Tuesday, April 1, 2014

"ግልፅ አደጋ በሎስ እንጀሎስ አብያተ ክስቲያናት" በሚል ርዕስ ወጥቶ ለነበረው ጽሁፍ መልስ

Read in PDF

ለታዬ ብርሀኑ  ከታዛቢዎች የተሰጠ መልስ
  "ግልፅ አደጋ በሎስ እንጀሎስ አብያተ ክስቲያናት" በሚል ርእስ በታዬ ብርሀኑ ተጽፎ በድሕረ-ገጽ የተለጠፈውን፣ የሰዎችን ስም የሚያጠልሽ አንድ ኣሉቧልታዊ ጽሑፍ ታዝበናል። ስለሆነም አጭር መልስ ሰጥተንበታል። ለመልሱ መዘግየት ምክንያት፡- ከማን፣ ለማን፣ እና ለምን እንደ ተጻፈ ማጣራት ስለ ነበረብን ነው። እንግዲህ፡- ታዬ ብርሀኑ ብለህ ራስህ በመረጠከው ስም እንጠራሃለን። ታዬ! የቦጫረቅኸውና የዘባረቀኸው ኮተቴህ ብዙ ቢሆንም እንሆ አስፈላጊ የሆኑትን ነጥቦች ብቻ አንስተን ምክር አዘል መልስ ሰጥተናል።     
 ፩ኛ. ታዬ! የአባ ጽጌ ድንግል ስም ለማጉደፍና ስብእናቸውን ለማቍሰል ሆን ብለህ፣ ባልዋሉበት ዋሉ፤ ባልነበሩበት ነበሩ፤ ባልተናገሩበትም ተናገሩ ብለህ ጽፈሐል። ይህ ግን ውሸት ከመሆኑም በላይ በሰዎች ግል ሕይወትና መብት ላይ ገብተህ ተቆጣጣሪ የመሆንን ያክል የቃጣኸው ድፍረት ነው። ለምሳሌ፡- ለአባ ጽጌ ድንግል ወያኔነት ቅርባቸው እንደ ሆነ ኣስመስለህ ብዙ ደርድረህባቸዋል።  ነገር ግን ወያነ የሚያሰኛቸውን  በውል አስደግፈህ ማስረጃ ልታቀርብ አልቻልክም። ካሊፎርኒያ እንደሆነ የአመሪካ ጠቅላይ ግዛት እንጂ የወያነ ግዛት አይደለም። ስለሆነም አባ ጽጌ ድንግል በዚህ ዋሉ በዚህም አደሩ በማለት፣ ወያነ የሚያሰኝ ነገር እንደሌላቸው ጠፍቶህ ሳይሆን፣ "ቅንአት አኀዞሙ ለሕዝብ ዓብዳን" እንደሚባለው፣ አንተም እንዲሁ፣ ኣሉቧልታውን በምቀኝነት የጻፍከው ለመሆኑ ሕሊናህ ያውቀዋል። 
 አባ ጽጌ ድንግል፣ ከወያነ በኵል ግኑኝነት ካላቸው ሰዎች ጋራ ይገናኛሉ ለማለት ፈልገህ ከሆነ ግን፣ ይህም ከሓቅ የራቀ ነው። ምክንያቱም፡- አንተ ራስህን እንደ ሰይጣን፣ አቡሃ ለሐሰት ነኝ ብለህ፣ አምነህበት፣ እውነቱን ለመግደል ካልፈለግህ በስተቀር፣ በሎስ አንጀለስ፣ በማናቸውም አብያተ ክርስቲያናት፣ ወያነ የሚያስብል ነጥብ አለ ብለህ ስላመንክ አይደለም። በተለይ ያችን መከረኛይቱ አሮጌዋን ካርድ፣ ባስመሳይ ቅብ ቀባብተህ፣ ከተጣለችበት ቆሻሻ ላይ አንስተህ፣ የተጫወትኽበት ዋናው ምክንያት ግን፣ የሰዎችን ቀልብ ትስብልኝ ይሆናል በሚል አጉል ተስፋ ነው። እንዲሁም ለአሉቧልታህ እንደ ማጣፈጫ፣ ለመዋሸትህም እንደ ቅመም የተጠቀምኽባት መሆኑን ማወቅ ደግሞ ወደ እዮር ሰማይና መልዕለተ ሰማያት የሚመጥቅ፣ ልዩ ተመራማሪ (ሳይንትስት) መሆን አያስፈልገውም።   
 ታዬ! በል እንግዲህ በጨረፍታም ቢሆን እውነቱን እንነጋገር፡- አንተ ራስህ እንደ ኒቆዲሞስ  ውስጥ ውስጡን ከወያነ ኤምባሲዎች ጋራ ስታድር፣ ቀን ቀኑን ግን ከተቃዋሚዎች ጋራ የምትዘፍን አንተ አይደልህምን? አሁን አልታወቅም ብለህ በዚሁ ከምትቃዥ፣ ይልቁን' በምትናገረው ነገር ላይ ስለ እውነት አስብ። አባ ጽጌ ድንግል እዚህ አገር (አሜሪካ) ከገቡ በኋላ አገር ቤት ሄደው አያውቁም። የወያነ አስተዳደር ደግሞ አገር ቤት ነው ያለው። አንተን ግን እዚህ ከወያነ ኤምባሲዎች ጋራ መገናኘት ብቻ ሳይሆን አገር ቤት ድረስ በመሄድም ጭምር ከወያኔዎች ጋራ በቀጥታ ትገናኛለህ። ለምሳሌ፡- ቦሌ ኤርፖርት ስትደርስ ኢህአዴጋዊ ዩኒፎርም ለበስክ፤ ይታዘቡኛል እንኳ አትልም። እንድያውም ሳትጠየቅ፡- እኔ እንደዚህ አደርጋለሁ፤ እንዲህም፣ እንድያም ማድረግ እችላለሁ እያልክ፣ በአዲስ አበባና በክፍለ ሀገር ሁሉ ጉዳይህን ስታሰላስል ነበር የከረምኽው። ተመልሰህ ኤመሪካን ኤርፖርት ስትደርስ ደግሞ የተቃዋሚዎች ካባ ደረብክ። ብዙም ቀባጠርክ፡- እኔ እዛው በአገር ቤት እነደዚህ ሳደርግ፣ እንደዚህም ስሰልል ከረምኩኝ ብለህም እጅ ነሳህ፤ ዋሸህባቸውም። ታዬ! ለመሆኑ፣ እዚያው በአገር ቤት ምንና ምን ሠርተህ እንደ መጣህና ምን ኢየሠራህ እንደ ሆነስ በእውነት ከሰው የተሰወረ ይመስልሃልን?   ወይ ያለማፈር! በአሉቧልታው ቀጠልክበትና፣ "በሁለት ባላ ላይ መንጠልጠል ነው" ስትልም ተችተሃል። ይህ' ምን ለማለት ፈልገህ ይሆን? ጉድ እኮ ነው። 
 ታዬ! ከሁለት ባላ ላይ አንጋጦ የተንጠለጠለው' አንተ ነህ። ምክንያቱም፡- ከኦርቶዶክስ ያይደለ፤ ከጴንጤውም ያይደለ፤ እንዲሁ በማኸል የሚዋልል፣ የተንጠለጠለ እና ድፍረት ያጣ ሰው፣ ጴንጤ-ዶክስ ይሉታል። በሁለት ባላ ላይ መንጠልጠል ማለት ይህ ነው ነቃፊ ብቻም አትሁን! ...አስቀድመህ በራስህ ዐይን ያለውን ጕድፍ አውጣ፤ ሌሎችን ከመንቀፍህ በፊት ራስህንም ንቀፍ፤ ጠንቀቅ ማለቱም ብልህነት ነው እንላለን። ይህን ግን እንደ ቤተ ሰብ ምክር ብትቀበለው ይጠቅምሃል እንጂ አይጐዳህም። ስለዚህ ግድ የለህም "ምክር ሠናይት ለኵሉ ዘይገብራ"  እንዳለው ነውና ይህንን ምክር ተጠቀምበት።    ፪ኛ. ታዬ! በማታውቀው ነገር፣ ያልነበርክበትንም ታሪክ የምትጽፍ ሰው ነህናቤተ ክርስቲያንን የከፋፈለበማለት ስማቸውን ለማጠልሸት የሞከርከው ሌላው ደግሞ ቄስ ሙሴ ናቸው። ቄስ ሙሴ ይህነን ቤተ ክርስቲያን ከፈሉ ብለህ ያቀረብከው ማስረጃ ግን የለም። ቄስ ሙሴን መጨመር የፈልግክበት ጉዳይ ግን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታና ለሁከት ማቀጣጠያ ነዶ ይጠቅመኝ ይሆናል በሚል ክፉ አስተሳሰብ የረጨኸው
አርዮሳዊ መርዝ መሆኑንም እንዲያው ሳይታለም የተፈታ ነው። ምክንያቱም አንተ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነትና ስለ ሰላም መቼውም ቢሆን ሕሊናህ አስቦት አያውቅም። አንተ ክፉ ሰው፣ ነገሮችን በዚህም በዚያም በማዋከብ፣ የአማኙን የሰላማዊውን ሕዝብ ልቦና ለማስቀየጥና ለማታለል ሁሌ የማታድርገው ነገር የለም። ማንኛውም ነገር፣ ይጠቅመኛል የምትለውን ነገር ሁሉ ማድረግ እንጂ ስለ ፈሪሐ እግዚአብሔር የምታስብ ፍጡር አይደለህም። እንደ ሰይጣን በክርክር፣ በግርግርና በጠብ ማኸል ተውሽቀህ ለመኖር የምትመርጥ፤ ለካፊ፣ ጭር ሲል አልወድም ባይ ነህ። ፈሪሐ እግዚአብሔር ያለህና ሰለ ሰላም የምታስብ ቢሆን ኖሮማ፣ አራምባና ቆቦ በሆነ መልኩ፣ በሁለቱም አባቶች ማኽል ላይ ሳያገባህ ገብተህ፣ ሰላማቸውን ለማደፍረስ ባልጣርክ ነበር። ታዬ! በዚህ በኵል ባይሳካልህ ነው እንጂ፣ በአብያተ ክርስቲያን እና በአባቶች መካከል ለምን ሰላም ይሆናል ብለህ ነበረ ብዙም የከጀልኸው። ...ሌላው' ምን አደረጉ?   ሓፍረተ አልባ ደፋሩ ታዬ! መቼ እዚህ ላይ ኣቆምኽና ቀጠልክበት እንጂ። 
 አባ ጽጌ ድንግልን፣ ከተወገዘው ከቄስ ሙሴ ጋራ፣ አብረው ይቀድሳሉ ስትልም ተችተህባቸዋል። እስቲ ስለ ቅዳሴው ይቆይልንና ስለ ውግዘት ትንሽ እንበል። በመጀመሪያ፣ አንተ ስለ ውግዘት እንዲሁ በድፍረት መናገርህ ራሱ ያስቃል እንበልህ ወይስ ያስገርማል? ምክንያቱም ስለ መወገዝና ውግዘት አንተን መንገር ማለት ቀባሪውን ማርዳት ስለሚሆን፣ ያው ...ባጭሩ እንደ ምታውቀው ነው። ሊቀ ካህናት ሙሴ ግን የሚወገዙበትና የተወገዙበት ምንም ምክንያት የለም። ታድያ ምን አደረግህ ተብለው ተወገዙ? በማን? መቼ ተወገዙ? ፀረ መላእክት ተብሏልን? ፀረ ጻድቃን ተብሏል? ፀረ ሰማዕታት ተብለው ነው? እንዴት ተወገዙ? ፀረ ተዋህዶ ተብለው ነው? ፀረ ማርያም ተብለው ነው የተወገዙት? ጰንጤ ተብለው ነው ወይስ ጰንጤ-ዶክስ ተብለው የተወገዙት?   ኧረ! ኧረእ! ...ወንድማችን ታዬ፣ በመስተዋት ውስጥ የሚኖር ሰው የመጀመርያዋን ድንጋይ አይወረውርም የተባለውን' አልሰማህምን? ይሄስ በእውንት ድፍረት ብቻም ሳይሆን ሞኝነት የሌለብህ መሆንህንም ማረጋገጫ አይገኝልህም። ያለማፈርህና  ምን ያህል ዓይንህን በጨው አጥበህ ሰውን ልታሞኝ መሞከርህን ግን ገርሞናል። በግራሞት ብቻ የሚታለፍ ሆኖ ስለላገኘነው ደግሞ እንሆ ይህነን አጭር ምክር አዘል መልስ ለመጻፍ ተገደናል።   ታየ! ወንጌልን ስለ መታጠቅ በተመለከተም ብዙ ብለሃል።  
በወንጌል የሚያምን መንፈሳዊ ሰው ግን የሰው ስም በከንቱ አያነሳም፤ ለሓሜትና ለአሉቧልታ ጊዜ አይኖረውም፤ ክፋትም በልቡ የለም። ክርስትያናዊ ሕይወት ያለው፣ የእግዚአብሔር ሰው በዚህ ይታወቃል። አንተን ግን በውነት በገዛ ፈቃድህ ወንጄልን ታጠቅህ እንጂ ወንጌልን' አልታጠቅህም። ፈሪሳዊ መናፍቅ ሰው ከወንጌል ጋራ ምን ግኑኝነት አለውና፤ እንዴት ብትል? በቃል የምትሸመድደውን ያኽል፣ በጣትህ እንኳ የምትነካው አይደለህም፤ ይህ ደግሞ ፈሪሳዊነትህን ያመለክታል። ምክንያቱም ከመዝ ግበሩ ወከመዝ ንግሩ የሚለውን በወንጌሉ ቃል ሰውን የምታታልልና ኑሮህን የምትገፋ ሰው ነህ እንጂ በፍጹም ራስህን የምታድን፣ የመንፈሳዊነትና ክርስቲያናዊ ሕይወት ትርጉም እምታውቅ ሰው ግን አይደለም።  ታዬ! ይህ እውነት ካልሆነ፣ ታድያ የተኛው ወንጌል ነው ከእንተርኔት መስኮት በስተጀርባ ሆነህ የሰውን ስም አጥፋ፣ ግደል፤ የእፉኝትን መርዝ ትፋበት ብሎ ያዘዘህ? የቱኛው ወንጌል ነው ታዬ? እባክህ ተወን እንጂ! ወንጌለ መንግሥት' ሁሌም እውነት ናት፤ ታጋሽ ናት፤ የርኅራሄ፣ የሰላም፣ የይቅርታና የፍቅር እናት ናት። ወንጌል የዓለማዊ ኑሮ መጠቀምያ አይደለችም፤ አንተ እንደ ምትፈልጋት ዓይነት ግርግረኛ፣ አስመሳይ አይደለችም። ወንጌለ መንግሥት፣ የመንፈሳዊ ሕይወት ምግብ እንጂ የሐሜትና የአሉቧልታ መርዝ አይደለችም። ኦርቶዶክሳዊት እንጂ የጥረጥር፣ የክህደትና የመገለባበጥ መሣርያም አይደለችም። እውነቱ ይህ ነው፡- የሰው ስም ጥላ-ሸት መቀባት፣ ሐሜት፣ ክፋትና መቀኝነት ግን ነውር ብቻ ስይሆን ኃጢአትም ነው፤ እግዚአብሔርም አይወደውም።   ክፉዎችና ምቀኞች በእግዚአብሔር ፊት መቆም ኣይቻላቸም። ምክንያቱም፣ "...እግዚኦ መኑ ይቀውም ውስተ መካነ መቅደሱ" ካላ በኋላ፡ "...ዘንጹህ ልቡ ወንጹህ እደዊሁ፤ ወዘኢነሥኣ  ከንቶ በላእለ ቢፁ" የሚለውን የእግዚአብሔር ቃልና ምክር ማሳታወስ በተገባ ነበር።   በል ታዬ! አሁንም ቢሆን አልመሸም፤ ጌታ ወደ እውነት እንዲ መልስህ፣ ይቅር እንዲልህም ንስሐ ገብተህ ጸልይበት።  
እግዚአብሔር ትዕግሥቱንና ይሉኝታውን እንዲችርህ ፈቃዱ ይሁን።   

6 comments:

 1. Aba Selamawoch bewnet abba tsegay ke andualem gar tebabrew eyadergut yalwen eyawekachew endzi maletachu betam yegermal:: yewnet degafiwoch temeselun neber?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yehe yeaba selama sehuf aydelem eko! yeleloche new. ketazabi eyale. aba selama neza medrek mehonewan masaya engi. sehufun tedegefaleche malet aydelem.

   Delete
 2. Betam des yemil ye april fool tsehuf new
  Selaskachun betam enmsegnal

  ReplyDelete
 3. hi guys aba selama you gonna be crazy aba tsege is a fake monk he puts the church in trouble with andulem dagemawi.
  andulem dagemawi is anti- christ and the agent of MK . Aba tsege loves power for attacking his brothers.

  ReplyDelete
 4. wey gud, yehen yetsafut Aba Tsige sayhonu aykerum. Accsentachew yastawikal. This is how he talks. The sad thing is, it is non sense. No fact at all. Teret teret ena sidib bicha. I think betam tenadewal.

  ReplyDelete
 5. Aba Tsege; melse yemistfu kehone eko bedenb tsafu enji; yajaw beewnet yetedegefe yihe alubalta sidib betcha minun melse hone? Segw hulu sirawoton awkwal minim melse ayasfeligim. Firdu ke Egziabher negw; aye ya ken simeta....

  ReplyDelete