Friday, April 25, 2014

ፋሲካችን ማነው? ክርስቶስ ወይስ ማርያም?

Read in PDF

“ተፈሥሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ
ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ ዐፅመ ገቦሁ
የአዳም ፋሲካ እና የጎኑ አጥንት የምትሆን የሔዋን መሸጋገሪያዋ
ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ”
ይህ ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ድርሰት በመጽሐፈ ሰዓታት ውስጥ የሚገኝና በበዓለ ኀምሳ ዘወትር ማለዳ ከጸሎተ  ኪዳን አስቀድሞ በሚደርሰውና የአፄ ዘርዐ ያዕቆብ “ወንጌል” ወደሆነው ተአምረ ማርያምና ሌሎች አዋልድ መጻህፍት ምንባብ የሚያንደረድረው ድርሰት፣ ማርያምን “የአዳም ፋሲካ” እና “ሔዋንን ከሞት ወደሕይወት ያሸጋገረች ናት” ይላል፡፡ እንዴት የሚያሳዝን ድርሰት ነው!!! እውን ፋሲካችን ማነው? ክርስቶስ ወይስ ማርያም?

ይህን ጥያቄ መመለስ ቀላል ነው፡፡ ማንም ኦርቶዶክሳዊ አማኝ ፋሲካህ ማነው? ተብሎ ቢጠየቅ ፋሲካዬ ክርስቶስ ነው ማለቱ አይቀርም፡፡ እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤” ይላልና ቅዱስ ቃሉ (1ቆሮ. 5፥7)፡፡ ቅዱስ ያሬድም “ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ፡፡” ትርጓሜ፦ “በክርስቶስ ደም ታጥባ ምድር ፋሲካን ታደርጋለች፡፡” ብሏልና፡፡ ነገር ግን ቤተክርስቲያናችንን ስቶ ያሳታትና ከዚህ እውነት ፈቀቅ ብሎ እርሷም ፈቀቅ እንድትል ያደረጋት አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ካሳደረው ተጽዕኖ የተነሣ የተደረሰው ይህ ድርሰት ግን ፋሲካችን ክርስቶስ ሳይሆን ማርያም ናት ይላል፡፡ ነገር ግን ከልቡ ያፈለቀው ኑፋቄና ክሕደት እንጂ ምንም መጽሐፋዊ ማስረጃ የለውም፡፡

Thursday, April 24, 2014

ለመጪው ዓርብ ታቅዶ የነበረው የአቡነ ማትያስ የግብፅ ጉብኝት ተራዘመ

ምንጭ፡-http://www.ethiopianreporter.com/በግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በተደረገላቸው ግብዣ መሠረት በመጪው ዓርብ ግብፅን ለመጐብኘት ዕቅድ የነበራቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ጉብኝታቸውን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም የግብፅ ቤተ ክርስቲያን መጠየቋን ምንጮችን በመጥቀስ የግብፁ ‘ዴይሊ ሳባህ’ ጋዜጣ ዘገበ፡፡ 

የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ምንጮችን የጠቀሰው ዘገባው፣ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ቴዎድሮስ ሁለተኛ የኢትዮጵያው ፓትሪያርክ ጉብኝታቸውን እንዲያራዝሙ የጠየቁት፣ ሁለቱ አገሮች በታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ምክንያት ውዝግብ ላይ በመሆናቸው ምክንያት በኢትዮጵያና በግብፅ ቤተ ክርስቲያናት አማካይነት ለማስማማት ቢሞከርም ይሳካል ብላ እንደማታምን በመሆኑ ምክንያት ነው ሲል አመልክቷል፡፡ 

Saturday, April 19, 2014

ኢየሱስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ እኛን ስለማጽደቅም ተነሣእንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ


“ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል”
(1ጴጥ. 1፥3-5)

መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ መሞቱና ከሙታን ተለይቶ መነሣቱ በየዓመቱ ይከበራል፡፡ በዚሁ መሠረት ካህናቱና ምእመናኑ የጌታን ሕማማት በጾም በጸሎትና በስግደት ሲያስቡ ሰንብተዋል፤ የትንሣኤን በዓል ለማክበርም በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ ነገር ግን ጌታ የመሞቱና የመነሣቱ ምስጢር ገብቷቸው በዓሉን የሚያከብሩ ስንቶች ይሆኑ?
ብዙዎች ጌታን አይሁድ ሰቅለው እንደገደሉትና እርሱ ግን በታላቅ ኀይልና ሥልጣን እንደተነሣ ብቻ ስለሚያስቡ ከዚህ ዐልፈው የመሞቱን ምስጢርና የመነሣቱን ዓላማ አያስተውሉም፡፡ ከዚህ የተነሣ አይሁድን ሰቃልያነ እግዚእ (ጌታን የሰቀሉ) በማለት ለጌታ ያላቸውን ፍቅርና ሐዘኔታ አይሁድን በመጥላት ለመግለጽ ይጣጣራሉ፡፡ ጌታ ግን ለሰቀሉት አይሁድ “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ሲል ምሕረትን ከአባቱ ለምኖላቸዋል፡፡ ጌታን በመውደድ ስም እርሱ እንዲህ ያዘነላቸውን መጥላት ተገቢ አይደለም፡፡ ብዙዎች የማያስተውሉት የጌታ የመሞቱ ምስጢር ግን ከዚህ ይለያል፡፡
ቅዱስ ሉቃስ በጻፈው የሐዋርያት ሥራ ላይ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤ እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት። እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።” የሚል ቃል ተጽፏል (የሐዋ. 2፥22-24)፡፡ በዚህ የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተገለጠው እውነት ጌታ ለአይሁድ ተላልፎ የተሰጠው በይሁዳ ጠቋሚነትና “ሻጭነት” ቢሆንም፥ ዋናው ግን በእግዚአብሔር ውሳኔና በቀደመው ዕውቀቱ ስለኀጢአታችን ተላልፎ መሰጠቱና ሞታችንን መሞቱ ነው፡፡ ስለዚህ ሞቱ የኀጢአታችን ዕዳ የተከፈለበትና እኛ ነጻ የወጣንበት ማስረጃ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት የኀጢአታችን እዳ ተከፍሏልና ወደፊት የሞት ዕዳ የለብንም ማለት ነው፡፡ 

Thursday, April 17, 2014

‹‹ጎልጎታ››፡- ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር . . .!!!በፍቅር ለይኩን፡፡
ለዚህ መጣጥፌ የመረጥኩት የእውቁ ሠዓሊና ባለ ቅኔ የገብረ ክርስቶስ ደስታን ‹‹ጎልጎታ››በሚል ርዕስ የተጠበበትን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የሥነ ስቅለት አስደናቂና ዘመን አይሽሬ (classical) ሥራውን ነው፡፡ የዚህን ገጣሚና ሰዓሊ፣ እጅግ ተወዳጅና ተደናቂው የሆነውን ‹‹የጎልጎታን››ስነ ስቅለት፣ ፍቅርን ተጠበበትን ድንቅ ሥራውን ፅንሰትና ውልደት ታሪክ በአጭሩ ላውጋችኹ፡፡

ገጣሚና ሠዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጥበብ ታሪክ ውስጥ ስሙ ጎልቶ ከሚጠቀሱ የስነ ጥበብ ሰዎች ዘንድ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ እውቅና ታላቅ ሰው ነው፡፡ ገ/ክርስቶስ ዘመናዊ የስዕል ሙያን በአገር ውስጥና በአውሮፓ ከተማረ በኋላ በአገሩ እምብዛም አልቆየም ነበር፡፡ በአገራችን በተከሰተው የ1966 አብዮትናከነደደው የነውጥና የለውጥ እሳት የተነሣ እንደ ብዙዎቹ ኢትዮጵያውያን ምሁራንና ወገኖቹ የእርሱም ዕጣ ፈንታ ስደት ሆኖ ነበር፡፡
ገ/ክርስቶስ በትምህርትና በስደት ሕይወት ለረጅም ዓመታት በባሕረ ማዶ በቆየባቸው ጊዜያት ውስጥ አውሮፓውያኑ ወይም በአጠቃላይ ነጮች ለአፍሪካውያንና ለጥቁር ሕዝቦች ያላቸው ዘረኝነት፣ ንቀትና ጥላቻ በእጅጉ ያብሰለስለውና እረፍት ይነሳው ነበር፡፡

ከምንም በላይ ደግሞ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምድር ተምሳሌት፣ በዓለማችን ታሪክ ታይቶና፣ ተሰምቶ በማይታወቅ ጀግንነትና ወኔ ኢትዮጵያውያን፣ አባቶቹ ወራሪውን የኢጣሊያንን ቅኝ ገዢ ኃይል በዓድዋ ጦር ግንባር በአኩሪ ጀግንነት አሳፍረው የመለሱ ኃያላን መሆናቸውን አሳምሮ ለሚያውቀው ገ/ክርስቶስ ይህ የአውሮፓውኑ ትምክህትና ንቀት ከመገረምም በላይ ሆኖበት ነበር፡፡

Wednesday, April 16, 2014

ለስቅለት ዕለት የታሰበው የማኅበረ ቅዱሳን የአመፅ ጥሪ ይፈጸም ይሆን?

Read in PDF

ሁከት ፈጣሪው ማኅበረ ቅዱሳን ሚናውን ለይቶ መጫወት ሲገባው የጨዋታው መንገድ ጠፍቶበት ሃይማኖትና ፖለቲካን እያጣቀሰ የጀመረው ጉዞ ጦዞ ወደመጨረሻ የደረሰ ይመስላል፡፡ ከሰሞኑ እየደለቀ ያለው የሽብር ከበሮም ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ማቅ እንደተለመደው ከጀርባ ሆኖ በሚናገርባቸው ጋዜጦችና መጽሔቶች በተለይም ፋክት በተባለው መጽሔት ተመስገንን መናገሪያው አድርጎ ያስተላለፈው የዐመጽ ጥሪ ማቅ ዓላማውን ለማሳካት የት ድረስ ለመጓዝ እንደሚያስብ ያመላከተ ሆኖ አልፏል፡፡
በተመስገን በኩል ማቅ ያስተላለፈው ጥሪ የስቅለት በዓል ዕለት ምእመናን እንዲያምፁ የሚቀሰቅስ ነው፡፡ ከተመስገን በቀር አባላቱ እነታደሰ ወርቁና ብርሃኑ አድማስ “አትነሳም ወይ?” የሚል የዐመጽ ጥሪያቸውን በየመጽሔቱ ሲያስተላለፉ እንደነበር ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በተለይም ታደሰ ወርቁ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ መካከል የወጡ አክራሪዎች የተከተሉትን መንገድ መከተል እንደሚያዋጣና ለዚህም ማቅ ከጀርባ ሆኖ ያደራጃቸውን የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶችን ሊጠቀም እንደሚችል ጠቁሞ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ እነርሱን መያዝ የሚቻለው ተሐድሶን መቀስቀሻ በማድረግ እንጂ በቀጥተኛ ፖለቲካዊ ቅስቀሳ አለመሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

Monday, April 14, 2014

«ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ከሆነ እኔም አክራሪ ነኝ» የሚሉ ድምጾች ምነው በዙሳ?

Read in PDF

ምንጭ፡-http://dejebirhan.blogspot.com/

በአንድ ወቅት ዳንኤል ክብረት የተባለው ሰውዬ በእንቁ መጽሔት ላይ እንደተናገረው «ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ሆኖ የገደለው ሰው የለም!» ብሎ ነበር። በዳንኤል አስተሳሰብ «አክራሪ» ማለት በሃይማኖተኝነት ሰበብ ሰው የመግደል ደረጃ ላይ ሲደረስ መሆኑ ነው። ከመግደል በመለስ ያለው ኃይልና ዛቻ፤ማሳደድ ተፈቅዷል ማለት ነው? ሌላው የማኅበረ ቅዱሳን የሜሪላንድ አፈቀላጤ ኤፍሬም እሸቴ ደግሞ «አክራሪ ሃይማኖተኛ መሆን ጥሩ ነው» ሲል ተመራጭነቱን በማሳየት የማኅበረ ቅዱሳንን የማክረር እንቅስቃሴ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ሲታትር ታይቷል።  አክራሪ በባህሪው እኔ ትክክል ነኝ ከሚል ጽንፍ ተነስቶ፤ የምለውን ተቀበሉኝ፤ እምቢ ካላችሁ ወግዱልኝ፤ አለበለዚያ እኔው በኃይል አስወግዳችኋለሁ በሚል ድምዳሜ የሚያበቃ አስተሳሰብ ነው።  አንዳንዶች አክራሪነት በዚህ ዘመን የተከሰተ አድርገው ሲመለከቱ ይታያል። ትርጉሙና የተግባራዊ እንቅስቃሴው ስፋትና ጥልቀት ተለይቶ ታወቀ እንጂ አክራሪነት ጥንትም ነበረ።  በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 9 ላይ እንደተመለከተው ኢየሱስ ለሐዋርያቱ እንደነገራቸው «አስቀድማችሁ ወደሰማርያ ከተማ ሂዱና፤ ጌታ ይመጣል ብላችሁ አስናድታችሁ ጠብቁኝ» ብሎ ባዘዛቸው ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች መልዕክቱን እንዳልተቀበሉ ሐዋርያት ስለተመለከቱ «ጌታ ሆይ፥ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን?» ብለውታል።  ጌታ ግን፤ «የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም» ብሏቸዋል።  አክራሪዎች ራሳቸውን የእግዚአብሔር ብቸኛ ወታደሮች አድርገው ራሳቸውን ያስቀምጣሉ። ስለዚህ እኛን ያልመሰለ ይጥፋ ባዮች ናቸው። አስተምሮ፤ ተከራክሮ መመለስ ስለማይችሉ አጭሩ መፍትሄ ማስወገድ ነው።

እንደዚሁ ሁሉ በፖለቲካው ከተሰማሩት ድረ ገጾች አንስቶ እስከጥቃቅኖቹ ብሎጎች ድረስ አንዱ ከአንዱ እየተቀባበሉ የማያውቁትን ማኅበር ለማሳወቅና ለሃይማኖት ማክረር እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ የሚገልጹ ጽሁፎችን እስከማራገብ ድረስ ዘልቀዋል።  በፌስቡክና በትዊተር ገጾች «ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ከተባለ እኔም አክራሪ ልባል» ከሚለው ድምጽ አንስቶ የማኅበረ ቅዱሳንን ዓርማ የሚያሳይ ግለ ስእል በመለጠፍ አጋርነታቸውን ለማሳየት የሞከሩ ብዙዎች ናቸው።  ሁሉንም ስንመለከት «አክራሪ ሃይማኖተኛ» መሆን አስፈላጊ እንደሆነና «እኛም የዚሁ ሰልፍ አባሪ ሆነን ለሃይማኖታችን አክራሪ ነን» የሚል ይዘት ያለው አቋም እየተንጸባረቀ መገኘቱን መገንዘብ ይቻላል። ሃይማኖተኛ ነን የሚሉቱ ወገኖች ያሉበትን ምክንያት ከማየታችን በፊት ፖለቲከኞቹ ነገሩን ለማስጮህ የፈለጉበትን ምክንያት እንመልከት።


1/ ፖለቲከኞች ማኅበረ ቅዱሳንን የመደገፍ ምክንያት፤

ፖለቲከኛ ሃይማኖት የለውም ማለት ባይቻልም ሃይማኖተኛ ግን ፖለቲከኛ መሆን አይችልም። ፖለቲከኛ ሃይማኖት ሊኖረው የሚችለው ስለሃይማኖቱ አውቆና አምኖበት በመከተሉና እምነቱ የሚያዘውን ለመፈጸም እንደእግዚአብሔር ቃል ለመኖር ለራሱ ኪዳን የገባ ሳይሆን በውርስ ከቤተሰቦቹ የተረከበው ወይም በልምድ ሲከተለው ስለኖረ ራሱን ሃይማኖት እንዳለው አሳምኖ ሲያበቃ ከፖለቲካ የሚገኘውን የምድራዊ ሳይንስ ጫወታ የሚጫወት ሰው ነው። 

Thursday, April 10, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን ካለበት ጫና ለማገገም አቅጣጫ ማስለወጫ ያለውን ያረጀ ስልት ይዞ በኮሌጅ ተማሪዎች ላይ ዘመቻ ከፈተ

Read in PDF

በሁከት ፈጣሪ ጠባዩና ሁሉን ጠቅልሎ በመግዛት ፍላጎት እየናወዘ የሚገኘውና ከፓትርያኩና ከጠቅላይ ቤተክህነት፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሀፊዎችና ሌሎችም አገልጋዮች፣ እንዲሁም ከመንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ የገባው ማኅበረ ቅዱሳን እርሱ ላይ ያረፈውን ትኩረት አቅጣጫ ለማስለወጥ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትንና አገልጋዮችን ስም ማጥፋትን ሥራዬ ብሎ ተያይዞታል፡፡ የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች እንደሚባለው ያለቤተክህነት ዕውቅና በትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ሥራ ጣልቃ በመግባት በራሱ ፈቃድ ትልቅ ገቢ አገኝበታለሁ ብሎ ያሰበውና እንዳይካሄድ የታገደበትን የአብነት መምህራን ጉባኤን በሕገወጥ መንገድ በራሱ ሕንጻ ላይ ማካሄዱን ተከትሎ ቤተክርስቲያኗን በይፋ በሚዲያዎቹ ሁሉ ይቅርታ እንዲጠይቅ ደብዳቤ የተጻፈበት ቢሆንም ስሕተቱን ለማመንና ለመቀበል ዝግጁነቱ የሌለው ማኅበረ ቅዱሳን ግን እስካሁን ይህን ተግባራዊ አላደረገም፡፡ ሒሳቡንም ከጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ጋር በጣምራ ፊርማ እንዲያንቀሳቅስ የተጻፈለትን ደብዳቤም ሞኝህን ፈልግ ብሎታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ሀገረስብከት አስተዳዳሪዎች ጸሐፊዎችና ሌሎችም አገልጋዮች የተነሣበትን ተቃውሞ ማብረድ ሳይችል ነገሩ እንደተንጠለጠለ ይገኛል፡፡
በእነዚህ ሁሉ ጉዳዮች አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን በሚገባ ያስተዋለው ማቅም እርሱ በሚደጉማቸው እንደ ዕንቁና ፋክት ባሉ መጽሔቶቹና ከእነርሱ እየተቀበሉ ወሬውን በሚያናፍሱለት እንደሐራ ባሉ ስውር ብሎጎቹ ላይ “መንግስት ሊያፈርሰኝ ነውና ድረሱልኝ” የሚል ጥሪ ማስተላለፉ የሚታወስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደምም የእርሱ ቅጥር ሰራተኞች በሆኑት በእነብርሃኑ አድማስና በእነ ታደሰ ወርቁ በመጽሔቶቹ ላይ በእስልምናው በኩል ተሰልፈው እንደሚቃወሙት ዐይነት የዐመጽ ጥሪ በማስተላለፍ ያልተሳካለት ማቅ በቅርቡ የስቅለት ዕለት እግዚአብሔርን ማምለክ ትታችሁ ዐምጹ የሚለው ጥሪው የማቅን የፖለቲካ አቋም ከማሳየትና መንፈሳዊ ማኅበር አለመሆኑን ከማጋለጥ ባለፈ ተቀባይነት የሌለው ሰሚ አልባ ጩኸት ነው፡፡ ይሁን እንጂ በዚህ አቅጣጫ ብዙ እንደማይሳካለት የተረዳው ማቅ የምእመናንን ትኩረት ወደሌላ አቅጣጫ ለመውሰድ የስም ማጥፋት ዘመቻ በታወቁ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትና መምህራን ላይ ከፍቷል፡፡ ይህም በግርግር የእኔ ነገር ተድበስብሶ ይቀርልኛል በሚል ሒሳብ የገባበት ስሌት ነው፡፡

Wednesday, April 9, 2014

በዉኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ዉስጥ ያለዉ ችግር እንደሚባለዉ የአስተዳደርና የሙስና ችግር ብቻ ወይስ ሌላ?በዲያቆን የሻነው
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳዉሎስ የቤተክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ካረፉ ወዲህ እና በተለይ ከእርሳቸዉ በኋላ የተሾሙት ፓትርያርክ ብጹእ አቡነ ማትያስ ከተቀመጡ ወዲህ በቤተክርስቲያኒቱ እጅግ የተበላሸ የአስተዳደርና የሙስና ችግር እንዳለ በሰፊዉ ከመወራቱ ባሻገር ለዚሁ መፍትሄ ይሆናል የተባለ የመዋቅር ማሻሻያ በሰፊዉ እንደሚደረግ ተነግሮ ነበር፡፡ እነዚህ ከላይ የተገለጹት ችግሮች በተለይ ተንሰራፍተው የሚገኙት በአዲስ አበባ አገረ ስብከት ነዉ በሚል ቅድሚያ ተሰጥቶት የቅዱስ ሲኖዶስና የፓትርያርኩን ይሁንታ አግኝቶአል በሚል የአሰራር ሂደት ለዉጡን ወደ ስራ ለማስገባት በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር የሚገኙ የሚመለከታቸዉ ናቸዉ የተባሉ አካላት ዉይይት ተጀምሮ ነበር፡፡ በተቃራኒዉ ይህንኑ የማሻሻያ ስርአት ይቃወማሉ የተባሉ ቡድኖች ቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር በአሰራር ማሻሻያዉ ላይ ያላቸዉን ቅሬታ ይዘዉ በመግባታቸዉ ጉዳዩ እንዲቆም ተደርጎ ለመላዉ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር በሚመች መልኩ ስራ ላይ ማዋል እንዲቻል የአሰራር ሂደት ለዉጡ  በቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ስር ባሉ አካሎች እንዲገመገምና እንዲሻሻል ከቀድሞ ኮሚቴ እጅ የሰነድ ርክክብ ተካሂዶአል፡፡
            በቤተክርስቲያኒቱ አለ የተባለዉ የአስተዳደርና የሙስና ችግር በተነገረና የአሰራር ማሻሻያዉ ጥናት ይካሄድ ተብሎ በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወሰነ ከጥቂት ግዜያት በኋላ ተጠንቶ የተቀመጠ 1500 ገጽ የሚሆን የአሰራር ማሻሻያ ሰነድ በአንዴ ብቅ ብሎ  አዲስ አበባ አህጉረ ብስከት ላይ ስራ ላይ ሊዉል ነዉ ተብሎ ሲነገር እንኳን የአዲስ አበባ አድባራት የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮችን አይደለም በመላዉ ኢትዮጵያ የሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆችን ሳያስደነግጥ የቀረ ጉዳይ አይመስለኝም፡፡ ከባድ ነዉ የተባለዉ የቤተክርስቲያች ችግር ሰፊና ጥልቀት ያለዉ ዳሰሳ ሳይደረግበት በአንዴ የችግሩ መፍትሄዉ የሆነዉ የአሰራር ሂደት ማሻሻያ መገኘቱ ሲሆን በተጨማሪም  የዚህ ማሻሻያ ግብረ ሐይል ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ወርቁ ነዉ ሲባል ደግሞ ባለ ረጅም እጁ ነኝ ባዩ እና የቤተክርስቲያኒቱን መዋቅር ከወትሮዉም ጊዜ በላይ መቆጣጠር የሚፈልገዉ ማህበረ ቅዱሳን እጁ ያለበት መሆኑን ግልጽ ያደርገዋል፡፡ ታዴ በጨው የታጠበ ማቅ በመሆኑ እና በዚህም ምክንያት ጤነኛ ማሻሻያ ሊቀርብ ስለማይችል ተቃውሞው በርትቷል፡፡ ለውይይት የቀረበው ማሻሻያም ከዚህ የተሻለ ነገር አልተገኘበትም፡፡

Monday, April 7, 2014

አንዳንድ “ማኅበራት” ራሳቸውን «ቅዱስ» ሲሉ በጣም ያስቁኛል...

Read in PDF

ምንጭ፡-http://dejebirhan.blogspot.com/
(an article by Tedy Sih) በመጠነኛ መሻሻል የቀረበ
መቸም ለጽድቅ የሚሰሩ ፖለቲከኞች እንደሌሉት ሁሉ ፖለቲካን ስራየ ብለው የሚሰማሩበትና በሱም ለፅድቅ የበቁ ቅዱሳን የሉም፡፡ ለፖለቲካ ሲሉ ተደራጅተው ራሳቸውን ‹‹ቅዱሳን›› ብለው የሚሰይሙ ደፋሮች ግን አይጠፉም፡፡ የፖለቲካ ግባቸውን ለማሳካት የሚከተሉት እኩይ የትግል ስነ ዘዴንም ጭምር ‹‹ቅዱስ ጦርነት›› ብለው የሚጠሩ ነፈዞዎችም ሞልተዋል፡፡ እኛ ሀገር ወስጥ በእንዲህ ያለ ፖለቲካ ላይ የተጣዱ ‹‹ቅዱሳን ፖለቲከኞች›› እንደምናየው ሁሉ ‹‹ቅዱሳን›› ገጣምያን፣ ጋዜጠኞች፣ ምሁራን፣ ጥላቻ ቀስቃሾች፣ ጠብ ተንኳሾች፣ አመጽ ናፋቂዎች፣ ጦር አውርድ ባዮች ወዘተ መታዘብ ከጀመርን ሰነባብተናል፡፡ አሁን ደግሞ እነዚህን ሁሉ የሚያገናኘውን የሚስጥር ቋጠሮ ሊገልፅልን ፈልጎ በትጋት የተነሳ የሚመስል አንድ ‹‹ቅዱሳን ማኅበር»ኢህአዴግ ሊያጠቃኝ ተነስቷልእያለን ነው። 
 ከስሞታው ዜና እንደምንረዳው ይህ ማኅበር ራሱን እንደፖለቲካ ፓርቲ እንደሚቆጥር እማኝነት ይሰጣል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከፖለቲካ የለሁበትም ማለትም ይከጅለዋል። ባለህንጻ፤ ባለሆቴል፤ ነጋዴና ገንዘብ የሚሰበስብ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ አልተሰማም። ተቋም ነኝ ወይም ድርጅት ነኝ ማለት አንድ ነገር ነው። ነገር ግን «ቅዱስ ማኅበር» እባላለሁ ቢለን «ቅዱሱ ማኅበር» ለማለት የሚያስችለን ምክንያት የለውም። ሲጀመር ብላቴ የጦር ካምፕ ተነሳ፤ ሲጨረስ በስመ ክርስትና ባለቢዝነስ መሆን ቻለ፤ እውነታው ይህ ነው። ማኅበሩና ቅድስና ከመነሻው እስካሁን  ድረስ አይተዋወቁም። በስምም ሆነ በግብር ከማኅበሩ ጋር የሚመሳሰሉ የቅዱሳን ታሪክ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ አልነበረም።