Tuesday, April 1, 2014

የማይጠቅም ጩኸት                                            Read in PDF                  
 በጊዜው አበራ
በመጽሐፈ  ቅዳሴ  (ቅዳሴ  ያዕቆብ),አሜሃ  ይከውን  ክላህ  ዘኢይበቊዕ  ክላህ.   ትርጉም፦  በዚያን  ጊዜ  ጩኸት  ይሆናል።  የማይጠቅም  ጩኸት  ነው.  ይላል።  ጩኸት   በጊዜና  በአግባብ  ሲሆን  ከዕርዳታ  ያደርሳል።  ከሰውም  ጆሮ  አልፎ  በእግዚአብሔር  ዙፋን   ፊት  ይሰማል።  እንደ  ፈቃዱም  ፈጣን  ውሳኔንን  ያሰጣል።  አባቶች  ,የማይረባ  ጸሎት   ለጋኔን  አሳልፎ  ይሰጣል.  እንዲሉ  ያለቦታውና  ያለአግባብ  የሚሆን  ጩኸትም  ዕርዳታ   ሳይሆን  የኃይል  ፍጆታ  ብቻ  ይሆናል።    
የሊቁን  ቃል  እንደ  መንደርደሪያ  ተጠቀምኩ፥  ሀሳቤ  ግን  በዚህ  ሰሞን  በማቅ  ብሎጎች   ስለሚሰማው  ጩኸት  አንድ  ለማለት  ነው።  ማቅ  ሙሉ  ጊዜውን  ከሚጠቀምበት  ከሐራ   ተዋሕዶ  እና ከግርግሩ አንድ አድርገን ብሎግ  ሌላ  ለአንድ  ዓመት፣ ታይም  አውት   (Timeout)  ያላትን  ደጀ   ሰላም   ለጦርነት  ፍጆታ  አንቀሳቅሷል።  መስቀል  ያየ  ጋኔንየመጨረሻ  ቀኔ  ነው ለቀቅሁ  እንዲል  ማቅ  ማንም  ሳይደርስበት  ሥራውን  ስለሚያውቅ  ጩኸቱን  ተያይዞታል።      
ማቅን  አንዴ  ከቤተ  ክህነቱ፤  አንዴም  ከቤተ  መንግሥቱ  እንደ  አበደች  ውሻ  እንዲላከፍ   የሚያደርገው  ምንድነው?  በውስጡ  ደብቆ  የሚንቀሳቀስበትን  ፖለቲካዊ  ድርጅትነቱን   በይፋ  የሚያውጀውስለምንድር ነው?  ለዘመናት  በወንድሞች ላይ ያደረሰው ሰቆቃ  ልቡን አሳውሮ መንፈሱን አስጨንቆ አስክሮት  ይሆን?  ወይስ   እንደጋኔኑ  የመልቀቂያ እና ቤተክርስቲያኒቱን ተጣብቆ ሲያደርግ የነበረው ውንብድና ፍጻሜው መድረሱን “የጥፋት ሩጫውን መጨረሱ” እና ግብዐ-መሬቱ  መቃረቡ  ታይቶት  ይሆን?     በጩኸት  ቅኝቱ  ቤተ  ክህነትን፤  ቤተ  መንግሥትንና  ለዘመናት  ቤተ ክርስቲያንን  ያገለገሉ   ግለሰቦችን  ስም  በማጥፋት  ሽፋን  ማንነቱንና  አሁን  የከፈተውን  የጦርነት  ዓላማ  ለመደበቅ  ቢሞክርም  እውነቱ  ግን  ከማንም  የተሠወረ አይደለም፡፡

  1. ማንነቱ
  ማቅ  የሚገመገመው  እርሱ  ራሱ  ሌሎችን  ወንድሞች  በግምትና  በበቀል  እንደሚገምት  ይሆን  በራሱ  ጽሑፍ፤  በሚታየው  የነፍሰ  ገዳይነት  ሥራው  ነው።  ሰሞኑን  ብሎጎቹ   በሚያራግቡት  ጽሑፍ  ማቅ  ድርጅቱን  የምሁራን  ስብስብ፤  የሊቃውንት  መፍለቂያ   እንዲሁም  ጠቅላላ  የኦርቶዶክስ  ተዋሕዶ  ቤተ  ክርስቲያን  ምዕመናን  የራስዋ  የቤተ   ክርስቲያንዋ  ሳይሆኑ  የእርሱ  የድርጅቱ  አባላቶች  መሆናቸውንና  ሀገሪቱንና  ቤተ   ክርስቲያንዋንም  የማፍረስ  ኃይል  እነርሱ  ብቻ  ያላቸው  መሆኑን  አረጋግጦ  የፉከራ   ጩኸቱን  አስነብቦናል።    
ውሸትና  ቅጥፈት  ለማቅ  አዲስ  ነገር  ባይሆንም  ጽሑፎቹን  ለምናነብና  ገሀድ  የሆነ   ተግባሩን  ለምናውቅ  ግን  እጅግ  አስገራሚ  ነው።  ማቅ  የማቆች  ስብስብ  ሊሆን  ይችላል   እንጂ  የቤተ  ክርስቲያን  ሊቃውንት  ስብስብ  እንዴት  ሊሆን  ይችላል?  ያውም በሦስት ወር ኮርስ፡፡ የቤተ  ክርስቲያንን   ብርቅዬ  ሊቃውንት  ከቤተ  ክርስቲያን  አስወጥቶ  ለፕሮቴስታንት  እጅ  መንሻ  አድርጎ   የሰጠ  ነብሰ  በላ  ድርጅት  ነው።  የደበደባቸውን፤  አካለ  ስንኩል  ያደረጋቸውንና   የገደላቸውን  ቤት  ይቁጠረው።  የምሁራን  ስብስብ  ምሁራንን  እንዴት  ያሳድዳል? እንዲያው እኛ እንደምናውቀው ከሆነ ማቅ የቤተክርስቲያንን ሊቃውንት የሚጠላው የሚያሳድደውና የሚገድለው በዩንቨርሲቲ ዲግሪ ሸፍኖ በሶስት ወር ኮርስ ደረስኩበት ያለውን ሊቅነት ከንቱ የሚያደርግና መንፈሳዊ እውቀት ስላላቸው እነርሱን ባስወግድ ማን አላዋቂነቴን ይገልጥብኛል ከሚል የሰነፍ ተንኮል ተነስቶ ነው ፡፡የማቅ   ሚዛን  የእራሱን  ዓላማ  ማራመድ  እንጂ  የቤተ  ክርስቲያን  ሰው  መሆን  እንዳይደለ   ተግባሩ  ይመሠክራል።    
ማቅ  አጥብቆ  ከሚጠላቸውና  ጦርነት  ከከፈተባቸው  መካከል  ብዙዎቹ  ማቅ  በውትድርና   ማሰልጠኛ  ሳይወለድ  በፊት  አያሌ  ሊቃውንትን  አስተምረው  ለቤተ  ክርስቲያንዋ  ያበረከቱ   ሲሆኑ  በማቅ  በኩል  ግን  ሚዛን  አልደፉም።  ለምን?  የተማሩትን  ኦርቶዶክሳዊ   ትምህርታቸውን  ክደው  ከማቅ  ጋር  የፖለቲካ  አቀንቃኝ መሆን  ስላልቻሉ  ብቻ   ነው።  ይሄ ነው የማቅ ሚዛኑ!! ታዲያ  የቤተ  ክርስቲያንን  ብርቅዬ  መተኪያ  የሌላቸውን  አባቶች  የሚያሳድድ   የመንደር  አክሲዮን  እንዴት  የሊቃውንት  ስብስብ  ነኝ  ይለናል?
     በእርግጥም  ማቅ  በግቢ  ጉባኤ  የማቃዊ  ክርስትና  ክር  ያላሰረላቸው  ሊቃውንት  ሁሉ   በእርሱ  ዘንድ  ከቤተ  ክርስቲያን  መሰደድ፤  ለፕሮቴስታንት  ገቢ  መሆን  አለባቸው  ብሎ  ያምናል።  በዚህ  አጋጣሚ  አንባቢው  በአስተውሎት  እንዲመለከት  የሚጠየቀው  ቢኖር   በሀገር  ውስጥም  ሆነ  በውስጭ  ሀገር  ያሉ  እውነተኛውን  ኦርቶዶክሳዊ  አስተምህሮ   የሚያስተምሩ፤  ቀድሰው  የሚያቆርቡ  ሊቃውንት፤  ኦርቶዶክስን  ለጥቅም  ሳይሆን   በእምነትና  ለእምነት  የሚኖሩ  አባቶችና  እንድሞች  ሁሉ  በማቅ  የተወገዙ  ናቸው።   ለምን?  መልሱ  ማቅ  መሆን  ስላልቻሉ  ነው።  ማቅን  መሆን  ደግሞ  ህሊናን  መሸጥ   ስለሆነ  ከሞት  ይከፋል።    
ማቅ  በከፈተው  የጦር  ቀጠናው  ውስጥ  ስናየው  የሌት  (የሌሊት)  ወፍን  ይወክላል።   በሀገራችን  አባባል  ለምሳሌነገር  የሚመሰልና  የሚጠቀስ  አባባል  አለ።  እርሱም   ,የሌሊት  ወፍ.  የሚል  ገጸ  ባህርይ  ነው።  ወፏ  ሌሊት  ሌሊት  ,እኔ  ክንፍ  አለኝ   እበራለሁኝና  ወፍ  ነኝ.  ስትል  ቀን  ቀን  ደግሞ  ,እኔ  አይጥ  ነኝ፤  ክንፍም  የለኝም።   ኑሮዬ  በጉድጓድ  ውስጥ  ነው፡፡ ጥርሴም ምስክር ነው  ትላላች  ይባላል።  ማቅ  ሲያሰኘው  ድብቁ  አጀንዳው   ድንገት  ሲያፈተልክበት  እንደ  አንድ  የፖለቲካ  ፓርቲ  እራሱን  ወክሎ  በፖለቲካ  ሜዳ   ይቧርቃል።  አልመች  ሲለው  ደግሞ  የቤተ  ክርስቲያን  ልጅ  ነኝ  ይላል።  ይህንን   መሠሪነቱን  ግን  የራሱ  ተከታዮች  የሆኑ  አባላት  እንኳ  ብዙዎቹ  የሚያስተውሉት   አይደለም።      
ለምሳሌ  ከመሪዎቹ  ሌላ  ተከታዮቹ  የማቅን  ሥራ  በትክክል  ቢረዱ  በፍጹም   የማይስማሙበትን  አንዳንድ  ሥራዎቹን  ብንመለከት፦      
.  ለቤተ  ክርስቲያን  ብቻ  የተፈቀደ  የእግዚአብሔር   ገንዘብ   (አሥራት  በኩራት)  ሰብሳቢ  መሆኑ    
ይኽንን  ሳያፍር  የቤተ  ክርስቲያንን  ሥርዓትና  ደንብ  በመጣስ  ተከታዮቹንም   በመናቅ  በጽሑፍ  አስፍሮ  ያስነብበናል።  ከዚህ  የበለጠ  የቤተ  ክርስቲያንን  ቀኖና  መጣስ   አለ?  የሚገርመው  ሥርዓት  አፍራሹ  ማቅ  የቤተ  ክርስቲያን  ዘብ  ነኝ  ማለቱ  ነው።   ታዲያ  ይኽ  ጠባዩ  ,የሌሊት  ወፍ  አያሰኘውም?    
ከቤተ  ክርስቲያን  ከዘረፈው  ገንዘብ፤  በአብነት  /ቤቶች  ስም፤  በገዳማት  ስም   በሰበሰበው  የቤተ  ክርስቲያን  አንጡራ  ገንዘብ  ሆቴሎችን፤  የምግብና  የመጠጥ  ቤቶችን፤   ልዩ  ልዩ  ሱቆችን፤  ሕንጻዎችን  ተሽከርካሪዎችን  በየክፍላ  ሀገር፤  በየወረዳዎችና   በየአጥቢያ  አብያተ  ክርስቲያናት  አቋቊሞ  ይነግዳል።  ታዲያ  ማቅን  ከየት   እንመድበው?  ነጋዴ  ነው?  የፖለቲካ  ፓርቲ  ነው?  ወይስ  ለቤተ  ክርስቲያን  የሚሠራ   የቤተ  ክርስቲያን  ልጅ  ነው?  የቤተ  ክርስቲያን  ልጅ  ከሆነ  ሌላ  ካዝና  ሊኖረው  አይገባም   ነበር።  ቢኖረውም  እንኳ  የቤተ  ክርስቲያንዋ  የከፍተኛ  አማራር  ክፍል  የሆነው  ቤተ   ክህነት  የሚያውቀውና፤  የሚቆጣጠረው፤  ኦዲት  የሚያደርገው  መሆን  ነበረበት።   ,የመጨረሻዬ  ቀን  ነው.  የሚለው  ጩኸቱም  ለምን  ኦዲት  እደረጋለሁ?  ለምንስ   ፓትርያሪኩም  ሆኑ  ቤተ  ክህነቱ  እኔ  በአልኩት  አይሔዱም?  የሚል  መሆኑን  አንባቢ   ይመለከተዋል።        
ለ.ራሱን  ቅዱስ  ሲኖዶስ  አድርጎ  ማስቀመጡ  ነው።          
የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋሕዶ  ቤተ  ክርስቲያን  ተከታይ  የሆነ  ሁሉ  ስወርድ   ሲዋረድ  የመጣውን  ሃይማኖተ  አበውን፤  ሥርዓተ  አበውንና  ቀኖናን  የሚቀበል  ሁሉ   የቤተ  ክርስቲያን  የበላይ  አመራር  ቅዱስ  ሲኖዶስ  መሆኑን  ያምናል።  ከቅዱስ  ሲኖዶስ   በላይ  የቤተ  ክርስቲያን  መሪ  የሆነው  መንፈስ  ቅዱስ  ብቻ  መሆኑንም  ይቀበላል።  ለማቅ   ግን  ይኽ  አልተዋጠለትም።  ከቅዱስ  ሲኖዶስ  የወጡ  መመሪያዎችን  ሁሉ  አልተቀበለም።   በዚያ  ፋንታ  የራሱን  እየተካ፤  በሚጋልባቸው  ህሊና  አልባዎቹ  ጳጳሳት  ለቅዱስ  ሲኖዶሱ   ሥራ  ሁሉ  እንቅፋት  መሆኑ  የአደባባይ  ምሥጢር  ነው።  እንደ  ቦይ  ውኃ  የሚፈሱለት   ጳጳሳትም  አንደኛ  የአመለካከት  ዝንባሌያቸው  ከማቅ  የተሻለ  ባለመሆኑና በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ንቃተ ህሊናቸው ደካማ በመሆኑና ማቅ  አስቀድሞ  በተካነበት  የመሠሪነት  ሥራ  የነውር  ገበናቸውን  መዝግቦ  በዚያ  ኢያስፈራራ   ስለገዛቸው  ነው።  ለመረጃ  ያክልም፦  የአቡነ  ሉቃስን  የአቡነ  ሳሙኤልንና  የአቡነ   ገብርኤልን  ታሪክ  መመልከት  ብቻ  በቂ  ይመስለኛል።  ታዲያ  ለቅዱስ  ሲኖዶስ   የማይታዘዝ  እንዴት  የኦርቶዶክስ  ተዋሕዶ  ቤተ  ክርስቲያን  ዘብ  ነኝ  ይላል?  ባለማወቅ  ገንዘብህን  እያባከንክ፤  ቅድስት  ቤተ  ክርስቲያንህንም  እየጎዳ  ያለህ  የድርጅቱ  ሰለባ   የሆንክ  ሁሉ  ቆም  ብለህ  ልታስብ  ይገባሃል።      
ማቅ  በብፁዕ  አቡነ  ማቴዎስ  ይቅርታ  እንዲጠይቅ  ለተጻፈበት  የበላይ  መመሪያ  የሰጠው   ምላሽ  የለም።  አንደኛ  መንፈሱ  የይቅርታ  ሳይሆን  የሽብር  መንፈስ  ስለሆነ  ቦታ   አልሰጠውም።  ሁለተኛ  ሌሎችን  አባቶች  ሲያብጠለጥል  በአቡነ  ማቴዎስ  ላይ  ግን  ምንም   ከማለት  ተቆጥቧል።  ይኽም፦  አቡነ  ማቴዎስ፦  
(1)  ገና ልባቸው በማቅ ላይ ስላልጨከነና  
(2)  የዘረኝነት  ጉዳይም  ስለሆነበት  ነው።  ስለዚህ  አቡነ  ማቴዎስን  ከመጋፈጥ  ይልቅ   አቡነ  ሉቃስን  ኮርነር  ላይ  ማውጣት  ምርጫው  አስርጓል።      
    ራሱን  የሊቃውንት  ጉባኤ  አድርጎ  መሰየሙ።      
 ማቅ  ሳያፍር  የሊቃውንት  ስብስብ  ነኝ  ብሎ  እንደሚናገረው  የሃይማኖቱና   የሥርዓቱ  ወሳኝና  አውጋዥ  ክፍል  ሆኖ  ይስተዋላል።  ታላቋ  ቤተ  ክርስቲያን፤  ለዘመናት   ያፈራቻቸው  ሊቃውንትን  የስም  ማጥፋት  ቅባቱን  እየቀባ፤  የማይወክላትንና   የማያውቃትን  ቤተ  ክርስቲያን  ሲያምሳት  ዓመታትን  አስቆጥሯል።  አሁን  በመጨረሻ   ድብቅ  አጀንዳውን  ያወቁበትንና  ምሥጢሩን  የተረዱትን  የአዲስ  አበባ  አድባራትና   ገዳማት  አስተዳዳሪዎችን ቤተክርስቲያንን በመዋቅር ለውጥ ስም ለብቻህ አትቆጣጠርም ስላሉት እና በግልጽም ስለተቃወሙት ለምን ተቃወማችሁኝ በሚል መንፈስ አማሳኞች እያለ  ይጠራቸዋል።  ,የአብዬን  ወደ  እምዬ፤   የእምዬን  ወደ  አብ  ይላችኋል  ይኼ  ነው።      
 2. ለብፁዕ  ወቅዱስ  አቡነ  ማትያስ  የማይመለከታቸውን  ስምና  ገጸ  ባህርይ   ለምን  ሰጣቸው ?    
 2.1ይህ   ብዙ  ማሰብና  መርመር  የሚያስፈልገው  አይመስለኝም።  በአጭሩ   ቅዱስነታቸው  በሕይወታቸውም  ሆነ  በሥራቸው  አካሔድ  ከማቅ  ጋር  በምንም  መልኩ   ሊስማሙ  አይችሉም።  ቅዱስነታቸው  የእድሜ  ባለጸጋ  አረጋዊ፤  በቤተ  ክርስቲያን   እውቀት  የበሰሉ፤  ከሁሉም  በላይ  መንፈሳዊና  አባታዊ  ግርማቸው  ለቤተ  ክርስቲያን   ትልቅ  ሞገስ  የሰጠ  አባት  ናቸው።  በዓላማም  በቤተ  ክህነቱ  ውስጥ  እድሜ  ጠገብ  የሆነ   ሙስናን፤  ዘረኝነትንና  ግላዊ  ጥቅም  ላይ  የተመሠረተ  አድልዎን  ለማስወገድ  ታጥቀውና   ቆርጠው  የተነሱ  ታላቅ  አባት  ናቸው።  ለዚህ  ደግሞ  የመጀመሪያ  ገፈት  ቀማሽ   የሚሆነው  ማቅ  መሆኑ  አያጠራጥርም።  ምክንያቱም  በኦርቶዶክስ  ተዋሕዶ  ቤተ   ክርስቲያን  ውስጥ  እንደ  ማቅ  በሙስና  የሠከረ፤  ሊቃነ  ጳጳሳቱን  እርስበርስ   እንዲለያዩ፤  ቤተ  ክርስቲያን  በአስተምህሮም  ሆነ  በአስተዳደር  እንድትታወክ  ያደረገና ያማሰነ   ሌላ አይገኝምና  ነው።    
2.2 ማቅ   ከኢሕአዴግ  መንግሥት  ጋር  ፓትርያሪክ  ማትያስን  ማቆራኘት   ለምን  ፈለገ ?   የፖለቲካ  ተንታኞች  በአንዱ  ተጠግቶ  ሌላውን  የመውጋት  ሥልትን  (Proxy Ware)     ይሉታል።  ማቅ  ፓትርያሪኩ  ለድብቅ  ዓላማው  ስላልተመቹት  ከኢህአዴግ  ጋር  በማቆራኘት   ከእርሱ  ቅጥፈትና  ፖሮፓጋንዳ  የተነሳም  ሕዝቡ  ቅዱስነታቸውን  እንዲጠሉ፤  የፖለቲካ   ድርጅቶችን  ጨምሮ  አጋዥ  አድርጎ  ለማነሳሳት  ሞክሯል።  እስላሞቹንም  ለመቀስቀስ   የተቻለውን  ያክል  ዶስክሯል።  ለመሆኑ  ቤተ  ክርስቲያን  ቅዱስ  ብላ  በተቀደሰው  መንበሯ   ላይ  የሰየመችውን  አባት  አልታዘዝም፤  መመሪያም  አልቀበልም  ማለት  ብሎም  ስም   ማጥፋትና  የቤተ  ክርስቲያንን  ገበና  በአየር  ላይ  መዝራት  ከቤተ  ክርስቲያን  ልጆች   ይጠበቃል?  ቤተ  ክርስቲያን  ለጠላቶቿ  መዘባበቻ  እንድትሆን  የሚያደርግ  ድርጅት  የቤተ   ክርስቲያን  ዘብ  ነኝ  እንዴት  ይላል?  መልሱ  ለአንባቢያን  ይተዋል።    
የቅዱስ  ፓትርያሪኩ  ክብረ  ነክ  የሆነ  ፎቶን  በሚዲያ  መለጠፍ  የግለሰቡን  ሕይወት   የሚመለከት  ሳይሆን  የቤተ  ክርስቲያንን  ክብር  የሚያጎድፍ  ነው።  ቅዱስነታቸው   የወከሏት  ታላቋን  የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ  ተዋሕዶ  ቤተ  ክርስቲያንን  ነውና።  ስለዚህ   ,የሊቃውንት  ስብስብ  ነኝ.  ባዩ  ማቅ  ኦርቶዶክሳዊት  ተዋሕዶ  ቤተ  ክርስቲያናችንን   እንደደፈረ  ሊታወቅ  ይገባል።  አንድ  ሊባልም  የሚገባ  ነው።    
በመሠረቱ  የቀለም  ወይም  የስም  መቀያየር  ማንነትን  አይለውጥም።  ማቅ  ያልሆነውን   ነኝ  ቢለንም  ማንነቱ  ግን  ለእውነትና  ለቤተ  ክርስቲያን  ሥርዓት  የማይታዘዝ፤  ቋንቋውም   ሆነ  ተግባሩ  ፍጹም  ከክርስትና  የራቀ  መሆኑን  ነው  የሚያሳየው።      
2.3በዕለተ  ስቅለት  ሕዝቡን  ለሁከትና  ለጦርነት  እንዲሰለፍ  ማወጅ   የእብደት  ወይስ  ጠፍቶ  የማጥፋት  ዓላማ?  
ከላይ  እንደ  ጠቀስኩ  ማቅ  ጋጠወጥ፤  ሥርዓት  አልበኛ  ስለሆነ  የሚያካሔደው  ሁሉ   ማንነቱን  የሚያጋልጥ  ነው።  ከመንበረ  ፓትርያሪክ  እስከ  አጥቢያ  ቤተ  ክርስቲያን  ድረስ   መዋቅራዊ  አስተዳደርን  ዘርግታ  በብዙ  ሚሊዮን  የሚቆጠሩ  ምዕመናንን  የምትመራ  ታላቋ   ቤተ  ክርስቲያንን  በመድፈር፤  ምንም  ዓይነት  ፈቃድ  ከሚመለከተው  ክፍል  ሳይሰጠው   በምን  አለብኝነት  ሕዝበ  ክርስቲያኑን  ለሰላማዊ  ሰልፍ  መጥራት  ታላቅ  ድፍረት  ነው።   ከሁሉም  በላይ  በዕለተ  ስቅለት፤  ምዕመናን  የጌታን  ስቅለትንና  ሞትን  እያዘከሩ፤   በበደላቸው  እያለቀሱ፤  ለነፍሳቸው  ምህረትን  በሚለምኑበት  ቀን  ለጦርነት  ውጡ  ማለት   የተቃዋሚው    መንፈስ  እንጂ  ሌላ  ሊሆን  አይችልም።  ይኽ  ነው  እንግዲህ  የምሁራን   ስብስብ ነኝ ፣  የቤተ  ክርስቲያን  ልጅ  ነኝ  ባዩ።  
በሌላም  በኩል    የግብር ወንድሙ ከሆነው ሰለፊያ  ተብሎ   ከሚጠራው  የሙስሊሙ  የአክራሪ  ክንፍ  ጋር  ራሱን   መድቧል።  የሙስሊሙ  አክራሪዎች  ሁል  ጊዜ  በሰላማዊ  ሰልፍ  አመካኝተው  ሽብርን   የሚፈጥሩ፤  በሰላማዊው  ሕዝብ  ላይ  ቦምብ  የሚያፈነዱት  በበዓላቸው  ጊዜ፤  ቅዱስ   በሚሉት  ቦታቸው  ላይ  እንደሆነ  ይታወቃል።  ማቅ  ከዚህ  ኮርስ  የወሰደ  ይመስላል   በታላቁ  በዓል፤  በዕለተ-ስቅለት  ቤተ  ክርስቲያናችንን  የጦር  አውድማ  ለማድረግ   ያሰበው።       
3.   የማቅ  ሰለባ  ለሆኑ  ጳጳሳት  
በማወቅም  ባለማወቅም  የነፍሰበላው  ድርጅት  አባል  የሆናችሁ፤  በመምራት  ፋንታ   ተመሪዎች  የሆናችሁ  ጳጳሳት  ቆም  ብላችሁ  የሾማችሁን  መንፈስ  ቅዱስን  አስቡ።   ልታገለግልዋት  በመንበሯ  የተሰየማችሁ  አባቶች  ቤተ  ክርስቲያንን  ተመልከቱ።   ሀብት፤ንብረት  ይቀራል።  ክብርም  ያልፋል።  ታሪክ  ግን  ሲዘከር  ይኖራል።  ,ቀናችን   ደረሰ.  እያሉ  የሚጮኹ  ልጆቻችሁን  ለሁከት  ከማበራታታት  ታቅባችሁ  አጭዋኺው   መንፈስ  እንዲለቃቸው  ወንጌላችሁንና  መስቀላችሁን  አውጡ።  ለልጆች  አርአያ   የምትሆኑ፤  የምትመሩአቸው  አባቶች  ናችሁ  እንጂ  የልጆች  ሥራ  ሠሪዎች  ወይም   የልጆች  ተላላኪዎች  አይደላችሁም።  እንደሚታወቀው  በቅዱስ  ሲኖዶስና  በጠቅላይ  ቤተ   ክህነት  የሚወሰኑ  ውሳኔዎችን፤  እንዲሁም  የቤተ  ክርስቲያን  የውስጥ  ገበናን  ውስጥ   ለውጥ  የምታቀብሉ፤  ለዚህ  ድርጅትም  ሆነ  ለሌሎች  አፅራረ  ቤተ  ክርስቲያን  በማቀበል   ቤተ  ክርስቲያናችንን  ሰድቦ  ለሰዳቢ  የሰጣችሁ፤  እኛንም  ያሳፈራችሁን  አባቶች   እባካችሁን  ወደማስተዋል  ተመለሱ።  በደፈናው  ያስቀመጥኩኝ  ለአሁኑ  ስም  መጥቀስ   አስፈላጊ  ስላልሆነ  እንጂ  ይኽን  ሥራ  የሚተገብሩ  አባቶች  በደንብ  ይታወቃሉ።  በመረጃ   የተደገፈ  ጥናትም  ይኖራል።  ወደፊት  እንደ አስፈላጊነቱ  የምመለስበት  ይሆናል።    
 4. በማህበሩ  ውስጥ  በገንዘባችሁ፤   በእውቀታችሁ  ለቤተ  ክርስቲያን   ገልግሎት  ነው  ብላችሁ  ደፋ  ቀና  የምትሉ  ወንድሞችና  እህቶች!    
የተጠራችሁ  የሞተላችሁን  ክርስቶስን  ለማምለክ፤  የሞተላትን  ቤተ  ክርስቲያን   ለማገልገል  እንጂ  ነጋዴ  ድርጅትን  ለማደለብ  አለመሆኑን  ተገንዝባችሁ  ውሳኔአችሁን   እንድታስተካክሉ  በቤተ  ክርስቲያን  አምላክ  ስም  ትጠየቃላችሁ።  ቤተ  ክርስቲያን   እነእገሌ  ስለመሩአት፤  ወይንም  የማይመቹን  ሰዎች  ስለአሉባት  ሳይሆን  የክርስቶስ   መሠረት  ስለሆነች  እናከብራታለን።  ለአስተምህሮዋና  ለሥርዓቷም  እንታዘዛለን።   የኦርቶዶክስ  አስተምህሮና  ቀኖናዊ  ትውፊትም  የሚያዘው  ከሐዋርያት  ለተቀበልነው   ትውፊታዊ  ስርዓትና  አስተዳደራዊ  መዋቅር  መታዘዝ  ነው።
 የጀርባ  አጀንዳ  ያላቸው   የማኅበሩ  መሪዎች  ግን  ይኽንን  በፍጹም  አይቀበሉም።  ቤተ  ክርስቲያንን  የደፈሩ፤   ሥርዓቷን  የጣሱ  ናቸው።  በቅብዓ  መንፈስ  ቅዱስ  ተቀብተው  የቤተ  ክርስቲያን  መሪዎች   የሆኑትን  አባቶች  የሚያዋርዱ  በፍጹም  ኦርቶዶክሳውያን  ልጆች  ሊባሉ  አይችሉምና   አስቡበት።    
   በዘጠና  ሰባት  ምርጫ  ጊዜ  በገዢው  መንግሥትና  በፖለቲካ  ፓርቲዎች  መካከል  የተሠወረ   አጀንዳውን  ሲያራምድ  የነበረና  ለብዙዎች  የደም  መፍሰስ  ምክንያት  የሆነ  ማቅ  መሆኑ   በብዙ  መረጃ  የተደገፈ  ነው።  አሁንም  የፈሰሰው  ደም  ሳይደርቅ፤  የፈሰሰው  እንባ   ሳይታበስ፤  የዕለት  ዳቦ  ለማግኘት  ደፋ  ቀና  የሚለውን  ሕዝባችንን  ከመንግሥት  ጋር   ለማጋጨትና  ደም  ለማፋሰስ  ለጦርነት  ጋብዞዋችኋል።  
ኦርቶዶክሳዊት  ተዋሕዶ  ቤተ   ክርስቲያናችንም  በሰላም  ዓመታዊውን  የስቅለት  በዓል  እንዳታከብር  ለሁከት   ተመኝቶአታል።  ይኽ  በደም  መፍሰስ  የሚደሰት  መንፈስ፤  በቤተ  ክርስቲያን  ሁከትም   የኃሤት  አታሞውን  የሚመታ  አካል  ማን  እንደሆነ  ይታወቃል።  ከዚህ  መንፈስ   እራሳችሁን  ለዩ።  ለቤተ  ክርስቲያናችንም  ሆነ  ለሀገራችን  በጋራ  እንድንቆም  በጸሎት   ኅብረት  እንተባበር።      
  ወንድማችሁ  ጊዜው  አበራ  ነኝ!        
ይቆየን!!!

29 comments:

 1. ምነው "የጊዜው አበራ" ጭንቅላት ከኣስር አመት ልጄ አነሰብኝ?? በ"እውነቱም" ቤ"ጥበቡም"!

  ReplyDelete
  Replies
  1. የአሥር ዓመቱ ልጅህ ጭንቅላት ከአንተ በጣም የተሻለ ነው ማለት ነው።

   Delete
 2. Aba selamawoch lemehonu yekhdetachuh menesha mindin new ?

  ReplyDelete
 3. I don't expect valuable information from you because you are not ORTHODOX. You are from other religion; therefore, beter to shat up your mouth.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yene tsigie sitotaw. protestant nachew, Aba Selamawoch

   Delete
 4. በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስር በሚገኘው እና የተለያዩ አርኪ እና ስኬታማ ጉዞዎችን በማድረግ ታላቅ ስራ በሰራው በማህበረ ቅዱሳን ላይ ወያኔ የፖለቲካ ብትሩን በመምዘዝ ሊያወድመው መሆኑን ይህንን ሰሞን አበይት ከተባሉ ጉዳዮች አንዱ ሲሆን ይህንን ተከትሎ የወያኔ ካድሬዎች እና በሃይማኖቱ ውስጥ የተሰገሰጉ ቡችሎች ጸረ-ማህበረ ቅዱሳን ዘመቻቸውን ተያይዘውታል።

  ለዘመናት በሰላማዊነታቸው ወደር ያልተገኘላቸውን የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ወኪሎች ባልተገኙበት ባልዋሉበት ባላሰቡት ባልደገሱት በአክራሪነት እና በአሸባሪነት በመፈረጅ እንዲሁም ህዝበ ሙስሊሙን በመግደል እና በማሰር በማንገላታት ላይ የተሰማራው ወያኔ የሽብርተኝነት ፍረጃ ካርታውን ወደ ተዋህዶ እምነት በማዞር ማህበረ ቅዱሳንን አሸባሪ በማለት ለስልጣኑ የሚያሰጉ መሆናቸውን በመደስኮር ላይ ይገኛል።

  ለተነሳለት የከፋፍለህ ግዛ እና የጎሳ ፖለቲካ ፖሊሲ አልመች ብሎ የተገኘውን ሁሉ አሸባሪ አክራሪ በማለት ማህበረ ቅዱሳንንም ባልዋለበት የማክረር እና የማሸበር ድርጊት በመወንጀል ተግባር ላይ መሰማራቱ የጀመረውን ኢትዮጵያን ከፋፍሎ በጎሳ ቡድንተኝነት እያናከሱ በስልጣን ለመኖር ያሴረውን ሴራ እንደሚያከሽፍበት በከባዱ እንቅፋት ሆኖ ስላገኘው ነው።

  የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም ይሁኑ የተዋሕዶ አማኞች መሰረታቸውን ጎሳ ሳይሆን ኢትዮጵያ የሚል እደምታ መኖሩ እና በብሄር የተከፋፈለ አካሄድ አለመከተላቸው የወያኔ ስጋት ሆኖበታል። በመስኪዶችም ሆነ በቤተክርስቲያን ደረጃ ቀበሌያዊ የጎሳ ጥየቃ እና ምደባ አለመኖሩ ያንገበገበው ወያኔ የኢትዮጵያ አንድነትን የሚሰብኩ እና በህዝቦች መካከል ፍቅርን የሚያሰርጹ ሆኖ ስላሰበው ብቻ መፍረስ መደርመስ መሪዎቹን መታሰር እንዳለባቸው ግብሩ ይመሰክራል።

  በሙስሊምም ይሁን በተዋህዶ አማኞች ቀኖና ውስጥ ቀለም ዘር ጎሳ የመለያየት ትምህርት አለመኖሩ የሃይማኖቱን ምሁራን የአንድነት የፍቅር እና የሰላም ተምሳሌት እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ይህ ደሞ ለወያኔ የከፋፍለህ ግዛ የጎሳ ፖለቲካ የማይመቸው ስለሆነ ማህበረ ቅዱሳንን በ97 ምርጫ ወቅት ለወያኔ መሸነፍ አንዱ ተጠያቂ አድርጎ በሰነዱ ወንጅሎታል። ስለዚህ አምነቶቹን እና አማኞቹን ለመከፋፈል የሚችለው እንደ ማህበረ ቅዱሳን ያሉትን እና እንደ ሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን በአክራሪነት በአሸባሪነት በመወንጀል ማፈራረስ ከዚያም ማሰር ማንገላታት ስራዬ ብሎ ታያይዞታል።

  ያሰማራቸውም ቡችሎቹ ለመጪው ምርጫ ስጋት ያሳድራል ስለተባሉ ብቻ በጭፍን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ በጅምላ የሚያካሂዱትን ጥላቻ በማህበረ ቅዱሳንም ላይ ጀምረውታል። የኢትዮጵያን አንድነት በጠበቀ መልኩ ለመጪው ትውልድ ያስተላልፋሉ ታሪኬን ያበላሹብኛል ያላቸውን ሁሉ እየገዘገዘ መጣል የለመደው ወያነ በማህበረ ቅዱሳንም ላይ የጀመረው ግሬደራዊ የጥላቻ ዝቆሽ ከዚሁ ጋር የተያያዘ ነው።

  እንደ ኢትዮጵያውያኑ ሙስሊሞች እና የተዋህዶ አማኞች ሁሉ ነገ ባለተራ የሆኑት የፕሮቴስታት አማኞችም ከወዲሁ ስጋት አድሮባቸዋል፡፤ በጎሳ ስም የተከፋፈለ የበተክርስቲያን እና የመስኪድ ስያሜ የተመኘው ወያኔ ይህንን ለማሳካት ደፋ ቀና በማለት ላይ ስለሆነ ኢትዮጵያውይንን በጋራ ሃይማኖት ሳንለይ ይህንን የእምነት ጸር የሆነ የሰይጣን ተልእኮ በመያዝ ሃይማኖቶችን ሊያደፈርስ የሚፈልገውን ሕወሓት/ኢሕአዴግ የተሰኘውን የሽብር እና በፖለቲካዊ አክራሪነት የአንድነት የፍቅር የሰላም ፀር የሆነውን ቡድን ወደ ከርሰ ማቃብሩ ልንከተው ይገባል

  ReplyDelete
  Replies
  1. በአማን ነጸረ :


   ዘሱቱኤል የተባለ የጥንት ባለቅኔ በድምጸ-ብዙኃን መታገት ቢያንገበግበው እንዲህ አለ፡
   ማእከለ አራዊት ንኬልህ ወአልቦ ዘይሰምአነ፣
   እስመ አራዊት ይበዝሁ እምኔነ!!
   1. እናንት የማኅበረቅዱሳን አመራሮች፡ ኢቲቪን ለመክሰስ አደባባይ ስትወጡ ይገርመኛል፡፡በቤ/ክ ዙሪያ በሚሰሩ የኢቲቪ ዶክመንተሪዎች እኮ ከእናንተ አባላት ውጭ ሰው አይተን አናውቅም፡፡ስለባህላዊ እጸዋቱም፣ስለአብነት ትምህርት አሰጣጥም፣ስለበዐላትም፣ስለታሪክም፣ስለመቻቻልም ቤ/ክ ሊቃውንት የሌሉዋት እስኪመስል ድረስ በግቢ ጉባኤ ቆይታ ቅዳሜና እሑድ የወሰዳችሁዋቸውን ኮርሶች ስትናገሩ እየሰማን እንዳልሰማን፣እያየን እንዳላየን አለፍን፡፡የኢቲቪ ጋዜጠኞችን ምነው ሰው ታጣና የስንት ሊቃውንት እናት ቤ/ክ በየጊዜው በነዲያቆን እከሌ ብቻ የምትወከል ብንል ሊቃውንቱ ሚዲያ አይወዱም፤እነዲያቆን እከሌ ግን በቀላሉ ማግኘት ስለሚቻል ነው አሉን፡፡ዝም አልን፡፡ሁኔታው ቀጠለ፡፡ዝም አልን፡፡መጨረሻ ቀና ብንል ማሊያ ቀይራችሁ ከማኅበረቅዱሳን አመራር ወዲያ ሊቅ ላሳር፣ቤ/ክ ያለማኅበሩ ኦና ናት፣ማኅበሩ ባልተፈጠረበት ዘመን ቤ/ክንን ያን ሁሉ መከራ ተሸክሞ ለዚህ ማብቃቱ ተረስቶ ቤተክህነቶቹማ ሊሸጡዋት ሲደራደሩ ነበር እየተባለ ይዘፈናል፡፡ግሩም!!የግሩም ግሩም!!
   2. በአናቱም ጳጳስ እንጅ ሃይማኖትና ስርዐት ያላዋሰችን የግብጽ ኮፕት ቅኔና ዜማ ስለሌላት እሱን ትተን ልክ እንደሷ በግቢ ጉባኤ ኮርስ ቤ/ክ መምራት ማለት ዘመኑን መዋጀት ነው ተባልን፡፡እና ሰው እንደቤቱ እንጅ እንደጎረቤቱ አይኖርም፤በዚህ ላይ ያለ ዝማሬ-ያሬድና ያለ ምስጢረ-ቅኔ ቤ/ክ ምኑን ቤ/ክ ሆነች፤እንደገና በዚህም ላይ ግብጾች እንደእናንተ አድገው ጎልመሰው ዲግሪ ከጫኑ በሁዋላ በ30 እና በ40 አመታቸው ዲቁና እየተቀበሉ ሳይሆን ከልጅነታቸው ጀምሮ ጎን ለጎን መንፈሳዊ ት/ት ሲማሩ ከቆዩ በኋላ በትንሹ 10 አመት በቲዎሎጅ ትምህርትና ገዳም ወርደው በትህርምት ካሳለፉ በሁዋላ ነው የቤ/ክ አመራር ላይ የሚወጡት፣በዚህ መስፈርት ከሄድን ደግሞ በ20 አመት ከአንድ እጅ ጣት የማይበልጡ ግለሰቦች ስላፈነገጡ ብቻ በሺህ የሚቆጠሩ ትጉሃን ምሩቃንን ደምራችሁ በመናፍቅ መፈልፈያነት የምትከሱዋቸው መንፈሳዊ ኮሌጆች ናቸው አመራሩን ይረከቡ ቢባል የሚያምርባቸው ብንልም ማን ሰምቶ!!ሆ በል ሲሉ ሆ ማለት ሆነ!!
   3. ማኅበራዊ ሚዲያ ከግል ፕሬስ ገጥሞ ጨሰ አቡዋራው ጨሰ ይላል!!አሁንም ልድገምላችሁ ከባዮሎጅ እና ኬሚስትሪ ጎን ለጎን በትርፍ ጊዜያቸው ቅዳሜና እሁድ በወሰዱት ኮርስ ቤ/ክ እንምራ የሚሉ ካሉ ተሳስተዋል፡፡ባይሆን እንደ ምዕመን ወኪል ወይም እንደ ሰ/ተማሪ ሰ/ጉባኤ ተመርጠው በዛ በኩል በውሳኔ ሰጭነት ይሳተፉ ቢባል ያስኬዳል፡፡ከዚህ ውጭ እንሁን ማለት ግን አንድም በዲያስፖራው ቤ/ክ ህግና ስርዐት ጥሶ ዐውደምህረቱን የፖለቲካ መናኸሪያ ያደረገውን ቦርድ የሚባል ካድሬያዊ አደረጃጀት ለማምጣት መጣር ነው እንዲያም ሲል እንደመናፍቃኑ ሽማግሌ ተብየ ተነታራኪዎች በየቀኑ እየተነታረከ ቤ/ክ እንደ መርካቶ ሽንሽን ሱቅ የሚከፍል ቡድን መፍጠር ነው፡፡በነገራችን ላይ ቤ/ክ ምትመራበት ቃለዐዋዲ ለሰ/ት/ቤት ካልሆነ በቀር ለማኅበር ተብሎ የወጣ ድንጋጌ የለውም፡፡ማኅበረቅዱሳን የተቋቋመው በመመሪያ እንጅ በቃለዐዋዲ አይደለም፡፡እዚህ የምንሰማው ግን ሌላ ነው፡፡
   4. በወዲያኛው ወገን ያለው ድምጽ እንዲሰማ አይፈለግም፡፡ምክንያቱም ይህ የሳጥናኤልና የሚካኤል ሰራዊት ጦርነት ነው ተብሎ ታውጇል፡፡ነገር ግን ትግሉ ከሕግና ከሥርዐት በታች ማደር አለበት በሚሉ ወገኖችና የለም ለሌላው ሕግ አወጣለሁ እንጅ ለኔማ ምን የቆረጠው ነው በሚል አካል መሀል የሚደረግ ነበር፡፡በጥፋታቸው ይወዳደሩ ከተባለም አማሳኞች ተብለው ከፍርድ በፊት ስም የወጣላቸው ወገኖች የፈጸሙት ጥፋት ከማኅበሩ ቡድናዊ ጥፋቶች አይብስም ነበር፡፡ለዚህ ሳይሆን ይቀራል መጽሐፍ “ወክልኤቱ ይሰድድዎሙ ለእልፍ” እንዳለው በጥቂት ግለሰቦች ማኅበሩ እንዲሕ የሚሸበረው!!ግዴለም ልሳን አለን ብላችሁ አባቶችን በጽርፈት አታንሱ፣ወደላይ አያድጣችሁ አልን፣ሚዛናዊ ዘገባ አቅርቡ ያለበለዚያ ውሸታሙ እረኛ መሆን ይመጣል አልን፣ማን ሰምቶ!!ማን አጣርቶ!!ጠረፍና ጠረፍ፣ዳር እና ዳር፣አንዳንዴም ከባህር ወዲህና ባህር ማዶ ሆኖ ባላዩት ባልሰሙት ማኅበሩ ያለውን ብቻ ይዞ ማስተጋባት ሆነ!!ይሄው አሁን የፈለጋችሁትን ዶሴ በየኢንተርኔቱ ብትለቁ ቁብ የማይሰጠው ልቡ የደነደነ ቤ/ክህነት በራሳችሁ ላይ አቆማችሁ፡፡አሁንም እናርም ካልን ግን አልረፈደም!!ሁሉም ይደርሳል!!

   Delete
 5. አዎ፣ ማኅበሩ ከአባላቱ ላብ ባገኘው የፈቃድ ድጋፍ እና አገልግሎቱ በገባቸው ኦርቶዶክሳውያን ርዳታ ሕንጻውን ጨርሷል። አሁን ሲያዩት ያጓጓል። ለእነ ሆድ አምላኩ ዝርፊያ የማይመች ይህንን የመሰለ ነገር አይቶ ማለፍ አይቻላቸውም። ስለዚህም አይሁድ ጌታን በሰላላ ዲናር ክህደት ለመስቀል ሞት እንዳበቁት፤ በግዑ ለእግዚአብሔር (የእግዚአብሔር በግ) ክርስቶስን አርደው ሳይበሉት እንደቀሩት፣ እነዚህ የዘመናችን ተረፈ አይሁድም ማኅበረ ቅዱሳንን ለመስቀል ቋምጠዋል። ላይበሉት፣ ላይጠቀሙበት።

  ReplyDelete
 6. መኅበረ ቅዱሳን በስደት የሚኖሩትን አባቶች ላለፉት 21 ዓመታት በስደት በሚኖረው ማኅበረ ክርስቲያን ዘንድ ተቀባይነት እንዳያገኙ ከፍተኛ የሆነ መሰናክል ሲፈጥርባቸው ቆይቶ ነበር። ይህንም በማድረጉ ከአገዛዙ ጋር ሰምና ወርቅ ሁኖ ቆይቶ ነበር። እኔ በዚህ ምክንያት የማኅበሩን ክርስቲያናዊ ተልዕኮ ከሚጠራጠሩት መካከል አንዱ ነበርኩ። በሌላ በኩል ግን አዲሱን ትውልድ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን እንዳይረሳ ሲያደርጋቸው በቆየው ኣድራጎቱ ሳደንቀው ቆይቻለሁ። በዚህ ምክንያት እኔና ማኅበረ ቅዱሳን አንድ ስንሆንና ስንለያይ ቆይተናል። አሁን ግን በአገዛዙ የጥቃት ኢላማ ውስጥ ስለገባ ኢትዮጵያዊ የሆነው ሁሉ ጥቃቱን ለመከላከል ከማኅበሩ ጎን መቆም ይጠበቅበታል። እኔም አብሬው ለመቆም ተነስቻለሁ። በየተራ መመታቱ መቆም አለበት። ቀበሮው ወያኔ መንጋውን አየነጠለ ሊበላው አይገባም !!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሰማህ ወዳጄ ማቅ የሚፈልገዉ ይህንኑ ነዉ በአገዛዙ የጥቃት ኢላማ ውስጥ ስለገባሁ ኢትዮጵያዊ የሆነው ሁሉ ይደረስልኝ ለማለት የሚያስወራዉ ወሬ መሆኑን ብትረዳና የቀደሞዉነ አቅዋምህን ብትይዝ ጥሩ ነዉ። አኔና ማቅን ያጣላን ጸረ ወንጌልነቱ ብቻ ነዉ። እንዲህ ዓይነት ወንጀል ለሚፈጽም ድርጅት ይቅርታ የማደርገዉ ንሰሐ ገብቶ በወንጌል ስርጭት ሲሳተፍና ወንጌላዊያንን መሳደዱን ሲያቆም ነዉ። ስለዚህ ለምድራዊ ፖለቲካ ብዬ በሰማያዊዉ ንጉሥ ላይ ያመጸን ማህበር ለማዳን አልሞክርም የጌታ ቀን መጣ ከማለት በስተቀር። ልጆቼን በግቢ ጉባዔ እንዲሳተፋ የጎተጎትኩት ወንጌልን የተማሩልኝ መስሎኝ እንጂ ማቅ የተባለ የወንደሞች ከሳሽን ኤምፓዬር ለማጠናከረ አልነበረም። አሁንም ወንድሜ የነሱን ማደናገሪያ ስሞታ ትተህ እዉነቱን ያዝ።

   Delete
 7. ማቅ ይውደም። ከቤተክርሰቲያን የዘረፈውን ይመልስ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ይውደም ... hahaha yechin ke Menegesetu Hailemariam mehon alebet yekorejekat

   Delete
  2. ሌባ አንተ ውደም

   Delete
  3. Sayaresu Sayekofiru Le weferu anawatam....degenetu sikuaru, demgifitu hisab eyaweraredelen selehon wutetu gize ayewesedim....kalefut temaru MK hulem yenoral

   Delete
 8. Truth is the winner. "Gizew Abera" negn new yalkew. You have small head and in that chicken head you tried to distort facts and gave you conclusion. There will not be nothing on MK..siyamerehe yikir!! very small group of Kehadi gilesebch tesebesobew silechohu...minim ayimetam. Gizew yechelemebeh enji yeberaleh ayimeselim

  ReplyDelete
 9. በሰዎች ላይ ሁከተን የሚያሳውጅ ማንም የማያውቀውን ህዘብ ለማተራመስ የታወጅ ነገር ሁሉ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የፈረሰ ይሁን፡፡ ስራውን ለማፍረስ ወንድሞች መጸለይ አለብን መቼም ማቅ ወዶ አይደለም በሰይጣን አገዛዝ ውስጥ ሰለሆነ ታውረዋል ልንጸልይላቸው ይገባል፡፡ ማስተወልን ይስጣቸው፡፡

  ReplyDelete
 10. የዘመናችን ተረፈ አይሁድም ማኅበረ ቅዱሳንን ለመስቀል ቋምጠዋል

  ReplyDelete
 11. Ohh, aba selamawoch..men aynet ye seytan menfes naw yeyazachehu??? I am not a member of mahebere kedusan but I participated the sunday( 21/7/2006) Religious trip to addis Alem which was orgainzed by mahebere kedusan... i was really appreciate the way they orgainzed all the activities and Religious teaching for more than 6000 attendants. Please you aba selama people I think u r jealous of mehebere kedusan... for their wide acceptance by the Ortodox christians especially by youngesters...

  ReplyDelete
 12. mk nefes geday dereget new.

  ReplyDelete
 13. ማቅን የመሰለ አጥፊና በግል ፕሬስ ነኝ ባዮች አጨብጫቢዎች የተከበበ ማኅበር አለ እንዴ? እሱ መፍረስ ብቻ አይደለም ሌላም ነገር ቡኖር ይገባዋል። ለሰይጣን ደቀመዝሙር ይሄን ያህል አሽኮሌሌ ማለት ምንድር ነው?

  ReplyDelete
 14. How can an orthodox can believe this article while this blog is serving (striving) for destructing EOTC. try to post on orthodox website(blog) for the discussion otherwise you(the writer) has hidden agenda in this article...may be working for anti-orhtodox.lezare altesakeam

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድወሰንApril 3, 2014 at 4:45 AM

   ማህበረ ቅዱሳን ንስሐ ካለገባና ኢየሱስ የሚለዉን ስም ከፍ አድርጎ ማንሳት ካለጀመረ መከራዉ ብዙ ነዉ ምኑን አይታችህ ነገረ ቅዱሳን እንጂ ነገረ ክርስቶስ እንደማያስፈልግ የሚሰብክ ከጌታችን ይልቅ የድርጅት ፖለቲካ ባህልና ተረት የሚበልጠቡት ከሆነ መንግሥት ቢተወዉም የበደለዉ ጌታ በሌላ የመጣበታል ስለዚህ ማቅ መክፈል ያለበት ዕዳ አለና ዝም ብለን እንጠብቅ

   Delete
 15. The government of Ethiopia shall focus in enhancing development of the country and uprooting corruption including parasites among itself.The issue of Mahibre Kidusan is a religious one! If there are individuals in it against the government, it is better to ask them. However, if the Tehadiso who are against EOTC, and ant- reformist and corrupt clergy are to gain power in order to weaken MK, we will through our tear towards the Sky.!

  ReplyDelete
 16. Yemigermew eraasun gizew abera bilo yetraw yechelemaw lijm hone aba selama nen bayoch yebetekirstyan lijoch alemehonachew new semonun enkwan emebetachinn yesedebubet bier sayderiq zare degimo sile mk maninet negerun enante menafiqan mehonachihu eyetaweqe endihun betekirstyanin enadisat zemechachihun MK sileneqabachihun siletagelachihu yene shiferaw t/Maryam penteoch telalaki honachihu mesratachihu yetaweqe new yiliqs papasatunina abalatun kemitmekiru erasachihun mikeru enante silechohachihu yemimeta andach neger yelem mk norem alnorem yenante minfiqina dagim b/k wist aygebam gizew atefam hone yemenafiqan budin tesfa quretu

  ReplyDelete
 17. mk is down soon

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድወሰንApril 3, 2014 at 4:45 AM

   ማህበረ ቅዱሳን ንስሐ ካለገባና ኢየሱስ የሚለዉን ስም ከፍ አድርጎ ማንሳት ካለጀመረ መከራዉ ብዙ ነዉ ምኑን አይታችህ ነገረ ቅዱሳን እንጂ ነገረ ክርስቶስ እንደማያስፈልግ የሚሰብክ ከጌታችን ይልቅ የድርጅት ፖለቲካ ባህልና ተረት የሚበልጠቡት ከሆነ መንግሥት ቢተወዉም የበደለዉ ጌታ በሌላ የመጣበታል ስለዚህ ማቅ መክፈል ያለበት ዕዳ አለና ዝም ብለን እንጠብቅ

   Delete
  2. UP soon ....

   Delete
 18. Mk Mudaye Metsuat ayegelebetim....bekireb yenante berehan yechelemal....Hulum mereja teyezoal....ke jereba yalewum wulude aganeit yetefalu...

  ReplyDelete
 19. well said Mr. Abera. Time for MK to be dismantled and transfer all the money and matierals holy synod since it belongs to EOTC. MK from now on should act like a sunday school not like holy synod. MK has an innocent blood in his hands. Ethiopia will stretch her hand to GOD, Now and Forever! Amen.

  ReplyDelete