Saturday, April 19, 2014

ኢየሱስ ስለ ኀጢአታችን ሞተ እኛን ስለማጽደቅም ተነሣእንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ


“ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል”
(1ጴጥ. 1፥3-5)

መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ መሞቱና ከሙታን ተለይቶ መነሣቱ በየዓመቱ ይከበራል፡፡ በዚሁ መሠረት ካህናቱና ምእመናኑ የጌታን ሕማማት በጾም በጸሎትና በስግደት ሲያስቡ ሰንብተዋል፤ የትንሣኤን በዓል ለማክበርም በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡ ነገር ግን ጌታ የመሞቱና የመነሣቱ ምስጢር ገብቷቸው በዓሉን የሚያከብሩ ስንቶች ይሆኑ?
ብዙዎች ጌታን አይሁድ ሰቅለው እንደገደሉትና እርሱ ግን በታላቅ ኀይልና ሥልጣን እንደተነሣ ብቻ ስለሚያስቡ ከዚህ ዐልፈው የመሞቱን ምስጢርና የመነሣቱን ዓላማ አያስተውሉም፡፡ ከዚህ የተነሣ አይሁድን ሰቃልያነ እግዚእ (ጌታን የሰቀሉ) በማለት ለጌታ ያላቸውን ፍቅርና ሐዘኔታ አይሁድን በመጥላት ለመግለጽ ይጣጣራሉ፡፡ ጌታ ግን ለሰቀሉት አይሁድ “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ሲል ምሕረትን ከአባቱ ለምኖላቸዋል፡፡ ጌታን በመውደድ ስም እርሱ እንዲህ ያዘነላቸውን መጥላት ተገቢ አይደለም፡፡ ብዙዎች የማያስተውሉት የጌታ የመሞቱ ምስጢር ግን ከዚህ ይለያል፡፡
ቅዱስ ሉቃስ በጻፈው የሐዋርያት ሥራ ላይ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤ እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዓመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት። እግዚአብሔር ግን የሞትን ጣር አጥፍቶ አስነሣው፥ ሞት ይይዘው ዘንድ አልቻለምና።” የሚል ቃል ተጽፏል (የሐዋ. 2፥22-24)፡፡ በዚህ የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ የተገለጠው እውነት ጌታ ለአይሁድ ተላልፎ የተሰጠው በይሁዳ ጠቋሚነትና “ሻጭነት” ቢሆንም፥ ዋናው ግን በእግዚአብሔር ውሳኔና በቀደመው ዕውቀቱ ስለኀጢአታችን ተላልፎ መሰጠቱና ሞታችንን መሞቱ ነው፡፡ ስለዚህ ሞቱ የኀጢአታችን ዕዳ የተከፈለበትና እኛ ነጻ የወጣንበት ማስረጃ ነው፡፡ በዚሁ መሠረት የኀጢአታችን እዳ ተከፍሏልና ወደፊት የሞት ዕዳ የለብንም ማለት ነው፡፡ 

እንደሞቱ ሁሉ ትንሣኤው ደግሞ በብዙዎች ዘንድ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ መነሣቱ የሚታሰብበት ብቻ ተደርጎ ነው የሚወሰደው፡፡ ትንሣኤው ይዞልን የመጣው የምሥራች ግን እጅግ ታላቅ ደስታ ነው፡፡ ጌታ ሞትን ድል አድርጎ የተነሣው እኛን ስለማጽደቅ ነው ይላል መጽሐፍ (ሮሜ 4፥24-25)፡፡ ሞቱ የኀጢአታችንን መደምሰስ ሲያበሥር ትንሣኤው ደግሞ በተከፈለው ዕዳ መሠረት መጽደቃችን የተረጋገጠበት ሰነድ ነው፡፡ ሞቶ የነበረው ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቷል፤ መነሣቱም ዕዳችን የመከፈሉንና እኛን የማጽደቁን የምሥራች ነው ይዞልን የመጣው፡፡ ይህን ሳያስተውሉ የጌታን ሞትና ትንሣኤ ማክበር ትርጉም የለውም፡፡
በክርስቲያኖች ዘንድ የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በየዓመቱ የሚከበር በዓል ከመሆን ያለፈ ትርጉም ያለው ትልቅ ክሥተት ነው፡፡ በዓሉን የምናከብረው የተደረገልንን ታላቅ ማዳን ለእኔ የተደረገ ነው ብለን በማመንና በመቀበል ከሆነ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በመብልና በመጠጥ፣ በአስረሽ ምቺው ፈንጠዝያ ከሆነ ግን ትርጉም የለውም፡፡
ወገኔ ሆይ ክርስቶስ የሞተው የአንተን የኀጢአት ዕዳ ለመክፈል ነውና ዕዳህ ተከፍሏል፡፡ ከአንተ የሚጠበቀው ዕዳህ እንደተከፈለና ከሞት ፍርሃትና ከዲያብሎስ እስራት ነጻ እንደወጣህ ማመን ብቻ ነው፡፡ “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።” ተብሏልና (ዕብ. 2፥14-15)፡፡ ስለዚህ ስለኀጢአታችን ሞቶ የተቀበረው ክርስቶስ ሞትን ድል ነስቶ የተነሣው በእርሱ ሥራ ያጸደቀህ መሆኑን ለማወጅ ነው፡፡ አሁንም ከአንተ የሚጠበቀው ይህን ዐዋጅ ሰምተህ በእርሱ ሥራ ያጸደቀህ መሆኑን ማመንና መቀበል ነው፡፡ “መድኀኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኀጢአቴ ሞቶልኛል፤ እኔን ለማጽደቅም ተነሥቶልኛል፤ በእርሱ ካመንሁኝ የዘላለም ሕይወት አለኝ” ብለህ ማመንና መቀበል ይጠበቅብሃል፡፡ ይህን ካደረግህ የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ምስጢር ገብቶሃል ማለት ነው። ከዚህ ውጪ ሆነህ የሞተበትን ቀንና የተነሣበትን ዕለት የምታከብር ብቻ ከሆንህ ከስረሃል፡፡ ስለዚህ ስለምን ትዘገያለህ? የኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ የመዳንህ ሥራ የተከናወነበት መሆኑን በእምነት ተቀበል፡፡
ኢየሱስ፥  ክርስቶስ መሆኑን አምኖ መቀበል ለመዳን ቁልፍ ውሳኔ ነው፡፡ ይሁን እንጂ አንዳንዶች ይህ የሌሎች አባባል ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሣብ ነው፤ የሚከተሉትን ጥቅሶች ሐሳብ መመልከት እንችላለን፡፡
“የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም። ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤” (ዮሐ. 1፥11-12)፡፡
“እንግዲህ ጌታን ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ።” (ቆላ. 2፥6)፡፡
ክርስቶስን አምኖ መቀበል መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐሳብና እያንዳንዱ ክርስቲያን ሊተገብረው የሚገባ የውሳኔው መግለጫ ነው፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃውንትም አባባሉን ይጠቀሙበታል፡፡ በመጽሐፈ ቅዳሴ ላይ የሚከተለው ቃል ሰፍሯል፡፡ “ያ ቃል ቀድሞ የነበረ ነው፡፡ ያ ቃል የእግዚአብሔር ቃል ነው፡፡ ያ ቃል ሥጋ ሆነ፡፡ በእኛም አደረ፡፡፡ ለአባቱ እንደ አንድያ ልጅ የሚሆን ክብሩን አየን። ያ ቃል ወደ ወገኖቹ መጣ፤ ወገኖቹ ግን አልተቀበሉትም፤ የተቀበልነው እኛ ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ነን” (መጽሐፈ ቅዳሴ 1984፣ ገጽ 107)።
ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅም ትምህርተ ክርስትና 2ኛ መጽሐፋቸው ላይ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህናትነት፣ ነቢይነትና ንጉሥነት ካብራሩ በኋላ በመጨረሻው ላይ እንዲህ ብለዋል፦ “… ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ብለን ጌታችንን ስንጠራው የዳንን ወገኖች፥ መድኅንም ያለን ሕዝቦች ነን፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ፥ ክርስቶስ እንደ ሆነ አምነን እንቀበላለን፡፡” (ገጽ 36-37)፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስን መቀበል ማለትም “እርሱ የሞተው የእኔን ኃጢአት ተሸክሞ ስለኔ ነው፤ የተነሣውም እኔን ለማጽደቅ ነው፤ በእርሱ ባምን እድናለሁ” ብሎ ማመንና ይህን እውነት ከልብ በመቀበል እርሱን ለመከተል መወሰንና በውሳኔው መሠረት መኖር ነው፡፡ አንድ ክርስቲያን ነኝ የሚል ሰው ክርስቲያን የሆነው በዚህ መሠረት ካልሆነ በየትኛውም ክርስቲያናዊ ሃይማኖት ውስጥ ይጠለል አይድንም፡፡ የሚያድነው ይህን እውነት መቀበል እንጂ ከቤተሰብ በተወረሰ የአንድ ክርስቲያናዊ ሃይማኖት ተከታይ መሆን አይደለም፡፡ ክርስቶስን አምኖ መቀበል የግል ውሳኔ ነው፡፡   
እግዚአብሔር በክርስቶስ ሥራ እንዲሁ በጸጋው ያጸደቀህ ደግሞ የእግዚአብሔርን ፈቃድ እየፈጸምህ ለመኖር ነውና በእምነት የተቀበልኸውን መዳን በሚያረጋግጥ ሕይወት ልትመላለስ ይገባሃል፡፡ ይህም ሲባል እግዚአብሔር ያዘዘህን ትእዛዝ በመፈጸምና እንዳታደርገው የከለከለህን በመጠበቅ እርሱን ደስ እያሰኘህ መመላለስ አለብህ ማለት ነው፡፡ ይህን የምታደርገው ግን ስለጸደቅህ ነው እንጂ በሥራህ ጽድቅን ለማግኘት ብለህ አይደለም፡፡ በዚህ መሠረት ብትኖር በትንሣኤ ዘጉባኤ ዋጋህ ታላቅ ነው፡፡
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እም ይእዜሰ 
ኮነ 
ፍሥሐ ወሰላም

ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ
በታላቅ ሀይልና ሥልጣን
ሰይጣንን አሰረው
አዳምን ነጻ አወጣው
ከእንግዲህ ወዲህ ደስታና ሰላም ሆኗል

 

11 comments:

 1. "በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን" ለምንት ውእቱ ዘተገድፈት?

  ReplyDelete
  Replies
  1. አኮ ዘተገድፈት በአእምሮ አላ በስሕተት "ይህ የጣፊ ስሕተት ነው" እንዲሉ አበው፡

   Delete
 2. Eyesus yadenale! Tebarke!

  ReplyDelete
 3. “ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
  አሰሮ ለሰይጣን
  አግዐዞ ለአዳም
  እም ይእዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሰላም”

  “ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ
  ሰይጣንን አሰረው
  አዳምን ነጻ አወጣው
  ከእንግዲህ ወዲህ ደስታና ሰላም ሆኗል” ብለህ የጻፍከውና ይ ህንኑ ፖስት ደረግከው
  የግእዝ ዕውቀትህ በጣም የሚደነቅ ነው እባክህ፡፡ ግእዝን እንደሚያውቅ ሰው የቤተክርስቲያንን ቋንቋ ለመናገር ትሞክራለህ፡፡ መሞከርህ ባይከፋም ለህዝብ በሚነበብ ብሎግ ደፍረህ የማታውቀውን ስትጽፍ አለማፈርህ ደግሞ እውነትም ይህ ብሎግ የጥራዝ ነጠቅ አጨናባሪዎች መሆኑን ያሳየኛል፡፡ ከጸሀፊው ይልቅ የአታሚው ይገርማል ፡፡ምን ስህተት እንዳለበት ሳያጣራ ፖስት ማድረጉ፡፡ እውርን እውር ቢመራው ተያይዞ ገደል ይሏል ይህ ነው፡፡ ለካ ይህ ብሎግ ከስድብና ከስም ማጥፋት በስተቀር ምን አያውቅም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሊቅነት የሚለካው ግእዝን በማወቅ አይመስለኝም፡፡ ግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ በርግጥ የተገደፈ ሐረግ አለ"በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን" የሚለው፡፡ ነገር ግን ሊቅ በቅንነት የጐደለውን ሞልቶ የጠመመውን አቅንቶ ያነባል እንጂ ሁሉን በጅምላ ውድቅ አያደርግም፡፡ አንተ ግን ዐላማህ ስሕተት መፈለግ ስለሆነ ስሕተትን አጕልተህ የተላለፈውን መልእክት ለማዛበት ሞከርህ፡፡ እንደሚመስለኝ ይህን ዐርማለሁ ብለህ የተነሣኸው ግእዝ ስለምታውቅ ሳይሆን ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን የሚለው ከሊቃውንቱ ዐልፎ የሕዝባውያኑም ስለሆነ ነው፡፡ ደግሞም እንዲህ ያለ ስሕተት መፈጸም እንደስሕተት የሚወሰድ እንጂ ስም ማጥፋት ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ወደልብህ ተመለስ፡፡ ኢየሱስ ስለኀጢአትህ ሞቷል አንተን ሊያጸድቅም ተነሥቷል፤ በእርሱ ብታምን ትድናለህ፡፡ ባታምን ግን ይፈረድብሃል፡፡

   Delete
  2. እሽ አሰፈራጁ!!!!!

   Delete
 4. ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
  አሰሮ ለሰይጣን
  አግዐዞ ለአዳም
  እም ይእዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሰላም

  ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ
  ሰይጣንን አሰረው
  አዳምን ነጻ አወጣው
  ከእንግዲህ ወዲህ ደስታና ሰላም ሆኗል

  ReplyDelete
 5. “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።” (ዕብ. 2፥14-15)፡፡

  ReplyDelete
 6. He/she, who is sent by God, speaks the word of God. He/she who is from God, he/she speaks only the word of God. Those who are from God, they speak and write only the word of God and only the things that build up people rather than bad things that ruin the speaker/writer as well as the listener/reader. Those who are from God, they speak/write peace, God's mercy, His love, and His deeds. Those who are from God, they never write/speak such bad things as insulting people, about despising people,about failure of people, about sin of people etc. If people are from God, they speak/write the word of God. If people are from God, they listen/read the word of God. Writing about one's failure, about one's sin, about one's wrong doing never lets people be member of the God family. We all need to speak/write and listen/read the word of God. Those who are from God, they listen His voice; those who are sent from God, they speak/write the word of God. Those who are from God, they correct a wrong-doer wisely with the wisdom of God. Those who are from God, they advise people with wisdom that the wrong-doer be corrected. St. Paul tells us to speak in a manner that builds others; he tells us not to speak eachother in a manner that ruins all of us. God is love, God is gracious, God is merciful. Those who are from God love each other.

  ReplyDelete
 7. kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk alsemama

  ReplyDelete