Wednesday, April 2, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን የሚፈርሰው በራሱ ተግባር ነው፤ ኢሕአዴግ ላለፉት 22 ዓመታት መቼ ነካው?ምንጭ፡- http://dejebirhan.blogspot.com/
የሀገሬ ሰው «ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል» ይላል። ይህ አባባል ለሰሞነኛው የማኅበረ ቅዱሳን የጅቡ በላኝ ጩኸት ይስማማል። ኢህአዴግ ሊያጠፋኝ ነው ሲል በየግል ጋዜጣው ማስወራቱ 22 ዓመታት ኢህአዴግ በሚመራት ሀገር ውስጥ ያልነበረ ይመስላል። ሲነግድ፤ ሲያስነግድ፤ ሲሸጥ ሲለውጥ፤ከግብርና ታክስ ተከልሎ በሚሊዮኖች ብር ህንጻ ሲገነባ በሀገሪቱ ኢህአዴግ ያላየው ወይም የማያውቀው ይመስላል።

ኢህአዴግ ማኅበረ ቅዱሳንን በአስማት ይሁን በምትሃት እስከዛሬ ሳያየው ቆይቶ አሁን ለማየት ዓይኑን ሲከፍት ማኅበረ ቅዱሳንን አገኘውና ሊበላው ስለሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ኢህአዴግ ሊያጠፋኝ ለምን ፈለገ ሲል ለመጠየቅ የተገደደ ይመስላል። በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለው ተግባሬ ከማኅበረ ካህናቱ ጋር አጋጨኝ፤ በማያገባኝ አስተዳደር ውስጥ እጄን ሳስገባ ተገኘሁ እንዳይል ከመሬት ተነስቶ ኢህአዴግ ሊውጠኝ ነው ወደሚል ቅስቀሳ መግባቱን  ከመምረጡ በስተቀር በምድር ላይ ያለው እውነታ ግን የምርጫ ዘጠና ሰባት ውጤትና ተከትሎ የመጣው ፖለቲካዊ ቀውስ ስንቱን ፓርቲና የተቃዋሚ መሪዎች እየደፈጠጠ ሲያልፍ ማኅበረ ቅዱሳን ግን በቤተ ክርስቲያኒቱ ታዛ ተጠልሎ አልፏል። ኢህአዴግ ቢያጠፋው ኖሮ ያኔ ባጠፋው ነበር።


ይህ ህንጻ የማነው? የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን? የመንበረ ፓትርያርክ? የኢንቨስተር? የነጋዴ? የአስመጪና ላኪ?
ከዚህ በፊት ማኅበሩ እንደጥራጊ አውጥቶ የጣለው ዳንኤል ክብረት ይህን ኢህአዴግ ሊበላኝ ነው የሚለውን የማኅበረ ቅዱሳንን ዘፈን እንዲህ ሲል በደጀሰላም ብሎግ ላይ አውጥቶ ነበር።
«እኔ እንደምገምተው የማኅበሩ አባላት መንግሥትን እንዲፈሩ እና እንዲጠሉ የሚፈልጉ አካላት በአመራሩ ውስጥ ሳይኖሩ አይቀርም፡፡ ምንጊዜም አንዳች ከባድ ነገር ሲነሣ መንግሥት እንዲህ ብሎናል፣ በዚህ ስብሰባው እንዲህ ብሏል፣ ሊዘጋን ነው፣ ሊያስረን ነው፣ ሊጨርሰን ነው ከማለት ያለፈ አንድም ቀን በጎ ነገር ስለ መንግሥት የማያነሡ አካላት አሉ»

 ስለዚህ ከዚህ አባባል ተነስተን ልንል የምንችለው ነገር ይህ መንግሥት ሊበላን ነው የሚለው ዜማ እንደስልት የተያዘና መንግሥት በአባላቱ ዘንድ እንዲጠላ የተዘየደ መሆኑ ነው። ከዚያም ባሻገር መሰሪ ስራውን ለመደበቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ በሌሎች ሰዎች ዘንድ ለመሳል የታቀደ ጥበብ ሲሆን ጻድቁ ማኅበረ ቅዱሳንን ኢህአዴግ ሊያጠፋው ስለሆነ ኦርቶዶክሳውያን የሆናችሁ ሁሉ የዚህን መንግሥት መሠሪነት ተመልከቱ ብሎ ክፉ ስዕል ለመስጠት የተፈለገ ብልጠት ነው።
እውነቱ ግን ማኅበረ ቅዱሳን ነጋዴ ድርጅት መሆኑ ማንም ያውቃል። የግል ይሁን የአክሲዮን ማኅበር መሆኑ ያልታወቀና የራሱን ሀብት የፈጠረ ተቋም ስለመሆኑም ስራው ምስክር ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ከንግድ ተቋማቱና ከልዩ ልዩ የገቢ ምንጮቹ ባሻገር የራሱ የሆኑ አባላት ያሉትና የአባልነት መዋጮ የሚሰበስብ ድርጅት ነው። ከዋናው ማዕከል ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ ቁመት የራሱ የሆነ መዋቅርና  ራሱን የቻለ አደረጃጀት ያለው ነገር ግን አደረጃጀቱ በየትኛው የሀገሪቱ  የአደረጃጀት ፈቃድ ላይ እንደቆመ ያልታወቀ መሆኑም እርግጥ ነው። ይህንን የራሱ ተቋማዊ ኅልውና ያለውን ማኅበር በሀብቱ፤ በንግድ ተቋማቱ፤ በመዋቅራዊ አካላቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመቆጣጠርና የማዘዝ ምንም ሥልጣን የላትም።  በአንጻሩም ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስር ተሸፋፍኖ እንደመጠለሉ መጠን ቤተ ክርስቲያኒቱ በማኅበሩ ላይ የመቆጣጠርና የማዘዝ ሥልጣን እንዳላት ግምት ያለው በመሆኑ መንግሥት ይህን ድርጅት ነክቶት አያውቅም። ስለዚህ ይህንን ማኅበር ቤተ ክርስቲያኒቱም፤ መንግሥትም ሳይመለከቱት ከሁለት ወገን ቁጥጥር ነጻ ሆኖ 22 ዓመት ዘልቋል።
 «ለሁሉም ጊዜ አለው» እንዲሉ ሆኖ ማኅበሩን ማነህ? ምንድነህ? የት ነህ? ምን አለህ? ምን አገባህ? የሚሉ ካህናትና የአመራር አካላት ተባብረው በመነሳት መጠየቅ ሲጀምሩ ጥቂት ሟሳኞችና አሟሳኞች ወደሚል ሃሳብ ለመውረድ ተገዷል።  በምንም ደረጃ ያሉ ሰዎች ማኅበረ ቅዱሳንን መክሰስ መቻላቸው የማኅበሩን ማንነት ማሳያው ተግባሩ እንጂ ክሱ አይደለም።  እየተከሰሰ ያለው ማኅበር በተግባሩ ያልታወቀ ማኅበር ባለመሆኑ በሟሳኞችና አሟሳኞች የቃላት ጫወታ እየፈጸመ የቆየውን ሸፍጥ ሸፍኖ ማስቀረት አይቻልም።
ማኅበረ ቅዱሳን በተግባር በሌለው ሥልጣንና መብት መናፍቃን ናቸው ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን በራሱ ጥቁር መዝገብ አስፍሮ አስደብድቧል፤ ሰልሏል፤ ስም አጥፍቷል፤ አስፈራርቷል፤ እንዲሰደዱ አድርጓል። ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያኒቱ ስም መጽሔትና መጻሕፍትን፤ ካሴትና ቪዲዮ፤ አልባሳትና ንዋየ ቅድሳትን ከታክስና ከቀረጥ ነጻ ሆኖ ነግዷል። የማኅበረ ቅዱሳን አቋም የሚቃወሙ ሁሉ ጠላቶቹ ናቸው። የሚደግፉት ደግሞ ጳጳሳቱ ሳይቀሩ ወንጀል ቢኖርባቸው እንኳን የቤተ ክርስቲያኒቱ ታማኝ አገልጋይ ተደርገው ዜና ይሰራላቸዋል፤ ሙገሳ ይሰጣቸዋል። አባ እስጢፋኖስን ማንሳት ይቻላል። ጠላቶቼ ከሚላቸውና ስማቸውን ሌሊትና ቀን ሲያጠፋቸው ከቆዩት ጳጳሳት ውስጥ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ደግሞ የጥላቻ የአፍ መፍቻው ናቸው። ሌሎቹም ፈርተው አንገታቸውን ደፍተውለታል። የተገዳደረውን አንገት ያስደፋል፤ አለያም ቀና ካለ አንገቱን ይሰብራል።  ሌላው ቀርቶ ሲያመሰግናቸው የነበሩትን አዲሱን ፓትርያርክ ጠላቶቼ የሚላቸውን ሰዎች ሲቀጣ በቆየበት መልኩ በስም ማጥፋት ቅጣት ናዳውን እያወረደባቸው ይገኛል። ለራሱ ኅልውና ብቻ የሚጨነቅ፤ ካልመሰለው ደግሞ ሲያወድሳቸው ለነበሩት ሳይቀር ግድ የሌለው ማኅበር ስለመሆኑ ከድርጊቱ ተነስቶ መናገር ይቻላል።  ወትሮውንም ሸፋጭ ነጋዴ ገንዘቡን እንጂ ወዳጅና እውነት በእሱ ዘንድ ዋጋ የሌላቸው ስለሆኑ የሚያስበው ጊዜያዊ ትርፉን ብቻ ነው። በዚህ ዙሪያ ማኅበሩ አሸንቅጥሮ የጣለውና ለተቀበለው የእጅ መንሻ በውጪ እንዳለ የሚለፈልፈው ዳንኤል ክብረት ማኅበሩ ስለግለሰቦችና ስለቤተ ክርስቲያኒቱ ደንታ ቢስ እንደሆነ ያጋለጠው እንዲህ ሲል ነበር።
«ዲያቆን በጋሻው ማስተማር የጀመረው መቼ ነው? ማኅበሩ በነዲያቆን በጋሻው ላይ ሃሳብ ዛሬ መሠንዘር ለምን ጀመረ? በጋሻው ለቤተ ክርስቲያን አደጋ ነው ብሎ ስላሰበ አይደለም፡፡ በጋሻው ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ስለ ተናገረ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ምንም ያልተናገረው ማኅበር ስሙ ሲነሣ ቤተ ክርስቲያን ተነካች ብሎ ተነሣ፡፡ ማኅበሩ አቡነ ጳውሎስን በተመለከተ የተለየ አቋም መያዝ የጀመረው መቼ ነው? «እርሳቸው ማኅበሩን ሊያፈርሱ ነው» ብሎ መሥጋት ከጀመረ በኋላ፡፡ አባ ሠረቀንም ቢሆ ንኮ ዛሬ ዛሬ በእምነት ችግር ይከሳቸዋል እንጂ፣ ከእርሳቸው ጋር ያለው ዋናው ችግሩ ማኅበሩ መነካቱ ነው፡፡ አባ ሠረቀ ማኅበረ ቅዱሳንን ሳይነኩ የፈለጉትን ቢሆኑ ኖሮ አይናገራቸውም ነበር፡፡ ባለፈው ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ ችግር ሲፈጠር፣ ዝምታን መርጦ የነበረው አመራር የመንግሥት አካላት ከቤተ ክህነቱ ባለሥልጣናት ጋር ሆነው ስለ ማኅበሩ ሲያወያዩት ግን አገር ይያዝልኝ አለ፡፡ የአዋሳ ምእመናንን ችግር በዝምታ ያለፈው አመራር አባ ሠረቀ አንዳች ነገር ተናገሩ ብሎ ድምፁን አሰምቶ ተናገረ፡፡ እነዚህ እና መሰል ሁኔታዎች አመራሩ የሚቆረቁረው ማኅበሩ ሲነካ እንጂ ቤተ ክርስቲያኒቱ ስትነካ አለመሆኑን ያመለክታሉ» ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን ከራሱ በላይ ማንንም እንደማይወድ እርግጥ ነው።
ማኅበረ ቅዱሳን በፖለቲካው ዙሪያ ከምርጫ 97 በፊትም ሆነ በኋላ ስላለው ሁኔታ መንግሥት በቂ መረጃ እንዳለው ይሰማል። በዚህ ዙሪያ መንግሥት ያለውን መረጃ እስኪያወጣ ድረስ የምንለው ነገር የለም። ነገር ግን ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲያምሳት መቆየቱን፤ እጁን እያስገባ ሲኖዶሱን ሳይቀር እንደሚጠመዝዝ እናውቃለን። ማኅበሩ ደፋርና የልብ ልብ የተሰማው አንዳንድ የሲኖዶስ አባላት ተጠግቶ የጉባዔ ሃሳብ በራሱ መንገድ እስከመጠምዘዝ የመድረሱን አቅም እየለካ በመሄዱ ነው። ዛሬ ላይ ያ ነገር የለም። ፓትርያርክ ማትያስ ለዚህ የማኅበሩ ሃሳብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ገና አንድ ዓመት ሳይሞላቸው ከኢህአዴግ ጋር ተመሳጥረው ሊያጠፉኝ ነው እያለ ስም ወደማጥፋት ወርዷል። በተቃራኒው ደግሞ ማንም እንደማያጠፋው በሚገልጽ ጀብደኝነቱ ፓትርያርክ ጳውሎስም እንደዚሁ ሊያጠፉኝ ሞክረው እንደማያዋጣቸው አውቀው አጃቸውን ከእኔ ላይ ለማንሳት ተገደዋል በማለት ለፓትርያርክ ማትያስ የማስጠንቀቂያ ማስታወቂያ እየሰራ ይገኛል። እጅዎን ከእኔ ላይ የማንሳትን ጉዳይ ችላ ሳይሉ ከቀድሞው ፓትርያርክ ትምህርት ውሰዱ በማለት ማሳሰቢያ እየሰጠ መሆኑ ነው። የሚፈራው ከተገኘ ጥሩ ጀብደኝነት ነው፤ ነገር ግን ባለቀ ጊዜ ማላዘን ዋጋ የለውም። ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያኒቱ ስንት ችግር ባለባት ሰዓት ራሱ ችግር ፈጣሪ ሆኖ ካለቦታው የተገኘ ማኅበር ስለሆነ ተገቢ ቦታውን መያዝ ካለበት ሰዓቱ አሁን ነው። ማኅበረ ካህናቱና የቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር አባላት ጠንክሮ መታገል የሚገባችሁ ወቅት ቢኖር ዛሬ ነው። ማኅበሩ ቁጭ ብሎ አዋጭ የሆነውን መንገድ መቅረጽ ካለበት ቶሎ ብሎ ይህንኑ እንዲፈጽም ምክር እንለግሰዋለን። የአክሲዮን ማኅበር፤ የሃይማኖት ተቋም፤ በጎ አድራጊ ድርጅት ወይም የተሻለ ነው ብሎ የደረሰበትን ውሳኔ ወደተግባር መቀየር ካለበት ቀኑ ሳይመሽ በብርሃኑ ይሆን ዘንድ ልናሳስበው እንወዳለን። ሲሆን ዘንድሮ፤ ካልሆነም በቀጣዩ ዓመት፤ ቢረዝም፤ ቢረዝም አንድ ቀን ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጉያ እንደመዥገር የተጣበቀበት ቀን እንደሚያበቃ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ምክንያቱም ማኅበሩና ተግባሩ፤ ካህናቱና አስተዳደሩ መቼም ቢሆን አሁን ባለው መንገድ አብረው መጓዝ አይችሉምና ነው።  ከዚህ ሁሉ ፓትርያርኩም፤ ካህናቱም፤ አመራሮችም፤ መንግሥትም ይህንን ማኅበር ቦታ የማስያዙን ጉዳይ ችላ ሊሉት አይገባም። ማኅበረ ቅዱሳን ሳይኖር ቤተ ክርስቲያን ነበረች፤ ማኅበረ ቅዱሳን ሳይኖርም ትኖራለች!!!  «ማኅበረ ቅዱሳን ከሌለ ቤተ ክርስቲያን ትጠፋለች» የሚለው ራሱ ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ነው።

43 comments:

 1. Libona ystachehu kmahiber kidusan lay wored belu

  ReplyDelete
 2. ዳባ የለበሽው ሰላማ በይ ያለቤትሽ ቤተኛ መስለሽ ገብተሽ ስትፈተፍቺ ቆይተሽ ዝናርሽን ጨረስሽና ለተለያዩ አካላት የቤት ስራ ሰጥተሽ በዙፋንሽ ላይ ቁጭ በይና ተመልከቺ እውነትሽን ነው ይበቃሻል፡፡ በሉ ምድራውያን የሆናችሁ ሁሉ ያላችሁን ጦር ወርውሩ ለሁሉ ነገር መጨረሻው አሁን ነው ብለሽ ማወጅሽ ባለሽ የሰይጣናዊ የአስተሳሰብ ደረጃ ያስደንቅሻል፡፡ የተወረወረን ጦር አቅጣጫ የሚቀይረውን ሰማያዊውን ለማሰብ ሰይጣናዊ ባህሪሽ አይፈቅድልሽምና

  ReplyDelete
  Replies
  1. ትክክለኛ የሞት ማጣጣር ይሏል ይኼ ነው! በለው!

   Delete
  2. እውነት ብላችኋል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ጠባቂዋ ማን እንደሆነ ሰላማዎች ስለዘነጋችሁት ማህበራት ቢፈርሱ እንኳን ድንጋዮችን አፍ አውጥተው እንዲናገሩ የሚያደርግ፣ አህዮችን የሚያናግር፣ እናንተን በነፋስ አውታር ወጥሮ እውነትን እንድትመሰክሩ ሊይዝ የሚችል አምላክ ነው ፡፡ የሰላማ ተከታዮች የተሰጣችሁን ጊዜ ተጠቀሙበት ንስሐ ገብታችሁ ብትመለሱ ይበጃችኋል፡፡

   Delete
  3. አይ አባ ሰላማ ማህበሩ ማነቆ ሆነባቸሁ አይደል?

   Delete
 3. ለ 22 ዐመታት ኢህዴግ ማህበረቁዱሳን ለማፍረስ ታገለ አሁኑም እንደዚያው። እኔ የሚገርመኝኮ የናንተ ከንቱ ምኞትም ጭምርም ነው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 4. Yeferse Yeferese begegize yiferese. yihe yeaganente mahebre

  ReplyDelete
  Replies
  1. libonahin Yasawek, Yeagant hasabna nafkot Yaderbh/sh,

   Delete
 5. MK gira tegabtoal. Meneshawun wushet adirgo wede medireshawu wushet sirot, mehal menged layi eiwunet kech alechibet. Tedenagete! Diabilos degmo kedategna balenjera newu. "Yerasih guday" sayilewu yekere ayimesilegnim.

  ReplyDelete
 6. skelew, sikelew, this is the protestant menafkan ( debilos- led organization) brag. enante ye sitan trikm, mahaberu andach neger ayhonm , truth always the winner.

  ReplyDelete
 7. እንደማውቀውና እንደምረዳው ይህ ሲያዩት ዓይንን ደም የሚያለብስ ህንጻ ህንጻ በእውነቱ ከሆነ የማኅበረ ቅዱሳን ነው፡፡ ይህ ህንጻ የቤተክርስቲያኒቷ ነው፡፡ ካላመናቸሁ የሰፈረባችሁ የዛር መንፈስ ፒርርርርርር ሲፈልግ ደግሞ ቲርርርርርር ያድርጋችሁ!! እውነት እውነት ነው ሀሰት ደግሞ ሃሰት ስለሆነ ከሃሰተኞች ጋር ትጠፋለች፡፡ ይህንን ጠብቁ!

  ReplyDelete
 8. ደጀ ሰላሞች ከተነቃባችሁ ቆየ እኮ የበግ ለምድ ለብሳችሁ የኦርቶዶክስ መለያ ለብሳችሁ የምትተውኑ የኢህዴግ ትንሹ መንፈሳዊ መሳይ ብሎግ ናችሁ እኮ እኔ የሚገርመኝ ትወናችሁ ለምን እንደማይዋጣለት ነው እኔ እንደግለሰብ ብተውን ኖሮ ከዚህ በላይ እተውን ነበር ታዲያ ማህበሩ እግዚአብሔርን ካልሰበከ የእንንተን ምንግስት አምላክ ቡፋኒቱን/ሉሲፈሩን ይስበኩ እንዴ ኢትዮጵያን ጣዖት ለማስመለክ አትሯሯጡ እግዚአብሔር የእጃችሁን ሳይከፍላችሁ አይቀርም ጠብቁት !

  ReplyDelete
 9. Rebel group has founded by deseret father will attack fundementalist mk, not Gov. Ethiopian gov. Greanted religious freedom to all citizen. Mk, esat, and ginbot seven are enemy of PEACE. for all over the world. Zero chance amahara mk will back to power. Go to bichena not arat killo. Bichina is the home of where you came from. We all fight mk.

  ReplyDelete
 10. አባ ሰላማዎች እነማን እንደሆናችሁ እናውቃችኋለን፣ ውሾች ናችሁ።

  ReplyDelete
 11. ምንም የማይወጣለት ጽሁፍ ነው። በርታ

  ReplyDelete
 12. Nefse enqulichliche mk ayfersim rasih tsehafi rasih simihin qeyireh asteyat sechi

  ReplyDelete
 13. min agebah adarashih hideh atchefrim ye enat tut nekash

  ReplyDelete
 14. Laba drjt bifers tgojiw laba enji hzbu aydelem

  ReplyDelete
 15. Laba drjt bifers tgojiw laba enji hzbu aydelem

  ReplyDelete
 16. ኣብዝሃኛዉ በተማሪ ዳቦ መሰራቱን ማንም ያዉቃል። ከየኮሌጁ በጾም ወቅት የቁርስ ዳቦችንን ለስንት ኣመትት እንደተዋጣ ብታዉቅ ኣንዲህ ለማለት ባልደፈርክ...

  ReplyDelete
 17. Egziabher sitagesew yelele meselewo ende???? Wey mehabere erkusan !!!!! Temesgen legefegnam gefegnan tazeletal.yefeth ministeru sayker wenjel eyeserachu endateteyeku siyaderg norachu ..ye amlak yeferdu ken metabachu....ahun gin ministeru keamlak fird enanten kerto erasunm Ayaterfem.kiber le egziabher yihun.

  ReplyDelete
 18. አባ ጨለማ !!!!ምንም ብትፍጨረጨሪ ኦላማሽ ግቡን አይመታም።

  ReplyDelete
 19. ለ 22 ዐመታት ኢህዴግ ማህበረቁዱሳን ለማፍረስ ታገለ አሁኑም እንደዚያው። እኔ የሚገርመኝኮ የናንተ ከንቱ ምኞትም ጭምርም ነው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 20. የተወደዳችሁ ክርስቲያኖች ማህበሩ ለቤተክርስቲያናችን ዓምድ ነው

  ReplyDelete
 21. Mewugiyawun bitkawom lerasih yibasih............. for chingaf menafik

  ReplyDelete
 22. Ager siyarej endenante ayinet jarit yabekilal

  ReplyDelete
 23. Dirty stuffs :(

  ReplyDelete
 24. ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ሾተላይ! ጽንሱ በሰላም ተወልዶ ሊሳም ሲል የሚገድል፡፡ መቼ ነው የሚፈወሰው መቼም በሽታን በሽታ አሞት አያውቅም፡፡ ያሳምማል እንጂ፡፡ ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያንን የወላድ መሐን እንዳደረጋት ማሰብ አይፈልግም፡፡ ዘማዊና ጠንቋዮቹ አይቆረቁሩትም፡፡ መልክአ ሳጥናኤል ደጋሚዎቹ ርእሱ አይደሉም፡፡ ወንጌል ተሸካሚዎቹ ግን በዚህ በማኅበረ ሰይጣን እንደጎበጡ ከሚወዱት ሕዝባና ወገን እንደተለዩ እናውቃለን፡፡ ፕሮቴስታንት መቶ ዓመት ለፍቶ ያላገኘውን ባለፉት ሃያ ዓመታት ማኅበረ ቅዱሳን ገፍቶ ሰጥቶታል፡፡ በሽርክና መሥራታቸውን እጠራጠራለሁ፡፡ ምክንያቱም ፕሮቴስታንቱም የሚፈልጉትን ሰው የእኛ ነው እያሉ ለማኅበረ ቅዱሳን ይናገራሉ፡፡ ሕጻን አሮጊት የማይለዩ ያበዱ ውሾች መሆናቸው ያሳዝናል፡፡ ሁሉም አባላቱ ግን በዚህ ሚዛን አይታዩም፡፡ እኔም የማኅበሩ አባል ነኝ፡፡ እውነትን ግን ብንነጋገር መደማመጥ ሳይሆን ስም መለጣጠፍ እንደሚመጣ ስለማውቅ እኔን ከሚመስሉ ሆደ ባሻዎች ጋር አዝኜ እኖራለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. እባክዎትን ማስረጃ ይኖርዎታል? ካለ እናምንዎታለን:: ካልሆነ ግን ጊዜያችንን በመግደልዎ እናዝናለን

   Delete
 25. Mahber saytan yebetekrstiyanachen amd Adele amed enjji.yastemarwachu hulu teragamiwoch ena tesadabi bicha ...wengel biyastemrwachu noro lebetecrstiyan tekomo neber yekomachut gin lebercrstiyan tenk kehone lebba yeditabilosen sira masfesemiya mahber gar new.ahunem selote Michael beseyfy endiyafersewo new

  ReplyDelete
 26. በጣም ነው ምታሳዝኑት ጅሎች ተሃድሶ/መናፍቃን/ጴንጤ ያው አንድ ናችሁ:: ማህበረ ቅዱሳን በእ/ር ቸርነት ሁሌም ይኖራል እስቲ ቅጥል በሉ

  ReplyDelete
 27. መፀሀፍ ቅዱስ በቀጥታ: በትርጓሜ፣በሚስጥር፣በአንደምታ ይነገራል።ፊደል ይገድላል "ትርጉም ግን ያድናል።

  ReplyDelete
 28. Oh my God! !!! Ahundegmo yedabo santim aterakmen new genbun yeseranew alachu...what about all the me emen kewchi beyegizew siredachu yeneberwo...a safari new misgana bis athunu.

  ReplyDelete
 29. እንዳያዝን፣ የከተማዋን ጥፋት ያይ ዘንድ አልወድለትም"
  ማውጫ፦ From Contributors Posted by DejeS ZeTewahedo

  (ወልደ አረጋዊ ለደጀሰላም እንደጻፉት መጋቢት 27/2006 ዓ.ም፤ April 5/2014)፦ ታላቁ የእግዚአብሔር ነቢይ የማይቀረውን የኢየሩሳሌምን ጥፋትና በከላውዴዎን ንጉስ እጅ፣ ለከለዳውያን ሠራዊትና፣ ለባቢሎን ሕዝብ ተላልፋ መሰጠቷን እግዚአብሔር ራሱ በተረዳ ነገር በገለጠለት ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ልብሱን ቀዶ፣ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ፣ በቤተ መቅደስ ውስጥ ከባሮክ ጋር እያለቀሱ ተቀመጡ፡፡ ነቢዩ ኤርምያስ እግዚአብሔርንም ሁለት ታላቅ ነገሮች ለመነው። ጉዳዮቹም፦
  ፩ኛ. ተሰውረው እግዚአብሔርን ስለሚያገለግሉባቸው ንዋያተ ቅድሳት ዕጣ ፈንታ እና
  ፪ኛ. ስለ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ጉዳይ ነበር፡፡

  ኤርምያስም እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ ጌታዬ ሆይ፤ እለምንሃለሁ፣ ሕዝቡን ብዙ ዘመን ለጠበቃቸው፣ እኔን ባሪያህ ኤርምያስንም ከሃገሩ ሰው ሁሉ ይልቅ ለጠበቀኝ ለኢትዮጵያዊው ለአቤሜሌክ የማደርገውን ግለጥልኝ፡፡ እርሱ ከረግረግ ጒድጓድ አወጣኝ፣ እንዳያዝን የከተማዋን ጥፋት ያይ ዘንድ አልወድለትም” (ተረፈ ባሮክ ፪፥ ፰-፱)።
  ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ በነቢዩ በኤርምያስ እንደተመሰከረለት በዚያ ዘመን ከነበረ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም የኢየሩሳሌም ነዋሪ ይልቅ የከተማዋ ለባዕዳን ወረራ ተላልፋ መሰጠት እና ከዚያም ጋር ተያይዞ የሚመጣውን የጥፋት ዘመን ቢመለከት እጅግ የሚያዝንና በኃዘኑም አብዝቶ የሚጎዳ መሆኑን ነበር፡፡
  እንግዲህ ነቢዩ ኤርምያስ “…. እንዳያዝን የከተማዋን ጥፋት ያይ ዘንድ አልወድለትም” ብሎ እንደማለደለትና የኃያሉ የእግዚአብሔር ቸርነት ተደርጎለት አቤሜሌክ እንደዋዛ ለ66 ዓመታት አንቀላፍቶ የወዳጆቹን የእስራኤላውያንን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሚወዳትን የኢየሩሳሌምን በጠላት መወረርና መጥፋቷን ሳያይ ቀርቷል፡፡
  አባቶቻችን እንኳንስ ለታላቋ ውድ ሀገራቸው ለኢትዮጵያ አንድነት እና ነጻነት፣ ለቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናቸው ልዕልና እና ክብር ይቅርና በፍቅርና በሰላም ለተወዳጇቸው ሁሉ ከራስ በላይ የሚታመኑ የልብ ወዳጅ የሚሆኑ እና የወዳጆቻቸውን ጥፋት በቸልታ የማይመለከቱ የእውነትና የደግነት አውራ መሆናቸውን በብዙ የተከበሩና የታመኑ የዓለማችን ታሪካዊ መዛግብት ላይ ሰፍሮ እናገኛለን፡፡ ይልቁንም በታላቁ መጽሐፍ፡፡
  እውነት ነው! እነዛ ቅዱሳንና ጽኑዓን አባቶቻችን በዘመናቸው ከተነሱባቸው ሀገር አፍራሽ፣ ሃይማኖት ለዋጭና፣ ታሪክ አቆሻሽ የሀገር ውስጥና የባዕዳን ጠላቶች ጋር ተጋድለው፣ ኊልቆ መሣፍርት የሌለው ውድ ሕይወታቸውንና ንብረታቸውን ሰውተው እነሆ ዛሬ እኛ በታላቅ ክብርና ሞገስ የምንኖርባትን ብቸኛዋን የክርስቲያን ደሴት አውርሰውናል።
  እነሆ ዛሬ ሌላ እውነትም አለን፤
  ዛሬ በእኛ ዘመን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በጠና ታማለች፡፡ አዎ የመናፍቃንና የኢአማንያን የተቀናጀና የተቀነባበረ የጥቃት ዘመቻ ተከፍቶባታል፡፡ የማይተባበሩት ተባብረውባት፣ አንድ የማይሆኑት በአንድነት ዘምተውባት፣ በቤቷ የተሰገሰጉት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ከዘመኑ አብዮታዊ ዲሞክራሲያውያን ጋር አብረው እነሆ ሊያጠፏት ዘምተውባታል፡፡
  ታላቋ ሀገራችን ኢትዮጵያም እንዲሁ ተዘምቶባታል፡፡ ለፍቅር ሳይሆን ለጥላቻ፣ ለእርቅ ሳይሆን ለበቀል፣ ወደ አንድነት ሳይሆን ወደ መበታተን የሚወስዳት የእነ ዮዲትና ግራኝ ውላጆች፣ የእነ ሞሶሎኒ ደባና ሴራ ራሱን አዘምኖና አደራጅቶ በማን አለብኝነት ዳግም ህልውናዋ ላይ ተዘምቶባታል፡፡

  እነሆ ዛሬ፤
  ፨ ለእኛ እንደ አቤሜሌክ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን እና የታላቋን ኢትዮጵያ ሀገራችን ከተደቀነባቸው የወል ጥፋት የሚሰውረን እንደ ኤርምያስ ያለ ነቢይ ከወዴት እናገኝ ይሆን? እንደ ጻድቁ አባታችን እንደ አቡነ ጴጥሮስ ተዋሕዶን ለተኩላ፣ ኢትዮጵያን ለባንዳ አሳልፈን እንዳንሰጥ የሚገዝተን ጀግና መሪ ወዴት እናመጣ ይሆን?
  ፨ ዛሬ እንደ ቀደሙት አባቶቻችን ትናንት የክርስትና መሰረት እና ደሴት ለነበሩት ዛሬ ግን በግፍ የሚረግፉትን የሶርያና የግብጽ ክርስቲያን ወንድሞቻችንን መታደግ ባንችልም፤
  ፨ በሀገራችን ገዳማቱና አብያተ ክርስቲያናቱ በቃጠሎ ሲወድሙ፣ ካህናቱና ምዕመኑ በቀያቸው እንደ በግ ሲታረዱና በግፍ ሲሳደዱ፣ ግድ የሚለው የቤተ ክርስቲያን መሪ እንዲሁም የዜጎቹ መሳደድ የሚያሳስበውና ሀገራዊ ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት እና ተቋም የኖራል በሚልና ለችግሮች ሁሉ ተገቢው መፍትሔ በሚመለከተው አካል ይሰጣል በሚል በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና በክርስቲያናዊ ሆደ ሰፊነት ፍትህን በትዕግስት መጠበቃችን፤
  ፨ ቅዱስ ሲኖዶሱ በመንግሥት ባለሥልጣናት ሲደፈርና ብፁዓን አባቶቻችን በዘመኑ ጋጠወጦች ሲጎሸሙና ሲዋከቡ፣ ይልቁንም ለዘመናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሁለት ሲኖዶስ ስር እንድትቆይ ያደረጋትን ውጫዊ ሴራ ለማክሸፍ አባቶቻችን በተጉ ጊዜ በመንግሥት አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነትና በቤተ ክህነቱ ውስጥ በተሰገሰጉ የፕሮስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች ደባ የዕርቁ ሂደት ሲከሽፍ እያየን እንዳላየን ማለፋችን፤
  ፨ ይልቁንም በአለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ቤተ ክርስቲያናችን ከየአቅጣጫው ከተጋረጡባት የመናፍቃን የተቀነባበረ ወረራና ጥቃት፣ ከአክራሪ እስልምና ጅሃዳዊ ዘመቻ፣ በእቅፏ ተሰግስገው ከሚገዘግዟትና በጎጥ ተደራጅተው ከሚቦጠቡጧት ሙሰኛ ካድሬዎች ዘረፋ ከመታደግ መዘግየታችን፤ ወዘተ ያሳበየው የጥፋት ሃይል፤

  በሌላ በኩል፤
  ፨ ጥንታዊ ገዳማቶቻችን በቀለብ፣ በአልባሳት፣ በውኃ፣ በመብራት፣ በንዋየ ቅድሳት፣ ወዘተ እጥረት እንዳይዘጉና ቅዱሳን አባቶችና እናቶቻችን እንዳይሰደዱ፤ የአብነት ጉባዔያት በመምህራን ደሞዝ፣ በተማሪዎች ቀለብና አልባሳት ማጣት ተማሪዎች እንዳይበተኑና ቤተ ክርስቲያናችን ተተኪ እንዳታጣ፤
  ፨ ይልቁንም በሀገራችን ከተማሪው አብዮት ጋር ተያይዞ በተከሰተውና ዘመን በወለደው የግራ ዘመም የፖለቲካ አስተሳሰብ ምክንያት ከክርስቲያናዊ ሕይወት በተጻራሪው የሚሄደውንና እንደዋዛ የተፈጠረውን የትውልድ ክፍተት ለመሙላት፣ እንዲሁም ወጣቱን ትውልድ ከተጀመረው የክህደት ቁልቁለት ለመታደግ በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ሌት ከቀን እየባዘነ ያደራጀ፣ ያስተማረና፣ ቤተ ክርስቲያን የወላድ መሐን እንዳትሆን የታደገን ክፍል፤
  ፨ አንዳንድ አምባገነን የመንግሥት ባለሥልጣናት በተለያዩ መድረኮች ያለ ስሙ ስም፣ ያለ ምግባሩ ምግባር በመስጠት ለመወንጀል ሲሞክሩ በዝምታ መመልከታችን ቤተ ክርስቲያናችንን በሚመሩት አባቶቻችን ጭምር ሲነገር መስማታችን አስደንጋጭ ከመሆኑም ባሻገር መጭውን ጊዜ ከወዲሁ በአንድነትና በጥንቃቄ እንድንመረምርና የመፍትሄ አቅጣጫም እንድናስቀምጥ የግድ የሚል ሆኖ ይሰማኛል፡፡
  ስለሆነም ሁላችን የተዋሕዶ ልጆች በአንድነት በማኅበረ ቅዱሳን አባላትና አመራሮች ላይ የተከፈተውን የስም ማጥፋት ዘመቻ በማውገዝና በመንግሥትና በቤተ ክህነቱ ውስጥ ተሰግስገው በሚገኙ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች አማካኝነት እየተወሰደባቸው ያለውን የማዋከብና የማሸማቀቅ እርምጃ በአስቸኳይ እንዲቆም አስፈላጊውን የተቀናጀ እንቅስቃሴ ከወዲሁ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ካልሆነ የአቤሜሌክ የልጅ ልጆች የሀገራችንና የቤተ ክርስቲያናችንን ጥፋት በዓይናችን ከማየት ማን ይታደገን ይሆን?

  ReplyDelete
 30. Yemahberu metfat Yebetcrstiyan tifat aydelem lebetcrstiyan tizaz algeza yale mahber yewengel telat ( yecrestos telat ) yemiyafersew eko weyane aydelem.....medahniyalem new ..mekniyatum be ersu meseret lay selaltemeseretu.....mahberu be gibi gubaem yihun beyebetcrstiya siyastemeru sideben meleyayeten adman enjji kehulu yemibeltewon kidus wengel aydelem.mahberu
  lerasu wedajje ena group fester enjji lebetcrstiyanachen seb And alemergagaten
  new ysterefew ahunem egziabher amlak liyastemrachew yefelgew neger ale...this is the time mahber beye temhert tekwamu bazegajwachew temariwoch amakagnete hager yemawekun sira yemijemerut betecrstiyanwan for 22 years siyawkwat norewal...I have an advise for you mk tefatachun amnachhu yikerta teyeku.

  ReplyDelete
 31. Bemahbrkefusan lay yetekefetewon sem matefat enawgeze?????? Mk sim sitatefa manawegezat??? Sitdebedeb setasdebedeb setkefafel setasaser man
  Teye alat????? This is your time mk yemayder
  meslosh neber ende banchi lay.????..non no no no.....yedersal ::yenesu orthodoksoch emba and blood is on your hands. .

  ReplyDelete
 32. Degmo a darash hiduna cheferu yilale ende mahber erkusan yod abisiniya adarash
  ay delem ende beyeweru gubai belew yemisebesebut???? Yenesu aybesem????
  Lemhberu gize chiger yelwom lelelawo sihone
  Mahberwa tawgzalch..wef awogez mahber.

  ReplyDelete
 33. For whom is this building belongs to???? you asked, and you know the answer. Let me remind you. That building infront of Teklay Betekhinet/ and kidist mariam Belongs to the Ethiopian Orthodox church. As a system MK has takken the initiation and built by the money from members and the church followers. Your problem is, << the building will not be rented for protestants and their followers, like aba sereke>> The church knows the purpose of the building, it is for the church service, in BLACK AND WHITE.

  ReplyDelete
 34. That bolding is not our church bilding its not under the church's name its mks ...yenged tekwam...rent it out for Muslims selfewoch cos both mk and selfe belong together. .period::

  ReplyDelete
 35. አባ ሰላማዎች እናነተ እኮ ስለ ማህበረ ቅዱሳን አያገባችሁም። እባካችሁ ስለ ራሳችሁ ድርጅት አውሩ። ለቤተ ክርስቲያን ጠባቂዋ ማን እንደሆነ ሰላማዎች ስለዘነጋችሁት ማህበራት ቢፈርሱ እንኳን ድንጋዮችን አፍ አውጥተው እንዲናገሩ የሚያደርግ፣ አህዮችን የሚያናግር፣ እናንተን በነፋስ አውታር ወጥሮ እውነትን እንድትመሰክሩ ሊይዝ የሚችል አምላክ ስላለን ዝም በሉ፣ በድጋሚ ዝም በሉ

  ReplyDelete
 36. mk is the right hand of the church next to God and holiy sinode  ReplyDelete
 37. I think most of you mk followers are ignorant. .how came you say this the devil's own mahber will be the church s right hand ???not in a million year.they are anti Crist ...when Christians call on Jesus name mk and his followers can't stand. ..they will be upset ...

  ReplyDelete
 38. ሲነቃባችሁ ለፈለፋችሁ አይደል??

  ReplyDelete