Wednesday, April 9, 2014

በዉኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ዉስጥ ያለዉ ችግር እንደሚባለዉ የአስተዳደርና የሙስና ችግር ብቻ ወይስ ሌላ?በዲያቆን የሻነው
ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳዉሎስ የቤተክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ካረፉ ወዲህ እና በተለይ ከእርሳቸዉ በኋላ የተሾሙት ፓትርያርክ ብጹእ አቡነ ማትያስ ከተቀመጡ ወዲህ በቤተክርስቲያኒቱ እጅግ የተበላሸ የአስተዳደርና የሙስና ችግር እንዳለ በሰፊዉ ከመወራቱ ባሻገር ለዚሁ መፍትሄ ይሆናል የተባለ የመዋቅር ማሻሻያ በሰፊዉ እንደሚደረግ ተነግሮ ነበር፡፡ እነዚህ ከላይ የተገለጹት ችግሮች በተለይ ተንሰራፍተው የሚገኙት በአዲስ አበባ አገረ ስብከት ነዉ በሚል ቅድሚያ ተሰጥቶት የቅዱስ ሲኖዶስና የፓትርያርኩን ይሁንታ አግኝቶአል በሚል የአሰራር ሂደት ለዉጡን ወደ ስራ ለማስገባት በአዲስ አበባ አህጉረ ስብከት ስር የሚገኙ የሚመለከታቸዉ ናቸዉ የተባሉ አካላት ዉይይት ተጀምሮ ነበር፡፡ በተቃራኒዉ ይህንኑ የማሻሻያ ስርአት ይቃወማሉ የተባሉ ቡድኖች ቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር በአሰራር ማሻሻያዉ ላይ ያላቸዉን ቅሬታ ይዘዉ በመግባታቸዉ ጉዳዩ እንዲቆም ተደርጎ ለመላዉ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር በሚመች መልኩ ስራ ላይ ማዋል እንዲቻል የአሰራር ሂደት ለዉጡ  በቤተክርስቲያኒቱ መዋቅር ስር ባሉ አካሎች እንዲገመገምና እንዲሻሻል ከቀድሞ ኮሚቴ እጅ የሰነድ ርክክብ ተካሂዶአል፡፡
            በቤተክርስቲያኒቱ አለ የተባለዉ የአስተዳደርና የሙስና ችግር በተነገረና የአሰራር ማሻሻያዉ ጥናት ይካሄድ ተብሎ በቅዱስ ሲኖዶስ ከተወሰነ ከጥቂት ግዜያት በኋላ ተጠንቶ የተቀመጠ 1500 ገጽ የሚሆን የአሰራር ማሻሻያ ሰነድ በአንዴ ብቅ ብሎ  አዲስ አበባ አህጉረ ብስከት ላይ ስራ ላይ ሊዉል ነዉ ተብሎ ሲነገር እንኳን የአዲስ አበባ አድባራት የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮችን አይደለም በመላዉ ኢትዮጵያ የሚገኙ የቤተክርስቲያኒቱ ልጆችን ሳያስደነግጥ የቀረ ጉዳይ አይመስለኝም፡፡ ከባድ ነዉ የተባለዉ የቤተክርስቲያች ችግር ሰፊና ጥልቀት ያለዉ ዳሰሳ ሳይደረግበት በአንዴ የችግሩ መፍትሄዉ የሆነዉ የአሰራር ሂደት ማሻሻያ መገኘቱ ሲሆን በተጨማሪም  የዚህ ማሻሻያ ግብረ ሐይል ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ወርቁ ነዉ ሲባል ደግሞ ባለ ረጅም እጁ ነኝ ባዩ እና የቤተክርስቲያኒቱን መዋቅር ከወትሮዉም ጊዜ በላይ መቆጣጠር የሚፈልገዉ ማህበረ ቅዱሳን እጁ ያለበት መሆኑን ግልጽ ያደርገዋል፡፡ ታዴ በጨው የታጠበ ማቅ በመሆኑ እና በዚህም ምክንያት ጤነኛ ማሻሻያ ሊቀርብ ስለማይችል ተቃውሞው በርትቷል፡፡ ለውይይት የቀረበው ማሻሻያም ከዚህ የተሻለ ነገር አልተገኘበትም፡፡

ክብርትና ገናና የሆነችዉ ቤተክርስቲያናችን ለዘመናት ሰዎችን ሳታጣ በአምላኳ ከብራ ከቆየች በኋላ በተለይ ባለፉት 20 ዓመታት መጣሁልሽ እያለ እያስፈራራት በሰይጣናዊ ሀሳቡ ሊያጠምቃት በመፍጨርጨሩ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብታለች፡፡ ለመሆኑ / ችግር ዉስጥ የገባችዉ  የአሰራር ሂደት ለዉጥ አጥታ ነዉ?  ወይስ  በወንጌል አማካይነት በስነምግባር የታነጸ  ሰዉ (ትዉልድ) አጥታ?  ማህበረ ቅዱሳንስ ከእርሱ በላይ የቤተክርስቲያን ችግር ሆኖ የተፈጠረ ነገር ኖሮ ነዉ ወይ? የቤተክርስቲያኒቱን ችግር መልካም አስተዳደርና ሙስና ብቻ ነዉ  እያለ የሚደሰኩረዉ፡፡
በዉኑ ነገሮችን ዘርዘር አድርገን ስናያቸዉ፡-

በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ትልቅ አደጋ ተፈጥሮአል ብሎ ማቅ ይሁን ሌላ ለቤተክርስቲያኒቱ እቆረቆራለሁ የሚለዉ አካል ከመልካም አስተዳደር እጦትና ከሙስና ጀርባ ያለዉን ችግር ለምን በጥልቀት መመርምሮ መናገር ያቃተዉ፡፡
ቤተክርስቲያኒቱ ከተቋቋመችበት አላማ ጀምረን ስንነሳ (አንድን ምእመን 40 እና 80 ቀን በጥምቀት በልጅነት ከተቀበለች በኋላ በቁርባን አሳድጋ በወንጌል ኮትኩታ የእግዚአብሔር መንግስት ባልደረባ (አገልጋይና ምእመን) ማድረግ እንደሆነ የታወቀ ነዉ፡፡) በዚህ መልክ ያደገ አማኝ ደግሞ ፍሬዎቹን ገላትያ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
የዚህ ፍሬ ባለቤት ሆኖ ያደገ አገልጋይም ይሁን ምእመን ለሐገርም ይሁን ለቤተክርስቲያን ምን
እንደሚሰራ የታወቀ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ ከጥቂት አመታት ወዲህ ከዚህ በተቃራኒዉ ሲሰራ ስለተኖረ ሐጢአት አድጎ በስነ ምግባር ብልሹ የሆነ ትዉልድ ተፈጥሮ በሐገርም በቤተክርስቲያንም የምናየዉን ችግር ወልዶአል፡፡ ስለ ኢትዮጵያችን የአሁኑ ትዉልድ የስነ ምግባር ችግርና ሙሰኝነት በተለያየ መንገድ ስለምንሰማዉ፤ አሁን ለምናወሳዉ ጉዳይ ስለማይጠቅመንም መናገሩን አልገፋበትም፡፡ ግን ደግሞ በሐገርም እየታየ ላለዉ የሰዉ መጥፋት ችግር እኮ ቤተክርስቲያናችንም አንዷ ተጠያቂ ነች፡፡ ለምን?  ቢባል  የሚጠበቅባትን ስራ በተለይ እላይ በጠቀስኳቸዉ አመታት ዉስጥ ወደ ጎን በመተዋ፡፡ አባታችን ዳዊት ልጁን ሰሎሞንን ወደ ህዝብ ማስተዳደር ስራዉ
ከመግባቱ በፊት ሲመክረዉ ብዙ ሐተታ አላበዛበትም ያለዉ ሰዉ ሁን ነዉ፡፡ (መጽሐፈ ነገስት ቀዳማዊ 2 ቁጥር 3)  ምክንያቱም በዘመኑ የጠፋዉን አዳም በዳግም ትንሳኤ (አማናዊቱን የሰዉነቱን መቅደስ ምሳሌ) የሆችዉን መቅደሱን ለመስራት አምላክ የሚፈልገዉ ሰዉን ስለሆነ፡፡ በምድር የሚኖረዉ ሰዉ ሁሉ አምላክ የሚፈልገዉን የሰዉነት ባህርይ የማያሟላ በመሆኑ፡፡ በዚህ ምክንያትም ሰሎሞን የአባቱን ምክር በመስማቱ  አምላክ ለሶሎሞን ያደረገለትን (መጽሐፈ ነገስት አንደኛ 3 ቁጥር 15) አንብቦ መረዳት ይቻላል፡፡ ታዲያ ይሄንን እዉነት እንዲሁም አዳምን (ህዝብን) ወደ ቀደመ ክብሩ የመለሰዉ ኢየሱስ ክርስቶስ (ሁለተኛዉ አዳም) በመጣበትና የሰይጣንን ክፉ ምክር አሽንፎ ህይወት ባወጀበት
ዘመን፤ ያዉም የዚህ እዉነት ምስክርና ግንባር ቀደም የሆነች አገርና ቤተክርስቲያን በዚህ ችግር መዉደቃቸዉ እጅግ አድርጎ ሰዉን ብቻ ሳይሆን አምላክንም ያሳዘነ ተግባር ነዉ፡፡ ለምን ብንል በሐገርም በቤ/ክም  የሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር ባለቤት የሆነዉ ጠላት ዲያብሎስ በሰዉ ልብ ነግሶ በመታየቱ፡፡
ስለዚህ መጀመሪያ እልባት ሊያገኝ የሚገባዉ የተበላሸዉን የአገልጋይና የምእመን ህይወት የመስራት ጉዳይ ማስቀደምና  በዚሁ ላይ አቅዶ  መስራት ሲሆን የቀረዉን ከዚህ ቀጥሎ ወይም ጎን ለጎን መስራት ይቻላል፡፡ የሰዉ ስብእና ደግሞ የሚሰራዉ በእግዚአብሔር ቃል ወይም በወንጌል ነዉ፡፡ ይህ ባልተሰራበት ቦታ የሂሳብ ስርአቱ ደብል ኢንትሪ ስለሆነ ሙስና ይቆማል ማለት ዘበት ነዉ፡፡ የአስተዳደር መዋቅሩን በማሻሻል  የአስተዳደር ስርአቱ አድልዎ የሌለዉ ይሆናል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነዉ፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሁለቱ ማሻሻያዎች ተተግብሮባቸዉ የምናያቸዉ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ዉስጥ አሁን በሚዲያ እንደምንሰማዉ ብልሹ አሰራሩና ሙስናዉ ቀንሶ አልታየም፡፡ ምክንያቱም
የተሻሻለዉን አሰራር ያልተለወጠ ሰዉ ቢሰራዉ ዉጤቱ ምንድነዉ?  ስለዚህ ቤተክርስቲያኒቱ አሁን የሚታየዉን ችግር ሰለጠንን ብለዉ የሚያወሩ አገሮች የሚልኩልንን አሰራር ብቻ ተግባራዊ ለማድረግ ግዜ ከማባከን ይልቅ ወደ ዋናዉ የቤተክርስቲያኒቱ አላማ ሰዉን በወንጌል የመስራት አብዮት (Revolution)  ብታዉጅ መልካም ነዉ እንላለን፡፡
ይህ ካልሆነ ግን የማህበረ ቅዱሳን ለቤተክርስቲያን አጉል አስባለሁ ባይነትና አሁን የተያዘዉን ዳር የማያደርስ
መንገድ ይዞ መቀጠል ከዚህ በፊት በቤተክርስቲያን ሰፍኖ ያየነዉን ችግር አባብሶ ከመቀጠል ያለፈ የሚያመጣዉ ዉጤት አይኖርም?  ማህበሩ እራሱ የዚህ የስነ ምግባር ብልሹነት ችግር ተጠቂ በመሆኑና እንዲያዉም  የቤተክርስቲያን አባቶችን የራሱን ሃሳብ እንዲያስፈጽሙለት የተለያየ መደለያ በመስጠትና የተበላሸ አሰራር በቤተክርስቲያኒቷ እንዲሰፍን ያደረገ፥ በተጨማሪም የራሱን ጥቅም ብቻ በማሳደድ ሀብት ሲያካብት በነበረበት ወቅት ይህ ድርጊቱ እንዳይጋለጥ ንጹህ የቤተክርስቲያን አባቶችን በማሸማቀቅ ንጹህ የቤተክርስቲያን ልጆችንና አገልጋዮችን በማሳደድ ከከረመ በኋላ አሁን ክፉ ግብሩ ሲጋለጥ ከገባበት ወጥመድ ሾልኮ ለመዉጣት እንዲያመቸዉ ለቤተክርስቲያን አሳቢ በመምሰል ብቅ ማለቱ የተኩላነት ባህርይዉን ከማሳየት ዉጪ  ሌላ ነገር ሊባልለት አይችልም፡፡  
ማቅ ራሱ ጠንካራና ታማኝ  ከሆነ መጀመሪያ በገዳማት፥ በአብነት /ቤት ስም እንዲሁም ከአባላቱ በሰበስበዉ ገንዘብ የገነባዉ ፎቅ ባለቤቱ ማን እንደሆነ በግልጽ መጀመሪያ ለምን ለቤ/ አያሳዉቅም?  በማህበሩ እጅ ያለዉን ሐብትና ገንዘብ አስመርምር ሲባል እንቢ ማለቱስ ከምን የመጣ ነዉ?  
በተጨማሪም የማህበሩ የተለያዩ የንግድ ተቋማትን በአመራሮቹ ስም እየቀየረ የሚገኘዉ ከእኩይ ተግባሮቹ መገለጫዉ ከብዙ በጥቂቱ ሆኖ ሳለ ለመሆኑ  እርሱ ማን ሆኖ ነዉ ስለ ቤ/ ችግር የሚናገረዉ፡፡ ለነገሩማ ለማህበሩ ከህግና ከስርአት ዉጪ መሆንና በቤ/ ዉስጥ አሁን ለሚነሳዉ ችግር ትልቅ ድርሻ የሚወስዱ፤ ከጌታ ምእመኑን ለመጠበቅ አደራ ተሰጥቶአቸዉ ሃላፊነታቸዉን  ያልተወጡ  አባቶችም የሉም ማለትም አይደሉም፡፡   አሉ፣ ማህበሩ ራሱን እንዲያስተካክል አስተያየት ሲሰጥ ለችግሩ እልባት ከመስጠት  ይልቅ  የአይኔ ብሌን  ተነካ በማለት  የቤተክርስቲያኒቱን ችግር አባብሰዉ እዚህ ያደረሱ ጥቂቶች አይደሉም፡፡
ለመኪናቸዉ ጎማ የተቀየረላቸዉ፥ ከማህበሩ አበል የተከፈላቸዉ፥ በቦሌ ለገነቡት ቤት የባለሞያና የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸዉና የቆሙለትን አላማ የዘነጉ አባቶችም ጥቂት አይደሉም፡፡ አሁንም ችግሮችን ለማስተካከል ሊወሰድ ለታሰበዉ እርምጃ እንቅፋት እንደሆኑም ቀጥለዋል፡፡ ማስተዋልን እንዲሰጣቸዉ አምላክን እንለምናለን፡፡
አሁን  የቤተክርስቲያንን (የምእመኑን) ችግር በወንጌል በኩል በጥሞናና የቤተክርስቲያኒቱን (የሐገሪቱን) የቀደመ  ክብር በማሰብ ስርነቀል ለዉጥ ለማምጣት አባቶችና ማስተዋልን የሰጣቸዉ አገልጋዮችና ምእመናን የያዙትን ስራ መቀጠል አለባቸዉ በማለት አደራ እንላለን፡፡
 ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!!

23 comments:

 1. beka selemaheberu kemawerat lela yemetawekut nege yelem aydel? hametegnoech.

  ReplyDelete
 2. ወንድሜ ዲያቆን የሻነው የኢኦተቤክ አስተዳደራዊ ችግር ወንጌልን ካለመስበክ ይመነጫል ባልከው አልስማማም፡፡ስለ 6 ምክንያቶች!!
  1. ወንጌል በተለይ በከተማው በየዕለቱ በሳምንት ለ7 ቀናት በየአጥቢያው በማታ ፕሮግራምና በቅዳሴ ላይ ስለሚሰበክ አባባሉ እውነታን ይደፈጥጣል፣
  2. በተመሳሳይ መልኩ ወንጌልና አዋልድ መጻህፍቶቻችንን ይዘን ከዚህም የባሱ የሰማዕትነት ዘመናትን መሻገራችንን ታሪክ ስለሚመሰክር ክርክሩ በታሪክ አይንም የከሰመ ነው፣
  3. እንደኛ ተመሳሳይ ስርዓት ያላቸውና እኛ የምንቀበላቸውን መጻህፍት የሚቀበሉ ሌሎች የኦሪየንታል አብያተክርስቲያናት ገድላትንና ድርሳናትን ከወንጌል አዋህደው ማስተማራቸው ያመጣባቸው የአስተዳደር ችግር ስለሌለ፣ይልቁንስ ባለ ብዙ አዋልዷ ካቶሊክ 1.1 ቢሊዮን ምዕመን በአንድ መንበር ስር አድርጋ ከሀገር በላይ የገነነ የአስተዳደር ስርዐት መዘርጋቷ ያንተን ጽሁፍ ያፈርሰዋል፣
  4. ወንጌል መስበክ ከእኛ በላይ ላሳር የሚሉ በፕሮቴስታንት ስር ያሉ የባህር ማዶም ሆነ የሀገራችን ቸርቾች ይህ ነው የሚባል የተደራጀ ማእከላዊ የአስተዳደር መዋቅር የሌላቸው መሆኑ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የአስተዳደር ነገር ያልሰመረላት ወንጌል ስለማትሰብክ ነው የሚለውን መላ ምት ውድቅ ያደርገዋል፡፡ሆኖም ፕሮቴስታንት ይበዛበታል በሚባለው ደቡባዊ የሀገራችን ክፍል በመልካም አስተዳደርም ሆነ ወንጀል በመቀነስ ረገድ ኦርቶዶክሳውያን ይበዙበታል ከሚባለው ክልል ትግራይ የተሻለ ሆኖ ስለመገኘቱ ማስረጃ ካቀረብክ አስተያየትህን እናጤነዋለን፡፡ መረጃህ አዲስአበባን ማእከል ያደረገ ከሆነም ከሰሜን ኢ/ያ የሚመጡትንና በተለምዶ ቆምጨ የምንላቸው ሎተሪ አዟሪ ኦርቶዶክሳውያን ከደቡብ ኢ/ያ ከሚመጡት በአብዛኛው የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሊስትሮዎች የትኞቹ በውንብድና ወንጀል ላይ እንደተሰማሩ ለማወቅ ከማረሚያ ቤቶቻችን ማጣራት የተሻለ ይሆናል፡፡
  5. የምግባር ህጸጽ በሃይማኖትና በትምህርት ይታረማል ለማለት እንዳልችል ብዙ ተሞክሮዎቼ ይከለክሉኛል፡፡የተሻለ ክፍያ ስላገኘ የፈረመውን ውል የካደ የፕሮቴስታንት ዘማሪ አይቻለሁ፣ቤት ሸጦ ክፍያ ከተቀበለ በኋላ የካደ ፕሮቴስታንት አጋጥሞኛል፣ቃል የገባላትን እጮኛውን የካደ ፕሮቴስታንት ጓደኛም አለኝ፡፡ተመሳሳይ ድርጊቶችን የፈጸሙ ኦርቶዶክሳዊና ሙስሊም ሰዎችን አውቃለሁ፡፡ስለዚህ ሀገራዊ የስነምግባር ውድቀቶችን ኦርቶዶክስ ላይ ለመከመር ስትንደረደር ተመለስ፣በህግ እለሀለሁ፡፡ያለማስረጃ ዝምብሎ መደምደም አይቻልም፡፡በሐሜት ደረጃ ከሆነ ግን ኦርቶዶክሳውያን በመጠጥ የሚታሙትን ያህል ፕሮቴስታንቶች ደግሞ በፍቅረ ነዋይ እና በበላተኝነት(አብዝቶ በመመገብ) ብዙ ሲታሙ እሰማለሁ፡፡
  6. ኦርቶዶክሳውያን በየቤተእምነታቸውና በየደጃቸው በፈጣሪያቸውና በቅዱሳን ስም ለነዳያን የሚያደርጉትን ገደብ የሌለው ምጽዋት ምንጩ ብራብ አብልታችሁኛል የሚለው አምላካዊ ቃልና ነቢይን በነቢይ ስም ወይም ጻድቅን በጻድቅ ስም ለመቀበል በቅዱሳን ስም የሚደረጉ ዝክሮች መሆናቸውን መርሳት የለብንም፡፡ስለሆነም የኦርቶዶክስ ወንጌልን አለመስበክ አስተዳደሩዋን እንዳይሻሻል አደረገው፣የሀገር ምግባር አጎደለ የሚለው ክስ ሊበሉዋት ያሰቡዋትን ከማስተረት ውጭ ሀቅ የለውም፡፡
  በማኅበረቅዱሳን ዙሪያ ቅሬታ ቢኖረኝም እናንተ ከምትሉት ጋር ስለማይገናኝ ትቸዋለሁ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ህሩይ ወይስ ጠዋይ?

   Delete
  2. ሕይወት የጌታ ባሪያApril 9, 2014 at 11:02 PM

   ወንድሜ ህሩይ!! አንተ የመደበኛ ት/ቤት የታሪክ ወይም ስነዜጋ አስተማሪ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ምክንያቱም መልሶችህ ሁሉ በተቀመጠ ካርኩለም ዉስጥ የሚሽከረከሩ ናቸዉ፡፡ ታሪክና ባህልን የሚያጣቅሱ፡፡ እኛ ደግሞ የምንጠይቀዉ የመንፈስ ምግብ ስለሆነዉ ነፃ የሆነ ወንጌል ነዉ፡፡ እናንተ ኢህአዴግን ትቃወሙና አሰራሩን ደግሞ ያለ ምንም ይሉኝታ ትኮርጃላችሁ፡፡ እንደ እርሱ ዓይን ያወጣ ጥፋት ሲነገርህ ዓይኔን ግምባር ያድርገዉ፣ አላወቀዉም ትላለህ። ወይም ጭዳ በግ ትፈልጋለህ፣ እስቲ ህሩይ ልጠየቅህ የትኛዋ ቤተክርስትያን ናት አንድን ሰባኪ ያልተደቃቀለ ወንጌል ሰብኮ በሰላም የምታሳድር? ገላትያ ወይም ሮሜን እየሰበከ ስለተክለሃይማኖት ስለ አቡዬ አልተናገርክም ተብሎ ስንቱ ሰባኪ አልተፈናቀለም ነዉ የምትለዉ? ይህንን ገሃድ እዉነት እያወቅህ እንደ ኢህአዴግ መብራት አንዳንድ ቦታ ብቻ ነዉ የጠፋዉ፣ጠላቶች ሲያጋነኑ ነዉ እያልክ ነዉ፣ ከሁሉ የሚያቅለሸልሸዉ ደግሞ ተራ የሆነ የግለሰቦችን ወንጀል ከሃይማኖቶች ጋር ለማነጻጸር መሞከርህ ነዉ፣ ባይገባህ ነዉ እንጂ ለእነዚህ ለምትላቸዉ ሁሉ ልትጸልይ ይገባ ነበር፡፡ይህኔ ወይ ንሰሐ ገብተዉበታል ወይም ነገ ጨካኝና ከሳሽ ያልሆነዉ ጌታ እግር ላይ ወድቀዉ ይሰረዝላቸዋል፡፡ ለማንኛዉም ዘመኑ 21ኛ ክዘ ነዉ። እያታለሉ መዝለቅ የለም! አዲሱ ትዉልድ የሚመራበት መንፈሳዊ ሐቅ ይፈልጋል። እርስ በርሱ የሚጣረስ የማያሳምን ትምህርት ክርስትና ነዉ ብትለዉ ክርስቶስን ፍለጋ ወደሚገባዉ መንገድ ይሄዳል እንጂ ቆሞ አይጠብቅህም። ለዚሀም ነዉ አሃዱ አብ ተብሎ ከሚቀደስበት ቤት እየፈለሰ ጥሎህ እየሄደ ያለዉ። እስቲ የሃይማኖትች ስብጥር የያዘ ስታቴስቲከስ ተመልከት! የየትኛዉ ቤተእምነት ነዉ እያሻቀበ ያለዉ?አንተና መሰሎችህ ግን ይህችን ቤተክርስቲያን ብትፈርስ ደንታም ያላችሁ አተመስሉም፡፡ ይህንን የማያዋጣ ምሁርመሁር የሚመሰለ ክርክርህንና ጃርገኖችን አቁምና ትዉልዱን ታደግ! የነተክልዬ ተቅማጥ አያድንም። የእምቤታችን «ተአምር» እንደ ሥጋ ወደሙ አይቆጠርም፣ ዉሸታችንን ነዉ ብለህ ድፈር!!! እግዚአብሔር ይርዳህ።

   Delete
  3. Beaman Hiruy.

   Delete
  4. Kemesadeb masireja yalew mels mestet wey yehagere sew mogn yashenifal min bilio bilu embi bilo

   Delete
 3. ende enanate ayinetum tehadiso ale !! Ye Mahibere Kidusan fetena ke Egziher yemimeta leteshale yemiyabeka new. Fetenawum yemimetaw kenemewuchaw new !! Bizum atizlelu behuala tafiralachihu !!!

  ReplyDelete
 4. Lante lerasih libona yistih ante lemhonu meche bewengel amneh new wengel altesebekem yemitilew ? Wengel washu tilalech m?antegin tiwashale ruq anhidina ezihu qiraqinbo tshufih lay tadesse assefa yemilewin tadesse werqu bilehal lemin bibal libh yawiqewal yiliqunu ante rasih qenu saymeshibih nisha giba

  ReplyDelete
 5. Wow endet yale d/n new dedeb

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሕይወት የጌታ ባሪያApril 9, 2014 at 11:02 PM

   ወንድሜ ህሩይ!! አንተ የመደበኛ ት/ቤት የታሪክ ወይም ስነዜጋ አስተማሪ ሳትሆን አትቀርም፡፡ ምክንያቱም መልሶችህ ሁሉ በተቀመጠ ካርኩለም ዉስጥ የሚሽከረከሩ ናቸዉ፡፡ ታሪክና ባህልን የሚያጣቅሱ፡፡ እኛ ደግሞ የምንጠይቀዉ የመንፈስ ምግብ ስለሆነዉ ነፃ የሆነ ወንጌል ነዉ፡፡ እናንተ ኢህአዴግን ትቃወሙና አሰራሩን ደግሞ ያለ ምንም ይሉኝታ ትኮርጃላችሁ፡፡ እንደ እርሱ ዓይን ያወጣ ጥፋት ሲነገርህ ዓይኔን ግምባር ያድርገዉ፣ አላወቀዉም ትላለህ። ወይም ጭዳ በግ ትፈልጋለህ፣ እስቲ ህሩይ ልጠየቅህ የትኛዋ ቤተክርስትያን ናት አንድን ሰባኪ ያልተደቃቀለ ወንጌል ሰብኮ በሰላም የምታሳድር? ገላትያ ወይም ሮሜን እየሰበከ ስለተክለሃይማኖት ስለ አቡዬ አልተናገርክም ተብሎ ስንቱ ሰባኪ አልተፈናቀለም ነዉ የምትለዉ? ይህንን ገሃድ እዉነት እያወቅህ እንደ ኢህአዴግ መብራት አንዳንድ ቦታ ብቻ ነዉ የጠፋዉ፣ጠላቶች ሲያጋነኑ ነዉ እያልክ ነዉ፣ ከሁሉ የሚያቅለሸልሸዉ ደግሞ ተራ የሆነ የግለሰቦችን ወንጀል ከሃይማኖቶች ጋር ለማነጻጸር መሞከርህ ነዉ፣ ባይገባህ ነዉ እንጂ ለእነዚህ ለምትላቸዉ ሁሉ ልትጸልይ ይገባ ነበር፡፡ይህኔ ወይ ንሰሐ ገብተዉበታል ወይም ነገ ጨካኝና ከሳሽ ያልሆነዉ ጌታ እግር ላይ ወድቀዉ ይሰረዝላቸዋል፡፡ ለማንኛዉም ዘመኑ 21ኛ ክዘ ነዉ። እያታለሉ መዝለቅ የለም! አዲሱ ትዉልድ የሚመራበት መንፈሳዊ ሐቅ ይፈልጋል። እርስ በርሱ የሚጣረስ የማያሳምን ትምህርት ክርስትና ነዉ ብትለዉ ክርስቶስን ፍለጋ ወደሚገባዉ መንገድ ይሄዳል እንጂ ቆሞ አይጠብቅህም። ለዚሀም ነዉ አሃዱ አብ ተብሎ ከሚቀደስበት ቤት እየፈለሰ ጥሎህ እየሄደ ያለዉ። እስቲ የሃይማኖትች ስብጥር የያዘ ስታቴስቲከስ ተመልከት! የየትኛዉ ቤተእምነት ነዉ እያሻቀበ ያለዉ?አንተና መሰሎችህ ግን ይህችን ቤተክርስቲያን ብትፈርስ ደንታም ያላችሁ አተመስሉም፡፡ ይህንን የማያዋጣ ምሁርመሁር የሚመሰለ ክርክርህንና ጃርገኖችን አቁምና ትዉልዱን ታደግ! የነተክልዬ ተቅማጥ አያድንም። የእምቤታችን «ተአምር» እንደ ሥጋ ወደሙ አይቆጠርም፣ ዉሸታችንን ነዉ ብለህ ድፈር!!! እግዚአብሔር ይርዳህ።

   Delete
 6. WOW BANTE YIHUN

  ReplyDelete
 7. Ersihin Diacon eyalk yemitera menafik tehadiso protestant chinblihin awlik.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማሩ ከበደ የኤሉሚናቲ አባል መሆንህን አርማህ በሆነችዉ ዓይን ተረድቻለሁ፡፡ ስለዚህም እየተሳደበ ያለዉ በዓይኑ ዉስጥ የሚታየዉ አዉሬዉ ስለሆነ በእሱስ ስም ለቆህ ይዉጣ!!!!

   Delete
 8. ya it is true. wongel nesa yawetal. chegerese wengel new EOTC.

  ReplyDelete
 9. Dear writer,
  Are you sure that the chairman is ታደሰ ወርቁ?
  If you want to be good writer in the future make your source reliable and correct.
  Besides try to accumulate knowledge in the area of your subject before you write.
  Regarding your argumentative approach I fill comfortable. At least you have tried to be out of blind hatred.
  Lastly I have one question what do you mean by 'WONGEL', and who should preach this 'WONGEL'? Do you think those that we see now everywhere have moral to preach 'WONGEL'?

  ReplyDelete 10. ተሃድሶዎች የጴንጠየ ተላላኪ…ቤተክርስቲየሰንን ለማዳከም የተለያየ ዘዴ ብትጠቀሙም አሁንም በራሳችሁ አንደበት ስለ ማንነታቸሁ አስረዳችሁን እኮ….. የማመሰግነው ብኖር እስከ ዛሬ ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ የሆነውን ማኅበረ ቅዱሳንን ሳለውቅ የቆየው ሲሆን እናንተ ለማስጠላት በሰራቸሁት ስራ እንዳውቅ አድርጋችሁኛል…. እኛ ቤተክርስቲያንን ፀንተን እንጠብቃለን//////

  ReplyDelete

 11. እናንተ ዋሾዎች አታርፉም…..ተነቃባችሁ የት ትደርሱ ሰይጣን እራሱ በቅርቡ ሳያባርራችሁ አይቀርም …

  ReplyDelete
 12. Your anti-EOTC protestant beliver. Your mission to increase contradictionin EOTC!

  ReplyDelete
 13. lemhonu aba selama khnetweym dikon yemil tamnalachu ende endih kohene degumachhu testekaklewal malet new

  ReplyDelete
 14. endene minm waga yelelw neger new

  ReplyDelete
 15. Orthodox Tewahedon ya maserete MK aydelem lazih zemen ba fetena alfa ezih sitederes MK alneberem alebotawu ende Tsehaft ferisawi ba geta kan tegenye. silazih yamitayewun mekdes siyay amanawi mekdesun amlakun resa silazih la abalatu entseley mewakru yifersal yihe tiyake yelewum.

  ReplyDelete
 16. Selam yibzalachu kemastewal gar ene yemilew 3 amet mulu mahbere kidusanin sitiwenejilu orthodox tewahido tadiso yasfelgatal sitilu wendimoch ayidekimachum malete minim bikefelachum komi bilachu
  yih yemiseraw Egiziyabher yasdestehal we bilachu teyiku enji.demomi eko manim yezerawn new yemiyachidew .manim leseraw fird ke Egiziyabher enji kesew liflefa (Aba Selama) adelem hulun esu new yemiyastekakil lewendimochachuh tseliyu.lelaw yemimekrachu neger enate ketemeseretachu 1992 E.C jemiro yimeslegnal ena enatem ende mahbere kidusan enditihonu yehintsa balebet lelam lela neger lemagignet bemastewal, betinikare,endihum keminim belayi betselot Egiziyabher amilakin teyiku tikikilegnawn menged yimerachual. egiziyabher yistilign Amen.

  ReplyDelete