Friday, April 25, 2014

ፋሲካችን ማነው? ክርስቶስ ወይስ ማርያም?

Read in PDF

“ተፈሥሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ
ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ ዐፅመ ገቦሁ
የአዳም ፋሲካ እና የጎኑ አጥንት የምትሆን የሔዋን መሸጋገሪያዋ
ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ”
ይህ ኢመጽሐፍ ቅዱሳዊ ድርሰት በመጽሐፈ ሰዓታት ውስጥ የሚገኝና በበዓለ ኀምሳ ዘወትር ማለዳ ከጸሎተ  ኪዳን አስቀድሞ በሚደርሰውና የአፄ ዘርዐ ያዕቆብ “ወንጌል” ወደሆነው ተአምረ ማርያምና ሌሎች አዋልድ መጻህፍት ምንባብ የሚያንደረድረው ድርሰት፣ ማርያምን “የአዳም ፋሲካ” እና “ሔዋንን ከሞት ወደሕይወት ያሸጋገረች ናት” ይላል፡፡ እንዴት የሚያሳዝን ድርሰት ነው!!! እውን ፋሲካችን ማነው? ክርስቶስ ወይስ ማርያም?

ይህን ጥያቄ መመለስ ቀላል ነው፡፡ ማንም ኦርቶዶክሳዊ አማኝ ፋሲካህ ማነው? ተብሎ ቢጠየቅ ፋሲካዬ ክርስቶስ ነው ማለቱ አይቀርም፡፡ እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤” ይላልና ቅዱስ ቃሉ (1ቆሮ. 5፥7)፡፡ ቅዱስ ያሬድም “ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ፡፡” ትርጓሜ፦ “በክርስቶስ ደም ታጥባ ምድር ፋሲካን ታደርጋለች፡፡” ብሏልና፡፡ ነገር ግን ቤተክርስቲያናችንን ስቶ ያሳታትና ከዚህ እውነት ፈቀቅ ብሎ እርሷም ፈቀቅ እንድትል ያደረጋት አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ካሳደረው ተጽዕኖ የተነሣ የተደረሰው ይህ ድርሰት ግን ፋሲካችን ክርስቶስ ሳይሆን ማርያም ናት ይላል፡፡ ነገር ግን ከልቡ ያፈለቀው ኑፋቄና ክሕደት እንጂ ምንም መጽሐፋዊ ማስረጃ የለውም፡፡

ካህናቱም ሆኑ ምእመናኑ ፋሲካቸው ክርስቶስ መሆኑን ቢያምኑም ይህ ድርሰት ግን ይህን እውነት በመካድ ፋሲካችን ማርያም ናት ይላል፡፡ ድርሰቱ በግእዝ የተዘጋጀ ስለሆነ ካህናቱ ምስጢሩን ሳይረዱ ወይም ምንያህል ስሕተት እንደሆነ ሳይገነዘቡ በልማድ በዜማ ስለሚሉት የዚህ ድርሰት ችግር አልታያቸውምና ያለምንም ቅሬታ መሳቀቅ አፋቸውን ሞልተው ከአንጀታቸው ያዜሙታል፡፡ ማርያምንም ያለሥራዋ ያላደረገችውን አድርጋለች፤ ያልሆነችውን ሆናለች በሚል ድፍረት “የአዳም ፋሲካ ነሽና ደስ ይበልሽ” እያሉ በዚህ የክርስቶስ ፋሲካነት በሚታሰብበት ወርኃ ፋሲካ መመስገን የሚገባው የታረደው በግ ክርስቶስ ሳይሆን ባላደረገችው ነገር የጌታ እናት ማርያም እንድትመሰገን ሲደረግ ኖሯል፡፡ ካህናት ሆይ እስከ መቼ ይህን ሐሰት ታዜማላችሁ? ፋሲካችሁ ክርስቶስ ሆኖ ሳለ ፋሲካችን ማርያም ናት እንዴት ትላላችሁ? ቅዱስ ሲኖዶስስ እንዲህ ያለው ኑፋቄ እንዲታረም ለምን አያደርግም?

ይህ በሐሰት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ትልቅ ስሕተትና አምልኮተ ባእድ ነው፡፡ ምስጋና የሚገባውም እግዚአብሔርና የታረደው በግ መንፈስ ቅዱስም ብቻ ነው እንጂ በክርስትና ትምህርት ውስጥ ከፈጣሪ በቀር ምስጋናን የሚጋራ ሌላ አካል ፈጽሞ የለም፡፡ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ “ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ” ይላል (መዝ. 18፡3)፡፡

 መጽሐፍ ቅዱስም ፋሲካችን ክርስቶስ ስለታረደና በደሙ ስለዋጀን ምስጋና እንደተገባው ይመሰክራል፡፡ መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ። አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥ በታላቅም ድምፅ። የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ። ራእ. 5፡9-10፡፡ እውነቱ ይህ ሆኖ ሳለ ታዲያ ከየት አምጥተን ነው የአዳም ፋሲካ የሆንሽ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ የምንለው፡፡ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ አድረህ ሕዝባችንን ያሳትክና በሥላሴ ላይ አራተኛ አካል ማርያም እንድትመለክ ያደረግህ አንተ ክፉ ጠላት እግዚአብሔር ይገሥጽህ!!!


ጌታ ሆይ የአዳም ፋሲካው አንተ ነህ! መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ” ስለዚህ ፋሲካችን ክርስቶስ ሆይ ስምህ ይባረክ እያልን እናመሰግንሃለን፣ ከአንተ በቀር ሌላ ፋሲካ አናውቅም!!!


45 comments:

 1. ፋሲካ ለመሆኔ መመዘኛው መታረድ ነው።እመቤታችንን ምንም ብንወዳት እስዋ ለበደላችን ሥርየት ታርዳልኛለች ልንል አንችልም። ይህ ፍጹም ስህተት ነው። ቤተክርስቲያነችን እውነት ሳያንሳት እንደነዚህ አይነት የሀሰት ትምህርቶችን ግን ተሸክማ ትገኛለች። ይህ አሳዛኝ ነው። የግድ በእምነትና በድፍረት ልንቃወመው ልናስወግደውም ይገባል። ከዚህ የተሻለም አማራጭ የለንም። የክርስቶስን ክብር የሚጋርድ ነገር መጨረሻው ጥፋት ነው።

  ReplyDelete
 2. ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሀፂባ በደመ ክርስቶስ!!

  ReplyDelete
 3. ``ይህ በሐሰት ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ትልቅ ስሕተትና አምልኮተ ባእድ ነው፡፡``
  እውነት ነው።አምልኮተ ባእድ

  ReplyDelete
 4. “መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ። አየሁም፥ በዙፋኑም በእንስሶቹም በሽማግሌዎቹም ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ ሰማሁ፤ ቍጥራቸውም አእላፋት ጊዜ አእላፋትና ሺህ ጊዜ ሺህ ነበር፥ በታላቅም ድምፅ። የታረደው በግ ኃይልና ባለ ጠግነት ጥበብም ብርታትም ክብርም ምስጋናም በረከትም ሊቀበል ይገባዋል አሉ።” ራእ. 5፡9-10፡፡

  ReplyDelete
 5. be mariam misgana ena zema yeminaded ena yemikawom esu yedabilos lij new. egna enamesegnatalen enante tekatelalachihu

  ReplyDelete
  Replies
  1. በማርያም እውነተኛና የሚገባት ምስጋና ማንም አይናደድም። ማርያምን ፍጡር መሆንዋን ረስቶ አምላክ ነሽ አዳኝ ነሽ አላንቺ ክርስቶስ ዋጋ የለውም የሚል "ምስጋና" ግን እርሱ ከዲያቢሎስ ነው። በዚህ የሚደሰት ዲያቢሎስ እና ተከታዮቹ ብቻ ናቸው። ማርያምም ብትሆን እንዲህ ባለ ከንቱ ወሬ ታዝናለች እንጂ አትደሰትም። የእርሷ ክብር እውነተኛው ጌታ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ከብሮ ማየት ነው። የታረደው በግ እውነተኛው ፋሲካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ማርያምን ፋሲካችን የሚል እርሱ ከዲያቢሎስ ነው። የእርሶ ደሰታ በየትኛው ወገን ነው? ከዲያቢሎስ ወይስ ከእውነተኛዎቹ? እራስዎትን ይመልከቱ እና ምርጫዎትን ያስተካክሉ። እንዲሁ በጭፍን እየተጓዙ የሞትን መንገድ አይምረጡ።

   Delete
  2. ምን ያለኸው ነህ በጎንደር! የተጻፈው ክርስቶስ እንጂ ማርያም የአዳም ፋሲካ አይደለችም የሚል ነው፡፡ አንተ ግን "ቢሆንም ይህንኑ ኑፋቄ መዝሙራችን አድርገን እንዘምርላታለን" እያልክ ነው፡፡ እንዲህ ማድረግ መብትህ ነው፡፡ ምንም አልክ ምን ማርያም የአዳም ፋሲካ መባል ከቶ አትችልም፡፡ ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐቅ መግለጥ ማርያም መጥላት አይደለም፡፡ ማርያምን በዚህ መንገድ ማክበርም አይቻልም፡፡ እንዲህ ስለተባለ በግሌ አልቃጠልም፡፡ እኔ የማርያም ወዳጅ እንጂ የማርያም ጠላት አይደለሁምና፡፡ የማዝነው ይህን ስሕተት እየተመራህበት ከቀጠልህና ወደጌታ ካልተመለስክ በመጨረሻ አንተ በሲኦል የምትቃጠል መሆንህን ሳስብ ግን ስለአንተ ቅጥል እላለሁ፡፡ - መጥፋትህ እያሳዘነኝ፡፡

   Delete
 6. በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ አድረህ ሕዝባችንን ያሳትክና በሥላሴ ላይ አራተኛ አካል ማርያም እንድትመለክ ያደረግህ አንተ ክፉ ጠላት እግዚአብሔር ይገሥጽህ!!!

  አሜን!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 7. አሜን !!!!!!!!!!!!!! ኧረ ወገኖች እንንቃ... እግዚአብሔር እኮ በሰማይ ያለውን ሳይቀር ነገረን... በሰማይ ሌላ ምስጋና የለም... እርሱ ብቻ ይነግሳል። ማሪያም ምን ልሁን ብላ ትታረዳለች???? ለሷም እኮ ልክ እንደ እኔ እና እንደ እናንተ ፋሲካዋ ኢየሱስ ከርስቶስ ነው።

  ReplyDelete
 8. I didn't know that. Unorthodox thewado needs reform. Who is gonna stay in this church unless the have to be true Orthodox.

  ReplyDelete
  Replies
  1. So you can go!! who beg you to stay. Go and dance at pentecostal church.

   Delete
 9. አቤት!!!!!!!!!!!! እግዚአብሔር ከላይ ሲያየን ከነስንት ትብታባችን ይሆን የሚያየን... ቤተክርስቲያን የንስሐ ጊዜ ያስፈልጋታል። አዳኟን ትታ የያዘቻቸው ግሳንግሶች የምትጥልበት ኃይል ልትቀበል የሚትችለው እስካሁን ያጠፋቻቸውን፣ የእግዚአብሔር አደራ የወንጌሉን ቃል ትታ በውሸትና በመመቻመች የተሟሟቀችበትን ጊዜ የምትጥልበት ጊዜ የንስሀ አዋጅ ያስፈልጋታል። የስንቱ ነፍስ ጠፋ... ሀሰትን በድፍርት በአውደምህረቷ፣ በመቅደሶቿ... የሚናገሩትስ "አገልጋዮች" ክርስቶስ የሞተላቸውን እነርሱ በሀሰት ትምህርት እየገደሉ... እስከመቼ ይሆን ጌታ ዝም የሚለው??? አሁን ካለንበት ጊዜ የተሻለ ጊዜ ለመመለስ አይመጣልንም። ዛሬአችንን ልንጠቀም ይገባል። ሊወገዝ የሚገባውን ልናወግዝ... ልንጥል የሚገባውን ልንጥል ዛሬ ልንወስን ይገባል። የክርስቶስ ሊመጣ በመቼውም ጊዜ በላይ በቀረበበት በዚህ ጊዜ... ወደ ታረደልን ልንመለስ ይገባል!!!!!!!!

  ReplyDelete
 10. አቀራረቡ ይበል ነው ዳሩ ግን ሰው ክቡር ሲሆን ዕውቀቱን ባለመጠቀሙ ከእንስሳ ያንሳል።
  ለምን በለኝ ለምንማ? በወፍ በእንስሳ በአውሬ እና በዕንጨት በመሳሰለው ሁሉ በማምለኩ ነዋ!
  እንዲህ ያለ ፍጡር ( ማርያም አምላክ ናት)አትበል ብትለው ይሆን ይሆንን እንጃ!
  ሙከራው አይከፋም አጼ ዘርዐ ያዕቆብንም ከመንገድ ያወጧቸው መነኩሴዎች ናቸውጂ ወደው
  አይዶለም

  ReplyDelete
 11. ምደረ መናፍቅ ሁሉ የገረመኝ የማታምንበትን የቅዱስ ያሬድን አባባል መጥቀስህ ነው ዳሩ ግን የግብር አባትህ ዲያቢሎሰ ጌታን ሲፈትነው ጥቅስ ጠቅሱዋል ለመሆኑ ሙሴ የፈርኦን አምላከ ተብልዋል ይህ ሲባል ፈርዎንን ፈጠረው ማለት ነው?ሌላው ሙሴ በሀዋርያት ስራ ላይ "...ሙሴ ቤዛ ባይሆናቸው ኖሮ..."ይላል ታዲያ ይህ አባባል ሙሴ ተሰቅሎ አዳነን ማለት ይሆን?ማርያም የአዳም ፋሲጋ ማለት የአዳም ደስታው ማለት ነው ለምን ቢባል በሄዋን ምክንያት ሞት በድንግል ምክንያት ህይወት ተገኘ ጌታ ከእሱዋ ተወልዶ አዳነን

  ReplyDelete
  Replies
  1. የምር ሰይጣን ያሳወረክ ምስኪን ነክ፡፡ የዚህ አለም ክፉ እንዳያስተውሉ አይምሮዋቸውን አሳወረ የሚለውን ቃል ብነግርህም እስም ለታወረ ሰው የሚገባ አይደልመ፡፡ የቀናክ ቢመስልህም ምንም አታመጣም የሲኦል ሲሳይ ነው የምትሆነው፡፡ ጳውሎስ የቀና መስሎት ለመግደል ሲሮጥ ጌታ አግኝቶታል እሱን ምሳሌ ብታደርገው ነው የሚያዋጣክ፡፡ እሱም ረብ የሚለውን ነገር ሁሉ ስለጌታ ሲል እደጣለ ካነበብክ፡፡ የሰይማኖት ቲፎዞክን በመተው አምልጥ እግዚአብሄር ይርዳክ

   Delete
 12. Visit the new blog
  www.tibebeamlak.wordpress.com

  ReplyDelete
 13. ህዝባች ንን በስንዴና በዘይት ልቦናውን የተበተብክ የሀሰተኛው ክርስቶሰ መንፈሰ የአፄ ዘረአያእቆብ እመቤት ትጣልህ።በቅዱሳንላይ ልትነሳ የተሰጠህ ግዜ ደርሷልእና በቃላት የጀመርከው በሰይፍ ይጠናቀቅ ዘንድ ቃሉ እንዲህ ይላል።ዘንዶውም,,,,,,,

  ReplyDelete
  Replies
  1. ተራጋሚው አጋንንታዊ ግለሰብ
   ልምከርህ
   የሀሰተኛ የክርስቶስ መንፈስ እየሰራ ያለው በአንተ እና በመሰሎችህ የእግዚአብሔርን እውነት ተጋፊዎች ነው። ማርያም ፋሲካዬ ነች ብለህ የምታምን ከሆነ አንተ ከሃዲ ነህ። ክርስቶስን የማታውቅ የደነዘዝክ አጋንንታዊ አካሄድን የሜትከተል ነህ። ይሄ ዘርአያዕቆብ የምትለው ቃልቻም ያደረበት መንፈስ ክፉ ምክር መክሮት አምልኮተ ማርያምን ያስጀመረ የአሰተኛው መንፈስ አገልጋይ ነው። በሱ ያደረው የወደቀው ነው እንጂ የሚጥለው አይደለም። ይልቅስ ወደ እግዚአብሔር እውነተኛ ሀሳብ ተመለስ እና ንስሀ ግባ ፋሲካ ሆኖ የታረደልህን ክርስቶስን ተቀብለህ ዳን።
   መጨረሻው ጥፋት ከሆነ ጉዞ ጌታ ይሰውርህ።

   Delete
  2. ተራጋሚው አጋንንታዊ ግለሰብ
   ልምከርህ
   የሀሰተኛ የክርስቶስ መንፈስ እየሰራ ያለው በአንተ እና በመሰሎችህ የእግዚአብሔርን እውነት ተጋፊዎች ነው። ማርያም ፋሲካዬ ነች ብለህ የምታምን ከሆነ አንተ ከሃዲ ነህ። ክርስቶስን የማታውቅ የደነዘዝክ አጋንንታዊ አካሄድን የሜትከተል ነህ። ይሄ ዘርአያዕቆብ የምትለው ቃልቻም ያደረበት መንፈስ ክፉ ምክር መክሮት አምልኮተ ማርያምን ያስጀመረ የአሰተኛው መንፈስ አገልጋይ ነው። በሱ ያደረው የወደቀው ነው እንጂ የሚጥለው አይደለም። ይልቅስ ወደ እግዚአብሔር እውነተኛ ሀሳብ ተመለስ እና ንስሀ ግባ ፋሲካ ሆኖ የታረደልህን ክርስቶስን ተቀብለህ ዳን።
   መጨረሻው ጥፋት ከሆነ ጉዞ ጌታ ይሰውርህ።

   Delete
 14. አንቲ ውእቱ ፋሲካሁ ለአዳም።ምንት ትርጓሜሁ ፋሲካ?መጀመሪየ እንረዳ!!!!!

  ReplyDelete
 15. ለክርስቶስ ብቻ የተነገረ

  “እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።” (ዕብ. 2፥14-15)፡፡

  ማርያምም ብትሆን ይህ አይገባትም የእርስዋ አይደለም እና

  ReplyDelete
 16. Melekot yitaredal ende? Fasikachin Kirstos ke Dingil Maryam benesaw siga siletarede, Mariyamin Anesata!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. WEDAJE, AHUN BANTE BET MISTIR AMESTIREH MALET NEW! YIHE NEW ENGIDIH YEMAHIBEREKIDUSAN MISTIR (IS IT FROM ENCYCLOPIDIA OF MK?) ...ESKI YANTEN MISTIR AGEBAB ENIKETEL ENIBEL;
   1. YANI HULU MEKERA BESIGA YETEKEBELECHILIH MARIYAM NAT?2. YETESEKELECHILIN MARIAM NAT
   2. MEKABIRIN FENIKILA YETENESACHIW MARYAM NAT?
   3. ARGE EGIZIYABHER BEYIBABE - YAREGECHIW MARIYAM NAT?
   BETEZEGA BER GEBITA SELAM LEKULKIMU BILA YATSINANACHIW MARIYAM NAT?

   BY THE WAY YIHIN HULU AMILAKE YEKEFELEW LANTE LEWENDIME, LENE LEBARIYAW ENDIHUN LENATU LEDINGIL MARIYAMIM NEW. " DINGIL FETARIWAN / ADAGNUN WELEDECH MILEWIN ZENEGAHIW ENDE?'

   GETA YABIRALEH...." BIYAWIKUS NURO ...BALISEKELUT NEBER"

   Delete
 17. weyenai gudathehu eneken setefelegu elete meteate enedayederese neseha gebu zelalemawiwe fasika keresetose betha new lesem ateraru kebere yegebawe kemewenejel wetathu amesegaj yaderegathu

  ReplyDelete
 18. በርግጥ እመበታቺን ምስጋና አንደምገባት ስለራሱዋ ትንቢት በተናገረቺበት በ ሉቃስ ፩:፬፭ ላይ "ከዛሬ ጀምሮ ትዉልድ ሁሉ ብፅእት ይልኛል"በማለት ተናግራለች;ብፅእት ማለትም ምስጉን ማለት ነው.በ መዝሙረ ዳዊት ፰፮ :፭ ላይም "ሰው ሁሉ እናታቺን ፅዮን ይላል :በዉስቷም ሰው ተወለደ :እርሱ ራሱም ልዑል መሰረታት"ይላል.ስለዚህም እናታቺን እያልን አናመሰግናታለን;ይሄ ማለት ግን አምላካችን ክርስቶስን ከምናመሰግንበት ቃል ጋር አንድ መሆን የለበትም;እናም ፋስካቺን ክርስቶስ ነው.እንዴት ስለመቤታቺን ሊነገር እንደቻለ የተሻለ እዉቀት ያላቺሁ ብታብራሩልን ጥሩ ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. Wendime Hiruy! Egiziabher yistilign.Bemigeba teredichalehu.kelay yalewun yetsafkut ene neberku.melsunim sitebik neber.melisunim agignichalehu.melisum "እስመ ግዕዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሣኤሁ" hono agignichawalehu.Egiziabher rejim edme ena tena yistilign.Nurilin

   Delete
 19. አባ ሰላማዎች ምን ያህል ክፉ እንደሆናችሁና በትክክል ይህችን ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ቢቻላችሁ ለማፍረስ ባይሳካ ለማዳከም ቆርጣችሁ እንደተነሣችሁ የበለጠ የተረዳሁበት ጽሑፍ ነው። ምክንያቱም ቅዱሳኑን /ድንግል ማርያምን ጨምሮ/ ለመሳደብ በአጠቃላይ ቤተክርስቲያኒቱን ለማብጠልጠል ይጠቅመናል ይመቸናል የምትሉትን ብቻ እየፈለጋችሁ ስለሆነ የምትፅፉት። እንደዚያማ ባይሆን ኖሮ ቢያንስ በዚህ ጽሑፍ ላይ " ተፈስሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሄዋን እንተ ይእቲ አፅመ ገቦሁ" ከሚለው ቀጥሎ " እስመ ግዕዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሣኤሁ" የሚለውን ትጠቅሱት ነበር። ግን ያን አትፈልጉም ምክንያቱም " አዳምና ሄዋን ነፃነታችውን ያገኙት በልጅሸ በክርስቶስ ትንሣኤ ነው።" የሚል ትርጉም ስላለው። ይህ ደግሞ ከላይ የደረታችሁትን ክስና ተራ አሉባልታ ፉርሸ ያደርግባችሁአል።
  ትክክለኛ ትርጉሙም ድንግል ማርያም ሆይ ልጅሸ ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው ለአዳምና ለሄዋን ነጻነትን አጎናፅፎአቸዋልና ደስ ይበልሸ ማለት ነው። የአዳምና የሄዋን ፋሲካ ነሸ ማለት ደስታቸው ክርስቶስ ከእርሳ በነሣው ፣ሥጋ እንደታረደ ለማመልከት እንጅ ዋናው ምሥጢር ያለው እናንተ በክፋት ልትጠቅሱት ያልፈለጋችሁት "እስመ ግዕዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሣኤሁ" የሚለው ነወ።
  በእውነት በጣም ታሳዝናላችሁ ቤተክርስቲያኒቱን እንካን ጠለቅ ብለው የማያውቁትን ከማደናገር የዘለለ ምንም ልታደርጉአት እንደማትችሉ እናምናለን ።እናንተ ግን የቤተክርስቲያኒቱ የሆነውን ሁሉ በማጣመም እድሜያችሁን ስትጨርሱ ማየት ያሳዝናል። ደስ የሚለው ደግሞ የናንተ አፍራሸ ተልዕኮ ብዙዎቻችንን ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ እያጠነከረን መጣ!!

  ReplyDelete
 20. ታዲያ ይህንድህረ ገጽ የሚያነብ ምንይገጥመው ይሆን አላማውን በግልጽ ያስቀመጠ የሙቤታችን ጠላት
  የዲያቢሎስመሆኑ አይደል

  ReplyDelete
 21. የእኔን ጽሁፎች በአባ ሰለማ ብሎግ ያነበባችሁ ሁሉ በአንድ ቃል ታስታውሱኛላችሁ፡፡ “ቁንጽል” በምትለው ከፊል ተግሳጽ ከፊል ጽርፈት የሆነች ቃል፡፡ቋንቋዋ ለሰላማ ጸሐፍት የስራ ውጤቶች በልክ የተሰፋች ስለምትመስል እደጋግማታለሁ፡፡ተስፋ አደርጋለሁ እነሱም ይታገሱኛል፡፡ምክንያቱም ማስረጃየን ስለማመጣው፡፡ይህ ጽሁፍም ቁንጽል በሚለው ቃል ይገለጻል፡፡ለቁንጽልነቱ 3 ነጥቦችን እጠቅሳለሁ፡፡
  1. ጸሀፊው ሙሉውን ቃል አላስቀመጠውም!!ስለዚህ እኔ ሙሉውን ላስቀምጥልህ!!
  ተፈስሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ፣
  ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይዕቲ አጽመ ገቦሁ፣
  እስመ ግእዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሳኤሁ፣
  በወርሃ እብሬትኪ እግዝእትየ ዘኢይትረከብ ከማሁ፣
  መኑ ዘይቴክዝ ወመኑ ዘይላሁ፡፡
  ትርጉም…. “የአዳም ፋሲካው፣ከአዳም የጎን አጥንት የተገኘች የሔዋን መሸጋገሪያ የሆንሽ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡መዳናቸው (የአዳምና ሔዋን) በልጅሽ ትንሳኤ ሆኑዋልና፡፡እመቤቴ ሆይ፡ባንች ሰሞን/ዘመን እንዲሁ የሚያለቅስም የሚተክዝም አይገኝም፡፡”
  አርዮስ ፈጠረኝ የሚለውን ብቻ አይቶ፣ወለደኝ እስከሚለው ለማንበብ ባለመትጋቱ እንደሳተው ሁሉ ቁንጻዩ ጸሀፊም ዝቅ ብሎ ለማንበብ ባለመታደሉ….እስመ ግዕዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሳኤሁ…መዳን በልጅሽ ሆኗልና….የሚለውን ሳያይ ፋሲካ የምትለውን ቃል ብቻ ቆንጽሎ አደባባይ ይወጣል፡፡
  2. ፋሲካ የሚለው ቃል ትርጉም
  ፋሲካ በእብራይስጥ ..ፓሳህ…አለፈ ማለት ነው፡፡ቃሉ እስራኤላውያን በግብጽ ሳሉ ጉበናቸውን በበግ ደም እየቀቡ በግብጻውያን ላይ የመጣው መቅሰፍት ሳይደርስባቸው እንዳለፈ የሚያሳይ ነው፡፡ቃሉ በግእዛችን ይህንኑ የእብራይስጡን ትርጉም በሚያመለክት መልኩ ሆኖ ነገርግን አዲሱ ፋሲካችን ክርስቶስ ስለመሆኑ ለመግለጽም በቁሙ(በቀጥታ) ጥቅም ላይ ይውላል፡፡በሌላም በኩል ደስ መሰኘት በሚል ይተረጎማል፡፡አስተፍከነ-ደስ አሰኘ-ፋሲካ- ጥሬ ዘር ተብሎ ቃሉ ይመዘዛል፡፡ከላይ ያለው…ተፈስሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ…የሚል ቃልም “የአዳምን ደስታ ያስገኘሽ ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ” ተብሎ ነው የሚፈታው፡፡ምነው በአማርኛስ ቢሆን ፋሲካ የሚለው ቃል ደስታ የሚለው ቃል ተለዋጭ መሆኑን በሚያመላክት መልኩ ሁልጊዜ ደስታ የለም ለማለት “ሁልጊዜ ፋሲካ የለም” እንል የለ እንዴ!!ምነው ታዲያ የሰላማው ቆንጻይ እንደ ጋሪ ፈረስ ፊደሉን ብቻ ይዞ ጎታች ሆነብንሳ!!መዳን በልጅሽ ሆኗልና (እስመ ግእዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሳኤሁ) እያለ ደራሲው የድርሰቱን ይዘት (context) በቅጡ ሳይረዱ ደራሲው ልክ ስለጌታ እውቀት እንደሌለው አድርጎ ተሳልቆ ውስጥ መግባት ነውር ነው!!ደግሞስ እንኳን እመቤታችን ስንትና ስንት ኢ/ዊ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ፋሲካ እየተባሉ ይጠሩ የለ!!መቼም አዳኝ እያልናቸው አይደለም!!ይገባናል-ደስታ እያልናቸው ነው!!ከዛማ ይልቅ እናንተ ልጆቻችሁንና ጣቢያችሁን ኤልሻዳይ-ሁሉን ቻይ እያላችሁ ትሰይሙ የለ!!

  3. የአዳም ፋሲካሁ ደራሲንና ንጉሥ ዘርዓያዕቆብን ምን አገናኛቸው…???
  የ“ተፈስሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ” ደራሲ 21 መጻህፍትን የደረሱት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ናቸው፡፡የኖሩትም ከ1357 እስከ 1417 ነው፡፡ዘርዓያዕቆብ የነገሠው ከ1426 እስከ 1460 ዓ.ም ነው፡፡ድርሰቱ እንዴትም ከዘርዓያዕቆብ ጋር አይገናኝም፡፡ብቻ ዘርዓያዕቆብን በመጥራት እምነቱ ከላይ የተጫነ ለማስመሰል ትማስናላችሁ፡፡ከንቱ ድካም፡፡ይሄ ድርሰት ከዘርዓያዕቆብ ጋር የሚያያዝበት ምክንያት የለውም እንጅ ቢያያዝ እንኳ አንዳች ህጸጽ የለበትም፡፡እናንተ ግን ወንጌሉን ለመተርጎም በጉባኤው አላለፋችሁምና መልካመልክ እየቆነጸሉ ቲፎዞ ማስጨብጨቡን ግፉበት!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. e/r ybarkh.ezih yegehaneb dej lay honeh ewnetegnawn menged bemamelaket tga e/r keante gar yhun.dngl tqumlh!

   Delete
  2. እግዝያብሄር ይባርክህ፡፡በርታ እዚህ የገሃነብ ደጅ ላይ ቆመህ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሲደናበሩ የሚመጡትን እውነተኛውን እና የቀደመቺውን መንገድ በማመላከት በርታ፡፡ደለገለ ትቁምልህ

   Delete
 22. 1ኛ ጢሞ. 2፡14 የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤
  15 ነገር ግን በእምነትና በፍቅር በቅድስናም ራሳቸውን እየገዙ ቢኖሩ በመውለድ ትድናለች።
  ይህንን ለተመለከተ በውለድ ብቻ ሄዋን የምትድን መሆኑን የሚነግረን ይመስላል፡፡ ነገር ግን ማስተዋል ላለው ጌታችን መድሃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኖ በዚህ አለም ተመላልሶ ስለሰው ልጅ መከራን ተቀብሎ ተሰቅሎ ሞቶ ተነስቶ አርጎዋል፡፡ ይህ የነሳው ስጋ እንካችሁ ስጋዬን ደሜን ያለው ከማንም የነሳው ሳይሆን ከእመቤታችን የነሳውን ነው በዚህም ነው የአዳም ፋሲካ እያሉ የሚጠሩዋት የሄዋንም መድሃኒት ያሉዋት፡፡ ሄዋን በበላችው እጸበለስ አለም ተረገመ እመቤታችን ባፈራችልን ባስገኘችልን ጌታ ደግሞ ወደ ዘላለም ህይወት ተመለስን፡፡ ስለዚህ በመብል ጠፋን በመብል ተመለስን መጀመሪያ የተበላው ከእጽ የተገኘ ሲሆን የሁዋለኛው ግን ከእመቤታችን የተገኘ ነው፡፡ ስለዚህ ምኑ ላይ ነው ክፋቱ ነገሮችን በቀና እንያቸው፡፡
  ማቴ. 10፡40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።
  ይህ አባባል ደቀመዛሙርቱን ጌታንና የባህርይ አባቱን አንድ አድርጎ የሚያይ ይመስላል ግን በማስተዋል ላየው አቀባበሉ ይለያያል እነሱ ደቀመዛሙርት ናቸው ጌታ የባህርይ አምላክ ነው አብ ደግሞ የባህርይ አባቱ ነው ይህ የሚታወቀው በማብራራት ነው እንጂ ቀጥታ ቃሉ ስለተባለ አይደለም፡፡ እግዚአብሔርኮ እሱ አምላክ ሲሆን ሙሴን አምላክ አድርጌሃለው ያለ ነው፡፡ ዘጸ. 7፡1፤ እግዚአብሔርም ሙሴን አለው። እይ፥ እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌሃለሁ፤ ወንድምህም አሮን ነቢይ ይሆንልሃል። ታዲያ የናንተ በእመቤታችን ላይ ለምን ቅጥል ድብን ትላላችሁ በናንተ ያለ ክፉ መንፈስ ነው ይህም ከቀድሞ የተነገረ ነው በሁዋላም ተነግሮዋል፡፡ ዘፍ. 3፡15፤ በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትቀጠቅጣለህ። መጀመሪያ ጠላትነትን ባንተና በሴቲቱ አለ ቀጥሎ እነዴት እንደሚቀጠቀጥ ተነገረው ስለዚህ ጌታን አንስቶ እመቤታችንን ወይም እመቤታችንን አንስቶ ጌታን የታወቀ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Kale hiwot yasemalene!

   Delete
  2. በርግጥ እመበታቺን ምስጋና አንደምገባት ስለራሱዋ ትንቢት በተናገረቺበት በ ሉቃስ ፩:፬፭ ላይ "ከዛሬ ጀምሮ ትዉልድ ሁሉ ብፅእት ይልኛል"በማለት ተናግራለች;ብፅእት ማለትም ምስጉን ማለት ነው.በ መዝሙረ ዳዊት ፰፮ :፭ ላይም "ሰው ሁሉ እናታቺን ፅዮን ይላል :በዉስቷም ሰው ተወለደ :እርሱ ራሱም ልዑል መሰረታት"ይላል.ስለዚህም እናታቺን እያልን አናመሰግናታለን;ይሄ ማለት ግን አምላካችን ክርስቶስን ከምናመሰግንበት ቃል ጋር አንድ መሆን የለበትም;እናም ፋስካቺን ክርስቶስ ነው.እንዴት ስለመቤታቺን ሊነገር እንደቻለ የተሻለ እዉቀት ያላቺሁ ብታብራሩልን ጥሩ ነው
   yihen yetsafikut ene neberku.Hiruy Egziabher rejim edimena tena yistilign.Melsun aba selamawoch yaltekesutin እስመ ግዕዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሳኤሁ hono agignichewalehu.Hiruy Nurilin!!!

   Delete
 23. Mr Author,

  While you have fallen, you try to make others fall from grace.

  Eve Adam's wife brought condemnation, curse and death to the human race by disobeying God and embracing Satan in her life.

  On the other hand, the New Eve, St. Mary Mother of Christ, obeyed God and renounced Satan, and was chosen by God to be the Mother of Christ Jesus. She continued to obey God throughout Her life and followed Her Son Jesus and suffered with Him upto His Cross. Imagine a very loving mother seeing her child being crucified on a cross the way Christ suffered? This is great suffering for Her!

  Again, this obedience, unlike the original Eve, caused God to choose St Mary to be the bearer of the life giving God. Because of St. Mary's obedience to God, again unlike the original Eve, and Her Son's death on the cross, we all are saved. Aain, the original Eve brough us death, condemnation and eviction from the Praradise through Satan while the Second Eve brought us life and eternal joy through Christ Jesus. Because of that, St. Mary has a very unquie position in out heart and church. Yes, she is our Fasika, joy and pleasure. Mother Mary does not need to be directly crucified like Her Son in order to ba called our "Fasika" as Her Son's crucifixion is Her crucifixion. Afterall, it was the flesh He gained from Mary and unified with His Divinity that got crucified. Only divine can not be crucified.

  If you have read the Bible well, it calls the the Apostels and other saints as "Saviors" because they preached the true God that provides eternal salvation. If those carrying the message or gospel of God can be called "Saviors", what great name shall we call the Mother of Christ Jesus!
  ReplyDelete
 24. ድኅነተ በላኤ ሰብእ በተአምረ ማርያም
  https://www.youtube.com/watch?v=OT76YkWb-IA

  ReplyDelete
 25. Why you did not publish my comment? Was my comment against the evil spiritual propaganda being promoted?

  ReplyDelete
 26. እስኪ አሁን ይህን ዐይን ያወጣ ውሸት ሰው እውነት ነው ብሎ ይከራከርለታል? በጣም ያሳዝናል፡፡ እንዴት አድርገን ለመተርጎም ብንሞክር ማርያም ፋሲካ የምትባልበት ምን ዕድል ይኖር ይሆን? ኧረ እባካችሁ አንዳንዴም እንሸነፍ እንጂ ድርቅ አንበል፡፡ ፋሲካ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ ፋሲካ የለም፡፡

  ReplyDelete
 27. ENNANTE YETEREGEMACHEWU MENEFIKAN- TEHADISO PROTESTANT HOY ENDET NEWU YEMINFIKINNA FIREACHEWU; MERARAWU YENUFAKE TIMIHIRT ENDET TAFETACHEWU? LENEGERU YETERABECH NEFSI NERARAWUN NEGER TIMEGEBALECH AYDELE YEMILEWU,
  REHABTEGNECHI, LE KERSACHEW YETEGEZACHIW MENAFIKAN.
  SITBAZINU HILETE MITSUHAT ENDAYIDERSIBACHEWU LIBBI BELU
  YETEHADISO FUND/BIRRU YALKAL, YENUFAKE DEMOZ ZELALEMEWI MOT GIN EZZAW WEDE TILKU BERBAROS NEWU
  ENNA TEMELESU

  ReplyDelete
 28. MENAFIK- TEHADISO MENAFIK MIN FASIKA ALEWU?
  MINIS TINSAE?
  YEMOT LIJ, MUTICHA

  ReplyDelete
 29. በእንዳንተና በእንደኔ አይነት ጭራቅ ድምጽ ሳይሆን

  ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ስህተት ለባህርዩ በማይስማማው በእግዚአበሔር ተመረጠች! ምን ይዋጥህ !? ምርጫውን አትሰርዘው ፣ኮሮጆውን አትገለብጠው ነገር ምርጫው የልዑል እግዚአብሔር ነው ። በቃ- ተኝተህ ተኩስ።
  ኦርቶዶክሳዊያን በናታችሁ ነገረ ሃይማኖት በሚገባው ሰው ደረጃ ከፍ አድርጋችሁ አትመልሱለት። ከመጽሐፍ ቅዱስ አትጥቀሱለት። በደረ ጃው አነጋግሩት። ልክ እንደዚህ!
  'የአባ ሰላማው' አመሰግንሃለሁ ። ዋ! አመለከኝ እንዳትለኝ።

  ፖስት ባታደርጉት ስቄም አላባራ!

  መንቲሮ ነኝ

  ReplyDelete
 30. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ከልጇ ከወዳጇ ከእየሱስ ክርስቶስ መለየት አትችሉም።እሷ ወደዚህ አለም የመጣችው የመዳኛችን ምልክተረ፣ማህደረ መለኮት፣የአዲስ ኪዳን አማላጅ፣ለመሆን ነው እንጅ አመጣጧ እንደማንኛውም ሰው አይደለም።ስለዚህ አንድ ልጇን ለአለም መድሀኒት እንዲሆን ተስማምታ የማዳኑን ተግባር ከእርሷ ተገኝቶ እንዲፈፅም መልአኩ ገብርኤል ሲያበስራት "ይኩነኒ"ብላ አንድ ልጇን ለአለሙ ማዳን ሰጥታለች።ስለዚህ እመቤታችን ሰማእት ዘእንበለ ደም ናት ቤዛዊት አለም ምክንያተ ድህነት ትባላለች።እናንተ ደግሞ እየሱስን በወለደች ጊዜ ያሳደዳት ያልደረሰባት የቀደመው ዘንዶ የግብር ልጆች እኛን ቀሪ ልጆቸሠን የምታሳድዱ መናፍቀሰን ናችሁ።

  ReplyDelete
 31. ለኔ ፋሲካዬ ክርስቶስ ና ክርስቶስ ብቻ ነው። አቻ የሌለው እሱ ነው። ተወዳዳሪ የሌለው። ተገዳዳሪ የሌለው። እሱ ብቻ ነው።

  ReplyDelete
 32. PART-1 «ፋሲካችን ማነው? ክርስቶስ ወይስ ማርያም» የሚለውን ጥያቄ በማንሣት በበዓለ ሃምሳ ቅድመ ጸሎተ ኪዳን የሚደርሰውን «ለአዳም ፋሲካሁ፤ የአዳም ፋሲካ» የሚለውን የምስጋና ክፍል ኢ-መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድርሰት ነው በማለት ካህናቱ ምሥጢሩን ሳይረዱ፣ ምን ያህል ስህተት እንደሆነ ሳይገነዘቡ በልማድ በዜማ ስለሚሉት የዚህ ድርሰት ችግር ሳይታያቸው ያለምንም ቅሬታና መሳቀቅ አፋቸውን ሞልተው ያዜሙታል እያሉ የድንቁርናቸውን ጣሪያ ያሳዩናል። ምን ገዷቸው። «ልጅ ለናቷ…» አይደል የተባለው።
  ካህናቱ የዚህ ኃይለ ቃል ምሥጢር ካልገባቸው እነሱን ከሰማይ መልአክ ወርዶ አስተምሯቸው ነው? ወይስ እነርሱ ራሳቸው ከሰማይ ወርደው ይሆን? ይህ ሥርዓት የሚከናወነው በአንድ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ብቻ ቢሆን ጥያቄያቸው ለውይይት በቀረበ ነበር። ነገር ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ባለችበትና ካህናቶቿና ምእመናኖቿ ባሉበት የሚከናወን ልዩ ሥርዓተ ጸሎት ነው። አስተውሉ! «ካህናቱ» የሚለው ቃል ከላይ እስከታች ያሉ አገልጋዮችን የሚወክል ቃል ነው። እንዳው በኔ ሞት አላዋቂ ማነው? መልሱን ለአንባቢ።

  ፋሲካ ማለት ምን ማለት ነው?

  1· እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ ብሎት ነበር። «ትበልዕዎ በጒጒዓ እስመ ፋሲካሁ ለእግዚአብሔር = የእግዚአብሔር ፋሲካ ነውና በፍጥነት ትመገቡታላችሁ» ዘጸ 12፥11፤ የእግዚአብሔር ፋሲካ የተባለው እስራኤል በቤታቸው የሠዉት በግዓ ፋሲካ ነው።
  ዕዝራም «በሙሴ መጽሐፍ እንደተጻፈው በኢየሩሳሌም ባለው በእግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ካህናቱን በየማዕርጋቸው ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው አቆሙ ምርኮኞቹም በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን ፋሲካውን አደረጉ ካህናቱና ሌዋውያኑም አንድ ሆነው ነጽተው ነበር። ሁሉም ንጹሐን ነበሩ ለምርኮኞቹም ሁሉ፣ ለወንድሞቻቸውም ለካህናቱ፣ ለራሳቸውም ፋሲካውን አረዱ» ብሏል። ዕዝራ 6፥18-20፤
  ስለዚህ በዚህ ክፍለ ንባብ መሠረት ፋሲካ ማለት አንደኛ፦ በዓልን የሚያመለክት ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ለበዓሉ የሚቀርበውን መሥዋዕት ያመለክታል።
  2· ደስታ ማለት ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ «ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐፂባ በደመ ክርስቶስ = ምድር በክርስቶስ ደም ታጥባ ፋሲካን ታደርጋለች» ብሎ ዘምሯልና። የዚህ ክፍለ ንባብ ምንጭ «ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትሐሠይ ምድር = ሰማይ ደስ ይለዋል ምድርም ደስ ይላታል» የሚል ነው። ሥረወ ቃሉም የሚገኘው በኢሳይያስ 44፥23 ላይ ነው። ስለዚህ ፋሲካ ማለት ደስታ ማለት ነው።
  3· ማዕዶት ወይም መሻገሪያ ማለት ነው። «ፋሲካ ብሂል ማዕዶት ብሂል በዘቦቱ ዓዶነ እሞት ውስተ ሕይወት = ፋሲካ ማለት ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገርንበት ማዕዶት ማለት ነው» ብሎ እንደዘመረ ቅዱስ ያሬድ።
  4· ቀዳማዊ ሕግ ማለት ነው። «ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ = ይህች ፋሲካ የሕግ መጀመሪያ ናት» እንዲል።
  5· የትንሣኤው መታሰቢያ ነው። «ፋሲካ ፋሲካ ፋሲካ ተዝካረ ትንሣኤሁ ለመድኃኒነ = ፋሲካ የመድኃኒታችን የትንሣኤው መታሰቢያ ናት» እንዲል።
  6· ትንሣኤ ማለት ነው። «ትንሣኤ ሰመያ ለበዓለ ፋሲካ = የፋሲካ በዓልን ትንሣኤ ብሎ ሠየማት» እንዲል። ትንሣኤም ሁለት አይነት ነው። ትንሣኤ ልቡናና ትንሣኤ ዘጉባኤ።
  በውኑ መንፈሳዊ እረፍትና ደስታ ለማግኘታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደእኛ ለመምጣቱ ምክንያት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አይደለችምን? ፀረ ማርያም አቋም ያላቸውና ነዳያነ አእምሮ የሆኑ ይህ አይዋጥላቸውም ይሆናል። ለነገሩ ምን ገዷቸው።
  ከላይ ፋሲካ ማለት ቀዳማዊ ሕግ ማለት ነው ማለታችን ይታወሳል። የመጀመሪያውን ቃለ ብሥራት በመስማት እመቤታችን ዓለሙ በኃዘን እንዳይጠፋ «ይኩነኒ = ይደረግልኝ» በማለት ቀዳማዊት አይደለችምን። ከሷ ተወልዶ ዓለሙን ከወደቀበት መርገም እንደሚያድነው ሲነግራት እራሷን አሳልፋ አልሰጠችምን? ከዚህ በላይ ፋሲካ መሆንና መባል ከወዴት አለ? ልጇን እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስን ራሱን ለመስቀል አሳልፎ በመስጠቱ ፋሲካችን ስንለው እሷንም ለእግዚብሔር ፈቃድና ዓላማ ለእኛም የዘለዓለም ሕይወት ምክንያተ ድኅነት ለመሆን ራሷን አሳልፋ ስለሰጠች የአዳም ፋሲካ እንላታለን።

  ReplyDelete
 33. PArt-2
  ሌላው ይህን ክፍለ ጸሎት ለመንቀፍ የተዘጋጁ ሰዎች የራሳቸው የሆነ ችግር አለባቸው። የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፦
  1፣ ይህ ጸሎት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚጸለው በቃል ነው። በቃል ለማጥናት ደግሞ ትጋትና ማስታወስ አስፈላጊ ነው። እነዚህ ሰዎች ሙሉ ጊዜያቸውን የሚያውሉት ለከንቱ ወሬና ለከርሣቸው የሚሆን ፍርፋሪ ለመፈለግ ስለሆነ አይሆንላቸውም። ከሊቃውንቱ ጋር አብረው ቆመው መጽሐፍ ዘርገተው ቢታዩ ደግሞ ውርደት ይመስላቸዋል። እነዕገሌ ሁሉ በቃላቸው ነው ምነው እናንተስ ከሚለው ጥያቄ መሸሽ ይፈልጋሉ። ከማን አንሼ አይነት ነገር ይመስላል።
  2፣ የአገልግሎት ፍቅርና መንፈስ ጨርሶ የላቸውም። እንቅልፋሞችም ናቸው። ተርእዮ ይወዳሉ። ሰው በሚበዛበት ጊዜና መድረክ እንጂ መገኘት የሚፈልጉት በተመስጦ ሆኖ ወደ እግዚአብሔር በሚቀርብ አገልግሎት መገኘት አይወዱም። ማን ሊያያቸው። ቀድማችሁ ገብታችሁ አገልግሉ እንዳይባሉ አገልግሎቱን ማጥላላት ምርጫቸው ሆነ።
  3፣ እኩይ ዓላማቸውን ለማሳካት አይመቻቸውም። ለምሳሌ «ተፈሥሒ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ ወማዕዶታ ለሔዋን እንተ ይእቲ ዓፅመ ገቦሁ» የሚለውን ሲጠቅሱ «እስመ ግእዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሣኤሁ = በልጅሽ ትንሣኤ ነፃነታቸው ተደርጓልና» የሚለውን መጥቀስ አይፈልጉም። በትርጓሜያችን መጽሐፍ ጭብጡን አይለቅም ለሸፋጭ ለለዋጭ አይመችም የሚል ሐተታ አለ። ለሸፍጣቸው ስለማይመቻቸው ለማጥፋት የቻሉትን ያህል ይደክማሉ።
  ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «ፋሲካ» የተባለው በለበሰው ሥጋ ነው። ይህም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ «ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየአትት ኃጢአተ ዓለም = የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ» በማለት የተናገረውን የሚተረጉም ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስን «በግ» እያሉ ሲገልጹት እሱ ራሱ በርሱ ያመኑ ምእመናን «በጎች» በማለት ይጠራቸዋል። ይህ ማለት የምእመናን «አባግዕ» መባልና መሆን የክርስቶስን ስፍራ ይይዛል ወይም ይተካል ማለት አይደለም። ለዚህ ነው ሊቁ «ለአዳም ፋሲካሁ» ካለ በኋላ «እስመ ግእዛኖሙ ኮነ ለወልድኪ በትንሣኤሁ = በልጅሽ ትንሣኤ ነፃነታቸው ተደርጓልና» በማለት ማስረጃ ያስቀመጠው።
  ቅዱስ ኤፍሬምም በቀዳሚት ውዳሴው «ትትፌሣሕ ገነት እመ በግዕ ነባቢ ወልደ አብ ዘይነብር ለዓለም = ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖር የአብ ልጅ የተናጋሪው በግ እናት ገነት/እመቤታችን ደስ ትሰኛለች» ብሏል። እናቱ ስትደሰት የማይደሰት ልጅ የለምና። «ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ» ብሎ የገባለትን ቃል የፈጸመለት ከእመቤታችን ሰው በመሆን ነውና። እባብ የሞቱ ምክንያት እንደሆነ ሁሉ እመቤታችንም የድኅነቱና የፋሲካው ምክንያት ናትና።
  ሊቃውንት በየድርሳናቸው «ትምክሕተ ኵልነ፣ አንቲ በአማን ምክሐ ዘመድነ፣ ትክምሕተ ዘመድነ በወሊዶተ ዚአከ = የሁላችን መመኪያ፣ አንቲ የባሕርያቺን መመኪያ ነሽ፣ አንተን በመውለዷ የባሕርያችን መመኪያ ናት» እያሉ የገለጿት የአዳም ፋሲካ/ደስታ በመሆኗ ነው። እግዚአብሔር ከሰማይ ወደምድር በተመለከተ ጊዜ እሱን የሚፈልግ ጠቢብ ሰው አለማግኘቱን ቅዱሳት መጻሕፍት ይመሰክራሉ። መዝ 13፥2፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ለአዳም የገባው ቃል ኪዳን የሚፈጸምበት ዘመን ሲደርስ መልአኩን ልኮታል። «ወበሳድስ ወርኅ ተፈነወ ገብርኤል መልአክ እምኀበ እግዚአብሔር = በስድስተኛው ወር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ» እንዳለ ወንጌለ ሉቃስ። ሲያበሥራትም «ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ጸጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ = ደስ የተሰኘሽ ጸጋን የተመላሽ ሆይ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ» በማለት ነው። ስለዚህም ድንግል ማርያም የአዳም ፋሲካ/ደስታ ናት።
  ቅዱስ መጽሐፍ ሔዋንን «የሕያዋን ሁሉ እናት» (ዘፍ 3፥20) ብሎ ሲጠራት እመ ሕይወት ድንግል ማርያምን ፋሲካ ብንላት አላዋቂነት ነውን?

  ReplyDelete