Wednesday, April 16, 2014

ለስቅለት ዕለት የታሰበው የማኅበረ ቅዱሳን የአመፅ ጥሪ ይፈጸም ይሆን?

Read in PDF

ሁከት ፈጣሪው ማኅበረ ቅዱሳን ሚናውን ለይቶ መጫወት ሲገባው የጨዋታው መንገድ ጠፍቶበት ሃይማኖትና ፖለቲካን እያጣቀሰ የጀመረው ጉዞ ጦዞ ወደመጨረሻ የደረሰ ይመስላል፡፡ ከሰሞኑ እየደለቀ ያለው የሽብር ከበሮም ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ማቅ እንደተለመደው ከጀርባ ሆኖ በሚናገርባቸው ጋዜጦችና መጽሔቶች በተለይም ፋክት በተባለው መጽሔት ተመስገንን መናገሪያው አድርጎ ያስተላለፈው የዐመጽ ጥሪ ማቅ ዓላማውን ለማሳካት የት ድረስ ለመጓዝ እንደሚያስብ ያመላከተ ሆኖ አልፏል፡፡
በተመስገን በኩል ማቅ ያስተላለፈው ጥሪ የስቅለት በዓል ዕለት ምእመናን እንዲያምፁ የሚቀሰቅስ ነው፡፡ ከተመስገን በቀር አባላቱ እነታደሰ ወርቁና ብርሃኑ አድማስ “አትነሳም ወይ?” የሚል የዐመጽ ጥሪያቸውን በየመጽሔቱ ሲያስተላለፉ እንደነበር ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በተለይም ታደሰ ወርቁ ከሙስሊሙ ማኅበረሰብ መካከል የወጡ አክራሪዎች የተከተሉትን መንገድ መከተል እንደሚያዋጣና ለዚህም ማቅ ከጀርባ ሆኖ ያደራጃቸውን የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶችን ሊጠቀም እንደሚችል ጠቁሞ የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ይሁን እንጂ እነርሱን መያዝ የሚቻለው ተሐድሶን መቀስቀሻ በማድረግ እንጂ በቀጥተኛ ፖለቲካዊ ቅስቀሳ አለመሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
ጥያቄው ግን ማቅን በዚህ መንገድ ለመደገፍ የሚፈልግ ጤነኛ ሰው አለ ወይ? የሚል ነው፡፡ የማቅ ደጋፊ የሆኑ ምሁራን ተብዬዎች እንኳ ከሰሞኑ በየመጽሔቱ ድምፃቸውን ያሰሙት ስማቸው እንዳይጠቀስ በማድረግ ነው፡፡ “ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር እንዳሉት” እየተባለ ነው ሲዘገብ የሠነበተው፡፡ እነርሱ በፍርሃት ተሸብበው ምስኪኑን ወጣት ግጭት ውስጥ ለመክተትና ለመማገድ የነደፉት ስልት ብዙም የሚሰራበት ዕድል ያለ አይመስልም፡፡ ከጥምቀት ተመላሽ የተባለውና በታደሰ ወርቁ “ቅምጥ ኃይል” ተብሎ የተቆላመጠው ወጣቱ ክፍል በምን ሒሳብ ነው ማቅን ደግፎ የስቅለት ዕለት ለመቃወም የሚነሳው የሚለው እስካሁን ምንም አሳማኝ ነጥብ የለውም፡፡
ማቅ እስካሁን ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳውን ለማራመድ በሽፋንነት የሚጠቀምበት “ተሐድሶ” የሚለው ነጠላ ዜማው አሁን አድማጭ የሌለው ከንቱ ጩኸት እየሆነ ይገኛል፡፡ ከሰሞኑ በሌለ ታሪክ በቅድስት ሥላሴና በመቀሌው ከሳቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ላይ የከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ መሬት ላይ የሌለ የብሎግ ላይ ነብር ከመሆን አላለፈም፡፡
“እግዚአብሔር ሲጣላ አያነሳም በትር እያደናበረ ይነሳሃል ምክር” እንዲሉ አበው በአንድ ጊዜ ከሁሉም ጋር በመጋጨት ራሱን ትልቅ ታሪካዊ ስሕተት ውስጥ የከተተው ማቅ ከአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ሌሎች አገልጋዮች ጋር የገባበት የከረረ ጠብም መጨረሻው የሚያምር አይመስልም፡፡ ካህናት እንኳን ለማቅ ለአፄ ቴዎድሮስም እንዳልተኙ ታሪክን መመርመር ነው፡፡ ስለዚህ ማቅ በራሱ ጊዜ ራሱን እያፈረሰው ይገኛል የሚለው እውነታ እየጎላ መጥቷል፡፡
ከሁሉም የሚያሳዝነው የስቅለት በዓል ምእመናን ስለእነርሱ ቤዛ ሆኖ የሞተውን የክርስቶስን መከራና ስቃይ በማሰብ በጾምና በጸሎት በስገድትም ስለኃጢአታቸው ንስሐ መግባት ትተው ለእርሱ የተቃውሞ ድምፅ እንዲያሰሙለት ጥሪ ማስተላለፉ ነው፡፡ ከዚህ ይልቅ ማቅ በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል አሳውቆ ሰላማዊ ሰልፍ ለምን አያደርግም? ወይም ሌላ የመቃወሚያ መንገድ ካለ ለምን እርሱን አይጠቀምም? ለምን ሃይማኖታዊ በዓላትን ተገን በማድረግ ለመንቀሳቀስ ተነሣሣ? የሚሉት ጥያቄዎች የሚወስዱን ወደማቅ ተፈጥሯዊ ባሕሪ ነው፡፡ ማቅ ሃይማኖት ለበስ የፖለቲካ ድርጅት ነው፡፡ ከዚህ ማንነቱ አንጻር ዓላማውን ለማስፈጸም የሚፈልገው በአመፅና በሽብር መንገድ ነው፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ መከራና ችግር የጸናበት ክርስቲያን ድንገይ ለመወርወር ሳይሆን ለመጸለይ ነው የሚጠራራው ማቅ ግን የስቅለት ለት የክርስቶስን መከራ ማሰብ ማስታወስና የተደረገልንን በጎ ነገር ማድነቅ ሳይሆን ድንጋይ መወርወር ማመጽ ይገባችኋል እያለን ነው፡፡ እንዲህ ያለው ኢክርስቲያናዊ መንገድን መከተል የክረስቶስን መንገድና መቃወም ይሆናል፡፡ ምንም እንኳ በስቅለት ለት ማቅ የተመኘው ረብሻና ብጥብጥን ቢሆንም ህዝበ ክርስቲያኑ ግን  አምላኩን በትህትናና በፍቅር እያሰበ ዕለቱን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡ማቅ ግርግሩን እየናፈቀ ባለበት በዚህ ወቅት የትኛው ሃይማኖተኛ ነው ከማቅ ጎን የሚቆመው የሚለው የፊታችን አርብ የሚፈታ ይሆናል፡፡

36 comments:

 1. ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ፡፡ማቅን እንደ ደብረ ብርሃን ብርድ ልብስ ብትገለባብጡትም አላማው አንድና አንድ ሆነበባችሁ ፡፡አንድም በሁሉም አቅጣጫ ብትመለከቱት የተሳለ ሰይፍ ሆነባችሁ፡፡ እንዲህ ነው የተዋህዶ አርበኛ ይህ ነው የአባቶቹ ልጅ በቤተ ክርስቲያንን ስራ የሚሰራ ልጅ ምልክቱ፡፡ ድንጋዮቹን አፍ አውጥተው እንዲናገሩ የሚያደርገው አምላክ እናንተን እንድትመሰክሩ አደረጋችሁ፡፡ አሁንስ ምን ትሉ ይሆን፡፡ ለነገሩ የሚያሽከረክራችሁ ዲያብሎስ እስከ እለተ ምጽአት እንደሚያገሳ ስለተፀፃፈ ሁሌም የክፋት አባታችሁን ምክርና ሃሳብ እንደማንጋራችሁ ልታውቁ ይገባል፡፡ ለመሆኑ ጠብ ክርክር ግጭት አመፅ የማን መሰላችሁ የአባታችሁ አይደለምን፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድም ያልተጻፈ አታንብብ ያልተነበበም አትጻፍ የተጻፈውን የመረዳት ችግር ካለብህ አማርኛ እናስተምርሃለን።

   Delete
  2. ያልተፃፈ ስለመሆኑ አባትህን(ሰላማን) ጠይቅ መሠረትህ እርሱ ስለሆነ፡፡
   ለነገሩ የመናፍቅ ችግሩ ከላይ ነጥቆ ማንበብ ጠበባየዩ ሰስለሀሆነ የተፃፈን ነገር አላማ መቼ ይረዳል፡፡ የሰላማ ፅሑፎች መወናበድ አንተንም የአማርኛ መምህር ለመሆን እንድትዳዳ አደረገህ፡፡ በአማርኛ ውስጥም ቅኔ መኖሩን እንዳትረሳው፡፡ እንደወረደ የይተረጎምም፡፡ እኔም እደግመዋለሁ፡-
   ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ፡፡ማቅን እንደ ደብረ ብርሃን ብርድ ልብስ ብትገለባብጡትም አላማው አንድና አንድ ሆነበባችሁ ፡፡አንድም በሁሉም አቅጣጫ ብትመለከቱት የተሳለ ሰይፍ ሆነባችሁ፡፡ እንዲህ ነው የተዋህዶ አርበኛ ይህ ነው የአባቶቹ ልጅ በቤተ ክርስቲያንን ስራ የሚሰራ ልጅ ምልክቱ፡፡ ድንጋዮቹን አፍ አውጥተው እንዲናገሩ የሚያደርገው አምላክ እናንተን እንድትመሰክሩ አደረጋችሁ፡፡ አሁንስ ምን ትሉ ይሆን፡፡ ለነገሩ የሚያሽከረክራችሁ ዲያብሎስ እስከ እለተ ምጽአት እንደሚያገሳ ስለተፀፃፈ ሁሌም የክፋት አባታችሁን ምክርና ሃሳብ እንደማንጋራችሁ ልታውቁ ይገባል፡፡ ለመሆኑ ጠብ ክርክር ግጭት አመፅ የማን መሰላችሁ የአባታችሁ አይደለምን፡፡

   Delete
  3. እንደው ግን ምነው "አማርኛ አስተማሪዎቹ" (ድንቄም~) ...
   የግድ ከመንግስት ጋር ይጣሉ አባዜ? የሰላም ነው? ..

   ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ! ... ይበል!!

   ሰላማዊ አዕምሮን ላራሳችን/ ለመንግስታችን/ ለህዝባችን/ ባጠቃላይም ለህዝባችን ያድልልን!

   Delete
  4. ለ April 16, 2014 at 10:37 PM
   ማቅን ትልቅ አድርገህ በማየትህ የራስህን ትንሽነት ያሳያል። ማቅ ለቤተክርስታን የሰራላት ትለቅ ሥራ ምንድር ነው? እኔ ልንገርህ የሰራላትን ሳይሆን ግን የሰራባትን ነው። በሃያ ዐመት ታሪኩ ያየውን ሁሉ መናፍቅ ተሃድሶ እያለ ከ14 ሚሊየን ህዘብ በላይ ከቤተክርስቲያን እንዲወጣ አድርጓል። ጴንጤው የተስፋፋው እኮ ያንተ አምላክ ማቅ አንተ እና መሰሎችህ በሰራችሁለት የድንቡሽት ዙፋኑ ላይ እያለ ነው።
   ወንጌል እንዳትሰብኩ ጌታችን ኢያሱስ ክርስቶስን ከ2000 ሺህ ዓመት በፊት መወለዱን ገና አልሰማችሁ። ፍቅር እንዳትናገሩ የፍቅር ባለቤትና ጌታ የሆነው ኢየሱስ በመስቀል ላይ ስለፍቅር ብሎ ተሰቅሎ ኃጢአታችንን ጠርቆ ማስወገዱን አላወቃችሁ። እውነት እንዳትናገሩ አባታችሁ የሃሰት አባት የሆነው ዲያቢሎስ ነው።
   ይህ ባህሪያችሁና እና ማንነታችሁ ከደብረብርሃን ብርድ ልብስ ጋር ያመሳሰላችሁ። ወዲህም ወዳም ብትገላበጡ የጨላመውን ገዢ እና መንግስቱን ብቻ ማገልገል ብቻ ነው ሥራችሁ። በዚህ ዘመን ቤተክርስቲያን በሰይፍ ለመጠበቅ የሚሞክር የክርስቲያን ተቋም ማቅ ብቻ ነው። ያልተሰበከለትን የሚያነብ። ኢየሱስ ሳለ ሙሴን የሚናፍቅ የሚባለው እኮ በእንዲህ አይነት ድርጊቱ ነው። አሁንስ አማርኛ ለመማር ፈቃደኛ ነህ። ቅኔውንም ጨምሮ።

   Delete
  5. ለ April 16, 2014 at 11:33 PM
   ማን ከመንግስት ጋር ይጣሉ አለ? እነርሱ ካልተጣላን ስላሉ ተዉ ይቅርባቹ ተባለ እንጂ። ሰልፉ እኮ የተጠራው ለማህበሩ የህዝብ ግንኙነት ሥራ በሚሰራው በፋክት መጽሔት በኩል ነው። ይልቅስ ወደ አምስት ኪሎ አካባቢ ከቢሮዋቸው አሊያም ደግሞ በንግድ ተቋሞቻቸው በአንዱ ሄደህ ከመንግስት ጋር እንዳይጣሉ ምክር ቢጤ ለግሳቸው።

   Delete
  6. ..... እና ሰልፉ ምን ሆነ? 'በቆረጥ ኦርቶዶክስ ልጆች" ከሸፈ!? .....ቂቂቂቂ
   ሀ ሁ..
   ቀ ቁ ቂ ...ቂላ ቂል!!

   ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ! ... ይበል.. ይበል... ይበል!!

   Delete
 2. Oh my god. ....temariwon new limagedu yetenesut????? Lemen ???? Lemen yesekelet
  ken?????? Mk Greenspan alefech..belete a rbe
  Yefesesewo yeamlakachen dem ledehnetachen Beki new..Lela dem endifes atadergu....beselamawi menged adergut seytan kaltesenawetachu Beker ..i hate mk from the bottom of my soul. Now I hate them more...not the fool once the one on the top .

  ReplyDelete
 3. Lemind new mk behedebet hulu bewech hager behager bet tedebiko mitekusew lemin tikikilegna tekorekuari kehone anegtun leseyif yemayesetew?lelawen meyasewegaw wendimochun abatochun ehetochun endasadede ayeeeeeee amelake esrael yemeferejaw gize yederese yimeslal awede miheretun yeashemur mederek adergew sizebabetubet egzioo

  ReplyDelete
 4. ምናለ! አሁን እንኳ (በሰሙነ ሕማማት) አደብ ብትገዙ!

  ReplyDelete
 5. Your contradiction with Mahibre kidusn is because of you want to revise the Dogma of EOTC. You do not believe in the intercession of saints and you call Our Lord and Survivor Jesus Christs King of Kings aplha and omega "the Intercessor" ! ( confusing the act of intercession committed on the cross due to his human nature ). Although you have the right to take this believe, you do not have the right to form clandestine cell in EOTC to stir Lutheran type of violent Reformation as your western finical sponsors hoped. Mahibre kidusan exposed that you are Protestants 5th column and call upon EOTC Father to excommunicate you so that yo can join one of the denomination you choose unless you repent from heart confessing your sin.

  Know you are trying to mislead the Government by making them scared sothat MK will be made illegal and you can implement tehadiso agenda in EOTC unopposed. Is this not diabolic warfare?
  For your propaganda, nothing will happen on Friday. Temesgen shall understand EOTC believers war is spiritual not earthly. Nobody will be fooled by his propaganda for political and economic gain (sell his newspaper).

  Amen

  ReplyDelete
 6. " ማቅ እስካሁን ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳውን ለማራመድ በሽፋንነት የሚጠቀምበት “ተሐድሶ” የሚለው ነጠላ ዜማው አሁን አድማጭ የሌለው ከንቱ ጩኸት እየሆነ ይገኛል፡፡ " ይህን ስትሉ " ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ “ የሚባል ብሎግ በራሳችሁ ብሎግ ለጥፋችሁ እያስተዋወቃችሁ ባላችሁበት ጊዜ ላይ መሆኑን አላስተዋላችሁም?ወይስ 'ዓይናችሁን ጨፍኑ' ነው ነገሩ?ልብ ይስጠን።

  ReplyDelete
 7. I do not want to learn Amaharic. Please teach me Tigerna.

  ReplyDelete
 8. Enante aba selama satihonu aba diablos nachihu!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተው ተው ኢሊዩሙናቴ አባትህ እንዳይሰማህ

   Delete
  2. Maru Kebede, please remove your emblem, the illuminate eye!!! Geta yigesitsewu!!

   Delete
 9. በስቅለት ለት ማቅ የተመኘው ረብሻና ብጥብጥን ቢሆንም ህዝበ ክርስቲያኑ ግን አምላኩን በትህትናና በፍቅር እያሰበ ዕለቱን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡ማቅ ግርግሩን እየናፈቀ ባለበት በዚህ ወቅት የትኛው ሃይማኖተኛ ነው ከማቅ ጎን የሚቆመው የሚለው የፊታችን አርብ የሚፈታ ይሆናል::
  MK is not believe in bible or Lord God Jesus who died for our sin on the cross. MK is politician organization hiding him self behind the Orthodox Church...............Thank you Aba Selama. Happy holy day for truth orthodox Christians members.

  ReplyDelete
 10. ተናገር ሰላማ ልስህ ምንድን ነው፡፡
  የስቅለት ዕለት አመፀኛው አባትህ በነፋስ አውታር የታሰረበት መሆኑን ዘነጋኸው፡፡

  ReplyDelete
 11. ወይ አባ ሰላማዎች ለምን አርፋችሁ አትቀመጡም? ማኅበረ ቅዱሳን መቼም ቢሆን እናንተ ለምትፅፉት የውሸት ፕሮፖጋንዳ ሰሚ ጀሮ የለውም። እናንተም እውነቱ ስለምታውቁት ማኅበሩ ዛሬም ነገም ለቤተ ክርስቲያን የቆመ ማኅበር ነው። ፈተናዎች ቢኖሩም ማኅበሩ ፈተናዎች የሚቋቋመው በጸሎት እንጂ በዐመፅ አይደለም። ምክንያቱም ለሰይጣንና እንደ እናንተ ላሉ የሰይጣን ተላላኪዎች የሚያስፈራቹ ሰይፍ ሳይሆን ጸሎት ነውና። ማኅበሩ መቼም ቢሆን ዐመጽ እንደማያነሳ ስታውቁ ዐመፁ የተወው ደጋፊ አጥቶ ነው የሚል መልእክት ስትፅፉ ገርሞኛል! ሰይጣንና የሰይጣን ልዑካን ሁሉ የፈለጋችሁትን ማለት ትችላላችሁ በመጨረሻ ግን በመስቀሉ ኃይል ትጠፋላችሁ

  ReplyDelete
 12. Mk priest in USA made pregenant five women the same time. You gues need to be investigate.

  ReplyDelete
 13. Do you know the lion share of stock holder in mk? Most of them said that Gojam ethinic. They use metet to stay in business, for example Aba abrham or abrar strictly enforced and gave command to stopping Jesus name in Harar.My name is kalwold wold abrham.from Merkato.

  ReplyDelete
 14. ማ/ቅ/ን በሲኖዶስ የተወገዘ ፣ ከሚሽነሪወች በሚወረወር ፍርፋሪ የሚኖር ሳይሆን,,,,,

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከዲያቢሎስ መንግስት በተቆረጠለት ራሽን የሚተዳደር ነው።

   Delete
 15. Mk one of the biggest terroriest organization in horn of Africa, called eotc to demolish gov. in holy cross holiday. We all informed to our Christian brother to all over the world to support ethiopian gov. to do more fight terrorism in the horn. Eriterian gov.and others directley support finance to mk and other peace enemy in Ethiopia. Mk has opened office in Eriteria close to ginbot seven office. They recieved command with ato Andatgachew who. is the wanted criminal in Ethiopia.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቈ ቈቄቲ... አይ ውዳጄ እንግሊሺና ጽፈው ሞተዋልሳ !
   ግድ የለም/ በበ..በያው ባደጉበት ቋንቋ ቢናገሩ እንረዳዎታለን. ዲ ና ዴ ን ግን ይለዩ ታዲያ.

   Delete
  2. አንተስ ለሹመት ብትታጭ መልካም ነው፡፡ ይህን የመሰለ መረጃ አቅርቦ የሚያውቅ የለም፡፡ መረጃውን የያገኸው ከሲኦል ባለስልጣናት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ከአንተ ጋር ነበር መዛመድ፡፡

   Delete
 16. እናንተ የምትሉት እንጂ ማህበሩ ይህንን ሃሳብ ከመንዝ ጌራ ነኝ...አሁንም ወደፊትም አያስበውም ምክንያቱም ማቅ የኢትዮ.ቤ/ክያን ዶግማዋ፣ስርአቷ ሳይበረዝ ለትውልድ የሚተላለፍበትን መንገድ ስለሚያስብ እና በእግዚአብሄርና በአባቶች ፍቃድ የሚገዝ ስለሆነ ነው።

  ReplyDelete
 17. ማቅ የመንፈሳዊ ማህበር ነኝ እያለ ይፎክራል ነገር ግን የሚመካዉ በዘረጋዉ መዋቅር በአበላቱ ቁጥርና በደጋፊዎቹ ነዉ ይህ እንግዲህ አላማዉ ምን እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ቃሉ የሚመካ በእግዚአብሄር ይመካ ነዉ የሚለዉ፤፤ እነ ነብዩ ኤልያስ እነ ሃዋርያዉ ጳዉሎስና ሌሎችም ደቀመዛሙርት አለምን የገለባበጡት በመንፈስ ቅዱስ ሃይል እንጂ በአባላት ብዛት ወይም በዘረጉት መዋቅር አይደለም .
  በደንብ ላስተዋለዉ ማቅ ከግብፁ ሙስሊም ወንንድማማችነት ማህበር ጋር በታሪክም በስትራቴጂም ተመሳሳይ ናቸዉ ሁለትም በልማት ስም በሽፋን የሚንቀሳቁሱና በላቸዉ ነገር ሁሉን ማድረግ የሚችሉ ይመስላቸዋል ፡ የማቅ የመፍረሻዉ ግዜ ብዙ ሩቅ አይሆንም ለምን ቢባል አዉነተኛዉ ማንነቱ እየተጋለጠ ነዉ

  ReplyDelete
 18. Mk ,You paid money to Synodos papas for wogezet. That was not real wogzet.

  ReplyDelete
 19. Fiker Leikun menafik mehonun alawukim neber, good to know

  ReplyDelete
 20. ማቅ አልተሳካለትም። ስቅለትም በሰላም አለፈ።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለምን ይመስልሃል፡፡ አንተና መሰሎችህ ያሰባችሁት ሁከት እንዲፈጠር ነበር፡፡ ይህ ግን ያልታሰበና ወደፊትም ሊታሰብ የማይችል በመሆኑ ነው፡፡ አላማው አይደለማ፡፡ ወይ ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ! ይሏል ይህ ነው፡፡
   አናንተ የአማርኛ መምህራን ነን ባዮች፡፡ አንዳንዴ አባታችሁን ለመሸወድ ትሞክራላችሁ የግብር አባታችሁ ዲያብሎስ ብጥብጥ ለመፍጠር አያሳፍረንም ብላችሁ ነበር አይደል፡፡ ሞኛችሁን ፈልጉ የረጅም አመታት ልምድ ያለው መሆኑን ረስታችሁት ነው፡፡ የታሰረበት ቀን ስለሆነ ይፈራል፡፡

   Delete
 21. አባታችሁ መለስ ማ/ቅ ሳያፈርሰው ፈረሰ።አባታችሁ ሀ/ማ አቅም አጠረው ።ወይ ተሀድሶ!!!!!

  ReplyDelete
 22. Mk wede libu temeliso yebetekrstyanon tinsae mechem bihon mayet kerto masebim ayasham.

  ReplyDelete
 23. yamahebere kedusan abalat sayemaru kesena decuna eyatakabalu kihinatun eyaqaalalu beatamaqedasun bemadafar seriata beatakristian eyaxasunaw ena ebakachihu e/rn feru !!! Lanagaru enaneta Polaticanyochi !!

  ReplyDelete
 24. sayimaru memihir sayizeru geberie
  endet neh selama ekuye gebarie
  eshohin be eshoh bihonim negeru
  yihew yishalewal ledabilos gibru

  ReplyDelete