Friday, April 4, 2014

በኦክላንድ ሊካሄድ የነበረው እርቅ ሳይሳካ ቀረ። ለአባቶች መለያየት ዋና ምክንያት የኦክላንድ ቦርዶች መሆናቸው ተረጋግጧል።     Read in PDF
በሎስ አንጀለሱ የጥምቀት በዓል የተጀመረው የጳጳሳቱና እና የካህናቱ እርቅ ወደ ኦክላንድ መድኃኔ ዓለምና ኢየሱስ ሄዶ እንዲቀጥል በሽማግሌዎች ጥረት ተደርጓል። የዳላሱ ዲያቆንና የቅድስት ማርያሙ መነኩሴ ተንኮል በጥምቀት በዓል ላይ ሳይሠራ በመቅረቱ እግዚአብሔርን ያመሰገኑት አባቶች ወደ አቡነ መልከ ጼዴቅ ኦክላንድ ድረስ በመሄድ እርቁን ለማጽናት ሞክረው ነበር። ከጠቡ ምክንያቶች አንዱ የሆነው የኦክላንድ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን እንደነበረ ይታወሳል።
በኦክላንድ የተፈጠረው ችግር በመጠኑ ሲታይ እንደሚከተለው እነደሆነ ምንጮች ይጠቁማሉ። የደብሩ መተዳደሪያ ሕግ በየሁለት አመቱ ኮሚቴው ይለወጣል የሚል ሲሆን በተግባር ግን ታይቶ አይታወቅም። ቤተ ክርስቲያኑ ሲጀመር ጀምሮ የተሾመው ሊቀ መንበር አስካሁን ያው አንድ ሰው ነው። እርሱም አቶ ብንያም ይባላል። ለ20 ዓመት ያህል ሊቀመንበር ነው። በኢህአዴግ ልክ መሆኑ ነው። ጓደኞቹ አቶ አስራትና ወይዘሮ ደብሪቱም የቦርድ አባል ሆነው ከተሾሙ ልክ እንደ ብንያም 20 ዓመታቸው ነው። የቦርዱ ጸሐፊ ወይዘሮ ፍቅሬም ወደ እዚያው ትጠጋለች።
የደብሩ አባላት እነዚህ ሰዎች ከሥልጣን እንዲወርዱ በሕጉ መሠረት ምርጫ እንዲደረግ ቢመክሩም ሳይሳካ ቀርቷል። በብዙ ትግል ምርጫ ቢደረግም ለነዚህ ሰዎች እረዳት የሚሆን እንጂ ከላይ የተጠቀሱትን ሰዎች የሚነካ የለም። ከላይ የተጠቀሱት አይነኬ ሰዎች ኢህአዴግ ይውረድ እያሉ ሰላማዊ ሰልፍ የሚወጡ እንደነበረ ታዛቢዎች ይናገራሉ። እነርሱ ግን በጣታቸው እንኳ ሊነኩት አይፈልጉም። አሁንም አስመራጭ ኮሚቴ ተመርጧል እንዴት እንደሚሆን የምናየው ይሆናል ይላል ምንጫችን።

    በውጭ የሚገኙ የኢህአዴግ ተቃዋሚዎች ወይም እራሳቸው ኢሕአዴጎች እንደምንም ታግለው የቦርድ ሥጣን ከያዙ እሺ ብለው በጊዜያቸው አይወርዱም ወይም የራሳቸውን አመለካከት የሚያራምድ ሰው በማጭበርበር ይተካሉ። ባገር ውስጥ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ኢሕአዴግና ማህበረ ቅዱሳን ብቻ የሚወዳደሩባት ሲሆን በውጭ ባለችው ቤተ ክርስቲያን ግን አብዛኛውን ጊዜ ኢሕዴግና ኢህአፓ የሚታገሉባት ናት። የቤተ ክርስቲያን የሰላም እጦት ምክንያትም ይህ ነው።
በርካታ ካህናት እንደጠቆሙን ቦርድ እየተባለ የሚጠራውን የቤተ ክርስቲያን ኮሚቴ "ደርግ” እያልን ነው የምንጠራው ይላሉ። ከትንሿ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሥልጣን አንወርድም ያሉ ትልቁ አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ቢገቡ እዚያው በስብሰው አገር ያበሰብሳሉ ሲሉ አስቀውናል። በአሜሪካ የሚገኙ ከጳጳስ እስከ ካህን ሰባኪዎችም ጭምር የሚተነፍሱት በነዚህ ሰዎች ሳንባ ነው። ወደው ሳይሆን ሁኔታው ስለማይፈቅድላቸው ተረግጠው ይኖራሉ። አንዳንዶችማ ቅዳሴ አስረዘማችሁ እያሉ ማስጠንቀቂያ የሚሰጡ፣ አትስረቅ እያላችሁ እየሰበካችሁ ፓርኪንግ የሚሰራውን ሰው አስቀራችሁብን፣ ስለዚህ ገቢ ስለቀነሰ ደሞዝ አንጨምርም እያሉ የሚያሸማቅቁ ናቸው።
በቅዳሴ ሰዓት ቢሮአቸውን ዘግተው ካርታ የሚጫወቱ፣ ወይም ተኝተው አርፍደው ሁሉም ካለቀ በኋላ መጥተው ማስታወቂያ አለን ስብከቱን አሳጥሩ የሚሉ ደፋሮች ናቸው ይባላል። እንግዲህ የኦክላንድ ሕዝብ ከመድኃኔ ዓለም ወጥቶ የኢየሱስን ቤተ ክርስቲያን ያቋቋመበት አንዱ ምክንያት ከሥልጣን አንወርድም የሚሉና ምንም መንፈሳዊ ሕይወት ባልታየባቸው ሰዎች ምክንያት ነው ተብሏል።
  ሁለተኛው ምክንያት ግን የአቶ ብንያምና የአባ ቃለ ጽድቅ አለመግባባት ነው። አቶ ብንያም በአባ ቃለ ጽድቅ ክሬዲት ከስድስት መቶ ሺህ ዶላር በላይ የሚያወጣ ቤት ለአቡነ መልከ ጼዴቅ ገዝቷል። አባ ቃለ ጽድቅ እኔ ሳላውቅ የማይሆን ነገር አስፈርሞኛል ክሬዴቴም ተበላሽቶ የራሴን እድገት ጎትቷልና ስሜ ይውጣና በሌላ ሰው ይዛወርልኝ የሚል ጥያቄ አንስተው፤ ቤቱን ለመግዛት ያበደረው ባንክ ይህን ጥያቄ ሳይመልስ ቀርቷል በዚህ ምክንያት አለመግባባቱ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ አባ ቃለጽድቅ ጥለው የወጡ ሲሆን ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ ነው ተብሏል።
  ከዚህ በተጨማሪ የኦክላንድ ቦርድ ተራራ ላይ ለምንም የማጠቅም መሬት በአራት መቶ ሽህ ብር የገዛ ሲሆን ቤቱም ሆነ መሬቱ ሲገዙ ሕዝቡም አቡነ መልከ ጼዴቅም አያውቁም ነበር ተብሏል። ኦዲተርና ቁጥጥር ኮሚቴ ከሁለቱ ግዢዎች ማለት ከቤቱና ከመሬቱ ከሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ ዶራል በላይ ቤተ ክርስቲያኑ ተበልቷል ሲል አጋልጧል። ሁሉም ቦርዶች ባለ ሃብቶችና የተለያዩ ድርጅቶችን ክፍተው የሚነግዱ መሆናቸውን ከስፋራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ሀብቱን ከራሳቸው ያፈሩት ይሁን ከቤተ ክርስቲያኑ ያገኙት ግን እርግጠኛ ሆኖ መናገር የቻለ የለም። ከቦርድ ሥልጣን አንወርድም የሚሉበት ምክንያት ምን ይሆን? የሚለው ግን የብዙዎች ጥያቄ ነው።
   አቶ ብንያምና ወይዘሮ ደብሪቱ ግን ቤተ ክርስቲያኑ ሲገዛ ቤታችንን ስለአስያዝን ንብረታችንን አምነን ለማን እናስረክባለን የቤተ ክርስቲያኑ እዳ ተከፍሎ እስኪያልቅ ድረስ እንቀጥላለን የሚል አቋም እንዳላቸው ይነገራል። ይህን ምክንያት አንቀበልም የሚለው ሕዝብ ችግሩን ለማጣራት ብዙ ጥረት አድርጓል ከሦስት አራት ጊዜ በላይ ሽማግሌ ገብቶበታል ምንም መፍትሔ አልተገኘም ነበር። ይህ በእንዲህ እያለ ቦርዱ ሦስት የሰንበት ተማሪዎችን እየላከ ጣልቃ በማስገባት እጅግ በጣም ይዋደዱ የነበሩትን አቡነ መልከጸዴቅና አባ ቃለ ጽድቅን እንዲጣሉ አደረገ።
አባ ቃለ ጽድቅ አቡነ መለከ ጼዴቅን ከቤቴ አስወጣለሁ እርሳቸውን አባርሬ ደብሩን እቆጣጠራለሁ እያሉ ነው የሚለው ወሬ በተደጋጋሚ ይላክላቸው ነበር። በመጨረሻ ጠቅላላ ስብሰባ ተደርጎ የሕዝብ ሽማግሌዎች ሪፖርት ለማቅረብ ተዘጋጅተው እያለ አሁንም ቦርዱ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ተሸፋፍኖ ቀረ። አባ ቃለ ጽድቅ ገብተው ችግሩን ይናገሩ ቢባልም ቦርዱ ከለከለ። ከዚህ በኋላ ነገሩ ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ቦርዱ የበላይነቱን እየያዘ መጥቶ አባ ቃለ ጽድቅንና ተከትሏቸው የሄደውን ሕዝብ አስወገዘ፣ ሦስት መቶ ሃምሳ ሺህ ዶላር ጠፍቷል ያሉ የቁጥጥር ኮሚቴዎችም ተወገዙ። ተጨማሪ የነበሩ ቦርዶችም በራሳቸው ፈቃድ ሥልጣን ለቀቁ።
   ሕዝቡ ወጥቶ የኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን ሲያቋቁም አባ ወልደ ትንሣኤ አባ ገብረ ሥላሴ በኋላ ብጹእ አቡነ ዮሴፍ እና ብጹእ አቡነ ያዕቆብ ቀሲስ መላኩ አባ ወልደ ኢየሱስ አባ ሃብተ ማርያም አባ ላእከ ማርያም መርጌታ ነቢዩ ቀሲስ እንዳልሃቸው ሄደው ሕዝቡን አጽናኑ። የአቡነ መልከ ጼዴቅና የነዚህ አባቶች ጠብ እየበረታ የመጣው በዚህ ጊዜ ነው። በኦሃዮው ሲኖዶስ ውግዘቱን ያንሱ ተብለው የተጠየቁት ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ ፈቃደኛ መሆናቸውን ነገር ግን ከቦርዳቸው ተለይተው ይህን ማድረግ እንደማይችሉ ተናግረዋል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ግን ያልተወያየንበት ውግዘት ስለሆነ አንቀበለውም ብለው ለኦክላንድ ኢየሱስ እውቅና ስጠዋል።
   ችግሩን በእርቅ ለመደምደም ከየአብያተ ክርስቲያናቱ የተውጣጡ የሽማግሌዎች ኮሚቴ፣ ለረጅም ጊዜ ከተወያየ በኋላ በ03/29/14 እርቁ እንዲከናወን ወስኖ ይመለከታቸዋል የተባሉ ልኡካንን  ወደ ኦክላንድ ልኮ ነበር። ከአስታራቂ ሽማግሌዎች ውስጥ ምእመናንን ወክለው የተገኙ ነበሩ። ከካህናት ለማስታረቅ ደፋ ቀና ሲሉ የከረሙት ሁለቱ አባቶች ማለት አባ ወልደ ትንሣኤና አባ ሀብተ ማርያም ነበሩ። እርቁ ሊካሄድ የነበረው ብጹእ አቡነ ዮሴፍና አቡነ ያዕቆብ ከአቡነ መልከ ጼዴቅ ጋር ሲሆን፤ እንዲሁም የመድኃኔ ዓለም እና የኢየሱስ አብያተ ክርስቲያናት ምእመናን እና ምእመናትን የሚጨምር ነበር። የረጀም ጊዜ ውይይትና ከፍተኛ ወጪ የፈጀ ነበር ተብሏል።
   በብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅና ቦርዶቻቸው፣ የኢየሱስ ምእመናን እዚህ ድረስ መጥተው ይቅርታ ይጠይቁን የሚል አቋም ይዘው የነበረ ሲሆን። ኢየሱሶች ግን የተበድልን እኛ ሆነን እያለ እኛው ሄደን ይቅርታ የምንጠይቀው ምን በደል ተገኝቶብን ሲሉ ተከራክረዋል። ሁሉም ተገናኝቶ መነጋገር ይሻላል በሚለው ተስማምተው ሁሉንም የሚያገናኝ መካከለኛ ስፍራ ተመርጦ አዳራሽ በክራይ ተይዞ ነበር። በተጨማሪም የኦክላንድ ኢየሱስ ሰበካ ጉባኤ አባላት ብጹእ አቡነ መልከጼዴቅ በቃለ አዋዲያችን እንዲመሩልን መተማመኛ ይፈርሙልን ባስተዳደራችን ገብተው ሰላም እንዳይነሱን እንሰጋለን የሚል ቅድመ ሁኔታ አቅርበው በሽማግሌዎች ውድቅ ስለተደረገ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመታረቅ ተስማምተው በተዘጋጀው አዳራሽ በሰዓቱ ተገኝተዋል።
ብጹእ አቡነ መልከሴዴቅም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ውግዘቱን ሊያነሱ እርቅ ለመፈጸም ተስማምተው የነበረ ሲሆን የመድኃኔ ዓለምን በዓል በሎስ አንጀለስ ኦሬንጅ ካውንቲ ለማክበር ከሄዱበት ባስቸኳይ እንዲመጡ ተደረጎ ነበር። ወደ አዳራሹ ይመጣሉ ተብሎ ሲጠበቅ ወደ ቤተ ክርስቲያናቸው በመሄዳቸው ብጹእ አቡነ ዮሴፍና አቡነ ያዕቆብ አባ ወልደ ትንሳኤ አባ ሀብተ ማርያም የኢየሱስን ሰበካ ጉባኤ አባላትና ከአርባ የማያንሱ ምእመናን አዳራሹ አስቀምጠው ወደ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሄደው ይዘዋቸው ሊመጡ ሲሞክሩ አይነኬዎቹ ቦርዶች እምቢ ብለው አስቀርተዋቸዋል።
 በተለይም የቦርድ አባል ያልሆነችው ወይዘሮ መሠረት ዋና የእርቁ ተከላካይ ሆና ታይታለች። ይህች ሴት ባንድ ወቅት ኦዲተር ሆና በሠራችበት ወቅት ያቶ ብንያም ገመና ሸፋኝ ነበረች ይሏታል። ሳይጠሯት አቤት እያለች ጠቡን የምታቀጣጥልም እርሷ ናት ተብሏል። ባለፈው ዓመት የጥምቀት በዓል ላይ ፓትርያርኩን እና አቡነ መልከ ጼዴቅን ለመለያየት ስትሞክር ታይታለች። ቅዱስ ፓትርያርኩን አቡነ መልከ ጼዴቅን ለምን አያከብሯቸውም ካልፈልጓቸው እኛ እንወስዳቸዋለን ብላ ከድንኳን አስወጥታ ልትወስድ ስትል በፖለቲካዋ የነቁ ሰዎች አክችፈውባታል ተብሏል።
በሰሞኑ እርቅም ሳይጠሯት መጥታ ከቦርዱ ጋር ሆና እርቁን አክሽፋዋለች። ይህች ሴት አባ ወልደ ትንሣኤን ለመሳደብ በሞከረችበት አረፍተ ነገሯ ቀኖና እና ዶግማ ታስተምራለህ ሕዝብ ለማሳሳት ትሞክራለህ ስትል የተጫነችውን ጭነቷን ያለ አግባብ አውርዳዋለች። "ሲሉ ሰምታ ዶሮ ሞተች በጢስ ገብታ የምትባለው ይህች ናት‚። ዶግማና ቀኖና ማስተማር የእውነተኛ አባቶች ምልክት እንጂ ማንም ወንበዴ ሊያደርገው የማይችል መሆኑን ሳትገነዘብ ለመተቸት መሞከሯ ወሬኛ መሆኗን ያመለክታል።  
   ቅዱስ ፓትርያርኩ በተደጋጋሚ የኦክላንድ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያንን መቀበላቸውን በደብዳቤ አረጋግጠዋል በቃልም አስረድተዋል። በቅርቡም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሰል ደብዳቤ ለአቡነ መልከ ጼዴቅ ልከው ነበር። ስልጣናቸው ግን ሊከበር አልቻለም የፓትርያርክነታቸው ክብርና ሥልጣን የት አለ? የኦክላንድ ቦርዶች የፓትርያርኩን ደብዳቤ ከጉዳይ አልጻፉትም። አቡነ መልከ ጼዴቅንም እርጅናቸውን ተጠቅመው እያስፈራሯቸው መወሰን እንዳይችሉ አድርገዋቸዋል። እንዲያውም ጳጳሳቱን ቤተ ክርስቲያንን ለማፍረስ የተነሣችሁ ሕገ ወጥ ናችሁ ዓይነት ስድብ ሊሳደቡ ሞክረዋል። ከዚህ በፊት ከኦክላንድ ሰንበት ተማሪዎች አንዱ በስልክ ብጹእ አቡነ ዮሴፍን ለባለጌ እንኳ የማይገባ የስድብ ቃል አውጥቶ መሳደቡ የሚታወስ ሲሆን ማን እንደሆነም ታውቋል።
  በዚህ የቦርዶች ድርጊት ያዘኑት ጳጳሳቱ  እባካችሁ እኒህን አባት በሽምግልናቸው ተከብረው ይሙቱ ነጻ አድርጓቸው ሲሉ ቦርዱን ተማጽነዋል። አቡነ መልከ ጼዴቅ የፓትርያርኩ ተጠሪ እንጂ ፓትርያርክ አይደሉም እኛ የመጣነው የርሳቸው ውግዘት ይሠራል ብለን አምነን ሳይሆን የፓትርያርኩን ሥልጣን እንድታከብሩ ለመጠየቅና እርቅ ፈጽማችሁ በሰላም እንድትኖሩ ልንረዳችሁ ነው በማለት አስረድተዋል። ብጹእ አቡነ መልከ ጼዴቅ እርቁን ለመፈጸም ከፍተኛ ፍላጎት ያሳዩ ሲሆን አይነኬዎችን ፍርተው ምንም ማድረግ እንዳልቻሉ ውግዘቱን እንኳ ለማንሳት ሲሞክሩ እንዳልፈቀዱላቸውና ተመልሰው የቦርዶችን አቋም እንደያዙ ታውቋል። አባቶችም ችግሩ ያለው ከቦርዱ ላይ መሆኑን ተገንዘበው ለአቡነ መልከ ጼዴቅ ጸሎት አድርገውላቸው ተመልሰዋል።
  ዘግይቶ በደረሰን ዜና ይህን ድርጊት የሰሙ መላው ጳጳሳትና ካህናት በኦክላንድ ሊደረግ የነበረው የመጭው ግንቦት የሲኖዶስ ስብሰባ ቦርዶቹ የፓትርያርኩን ሥልጣን ባለመቀበላቸው እንዲሰረዝና በዚያው መንበረ ፓትርያርኩ ባለበት በዲሲ እንዲሆን የወሰኑ መሆናቸው ታውቋል  የፓትርያርኩ ትእዛዝ ካልተከበረ በሲኖዶስ መሰብሰቡ ትርጉም የለውም በሚለው ተስማማተዋል። አንዳዶች በመጭው የግንቦት ሲኖዶስ የኦክላንድ ቦርዶች ከሥልጣን እንዲወርዱና ሂሳቡ በአግባቡ እንዲመረመር እንዲጠየቁ፤ የመድኃኔ ዓለም አባላትም ለቤተ ክርስቲያን ሥልጣን እንዲገዙ ጥሪ እንዲቀርባላቸው ሲሉ አሳስበዋል።    

25 comments:

 1. tehadeso selame new

  ReplyDelete
 2. በመጀመሪያ ለአቡኑ፥ እኛ ምእዕመናን አባትነዎትን በማክበር፣ ዳኝነቱን ለፈጣሪ ትተንና በጽኑው የኢትዮጵያዊ ይሉኝታ ተሸንፈን ሁሉንም ግፍ ለዘመናት መቻላችንን ሕሊናዎ ምስክር ይሆናል ብለን እናምናለን። ነገር ግን ለሁሉም ልክ አለው፤ ሥፍሩ ሲሞላ ይፈሳልና እኛማ «ካህኑ የሁላችንም ራስና የክርስቶስ ወኪል ነው» ነው የምንለው። አሁንም እንወደዎታለን፣ እናከብረዎታለን።
  ለቦርድ አባላቱ፦ ብንያም , ደብሪቱ , አሥራትና ፍቅሬ እንደውነቱ ከሆነ፣ ምን ጊዜም የቦርዱ ዋናው ስጋት መመርመር፣ መከሰስና፣ ከሥልጣን መውረድ እንጂ የመድኀኒዓለም መዘጋት አይደለም፣ አልነበረምም። ምክንያቱም የሠሩትንና አሁንም የሚሠሩትን ወንጀል ያውቁታልና በሕግ መነጸር ከታዩ በኌላ የሚከተለው ነገር ምን እንደሚመስል በሕልማቸው እየመጣ እንቅልፍ አሳጥቷቸዋል። ግን ወደዱም ጠሉም ይዘገይ እንደሆነ ነው እንጂ ይኸ አይቀርላቸውም። እኛ የመድኀኒዓለም ምዕመናን በዚህ ጥኑ እምነት አለን። የምንተማመነውም በራሳችን መሆን አለበት። ከአሁን በኌላ ሰጎኗ እንዳደረገችው ራሳችንን አሸዋ ውስጥ ቀብረን ለምንም ያህል ጊዜ ብንጠብቅ የቤተክርስትያናችን ችግር በዝምታ አይፈታም።
  ምን ጊዜም በፈጣሪያችን ተስፋ የማንቆርጥ፣
  እምነታችንን የየዋህነት ሰለባ ላለማድረግ ቆርጠን የተነሣን
  የኦክላንድ መድኀኒዓለም ካቴዴራል ምዕመናን ፤

  ReplyDelete
  Replies
  1. Eske ahun leseten tigist Egziabher yimesgen, esu gin be semu lemiatefu kesash amlakim negwina, ye firdu gize ahun negw.

   Delete
  2. I am Yemedhanealem Member but I do not share your view of what is going on at our church. We are at peace and believe that Abatachin deserves the credit for our church to get where we are. He has served the Orthodox Haymanot for over 70 years and has the wisdom to direct us in the right direction. I understand many have a problem with the amount of years the board has served but I know for a fact every time they wanted to get off the board they were asked by Abatachin and other elders of the church to stay on. When looking and asking members to become board members many say they cannot serve and has always been a problem finding willing members to serve on the board.
   Please leave us alone, we are fine and will be fine without your crazyness. You decided to leave us, if you want to come back we will gladly accept you back. But don't try and create problems that does not exist in our Church. You should have been at the Medhanealem Beal what a blessed event it was. Medhanealem Abatachinin and Lesu Yemiagelegelutin Yitebik. Egziabher lehulum wagawin Yemikefil Amlak newina!

   Delete
  3. Yemedhanealem member that is ok with what has been said in this article must be in denial or must be part of the problem, Really; you are saying you want to be left alone; the truth hurts so, deal with it.

   Delete
  4. I understand you do not share my view when it comes to the Abune and that he deserves the credit for directing the Ethiopian orthodox religion. what the Abune did was flying from state to state and expanding his own personal support or Zufan, that is all I saw him do, tell me what has said or done for the poor, the homeless, the sick and the lost in his own city. Have you seen him raising fund for the less fortunate,have you seen him gathering our lost youth walking the street confused and helpless, has he ever used the podium to talk about the poor people of Ethiopia??? No, No he does not have time for the wretched, because he is too busy talking about his high almighty position in Atse Haileselasie, how he was the his advisor, Your abune always aligned himself with the haves not the have not. Let us think, when Jesus was on earth, how did he live his life? did he not fed the hungry and clothed the naked, healed the sick, where was he? tell me why do you want to give him credit, for flying around the world with the hard earned money from members. As a leader of the western region did he lead by forgiving what ever it takes, to bring his people together? no one church is better than the other, God is in the heart of the believer not at any particular church. let us lead our clergy to stop living in comfort and luxury but live like the almighty!!

   Delete
  5. Amen!! This is truth what the Abune did around the nation creating problems in the holy church between the priests and members. Please pray for him for this short term of his life. Let God forgive him what he did in all his life.

   Delete
 3. Eyesus yelelebet yebetkerstian agelgelote always without peace.

  ReplyDelete
 4. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 5. This should have been written a long time ago as this has been "ye adebabay Mistir" for a while. Now it is known and written about, what are Ye Medeanalem members going to do about it........eske meche negw enablers yemihonew hizbu?

  ReplyDelete
 6. በዚህስ የማህበረ ቅዱሳን እጅ የለበትም? እርሱን ሳታነሱ ስትቀሩ ምነው ምን ነካቸው ብየ ነዋ።

  ReplyDelete
 7. Please members of Medhanialm church keep this cathedral from those so called board members specially Asrat yegezu and Meseret Yilma who is playing with Abatachen and speak up and make a change to save this church.

  ReplyDelete
  Replies
  1. You are absolutely right. Naming the known board members that is creating caios is very critical.

   Delete
  2. So very true!

   Delete
 8. what is the meaning of love and forgiveness, what is the purpose of religion leaders? as leaders of our orthodox religion why don't use your leadership role by practicing what you preach. Please be the first to extend your arms and embrace all without reservation. To give excuse such as board members have to agree with the matter of forgiveness is weak and very worldly.

  ReplyDelete
  Replies
  1. I agree wholeheartedly. There is no spirituality shown in any of the named people's lives; just self serving comfort and deceit. Egziabher gin yiferdal.

   Delete
 9. Wey gud! Abet Kilet.

  ReplyDelete
 10. Asrat and Binyam should go. It looks like these guys have finanncial advantage to their bussness. How in the hell one could admnister for 20 years as the board memeber. It is unbelivable. Sorry for Abune Melktseded, he is surrounded by mafia group.

  ReplyDelete
  Replies
  1. why are you sorry for Abune Melktsdek for surrounding himself with people who will take care of him, keeping him in the utmost comfort. The Abune likes his comfort, the so called Menokse likes to mingle with people he could easily manupilate. If this Menokse wasfor real, he would not even leave his poor country, he would have stayed back home and suffered with his people, he would have died for his people, teach and work for his country.

   Delete
 11. I have been a member of Ethiopian Orthodox church for over 20 years, I have pledged and paid mortgage to help purchase 2 churches and a residence for Abune in my city. what surprises me, why our priests and Abunes, all religion leaders do not use the church to fund raise for the poor and sick and helpless in our community, how about using the church space to bring in our homless Ethio. teens who are wondering the street, lost and depressed, how about opening the church door 7 days a week so our seniors could come in to pray or get counseling. I am just wondering why do we pay the church mortgage and the salary of priests but get very minimum service one day a week, perhaps the occasional christening, marriage,and death ceremony is not adequate. What I am trying to say is kristina btegbar yhun, kesoch kristina betgbar mhone endalebet masayet yehun kedemiaw serachu yehun, what I see you doing is not what Jesus Christ did on while living on this earth. Mekedes becha ayebekam!!! Remember we are into 21st century, you can not use the 11th century doctrine to teach and influence.It will not work especially the young generation.

  ReplyDelete
 12. Debere Selam Eyesus church founded by some of us who are visionaries, we worked hard to establish a church in a very short  Debre Selam Eysus of Oakland is founded by people who are visionaries, a church where all members are treated fairly and equally, a church where its main objective to be helping the needy and those who are less fortunate in our community, a church where its laws and regulations will be discussed in a melate jubae (general meeting) before it is constituted into laws. But no that is not what happened, we got fooled by the priest who made up all the rules and regulations and claimed this is how Ethiopian orthodox church is run back home, and that is how we are going to run our church. This priest also gave himself the power to run the church in the business aspect and the religion aspects of its activities. In addition he became the one to approve and disapprove all matters including elected officials. When approached and asked that the church bylaws are heavy handed, and unbalanced that it does not allow the members to have a voice, he responded sarcastically by saying this is a church and not a corporation. What the priest did not realize was that the church is owned by its members and the members participate in designing the bylaws as they see it fit, and vote on every law and the law that has the most vote will become the law of the church until they choose to change it again. These are just some of the problems we are facing with the so called educated priest (monk??) who has dug his own hole and was dismissed by church members. Good riddance!!!! Amen. Mind you, although this priest is removed from the church, unfortunately, the bylaws he designed to allow him as he pleased is still the law of the church. A lot of church members are not concerned about the bylaws, but a few of us are visionaries, we can smell stink from afar!!!


  ReplyDelete
 13. Sorry to hear this kinds of comment from one of the so called member. First for most the Kale Awadi what ever you called bylaws not like you describe please read it and understand what it means please do not poison the orthodox believer of Iyesus. Yes a few members are disagree that's true try to discuss peacefully and make improve democratically.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Kale Awadi has a set of rules and regulations how a church is is built and run, and one of the fundumental law is that a single church must go through the stat,or woreda or hagere sebiket and get the blessing of the Abune or papas, any church does not make its own law of going directly to the Patriarch, so my dear member the priest put that article to suit his will. And so the church bylaw is not kale Awadi, We can call it Kale Menokese!!

   Delete
 14. ምድረ ተሃድሶ ተባሉ

  ReplyDelete