድረግ ለእርሱ ትልቅ ውርደት ነውና ይቅርታ ይጠይቃል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ይቅርታ ካልጠየቀ ደግሞ የቤተክህነቱ ውሳኔ በአቡነ ጳውሎስ ዘመን እንደነበረው የተለሳለሰ ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ጸሀፊዎችና ሌሎችም አገልጋዮች በማቅ ላይ ከፍተኛ ግፊት ማድረጋቸውን አጠናክረው በቀጠሉበት በዚህ ወቅት ይህን ፋይል ሳይዘጋ ማንአለብኝ ባዩና ሕገወጡ ማቅ በትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ሥራ ጣልቃ ገብቶ በጠራው የአብነት መምህራን ጉባኤ ሌላ ውስብስብ ችግር ውስጥ ራሱን እየከተተ ነው፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩና ሌሎቹም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በማቅ ላይ ጠንከር ያለ አቋም እንደያዙም እየተነገረ ነው፡፡ ይህን ይቅርታ የመጠየቅ የቤት ሥራ ማቅ በተገቢው መንገድ ይፈጽም ይሆን ወይ የሚለው ግን የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል፡፡
እንግዲህ ማኅበሩ ልብ ገዝቶ እና ለቤተክርስቲያን ውሳኔ ተገዝቶ ይቅርታ ከጠየቀ ባለው ሚዲያ ሁሉ ማለት በሐመር መጽሔት በስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ እና በህጋዊ ዌብሳይቱ ሲሆን እውነተኛ የይቅርታ ልብ ካለው ደግሞ የነውጥ ብሎጎቹ ሃራ ተዋህዶ እና አንድአድርገንም ጭምር ቢካተቱበት አይከፋም፡፡ እንዲሁም ሰሞኑን የህዝብ ግንኙነት ስራውን እየሰሩለት ያሉት ጥቅመኛው የሰንደቅ ጋዜጣ እና አዲስ አድማስም የይቅርታውን ዜና ቢዘግቡለት ይቅርታው ሙሉ ይሆናል፡፡ ዜና አቅራቢያቸው አሉላን ማኅበርህን የሚደግፉ ዘገባዎችን ብቻ ሳይሆን ማኅበርህ ቤተክርስቲያንን የሚበደድላትን በደል አስመልክተህ ዘገባ ሥራልን ማለት ይገባቸዋል ፡፡ እነ እንቁ እና አዲስ ጉዳይ ያሉ የማኅበሩ ሰዎች መጽሔቶች እና እንደ እነ ሎሚ ያሉ አጫፋሪዎችም የይቅርታውን ዜና ቢያወጡለት ለማኅበሩ ትልቅ እድል ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች በማቅ ተረቀቀ የተባለውን ሕገ ወጥ ደንብ አንቀበልም በማለት የያዙትን አቋም እንዳልለወጡና ተቃውሟቸውን አጠናክረው እንደቀጠሉ እየተነገረ ነው፡፡ ዐቢይ ጾም ከገባ ወዲህም እንኳ ፓትርያርኩ ዘንድ ቀርበው ተቃውሟቸውን እንዳሰሙና በማቅ ላይ የያዙት አቋም ካልተለወጠ ወደፊት እንደሚገፉበት ተናግረዋል፡፡ ፓትርያርኩም ከጎናቸው እንደሚሆኑና ማቅን ሥርዓት በማስያዙ ስራ አብረው እንደሚሰለፉ ቃል ገብተዉላቸዋል ተብሏል፡፡ ያንን ተከትሎም የማቅ ብሎጎች ፓትርያርኩን የማብጠልጠልና በአቡነ ኤልሳ እስከማዘለፍ የደረሰ ተራ አሉባልታ ውስጥ ገብተው መሰንበታቸው የሚታወስ ነው፡፡ አስተዳዳሪዎቹና ሌሎቹም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ቤተክርስቲያንን ከማቅ ሕገወጥ ጣልቃገብነትና ወረራ ለመታደግ በቅርቡም ፈቃድ ጠይቀው አንድ ትልቅ ስብሰባ እንደጠሩ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ የሚሆነውን እየተከታተልን ለመዘገብ የምንሞክር መሆናችንን ከወዲሁ እንገልጻለን፡፡

32 comments:

 1. MK do it Just like Written in here
  ማኅበሩ ልብ ገዝቶ እና ለቤተክርስቲያን ውሳኔ ተገዝቶ ይቅርታ ከጠየቀ ባለው ሚዲያ ሁሉ ማለት በሐመር መጽሔት በስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ እና በህጋዊ ዌብሳይቱ ሲሆን እውነተኛ የይቅርታ ልብ ካለው ደግሞ የነውጥ ብሎጎቹ ሃራ ተዋህዶ እና አንድአድርገንም ጭምር ቢካተቱበት አይከፋም፡፡ እንዲሁም ሰሞኑን የህዝብ ግንኙነት ስራውን እየሰሩለት ያሉት ጥቅመኛው የሰንደቅ ጋዜጣ እና አዲስ አድማስም የይቅርታውን ዜና ቢዘግቡለት ይቅርታው ሙሉ ይሆናል፡፡ ዜና አቅራቢያቸው አሉላን ማኅበርህን የሚደግፉ ዘገባዎችን ብቻ ሳይሆን ማኅበርህ ቤተክርስቲያንን የሚበደድላትን በደል አስመልክተህ ዘገባ ሥራልን ማለት ይገባቸዋል ፡፡ እነ እንቁ እና አዲስ ጉዳይ ያሉ የማኅበሩ ሰዎች መጽሔቶች እና እንደ እነ ሎሚ ያሉ አጫፋሪዎችም የይቅርታውን ዜና ቢያወጡለት ለማኅበሩ ትልቅ እድል ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. yes it is true

   Delete
  2. Yikerta Teyiku Malet Bete-Christianm Geba Poleticaw gar bech meslogn....kkkkkkkkk (Yikreta Man-Manen Newu Yemiteykew????)

   Delete
 2. Ellelelelelelelelellelelelellelelelelellelele

  ReplyDelete
 3. lewushetachihu nsha gbu
  MKn tewut please! please! please! wow

  ReplyDelete
  Replies
  1. ደብዳቤውን ማንበብ አትችልም እንዴ? ምንአይነቱ እንጭጭ ማቅ ነህ? ውሸት የሚባለው ያልሆነውን መዘገብ ነው። የምታነበው ጽሁፍ ግን የሆነ የተደረገ ነው። ማቅ አጭበርባሪ እና ዋሾ ስለሆነ በየብሎጉ እና ጋተር ፕሬስ የሚዘላብደውን እያመንክ እውነተኛ ዜናን ውሸት ብለህ አትጥራ። በርቺ አባ ሰላማ ከአንቺ ነው ሚዛናዊነትን የማወቅ እድል ያለን። እናመሰግናለን።

   Delete
  2. Bedebdabe Yetetsaf Hula Man newu Tekekel Yaregew Wedaje?

   Delete
 4. political opinion balance than spiritual order; Patriarchate and responsibility in our church just like a duty

  ReplyDelete
 5. ትክክለኛ ውሳኔ ነው። እናመሰግናለን አቡነ ማቴዎስ

  ReplyDelete
 6. it is a very good news. from now on they may think twice before they do anything stupid again.

  ReplyDelete
 7. ማኅብር ተብዮው የነቢዮች ደም የከሰሰው ይመስላል ባገር ውስጥ ማሳደድና ማድማት
  አልበቃው ብሎ በውጭ የሚገኙ አባቶችን በመናቅና በማቃለል አንድና አምሥት ቁጥር ነው
  ይህም በግዚአብሔር ቤት ገብቶ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደማለት ያስቆጥርበታል።2.ተሰሎንቄ 2/4--5

  ReplyDelete
 8. በዚህ ቴክኖሎጂ ባደገበትና የሰው ልጅ አስተሳሰብ ልቀት በደገበት ጊዜ እንደ እናንተ አይነት አስነዋሪ እና የራሱ ዓላማ የሌለው ተላላኪ ተግባርን የሚፈፅሙ ሰዎች በተለይም በቤተክርስቲያን አካባቢ ተደብቃችሁና ተቀላቅላችሁ በመኖራችሁ እያዘንን ነገር ግን ከዚህ በኅላ ተነቅቶባችኋል እንፋርዳችኋለን……… ደግሞ ማኅበረ ቅዱሳን ትናትና፣ዛሬ፣ነገና እስከ ምፅዕት ትፈሩታላችሁ እሱም ለቤተክርስቲያን ዘብ መቆሙን ያቀጥላል እኛም እናግዘዋለን…….. ተሃድሶዎች

  ReplyDelete
  Replies
  1. አዎ እንፈራዋልን፡፡ ለምን መሰላህ ሰይጣንን የማይፈራ ማን አለ፡፡ የእግዚአብሔርን ህዘብ ከበረቱ የሚያስወጣ ፡፡ የጌታ የሆኑት የሚወደዱ እንደሆኑ እናውቃን እንጂ የሚያስፈሩ አይደሉም ክብራችሁ ማስፈራት ከሆነ ቀጥሉ፡፡ ግን በጌታ ለመወደድ ጥረት አድርጉ እንላለን እኛ በክስቶስ ፍቅር እንደዳንን እናምናለን፡፡

   Delete
  2. Gogmangog. Tser kerstos lehone mahiber zeb tekomaleh? Ke iyesuys ena ke mk meret betebal mk nw yemitelew lemin bebal dagmegna altewldekimena.geta fetun wede ante yemeles.

   Delete
  3. TsereKirstos Ema Endante Yalewu Newu, as I can see from your words.

   Delete
 9. all true orthodox tewahedo church members are so happy for great and right decisions.Our senodoss must need to close MK office from kidist mariam area,..................Thanks, our lord God for your great newis

  ReplyDelete
 10. Enesu eko betekrestiyanen kerto Amlaknm bih one yikerta syteyikum....yediyabilos liking beteley awkew lemiyatefut.

  ReplyDelete
 11. what is the entanshion of you guys?

  ReplyDelete
 12. ወይ ማቅ መረ አሁን እንኳን አስተውሉ አንደ እራሔል እንባ የተገፉ ወንድሞችና ቅዱስን ደም እና እንባ በጌታ ፊት እየጮኸ እኮ ስለሆነ ነው እናንት መቼም በጌታ ፊት መቆም አይቻልም እንጂ ቢገጥም እንቢ ማለት ትጸናላችሁ ግን እርሱ ማንም በማይቀርበው ብርሃን ውስጥ ይኖራል፡፡ ስለዚህ ከፍታችሁ የምታጠፉትን ህዝብ ያዙና ወደ መዳን ኑ፡፡ ጌታ የንስሐ ጊዜ እየሰጣችሁ ነው፡፡ ፖለቲካ ምናምን የምትሉትን አቁም በእግዚአብሔር ካመናችሁ ሹመት ሁሉ ከላይ ከጌታ ነው፡፡ ለማንኛውም እኛ የጌታን ነገር ለምንገልጠው ጌታ እየረዳን ነውና ደስ ሎናል፡፡ ለአባታችን ማስተዋልን ስለሰጣቸው ያከበርነው ጌታ ብቻውን ይክበር እንላለን፡፡

  ReplyDelete
 13. Yethadesso revolution movment tewage amatiyan or rebel that founded by reform in eotc will start military action soo in mk. All ethiopian support ed this rebel majority from soouth. We support current ethiopian gov.,but fight fundamentalist mk.

  ReplyDelete
 14. I wiil give all they needs to fight terror mk in Ethiopian.

  ReplyDelete
 15. Abaselama , Mk called you tehadesso why you do not call them terrorist.

  ReplyDelete
 16. AnonymousMarch 19, 2014 at 12:44 PM እሱም ለቤተክርስቲያን ዘብ መቆሙን ያቀጥላል እኛም እናግዘዋለን…….. ተሃድሶዎች ብሎአል እስቲ በሞቴ ተሃድሶዎች ብሎ ስድብ ምንድርነዉ ፤ ተሃድሶ እኮ መንፈስ ብርሃን ሲሰጥ ማለት ነዉ፤ ከግሳንግስ ጸድቶ ወደዱሮዉ ህልዉና መመለስ ማለት ነዉ፤ ወንድሜ ምን ሆነህ ነዉ ወደስድብ የለወጥከዉ፤ ጌታችን ያብራልህ

  ReplyDelete
 17. እዚህ ጋ ማሰብ የሚችል ሰው ካለና የዳቢሎስ እርኩስ መንፈስ እንደ አባሰላማ ተብየዎቹ የተጠናወተው ካልሆነ በስተቀር መለየት ይቻላል ደብዳቤው ተፅፎ የወጣው በ 4/7/2006 ይላል ነገር ግን ስብሰባው የተካሄደው በ 13/07/2006 ይላል ይገርማል ተራ ማወናበድ ውስጥ ባትገቡ መልካም ነው ዲያብሎስ የመናፈቅንና የዲያብሎስን እንዲሁም የከፋፋዮችን ሥራ ይሰራ እግዚአብሔር ግን ሁልግዜ መልካምን ነገር ያደርጋል የእግዚአብሔርም የሆነ መልካምን ያደርጋል ልክ እንደማኅበሩ (ማኅበር ቅዱሳን) ምለት ነው ::አትልፉ የ እግዚአብሔር የሆነን ማንም አሸንፎት አያውቅም እንደሻማ እየቀለጠ ለሌሎች ብርሃን ይሆናልና !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማሰብና ማንበብ የምትችል ሰው ከሆንክ ያልተጻፈ አታነብም። እውነተኛውን ነገር ውሸት ለማለት አትደፍርም ነበር። ከንቱ ስለሆንክ ደግሞ አላስፈላጊ ማጭበርበር ለመፈጸም ትፈልጋለህ። በትክክል ደብዳቤውን አንብብ ደብዳቤው የተጻፈው አንተ እንዳልከው በ04 -07- 2006 ነው ደብደቤው ስብሰባው የተካሄደው የሚለው በ13-06-2006። ህሊና ያለው አንባቢ ያስተውል። ወደ ደብዳቤውም ሄዶ የተጻፈውን ያንብብ። ህልምህን እና እንደ ማቅ ሁሉ የሰይጣን መልዕክተኝነትህን የለመድክበት ፈጽመው። ስድብህን ወደ ራስህ አዙረህ ዋጠው።

   Delete
  2. ስማ ጫኔ ምንልሁን ብለህ ነው ማንበብ አልችልም ቁጥር አላውቅም። የዲያቢሎስ እርኩስ መንፈስ የተጸናወተኝ ነኝእያልክ እራስህን የምታሳደበው? እውነቱን በፈለከው መንገድ በማጣመም ቁጥር ያዛባከው እና ያልተጻፈ የነበብከው አንተ ነህ። በደንብ አንብብ ስብሰባው የተካሄደው በ13-06-2006 ነው ደብዳቤው የተጻፈው በ04-07-2006 ነው። አንተን ብሎ የኢትዮጵያ የልብ ትርታ!!! አረ አገሬ እንዲህ ያለ የተውገረገረ የልብ ትርታ የላትም።

   Delete
 18. ህሊና ላለውና እንደ አባሰላማ ድህረ ገፅ የሰይጣን ወገን ያልሆነ ሰው ደብዳቤውን አንብቦ ወሸት መሆኑን መረዳት ይችላል::ደብዳቤው የወጣው በ 4/07/2006 አ.ም ይላል ስብሰባው ግን የተካሄደው በ 13/07/2006 አ.ም ይላል::ምን የሚሉት ማጭበርበር ነው ?ከመቼ ወዲህ ነው ክፉና የሰይጣን የሆነ አሸንፎ የሚያውቀው ?ሁልግዜ የእግዚአብሔር የሆነ ብቻ ያሸንፋል ::ማኅበሩም እውነተኛ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ያለበት ነው :መናፍቃንና የወያኔ መንግስት ቤተክርስትያንን ለማጥፋት ቀን ከሌሊት ቢጥሩም አይሳካላቸውም መቸም አያሸንፉም ::ስለዚህ እናንተ የመናፈቃን አቀንቃኞች ሆይ እባካችሁ ደብዳቤውን በደንብ አንብቡት የ አቦጊዳ ሽፍታ አትሁኑ!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማሰብና ማንበብ የምትችል ሰው ከሆንክ ያልተጻፈ አታነብም። እውነተኛውን ነገር ውሸት ለማለት አትደፍርም ነበር። ከንቱ ስለሆንክ ደግሞ አላስፈላጊ ማጭበርበር ለመፈጸም ትፈልጋለህ። በትክክል ደብዳቤውን አንብብ ደብዳቤው የተጻፈው አንተ እንዳልከው በ04 -07- 2006 ነው ደብደቤው ስብሰባው የተካሄደው የሚለው በ13-06-2006። ህሊና ያለው አንባቢ ያስተውል። ወደ ደብዳቤውም ሄዶ የተጻፈውን ያንብብ። ህልምህን እና እንደ ማቅ ሁሉ የሰይጣን መልዕክተኝነትህን የለመድክበት ፈጽመው። ስድብህን ወደ ራስህ አዙረህ ዋጠው።

   Delete
 19. MK is a church within a church, and I don't really know how they end up like an appendix to the true orthodox tewahdo, they don't listen to the church, they think they are the only true church. Their main goal is to destroy the church if they can. They are totally disconnected from the basic foundation and principle of the church, LOVE. They hate everybody except their members and are not sent by the loving a lord. My God open their eyes to see his purpose to his children whom they hate, prosecute, kill and remove from their mother church. The Lord will ask their blood from them.

  ReplyDelete
 20. I don't think Yonkers yemiteyku.kefetari yetetalu eko nachewo...they are not afraid or have respect for the sinodos or fathers.mk is the devil's own.

  ReplyDelete
 21. Amlaken bezarew elet yihn selegeletselgne amesegnewalhu.endenante aynetoch yebeg lemd yelebsachutn awlko selasayegne,yihnenm lebzoch endemseker yargegne. Min alachhu??MK minew begun alaserk alachhu?? Abatochun be eregnet yemyagiz honebachhu?? Endelbachhu le mefenchet en aremun be betechristian alazeram ale??wetatun betkim endatyizut temro awko besegam benefsem be hulet bekul yetesal aregbachhu?? Gedamat ena adbarat lay kirsun yemitebek wetat endifeter aderge??are sentun bedelacchu??
  Wekesut bedenb bizum aydenkim endewm bergtegna manentun asaweku. Meche yesematat gedel balubet zemn tesebeke? Amlakes sele seme tiwekesalachhu ale engi timerekalachhu alale.
  Mkn ke abatoch lematalat, ke mengist lematalat gudgwad kofru gin tenkek belu bekoferachhut gudguad endatgebubet.

  ReplyDelete