Monday, April 14, 2014

«ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ከሆነ እኔም አክራሪ ነኝ» የሚሉ ድምጾች ምነው በዙሳ?

Read in PDF

ምንጭ፡-http://dejebirhan.blogspot.com/

በአንድ ወቅት ዳንኤል ክብረት የተባለው ሰውዬ በእንቁ መጽሔት ላይ እንደተናገረው «ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ሆኖ የገደለው ሰው የለም!» ብሎ ነበር። በዳንኤል አስተሳሰብ «አክራሪ» ማለት በሃይማኖተኝነት ሰበብ ሰው የመግደል ደረጃ ላይ ሲደረስ መሆኑ ነው። ከመግደል በመለስ ያለው ኃይልና ዛቻ፤ማሳደድ ተፈቅዷል ማለት ነው? ሌላው የማኅበረ ቅዱሳን የሜሪላንድ አፈቀላጤ ኤፍሬም እሸቴ ደግሞ «አክራሪ ሃይማኖተኛ መሆን ጥሩ ነው» ሲል ተመራጭነቱን በማሳየት የማኅበረ ቅዱሳንን የማክረር እንቅስቃሴ ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ሲታትር ታይቷል።  አክራሪ በባህሪው እኔ ትክክል ነኝ ከሚል ጽንፍ ተነስቶ፤ የምለውን ተቀበሉኝ፤ እምቢ ካላችሁ ወግዱልኝ፤ አለበለዚያ እኔው በኃይል አስወግዳችኋለሁ በሚል ድምዳሜ የሚያበቃ አስተሳሰብ ነው።  አንዳንዶች አክራሪነት በዚህ ዘመን የተከሰተ አድርገው ሲመለከቱ ይታያል። ትርጉሙና የተግባራዊ እንቅስቃሴው ስፋትና ጥልቀት ተለይቶ ታወቀ እንጂ አክራሪነት ጥንትም ነበረ።  በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 9 ላይ እንደተመለከተው ኢየሱስ ለሐዋርያቱ እንደነገራቸው «አስቀድማችሁ ወደሰማርያ ከተማ ሂዱና፤ ጌታ ይመጣል ብላችሁ አስናድታችሁ ጠብቁኝ» ብሎ ባዘዛቸው ጊዜ የከተማይቱ ሰዎች መልዕክቱን እንዳልተቀበሉ ሐዋርያት ስለተመለከቱ «ጌታ ሆይ፥ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን?» ብለውታል።  ጌታ ግን፤ «የሰው ልጅ የሰውን ነፍስ ሊያድን እንጂ ሊያጠፋ አልመጣም» ብሏቸዋል።  አክራሪዎች ራሳቸውን የእግዚአብሔር ብቸኛ ወታደሮች አድርገው ራሳቸውን ያስቀምጣሉ። ስለዚህ እኛን ያልመሰለ ይጥፋ ባዮች ናቸው። አስተምሮ፤ ተከራክሮ መመለስ ስለማይችሉ አጭሩ መፍትሄ ማስወገድ ነው።

እንደዚሁ ሁሉ በፖለቲካው ከተሰማሩት ድረ ገጾች አንስቶ እስከጥቃቅኖቹ ብሎጎች ድረስ አንዱ ከአንዱ እየተቀባበሉ የማያውቁትን ማኅበር ለማሳወቅና ለሃይማኖት ማክረር እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ የሚገልጹ ጽሁፎችን እስከማራገብ ድረስ ዘልቀዋል።  በፌስቡክና በትዊተር ገጾች «ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ከተባለ እኔም አክራሪ ልባል» ከሚለው ድምጽ አንስቶ የማኅበረ ቅዱሳንን ዓርማ የሚያሳይ ግለ ስእል በመለጠፍ አጋርነታቸውን ለማሳየት የሞከሩ ብዙዎች ናቸው።  ሁሉንም ስንመለከት «አክራሪ ሃይማኖተኛ» መሆን አስፈላጊ እንደሆነና «እኛም የዚሁ ሰልፍ አባሪ ሆነን ለሃይማኖታችን አክራሪ ነን» የሚል ይዘት ያለው አቋም እየተንጸባረቀ መገኘቱን መገንዘብ ይቻላል። ሃይማኖተኛ ነን የሚሉቱ ወገኖች ያሉበትን ምክንያት ከማየታችን በፊት ፖለቲከኞቹ ነገሩን ለማስጮህ የፈለጉበትን ምክንያት እንመልከት።


1/ ፖለቲከኞች ማኅበረ ቅዱሳንን የመደገፍ ምክንያት፤

ፖለቲከኛ ሃይማኖት የለውም ማለት ባይቻልም ሃይማኖተኛ ግን ፖለቲከኛ መሆን አይችልም። ፖለቲከኛ ሃይማኖት ሊኖረው የሚችለው ስለሃይማኖቱ አውቆና አምኖበት በመከተሉና እምነቱ የሚያዘውን ለመፈጸም እንደእግዚአብሔር ቃል ለመኖር ለራሱ ኪዳን የገባ ሳይሆን በውርስ ከቤተሰቦቹ የተረከበው ወይም በልምድ ሲከተለው ስለኖረ ራሱን ሃይማኖት እንዳለው አሳምኖ ሲያበቃ ከፖለቲካ የሚገኘውን የምድራዊ ሳይንስ ጫወታ የሚጫወት ሰው ነው። 

 ምክንያቱም ፖለቲካ ባላጋራህ የሆነውን የሌላኛውን ሰው አመለካከትም ሆነ ተግባር በምትችለው መንገድ በልጠህ ወይም ጠልፈህ በመገኘት ምድራዊ ሥልጣንን መቆጣጠር ማለት ሲሆን ሃይማኖት ደግሞ የሰውን ልጅ ጠላትነት የማይቀበል፤ ባላጋራውም ሰይጣን ብቻ መሆኑ አምኖ ለእግዚአብሔር መንግሥት ሲል ሃይማኖታዊ መመሪያውን በመከተል ለማይታየው ሰማያዊ ሕይወት ሲል ከሚታየው ጠልፎ የመጣልና የመዋሸት ዓለም የጸዳ ማለት ነው። የዲሞክራሲ ጣሪያ ነክተናል ከሚሉት አንስቶ የነሱኑ መንገድ ተከትለናል እስከሚሉቱ ድረስ ሁሉም ፖለቲከኞች በፖለቲካል ቲዎሪ ከሚነገረው ታሪክ ባሻገር ማስመሰል፤ መዋሸት፤ ማታለል፤ ጠልፎ መጣል ወይም እውነተኛ መስሎ መታየት፤ ሀቀኛ፤ የህዝብ ወገንተኛ መሆንን መደስኮር በሁሉ ዘንድ መኖሩ በማስረጃ አስደግፎ መናገር ይቻላል።  በግርድፉ የተቀመጠውን የፖለቲካ ትርጉም ብንመለከት ለምድራዊ ስልጣን መታገል የመጨረሻ ግብ መሆኑ እውነት ነው።
« Politics is the activities associated with the governance of a country or other area, esp. the debate or conflict among individuals or parties having or hoping to achieve power»
« ፖለቲካ ከሀገራዊ ወይም ከክልላዊ የሕዝብ አስተዳደር ክንዋኔዎች ጋር በተዛመደና በተለይም በተቃርኖአዊ የእርስ በእርስ የሃሳብ ፍጭት የተነሳ ተስፋ በሚሰጥ የፓርቲዎች ስነ ሞገት ብልጫ አግኝቶ የስልጣን ኃይልን የመጨበጥ ግብ ያለው ነው»
ፖለቲካዊ ስልጣን ማለት ግን ለሃይማኖተኛ ጥቅም አይሰጥም፤ ወይም አይጎዳም ማለት አይደለም። እንደሚመራበት የፖለቲካ ርእዮት /አመለካከት/ ይወሰናል። ሃይማኖታዊ መንግሥት ባለበት ሀገር መንግሥቱ ለተመሰረተበት ሃይማኖት አብላጫውን ወይም ዋናውን አገልግሎት ይሰጣል። ሌሎች ሃይማኖቶች እንደመንግስታዊው ሃይማኖት እኩል መብት ሊኖራቸው አይችልም።  ሃይማኖት የለሽ መንግሥት ከሆነ ደግሞ ሁሉም ሃይማኖቶች የመንግስቱ ጠላቶች ነው። ሴኩላር/ ገለልተኛ/ የመንግስት አወቃቀር ባለበት ሀገር ደግሞ መንግስት በሃይማኖቶች ጉዳይ ጣልቃ እንደማይገባ ይደነግጋል። ጣልቃ የማይገባው ለሴኩላር መንግሥታዊ አወቃቀሩ ስጋት እስካልሆኑ ድረስ ብቻ ነው። እንደመንግሥታዊው የፖለቲካ አወቃቀር ሥርዓቱ ሃይማኖትን ሊጠቅም ወይም ሊጎዳው መቻሉ እርግጥ ነው። በኢትዮጵያ ታሪክ በአፄዎቹ፤ በደርግና በኢህአዴግ መካከል ባለው የፖለቲካ ርእዮት የተነሳ ፖለቲከኞቹ ሃይማኖትን የሚመለከቱበት መነጽር የተለያየ ነው። ሃይማኖትን በተለያየ መነጽር የሚያዩ ፖለቲከኞች፤ ሃይማኖተኞች ሊሆኑ አይችሉም።  ፖለቲከኞች የቆሙለትን የተለያየ የፖለቲካ ስርዓት ያገለግላሉ።  ፖለቲከኛ ሆኖ ሃይማኖተኛ ለመሆን ከባድ የሚሆነው ለዚህ ነው። ሃይማኖተኛ ሆኖ መዋሸት አይቻልም። ፖለቲከኛ  ስርአቱን እስከጠቀመ ድረስ ይዋሻል፤ የሌለ ተስፋ ይሰጣል።  አላስፈላጊ ወይም ጠቃሚ ካልሆነ ደግሞ ማስተባበያ ወይም ይቅርታ ሊጠየቅ ይችላል። ለሃይማኖተኛ ንስሀ እንጂ ማስተባበያ ወይም ይቅርታ የሚል የአደባባይ ዲስኩር የለም። ፖለቲከኛ ሃይማኖት ሊኖረው ቢችልም ሃይማኖተኛ ግን በጭራሽ ፖለቲከኛ መሆን አለመቻሉ እርግጥ ነው። ታዲያ የልምድ ሃይማኖት ያላቸው ነገር ግን ሃይማኖተኛ መሆን የማይችሉ ፖለቲከኞች ማኅበረ ቅዱሳን ሲነካ የሚጮሁት ለምንድነው? የሚለው ጥያቄ መመለስ አለበት። ዋናው ነጥብ «የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው» ከሚል የፖለቲካ ፍልስፍና የተነሳ ነው። 

 ሃይማኖት የሌላቸው /እምነት የለሾች/ ይሁኑ ማኅበረ ቅዱሳንን በልምድ የሚመሳሰሉ ባለሃይማኖቶች እና «ማኅበሩ ተነካ ማለት የእግዚአብሔር መንግሥት ተነካ» ባይ የዋሆች ሁሉም በአንድነት ውጥንቅጡ በወጣ አቋም ውስጥ ሆነው ለማኅበሩ ለመጮህ ሞክረዋል። የሚገርመው ደግሞ የማኅበረ ቅዱሳንን መጥፋት የሚመኙ እስላሞች ሳይቀሩ «የሃይማኖት ነጻነት ይከበር» በማለት ለማኅበሩ ያላቸውን ድጋፍ ለማሳየት መሞከራቸው ነው። ዋነኛ ዓላማቸው የሃይማኖት መከበር ስላሳሰባቸው ሳይሆን በእስልምና ጎራ ያሉ ታሳሪዎችን ድምጽ ከማኅበረ ቅዱሳን ጎራ ካሉት ጋር በማስተሳሰር ጉዳዩን ለማጦዝ ከመፈለግ የተነሳ ነው።  በዘመነ ኢህአዴግ እስልምና ተጨቁኗል ቢሉ ለሰሚው ግራ ነው።  በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ብቻ የእስላም መስጊድ ከቤተ ክርስቲያን ቁጥር የበለጠው በዘመነ ኢህአዴግ መሆኑ በጭራሽ ሊስተባበል የሚችል አይደለም።  ከአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ 16% ለሆነው የእስልምና ተከታይ 180 በላይ መስጊዶች ሲኖሩት 74% ከመቶው ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ቁጥር 150 ገደማ ብቻ ነው። በኦርቶዶክስ ተጨቁነን ነበር የሚሉትን አቤቱታ እንደኢህአዴግ ያካካሰላቸው መንግስት ለእስላሞች የለም ማለት ይቻላል። በዘመነ ኢህአዴግ የተሰራው መስጊድ በሺህ ዘመናት ውስጥ ከተሰራው ይበልጣል።
 እንዳላት ተከታይ ብዛትና ሊኖራት እንደሚችለው የድርሻ ስፋት ድምጿ ያልተደመጠው ኦርቶዶክስ ናት ማለት ይቻላል። ከመንግሥታዊ ክፍል ያሉ፤ ፕሮቴስታንቱም፤ እስልምናውም፤ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ የሚለው አሮጌ ፖለቲከኛው ሁሉንም ስንመለከት በግልጽም ይሁን በስውር ይህች ቤተ ክርስቲያን ለሀገሪቱ ባበረከተችው ከመጠቀምና በስሟ ከመነገድ በስተቀር ያደረጉላት አንዳችም ድጋፍ የለም። ላበረከተችው በጎ አስተዋጽኦ ዋጋ መስጠት በራሱ ትልቅ ነበር።

ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን «ልጠፋ ነው» እያለ ለሚያሰማው ጩኸት ፖለቲከኞቹን ያስተባበራቸው ኢህአዴግን እንደጋራ ጠላት ለመፈረጅ እንጂ በሃይማኖት ስለተሰሳሰሩ አይደለም። ኦርቶዶክስ እንድትጠፋ ሲሰሩ የቆዩ የቀድሞ መንግስት ፖለቲከኞች፤ የተለያዩ የሌኒናዊ ፓርቲ አባላትና ርዝራዦች ሳይቀሩ ለማኅበረ ቅዱሳን ሲጮሁ እያየን ነው። እውን ለኦርቶዶክስ አዝነው ነው? የቤተ ክርስቲያኒቱን ሃይማኖታዊ መሪዎች ከመግደል አንስቶ፤ ጣልቃ ገብቶ በመሾም፤ ሲኖዶሱን በመከፋፈልና በማዳከም ትልቅ ድርሻ ያላቸው እነዚህ ጮኸው የማይሰለቹ ፖለቲከኞች ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ። ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳንን ለመደገፍ መሞከራቸው ቤተ ክርስቲያኒቱን የማዳከም ቀጣይ ተግባራቸው ማሳያ ተደርጎ ከሚወሰድ በስተቀር ቤተ ክርስቲያኒቱ ከማኅበሩም ሆነ ከፖለቲከኞቹ ያተረፈችውም ምንም ነገር የለም።

2/ ሃይማኖተኞች የማኅበሩ ደጋፊዎች፤

ማኅበሩ ራሱ እንደሚለው ከሆነ 35,000 መደበኛ አባላትና 500,000 ተከታይ አባላት እንዳሉት ይነገራል። ያለውን የፋይናንስ አቅም በትክክል ባይናገርና ባናውቅም ቅሉ ከልዩ ልዩ የንግድ ተቋማት ገቢ ምንጮቹ የሚያገኘውን ካፒታል ሳንጨምር ከ35,000 አባላቱ ላይ ብቻ በግርድፉ ብንገምት በወርሃዊ መዋጮ መልክ 10 ብር ቢሰበስብ 350,000 ብር ወርሃዊና ከ500,000 ተከታይ አባላቱ ላይ ደግሞ ለልዩ ልዩ የማኅበሩ ልማታዊ ስራዎች ሰበብ በዓመታዊ ድጋፍ 10 ብር በነፍስ ወከፍ እንዲሰጡት ቢጠይቅና ካሉት ተከታይ አባላቱ መካከል 400,000 ያህሉ ለ10 ብር የድጋፍ ጥያቄው ምላሽ ቢሰጡ 4,000,000 ብር ያገኛል ማለት ነው። ከወርሃዊ  የአባልነት መዋጮ ገቢው ጋር በዓመት ሲሰላ ከ8 እስከ 9 ሚሊዮን ያላነሰ በዓመት ይሰበስባል ማለት ነው። ይህ ስሌት በመንፈሳዊ ጉዞ ሰበብ፤ በመጽሔት፤ በሆቴልና በሱቅ ሽያጭ፤ በካሴት፤ በሲዲ፤ በእርዳታ ጥሪ፤ ከበጎ አድራጎት፤ ከለጋሽ፤ ከቤት ኪራይ ወዘተ የሚገኘውን ግዙፍ ገቢ ሳይጨምር መሆኑ ታሳቢ ይደረግ።  ጆርጅ በርንስ እንዲህ ይላል። « Don't stay in bed, unless you can make money in bed»  «አልጋህ ላይ ሆነህ ገንዘብ ካላገኘህ በቀር አልጋህ ላይ አትቆይ» እንደማለት ነው። ይህ ብሂል የገባው ቅዱስ ማኅበር «መኒ» ይሰራል። «መኒ» የማይገዛው ስልጣን፤ ጉልበትና እውቀት በሌለበት ዘመን የእግዚአብሔርን ለእግዚአብሔር አይባልም።

ይህ ማኅበር ከአንታርክቲካ በስተቀር በሁሉም ዓለማት ላይ ቢሮዎች አሉት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ባለችበት ቦታ ሁሉ አለ። በሳንባዋ ይተነፍሳል፤ በደም ስሯም ይዘዋወራል። ነገር ግን መዋቅሩና የመዋቅሩ መረብ ማኅበረ ቅዱሳዊ ነው። አብዛኛው አባላቱና ደጋፊዎቹ አብረው የተሰለፉት ቤተ ክርስቲያኒቱን የደገፉና የረዱ እየመሰላቸው መሆኑ እርግጥ ነው። የቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር ከዘመኑ ጋር መዘመን ባይችልና ባንቀላፋበት ቦታ ሁሉ ማኅበሩ እየተገኘ ከበሮ እየመታ፤ እየዘመረ አለሁልሽ እያለ ማኅበሩንና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለይቶ የሚያይ ተከታይ ባይኖር አያስገርምም።  የሚገርመው እንመራሃለን የሚሉቱ የማኅበሩ ተመሪ ሆነው መገኘታቸው ነው።

ሀ/ ሊቃነ ጳጳሳቱ፤

ሊቃነ ጳጳሳቱን ማኅበሩ እንዴት አባል አድርጎ እንደሚይዝ ዝርዝር ውስጥ አንገባም። ነገር ግን ሊቃነ ጳጳሳቱ የሲኖዶስ አባልና በቤተ ክርስቲያኒቱ የአንዱ ሀገረ ስብከት ወይም ክፍል ተጠሪ ሆነው ሲያበቁ የማኅበሩን ዓላማ ተቀባይ፤ የማኅበሩ ጠበቃና ተከራካሪ ሲሆኑ ግርምት ይፈጥርብናል። ዋናው ጥያቄ የሚነሳውም ማኅበሩ የሲኖዶሱ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ነው ወይ? ሊቃነ ጳጳሳቱ በሀገረ ስብከታቸው መሥራት ያልቻሉትን የሚሰራላቸው ወኪላቸው ነው ወይ?  ምን መስራት ያልቻሉትን፤ ምን መስራት እንዲችልላቸው፤ የትኛውንስ ጉዳይ እንዲያስፈጽም ውክልና ተሰጥቶታል?
 በማኅበሩ ስያሜና ቁመና እንዲሁም በሲኖዶስና በሊቃነ ጳጳሳት መካከል ያለው የሥልጣን፤ የደረጃ ክፍተት የሚለካው በምንድነው? የሚሉ ጥያቄዎች ግራ የሚያጋቡና ምላሻቸውንም በውል የሚያውቅ አለመኖሩ ጉዳዩን አስደማሚ ያደርገዋል።  ስለዚህ ጥርት ያለ መልስ የሌለው የአንድ ማኅበር ዓላማ በአእምሮአቸው የሰረጸ ነገር ግን የሲኖዶስ አባል ነን የሚሉ ሊቃነ ጳጳሳት በአንድም፤ በሌላ መንገድም የማኅበሩ ጉዳይ ፈጻሚ ሆነው መገኘታቸው እርግጥ ነው።

ለ/ ወጣት የሰንበት ት/ቤት አባላት፤ የጥምቀት ተመላሽ ማኅበር፤ የጉዞና መንፈሳዊ ማኅበራት፤

እነዚህ ወጣት ክፍሎች ከማኅበሩ ሰፊና ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴ አንጻር በቁጥጥር ስር መዋላቸው የግድ ነው። ደግሞም አስፈላጊ መሳሪዎች ናቸው። በአንድ በኩል በችግር ወቅት ለማንቀሳቀስ፤ በሌላ መልኩም በችግር ቀን ለመደበቅ ሊያገለግሉ ይችላሉ። መሰረታዊ የትጥቅ መሳሪያቸው ደግሞ «ቤተክርስቲያንን ከልዩ ልዩ ኃይሎች መጠበቅ» የሚል መንፈሳዊ መሰል ትጥቅ ሲሆን ወጣቶቹ ዓይናቸውን በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በእምነት እንዲጥሉ በማድረግ ማኅበሩ ለሚፈልገው ዓላማ ማገልገል እንዲችሉ ተደርገው ይቀረጻሉ። ወጣቶቹ በእርግጥም ከልባዊ እምነት ተነስተው የሚከተሉ ስለሆነ ቤተ ክርስቲያንን እንደማገልገል እንጂ ማኅበሩን እንደመታዘዝ አይቆጥሩም ወይም ማኅበሩን ማገልገል የቤተ ክርስቲያኒቱን ፈቃድ እንደመፈጸም አድርገው እንዲያስቡ ተደርገዋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ ሰንበት ተማሪዎች፤ የጥምቀት ተመላሽ ቡድኖችና የጉዞ ማኅበራት የማኅበሩ ታዛዥና ተጠባባቂ ኃይሎች ናቸው። የእነዚህ ማኅበራት አባል ሆኖ ማኅበረ ቅዱሳንን ማውገዝ ወይም መቃወም በጭራሽ አይታሰብም።

ሐ/ የመንግሥት ተቋማት አባሎቹ፤

ማኅበሩ ከሚያገኘው ሰፊ የፋይናንስ አቅም አኳያ አባላትን ለመመልመል መጠቀሙ እንዲሁም ከሚጓዝበት አደገኛ የስብከት ዘዴው አንጻር አእምሮአቸውን የመጠምዘዝ ስልት ረገድ በመንግሥታዊ ተቋማት ውስጥ ብዙ አባላትን ማደራጀት ችሏል። የማኅበሩን አቅም ማደራጀት ብቻ ሳይሆን አንድ አቅጣጫ ማየት እንዲችሉ ተደርገው የተቀረጹ የመንግሥታዊ ተቋማት አባላቱ በጣም ጠቃሚ ክፍሎቹ ናቸው።  በመንግሥት ጉዳይ እንደማይገቡ ማሳያዎቹ ናቸው። በሌላ መልኩም የመረጃ ምንጭ ሆነውም ያገለግላሉ። የየትኛውም የመንግሥት ተቋማት ሰራተኛ በየትኛውም ማኅበርና የእምነት ተቋም ውስጥ አባል የመሆን መብት ያለው መሆኑ ባይካድም የያዘውን የመንግስት ስራ ለማኅበሩ አገልግሎት ማዋል ግን ወንጀል ነው። ፖሊሳዊ ስልጣናቸውን በመጠቀም ለማኅበሩ አገልግሎት ተሰማርተው ያላግባብ ያሰሩ፤ የደበደቡ አሉ። ቤተ ክርስቲያኒቱ ስትጠይቃቸው ከመተባበር ይልቅ ማኅበሩ ሲጠራቸው አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጡ የመንግሥታዊ ስልጣን አካላት መኖራቸው ማኅበሩ የቱን ያህል ስር እንደሰደደ ያሳያል። እነዚህ አካላት ከማኅበሩ ጎን በግልጽም፤ በስውርም መቆማቸው ነገሩን ከባድ ያደርገዋል።

3/ ማኅበሩ ራሱን ለማዳን የሚቀያይራቸው ስልቶች፤

ማኅበሩ የልዩ ልዩ ሰዎች ተዋጽኦ መሆኑ እንዳለ ሆኖ አመራሩ ራሱን ከወቅቱ የፖለቲካ ሙቀት ጋር በማስማማት የሚያደርጉት የጉዞ ስልት እጅግ የሚደነቅ ነው። ማኅበሩ ሃይማኖታዊ ድርጅት እንዳይደለ ይታወቃል። የድርጅት/ Organization/ ቅርጽ ያለው ነገር ግን በተቋምነት/ Institution/ ደረጃ የተደራጀ ይመስላል። ደግሞም በቤተ ክርስቲያን ስር ያለ የሰንበት ተማሪዎችም ማኅበር ለመምሰልም ይሞክራል። ምሁራን አመራሩ በሳል ስለሆኑ ከሰንበት ትምህርት ቤት ማደራጃ መምሪያ ስር ያወጡት አለምክንያት አይደለም። የሰንበት ት/ቤት በመባልና የሚንቀሳቀስበት ቅርጽ ተመሳሳይ ስላይደለ እንዳይበላሽበት ከመፈለግ የተነሳ የተዘየደ መላ መሆኑ ነው። ዛሬም ያ የማኅበሩ አመራር ኢህአዴግ ከገባበት የሙስሊሞች እንቅስቃሴ፤ ከምርጫ 2007 ዝግጅት እና የጥላቻ ፖለቲካ ካሰባሰባቸው ኃይሎች ጋር ያለበትን ክፍተት በመጠቀም ከመንግሥት ጋር ያለውን ልዩነት ለመጠቀም እየሰራ ይገኛል። በአንድ ወገን ስለማኅበሩ ጉዳይ እያስጮኸ ፤ በሌላ መልኩ ደግሞ ከጩኸቱ በሚገኘው የስውር ድምጽ ብዛት መንግሥት ወደያዘው ፤ልቀቀው እሰጥ አገባ እንዳይሄድ ባለበት በማስቆም ለመንግስት ፈቃዳት ሁሉ ታማኝ መሆኑን ለማሳየት በመሞከር ራሱን በማዳን ስልት ላይ ተጠምዷል። የቅዱሳን ማኅበር ሳይሆን ጠንካራ የፖለቲካ ቅዱሳን ያሉት ማኅበር ስለሆነ ሊደነቅ ይገባዋል።

4/ ማኅበሩና የመጨረሻ ውጤቱ፤

በትግርኛ የሚተረት አንድ ተረት አለ። «ወጮስ እንተገምጠልካዮ ወጮ» ይላሉ። «ብርድ ልብስን ብትገለብጠው ያው ብርድ ልብስ ነው» እንደማለት ነው። ያውም የደብረ ብርሃን ብርድልብስን ብትገለብጠው ያው ዥንጉርጉሩ  የደብረ ብርሃን ብርድ ልብስ ነው። የሰንበት ት/ቤት?/Sunday school/  ድርጅት? /organization/ ተቋም? /Institution/ የቱ እንደሆነ ማኅበረ ቅዱሳን እስካሁን የለየለት አይደለም። ነገር ግን ቅርጹንና መልኩን እንደእስስት እየቀያየረ 22 ዓመት ቆይቷል። ቤተ ክርስቲያኒቱ ለማኅበሩ ምኑ እንደሆነች ሲኖዶሱ በእርግጥ አያውቅም። ማኅበሩ ግን ቤተ ክርስቲያኒቱን እንዴት እንደሚጠቀምባት አሳምሮ ያውቃል። በጣም አደገኛና ስልታዊ ጉዞ የማድረግ ብቃት ያለው አመራር እንዳለው በጉዞው ላይ የሚያጋጥመውን ሳንካ ካለፈበት ተነስቶ መናገር ይቻላል። እውነተኛና ቅን የቤተ ክርስቲያን አባላት የሱም አባል መሆናቸው ሳይዘነጋ ማለት ነው። ነገር ግን ማኅበሩ  ቢደግፉት፤ ቢከተሉት፤ ቢጮኹለት፤ ቢታገሱት እንደ«የደብረ ብርሃን ብርድ ልብስ ቢገለብጡት ያው ብርድ ልብስ» ከመሆን የሚያልፍ አይደለም!!


36 comments:

 1. Aba selama resihin aba diablos bileh bitseyim yishalihal. Min tihon? Rashin sikel. Pastor diablos yemecheresha zinarun eyeworere new

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከዚህ የተሻለ ጭንቅላት እኮ ከእናንተ አይጠበቅም። አስተምረን እንመልሳለን እንዳትሉ በየትኛው እውቀታችሁ። ሀሳበቸውን አዳምጠን ለመመካከር እንፈልጋለን እንዳትሉ በየትኛው መንፈሳዊነታችሁ በጣም ታዛዝናላችሁ። ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት በክርስቲያን ማኅበረሰብ ውስጥ እንደበቀለ ሁሌም ይገርመኛል። ሀሳባችሁ ሁሉ ልክ እንደ እስላም እረደው ግደለው ብቻ ነው። So Sorry For you People.

   Delete
 2. በእውነት! ማቅ አይደለሁም። አጻጻፍ አትችልም! ጥሩ ካልተጻፈ የሚጻፈው ደግሞ ሓሳቡ ጥሩ እንኳ ቢሆን ለማንበብ ይዘጋል

  ReplyDelete
 3. ማኅበራችን ማኅበረ ቅዱሳን ዓላማን ግብ ያለው በመሆኑ በጊዜው በሚታዩ ጥቅመኞችና አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ሁከት ሳንዘናጋ የወንጌል ተልእኳችንን በጥበብና በትዕግስት ከግብ ማድረስ ይገባናል እንላላን፡፡ ስለዚህ ሐዋርያው ያዕቆብ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ እወቁ፡፡ ያዕ.1፡2 እንዳለ ስለ እምነታችንና ስለቤተ ክርስተያናችን የምናደርገውን አገልግሎት ፈታኙ ዲያብሎስ ሊያደናቅፍ ሠራዊቶቹን ቢያሰማራም እግዚአብሔር አምላካችንን ትዕግስትንና ጽናትን እንዲሰጠን ፈተናውንም እንዲያሳልፍልን በጽናት እንለምነው፡፡- እርሱ በሰው ዘንድ የማይቻለውን እንድንችል ማድረግ ያውቅበታልና፡፡ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

  ReplyDelete
 4. wey gude. min yisalesal mk

  ReplyDelete
 5. «የደብረ ብርሃን ብርድ ልብስ ቢገለብጡት ያው ብርድ ልብስ» ኪኪኪኪኪኪኪካ

  ReplyDelete

 6. ያለ ፈተና ዋጋ ያለ መከራም ፀጋ የለም፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ማኀበሩን ይጠብቅ፡፡ የሚያስከፍለንን መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀታችንን ማን በነገራችሁ፡፡

  ReplyDelete
 7. እንኳን ደስ አላችሁ! ገና ማኅበሩ ይጠነክራል... እናንተም ትዋሻላችሁ... ደጋፊው ይበዛል... የተሃድሶዎች ሴራ ይፈራርሳል... ቤተ ክርስቲያን ለዘላለም ትኖራለች። እናንተ ግን ወደ አዳራሻችሁ ትገባላችሁና ማኅበሩ ግን ቤተ ክርስቲያናችን ዛሬም ነገም ይጠብቃል። እርርርር... በሉ

  ReplyDelete
 8. አባ ሰላማዎች ከፋችሁ እንዴ? ምን ይደረግ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ሰንበት ተማሪዎቹ፣ የጥምቀት ወጣቶቹ፣ የመንግስት ሰራተኞቹ፣ነጋዴው፣ አባሉ፣... ደጋፊው እኮ በዛ! መዋቅሩም ከአንታርቲካ ውጪ በዓለም ሁሉ ተቆጣጥሮታል። ወይኔ የምንፍቅና ትምህርታችሁ እንዳታስተምሩ ፣ ቤተ ክርስቲያን እንዳታፈራርሱ ምቀኛ ሆነባችሁ አይደል! ችግር የለም በቃ ተስፋ እንቆረጣችሁ በፅሑፋችሁ አይቼአሎህና በቃ አትድከሙ ዝም ብላችሁ ወደ አዳራሻችሁ ተመለሱ። እንዲህ የምላችሁ በንዴት ጨጎራችሁ እንዳይላጥ ብየ እንጂ ከፈለጋችሁ ግን ሰሚ የሌለው የውሸት ፕሮፖጋንዳችሁ መቀጠል ትችላላችሁ እርር... በሉ

  ReplyDelete
 9. 2.1 ወይ ተሃድሶዎች ስለ ማኅበረ ቅዱሳን ገና ምን አይታችሁ ጠላት ዳቢሎስን ከቤተክርስቲያን እስከሚወጣ ብዙ ይሰራል ደጋፊዎቹ የኦርቶዶክስ ልጆች በሙሉ ነን…

  ReplyDelete
 10. 1. ማኅበረ ቅዱሳን የምታውቁት መስሏችሁ ነው አታውቁትም 4 ኪሎ ያለው ህንፃሰላችሁ አለም አቀፍ እኮ ነው…… በተማረው የተዋህዶ ልጆች በሙሉ

  ReplyDelete
 11. Dear My Brother! You have to be sincere when you write on something spiritual! It shall not be based on vengeance. When the Government or EOTC something negative about Mahibre Kidusan Tehadiso and despot clergy echo. The fact Mahibre kidusan has several educated members who have root and contact with Sunday schools and strongly advocated the creed and the cannon OF EOTC is apostolic made it focus of attention. For the tehdiso, it is an obstacle to stir Luthrean like reformation in EOTC to establish Geeze speaking protestant denomination , for Pentecostals and charismatic it is an obstacle for Zemcha Philipos.
  I did not attend any Gubae by the association except reading Hamer and other publication and Books. I have also listened to the veteran preacher such as Birhanu, Dejene and Daniel. Let me mention one case. The EOTC Books are 81 while our protestant brethren have only 66. In one of books sponsored by Mahibre Kidusan, I read about how dead sea scroll was discovered and its relations and only EOTC the the two books one is Book of Enoch. This incited me to read about dead sea scrolls, after which I concluded the Books of Bible are 81 and our protestant Breathen only accepted the Bible that was censored by Jewish after Birth of Chirst to omit clearly written statement on his coming! I am also convinced that Mahibre Kidusan is working to strengthen EOTC by scarifying time their money. The founders of the association the Holy Father Abune Gorgorios shall be praised for having a vision of keeping EOTC from Pentecostals and protestant encroachment by Teaching the Gospel and Church History for the Youth in Higher Education. Let God be praised for working through the Abune!
  The Mahibre shall exist until the threat of encroachment of Pentecostals (stealing sheep) and the like and tehadiso is over and development unit are established in every Parsih and Gedem and the management of the Churches I modernized. It shall try to solve all obstacles by prayer to GOD in a peaceful way and without engaging in controversies. It shall also forgive the accusers!

  Let GOD Keep the Unity of EOTC!

  ReplyDelete
 12. Mirte sehufe. endihe new engi kesafu ayker!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 13. «የደብረ ብርሃን ብርድ ልብስ ቢገለብጡት ያው ብርድ ልብስ»
  aydeleme Yemetel wedihe na

  ReplyDelete
 14. Yemahibere kidusan mefres bizu sew liyasdesit bichilim siraw gin aykuwaretim. Sewochu kalmotu besteker.

  ReplyDelete
 15. WEY TEHADSOWOCH CHUHET ENA WESHET ALEKEBACHU GENA ENATEM TETEFALACHE YMENAFK TELALAKIWOCH...

  ReplyDelete
 16. Wow you just gave up like that. I could see your frustration. Yes MK has many supporters. Why? Because the people know that it is working for the betterment of EOTC. Please stop lying and trying to get government attention. No one will buy your idea.

  ReplyDelete
 17. Betam Betam Tekatelachihu Ayidele?

  ReplyDelete
 18. tekatel errrrr bel mahibere kidusan will stand on the right side and you!!!!!!!!!! will stand on the left side according to what you are doing. unless u get forgiveness from God.Temeles nisha giba abreh sira. Iknow you and you know me.

  ReplyDelete
 19. Abetu lebete yemtekena amlak hoye...ke kale wengel hizbun aglelelew betretachew kadenekorut Simhen yemiterawon
  hulu yemiyasadedewon yihenin yedabilos telalaki parasites mahbere atfalen.geta hoy kale bicha tenager enersum endegum yibetenalu.lezelalemu amen....

  ReplyDelete
 20. andim sw enquan ende E/R HASAB yeminager ena yemitsif yelem metechachet erasachihun feligu lib yisiten amen

  ReplyDelete
 21. Yewenedemoch kesash yetebale seyitan yemeserabet kifo mahiber new geta yafirisew

  ReplyDelete
 22. hasabhen ekebelewalehu mk agelgayochene kemekses wechi wengelen sisebk semche alawkem kekerstos yelk yemiyasbeltachew bezu taotoch alute yeeyesus sem sitera yakatlachewal leks endemirotut wengelen bisebku betekerstiyanachen yehen yulu teketay balatach!kekrstos wengel yelk yerasachewn keberna tekem yemiyasbeltu letesededut nebs hulu yeteyekubetal!

  ReplyDelete
 23. yihen yetsafew sew bewinet ye paster melese wegun tirgum yanebebe denkro new lukas 9 yesew lij liyaden metwal yemilew ersu endemilew bete crstiyanen yemiyafersew hulu abro yinur maletu new tadye endih kehone ye 5 gebeyawin hizeb lemin betene ante betachenen afrashye menafik ye gedel mmitu ke mthon mejemerya ye betecrstiyanen trgum temar

  ReplyDelete
 24. The page of Aba selama is Aba selama what ever you turnover it like Debre Berhan blanket. To get good attention about MK you have to at least write other positive things on EOTC. How could you get attention by polishing black ink on our church. I am afraid you are wasting your time on this page. MK is Mk it will go further without answering for such mad and stupid writers.

  ReplyDelete
 25. በህማማት ጩኸታችሁ በረከተ ልክ አለሙ ሁሉ ተከተለው እኮ ብለው እንደጮሁት አይሁድ፤ በጣም የሚገርማችሁ ነገር የተማረውና ወጣቱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጅ ብቻ ሳይሆን ልጆቻቸውም ጭምር የማህበሩ አባልና ደጋፊ ናቸው፡፡ ታዲያ ምን ይሻላችሁ ይሆን ማህበር እናፈርሳለን ስትሉ ልጆቻችንን ከቤት እያወጣችሁ ልትበትኑ ይሆን? ወይስ? አልገባንም: ለማንኛውም መቼም ሊገባችሁ ስለማይችል የደብረብርሀን ብርድልብሳችሁን ለብሳችሁ ወደ አዳራሻችሁ፡፡ቁራሽ ለሚወረውሩላችሁ ጌቶቻችሁ ኪሳራም ውጤት ነው የኛ ሆድ ከሞላ ይበቃል በሏቸው፡፡ ታዲያ ምን ይደረግ በእግዚአብሄር የሚያምንን መጋፋት መጨረሻው ኪሳራ ነውና፡፡ የኦርቶዶክስ ልጅ እኮ እንደናንተ ሆድ አምላኩ አይደለም፡፡

  ReplyDelete
 26. I wishe you forget about MK and follow the truth about Jesus Christ.Jesus save you not MK.

  ReplyDelete
 27. my cross checking method to know who mahibere kidusan is : enante(abaselamawoch) benekefachihut ena besedebachihut meten mahibere kidusan lebetkiristian ejig melkam sira eyesera mehonun eradalehu. Enante gin bitameseginut ena bitewedut yane mahibere kidusan lebetekiristian telat endehonat argitegna ehonalehu.....neger gin enantem atameseginutim mahiberekdusanim lebtekiristian alegnitawa huno yikatilal....lezelalem amen!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. wendeme dereje egeziabeher yebarekeh egeziabeher yeseteh lik new yetenagerekew

   Delete
 28. “ይህ ማኅበር ከአንታርክቲካ በስተቀር በሁሉም ዓለማት ላይ ቢሮዎች አሉት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ባለችበት ቦታ ሁሉ አለ። በሳንባዋ ይተነፍሳል፤ በደም ስሯም ይዘዋወራል። ”
  ይህንን ካወቃችሁ ታዲያ ለምን ማኅበሩን ለምን ለቀቅ አታደርጉም፡፡ ታዲያ ምንድን ነው የፈለጋችሁት ቤተክርስቲያን ባልዋለችበትና በማትወከወለው ጉባኤ ባዕድ ትምህርትን እንዲቀላውጥ ወይስ ከቤተክርስቲያን እንዲለይ እንደእነ መጋቢ ማን ነበር ያላችሁት፤ ያ በጋሻው፡፡

  ReplyDelete
 29. አይ አባ ሰላማ በሉ ሰማናችሁ ለቤተክርስቲያን ማን እንደሚጠቅም ለይተናልና አትልፉ ። ዘፍኞቻችሁን ይዛችሁ አዳራሻችሁ ግቡ ድሮም ከኛ ጋር አልነበራችሁም ።

  ReplyDelete
 30. Yes. I repeat, Yes, I also need to be < Akrari> if the meaning given to peaceful bodies changed to < Akrary>. The sound is repeated because of this implication. You, please, leave the name Abba Selama for the real church, Orthodox Tewahido. You are typically protestant.

  ReplyDelete
 31. ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ ከሆነ እኔም አክራሪ ነኝApril 29, 2014 at 1:37 AM

  መናፍቅቅቅቅቅቅ!

  እባካችሁ የቅዱስ አባታችንን አባ ሰላማን ስም ለቀቅ አድርጉ!! በግብርም በእምነትም እጅግ ትለያያላችሁና:: በግብር አባታችሁ በዲያቤሎስና በተከታዮቹ ለምሳሌ እንደነ ሉተር, አሪዎስ ወ.ዘ.ተ. ባሉት ሰዎች ስም በግልፅ ተጠቀሙ::


  ይህ ማኅበር ከአንታርክቲካ በስተቀር በሁሉም ዓለማት ላይ ቢሮዎች አሉት። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ባለችበት ቦታ ሁሉ አለ። በሳንባዋ ይተነፍሳል፤ በደም ስሯም ይዘዋወራል። ”
  ይህንን ካወቃችሁ ታዲያ ለምን ማኅበሩን ለምን ለቀቅ አታደርጉም፡፡ ታዲያ ምንድን ነው የፈለጋችሁት ቤተክርስቲያን ባልዋለችበትና በማትወከወለው ጉባኤ ባዕድ ትምህርትን እንዲቀላውጥ ወይስ ከቤተክርስቲያን እንዲለይ እንደእነ መጋቢ ማን ነበር ያላችሁት፤ ያ በጋሻው፡፡

  ReplyDelete
 32. እኔም አክራሪ ነኝ

  ReplyDelete
 33. tahadiso(protestant)ye 666(le awurew manged taragi nachu)minim atamatum manafik ula dagmo ba bir tagaztachu birr naw wayes egziabiher new yemitamaljut?

  ReplyDelete