Sunday, March 9, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን የፓትርያርኩን እጅ የመጠምዘዝ፤ እምቢ ካሉም የማስወገድ ትግሉን አጠናክሮ ቀጥሏል!! (ከማን ጋር ሊሰሩ ነው? » አባ ኤልሳዕ

 • የአሀዳዊ መዋቅር ምንጭ በሆነው ሲኖዶስ የምትተዳደር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን ምኗ ነው? 

በአንድ ወቅት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ «በመንግሥት ሌቦች እጃችን ታስሯል» ማለታቸው አይዘነጋም። ከትንሹ በቀቀን ካድሬ አንስቶ እስከ ትልቁ ዓሳ ነባሪ/አንበሪ/ ሹመኛ ድረስ የመዋጥ፤ የመሰልቀጥ ተግባሩን ተመልክተው «የመንግሥት ሌባ እጃችንን አስሯል» ማለታቸው ይህንን ሁሉ በአንዴ ለማስቆም አለመቻላቸውን መግለጻቸው ብቻ ሳይሆን ከስፋቱ አንጻር ለማስቆም መሞከር ውጤቱ አደገኛ ሊሆን መቻሉን ለማመልከት« እጃችን ታስሯል» በማለት የችግሩን ስር መስደድ በአጭር ዐረፍተ ነገር ለመግለጽ ሞክረዋል። እዚያ አደገኛ ደረጃ ላይ የተደረሰው ግን በአንድ ጀምበር ሳይሆን ቀስ በቀስ አንዱ አንዱን እየዋጠና እየፋፋ እንደመሆኑ መጠን እጅ ከመታሰሩ በፊት አስቀድሞ ትንሽ በትንሹ እርምጃ ቢወሰድ ኖሮ አስጊነቱ ያን ያህል ባላሳሰበ ነበር።  ስርቆት ምንጊዜም ከክፉ ሰዎች ልቡና በሚመነጭ ሃሳብ የሚፈጸም ተግባር ነው። ክፉ ሰዎች ደግሞ ሰውን ከመግደል ወደኋላ አይመለሱም። እግዚአብሔርን ማወቅ ከሰዎች ኅሊና ውስጥ ሲጠፋ ጭካኔ ይስፋፋል። እርግማን፤ ግዳይ፣ ስርቆት፤ ደም ማፍሰስ ይበዛል።
በአንድ ወቅት የእስራኤል ልጆች ኃጢአት በመብዛቱና የካህናቱ ርኩሰት መጠን ከማጣቱ የተነሳ እግዚአብሔር አዝኖ የሥራቸውን ዋጋ ይቀበሉ ዘንድ ጥፋት እንደተዘጋጀባቸው መጽሐፍ ቅዱሳችን ይነግረናል።( ሆሴዕ ምዕ 4 እና 5) ሌብነትን መዋጋት ህግን እንደማስከበር ብቻ ሳይሆን መታየት ያለበት ደም ለማፍሰስ የማይመለሱ ሰዎችን ከኅብረተሰቡ ውስጥ እንደማውጣት ይቆጠራል።

እንደዚሁ ሁሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከፓትርያርኩ ጀምሮ እስከ አጥቢያው አገልጋይ ካህን ድረስ እጃቸውን ወደኋላ አስሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እየነገደ የፈረጠመውና በመዋቅሩ የዓሳ ነባሪ ያህል የገዘፈው ማኅበረ ቅዱሳን መሠረታዊ ጥቅሙን ለማስከበር ሲል ብቻ ከዚህ በፊት ለፓትርያርኩ ይሰጥ የነበረውን የምስጋና ካባ አውልቆ እጃቸውን ወደመጠምዘዝ ተግባር መሸጋገሩን እየተመለከትን እንገኛለን። የዚህ ሁሉ ዋናው ምክንያት በጥቅሙ መስመር ላይ የሚቆም ማንም ሰው የጥቅሙ ጠላት በመሆኑ አስቀድሞ እጁን በመጠምዘዝ ወደቀድሞ አስተሳሰቡ ለመመለስ በየትኛውም መልኩ መታገል፤ ካልተቻለ ደግሞ ከቆመበት የጥቅሙ መስመር ላይ ማጥፋትና ማስወገድ የጥቅመኛ መዳረሻ ግቡ ነው። ምን ጊዜም በማግበስበስ የበለጸጉ ሰዎች ጥቅማቸውን የማያስጠብቀውን አመራር ለማስወገድ እረፍት የሌላቸው መሆኑ ታሪክ ያስተምረናል። ሰሞኑን  የማኅበረ ቅዱሳንና የተባባሪ ጳጳሳቱ ጩኸት አቶ መለስ እንዳሉት የፓትርያርኩን እጅ የመጠምዘዝና ወደኋላ በማሰር ወደቀድሞ የማኅበሩን ጥቅም የማስከበር መስመር የመመለስ ትግል ተጠናክሮ መቀጠሉን እያየን ሲሆን ችግሩ በዚህ የማይፈታ ከሆነና ከቀጠለ ፓትርያርኩን የማስወገድ እርምጃ እንደሚከተል ሳይታለም የተፈታ ነው። እንዴት ይፈጸማል? የሚለውን ወደፊት የምናየው ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ግን ክፉ ሰዎች / ክፉ መሪዎች/ ክፉ ሀገራት/ ወዘተ ምን ጊዜም የማይስማማቸውን ከመግደል እንደማይመለሱ በእርግጠኝነት ልንናገር እንችላለን።
«ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፤ ካላሰናከሉም እንቅልፋቸው ይወገዳልና» ምሳሌ 4፤16
በዚሁ አጋጣሚ የምናሳስበው ነገር እውነተኛን የሚጠብቅ እግዚአብሔር እንደማያንቀላፋ ቢታወቅም  በተሰጠን ልቡና ራሳቸንን እንዳንጠብቅ የሚያዘናጋን ባለመሆኑ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በሚበሉት፤ በሚጠጡትና በሚለብሱት ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ማስገንዘብ እንወዳለን።  እውነት ነው! «ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ» ማቴ 10፤28 በማለት እንደተናገረው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ብቻ በሕይወታችን በማስቀደም ማገልገል እንደሚገባ እንጂ የሚያሳስበን በስጋ መሞት እንደማያስፈራን ይታወቃል።
ፓትርያርክ ማትያስ ከማኅበረ ቅዱሳን እስራት ነጻ ሰው መሆናቸውን መግለጽ በጀመሩ ማግስት፤ እስራታቸውን አምነው እንዲቀበሉ የማኅበሩ እስረኝነታቸውን ያረጋገጡ ጳጳሳት ቢቻል በምክር ሽፋን እጃቸውን እንዲሰጡ አለሳልሰው በማባበል፤ ፓትርያርኩ የአቋም ሰው በመሆን ከቀጠሉ ግፋ ሲል ደግሞ ወደፊት በማስፈራራት፤ አድማ በመምታትና በስመ ድምጽ ብልጫ የፓትርያርክነቱን ሥልጣን በመቀማት እግር ተወርች የማሰሩ ዘመቻ በእርግጥ ይቀጥላል። አባ ጳውሎስንም እንዲሁ ነበር ያዋከቡት።
ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ እንጂ የማኅበረ ቅዱሳን ፓትርያርክ የመሆን ግዴታና ውል የለባቸውም። እኛም እንደተለመደው የምንጠይቀው ነገር ቢኖር አንድና አንድ ብቻ ነው።
የአሀዳዊ መዋቅር ምንጭ በሆነው ሲኖዶስ የምትተዳደር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን ምኗ ነው? የሲኖዶስ አባላት ጳጳሳቱ የሚያገለግሉት ለማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ለቤተ ክርስቲያን?

19 comments:

 1. Ante Yemitagelegilew Be Awrew Menfes Lemimeraw Ye Protestantawi Tehadiso Budin Weyis Kidusan Hawariyat besebesebuat be andit kidist betekristian sireat... please change the name Aba Selama...rather call yourself Yemulu Wongel church Arbegna. It's not about Mk ...it is about your agenda of protesting dogmatic as well as canonical issues of the Orthodox Tewahido Church...

  ReplyDelete
 2. አይ አባ ሰላማዎች የምትገርሙ ተሃደሶዎች የውም በጣም ተራዎች ድሮ ሳናውቃችሁ ያታለላችሁን አይበቃችሁም …….. ባላወኩበት ዘመን የቤተክርስቲያን ጠባቂ የሆኑትን ማኅበረ ቅዱሳንን እናንተ በሰጣችሁን መረጃ መሠረት መቃወማችን ፀፅቶናል …….. እንደ እናንተ አይነተ ተሃድሶዎችን ከቤተክርስቲን እየመነጠቁ ስለሚያወጡ አሁን ደግሞ አካሄዳችሁን ቀይራችሁ አባቶቻችንን በዘርና በገዘብ በማታለል ማኅበሩን ማጥፋት እንኳን ባትቸሉ በሥራው እንቅፋት ለመሆን የምትጥሩት ጥረት ይገርማል በእውነት የሰላም ባለቤት እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጣችሁ…….. ይህን ብሎግ የምታነቡ ምዕመናን እስኪ መረጃ በደንብ አጣሩ እኔ በደረኩት ማጣራት ማኅበረ ቅዱሳን ጋር የሚጣሉ እንደምናውቃቸው 1ኛ፣ መናፍቃን ተሃድሶዎች 2ኛ የቤ/ን ሥርዓ መጠበቅ የማይፈልጉ መድሃኒተኞች 3ኛ. ቤተክርስቲንን በመመዝበር ፎቅ የሰሩ መኪና የገዙ ሌቦች በአጠቃላይ ቤተክርስቲያንን ማጥፋት የሚፈል ሁሉ ለቤተክርስቲያን ዘብ የቆሙትን የማኅበረ ቅዱሳን አባላትን ማጥፋት ይፈልጋሉ ባይችሉም ……. እንደ ማስረጃ ከፈለጋችሁ የዚህ ብሎግ አዘጋጅ መርጌታ ፅጌ ስጦታው ከማህበሩ ጋር ሲጣላ ኑሮ ማኅበሩ መረጃ አቅርቦ በምፍቅና ተወግዞ ከቤ/ን ከተባረረ ወዲህ አሁን ያለው በምንፍቅና አዳራሽ ውስጥ ነው……. ስዚህ ክርስቲያኖች ልብ ልንል ይገባል፤፤፤፤፤ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአማላጅነቷ የአሥራት ሀገሯን ቤተክርስቲያናችንን በቤቷ ውስጥ ከመሸጉ ከተሃድሶዎችና ከሌቦች ይጠብቅልን

  ReplyDelete
  Replies
  1. የኔ ወንድም እግዚአብሔር አይኖችህን ያብራቸው!ሌላ ምንም ማለት አልችልም፡፡ዘመን ያስቆጠረውን ያለፉ ጥቂት ሆዳም እና ከርሳም አባቶች በአንድ ወቅት ያፈለሱትን ባዕድ አምልኮ በመከተል በታሪክና በትውልድ ሊወቀሱበት የሚገባዉን ኮተት ሰብስቦ ቤተ ክርስቲያንን በጨለማ ለመምራት እየተጋ ያለውን ማቅን መወገንህ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ ተዉ እንጂ እናንተ ሰዎች! ተምረንም እንዳልተማሩት ብዙሃን አባቶቻችን እኛም እነዚያን የጨለማ ግዞተኞች ተከትለን እንጥፋ? እኔ ምለው መቼ ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚነበበው? መቼ ነው እውነትን የምንፈልገው? ሁሌ በስማ በለው? መቼ ነው በቤተ ክርስቲያኒቱ ያሉት እነዚያ የሚዘገንኑ ተረቶች የሚወገዱት? (የሚያነበው ቢሆን ይኼ ትውልድ መቼም በቤተ ክርስቲያኒቱ የቅርብ ዓመታት ታሪክ ይሸማቀቃል ብየ አስባለሁ) ዛሬም እንደ ጨለማው ዘመን እነዚያን ተረቶች በእግዚአብሔር ቤት እያየናቸው ለልጆቻችን በስማበለው ልናወርሳቸው ነው? ማቅ እኮ ግትር እና የዉርስ ሀይማኖትን ለማስቀጠል ብቻ (ትክክል ይሁን አይሁን ማቅ አይገደዉም ዋናው የቀደመዉን ይዞ ማቆየት ነው) የሚሮጥ ጭፍን ተምሮ ያልተማረ የማሃይማን ስብስብ ነው፡፡ ይቅርታ!

   Delete
  2. 1. @Anonymous march 11,2014 at 12:10 AM ጥሩ መፈክር አሰሚ ይወጣሃል!!ይሄን ያህል ስድብ ከምትጽፍ አንተ ሆዳም ያልካቸው ቅዱሳን አባቶች የዛሬዎቹ ጌቶችህ ገና ስይገረዙ ወደ ቁዋንቁዋህ ከተረጎሙልህ መ/ቅዱስ አንድ ቃል ብትናገር መልካም ነበር!!እኛንም ላንተ መልስ ለመስጠት ስንል መ/ቅዱስ እንድናነብ የበለጠ ታተጋን ነበር!!ለማንኛውም ማኅበረቅዱሳን ኖረ አልኖረ ኦርቶዶክስ በቀደመው የቀና መንገድ ትቀጥላለች!!ለወደፊት ይቆጭሀል የሚባለው አነጋገር የሚሰራው ወቅቱን እያየ ለሚለዋወጠው ስርዓት አልባው ፕሮቴስታንቲዝም ነው!!ለእኛ አይሰራም!!
   2. ከቻልክ ማኅበረቅዱሳን ካወጣችው መጻህፍት ውስጥ አንዱን መሃይምነታቸውን ያሳያል የምትለውን ጥቀስና መልስ ስጥ - መቸም እንደአነጋገርህ መ/ቅዱስ በጉንጩ ነህ!!አቤት…አቤት ያንተን መ/ቅዱስ እውቀት አፈሰስከው እኮ!!...ጭፍን…ተምሮ ያልተማረ…የመሃይምናን ስብስብ….የጨለማው ዘመን…ተረት የሚሉት ቃላቶችህ የፕሮቴስታንቲዝም አስተምህሮ ምን ያህል በወንጌል እንዳነጸህ ያሳያል!!እንዲህ የስድብ ሜኑ ደርዳሪዎች ያሉበት ዕምነት እያለልኝ ስለክርስቶስ መስክረው አክሊለክብር የተቀበሉ ቅዱሳንን ታሪክ አብነት እንዲሆናችሁ እያለች በምታስተምረው ኦርቶዶክስ ውስጥ በመኖሬ እንዲቆጨኝ አድርገሃል!! ደግሞ አንተ ያው በራዕይ ጌታ የነገረህን ስለምትናገር ቃልህ ሆዴን በልቶታል!! ጌታ የገለጸልህ የትንቢት ስጦታም ከአባባ ታምራት ሳይበልጥ እንደማይቀር ሰምቻለሁ!!ትንቢትና ትዕቢት እየተምታቱብኝ ስለምንተባተብ አትፍረድብኝ!!እንዳንተ እነ ጆሹዋና እነ ፓ/ር ዳዊት ስላልጸለዩልኝ ነው!!
   3. እውነቱን ልንገርህ!!የእናንተ ትልቁ ስህተታችሁ ኦርቶዶክስን በማኅበቅዱሳን ቁመት ልክ አድርጋችሁ ማሰባችሁ ነው!!ማኅበረቅዱሳን ለቤ/ክ አንድ የድርሻውን የሚወጣ ለሃይማኖታቸው ቀናኢ የሆኑ ዘመናዊ ምሁራን ኦርቶዶክሳዊ ስብስብ ነው!!ነገር ግን ብቻውን ሃይማቱን ይዞ የቆመ አካል አይደለም.!!የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ አካል አንዱ ክርስቶስ ሲሆን የአካሉ ብልቶች ደግሞ ብዙዎች ናቸው!!ማኅበረቅዱሳን ከብልቶቹ እንደ አንዱ ነው!!ስለዚህ እሱን በማሸማቀቅና በማጥፋት ቤ/ክንን እንይዛታለን ካላችሁ ትልቅ ስህተት ነው!!ሲጀመር አሁን ያለው ጥቃቅን አለመግባባት እንዴት አድርገን ኃላፊነታችንን ብንከፋፈል ነው የበለጠ ሃይማኖታችን እንደተቁዋም የምትጠነክረው በሚል ውይይት ውስጥ የሚካሄድ አመራርን የሚመለከት የአካሄድ ልዩነት እንጅ የነገረ ሃይማኖት ክርክር ውስጥ አልተገባም!!በዚህ ሂደት ደግሞ ማኅበሩ በሲኖዶስ እና በጠቅላይ ቤ/ክህነት ስር ያለ ጠንካራና ለተልእኮ የሚፋጠን ማኅበር ይሆን እንደሆነ እንጅ የሚዳከም አይመስለኝም!!አያርገውና እሱ ቢዳከም እንኩዋ አባላቱ ያልሆነው ለእናንተ አንተኛም!!በደመ ክርስቶስ በተቀደሰችው ቤ/ክ ባዕዳኑ የሉተር ውላጆች ሲቆሙ ከምናይ ሞታችንን የምንመርጥ ልጆቹዋ ሚሊዮነ-ሚሊዮናት ነን!! ኦርቶዶክስን በማቅ ቁመት አትለኩ!! ታሪካዊውም ሆነ ወቅታዊ ሁኔታው ስለማይደግፋችሁ!!
   እኔም ይቅርታ!

   Delete
  3. ኦርቶዶክስን በማቅ ቁመት አትለኩ!!
   የሚለው ሀሳብህ ትልቅ ሀሳብ ነው። ይህንን ግን ለማቅ ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆን ለደጋፊዎችም ንገራቸው።
   ኦርቶዶክስን በማቅ ቁመት በመለካት ደጋፊዎቹ እና አባላቱ ይብሳሉና!!!!

   Delete
 3. amlakachen egeziabher lebet kerestiyanachen yemisrutene ened mahber kdusan ayentochn mahberta yebezalen

  ReplyDelete
 4. Unreliable source confirmed Aba Paulos poisened by mk elements. It is key and relevant to increase security caution Aba Mathias for all his activity to stay away from Aba Abrham group. Aba Elsea is working hard to return his Gondre patriarch, but mk and sneaked the floop side of coin. Mk had killed 45, 000 monk.for the past twenty years. We have researched on the close door. We will rlease the name of monk soon.

  ReplyDelete
 5. this is 100 % true we will fight mk

  ReplyDelete
  Replies
  1. alekerebachihum...aba selebawech tedebiko kemawurat megelet yasefelegal yane fitlefit enaweralen.. yechelema lejoch selehonachihu and ken fikiren sebekachihun atawukum...Le enat betekirestian zeb lemekom yegid bemahiber antakefim egnam wuch honen enetebekatalen..

   Delete
 6. Our research has included the assest , tribe and sexual life of mk leaders accross the world will be inform to the public. For example Ato Daniel Kibret net worth money in his family name in South Africa Bank 45,000,000 millon ethiopian birr deposite in his ex wife name. Tribe Gojame and he got Diploma in Amaharic language. To save this amount of money, he will be stay in this world 45,000 years.

  ReplyDelete
  Replies
  1. yegna Professor eski researchun post adiregewu...yemender weregna neh!!!!!!!!!!

   Delete
  2. ዳንኤል ክብረት መቼም ወንጌልን አላሰደደም አልልም። በሱ ፊታዉራሪነት አያሌ የወንጌል ወጣቶች ከቤተክርስቲያን ተባርረዋል፤ ተደብድበዋል። ከክርስቶስ ይልቅ ወጌና ባህሌ ይበልጥብኛል ማለቱ እርግጥ ነዉ፡፡ ይህንን ሁሉ ብር አለዉ የሚባለዉ ግን እኔ ሀሰት! እላለሁ። ምክንያቱም እኔ እስከማዉቀዉ እስከ ቅርብ ጊዜ በኪራይ እዚህ ግባ የማይባል ቤት ዉስጥ ሲኖር ነዉ። መኪናም እንደሌለዉ ነዉ የማዉቀዉ። ታዲያ ራሱንም ልጆቹን እያነገላታ ለሰማይ ቤት ነዉ የሚያጠራቅመዉ? ይህቺ እንኳን ካካ ነች። አንድ ልጨምር። ዳንኤል የተደበላለቀ ቢሆንም አንዳንዴ በል ሲለዉ ንጹሁን ወንጌሉም ሲሰብክ ሰምቼዋለሁ። ለአንድ ጊዜም ቢሆን በዚህ ስብከት የተፈወሰች ነፍስ ሂሳብ በምድራዊ ገንዘብ አይወራረድም። ደግሞ EBS ላይ እንደተመሰከረዉ ለማቅ ያለዉ ብቸኛ ሰባኪ ነዉ። ሌላዉ ነጠላ ሲያሳምር እንጂ ምንም ሲፈይድ አናይም።እባካችሁ ሰዎች! አገልጋዮችም ሰዎች ናቸዉና በሚኖራቸዉ ቁሳቁስ ላይ አታተኩሩ። ሲሆን እሰየዉ ማለት ይገባል።

   Delete
 7. Ergetkal, currently reside in Atlanta, he does not hold any type of education just simply tall and fulish naive his net worth 250, 000 us dollar saved only with two years period non taxed that indicate violation of US law. Tribe Gojame and. he just dropped high school at Bichena.

  ReplyDelete
  Replies
  1. enaminyitebes stupid!yemitaweraw hulu ayitimim..lemn zim atilim

   Delete
 8. ወንድሜ ህሩይ ሆይ!! "ስለክርስቶስ መስክረው አክሊለክብር የተቀበሉ ቅዱሳንን ታሪክ አብነት እንዲሆናችሁ እያለች በምታስተምረው ኦርቶዶክስ ውስጥ በመኖሬ እንዲቆጨኝ አድርገሃል!!"
  ይህ አባባልህ የአንተን ቀና ምኞት የሚያንጸባርቅ እንጂ እዉነታዉ ይህ አይደለም። ይህ ቢሆንማ ምን አጣላን? እኔ የምለዉ እነዚህ ስለክርስቶስ መስከረዉ፤ ስለራሳቸዉ ሳይሆን ሰለክርስቶስ ብቻ የተጋደሉትን አበዉ ቅዱሳንን ታቦት ቀርጸን: ቀን ወስነን: ነገሱ እያልን: የኛም የነሱም ጌታ ያደረገልንን እነሱ እንዳደረጉ እየተቆጠረ: እየተመሰገኑና እየተዘመረላቸዉ የአምልኮ ሂደት ሁሉ እየተፈጸመላቸዉ ጌታችንን አምላካችንን ክርስቶስን የሚያስቀናን ጉዳይ የቤተክርስትያናችንን አስተምህሮ አብነት እንዲሆናችሁ ብላ ነዉ ማለትህ የዋህነት ወይም ወገንተኝነት እንጂ የእዉቀት ማነስ እንደሌለብህ ታስታዉቃለህ። ከሁሉ የሚሰቀጥጠዉ ደግሞ ንጉሣችን ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ እየታወቀ ነገሱ እየተባለ ዕልልታዉና ስግደቱ መጦፉ ነዉ። እንዲያዉ አቶ ህሩይን እንደገና ልጠይቅ በዚያ የገብርኤል ወይም የአቡነ ተክለሃይማኖት ታቦት በሚወጣበት ሰዓት በዓይነ ህሊናችን የሚመጣዉ ክርስቶስ ነዉ ወይስ እነዚህ ቅዱሳን ፍጡራን? የኛ ቤተክርስቲያን ይህንን ጉድ አታምንበትም እያልከን ነዉ? ይህስ አያስፈርድባትም ትላለህ? ምዕመኑ ከዋሻ ዋሻ የሚንከራተተዉ የተሰቀለዉን ኢየሱስን ፍለጋ ነዉ ወይስ የአቡዬ እከሌን፤የቅድስት እከሊትን ገዳም ወይም ቤተ ክርስቲያን ብትግጥ እስከ ሰባት ቤት ነፍስህ የቤተሰቤህ ነፍስ ይፀድቃል እየተባለ አይደለም? እንግዲያዉስ ክርስቶስ እንዲሁ በከንቱ ተሰቀለ ማለት አይደለምን? እስቲ እንዲያዉ በምታምነዉ ይዤሃለሁ፤ አስረዳኝ። ይህ ምን ማለት ነዉ? ይህ ፕሮቴስታንት የሚያሰኝ ከሆነ ፕሮቴስታንት ልክ ነዉ። እኔስ ባስ ያለብኝ የኦርቶዶክስ ልጅ ነኝ ግን እሰከዛሬ የሃይማኖት ክርክር አልወድም እያልኩ አካፋን አካፋ ለማለት ድፍረት ያነሰዉን ማንነቴን ሳባብለዉ ኖሬአለሁ። ዉግዘት ከተባለ እንደኔ ዓይነቱ አድር ባይ መወገዝ አለበት እንደአንተ ዓይነቱ የአዋቂ አጥፊ ደግሞ ምን እንደሚባል አላዉቅም። እድሜ ለዚህ ብሎግ ተነፈስኩ።

  ReplyDelete
 9. ፍቅረ ሰላምMarch 13, 2014 at 1:31 AM

  ዳንኤል በፀረ ወንጌልነቱ ይታወቅ እንጂ ገንዘብ በማካበት ስላልሆነ ጥላቻችን ቅጥ ይኑረዉ፡፡ ይህንን ተዐማኒነት የሌለዉነ ዘገባ ትታችሁ ስለዳኒኤል ክርስትና ሪሰርች ብታደርጉና እሰብካለሁ እያለ ሰዉ የሚያሳስተዉን ብታጋልጡ ይሻላል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ስለ ዳንኤል የተጻፈው እኮ ዘገባ አይደለም። አስተያየት ነው። በዚህ የብሎጉ አዘጋጆች አይቀቀሱም

   Delete