Thursday, March 6, 2014

እምነት በአዋጅ ወይስ በእግዚአብሔር ቃል?

    Read in PDF
     
“እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው” ይላል ጳውሎስ በሮሜ 10፥17፡፡ እምነት በሰው አመለካከት ሊሆን አይችልም፣ እምነት ከተባለ እንደ እግዚአብሔር ቃል መሆን አለበት። ቤተ ክርስቲያን የምትባለው የክርስቶስ አካል ስትሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል አምነው የዳኑ ከነገድ ከቋንቋና ከሕዝብ ተዋጅተው አንድ የሆኑባት ጉባኤ ናት።

   የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም በመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አማካይነት በትንቢተ ኢሳይያስ ም 53 ትርጉም መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ ብላ በመጠመቅ የተመሠረተች ነበረች የሐዋ 8፥ 27-40። ከዚያም ቀስ በቀስ እየሰፋች መጥታ በቅዱስ ፍሬምናጦስ አማካይነት በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ህዳር 21 ቀን ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት ተብላ በአክሱም ተመሠረተች። አጼ ዘርዐ ያዕቆብ ህዳር 21ን የማርያም በዓል አድርጎ በታምረ ማርያም እስኪያውጅ ድረስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ማህበረ ጽዮን ሰማያዊት ተብላ የተመሠረተችበት ቀን በአል ነበር። ህዳር 21ን በተመለከተ የሚዘመረውን የያሬድ ቀለም (ዜማ) ድጓውን ብንመለከተው በአክሱም ስለተመሠረተችው ቤተ ክርስቲያን (ማኅበረ ጽዮን)የሚናገር እንጂ ስለ ድንግል ማርያም አይናገርም።

  ለምሳሌ፦ የሕዳር ጽዮንን ዋዜማ (በሐምስ) ብንመለከት "ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማሕቶት ኵለንታሃ ወርቅ አረፋቲሃ ዘዕንቍ ወመሠረታ ዘጽድቅ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ ትርጉም "ዘካርያስ የብርሃን ተቅዋም የሆነች፣ ሁለንተናዋ ወርቅ፣ ምሰሶዎቿ የዕንቍ መሠረቷ የጽድቅ የሆነች ቤተ ክርስቲያንን አየ፡፡” በማለት ዘምሯል (ዋዜማ ዘህዳር 21)። ቅዱስ ያሬድ እንዲህ ሲል የዘመረው በአክሱም ስለተመሠረተችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ነበር። በዚህ ታሪክ መሠረት ህዳር 21 የኢትዮጵያ ብሐራዊ በዓል መሆን ነበረበት። አጼ ዘርዐ ያዕቆብ ግን ይህን ታላቅ ታሪክ ለውጦ የማርያም በአል በማድረግ ታሪካዊ ደብዛውን አጥፍቶታል።

   ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ በብዙ ተግዳሮትም ቢሆን እያደገች መጥታለች የአሕዛብ ልማዶች፣ የአይሁድ ወጎች፣ የኒቆላውያን ሥራዎች፣ የእስልምና አስተምህሮዎች ዋና የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች ሲሆኑ እንደ ዮዲት ጉዲት ያሉ የውጭ ጠላቶችም ከባድ ፈተናዎች ነበሩ። እነዚህን ሁኔታዎች እየተቋቋመች በመውደቅና በመነሳት ላይ እያለች አጼ ዘርዐ ያዕቆብ ዘንድ ስትድርስ እስካሁን ድረስ ዋጋ እየከፍልንበት ያለውን ከባድ ስሕተት ፈጸመች። ይኸውም በእግዚአብሔር ላይ ሌሎች ደባሎችን አማልክት ደርባ ማምለክ መጀመሯ ነው። ዋናው የኢትዮጵያ የቁልቁለት መንገድ የተጀመረው እዚህ ላይ ሲሆን እስካሁን ድረስ ከዚህ ውድቀት ለመነሳት አልቻለችም። አገሪቱን የጣላት የቤተ ክርስቲያን ውድቀት ነው የሚል እምነት አለን፡፡ የቤተ ክርስቲያን ትንሣኤም የአገሪቱ ትንሣኤ ሊሆን እንደሚችል ጥርጥር የለንም።

   ከበርካታ አዋጆች ውስጥ በዘርዐ ያዕቆብ ድፍረት ከእግዚአብሔር ጋር እኩል እንዲመለኩ የታወጀላቸው ፍጡራን መካከል ማርያም እና መስቀል የመጀመሪያዎቹ ነበሩ። እስከ ዛሬም ድረስ የአጼ ዘርዐ ያዕቆብ አዋጅ ሳይሻር ማርያምና መስቀል ከእግዚአብሔር እኩል እየተመለኩ ነው። አዋጁን እንመልከት "ለእሉ ክልኤቱ ፍጡራን ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ እስመ ተአረዩ በክብሮሙ፤” ትርጉም "ለእነዚህ ለሁለቱ ፍጡራን ለመስቀልና ለማርያም ማለት ነው የፈጣሪ ምስጋና (አምልኮ) ይገባቸዋል በክብር እኩል ሆነዋልና፤” (መስተብቊዕ ዘመስቀልን ይመልከቱ)፡፡ እንግዲህ በዚህ አዋጅ መሠረት እስካሁን ድረስ ማርያምና መስቀልን እያመልክን መሆናችንን ማስረጃችንን እንደሚከተለው እናቅርብ።

ጸሎት ዘዘወትር ከሚለው ብንጀምር "እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐተ ስግደተ .. እሰግድ ለእግዝእትነ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢእየሱስ ክርስቶስ፤” ትርጉም "ለአብ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ፤ … ለወለደችውም ለእመቤታችን ለድንግል ማርያምም እሰግዳለሁ፤ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም እሰግዳለሁ፤” (ጸሎት ዘዘወትርን ይመልከቱ)፡፡ ስግደት አምልኮ ነው። እናም ከእግዚአብሔር ጋር ደብለን ለሁለቱም እየሰገድን ወይም ፍጡራንን እያመልክን እንደሆነ እናስተውል፤ ይህ ድርሰት በአጼ ዘርዐ ያዕቆብ የተድረሰ ነው።

ብዙ ጊዜ ምግብ ከተመገብን በኋላ የመገበንን አምላክ በምናመሰግንበት ጊዜ እነዚህን ሁለቱን ፍጡራን ማለት መስቀልና ማርያምንም እናመሰግናለን። "ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይደልዎሙ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ስብሐት ለእግዝትነ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ይደልዋ ለእግዝትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ፣ ስብሐት ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ይደልዎ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፤” ትርጉም "ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል፣ አዎ ይገባል፣ ለድንግል ማርያምም ምስጋና ይገባል፣ አዎ ይገባል፤ ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል፣ አዎ ይገባል።” (ሁልጊዜ ከማዕድ በኋላ የሚባል ነው)።

እግዚአብሔርን የምናመሰግንበት ቃልና መስቀልና እመቤታችንን የምናመሰግንበት ቃል ልዩነት የለውም። ይህም የሆነው "ለማርያምና ለመስቀል የፈጣሪ ምስጋና ይገባቸዋል፤ ከፈጣሪ ጋር እኩል ሆነዋልና፤” ሲል ዘርዐ ያዕቆብ ባወጀው መሠረት ነው። የእለት እንጀራችንን የሚሰጠን እግዚአብሔር ሆኖ እያለ ማርያምንና መስቀልን በርሱ ላይ ደርበን እንድናመሰግን መደረጉ ትልቅ ስሕተት ነው። ማርያምን መውደድ ሌላ ማርያምን ማምለክ ሌላ። ማርያምን መውደድ በቂ ሆኖ እያለ ማርያምን ከሥላሴ ጋር ማምለክን ምን አመጣው?
በሠርክ ጸሎት ጊዜ ምሕላ ወይም “አድኅነነ ሕዝበከ” ከተባለ በኋላ የጸሎት መዝጊያችን እንዲህ ይላል "ስብሐት ለእግዚአብሔር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ ስብሐት ለማርያም እመ አምላክ እግዝእትነ ወመድኃኒትነ፤ ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ ዕፀ መድኃኒት ኃይልነ ወጸወንነ፤” ትርጉም "እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል፤ የአምላክ እናት ለሆነች ለእመቤታችን ለመድኃኒታችን ለማርያምም ምስጋና ይገባል፤ መድኃኒትነት ላለው ዕንጨት ኃይልና መጠጊያ ለሆነን ለክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል፤” (ከማንኛውም ጸሎት በኋላ ሁልጊዜ የሚባል ነው)።

ልብ እንበል ይኸኛው የምስጋና ቃል እግዚአብሔርን ፈጣሪ፣ ማርያምን መድኃኒታችን፣ መስቀልን ኃይላችንና መጠጊያችን ይላቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይላችን እና መጠጊያችንም ያው እርሱ ብቻ መሆኑን አረጋግጦ ይናገራል። ታዲያ ማርያም መድኃኒታችንን የወለድችልን የመድኃኒታችን እናት እንጂ እንዴት መድኃኒታችን ትሆናለች? መስቀልም መድኃኒታችን የተሰቀለበት ዕንጨት እንጂ እንዴት መጠጊያችን ሊሆን ይችላል? ምስጋናውንስ ጌታ ብቻ መውሰድ አይገባውምን?

ብቻ በየአንዳንዱ ጸሎታችን ላይ ሁለቱም ማለት መስቀልና ማርያም ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ነው የሚመለኩት። የኪዳን ጸሎት ብምናቀርብበት ጊዜም ማርያምና መስቀል አብረው ይለመናሉ፡፡ “ሰላም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወፍቅራ ለእግዝእትነ ድንግል ወላዲተ አምላክ ሞገሰ መስቀሉ ወሀብተ ረድኤቱ የሀሉ ምስሌነ ለዓለመ ዓለም አሜን” ትርጉም "የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ሰላም፣ የማርያም ፍቅር፣ የመስቀሉ ሀብተ ረድኤት ከኛ ጋር ይሁን” (የኪዳን መግቢያ)፡፡ ምን አልባት መስተብቍዕ ከተባለ ማርያምና መስቀልንም እንዲህ እያልን እንለምናለን፤ "ወካዕብ ናስተብቍዖ ለዕፀ ቅዱስ መስቀል” “ወካዕበ ናስተበቍዓ ለእግዝእተ ኵልነ” ትርጉም "ቅዱስ መስቀልን ዳግመኛ እንማልደዋለን፣” “የሁላችን እመቤት ማርያምን ዳግመኛ እንማልዳታለን” ማለት ነው (መስተብቍዕ ዘመስቀልንና ዘማርያምን ይመልከቱ)። መስቀል ዕንጨት ነው፤ መስቀልን እንማልደዋለን ስንል ወደ መስቀል መጸለያችን ነው፤ እንዴት ሊሰማን ይችላል? መስቀል አምላክ ሆኖ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ስለ ታወጀ እንጂ ሌላ ምንም መልስ የለም።

እንግዲህ ከዚህ በላይ ያቀረብነው ማስረጃ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ያወጀው የማርያምና የመስቀል አምልኮ እስከ አሁን ድረስ አለመሻሩን ሕዝብ በማያውቀውና በማይረዳው ሁኔታ በግእዝ ተሸፍኖ ባማርኛም ቢሆን ማስተዋል የለም ከእግዚአብሔር ጋር ሁለት ጨምረን አያመልክን መሆኑን እናስተውላለን። ደቂቀ እስጢፋኖስ ይህን አዋጅ በመቃወማቸው ነበር ምላሳቸው ተቆርጦ እስከ አንገታቸው ድረስ ተቀብረው የከብትና የፈረስ መንጋ ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ የተነዳባቸው። (ታሪኩን ከታምረ ማርያምና ከፕሮፌሰር ጌታቸው ትርጉም በሕግ አምላክ ከሚለው መጽሐፍ ያንብቡ)፡፡

ፕሮፌሰር ጌታቸው ባሕረ ሐሳብ በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 336 ላይ "በዘርዐ ያዕቆብ ዘመን ያልነበረ ክርስቲያን እግዚአብሔርን ያመሰግናል” ብለዋል። ዛሬስ ዘርዐ ያዕቆብን ተክቶ እየሰራ ያለውን ማኅበረ ቅዱሳንን የሚመጣው ትውልድ ምን ይለው ይሆን? አሁንም ቤተ ክርስቲያን ይህን ገዳይ አዋጅ በአዋጅ እስካልሻረችው ድረስ አንዳንድ ቃላትን በማረም ብቻ ለውጥ አታመጣም፣ መጻሕፍት ሲታረሙ አዋጁን ተከትሎ የመጣው ልምምድም አብሮ መታረም አለበት። ይህ እርምጃ ቶሎ የማይወሰድ ከሆነና ጥያቄውን የሚያነሱ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን ማሳደዱ ከቀጠለ ግን ገና ያልተነኩ ጆሮን ጭው የሚያደርጉ አጋንንታዊ ምስጢራትን ወደ አደባባይ ማውጣታችን እየቀጠለና እየባሰ ይሄዳል።

በሚቀጥለው ጽሑፌ አባ ገብርኤልና አባ ሚካኤል የሚባሉ የግብጽ ጳጳሳት ካፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያን እድገት ወደ ኋላ ለማስቀረት ገበሬውን እንዳይሠራ በማውገዝ በኢትዮጵያ ላይ የፈጸሙትን ተንኮል አቀርባለሁ። ወገኔ ንቃ!!!!!!!
                                           ተስፋ ነኝ

36 comments:

 1. "እሰግድ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐተ ስግደተ .. እሰግድ ለእግዝእትነ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢእየሱስ ክርስቶስ፤” .... ይህ ድርሰት በአጼ ዘርዐ ያዕቆብ የተድረሰ ነው።"

  Is this not prepared by 318 liqaunts????

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን ቢሆንስ ምን ለውጥ ያመጣል? ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የሚጣላ ትምህርት ሁሉ ከአጋንንት ነው፡፡

   Delete
  2. I am asking this because the writer said that "ይህ ድርሰት በአጼ ዘርዐ ያዕቆብ የተድረሰ ነው" I agree if it is wrong it is wrong.

   Delete
 2. ebakachihu gubae yiterna ke likawuntu gar tekerakeru. Endaw ye belog tektatay enchichoch atasitu!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ደነቀ ትገርማለህ፡፡ በአንድ በኩል አቅምህን ማወቅህ ጥሩ ነው፡፡ አላስተዋልከውም እንጂ አንዱ የመከራከሪያ መድረክ እኮ ይኸው ብሎግ ነው፡፡ በተስፋ የቀረበው ሐሣብ ትክክል አይደለም የሚል ካለ በጨዋ ደንብ ሐሣቡን ይግለጽ ሁሉም የተሰማውንና የሚያምንበትን መከራከሪያ ያቅርብ፡፡ አንተ ያልከውን የጉባኤ ክርከር ግን ሊቃውንቶቻችን የሚያዘጋጁ አይመስለኝም፡፡ ሌላው ቀርቶ ባለፈው የጅምላ ውግዘት ሲያስተላለፉ በጉባኤ ለመነጋገር መች በሩን ከፈቱ? በሩን ቢከፍቱ የሚከተላቸውን ስለሚያውቁ በሩን ዘግተው አውግዘናል አሉ፡፡ ስለዚህ ወዳጄ ሞን አትሁን ይልቅስ ከእንጭጭነት ወደብስልነት ለመሸጋገር እንደ ተስፋ ያሉ ሊቃውንት የሚጽፉልህን መርምርና በቃሉ አረጋግጠህ ተቀበል፡፡

   Delete
  2. Always I am surprised how you twist history, and Word of God just according to your will. I will be delighted if you present What is Church teaching from Apostles era,not just gossip ,but historical and biblical facts. Any way may God reveal your hidden agenda to you and your follower.

   Delete
 3. Wendin Tesfa,

  I hope you read Abune Goigorios's 'Kiristna BeAlem Medrek Book. Gubae Efeson, in 431 EC was based on NisTros's thaugh regarding St Mariam. His examples on St. Mariam is the same with today's protestant thaught. Read it from PP 131-146.

  ReplyDelete
  Replies
  1. መቼ ይሆን አእምሮአችሁን የምታሰሩት እንዲሁም የምትሰሩበት? እስኪ አሁን ንስጥሮስንና ከማርያምና ከመስቀል አምልኮ ጋር ተያይዞ የተነሳውን ነጥብ ምን አገናኛቸው? ተስፋ፣ ማርያም ወላዲተ አምላክ አይደለችም አላለም፡፡ እርሱ ያለው ማርያምን በማክበር ስም አናምልካት ነው ያለው፡፡ እርሱ ማስረጃዎችን ጠቅሶ ያቀረበልን እውነት በትኩረት ሊመረመርና ቤተክርስቲያን አንድ ውሳኔ ላይ ልትደርስበት የሚገባ ነጥብ ነው፡፡ ዘወትር በጸሎትም ሆነ በምህላ አምልኮትን ለማርያምና ለመስቀል እያጋራን ነው፡፡ ይህ ደግሞ ቅልጥ ያለ አምልኮተ ጣኦት ነውና መስተካከል ሳይሆን መወገድ ነው ያለበት፡፡ ስለዚህ ይህን ሐቅ ውሃ በማይቋጥር መከራከሪያችሁ ለማስተባበል የምትሞክሩ ማቆች እባካችሁ እውነትን አትቃወሙ፡፡ ብትቃወሙ ግን ለእናንተ ነው የሚብስባችሁ፡፡ ስለዚህ ይህን እውነታ ከግምት ሳታስገባና አእምሮህን ሳታሰራ ዘለህ ወደንስጥሮስ የሄድከው ሰው ተመለስ!!!

   Delete
  2. Hello,

   Why do you think every question is from MK???? I am not MK. Stop judging everyone who raise question is MK and stop cursing. Lets be respectful eachother. You think you praise God by cursing others????

   Delete
 4. ተው ተስፋ አተውም ጉድ ማፍላት ሙያህ ሆነ በርታ

  ReplyDelete
 5. I am sure this writer is a former educated deacon priest or monk. He knows very well what he is writing. Few discrepancies but well written.

  ReplyDelete
 6. ወንጌላዊትMarch 7, 2014 at 12:17 AM

  እኔ የሚገርመኝ የማቅ ሰዎች ሁል ጊዜ በአግባቡ መልስ ከመስጠት ይልቅ ጆሮ ቆራጭ እንደሚባለዉ ዓይነት ፕሮቴሰታንት ስለሆናችሁ ነዉ ማለት ይቀናቸዋል፡፡ አሁን የተባለዉ ጌታችን ደባል አምልኮ አይፈልግም ክብር ምሥጋና ዉዳሴና ስግደት ለሱና ለርሱ ብቻ ይሁን አሜን ፡፡ ይህ ሲባል ግን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የሚገባዉን ክብርና ፍቅር ማሳነስ አይገባም፡፡ እንኩዋን እኛ ከምንም የማንገባ ፈጣሪያችን ራሱ መርጡዋታል አክብሮአታል፡፡ እኛ በተለያየ መንገድ አክብሮታችንን መገለጥ እንችላለን፡፡ መጀመሪያ የምሥራች ይዞ ለመጣ ለገብርኤል ያሳየችዉን ትህትናና እምነት በማድነቅ፣ ትንሽ ብላቴና ስትሆን ከጌታ ጋር በመሰደዱዋ ያየችዉን መከራ ፣ በጌታ ልደት ቀን ጋር በቤተልሔም እናስባታለን፣ ልደቱዋን በማክበርና እኛን ለማዳን እርሱዋን መርጦ ከሥጋዋና ከነፍስዋ ነስቶ ሰዉ መሆኑ ባሳየችዉ መሰጠትና ትህትና ስለሆነ የሚገባትን ሰዋዊ ምሥጋና እንሰጣታለን፡፡ ነገረ ግን ይህንን ሁሉ ላደረገ ጌታችን አምልኮ ምስጋና ይገባዋል ብለን የልደቱዋን ቀን ማሰበ ይቻላል፡፡ በምንም መልኩ ከአምልኮ ያልተናነሰ ና ከጌታ ጋር ፉክክር ዉስጥ እርሰዋን ማስገባት የመጨረሻዉ ወንጀል ነዉ፡፡

  ReplyDelete
 7. Mezmur32:1"le qenoch mesgana yigebal" Qedus Dawit be Mesfes Qedus temerto selale enamesegenachewalen.Dengel Maryam sew yemehon mesttir yetegeletsebat selehone,yeteseqelew sega,yefesesew dem kersua selenesaw enamesgenatalen,ensegdlatalen.Qedus paulos endalew,"getachenn yemayiwed binor yeteregeme yihun" endale ke qedus paulos gar enatunem yemayiwed yeteregeme new enelalen.qedus paumos ke geraye mesqel wuchi lela temket kene yiraq endale,egnam be mesqelu lek ende qedus paulos enmekalen.mesqelen mamesgen,le mesqel mesged malet eko bigabachihu,getachen bemeqel lay hono yefetsemewun hulu makber,mewded,megelets malet new."le elu keletu feturan (fatariwoch aydelum eyaleh eko new) sebhate fettari yidelomu (malet mesgana yigebachewal ale enji amleko alalem),bekebr and nachew yalew Dengel Maryam ena Qedus Mesqelen hono sale attameh ke Amlak gar new bileh teregomkew.ante ferenjoch endastemaruh eko qenun mulu sewochen amesgenalehu(thank you) setel tewul yelem,egna gen Dengel Maryamen ena Qedus Mesqelen enamesegenalen (thank you) malet enfelgalen,enameseganachewalen.egnan tewen.Getachen"enanten yeteqebele,enen teqebele...""enanten yetale enen tale...) yalew bigebah endih atenagerem nebere.leb yiseteh.

  ReplyDelete
 8. ደንቆሮ መናፍቅ

  ReplyDelete
 9. ከሁለት ዛፍ ያረፈች ወፍ ሁለት ክንፉዋን ትነደፍ!!
  ጸሐፊው ማረፊያ ያገኘ አይመስልም፡፡የእኛ ነው እንዳንለው የቤ/ክ ፈተናዎችን ሲዘረዝር ፕሮቴስታንቲዝምን ዘሎታል፡፡ጠረጠርነው፡፡ የእነሱ ነው እንዳንል በጉባኤ ቤታችን ያለፈ ይመስላል፡፡ የቤታችንን መጻህፍት ይቆነጻጽላል፡፡ ሁለት ዛፍ ላይ ያረፈ ወፍ!!ምናችን ሞኝ!!የድርሻችንን እንነድፈዋለን፡፡ ጀመርን…..ታዲያ እንደ አመጣጡ ለመመለስ ስንል እሱ የጠቀሳቸውን ብንጠቅስ ፍርድ የለብንም!!ተመሳሳይ ሚዛን መጠቀም ግድ ነው!!ቀጠልን….
  1. የቅ/ያሬድ ድጓ: ህዳር 21’ን ‘ለማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት’ እንጅ ለእመቤታችን አይሰጥም ቢለን ደነቀን፡፡ “በአይቴ ሀሊፈኪ ድጓ ተምህርኪ” አልነው!!ድጉዋውስ በግልጽ…. አመ ፳ ወአሀዱ ለህዳር እግዝእትነ ማርያም…ነው የሚለው በቀይ በተጻፈ አርእስቱ፡፡ አንባቢ እንዳትስት!!የህዳር ማርያምን ድጓ ገጽ 92 ተመልከት!!የዕለቱ(21) ታሪክ ማጠንጠኛ ታቦተ ጽዮን በኦሪቱ ዘመን ዳጎን በተባለ ጣኦት ላይ ስላደረገቸው ተአምር ሲሆን መምህራን ታሪኩን በሐዲስ ኪዳኑዋ አማናዊት ጽዮን በእመቤታችን ለውጠው ያከብሩታል፡፡ ቅ/ዳዊት በመዝ 131 ቁ 13….እስመ ኃረያ እ/ር ለጽዮን ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማህደሮ ዛቲ ይእቲ ምእራፍየ ለዓለም….ትርጉም…እ/ር ጽዮንን መርጦአታልና ማደሪያውም ትሆን ዘንድ ወድዶአታልና እንዲህ ብሎ፡ ይህች ለዘላለም ማረፊያየ ናት….ይህ ትንቢት ቀድሞ ለጽዮን ቢነገርም ፍጻሜው ለእመቤታችን ነው፡፡ ‘ለዘላለም ማረፊያየ ናት’ መባሉም ዘላለም ‘ወላዲተ አምላክ’ ስትባል የምትኖር መሆኑን ለማሳየት እንደሆነ አባቶች ተርጉመውልናል፡፡ ከዚሁ ከህዳር ማርያም ድጉዋ ትንሽ እንመርቅ….ዘካርያስ ርዕየ ተቅዋም ዘወርቅ፣ዘሕዝቅኤል ነቢይ እጹት ምስራቅ፣ለመሰረትኪ የሐቱ ዕንቁ፣ሰአሊ ለነ በአሚን ንጽደቅ…ትርጉም…ዘካርያስ ያየሽ የወርቅ ተቁዋም(መቅረዝ)፣የሕዝቅኤል የተዘጋች በር፣መሰረትሽ የሚያበራ እንቁ፣ማርያም ሆይ በማመን እንድንጸድቅ ለምኝልን!!አይ ያሬድ!!ባንተ አላፍር!! አልፎ ሂያጅ ሁሉ እንዳይበጥሰው አድረግህ ኦሪቱን ከሀዲስ ቀምመኸዋል!!
  2. በነገራችን ላይ ጸሀፊው የህዳር 21 ‘ዋዜማ’ ብሎ የጠቀሰው.…ዘካርያስ ርእየ… ዋዜማ ሳይሆን ነግሥ ነው፡፡ የህዳር 21 ዋዜማ…ኢየኃድጋ ለምድር ዘእንበለ ካህናት ወዲያቆናት….ነው፡፡ የእለቱ በሀምስም ‘ዘካርያስ ርእየ’ ሳይሆን… ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዚእ ኃረያ…(ዘይቤው ቅርብና ሩቅን ቢቀላቅልም) ትርጉሙ….ጌታ የመረጠሸ ማርያም ሆይ ለምኝልን… የሚለውን ስረዩን ነው የሚያዘው፡፡ ስለሆነም በህዳር 21 የቅ/ያሬድ ድጓ መሰረት ዕለቱ እመቤታችን የምትዘከርበት ስለመሆኑ አንገት እስከመስጠት እመሰክራለሁ፡፡ አንተ ‘ማኅበረ ጽዮን ሰማያዊት’ ብለህ ያነሳሀው ዕለት በድጉዋው መሰረት የሚውለው ህዳር 21 ቀን ሳይሆን ነሀሴ 10 ቀን ነው፡፡ ማየቱን ከፈቀድክ….ደብረጽዮን ዘአፍቀረ፣ኪያሃ ዘሰምረ ሀገረ…የሚለው ዓራራይን ጨምሮ ስለ ምድራውያንና ሰመያውያን ቅዱሳንና መላእክት ህብረት የሚዘክርበትን የቅ/ያሬድ የማህበር ድጉዋ ከገጽ 382 ጀምሮ ከዕብ 12 ቁ 22 ጋር እያመሳከርክ ተመልከተው፡፡ ሁለት ዛፍ ላይ አርፈህ አታደናግር፡፡ አንዱዋን ጠበቅ አድርግ!!
  3. ወደክብረ መስቀልና ነገረማርያም እንመለስ!!ቅ/ያሬድ በህማማት ጾመድጓ….ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ ….ሲል አስቀድሞ በመንፈስቅዱስ አነሳሽነት የደረሰውን ዛሬ ደርሳችሁ ከዘርዓያዕቆብ አለመስማማቱን በማየት ብቻ የእኛ ነው የምትሉት የጉንዳጉንዲው አባእስጢፋኖስም ቅ/ያሬድን ጠቅሶ…ስለዚህም ከእኛ በፊት የነበሩ መምህራን እንዳስተማሩን ለመስቀልህ እንሰግዳለን….ሲል አጽንቶታል፡፡ ከዛም በፊት ዳዊት በመዝ 59 ቁ 4…ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሀቸው …በማለት ስለመስቀል ትንቢት ተናግሮ ነበር፡፡ ይሄው ቅ/ዳዊት በመዝ በመዝ 131 ቁ 7….ወንሰግድ ውስተ መካን ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ…ትርጉም….የጌታችን እግር በሚቆምበት ስፍራ እንሰግዳለን ብሎ ተቀኝቱዋል፡፡ ታዲያ ለቆመበት ትቢያ ከሰገድን ደሙ ለተንጠባጠበበት መስቀልና 9 ወር ከ5 ቀን በማህጸን ለተሸከመችው ማህደረ መለኮትማ እንዴታ!!እንሰግዳለን እንጅ!!የዳዊት ጌታ በቆመበት ቦታ መስገድ ባዕድ አምልኮ አልተባለም!!የዕኛም የአክብሮት ስግደት እንጅ የአምልኮ እንዳልሆነ ጆሮአችሁ እስኪረግብ ነግረናችሁዋል!!ግን እናንተ መስማት የምትፈልጉት አስቀድማችሁ ስለእኘ በውስጣችሁ ያስቀመጣችሁትን ብቻ ስለሆነ ንግግራችን አይሰርጻችሁም!! “አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም” ነው ነገሩ!!ጭራሽ ለእመቤታችንና ለመስቀል መስገድን ያመጣው ዘርዓያዕቆብ ነው እያላችሁ ታስቁናላችሁ !!ወደው አይስቁ !!የእኛስ ይሁን የሌላው ሀገር ኦርቶዶክስና ካቶሊክ ክርስቲያኖች ለሁለቱ ፍጡራን ስግደትና ውዳሴ የሚያቀርቡት በዘርዓያዕቆብ ተገደው ነው ልትሉን ነው?? እንዴ!!እረ ተው!!እየተስተዋለ!!
  ይቀጥላል.....

  ReplyDelete
 10. …..የቀጠለ
  4. ልምጣልህ ወደ መስተብቁዕ በእንተ መስቀል!! ጸሀፊውና ብዙ ከኦርቶዶክሳዊት ሃይማኖት ያፈነገጡ ቤተክህነት ቀመስ ሰዎች ለእዛኛው ቤት ካደሩ በሁዋላ ተሻምተው የሚያነሱዋት ጥቅስ…ለእሉ ክልኤቱ ፍጡራን ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ…የምትለዋን የመስቀል መስተብቁእ ሐረግ ነው፡፡ ሌሎቹን አያነሱዋቸውም፡፡ ሁሉንም መስተብቁኦዎችና የኪዳን ጸሎቶች ተቀብለው ይህቺ ብቻ ቅር ካለቻቸው አስተዋዮች ናቸው ማለት ነው!!ግን ውሸታቸውን ነው!!እንደውም ኪዳንና ት/ኅቡአት አይነት ድርሰቶች አጥብቀው ስለክርስቶስ ስለሚተርኩና ይሄ ደግሞ ‘ኦርቶዶክስ ክርስቶስን አትሰብክም’ የሚለውን ልፈፋቸውን ስለሚሰብር ይሸሹዋቸዋል!!ንግባዕኬ ኀበ ጥንተ ነገር!!እንግዲህ ጸሀፊያችን…ስብሐተ ፈጣሪ ይደልዎሙ…ከሚለው ቃል በፊት ያሉትን ሐረጋት ማየት ሳይሆን ጫፍ ይዞ መላውን ጸሎተ ኪዳን ማጣጣል ነው የፈለገው!!ከሁዋላ ያሉት ቃላት ማየት አልፈለገም፡፡ ላስታውሰው፡፡ የመስተብቁዕ በእንተ መስቀል ደራሲ ስለእመቤታችን ስግደት አመክንዮውን ሲያስቀምጥ….እስመ ነስአ ሥጋ እምሥጋሃ እግዚአብሄር ፈጣሪሃ ወረከብነ ንህነ መድኃኒነ እምኔሃ….ትርጉም…እ/ር ፈጣሪዋ ከስጋዋ ስጋ ነስቶዋልና፣መድኃኒታችንን ከእሱዋ አግኝተናልና….በማለት ፈጣሪ ሳትሆን ፍጡር መሆኑዋን እንደሚያውቅ አሳውቆናል!!መስቀልን በሚመለከትም…እስመ ቀደሶ በደሙ ወአኮ በደመባዕድ….ትርጉም…በባዕድ(በፍጡር) ደም ሳይሆን በገዛ ደሙ ቀድሶታልና….በማለት ስግደቱ በዕለተ ዓርብ ከጌታ ጎን በቀራንዮ አደባባይ በመስቀሉ ላይ ስለተንጠባጠበው ደም እንጅ በዕለተ ሰሉስ(ማክሰኞ)ለተፈጠረው ዕጽ እንዳልሆነ ተናግሩዋል፡፡ደራሲው በህሊናው ጳውሎስ በቆላ 1 ቁ 20…በመስቀል ባፈሰሰው ደሙ ሰላምን አደረገ…ያለውን ለመትርጎም የሚንደረደር ረቂቅ አዕምሮ ያለው እንጅ አንተ እንደምትለው ፈጣሪን ከፍጡር መለየት ያቃተው ጨዋ አይደለም!!አባቶቻችንም መስቀልንና እመቤታችን ስለማምለክ ነግረውን አያውቁም!!እኛም የምናመልከውን ከምናለብረው ለይተን እናውቃለን!!አጉሉን ወሬ ከእናንተ ነው የምንሰማው!!አትቆንጽል!!ሙሉውን የድርሰቱን ይዘት አይተህ አቃንተህ ለመተርጎም ሞክር፡፡ በ2ኛ ቆሮ 3 ቁ 6 እንደተጻፈው ፊደል እንዳይገድልህ ቃላትና ሐረግ በመምዘዝ ለመደምደም የሚፋጠን ፊደላዊ አትሁን!!መተርጎም ካልቻልክና ቃሉ ሁሉ በቁሙ ይፈታ ካልክ በዘፀአት 7 ቁ 1 ለፈርኦን አምላክ የተባለውን ሙሴን ወደማምለክ አይነት የክህደት አዘቅት ትገባለህ፡፡ በዚህ ፊደላዊነትህ ጌታ ለሐዋርያው…በጎቼን ጠብቅ….ያለው እንደ ደደገኛ በግ አርቢ ሁን ሊለው ፈልጎ ነው ብለህ እንዳትተረጉም እፈራለሁ!!

  5. የእመቤታችንን መድኃኒትነት ከዘርዓያዕቆብ ሺህ አመት ገደማ ቀድሞ የተነሳው ቅ/ያሬድ.…ዘኮንኪ ዕፀ-ሕይወት በዲበ ምድር ፍሬኪኒ ፍሬ-ሕይወት ውእቱ…ትርጉም…በምድር ላይ የህይወት ተክል ሆንሽ፣ፍሬሽም የሕይወት ፍሬ ነው….ሲል ምዕራፍ በተሰኘ ድርሰቱ ውስጥ አንቀጸብርሃን ብሎ በሰየመው ርእስ ገልጾታል፡፡ ዋናው መድኃኒት ፍሬው መሆኑን ሳንስት ፍሬውን የተሸከመችውን ተክልም መድኃኒት እንላታለን!!ተክሊቱ ፍሬውን ስላስገኘች!!በየጸሎቱ መሃል የስሙዋ መነሳት ያሳደረብህን ቅሬታና ይሄን ነገር ዓጼ ዘርዓያዕቆብ ያመጣው እዳ አስመስለህ ያቀረብከውን በሚመለከትም ይሄው ይደግፈኛል ብለህ የጠቀስከውና እሱ ግን ቢያገኝህ አላውቅህም የሚልህ ቅ/ያሬድ በዚሁ በአንቀጸብርሃን ‘ለኪ ይደሉ’ ላይ….ስብሐት ለኪ ኦ ወላዲተ እግዚኣ ኩሉ….ትርጉም…የሁሉ ጌታን የወለድሽው ሆይ ምስጋና ይገባሻል….ይልብሃል፡፡ ታዲያ እኛም….እሰግድ ለእግዝእትነ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ፣እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ስብሐት ለእግዝእትነ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ፣ ስብሐት ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ…እያልን ስንዘምር አንድም የቀደሙ አባቶች ያስቀመጡልንን ስርዓት በመከተል በመሆኑ፣ሲቀጥልም እኛም መጻህፍትን መርምረን እንዳየነው ቅድስና ላለው ፍጡር የጸጋ ስግደት፣ የጸጋ ምስጋናና የምልጃ ጸሎት ማቅረብ ባዕድ አምልኮ ነው የሚል ጥቅስ ስለሌለ አልተሳሳትንም!!የጸጋ ስግደትና የአምልኮ ስግደት ልዩነት የሚምታታባችሁ ካላችሁ ህጹጽ ምሳሌ ከሆነላችሁ እንደ ጸሐይና ጨረቃ ማለት ነው!!ብርሃን ለፀይ የባህርዋ የራሱዋ ነው፣የጨረቃ ብርሃ ደግሞ ከፀሀይ የተገኘ ስለሆነ የባህርይ ሳይሆን የስጦታ- የጸጋ ነው!!እኛ ጌታን እንደፀሐይ፣በሃይማኖትና ምግባራቸው ቅዱሳን የተባሉትን ደግሞ ከጌታ የተቀበሉትን ብርሃን እንደሚያንጸባርቁ ጨረቃዎች ነው የምናያቸው!!ይብቃን!! ስለእመቤታችን ምስጋና የደረሱትን ከዘርዓያዕቆብ የቀደሙ ሊቃውንትን ዘርዝረን አንዘልቃቸውም!!ከ306 ዓ.ም እስከ 373 ዓ.ም የኖረው ቅ/ኤፍሬም የደረሰላት በትንቢተ ነቢያትና በምሳሌ ሐዋርያት የታጀበው ውዳሴ ማርያምም ብሉይና ሐዲስ የተቀመሙበት ነው - ከዘርዓያዕቆብ የቀደመ - በጣም የቀደመ!!
  6. በነገረ ማርያምና በክብረ መስቀል ጉዳይ ማኅበረቅዱሳንን ለማሸማቀቅ ትሞክራለህ!!ማኅበረቅዱሳን የጨመረውም የቀነሰውም ነገር የለም - ይሄን የማድረግ ፍላጎትም መብትም የለውም!!የነበረው እንዳይከለስ ከሌሎች የቤ/ክ ክፍሎችና መምህራነ - ወንጌል ጋር አብሮ መስራት ስላለበት ይሰራል - በዚህም 200% አብረነው እንቆማለን!!ማኅበሩ ከመቶ አመት በሁዋላ እንዳያፍር ስላልከውም የእኛ ሃይማኖት እንደ እናንተ በየመቶ አመት የሚለዋወጥ ሳይሆን በአለት ላይ የተመሰረተና እስከ ምጽአተ ክርስቶስ ጸንቶ የሚኖር ስለሆነ እድሜ ሰጥቶህ የዛሬ መቶ አመት ብታየውም እንደነበረ እንደምታገኘው አረጋግጥልሀለሁ!!በለውጥ ህግ የሚመራው ሳይንስ እንጅ የማይለወጠው ፈጣሪ ጋር የምንገናኝበት እምነትና ሃይማኖት አይደለም!!
  7. ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ ላይም ሳታስፈቅድ ልተመረጎዝ ትፈልጋለህ!!በዚህ አስተሳሰብህ የሚያስጠጉህ አልመሰለኝም!!ስለእመቤታችን ምን እንደሚሉ ካልሰማህ የአባ ባሕርይ ድረሰቶች ከሚለው መጽሀፋቸው ገጽ 8’ን ልጥቀስልህ…ለትምህርት ወደ ውጭ አገር ስሄድ እናቴ ልጄ በሰላምና በጠየና ከተመለሰ ከደጅህ አምጥቼ አሳልመዋለሁ ብላ የተሳለቸው ለዶፋ ሚካኤል መሆኑ ቀርቶ ለጉራምባ ማርያም ቢሆን እመርጥ ነበር….ስለት ለመስማቱስ ቅድስት ድንግል ማርያም(ባለምህረት ኪዳኑዋ)ትበልጣለች….ሲሉ በእመቤታችን ያላቸውን ትምክህት ገልጸዋል፡፡ እንግዲህ ማስረጃ ብለህ የጠቃቀስካቸው ቅዱሳንም ሆኖ ግለሰቦች ካንተ ጋር አልቆሙም!!ለሚወላውለው ልብህ ማረፊያ አላገኘህም!!አውቃለሁ!! ኢየሱስ አሳርፎኛል ትላለህ!!ታዲያ እሱ ካሳረፈህ የሰው ቤት ገብተህ ለማንጎዳጎድ አትሞክራ!!ባለህበት ጽና!!ወደሁዋላ አትይ!!እሱ ወላዋይነት ነው!!ያለበለዚያ…ከሁለት ዛፍ ያረፈች ወፍ.ሁለት ክንፉዋን ትነደፍ….እያልን እንሳለቅብሃለን - ቃለ እ/ር ጠቅሰን ተዋሕዶ ንቦች እንነድፍሃለን!!
  ስብሐት ለእግዚአብሄር ኪያነ ዘፈጠረ ከመ ናምልኮ!!
  ስብሐት ለማርያም እመአምላክ እግዝእትነ ወመድኃኒትነ!!
  ስብሐት ለመስቀለ ክርስቶስ እፀ መድኃኒት ኃይልነ ወጸወንነ!!


  ReplyDelete
  Replies
  1. Hiruy, Egziabhere yistilign. I don't know why they worry about EOTC belief if they are not belong to it. This to confuse the true Christian in EOTC.

   Delete
  2. ህሩይ አትሳሳት
   የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ለማሪያም አይሰግዱም፡፡
   የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተከታዮችም ለማሪያም አይሰግዱም፡፡
   ከፈለክ ይህንን ዌብ ሳይት አንብበህ ማረጋገጥ ትችላለህ፡፡ http://lacopts.org/orthodoxy/our-faith/the-holy-virgin-mary/

   ህሩይ አንተ ሁል ጊዜ ከምትሰጣቸው አስተያየት ብዙ ተምሬበታለሁ፤ ስለዚህ አስተያየተት ከመስጠት አትቆጠብ፤ ከእኛ አትራቅ/አርምሞ ለጊዜው ይቅርብህ ከእኛ ጋር ሁን/
   ይህንን ብሎግ ስላዘጋጁልን አባ ሰላማዎች ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
   ወንድሜ ደህና ሁን

   Delete
  3. ወንድሜ ማሙሽ እኔ አልተሳሳትኩም!!
   ካቶሊኮችና ኦርቶዶክሳውያን Worship የሚለውን ቃል በሁለት ይከፍሉታል!!worship of adoration and worship of veneration ሲሉ!! Worship of adoration ለፈጣሪ የሚቀርበውን ውዳሴና ሰጊድ ማለትም እኛ የባህርይ ስግደትና ውዳሴ የምንለውን ሲወክል worship of veneration ደግሞ ለቅዱሳን በስዕላቸው ፊት የምናቀርባቸውን የጸጋ ውዳሴዎችና ስግደቶች ያመላክታል!!ራሱ Veneration የሚለው ቃል በግሪኩ proskunesis በእንግሊዝኛው bowing down ማለትም ወደ አማርኛ ስንመልሰው ሰጊድ/ስግደት የሚለውን የአማርኛ አቻ ትርጉዋሜ ይይዛል!!
   ስለዚህ የግብጽ ኦርቶዶክሳውያን ወንድሞቻችንም ሆነ ካቶሊካውያን ቅድመ ስዕልና ቅድመ መስቀል ስለሚያቀርቡት ተማጽኖ፣ውዳሴና ሰጊድ ማወቅ ስንፈልግ ቁልፉ ቃል Worship ሳይሆን veneration ነው!! Veneration for/to Saints, veneration for/to holy cross, veneration for/to S.t Mary እያላችሁ Google’ን መጎልጎል ነው!!ታዲያ ፊደል እንዳይገድለን ጠንቀቅ!!
   ከላይ በተጠቀሰው ቃል ሰርች ካደረጋችሁ ከእኛ የሚስማማውንና ዓጼ ዘርዓያእቆብ ሳይፈጠር በግብጽ ኮፕቶችና በካቶሊካውያን ለመስቀልና ለእመቤታችን የተሰጣቸውን የክብር ስፍራ ታገኙታላችሁ!!
   ወንድሜ ማሙሽ ለአስተያትህ ያለኝ ክብር ይሄው…. በአድንኖ ክሳድ ይገለጻል!!

   Delete
 11. ዘመናቸንን ሁሉ ጨለማና ጨለምተኝነት ፈጀው! ቸሩ እገዚአብሔር መቼም ምህረት ያድረግልን! ዛሬ ግን ይኼ ትውልድ እንዲህ በቀላሉ እየሸፋፈነ የሚሄድ እንዳይደለ ልብ ይሏል፡፡ በብዙ ማስፈራሪያ መጽሐፍ ቅዱስን እንዳናነብ የተለያዩ ምክንያቶች ይቀርቡ የነበረው ይህ እና መሰል ውሸቶች እንዳይገለጡ ነበር፡፡ በትክክል ወደ መጽሐፍ ቅዱስ የምንመለስበትና መጽሐፍቶቻችንን የምንመረምርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ወገን! ዛሬ ለእውነት ወግነን የአባቶቻችን የበደል ክምር ቢያንስ ለሚቀጥለው ትውልድ እንዳናስተላልፍ ደግሞም ይህችን ምድር ከእርግማን ማውጣት እንድንችል እግ/ር ይርዳን፡፡የዚህች ምድር ታሪክ ሊቀየር የሚችለው እነዚህና መሰል ባዕድ አምልኮዎች ሲወገዱ እንደሆነ እረዳለሁ፤እግ/ርን እናመልካለን፣ ኢትዮጵያ የክርስትና ደሴት ነች እየተባለ ነገር ግን በውስጧ ብዙ እንደዚህ አይነት ቆሻሻ ነገሮች መያዛችን የሚያሳዝን ነው፡፡ እግ/ር ቤተ ክርስቲያንን ያጥራ!

  ReplyDelete
 12. It is true most abaselama blogger don't read the bible and are not thinkers.In the Tewahido church we believe St.Marry as Jesus's mother who is one of the creators together with the father and holly spirit.St.marry can do all what Jesus Christ,even more than what he has done for us by gift.He said,"If you believe you can do all what I have done even more than these"She has been given 12 different gifts in the bible(Raiy12:1-13)The gifts are represented by stars.For these gifts St Paul writes,"I Thank for all untold gifts God has given us"(2kor9:13-15)The untold gifts written by St.Paul are The saints.If there are saints to pray for,no one raises his /her hands before his mother.If we are given gifts(the saints) as St.Paul states, we have to use Them.We are doing this properly.We don't say St,Marry Created us.This is the exclusive right of the lord,Jesus Christ.We call her name to pray for us(inditamaliden).Saints have duty of praying for us as stated in the above verse of St.Paul.
  As regrades the Cross of Jesus Christ St.Paul states,"Kekirstos meskel beker lela timkihit kene yirak" yilal.It is this doctrine that should guide us,not the none sense logic of the protesters(protestants)

  ReplyDelete
 13. Do you know how Egypt Coptic's belief on St Mary?

  Read Abune Shenoda's book on http://tasbeha.org/content/hh_books/the_holy_virgin_st_mary/index.html
  "...HER SURNAMES AND SYMBOLS
  A. Surnames as regards her greatness
  and her relation with God:
  1. We give her the surname of The Queen who is by the right side
  of The King.
  2. Also we say about her: "Our mother the Holy Virgin".
  3. The Virgin is also compared to the ladder of Jacob"
  4. She was also called "the bride"
  5. We also give her the surname "the beautiful pigeon"
  6. The Virgin is also compared to the cloud
  B. Her surnames and symbols
  as regards her motherhood to the Christ our Lord:

  7. One of the surnames by which The Virgin has been
  described is "Theotokos"
  8. One of her surnames is also: "the golden censer".
  9. The Virgin is also surnamed "the second heaven"
  10. The Virgin is also surnamed "the city of God":
  11. In this quality, she was surnamed "the vine where was found
  the cluster of life"
  12. By this quality of motherhood, she has other surnames of
  which we mention:
  13. Among her symbols also: "the bush which the prophet Moses
  saw" (Exodus 3:2).
  14. Also a mong her symbols: "the ark of the Testimony".
  15. The Virgin is also compared to the pot of the manna;
  16. The Virgin is also compared to the rod of Aaron which
  germinated:
  17. The tabernacle of meeting (the dome of Moses). ..."

  I don't think Abune Shenoda learn this from ZereYaqob. If your thaught is from Orthodox Tewahedo, I don't see any difference between EOTC and Egypt Coptic church, please don't mislead people by putting Atse ZereYaqob in wrong place. If your thaught is from Protestant thaught, you have different ideology so we don't have to argue about it. Believe what you believe and we will believe what we believe. We don't have to argue because we have different idealogy.

  ReplyDelete
  Replies
  1. የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮችም ለማሪያም አይሰግዱም፡፡ ስግደት የሚገባው ለፈጣሪ ብቻ ነው የሚል እምነት አላቸው፡፡
   ከፈለክ ይህንን ዌብ ሳይት አንብበህ ማረጋገጥ ትችላለህ፡፡ http://lacopts.org/orthodoxy/our-faith/the-holy-virgin-mary/

   Delete
  2. ማሙሽMarch 7, 2014 at 11:41 PM

   Do you mean "No woman in history is more misunderstood than the Holy Virgin Mary. The Reverend Billy Graham once said, “We evangelical Christians do not give Mary her proper due.” However, Saint Mary receives her “proper due” within the Orthodox faith." Please read the message again. Thank you for the link.

   Delete
 14. ተስፋ መልካም ጽፈሓልና በዚሁ ቀጥል የውሸት አማልክትና ጀሌዎቻቸው አንገት እስኪደፉ ድረስ
  ቆማጣን ቆራጣ ካላሉት የሚለውንም አለመዘንጋት መልካም ነው።

  ReplyDelete
 15. Where do you think Atse Zera Yaikob found this theology? Glory to God almighty and thanks be to him, he must have a revelation, believe it or not it is the same way now in America Orthodox Christians venerate and ask her intersession. If there is any body thinking that, Ethiopian Orthodox Christians are the only ones who are doing this please go and see how Greeks, Russians, Serbians, Syrians, Copts, Bulgarians, Ukrainians and all other Orthodox Christians do. This opposition is not new, this started since Christianity begins and it will go all the way until time of judgment. Otherwise who do you think are anti Christs only who officially said so? No! no! no! there are so many who lie in his name do not be worried in this.

  ReplyDelete
 16. እግዜአብሔር ይባርክህ ወንድሜ ተስፍ የእግዜአብሔር አሳቡ ሁሉን በክርስቶስ ኢየሱስ ለመጠቅለል ነው እንጅ በማሪያም ወይም በመስቀል አይደለም እባካችሁ ወገኖቸ የሐዋርያውን የቅዱስ ጳውሎስን መልክት ወደ ኤፌሶን የጻፈውን ም. 1፡10 በደንብ አንብቡት ተስፉ ሥራህን ቀጥል እግዜአብሔር ይረዳሀል

  ReplyDelete
 17. This is not accurate information. Please, do more research. May God be with you.

  ReplyDelete
 18. This article is incorrect. Please, do more research. God bless.

  ReplyDelete
 19. Please use the Bible as the only source of your argument ,not logic.In the bible there are many peopleand angles who are worshiped (yetesegedelachewu).For instance St.John worshiped the angle came to him.Lot worshiped the two people came to him.Abraham worshiped his Ankle......So,What is the fault if we worship St.Marry.Are these men not followers of God.Can we say these people don't know what to worship and not?Egypt or Abune Shinoda are not our reference.Our reference is the Bible

  ReplyDelete
  Replies
  1. If you believe bible is the only source, then why don't you advocate the church to get rid of all those unbiblical teret teret it has been carrying for the past couple of centuries?

   Delete
 20. You didn't indicate the teret terets.I don't think you properly understand my message.The church does not have any teret terets.She is pure apostolic.It looks teret terets only for you,the protesters(protestants)

  ReplyDelete
  Replies
  1. If it clearly contradicts the bible then it's the work of some debtera; not the holy spirit!

   Delete
 21. Why not u write his is a teret teret that our church believes.Teret terets are beliefs of protestants who accept the meaningless sounds and words of their preachers as holly spirit.Those who oppose prayers of saints(2kor9:13-15),the gifts of his mother(raiy12:1), fasting,etc.

  ReplyDelete
  Replies
  1. How do you know I oppose those things you mentioned? I oppose teret teret books not intersession of saints or fasting!

   Delete