Thursday, March 27, 2014

ነገረ ማርያም የተባለው መጽሐፍ “ልዩ ወንጌል” በመሆኑ በሐዋርያት ሥልጣን የተወገዘ ነው                                                          ከመምህር አዲስ
ነገረ ማርያም ስለ ቅድስት ማርያም የሚናገር መጽሐፍ ነው። ስለማርያም የሚናገረውም በመጽሐፍ ቅዱስ ስለእርስዋ ከተጻፈውም በመጽሐፍ ቅዱስ ከማይታወቀውም ታሪክ እያመጣ ነው። አሁን አሁንማ ይህ መጽሐፍ እንደጸሎት እንዲደገም በመዝገበ ጸሎት ውስጥ ተካቶ ታትሟል። ብዙ ምእመናንም እንደ ጸሎት ያነበንቡታል። ምን ያህሉ ግን በውስጡ የያዘውን “ልዩ ወንጌል” አስተውሎ ይሆን? የሚለው ትልቁ ጥያቄ ነው፡፡  
 በቅድሚያ “ልዩ ወንጌል” (another gospel) የተባለው ምንድነው? ስለ ልዩ ወንጌል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በገላትያ 1፡6 ላይ “በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤” ተብሎ ተጽፏል፡፡ እንደዚሁም በ2ኛ ቆሮንቶስ 11፡4 ላይ “የሚመጣውም ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ብታገኙ፥ በመልካም ትታገሡታላችሁ።” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ከእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የምንረዳው ልዩ ወንጌል ተብሎ የተገለጸው ከእውነተኛውና የሚያድነውን የምሥራች ከያዘው ወንጌል በተቃራኒ የሚገኝና እውነተኛውን ወንጌል ለማስተባበል የሚሰበክና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እውነተኛውን ወንጌል የሚቃወም መልእክት ነው፡፡ እንዲህ ያለው የተሳሳተ “ልዩ ወንጌል” በሚያጋጥመን ጊዜ እንዳንቀበለውና በመልካም እንድንታገው ሐዋርያው ጳውሎስ በሁለቱም ጥቅሶች ውስጥ አስተምሮናል፡፡
እውነተኛው ወንጌል ስለኢየሱስ ክርስቶስ የሚናገርና መዳን በእርሱ በኩል ብቻ እንደሚገኝ የሚመሰክር ነው፡፡ ወንጌል ከዚህ ውጪ ሌላ መልእክት የለውም፡፡ ይህን ሐቅ ክዶ በሌላ ወገን ወይም በሌላ መንገድ መዳን እንደሚገኝ የሚሰብክ ሌላ መጽሐፍ ወይም ሰው ቢኖር መጽሐፉ ልዩ ወንጌል ሰውየውም የሐሰት አስተማሪ ነውና ሁለቱም የተወገዙ ናቸው፡፡ ምክንያቱም “ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን። አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።” ይላልና የእግዚአብሔር ቃል (ገላ. 1፡8-9)፡፡

ለመሆኑ ነገረ ማርያም የሚሰብከው ልዩ ወንጌል ምንድነው? ማርያም የሞተችው ለ99,999 ነፍሳት ቤዛ ለመሆን ነው ይላል። “ልዩ ወንጌል” ያልኩት ይህን ትምህርት ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ ስለሰዎች ሁሉ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ እንደተሰቀለና በተሰቀለው በእርሱ በማመን ብቻ ሰው እንደሚድን ይናገራል፡፡ ከዚህ ውጪ ስለኃጢአተኞች የሞተ ሌላ አዳኝ እንደሌለ ነው የሚመሰክረው። ልዩ ወንጌል ያልኩት ነገረ ማርያም ግን ማርያም ስለ99,999 ኃጢአተኞች መሞቷን ይተርካልና ልዩ ወንጌል ነው፤ በዚህም ምክንያት በሐዋርያት ሥልጣን የተወገዘ ነው፡፡ በነገረ ማርያም የተጻፈውን ልዩ ወንጌል ሙሉ ቃል ቀጥሎ እጠቅሳለሁ፤
“ከዚህም በኋላ እርሱም ፀሐየ ጽድቅ ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በጊዜ ሞቷ ከመከራ ወደ ዕረፍት ከሐዘን ወደ ትፍሥሕት ትሔጅ ዘንድ ሙቺ አላት፡፡ እርስዋም እግዝእትነ ማርያም “ልጄ ሆይ ወዳጄ ሆይ አንተን ወልጄ ያንተ እናት ሆኜ እኔ እንዴት ልሙት?” ብትለው፣ እርሱም ፀሐየ ጽድቅ ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በፈቃዷ እንዳልሞተችለት ዐውቆ ፱፼  ከ፱ሺህ ከ፱፻ ከ፺፱ ነፍሳት (ዘጠኝ እልፍ ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ወይም 99,999 ወይም ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ማለት ነው) በአንድ ቀን ተኰንነው ገሃነመ እሳት ሲወርዱ አሳያት።
“እነዚህም ነፍሳት እመቤታችንን እግእዝትነ ማርያምን ባዩ ጊዜ ‘እናታችን እመቤታችን ሆይ ለዘመዱ የማያዝን አንጀት እራሱን የማይሸከም አንገት አንጀቱም አንጀት፣ አንገቱም አንገት አይደለም፤ ከልጅሽ አስታርቂን፤ ከገሃነመ እሳት አውጪን፤ መንግሥተ ሰማያት አግቢን’ ብለው ቢያለቅሱባት እርሷም እመቤታችን እግእዝትነ ማርያም ‘ልጄ ሆይ ወዳጄ ሆይ ማርልኝ’ አለችው፡፡
“እርሱም ፀሐየ ጽድቅ ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ‘እኔ ደቂቀ አዳምን ከገሃነመ እሳት አውጥቼ መንግሥተ ሰማያት ያገባሁ ተገፍፌ፣ ተገርፌ፣ ተሰቅዬ፣ ተቸንክሬ፣ ሞቼ፣ ተነሥቼ አይደለምን? አንቺም ለነዚህ ነፍሳት በኃጢአታቸው ካልሞትሽላቸው ዘለዓለም በገሃነመ እሳት ወርደርው ይቀራሉ’ አላት፡፡ እርስዋም እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ‘እነዚህ ነፍሳት ዘለዓለም በገሃነመ እሳት ወርደው ሲቀሩስ (ከሚቀሩስ) ስንኳን አንድ ጊዜ ፯ ጊዜ ልሙት’ ብላ ሙታለች፡፡ ኋላም ለፍጥረቱ ሁሉ መጽደቂያ ሁና ተገኝታለችና ስለዚህ ውህብት (ስጥውት) (የተሰጠች) አላት፡፡
“ወልድኪ ነፍሳተ ሶበ አርአየኪ በእሳተ ኲነኔ ዘሐሙ፤ ይእቲኒ ትብል ቅትለኒ ለቤዛሆሙ’ እንዳለ አባ ጊዮርጊስ፡፡” (ነገረ ማርያም ገጽ )፡፡
ይህን የነገረ ማርያም ልዩ ወንጌል መጽሐፍ ቅዱስ ከሚያስተምረው የመዳን ትምህርት አንጻር ሲመረመር በርካታ ስሕተቶች ይታዩበታል፡፡ ስሕተት የተባሉትን ቀጥሎ እንመለከታለን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርትም እንመረምራቸዋለን፡፡
“ከዚህም በኋላ እርሱም ፀሐየ ጽድቅ ጌታችን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በጊዜ ሞቷ ከመከራ ወደ ዕረፍት ከኀዘን ወደ ትፍሥሕት ትሔጅ ዘንድ ሙቺ አላት፡፡ እርስዋም እግዝእትነ ማርያም “ልጄ ሆይ ወዳጄ ሆይ አንተን ወልጄ ያንተ እናት ሆኜ እኔ እንዴት ልሙት?” አለችው በሚለው አነጋገር ውስጥ፣ የጌታ ከተባለው ንግግር ይልቅ የማርያም የተባለው ምላሽ በመጽሐፍ ቅዱስ የምናውቃት የጌታ እናት ማርያም ምላሽ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ጌታ ተናገረ ለተባለው እርሷ በሰጠችው ምላሽ ይህን ኃላፊና ጠፊ ዓለም ከወዲያኛው ዘላለማዊ ዓለም አስበልጣለች፡፡ ወደዚያኛው ዓለም በሞት ከመሸጋገር ይልቅ እዚህ ኃላፊ ዓለም ላይ መኖርን መርጣለች፡፡ ይህ ደግሞ እንኳን የጌታ እናት ሌሎችም ቅዱሳን የማይመኙት ነው፡፡ ቅዱሳን የሚመጣውን ዓለም የሚናፍቁ እንጂ በዚህ ዓለም ላይ ተስፋቸውን የሚጥሉ አይደሉም፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ በዚህ ዓለም እያገለገለ በመኖርና ወደጌታ በመሄድ መካከል ቆሞ የቱን እንደምመርጥ አላውቅም ብሎ የተናገረበት ስፍራ አለ፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ ዓለም መሄድና ከክርስቶስ ጋር መኖር የተሻለ መሆኑንና ያንን እንደሚመርጥ አስታውቋል፡፡ “ይህ ናፍቆቴ ተስፋዬም ነውና፤ በአንድ ነገር እንኳ አላፍርም ነገር ግን በህይወት ብኖር ወይም ብሞት፥ ክርስቶስ በግልጥነት ሁሉ እንደ ወትሮው አሁን ደግሞ በስጋዬ ይከብራል። ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና። ነገር ግን በስጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን፥ ምን እንድመርጥ ኣላስታውቅም። በእነዚህም በሁለቱ እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፥ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤ ነገር ግን በሥጋ መኖሬ ስለ እናንተ እጅግ የሚያስፈልግ ነው።” (ፊልጵስዩስ 1፡20-24)፡፡
በማርያም ስም የተደረሰው ይህ ድርሰት የሣላት ገጸ ባሕርይ “ማርያም” በመጽሐፍ ቅዱስ ከምናውቃት የኢየሱስ እናት ማርያም ጋር ምንም አትመሳሰልም፡፡ በተለይ “ልጄ ሆይ ወዳጄ ሆይ አንተን ወልጄ ያንተ እናት ሆኜ እኔ እንዴት ልሙት?” የሚለው አነጋገሯ የማያደላውን ጌታ በዘመድ የሚሰራ አስመስላዋለች፡፡ የጌታ እናት መሆን ትልቅ ክብር መሆኑ ባይካድም ከሞት ለማምለጥ ግን አያገለግልም፡፡ ሞት ለስጋ ለባሽ ሁሉ የማይቀር እድል ነውና፡፡ ደግሞም ሞት ሥጋ ለባሽን ሁሉ ድንገት መጥቶ ይወስዳል እንጂ አልሞትም ብለው የሚያመልጡት ባለጋራ አይደለም፡፡ የነገረ ማርያም ደራሲ ገጸ ባሕርይ የሆነችው ማርያም ግን ለመሞት ፈቃደኛ አልሆነችም፡፡ እንዲህ ያለ ገለጻ በአንዳንድ ገድላት ውስጥም የተለመደ ነው፡፡ ለምሳሌ አቦዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በተመሳሳይ መንገድ እንዲሞቱ ሲጠየቁ “ለምንድነው የምሞተው? እኔ እንዳንተ (ጌታን ነው እንዲህ የሚሉት) ከዚህ ምድር ምግብ አልተመገብኩም፤ የእናቴን ጡት እንኳ አልጠባሁም፤ ስለዚህ አልሞትም” ማለታቸው በገድላቸው ውስጥ ተጽፏል፡፡ በዚህም ምክንያት አቦዬ እንዳልሞቱና እንደኤልያስና ሄኖክ እንደተሰወሩ ነው የሚተረከው፡፡ እንዲህ ማሰብም ሆነ መናገር ግን የቅዱሳን ባሕርይ አይደለም፡፡ የገድላትና የድርሳናት ደራሲዎች የሚስሏቸው ገጸባሕርያት የሚያሳዩት ጠባይ ነው፡፡
በዚህ የነገረ ማርያም ክፍል የምናገኘው እውነተኛውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ሳይሆን ደራሲው የሣለውን ገጸ ባሕርይ ነው፡፡ ይህ የደራሲው ኢየሱስ እናቱ አልሞትም ስትለው እርሷ እንድትሞት ለማድረግ ሲል ሌላ ስልት ይጠቀማል፡፡ እውን ይህ ድራማ መሰል ቀልድ በጌታ ዘንድ አለን? ይሁንና ኢየሱስ 99,999 ነፍሳት በአንድ ቀን ተኮንነው ወደ ገሃነመ እሳት ሲወርዱ ያሳያታል። እነዚህም ነፍሳት እመቤታችንን እግእዝትነ ማርያምን ባዩ ጊዜ “እናታችን እመቤታችን ሆይ ለዘመዱ የማያዝን አንጀት እራሱን የማይሸከም አንገት አንጀቱም አንጀት፣ አንገቱም አንገት አይደለም፤ ከልጅሽ አስታርቂን፤ ከገሃነመ እሳት አውጪን፤ መንግሥተ ሰማያት አግቢን” ብለው ቢያለቅሱባት እርሷም እመቤታችን እግእዝትነ ማርያም “ልጄ ሆይ ወዳጄ ሆይ ማርልኝ” አለችው፡፡”
የነገረ ማርያም ደራሲ ዓላማ የእርሱ ገጸ ባህርይ የሆነችውን ማርያምን ያለውድ በግድ የሆነ አሟሟቷን ማሳየት ብቻ ሳይሆን “ማርያም ቤዛዊተ ዓለም ናት” ለሚለው የተሳሳተ ትምህርት እውቅናን ለማጎናጸፍ ሐሰተኛ ማስረጃን ማቅረብ ጭምር ነው፡፡ ስለዚህ ነፍሳቱ ወደማርያም እንዲያለቅሱና ከልጅሽ አስታርቀሽ ከገሃነመ እሳት አውጪን እንዲሉ ያደርጋል፤ ልቅሷቸው በኢትዮጵያዊ ተረትና ምሳሌ የታጀበ መሆኑ ደግሞ ድርሰቱ እውን የሆነ ሳይሆን የተፈጠረ የአገር ቤት ድርሰት መሆኑን “እናታችን እመቤታችን ሆይ ለዘመዱ የማያዝን አንጀት እራሱን የማይሸከም አንገት አንጀቱም አንጀት፣ አንገቱም አንገት አይደለም” የሚለው ተረት ያሳያል፡፡ ማርያምም ልቅሷቸውን አይታ ልጄ ሆይ ማርልኝ አለችው፡፡
ቅዱሳን አንድ ኃጢአተኛ ሰው ተፈርዶበት ወደ ሲዖል ከወረደ በኋላ ንስሐ የመግባትና ከሲኦል ወደገነት የመዛወር እድል እንደሌለው ስለሚያውቁ በዚህ ሁኔታ ላለ ነፍስ ምሕረትን ከእግዚአብሔር አይጠይቁም፡፡ ለምሳሌ አብርሃም በሲኦል እየተሰቃየ የነበረው ባለጠጋ ላቀረበለት የአድነኝ ጥያቄ ከሲኦል ወደገነት መዛወር የማይቻልና በመካከላቸውም ትልቅ ገደል ያለ መሆኑን፣ ምንም ሊረዳው የማይችል መሆኑንም ነው ያስረዳው (ሉቃስ 16፡19-31)፡፡ የነገረ ማርያም ደራሲ የሳላት ገጸ ባሕርይ ማርያም ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ነፍሳትን ማርልኝ አለች ይለናል፡፡ ትልቅ ቅጥፈት!!!
ከእርሷ ማርልኝ ማለት ይልቅ የሚገርመው ልጇ ኢየሱስ ክርስቶሰ ሰጠ የተባለው ምላሽ ነው።“እኔ ደቂቀ አዳምን ከገሃነመ እሳት አውጥቼ መንግሥተ ሰማያት ያገባሁ ተገፍፌ፣ ተገርፌ፣ ተሰቅዬ፣ ተቸንክሬ፣ ሞቼ፣ ተነሥቼ አይደለምን? አንቺም ለነዚህ ነፍሳት በኃጢአታቸው ካልሞትሽላቸው ዘለዓለም በገሃነመ እሳት ወርደርው ይቀራሉ” እውን ጌታ እንዲህ ሊል ይችላል ወይ? በፍጹም!! ጌታ ሐሳቡን እንደ ሰው የማይቀያይርና የማይለወጥ ጌታ ነው፡፡ እርሱ ሰው ሆኖ የመጣው ዓለምን ለማዳንና ለብዙዎች ቤዛ ለመሆን ነው (ማቴ. 20፡28)፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስተምረንም ለኃጢአት ሁሉ የሚበቃ አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል (ዕብ. 10፡12)፡፡ ከእርሱ በቀርም ለሰው ቤዛ ሆኖ የሞተና ሰውን ከኀጢአቱ ሊያነጻ የሚችል ሌላ ቤዛ ፈጽሞ የለም፡፡ ታዲያ በምን ሒሳብ ነው ጌታ እናቱን “እኔ የሞትኩት ለአዳምና ለሔዋን ነው፤ አንቺ ደግሞ ለእነዚህ  ቤዛ ሆነሽ ሙቺላቸው፤ አሊያ ለዘላለም ከገሃነመ እሳት አይወጡም” ሊል የሚችለው? ይህ ትምህርቱ እንደዚህ ተረትና ድርሰት ላይ ለተመሰረተ ሰው ምንም ባይመስል በእግዚአብሔር እንደመቀለድ ነው የሚቆጠረው። ከዚህም በተጨማሪ የክርስትናን ዋና ትምህርት የሚንድ ትልቅ ክሕደት ነው፡፡ ጌታ ለሰው ሁሉ ነው የሞተው፤ በእርሱ የሚያምን ይድናል፤ የማያምን ግን ይፈረድበታል እንጂ ሌላ የሚሞትለት ቤዛ የለም፡፡ ስለዚህ ማርያም የሞተችላቸው 99,999 ነፍሳት አሉ ብሎ መናገር ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ሁሉ ቤዛ ሆኖ መሞቱን መካድ ነው የሚሆነውና ይህ ትምህርት ከአጋንንት ነው፡፡
ለነገሩ ደራሲው እነዚያ ነፍሳት በማርያም መሞት ምክንያት ወደ ገነት መግባታቸውን በቀጥታ አይነግረንም። እንደ ድርሰት ሥራ መጨረሻውን እኛ እንድንገምት ነው የሚተወን፡፡ ከዚያ ይልቅ ትኩረቱ ማርያም ቤዛዊተ ዓለም በመሆኗ ላይ ነውናኋላም ለፍጥረቱ ሁሉ መጽደቂያ ሁና ተገኝታለችና ስለዚህ ውህብት (ስጥውት) (የተሰጠች) አላት፡፡” ወደማለት ይሸጋገራል፡፡ ለፍጥረቱ መጽደቂያ ማነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አይደለምን? ማርያም ለመሆኑ ለፍጥረቱ መጽደቂያ የሆነችው ምን አድርጋ ይሆን?
“አሁን ግን በሕግና በነቢያት የተመሰከረለት የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጦአል፥ እርሱም፥ ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ልዩነት የለምና፤ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ።” (ሮሜ 3፥21-24)።
ለዚህ አጋንንታዊ ትምህርት አባ ጊዮርጊስ “ወልድኪ ነፍሳተ ሶበ አርአየኪ በእሳተ ኲነኔ ዘሐሙ፤ ይእቲኒ ትብል ቅትለኒ ለቤዛሆሙ፡፡” ማለትም “ልጅሽ በፍርድ እሳት እየተሰቃዩ ያሉ ነፍሳትን ባሳየሽ ጊዜ (ባሳያት ጊዜ ቢል በቀና ነበር) እርሷ ለቤዛቸው እኔን ግደለኝ አለች” አለ መባሉ የአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ አንዳንዱ ትምህርት የስሕተት ትምህርት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ ማርያም ቤዛ ሆና የሞተችላቸው ነፍሳት አሉ ብሎ የሚያስተምር ሰው ከመሠረቱ ሐሰተኛ እንጂ እውነተኛ ሊሆን አይችልም፡፡ ይህን ትልቅ እውነት ከካደ ሰው ሌላ እውነተኛ ትምህርት ይገኛል ብሎ ማሰብም አስቸጋሪ ነው፡፡
አባ ጊዮርጊስ በአንዳንድ አስተምህሮው የተነቀፈ ነው፡፡ በታሪክ ያልሆነን ነገር እየፈጠረ እንደጻፈ ይነገራል፡፡ ለምሳሌ ታላቁ አባት ዮሐንስ አፈወርቅ “አፈወርቅ” የሚለውን ስም የተጎናጸፈው በአንደበተ ርቱዕነቱና በጥሩ ሰባኪነቱ ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ግን መጽሐፈ ምስጢር በተባለ ድርሰቱ ውስጥ አርሱ አፈወርቅ የተባለው ንስጥሮስ እንድትሰቀልና በሀፍረተ ሥጋዋ ላይ ሁሉም እንዲተፋ ባደረጋት ሴት ላይ በመትፋት ፈንታ ሐፍረቷን በመሳሙ ማርያም አፈወርቅ አለችው ማለቱ ተጽፏል፡፡ የአይጥ ምስከር ድንቢጥ እንዲሉ የዘርዓ ያዕቆብ ታምረ ማርያምም ይህን እንደእንድ ታምር ጽፎታል፡፡
የአባ ጊዮርጊስ የፈጠራ ታሪክ እንደሚለው የቍስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት ንስጥሮስ እሑድ ዕለት በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ሳለ፣ አደፍ የሆነች ሴት መጣች፡፡ ስትመጣም የመንፈስ ቅዱስ ጥላ ሲለያት አየ፡፡ ወዲያውኑ ተዘቅዝቃ ቁልቁል እንድትሰቀል አደረገና እግዚአብሔር ከሴት ማሕፀን አልተወለደም” እያላችሁ በማኅፀንዋ ላይ ትፉ” ሲል አዘዘ፡፡ ሰዎች ሁሉ፣ እግዚአብሔር ከሴት ማሕፀን አልተወለደም እያሉ ሲተፉባት ሳለ፣ ዮሐንስ አፈወርቅ የዚያን ጊዜ ቄስ ነበርና፣ ሄዶ “እግዚአብሔር ከዚህ ማሕፀን ተወለደ ” ሲል የሴቲቱን አፈ ማሕፀን ሳመ ይላል፡፡ /መጽሐፈ ምሥጢር ክፍል ዘዘለፋ ንስጥሮስ/፡፡ ይህ ትረካ ንስጥሮስን ለማክፋት የቀረበ እንጂ ታሪካዊ እውነታውን የጠበቀ አይደለም፡፡ ንስጥሮስ ክርስቶስን ከሁለት የከፈለና ማርያምንም ወላዲተ አምላክ አይደለችም ብሎ የተናገረ መናፍቅ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዮሐንስ አፈወርቅ የቁስጥንጥንያ ሊቀጳጳሳት የነበረው ከንስጥሮስ በፊት ነው፡፡ ስለዚህ ዮሐንስ አፈወርቅ በንስጥሮስ ጊዜ ቄስ ነበረ የሚለውም ትረካ የታሪኩን ቅደም ተከተል ያልጠበቀ ነው፡፡ ስለዚህ አባ ጊዮርጊስ ከላይ በተጠቀሰው አስተምህሮው ማርያም ለነፍሳት ቤዛ ሆና ሞታለች ቢለን ልዩ ወንጌል አምጥቷልና በሐዋርያት ሥልጣን ውጉዝ ነው እንላለን፡፡

68 comments:

 1. እንዲያ በልልኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንዲያ

   Delete
  2. አይ እናንተ እኔ መጠቀስ በጠቀስኩኝ ግን ጥቅስ ሰይጣንም ይጠቅሳል ለሰይጣን የሚያቅተው መተግበር ነው ማመን ሰይጣንም ያምናል ለሰይጣን ያቃተው በተግባር መስራት ወይ ምግባር አለመኖር ነው ስለዚህ ስለ ጠቅላላ ኑፋቃያችሁ ግን በእውነት እግዚአብሔር ይቅር ይበላቹ ዝንቱ መፅሓፍ ተፅሓፈ ለተግሳፀ ዚኣነ "ይህ መፃፍ የተጣፈው እንገሰፅበት ዘንድ ነው" አናንተ እና መሳዮቸችሁ ይህንን የምትመለከቱበት ግዜ በእግዚአብሔር ፍቃድ እስኪመጣ ድረስ አታምኑም ስለዚህ ከበረከቱ አለመካተታችሁ እንጂ እምቤታችንስ ነብያት ተተንብየውላት ሓርያት ሰብከውላት ሊቃውንት ያሰተማሩላት ልዩ ጽዮን ናት -----------------------በእውነት ግን እናንተ ስለ ሐወርያ ቅዱስ ጴጥሮስ አና ሁላቸው ሐውርያት ለእናንት ምናችሁ ናቸው አታውቁዋቸውም ምንም ምንም ምንም ለእናንተ ክርስቶስ ምነባችሁ ነው ምንም ምንም ምንም ለእናንት ክርስትና ምናችሁ ነው ምንምን ምንም ምንም ስለዚህ ከእናንት ስለ ክርስትና ከማውራት ይልቅ ማንንቱ ቶሎ በሚረዱት አሕዛብ መናገር ይሻላል ምክንያቱ አማኒ መስሎ ከሚኖር ኢአማኒ ከሀዲ ሁኑ የሚኖር ኢአማኒ ይሻላል እና

   Delete
 2. እንዲያ በልልኝ

  ReplyDelete
 3. I never knew this kinds teaching existed in our church

  ReplyDelete
  Replies
  1. አባቶችሄን ጠይቃ!

   Delete
  2. በዚህ ድረገፅ ፖስት የሚደረጉ ሃይማኖታዊ ሀሳቦች የተጠቀሱትን የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎችና ሌሎች (ራዕየ ማሪያም፤ነገረ ማሪያም፤ ገድለ ተ/ተክለሃይማኖት ወዘተ) አንብበን ትክክለኛውንና ሐሰተኛውን መለየት እንድንችል የሚረዳን ይመስለኛል። አንዳንድ የክርስትና እምነት ተከታይ ጓደኞቼ ይህንን መልዕክት እንዲያነቡት ስጋብዛቸው ሰውየው(አባ ሰላማ) ከሃዲ መሆኑንና መናፍቅ(ፕሮቴስታንት) ስለሆነ እንዲህ አይነቱን ት/ት ያስታምራል በማለት ለማንበብ እንደማይፈልጉ ስሜታዊ መልስ ይሰጡኛል። ቁም ነገሩ ግን የሰውየው ማንነት ሳይሆን መልዕክቱን በጥሞና በማንበብና በመመርመር ተገቢውን መፅሐፍ ቅዱሳዊ መልስ መስጠት ነው(ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ ይለናል)። አንብበን እንድንረዳና እንድናገናዝብ ትክክለኛውን ለይተን እንድናውቅ እግዚአብሐር መንፈሳዊ ዓይኖቻችንን ይክፈትልን።

   Delete
 4. Yemayadrubet Bet Ayameshubet New Yetebalew Aydel Enante Kalemenachu hubet Lemin Silesu Taweralachu Minew Keneqefeta Yetseda Nsuh Yehone Zena post btadergu Aba Selamawoch. Lemehonu Aba Selama Yemilew Simun Bewuil Atenachutal Wey? Yeselam Abat Malet Min Malet New Kidusun Abat Egzeabher Amlak Yesetachew Tsega Enante Lemegfef Tchlalachu wey? Ke Aba Selams Weladete Amlak Dingile Mariam Atbeltim wey? Lenegeru Endyaw Lisafew Enj post ende matadergut Awuqalehungne.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ አለ ያገሬ ሰው ምንድር ነው የምትለው። ይልቅስ ጽሁፉን በትክክል አንብበህ ስህተት የምትለው ነገር ካለ አውጥቶ መናገር አይሻልም። ዝም ብለህ ለምን ትዘባርቃለህ። በመጀመሪያ በጸጋና በሀሰት ትምህርት መካከል ያለውን ልዩነት በትክክል መረዳት ያስፈልጋል። ነገረ ማርያም ጸጋ ሳይሆን የዲያቢሎስ መንግስት ውርስ ነው።

   Delete
  2. teretehen ezawu teret wulude ebuyan...semonun alekocheh wehini yeweredulehal yane abereh taferaleh...

   Delete
 5. O my God, so many thing we do not know about our church spiritual books ,it was hiding behind the Geez language .Gude fela zendero .........why it be like that? not right.....

  ReplyDelete
 6. ኣንተ የማታስተውል ሌላ ለሰው ያልተናገርከው ሚስጢር ይኖርሃል እንጂ የሃይማኖት ጥያቄ ኣለህ ለማለት ኣይቻልም :: ደግነቱ የእግዚኣብሄር የሆኑቱ ሁሉ ከማን እንደተማሩ ስለሚያውቁ ኣይስቱም ኣንተም ውስጥህን ኣትካዳት እንድትድን ደግሞም ጸልይ::

  ReplyDelete
 7. በሃዋርያት ውግዘት ታምናላችሁ እንዴ?

  ReplyDelete
 8. ለመሆኑ! በሃዋርያት ውግዘት ታምናላችሁ እንዴ? መንታ ምላሶች!!!! ቃላት እንድትመርጥ እነዛ ፓስተሮች አስለጠኑህ አይደል

  ReplyDelete
  Replies
  1. min malet new? temehirtun tikebelalehe? sehetetn sehetet malet lmin enferalen?

   Delete
 9. በተደጋጋሚ በዚህ ድህረ ገፅ ላይም ሆነ በሌላ ላይ በሚወጡ መጣጥፎች ላይ የሚሰነዘሩ ወቀሳዎችንም ሆነ ድጋፎችን በማንበብ በታዛቢነት የቆየሁ ሲሆን ዛሬ ግን አንድ ውሳኔ ላይ ስለደረስኩ ለወገኖቼ ይህንኑ ውሳኔዬን ላካፍል ደፈርኩ።
  ውሳኔዬም በሐዋርያት ሥራ ም 17 ቁ 11 ላይ ባሉት የተነገራቸውን ከመቃወም ወይም ደግሞ እንዳለ ከመቀበል ይልቅ ይህ ነገር እውነት ይሆንን በማለት ቃሉን በትጋት በመረመሩ እና እውነትነቱን ካረጋገጡ በኋላ ለማመን ወይም ለመወሰን ባልተቸገሩት የቤርያ ሰዎች ላይ መነሻ ያደረገ ሲሆን ግቤም ደግሞ በዮሐንስ ወንጌል ም 4 ላይ ከጌታ ኢየሱስ ጋር በነበራት ቆይታ ያደረገችውን ሁሉ ስለ ነገራት በጥያቄ በመሞላት የየመሰከረችውን ምስክርነት በመስማት ለማረጋገጥ እርምጃን በመውሰድ "ከእንግዲህ የምናምነው አንቺ ስለነገርሽን ብቻ አይደለም እኛ እራሳችን ሰምተነዋል" በማለት የዓለም አዳኝ መሆኑን የዓይን ምስክሮች ለመሆን እንደበቁት የሰማሪያ ሰዎች ለመሆን ይህ የተባለለትን መፅሃፍ "ነገረ ማሪያምን" ገዝቼ በማንበብ ከተገለጠው የእግዚአብሔር ቃል ጋር ይጣረሳል ወይስ ----ብዬ ለመመርመር ወስኛለሁ ለእናንተም እንዲሁ ይሁንላችሁ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ena wedaje esti bante ayn(eye) mn ymeslal ngeren?

   Delete
  2. Dear readers,
   What type of Books are evidences of our 'TIMIHIRTE HAYMANOT' ? why you try to judge the Church liturgy with this document only.
   The writer of the article why do you try to confuse those that are innocent on the church education? If you were a person to educate you had had also said about the education of our church on saint Mary.
   The book is not 'Negere Mariam' instead it is 'SENE GOLGOTA' a book for 'TSILOT" not a book for education.
   You have stated her opnion not to day as a very wrong point of the book, how could you educate the word of Our Lord Jesus Christ on the very last of his time on 'GETESIMANIE'.
   If I had had known to write in Amharic font ...
   Any ways do not quot literature's for 'Tsilot' to demonstrate the church education just for the seek of confusion. If you have any confusion go and ask 'MEMHIRAN', but do not spit what you have as if it is water.

   Delete
 10. Ba ergit ba betekristiyan meche endegebu yamaytawaku ka Metshaf kidus gar yamigachu bizu metsehaft endalu 'Papasat" saykeru yawukalu nager gin yihenen lemastekakel weyem wede hizeb endayders madereg yalebachewu enersu nachewu silezih la SINODOS" masasebiyawu bisetena. enya gin 'ORTHODOX TEWAHEDO' emenetachen endih aynet ezih giba yamaybal tsihuf tetsefo siletegenye yamitekeyer emenet aydelechem. sinaneb "Eyatelelen" enanebeb. yihenen tsihuf Post yaderekewu saw DINGEL MARIAMEN sawoch enditelu ena haymanot endikeyeru felegeh ka tsafek tesasetahal. saw eyastewale hiwotun endimera kehone tikomah tiru naw. "amlko lamigebawu amlko. kiber lamigebawu kiberen ensetalen" Ameeeen.

  ReplyDelete
 11. ጌታ አብዝቶ ይባርክህ።ቃለ ህይወት ያሰማልን።

  ReplyDelete
 12. እንደ ሳምሶን እናስተውል!!!!

  አዋጅ! አዋጅ!! አዋጅ!!! ዘመዶቼ! በማርያም ምክንያት ስንነታረክ እሱን ስሙት ያለችውን ሳንሰማው ሞት እየቀደመን መሆኑን ባንረሳ መልካም ነውና ሁላችንም እንደ ሳምሶን እናስተውል!!!! ሕይወት የግል ነውና፡፡

  ሕሊና

  ReplyDelete
  Replies
  1. He replayed 'take your mother' and he took her. We also took her... that is also what he said.

   Delete
 13. ምነው ብትተዉን ደንቁረን ብንቀር? እያሳወቃችሁን እኮ ግራ እየተጋባን ነው።

  ReplyDelete
  Replies
  1. 1ኛ እምነት ከመስማት መሆኑን ቅዱስ ቃሉ ስለሚያስተምረንና ቃሉን በማንበብና በመረዳት መስማት ይድኑ ዘንድ ጽኑ ፍላጎቴን እገልጻለሁ፡፡2ኛ ስለድንቁርና ካነሱ ዘንዳ:ድንቁርና በሰለጠኑ አገሮች ወንጀል ሆኖ ስለሚያስከስስ ነዉ እንጂ በኛ አገር ደንቁሮ መቅረት እንደመብት ሊፈቀድልዎት ይችላል፡፡

   Delete
 14. “ልዩ ወንጌል”

  ReplyDelete
 15. የእኛን ለእኛ ተውልን፡፡ እናንተ እኮ…… ስለዚህ የእኛን ለኛ፡፡

  ReplyDelete
 16. This is really an insightful and well written article. Our church and all Orthodox followers need these kinds of explanations and condemning to anyone who has false and twisted teaching of the church's doctrine. Everyone knows that the church is run and hijacked by few radicals and so-called "traditionalists" who try to protect their power and wealth in the church by spreading and using false teaching and scar tactics. In order to accomplish their goals, they train and unleash innocent cadres all over the world. I also would like to point out that there are some opportunists who want the destruction of the Ethiopian Orthodox church tradition and teaching as a whole and try to introduce their new philosophy and doctrine for their own sake.

  So we need to fight both sides and protect our church at this stage of time, and we need to be more pragmatist both in the spiritual and administrative reforms of the church. Some people go crazy when they hear the word "reform" and become very defensive, but we have to keep in mind that most of us have spent several years hearing those small radical groups preaching to brain-wash our minds.

  Finally, I would like to say that we should keep preaching the glory of the Lord Jesus Christ and His original teaching to be good one another and to our neighbors. Also we need a strong and truthful leaders in the church administration to get rid of the corruption what currently is going on both administratively and spiritually.

  Selam for all

  ReplyDelete
  Replies
  1. 100% true. be blessed

   Delete
 17. እውነትም “ልዩ ወንጌል”

  ReplyDelete
 18. what to say ?? yegermal ende kuran yaltekefetu ena yaltenebebu chirstina yemayshetu bezu yebetechrstian metsehafoch alu . alemawek endet kebad neger new ?

  ReplyDelete
 19. Hiruy Leake Likawint, minew tedebek?

  ReplyDelete
 20. ሰላም ኣምላክ ከእናንተ ይሁን" ይሄ መልእክት ለዋናው ጸሃፊ ነው

  ReplyDelete
 21. You didn't understand Negere Maryam Adis,she said that I don't want to die "for me i understand that she wants to go paradis like Henok or Elias,not like your mis understanding that she didn't want to leave this world.plus Yohannes 14:12 says that "whoever believe on me, he can do like me more than this"then Her mother believes on Her Son and she saved not only 99999 lives whynot 1Million,according to His Word and promise.let me ask you,when Our Lord prays on Getesemani"Father pass this cup from me" was He wanting to live here in this world or did He fear death?no.like this why do you think the question and anwser of Virge Mary like Her Son?The mother of Samuel the prophet said that God can send to hell and bring souls from hell,1sam2:6:then by the praying and death of St.Mary;Her Son brought souls from hell.From this I understood that Negere Maryam has not contradiction with Gospel but your thinking and translation have a very big contradiction.

  ReplyDelete
  Replies
  1. "Did He fear death?" Yes, he did. But that doesn't make his a less-redeemer. Instead, it makes him the true one. Never forget that He was fully human.

   Delete
  2. I think you're still confused by trying to defend and explain the purpose of "Negere Mariam". Sometimes the truth hurts for some of you and fight the church true teaching and doctrine until your last breath. So please open your mind and do some more independent readings and research about the true Ethiopian Orthodox Church. Even the Egyptians and Syrians Orthodox laugh at us for our mythological obsessions. Keep your minds and heart open!!!

   Delete
 22. እንገሊጣር ስለ 1 ሚሊዮን ነፍሳት የጻፍከዉ ወንድም እህት ስለነገረ ማሪያም ያነበብክ አተመስልምና እንደገና አንብበዉ ልብ ታወልቃለህ የምን በደበላለቅ ነዉ የእግዚአብሔርን ሥራ ለእመቤታችን የምትሰጡትን ተዉ እርስዋን እናከብር ብላችሁ የጌታን ክብርና የሱን ብቻ ችሎታ የሆነዉን አሳልፋችሁ መስጠት ያስጠይቃል ነዉ የተባላችሁት

  ReplyDelete
 23. የእንጦጦ መምህር ቢናገር በአመት፣ ያውም እሬት!!
  በሰላማ ብሎግ በኩል የሚቀርቡልን መምህራን ለመምህርነታቸው ዘርፍ የለውም፡፡የቅኔም፣የሀዲስም፣የብሉይም፣የድጓም….መሆን ይችላሉ፡፡ምክንያቱም ግእዝ ያወቀ ሁሉ ሁሉን መተርጎም ይችላል፡፡ምክንያቱም ፕሮቴስታንቶች በ1 አመት ኮርስ ሊጨበጥ የሚችለውን ግእዝ የጠቀሰ ሁሉ ሊቅ ረቂቅ ይመስላቸዋል፡፡ድሮ ፈረንጅ ሁሉ ሀኪም፣እንግሊዝኛ የቻለ ሁሉ ምሁር እንደሚመስለን መሆኑ ነው፡፡በየወቅቱ በሰላማ ብሎግ የሚቀርቡ ጸሀፍትም እውቀታቸውን 81ዱ መጻህፍትን በመተርጎም ሳይሆን ለምዕመናን መጽናኛ የሆኑ የመልካመልኮችንና ገድላተ ቅዱሳንን ነጠላ ንባብ እየፈለጉ መቆንጸል ሆኗል፡፡ቁንጸላው ሲካሄድ ከሁዋላ እና ከፊት ያሉ ምንባባት፣የጽሁፉ ይዘትና መልእክት፣የተጻፈበት ጊዜና ወቅት፣በቤ/ክ አገልግሎት ያለው ሚና ግምት ውስጥ አይገባም፡፡ብቻ ጥሬ ንባቡ ይያዝና ለተቃራኒ ሀይሎች ግዳይ ይጣላል፣ንባቡም እንደ አማኝ ሳይሆን እንደ ዓለማዊ ሰው በአመክንዮ ይብጠለጠላል፣ሲያስፈልግም እንደነ ተስፋየ ገ/አብ ያሉ በሙሴ ባህረ ኤርትራን መክፈል የሚሳለቁ ዓለማዊ ሰዎች የጻፉት ልቦለድ ሳይቀር ይጠቀሳል - ብቻ ኦርቶዶክስን ያጥላላ!!በጉባኤ ቤቶቹዋ የሀዲስ፣የብሉይና የሊቃውንት ትርጉዋሜዎች የምትሰጠው ቤ/ክ መገለጫዋ ገድልና መልክ ብቻ እንደሆነ ለማሳመን ጥቂት ተይዞ ብዙ ይወራል፡፡ይሄ ቅሬታየ ነው፡፡ለዚህ ነው የእንጦጦ መምህር ቢናገር በአመት፣ያውም እሬት ማለቴ፡፡ወደ ወንድማችን መምህር ሀዲስ…
  1.ስለ አማላጅነት አስተምህሮ
  በእመቤታችን አማላጅነት ላመነ ሰው አንድ ነፍስም ሆነ አንድ ሚሊዮን ነፍሳት አማለደች የሚለው የቁጥር ጨዋታ አያስጨንቀውም፡፡99,999ነፍሳት አማለደች መባሉም በሎጂክ አይን እያየን ወግ እናሳምር ካላልን በቀር አያስገርምም፡፡ምክንያቱም ከቢሊዮን በላይ ሕዝብ አሁንም አማልጅን እያላት ስለሆነ፡፡ስለ አማላጅነት መሰረቶች እናንሳ፡፡አማላጅነት በእኛ ቤ/ክ የራሱ መሰረታውያን አሉት፡፡
  (ሀ)የቅዱሳንን አማላጅነት ከውርስ ለሚመጣውና በደመክርስቶስ ብቻ ለተቀደደው የአዳም ውርስ በደል ሳይሆን በየእለቱ ከምግባረሠናይ በመራቃችን ለሚገጥመን ኃጢአትና ውድቀት ብቻ ነው ለመማጸኛ የምንጠቀመው፡፡ስለዚህ በ40/80 ቀኑ ተጠምቆ የክርስቶስን መድኃኔዓለምነት ያልተቀበለና በቃለ ወንጌል ያላመነ ሰው በቅዱሳን አማላጅነት ብቻ ይድናል ብለን አናምንም፡፡አናስምንም፡፡የቅዱሳኑን ጸሎትና ምልጃ የምንጠቀመውም ከአሚነ ስላሴ አፈንግጠን እንድንሄድ ከሚያደርግ ተግባር እንድንታቀብ ጸሎታቸውና የህይወት ተምሳሌትነታቸው እንዲያግዘን እንጅ በክርስቶስ ቦታ ልንተካቸው አይደለም፡፡በአብ ወልድ መንፈስቅዱስ ስም አጥምቃ የክርስቶስን ስጋና ደም ያልበላ ዘላለም ሕይወት የለውም እያለች ዘወትር የምትሰብክ ቤ/ክ ክርስቶስን በቅዱሳን አማላጅነት ተካቸው ማለት ሀቅን መሸሽ ነው፡፡እኛም እናምናለን፡፡ከአዳም በውርስ ለመጣብን ፍዳ መዳን በማንም የለም፤ በደመ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡እሱ ደግሞ እናንተ በየቀኑ ይማልድልናል እያላችሁ እለት በእለት የሚሰቀል እንደምታስመስሉት ሳይሆን በዕብ 9 ቁ 1 እንደተጻፈው እንዳያድግም ተደርጎ አንድ ጊዜ በበጉ ደም ዕዳ ደብዳቤያችን ተቀዷል፡፡ነገር ግን በስሙ አምነው ለሚወዱትና ትእዛዙን ለሚጠብቁ ቃልኪዳኑንና ምህረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ይጠብቃል ተብሎ በዘዳግ 7 ቁ 9 በነቢዩ ሙሴ እና በሉቃ 1ቁ 46 በእመቤታችን አንደበት የተነገረለት አምላክ ለወዳጆቹ በስማችሁ ቀዝቃዛ ውሃ ያጠጣ ሲል በማቴ 10 ቁ 12 የገባውን ቃልኪዳኑን ሚያጥፍ ዋሾ አምላክ እንዳልሆነ እናውቃለን፡፡አውቀንም ቅዱሳኑን አድርጉልን ሳይሆን በተሰጣችሁ ቃልኪዳን እኛ ከምናምነው እናንተን ካከበረው አምላክ ለምኑልን እንላለን፡፡ስለሆነም በቅዱሳን አማላጅነት ማመን በክርስቶስ ከማመን የሚመነጭ እንጅ ብቻውን ተነጥሎ የቆመ ግንጥል ጌጥ አይደለም፡፡እንዲያውም ቅዱሳን አማላጅነት የሚረዳው ላመነና ለተጠመቀ ብቻ ነው ብለን ነው የምናስተምረው፡፡ኑ!!እዩና እመኑ!!
  (ለ)ቅዱሳኑን አማልዱን ስንል በየቀኑ በመንበረ ስላሴ እየቀረቡ ለእኛ የመማጸን ግዴታ አለባቸው እያልን አይደለም፡፡ጌታ አንዴ አክብሮ ቃልኪዳኑን ሰጥቶዋቸዋል፡፡ስለሆነም በእነሱ ስም ለምናደርገው ሁሉ ራሱ ባለቤቱ ዋጋችንን በሰማያት አያስቀርብንም፡፡እርሱ ለወዳጆቹ የገባውን ቃሉን ያስባል፡፡አይዋሽም፡፡ዳዊት በመዝ 104 ቁ 9 እንዲህ ይለዋል….ቃልኪዳኑን ለዘላለም እስከሺህ ትውልድ ያዘዘውን ቃሉን አሰበ፣ለአብርሃም ያደረገውን ለይስሐቅም የሚለውን ለያዕቆብም ሥርዐት እንዲሆን ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን እንዲሆን፡፡እንግዲህ የአብርሃም አምላክ ሆይ ማረን ስንል አብርሃም ፊቱ ድረስ ሄዶ እስኪለምነው አይጠብቅም፡፡ለአብርሃም የገባውን ቃል አስቦ በእምነት የጠየቅነውን ያደርግልናል እንጅ፡፡በእንተ ማርያም መሃረነ ክርስቶስ ስንለውም እንደዛው ነው፡፡
  (ሐ) የቅዱሳን አማላጅነት የሚጠቅመን እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ነው፡፡አሁን አኮ ብንሞትም ገና የመጨረሻው ፍርድ አልተላለፈብንም፡፡ስለዚህ በማቴ 28 ቁ 20…እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ የተባሉት ሐዋርያት በዕብ 12 ቁ1 እንደተገለጸው እስከዓለም ፍጻሜ ድረስ መንፈሳቸው እንደ ደመና ከቦ እንደሚያማልደን እናምናለን፡፡ያንጊዜ ጌታ ሲመጣ ግን ሁሉም ቅ/ያሬድ ….ማዕረሩሰ ህልቀተ ዓለም ውእቱ… በሚል የደብረ ዘይት ድጓው እንደገለጸው እንደሰብል እንሰበሰባለን፡፡ከዚያ ወዲያ አማላጅነት ለም፡፡ያ ቀን እስኪደርስ ግን እንጠቀምበታለን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቶ /አባ ህሩይ ሆይ፣ የክርስቶስ ባሪያ ነኝ ስላሉ ደስ ብሎኛል።መቸም ኢየሱስ ጌታ ነዉ አይሉም። ምነዉ ቢባል የጴንጤ ነዉ ብለዉ። ከርስዎ ጋር ትንሽም ቢሆን የምጋራዉ አለ።እዉነት ነዉ ዝብርቅርቅና ድብልቅልቅ ባይሆን ጌታችንን አንዴ አንደኛ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሁለተኛና ሶስተኛ ባታደርግ፣ የኢኦተቤተ ክርስቲያን ብዙ የተዋጣላቸዉ ወንጌልን መሰረት ያደረጉ ትምህርቶችና ጸሎቶች አሏት። ለምሳሌ ቅዳሴያችንን ብናዳምጥ ልብ ዉስጥ የሚገባ የጌታ ፍቅርንና ምህረቱን ያዉጃል። በየመሐሉ ደግሞ እመቤታችንንና ሌሎች በሕይወት የሌሉ አባቶችን ለዉድድር ታቀርባለች። ታዲያ እኔ ጌታ ሆይ ይቅር በላቸዉ ብዬ ኤዲት እያደረግሁ ቅዳሴዬን አጣጥማለሁ፡፡ ክብር ሁሉ ላንተ ይሁን ጌታ ሆይ በዚህ ዙሪያ በዚህ ማለዳ የተሰበሰቡትን ልጆቸህን ትታደግ ዘንድ በልጅህ ስም እለምነሃለሁ፣ ብዬ አሜን! ሲባል ወደ ቤቴ እሄዳለሁ። ያ የፈረደበት ህዝብ ግን የነአባ ሚካኤልን የነአባ ገብርኤልን ግዝት ፈርቶ አማናዊዉን ሥጋና ደም ይተካል ተብሎ የሚለፈፈዉን «ተአምረ ማርያም»ን ለማዳመጥ ብድግ ይላል። ይሰቀጥጣል።ይህ ተአምር የተባለዉ መቸም ጉደኛ መጽሐፍ ነዉ። በእግዚአብሔረ ስም ይዤአቸዋለሁና ይህንን መጽሐፍ ገዝታችሁም ቢሆነ አንብቡት ለዚህ የሚወጣ ገንዘብ ለእዉነት ለሚቆም ሰዉ በረከትን ያስገኛልና ሊቆጫችሁ አይገባም። ሌሎችነ ገድላት እንደዚሁ። ደግነቱ ቄሶቻችን በአብዛኛዉ በግዕዝና በሌሊት ስለሚያነቡት ለመደበኛዉ ቅዳሴ የሚመጣዉ ምዕመን ወይ አይገባዉም ወይም አይደርስበትም። ይህንን ጉድ ብዙ ሰዉ ቢያነበዉና የኛን ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ቢያዉቅ እነ አቶ ህሩይም ከመፎለል አርፈዉ ይቀመጡ ነበር። በእዉነት ትልቅ ጾምና ጸሎት ያስፈለገናል ጎበዝ!!! በዚህ በሰሙነ ሕማማት ጌታችን ለቤተክርስቲያናችን ለጌታ የመለየት ዘመን እንዲያመጣላት ከጾሙ ጋር በእንባና በምልጃ እንለምነዉ።

   Delete
  2. ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ይመጣል ጌታ እንዳለው ነው፡፡ ዲያብሎስ ሔዋንን ሲያስታት ከጌታ ቃል ላይ በመጨመር ነበር እንጂ ሙሉ በሙሉ ውሸትን አልተናገረም ነበር፡፡ ዛሬም ያው አሳች በኢየሱስ የሚገኘውን ጽድቅ በማርያምና በቅዱሳን መላእክታን ስም ያምታታል፡፡ ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል እንደተባለው ነው፡፡ ዛሬ አብርሃም ለማንም አማላጅ እንዳልሆነ ወንጌል ይናገራል፡፡ ይህ የተከደነባቸው ለሚጠፉት ነው፡፡ በኢየሱስ በስሙ ይለመናል የኃጢያት ስርይት ይገኛል፤ የታመሙት ይፈወሳሉ፣ የደከሙት ይነሳሉ ወዘተ፤ ከዚህ ያለፈ ሁሉ የክፉው ልዩ ወንጌል ነው፡፡ ተአምረ ማርያምም ሆነ ነገረ ማርያምና ዘመዶቻቸው የፈጠራ ጽሁፎች ሁሉ ውሸት ለመሆናቸው ምንም የሚያሻማ ነገር የለውም፡፡

   Delete
 24. 2.ስለ ነገረማርያም
  (ሀ)በቁጥር ደረጃ አብዛኛውን የክርስቲያን አማኝ በያዘው በካቶሊኩና በኦርቶዶክሱ ዓለም ነገረ ማርያም(Mariology) የሚባል የጥናት መስክ በዩኒቨርሲና በኮሌጅ ደረጃ ይሰጣል፡፡በእኛም እነ ቅ/ያሬድና እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን ጨምሮ ብዙ አባቶች እመቤታችንን በሚመለከት በመንፈስቅዱስ አነሳሽነት የተጻፉ ድርሰቶችን አበርክተዋል፡፡ስለሆነም ስለእመቤታችን በኢ/ዊ ደራሲ ቢጻፍ ያኮራናል አንጅ አያሳፍረንም፡፡ዘይቤው ኢ/ዊ ወይም የአማርኛ ፈሊጣዊ አነጋገርን የተከተሉ ቃላትን መጠቀሙም ይበልጥ ምዕመኑ ምስጢሩን እንዲረዳው ያደርገዋል እንጅ አያደናግረውም፡፡ትርጉም ነው ከተባለም የአባቶቻችንን ቋንቋን አቃንቶ የመተርጎም ችሎታ ያሳያል እንጅ አያስነቅፍም፡፡ትርጉም በራሱ ነጻ ትርጉምና ውርስ ትርጉም የሚል ፈሊጥ አለው ይባላል፡፡እሱን አላውቅም፡፡ብቻ ለምሳሌ በዮሐ 10 ቁ 4 እረኞቹ ድምጹን ሲሰሙ ይከተሉታል ብሎ ጌታ ዕብራውያንን ባህል መሰረት አድርጎ የሰጠውን ምሳሌ እንደወረደ ለደብረብርሃን አርሶአደር ልስበከው ብትል ይስቅብሃል፡፡ምክንያቱም በእኛ ሀገር አሳዳሪውን የሚከተል ውሻ እንጅ በግ አይደለምና፡፡የነገረማርያም ጸሐፊም/ተርጓሚ …አንጀቱ አንጀት አይደለም፤አንገቱም አንገት አይደለም…ማለቱ ለኢ/ዊ እንደሚጽፍ/እንደሚተረጉም ስለሚያውቅ ነው ብለን እናምናለን፡፡
  (ለ)የእመቤታችን ከጌታ መነጋገር እና ሞትን ለመቀበል አለመድፈሯ እንዴት አንዳስገረመህ አልገባኝም፡፡ምናልባት በሃይማኖት ሳይሆን በሎጂክ ስለምትመራ ይሆናል፡፡ያለበዚያማ በዘፀ 32 ቁ 1 ጀምሮ የእግዚአብሄርንና የሙሴን… እስራኤልን ላጥፋ አታጥፋ… ክርክር መሰል ንግግርን ያነበበ ሰው የእመቤታችን ልጇን ማነጋገር ሊገርመው አይገባም ነበር፡፡በዚህ ላይ ጌታ ቦይ ፍሬንድና ገርል ፍሬንድ መረጠልኝ፣ፍሪጅ ገዛልኝ፣የመዝሙር ዜማና ግጥም ሰጠኝ፣ወዘተ…. እያሉ በየቀኑ ያለኔትወርክ ችግር ከጌታ ጋር እንደሚነጋገሩ ከሚያወሩን ሰዎች የጌታ እናቱን ከማረፏ በፊት ማናገር እንደተአምር ማየት እጹብ ነው፡፡ሞተ ስጋን ባለቤቱ በቀራንዮ ቢደመስሰውም ሞተ ስጋ ግን አልቀረልንም፡፡ ባለቤቱም ስቅላቲ ሲቀርብ በስጋው …ቢቻልህስ ይቺ ጽዋ ትለፍ… እስከማለት መንፈሱ መጨነቁን በማቴ 26 ቁ 38 አንብበናል፡፡ሐዋርያትም በሐዋ 8 ቁ 2 እና በሐዋ 9 ቁ 39 ስለእስጢፋኖስ እና ስለጣቢታ ሞት ማልቀሳቸውን አንብበናል፡፡ይሔ ሁሉ የሚሆነው ምን እምነትና ስራ ቢኖረን ወደጌታ ፍርድ ምንሄድበት ሞተ ስጋ ስላልተሻረ ነው፡፡ከሳሽም ሆነ ተከሳሽ ምን ማስረጃ ቢኖራቸው የፍርድ ወንበር ፊት ሲቆሙ መጨነቅ ግድ ነው፡፡እመቤታችንም ምን ወላዲተአምላክ ብትሆን ስጋ ለባሽ ነችና ሞትን ለመቀበል ብታመነታ አይገርምም፡፡
  (ሐ)እመቤታችን ቤዛ፣መድኃኒት መባሏ ያንገበግባችኋል፡፡ሊቃውንት …በስመ ሀዳሪ ይጼዋእ ማኅደር… ይላሉ፡፡ቤት በነዋሪው ይጠራል እንደማለት ነው፡፡እመቤታችንን መድኃኒት ቤዛ ስንላትም እንደዛ ነው፡፡የጌታ ማደሪያ ስለሆነች!!እንደዛ ባይሆንና እሱዋ ቤዛና መድኃኒት ነች ብለን ብናምን ለምን ከጌታ ለምኝልን ማለት አስፈለገ!!ምክንያቱም እሷ መድኃኒት ከሆነች አድኝን እንጅ አማልጅን ማለት አያስፈልገንም፡፡ከዚህ በፊት ጌታን በመርፌ ውስጥ እንዳለ መድኃኒት እመቤታችንን እንደሃኪም፣ጌታን እንደፍሬ እመቤታችንን እንደፍሬው ተሸካሚ ተክል እያደረግን የእሷ መድኃኒት መባል በዛ መልኩ እንደሚገለጽ ተናግረናል፡፡ከፈለጋችሁም ይሄን አንብቡት፡፡የፍጡር መድኃኒት መባል በእሷ አልተጀመረም፡፡ መሳ 3 ቁ 9 እንዲህ ይላል…የእ/ኤል ልጆች ወደ እ/ር ጮሁ፤እ/ርም የሚያድናቸውን አዳኝ የካሌብን ታናሽ ወንድሙን ጎቶንያልን አስነሳላቸው፡፡እንጨምር አብድዩ ቁ 21….በዔሳውም ተራራ ላይ ይፈርዱ ዘንድ አዳኞች ወደ ጽዮን ተራራ ላይ ይወጣሉ፤መንግሥቱም ለእ/ር ይሆናል፡፡ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች አዳኝ ሲባሉ የመዳን ምክንያት ሆኑ መባላቸው ነው የሚገባን እንጅ እ/ርን ተክተው የማዳን ስራ ይሰራሉ ማለት አይደለም፡፡እኛ እመቤታችንን ቤዛዊተ ዓለም እግዝእትነ ወመድኃኒትነ ስንላትም እንደሱ ማለታችን ነው፡፡በነህ 9 ቁ 27 እና በ2ኛ ነገሥት 13 ቁ 5 እ/ኤልን የሚታደጉ ታዳጊዎች፣አዳኞችተብለው የተጠቀሱ ግለሰቦች አሉ፡፡እሱን አንብቡት፡፡
  በተሳልቆ ስሜን ላነሳችሁ ሰዎች የጠፋሁት ተደብቄ ሳይሆን ቅዳሜና እሑድ መጻህፍት በማንበብና ቤ/ክ በማገልገል ማሳለፍን ስለምመርጥ ነው!!የድንግል ልጅ፣የክርስቶስ ባሪያ ማንን ፈርቶ!!ለመዝገበ ጸሎት ቆንጻይስ አባቶቻችንን አንጠራም!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቶ /አባ ህሩይ ሆይ፣ የክርስቶስ ባሪያ ነኝ ስላሉ ደስ ብሎኛል።መቸም ኢየሱስ ጌታ ነዉ አይሉም። ምነዉ ቢባል የጴንጤ ነዉ ብለዉ። ከርስዎ ጋር ትንሽም ቢሆን የምጋራዉ አለ።እዉነት ነዉ ዝብርቅርቅና ድብልቅልቅ ባይሆን ጌታችንን አንዴ አንደኛ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሁለተኛና ሶስተኛ ባታደርግ፣ የኢኦተቤተ ክርስቲያን ብዙ የተዋጣላቸዉ ወንጌልን መሰረት ያደረጉ ትምህርቶችና ጸሎቶች አሏት። ለምሳሌ ቅዳሴያችንን ብናዳምጥ ልብ ዉስጥ የሚገባ የጌታ ፍቅርንና ምህረቱን ያዉጃል። በየመሐሉ ደግሞ እመቤታችንንና ሌሎች በሕይወት የሌሉ አባቶችን ለዉድድር ታቀርባለች። ታዲያ እኔ ጌታ ሆይ ይቅር በላቸዉ ብዬ ኤዲት እያደረግሁ ቅዳሴዬን አጣጥማለሁ፡፡ ክብር ሁሉ ላንተ ይሁን ጌታ ሆይ በዚህ ዙሪያ በዚህ ማለዳ የተሰበሰቡትን ልጆቸህን ትታደግ ዘንድ በልጅህ ስም እለምነሃለሁ፣ ብዬ አሜን! ሲባል ወደ ቤቴ እሄዳለሁ። ያ የፈረደበት ህዝብ ግን የነአባ ሚካኤልን የነአባ ገብርኤልን ግዝት ፈርቶ አማናዊዉን ሥጋና ደም ይተካል ተብሎ የሚለፈፈዉን «ተአምረ ማርያም»ን ለማዳመጥ ብድግ ይላል። ይሰቀጥጣል።ይህ ተአምር የተባለዉ መቸም ጉደኛ መጽሐፍ ነዉ። በእግዚአብሔረ ስም ይዤአቸዋለሁና ይህንን መጽሐፍ ገዝታችሁም ቢሆነ አንብቡት ለዚህ የሚወጣ ገንዘብ ለእዉነት ለሚቆም ሰዉ በረከትን ያስገኛልና ሊቆጫችሁ አይገባም። ሌሎችነ ገድላት እንደዚሁ። ደግነቱ ቄሶቻችን በአብዛኛዉ በግዕዝና በሌሊት ስለሚያነቡት ለመደበኛዉ ቅዳሴ የሚመጣዉ ምዕመን ወይ አይገባዉም ወይም አይደርስበትም። ይህንን ጉድ ብዙ ሰዉ ቢያነበዉና የኛን ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ቢያዉቅ እነ አቶ ህሩይም ከመፎለል አርፈዉ ይቀመጡ ነበር። በእዉነት ትልቅ ጾምና ጸሎት ያስፈለገናል ጎበዝ!!! በዚህ በሰሙነ ሕማማት ጌታችን ለቤተክርስቲያናችን ለጌታ የመለየት ዘመን እንዲያመጣላት ከጾሙ ጋር በእንባና በምልጃ እንለምነዉ።

   Delete
  2. ቃለ ህይወት ያሰማልን።

   Delete
  3. አይ ህሩይ እንደ ባለዛር እኮ ነው የምትቀባጥረው። መጽኀፉ ላይ የተጻፈው ልዩ ወንጌል ነው አይደለም? አጭር መልስ ስጥ። ዝምብልህ አትቀባጥር

   Delete
  4. You confuse yourself to confuse others. Hold to the Truth before it is too late and stop confusing christians.

   Delete
  5. ህሩይ ደህና ነህ
   በእነዚህ ሰዎች አስተያየት ብዙ እንዳትከፋ፤
   የኛ ሀገር ሰው ከቁም ነገር ይልቅ መቀለድ/በሰው ላይ ማንጓጠጥ/ ይወዳል፡፡

   Delete
  6. እነ አስቴር፣ ሰዋሰው…..ወዘተ
   ህሩይ ሊቀ ሊቃውንት ለመሆኑ እኔ እመሰክርለታለሁ፤
   ህሩይ የኦርቶዶክስ ተዋህዶን እምነት/አስተምህሮ ከማንም በተሻለ ሁኔታ እየገለጸልን ነው፤……..ህሩይ ‘መናፍቃን’ የተባሉትን እንካ ‘ፕሮቴስታንት ወንድሞቻችን’ እያለ ነው የሚጠራቸው፤……..ከዚህ የምንረዳው ህሩይ ሊቅ ብቻ ሳይሆን በመልካም ስነ-ምግባር ጭምር የታነጸ ሰው መሆኑን ነው፡፡
   ያልገባችሁ ነገር ካለ በትህትና ጠይቁት እንጂ ሊቀ ሊቃውንት እያሉ በሰው ላይ ማንጓጠጥ ተገቢ አይደለም፡፡
   ልነግራችሁ የምፈልገው ህሩይ ስለ አንድ ነገር የመግለጽ/የማስተማር ችሎታው በጣም ከፍተኛ ነው፡፡
   የእኛ ማመን ወይም አለማመን ከህሩይ ሊቅነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም
   ከቻላችሁ ይቅርታ ጠይቁት
   ደህና ሁኑ

   Delete
  7. በክርስቶስ ኢየሱስ ስም ስላም ለአንተ ይሁን ህሩይ፡፡ ልክ ነው መቼም ሰው ወደብርሀን እስኪወጣ ድረስ የተረዳውን ያወራልን ልክ ነህ ግን በውኑ አንተ የክርስቶስ ባሪያ ከሆንክ በርግጥ አትፍራ ለእርሱ እውነት መስክር ለሁሉት ጌታ መገዛት አይቻልምና ክርስቶስ ጌታህ ከሆነ የሱ ብቻ ባሪያ ሁኑ፡፡ ጰውሎስ በወንጌል አላፍርም ብሎ ብዙ መከራን ስለጌታው ተቀብሏል የአንድ ጌታ ባሪያ ሲኮን መስቀል አለ መቼም አንዳንድ ወንድሞች መካከል መስቀል ሲባል የተመሳቀለው ምልክት ይምስላቸዋል ካለመረዳት መስቀል መከራ ነው፡፡ እናም ወንድሜ አንተ እንደምትለው ብዙ እውቀት ባይኖረኝም የክርስቶ የማዳኑ ነገር ግን እግዚአብሔር ይምስገን ገብቶኛል፡፡ ማለት መዳን በክርስቶስ የማዳን ስራ ብቻ መሆኑ ሊሎቹን ማከባበር የክርስቶስ ደም ማክፋፋት ነው በዚህ ደሞ ያደንን ጌታን እናሳዝናለን እግዚአብሔር በአምልኮቱ ቀናተኛ ነውና፡፡ ስለዚህ ወንድሜ ህሩይ በርግጥ እንደምትለው የክርስቶስ ባሪያ ከሆን ለሱ ብቻ ተገዛ፡፡ ሰዎችንም አታደናግር ማለት ሰው ልክ የአብርሀም ልጅ ነኝ በማለት የሚዳን ስለሚመስለው የቤ/ክ ልጅ ነኝ በማለት ብቻ መዳን ያለ ይመስለዋል ሰለዚህ እዳ አለብህ ወንድሜ ሰው ክርስቶስን ካለማነ አይድንም በልጁ የማያመን አሁን ተፈርዶበታል ነው የሚለው ቃሉ አስተውልና ከቻልክ አንተን የሚሰሙህንም ይዘህ ወደ ክርስቶስ እውነት ና፡፡ ጌታ በነገር ሁሉ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡ ለሁላችንም ማስተዋልን ይስጠን አሜን፡፡

   Delete
 25. Constructive criticism is a good thing! We have so many stories that have blinded the minds of the believers. Questioning those stories and challenging them is not a bad thing because it helps reveal the truth.

  The writer should not be labeled as "Pente Protestant" for raising the challenges that he raised. We should rather respond to the challenge if we have a better fact. Even if I love and believe St. Mary as my intercessor, I am not naïve to believe all the stories that have been written in Her name. I suspect there are so many false stories that some false-brothers have fabricated about Her; these brothers have basically defamed the Church and St Mary for that matter. So, we should take all these challenges as opportunities. Because of the challenges the Protestants made against the church, the EOTC has been forced to preach the bible in Cities since 23/25 years ago. The local areas are still in darkness though.

  We need the Pentes to go the local stronghold of the EOTC so that the church can start reaching out to those disadvantaged folks. Challenge is a good thing for dormant and inactive churches like the EOTC. We already lost about 10-15 million believers because of the church's weakness in educating the followers with the true word of God. We will continue to lose unless we clean and correct our house. God has given us a lot of spiritual wealth, but we have squandered and contaminated it with some human traditions and unworthy stories. This is the best time to do some clean up... I know the so-called Synod is lame and is focused on worldly administrative stuffs, instead of the Gospel and church ministry.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለAnonymousMarch 31, 2014 at 4:07 AM ቃከ ሕይወተ ያሰማልን፡፡ ለአቶ ህሩይ መላልሼ ጥያቄ ባቀርብ እንደተለመደዉ ፋከራ ብቻ እንጂ የመስቀሉን ምስጢር ለመግለጽና መዳን በሌላ እንደሌለ የታወጀዉን የምሥራች ሊቀበሉ አይፈልጉም፡፡ አንዴ ክርስቶስ በቻ አዳኝ ነዉ ይሉና ደግሞ እመቤታችንና ጻድቃንን ምልጃ ፍለጋ ይሄዳሉ፡፡ በቀራንዮ ላይ የፈሰሰዉ ደም እስከ ምጽዐት እንደሚያማልድም ይክዳሉ፡፡ ጌታችን አማልጃችን ነዉ የተባለዉም ዛሬ ቆሞ እንደሰዉ ያማልዳል ሳይሆን አንዴ በመሰቀሉና ደሙም አንዴ በፈሰሰዉ ደሙ ዋጅቶአቸዋልና በሱ ለሚያምኑት ሁሉ በሃጢአት ቢወድቁ እንክዋነ ያዝንላቸዋል ይራራላቸዋል ማለት ነዉ፡፡ ደግሞም በስሜ አንዳች ነገር ብትለምኑ ታገኛላቸዉ አለ እንጂ በሌላ ፍጡራን ስም ጠይቁ አላለም፡፡ ይህንን አስተምሮ አቶ ህሩይ ከዬት እንደመጣ ብትነግሩን ክርሰቶስን ከመጨቅጨቅ እናሳርፈዉ ነበር!!! አቶ ህሩይ እመቤታችን ቤዛዊተ ዓለም ከሆነች የዓለም ቤዛ ኢየሱስ መሆኑ ቀርቶአል እያሉ ነዉ፡፡ ከላይ ያለዉ ወንድም ወይም እህት እንደተናገሩተ ከአፈርኩ አይመልሰኝ ሳይሉ call spade a spade!!!

   Delete
 26. To anonymous March 30:at4:04pm.
  The most important thing you have to understand one big deal which is salvation is by only Jesus only by Jesus” I am the only way whoever come through me will see the father”. Think deep if you think Negere Maryam what about the whole world nobody heard about NegereMaryam . The only thing the world knows about Mary is she was Jesus ‘s mother and she was very good and obedience to God. Other than that the world knows Jesus is saver not Mary. So you think if the world does not know Negere Maryam no body saved the world so if it is not part of the Gospel how is the other world will be saved from hall. Or you think Negere Maryan is only for Ethiopian orthodox? May God open your mind.

  ReplyDelete
 27. childhood idea. you know nothing bout the teaching of Ethiopian Orthodox Tewahdo Church. the book which is called Negeremariyam was written by falls teachers or by those who do not have enough knowledge about the holy gospel. so this teaching is unacceptable teaching,

  ReplyDelete
  Replies
  1. አቶ /አባ ህሩይ ሆይ፣ የክርስቶስ ባሪያ ነኝ ስላሉ ደስ ብሎኛል።መቸም ኢየሱስ ጌታ ነዉ አይሉም። ምነዉ ቢባል የጴንጤ ነዉ ብለዉ። ከርስዎ ጋር ትንሽም ቢሆን የምጋራዉ አለ።እዉነት ነዉ ዝብርቅርቅና ድብልቅልቅ ባይሆን ጌታችንን አንዴ አንደኛ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሁለተኛና ሶስተኛ ባታደርግ፣ የኢኦተቤተ ክርስቲያን ብዙ የተዋጣላቸዉ ወንጌልን መሰረት ያደረጉ ትምህርቶችና ጸሎቶች አሏት። ለምሳሌ ቅዳሴያችንን ብናዳምጥ ልብ ዉስጥ የሚገባ የጌታ ፍቅርንና ምህረቱን ያዉጃል። በየመሐሉ ደግሞ እመቤታችንንና ሌሎች በሕይወት የሌሉ አባቶችን ለዉድድር ታቀርባለች። ታዲያ እኔ ጌታ ሆይ ይቅር በላቸዉ ብዬ ኤዲት እያደረግሁ ቅዳሴዬን አጣጥማለሁ፡፡ ክብር ሁሉ ላንተ ይሁን ጌታ ሆይ በዚህ ዙሪያ በዚህ ማለዳ የተሰበሰቡትን ልጆቸህን ትታደግ ዘንድ በልጅህ ስም እለምነሃለሁ፣ ብዬ አሜን! ሲባል ወደ ቤቴ እሄዳለሁ። ያ የፈረደበት ህዝብ ግን የነአባ ሚካኤልን የነአባ ገብርኤልን ግዝት ፈርቶ አማናዊዉን ሥጋና ደም ይተካል ተብሎ የሚለፈፈዉን «ተአምረ ማርያም»ን ለማዳመጥ ብድግ ይላል። ይሰቀጥጣል።ይህ ተአምር የተባለዉ መቸም ጉደኛ መጽሐፍ ነዉ። በእግዚአብሔረ ስም ይዤአቸዋለሁና ይህንን መጽሐፍ ገዝታችሁም ቢሆነ አንብቡት ለዚህ የሚወጣ ገንዘብ ለእዉነት ለሚቆም ሰዉ በረከትን ያስገኛልና ሊቆጫችሁ አይገባም። ሌሎችነ ገድላት እንደዚሁ። ደግነቱ ቄሶቻችን በአብዛኛዉ በግዕዝና በሌሊት ስለሚያነቡት ለመደበኛዉ ቅዳሴ የሚመጣዉ ምዕመን ወይ አይገባዉም ወይም አይደርስበትም። ይህንን ጉድ ብዙ ሰዉ ቢያነበዉና የኛን ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ቢያዉቅ እነ አቶ ህሩይም ከመፎለል አርፈዉ ይቀመጡ ነበር። በእዉነት ትልቅ ጾምና ጸሎት ያስፈለገናል ጎበዝ!!! በዚህ በሰሙነ ሕማማት ጌታችን ለቤተክርስቲያናችን ለጌታ የመለየት ዘመን እንዲያመጣላት ከጾሙ ጋር በእንባና በምልጃ እንለምነዉ።

   Delete
  2. Ena Awaqew Ante Neha Keyet Ende Metah Ena Wedet Ende Mathed Yalaweq Sew Yemeshaf Kidus Beqy Ewuqet Yelelachew Sewoch Nachew Negere Mariam Yesafut Sitl Tnish Atafrim wey?

   Delete
 28. እናንት አባ ጨለማዎች ከመተቸት በፊት መጠየቅና ለማወቅ መፈለግን አታውቁትም።እኛስ በሉተር ያልተበረዘ ያልተወገዘ ወንጌል በጃችን ይገዘኛል።በወንጌሉም ጌታችንና አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ በሰጠው ስልጣን "ለሚየሰምን ሀሉ ይቻለዋል"ባለው መሰረት በኤልሳቤት ማርያም ጌታችንን ከፀነሰች በሀኌላ "የጌታ ስራ ይሳካ ዘንድ የምታምኚ"ብላ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ስለመሰከረችላት ሁሉ ይቻላታል።በዮሀንስ ራእይ ላይ "ሴቲቱም ከዘንዶው ታመልጥ ዘንድ ሁለት እንደ ንስር አሞራ ያለ ክንፍ ተሰጣት ዘንዶውም እንዳልደረሰባት ባወቀ ጊዜ ከሁዋላዋ አየወንዝን ያህል ውሀ አፈሰሰ ምድርም እረዳቻት ውሀውን ዋጠችው።ዘንዶውም እንዳልደረሰባት ባወቀ ጊዜ የተቀሩትን የእየሱስ ክርስቶስ ምስክር የሚሆኑ ልጆቿን ሊወጋ ባህር ኣሸዋ ላይ ቆመ።ይላል ዘንዶው እነ አባ ጨለማ"እነ ሙሉ ወንጀል የተበረዘ መፀሀፍ ቅዱስ ይዛችሁ የጌታን ምህረትና ኪዳን ጥሳችሁ ስታችሁ ለማሳት የምትሯሯጡ ናችሁ።እናንተ የጨለማ አበጋዞች የዲያብሎስና የገሀነም መብት እናስከብራለን የምትሉ ንስሀ ግቡ "ያለ እመቤታችን አመሰላጅነት አለም አይይይድንም!!!!!"

  ReplyDelete
 29. እናንት አባ ጨለማዎች ከመተቸት በፊት መጠየቅና ለማወቅ መፈለግን አታውቁትም።እኛስ በሉተር ያልተበረዘ ያልተወገዘ ወንጌል በጃችን ይገዘኛል።በወንጌሉም ጌታችንና አምላካችን እየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጅ በሰጠው ስልጣን "ለሚየሰምን ሀሉ ይቻለዋል"ባለው መሰረት በኤልሳቤት ማርያም ጌታችንን ከፀነሰች በሀኌላ "የጌታ ስራ ይሳካ ዘንድ የምታምኚ"ብላ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ስለመሰከረችላት ሁሉ ይቻላታል።በዮሀንስ ራእይ ላይ "ሴቲቱም ከዘንዶው ታመልጥ ዘንድ ሁለት እንደ ንስር አሞራ ያለ ክንፍ ተሰጣት ዘንዶውም እንዳልደረሰባት ባወቀ ጊዜ ከሁዋላዋ አየወንዝን ያህል ውሀ አፈሰሰ ምድርም እረዳቻት ውሀውን ዋጠችው።ዘንዶውም እንዳልደረሰባት ባወቀ ጊዜ የተቀሩትን የእየሱስ ክርስቶስ ምስክር የሚሆኑ ልጆቿን ሊወጋ ባህር ኣሸዋ ላይ ቆመ።ይላል ዘንዶው እነ አባ ጨለማ"እነ ሙሉ ወንጀል የተበረዘ መፀሀፍ ቅዱስ ይዛችሁ የጌታን ምህረትና ኪዳን ጥሳችሁ ስታችሁ ለማሳት የምትሯሯጡ ናችሁ።እናንተ የጨለማ አበጋዞች የዲያብሎስና የገሀነም መብት እናስከብራለን የምትሉ ንስሀ ግቡ "ያለ እመቤታችን አመሰላጅነት አለም አይይይድንም!!!"

  ReplyDelete
 30. Aba selama either close this website or stop writing about Ethiopian Orthodox Church

  ReplyDelete
 31. Aba selama website owner u are dog

  ReplyDelete
 32. Bekerstos dem yedanewn alem ..yale mariyam amaljenet aydenem malet yekehdet
  hulu kehedet I think endezih belwo yemiyamnu menafkan nachew kezih belay menfake yelem.

  ReplyDelete
 33. 1ኛ እምነት ከመስማት መሆኑን ቅዱስ ቃሉ ስለሚያስተምረንና ቃሉን በማንበብና በመረዳት መስማት ይድኑ ዘንድ ጽኑ ፍላጎቴን እገልጻለሁ፡፡2ኛ ስለድንቁርና ካነሱ ዘንዳ:ድንቁርና በሰለጠኑ አገሮች ወንጀል ሆኖ ስለሚያስከስስ ነዉ እንጂ በኛ አገር ደንቁሮ መቅረት እንደመብት ሊፈቀድልዎት ይችላል፡፡

  ReplyDelete
 34. ምነው ይህቸነን ቤተ ክርስቲያን ለቀቅ አድርጋችሁ ራሳችሁን ችላችሁ በነፃነት የፈለጋችሁትን አምናችሁ አምልካችሁ እዛው ብትቀመጡ እንደ መዥገር ተጣብቃችሁ ካላበዘበዝን ካልመዘበርን ብላችሁ ድርቅ ባትሉ
  ምነው ሁሉም ከየአቅጣጫው ያልተገራ አንደበቱን በጨዋ አዕምሮው ቤተ ክርስቲያን ላይ ላይ ጣቱን ይቀስራል ሂዱ ምንም የማያውቁትን ሃይማኖት የሌላቸውን ሞክሩ በእውነት ላይ የተመሠረቱትትን አታሰናክሉ ብዙዎቻችሁ በቢዘዝነሰስ አድርጋችሁት እንደምትንቀሳቀሱ በውል ይታወቃል ግን ምን አለ ትንሽ አንገት ቢኖራችሁ

  ReplyDelete
 35. what is the need to approve comments? You want to post only comments that goes in line with your opinion? or is there any other hidden agenda?

  ReplyDelete
 36. የ666 መንፈስ ነዉ እንዲህ የሚያናግራቺሁ
  የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 12
  13 ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።
  14 ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት።
  15 እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።
  16 ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው።
  17 ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ፤
  [18] በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ።


  ትንቢተ ኢሳይያስ
  ምዕራፍ 64

  1፤ ሰማዮችን ቀድደህ ምነው ብትወርድ! ተራሮችም ምነው ቢናወጡ!
  2፤ እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጥ ዘንድ፥ አሕዛብም በፊትህ ይንቀጠቀጡ ዘንድ።
  3፤ ያልተጠባበቅነውን የክብርህን ሥራ ባደረግህ ጊዜ፥ ወረድህ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።
  4፤ ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላቸው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክን አልሰሙም በጆሮአቸውም አልተቀበሉም ዓይንም አላየችም።
  5፤ ጽድቅን የሚያደርገውን በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እነሆ፥ እነተ ተቈጣህ እኛም ኃጢአት ሠራን፤ ስለዚህም ተሳሳትን።
  6፤ ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
  7፤ ስምህንም የሚጠራ፥ አንተንም ሊይዝ የሚያስብ የለም፤ ፊትህንም ከእኛ ሰውረሃል፥ በኃጢአታችንም አጥፍተኸናል።
  8፤ አሁን ግን፥ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፥ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።
  9፤ አቤቱ፥ እጅግ አትቈጣ፥ ለዘላለምም ኃጢአትን አታስብ፤ እነሆ፥ እባክህ፥ ተመልከት፥ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነን።
  10፤ የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል፤ ጽዮን ምድረ በዳ ኢየሩሳሌምም ውድማ ሆናለች።
  11፤ አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰና የተዋበ ቤታችን በእሳት ተቃጥሎአል፥ ያማረውም ስፍራችን ሁሉ ፈርሶአል።
  12፤ አቤቱ፥ በውኑ በዚህ ነገር ትታገሣለህን? ዝምስ ትላለህን? አጥብቀህስ ታስጨንቀናለህን?
  እመአምላክ ቅድስት ድንግል ማሪያም እባክሽን ስምሽ ለጠላቶችሽ ይገለጥ

  ReplyDelete
  Replies
  1. “ይድኑ ዘንድ እውነትን ባለመውደድ የሚጠፉትን ሰዎች በሚያታልል በተለያየ የክፋት ሥራ ይመጣል፡፡ በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር በሀሰት እንዲያምኑ የስህተትን አሰራር ይልክባቸዋል” 2ኛ ተሰሎ 2፡10-11
   “ቃሌን መስማት እምቢ ብለው በልባቸው እልኸኝነት በመሄድ ሊያመልኳቸውና ሊሰግዱላቸው ሌሎችን ጣዖቶች የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝቦች ከጥቅም ውጭ ሆነው ይበላሻሉ” ኤር 13፡10
   “ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነው ለሚጠፉት ነው” 2ኛ ቆሮ 4፡3

   Delete
  2. አይ እናንተ እኔ መጠቀስ በጠቀስኩኝ ግን ጥቅስ ሰይጣንም ይጠቅሳል ለሰይጣን የሚያቅተው መተግበር ነው ማመን ሰይጣንም ያምናል ለሰይጣን ያቃተው በተግባር መስራት ወይ ምግባር አለመኖር ነው ስለዚህ ስለ ጠቅላላ ኑፋቃያችሁ ግን በእውነት እግዚአብሔር ይቅር ይበላቹ ዝንቱ መፅሓፍ ተፅሓፈ ለተግሳፀ ዚኣነ "ይህ መፃፍ የተጣፈው እንገሰፅበት ዘንድ ነው" አናንተ እና መሳዮቸችሁ ይህንን የምትመለከቱበት ግዜ በእግዚአብሔር ፍቃድ እስኪመጣ ድረስ አታምኑም ስለዚህ ከበረከቱ አለመካተታችሁ እንጂ እምቤታችንስ ነብያት ተተንብየውላት ሓርያት ሰብከውላት ሊቃውንት ያሰተማሩላት ልዩ ጽዮን ናት -----------------------በእውነት ግን እናንተ ስለ ሐወርያ ቅዱስ ጴጥሮስ አና ሁላቸው ሐውርያት ለእናንት ምናችሁ ናቸው አታውቁዋቸውም ምንም ምንም ምንም ለእናንተ ክርስቶስ ምነባችሁ ነው ምንም ምንም ምንም ለእናንት ክርስትና ምናችሁ ነው ምንምን ምንም ምንም ስለዚህ ከእናንት ስለ ክርስትና ከማውራት ይልቅ ማንንቱ ቶሎ በሚረዱት አሕዛብ መናገር ይሻላል ምክንያቱ አማኒ መስሎ ከሚኖር ኢአማኒ ከሀዲ ሁኑ የሚኖር ኢአማኒ ይሻላል እና

   Delete