Thursday, May 1, 2014

ለእግዚአብሔር ብቻ እንዘምር

Read in PDF

መዝሙር ለእግዚአብሔር ብቻ ሊቀርብ የሚገባው መሥዋዕት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በብሉይም በሐዲስም መዝሙር የእግዚአብሔር የብቻው ገንዘብ መሆኑን ይመሰክራል፡፡ ከእግዚአብሔር በቀር የሚዘመርለት ሌላ አካል እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ አያስተምርም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በትምህርትም በተግባርም መዝሙር ሲቀርብ የምናየው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ይህም የሆነው መዝሙር የአምልኮ መግለጫ ስለሆነና አምላክም እግዚአብሔር ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ ይህን የአምልኮ መግለጫ መንገድ መዝሙርን ለሌሎች ሰጥተን ብንገኝ፣ እግዚአብሔርን ብቻ ማመስገን ሲገባን ሌሎችንም ብናመሰግንበት ግን  ባዕድ አምላኪዎች እንሰኛለን፡፡
ዛሬ በቤተክርስቲያናችን መዝሙርና ቅኔ ለእግዚአብሔር ብቻ መቅረብ ሲገባው እየቀረበ ያለው ግን ለመላእክት፣ ቅድስት ማርያምን ጨምሮ ላንቀላፉ ቅዱሳን ጭምር ነው፡፡ በሕይወተ ሥጋ ያሉ ጳጳሳትም በተለያዩ ጊዜያት ቅኔና መዝሙር ሲቀርብላቸው እንመለከታለን፡፡ ይህ ግን ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ ነው። ከእግዚአብሔር ውጪ የሚዘምርላቸውና እንዲዘመርላቸው የሚፈልጉ ወይም ሲዘመርላቸው ተዉ የማይሉ ሁሉ ራሳቸውን ወደ ጣዖትነት እየቀየሩ መሆናቸውን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለባቸውም፡፡
በመዝሙረ ዳዊት ውስጥ መዝሙር መቅረብ ያለበት ለእግዚአብሔር ብቻ መሆኑ ለስምንት ጊዜ ያህል ተጽፏል፡፡ በሌሎቹም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ነቢያቱ ኢሳይያስና ኤርምያስ፣ እንዲሁም ሐዋርያው ጳውሎስ ለእግዚአብሔር ብቻ እንድንዘምር አዘዋል፡፡ በቅድሚያ ጥቀሶቹ እነሆ!
·        “በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል አደራረጉን ንገሩ” መዝ. 9፡10
·        “ቅዱሳን ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።” መዝ. 30፡4
·        ለእግዚአብሔር ተቀኙ ለስሙም ዘምሩ ወደ ምድረ በዳ ለወጣም መንገድ አድርጉ ስሙ እግዚአብሔር ነው፥ በፊቱም ደስ ይበላችሁ በፊቱም ይደነግጣሉ። … የምድር ነገሥታት፥ ለእግዚአብሔር ተቀኙ፥ ለጌታም ዘምሩ። በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ የኃይል ቃል የሆነ ቃሉን፥ እነሆ፥ ይሰጣል።” መዝ. 68፡4፡32-33
·        “ምድር ሁሉ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር እልል በሉ አመስግኑ፥ ደስ ይበላችሁ፥ ዘምሩምለእግዚአብሔር በመሰንቆ፥ በመሰንቆና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩ።” መዝ. 98፡4-5
·        ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ” መዝ. 147፡7
·        “ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርስዋም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፥ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፥ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ።” ኢሳ. 42፡10
·        “ለእግዚአብሔር ዘምሩ እግዚአብሔርንም አመስግኑ የችግረኛውን ነፍስ ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና።” ኤር. 20፡13
·        “የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ። በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።” ቆላ. 3፡16
በእነዚህ ጥቅሶች ሁሉ ውስጥ በትእዛዝ አንቀጽ “ዘምሩ” ነው የተባልነው፡፡ የምንዘምረውም ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ በትእዛዝ አንቀጽ ከቀረቡት ውጪም የሚከተሉትን እናገኛለን፡፡
·        “በምድር ያሉ ሁሉ ለአንተ ይሰግዳሉ፥ ለአንተም ይዘምራሉ፥ ለስምህም ይዘምራሉ።” መዝ. 66፡4
·        “በእግዚአብሔርም መንገድ ይዘምራሉ የእግዚአብሔር ክብር ታላቅ ነውና።” መዝ. 138፡5
·        “መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ” ራእ. 5፡9-10፡፡
·        “ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ፥ ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፥ መንገድህ ጻድቅና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ፥ የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፥ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ በፊትህም ይሰግዳሉ እያሉ የእግዚአብሔርን ባሪያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።” ራእ. 15፡3-4
እነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የምንረዳው መዝሙር መቅረብ ያለበት አምላክ ለሆነው ለእግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከእግዚአብሔር በቀር ለመልአክም ሆነ ጻድቅ ለተባለ ሰው ዘምሩ የሚል ትእዛዝ አልተሰጠንም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለእግዚአብሔር ካልሆነ በቀር ለሌሎች ፍጡራን መዝሙር ያቀረቡ የእግዚአብሔር ሰዎችንም አናገኝም፡፡ ታዲያ ከየት አምጥተን ነው ለማርያም ለመላእክትና ለጻድቃን ሰማዕታት የምንዘምረው? ለዚህ ልምምድ አብነት የሆነንስ ከቶ ማን ይሆን?
ነገሩ ከእግዚአብሔር ካልሆነና ከመጽሐፍ ቅዱስ ካልተማርነው ሊሆን የሚችለው ከሰው ወይም ከሰይጣን ነው፡፡ እንዲህ የሚያደርግ ሰውም በማን መንፈስ እንደሚመራ ብዙ ጥናት ማድረግ አይጠበቅም፡፡ መዝሙርን ለእግዚአብሔር ብቻ መዘመር ትቶ በመዝሙር ያንቀላፉና በሕይወት ያሉ ፍጡራንን የሚያሞግስ እርሱ ከእግዚአብሔር ሐሳብ ፈጽሞ የራቀ እግዚአብሔርን በሚያስቈጣ ተግባር ውስጥ የሚገኝ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ምክንያቱም ተደጋግሞ እንደተነገረው በቅዱሳን ስም የሚቀርበውን መዝሙር የሚሰማውና የሚቀበለው ቅዱሳኑ ሳይሆኑ በስማቸው የሚነግደውና ከጥንቱ “በልዑል እመሰላለሁ” ኢሳ. 14፡14 ብሎ ከክበሩ የተዋረደው ሰይጣን ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቅዱሳንማ እንኳን ይዘመርልን ሊሉ ሊዘምሩላቸው የሚዳዱትን ሊከለክሉ እንደሚችሉ ነው የምናውቀው፡፡ በልስጥራን እግረ ሰላላ የነበረውንና ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮ ተራምዶ የማያውቀውን ሰው ጳውሎስና በርናባስ፣ እርሱ ብቻ ፈዋሽ በሆነው በኢየሱስ ስም በፈወሱት ጊዜ እንደአማልክት ቆጥረው ሊሠዉላቸው በወደዱ ጊዜ አልተቀበሏቸውም፡፡ ይልቁንም ልብሳቸውን ቀደው ወደእነርሱ ሳይሆን ወደ እግዚአብሔር ፊታቸውን እንዲመልሱ አስተማሯቸው፡፡ ያን ጊዜ እንዲህ ዓይነት ምላሽ ለሰጡት ለእነ ጳውሎስ ካንቀላፉ በኋላ ዛሬ በስማቸው ብንዘምር ስለማይሰሙን እንጂ  ከዚያ በበለጠ በተቃወሙን ነበር፡፡ እንደነጳውሎስ ሁሉ ቅዱሳን መላእክትም ሆኑ ጻድቃን ሰማዕታት የምንዘምርላቸው መሆኑን ቢያውቁ ኖሮ አይቀበሉንም ነበር፡፡ እንዲያውም በጭንቅ ያስተዉን ነበር፡፡
በሕይወት ያሉ አንዳንድ ጳጳሳት ግን “ኦ አባ ቅዱስ ዕቀቦሙ” እየተባለ ሲዘመርላቸውና እግራቸው ላይ እየተወደቀ ሲሰገድላቸው ሁሉንም ሲቀበሉ እንጂ ሲቃወሙ አልታዩም፤ አልተሰሙም፡፡ በሐዋርያት ፈለግ እየተጓዡ አይደለምና፡፡ አቡነ መርሐ ግን በአንድ ወቅት “ኦ አባ ቅዱስ ዕቀቦሙ” እየተባለ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲዘመር እንደተቆጡና “ይህ እኮ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአብ የጸለየው ጸሎት ነው፤ ለእርስዎ አይስማማም” ብለዋል እየተባለ ይነገራል፡፡ እንዲህ ያለው ተግባር ጳጳሳት ዝቅ ብለው መንጋውን እንደሚገባው ከማገልገል ይልቅ መንጋው እንዲያመልካቸው የሚፈልጉ መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህ ግን በፍጹም ሊሆን የማይገባው መንፈሳዊ ያልሆነ ተግባር ነው፡፡ ስለዚህ ብፁዓን አባቶች እንዲህ ያለውን አድራጎት ሊቃወሙና “እንዘምርላችሁ እንስገድላችሁ” የሚሏቸውን ሁሉ ተዉ ይህ ለእግዚአብሔር ብቻ ነው መቅረብ ያለበት ሊሉ ይገባል፡፡ አሊያ በብዙ ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
በቤተ ክርስቲያን ዘማርያን መዝሙር ሲያወጡ  ለእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም የዘመሯቸውን ዝማሬዎች በሲዲያቸው ያካትታሉ፡፡ አንዳንዶቹ ይህን የሚያደርጉት መቼም ሰውን ደስ ለማሰኘትና ተቃውሞ እንዳይነሳባቸው በሚል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ግን አሳዛኝ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለሰው መኖር ነው፡፡ የሚያኖር ደግሞ እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለም፡፡ እውነቱን ብቻ የዘመሩ ምን ሆኑ? ምን ጐደለባቸው? ምንስ አጡ? ሐሰትን ቀላቅለው የዘመሩትስ ምን አተረፉ? ምን ተጨማሪ ነገርስ አገኙ? በማስተዋል ካየነው ይህ የተሳሳተ ስሌት ነው፡፡
በአጠቃላይ ከእግዚአብሔር ውጪ የሚዘመርለትና የሚሰገድለት አካል ካለ፣ እርሱ ለሚዘምርለትና ለሚሰግድለት ለዚያ ሰው ጣዖት ሆኗል፡፡ በአክብሮት ስም የሚያመልከው ጠዖቱ ነው፡፡ ስለዚህ መንፈሳዊና እውነተኛ ከሚመስል ከዚህ የአምልኮ ጣዖት መንገድ መውጣት የእያንዳንዱ ምእመን ኃላፊነት ነው፡፡ ዝማሬያችን መቅረብ ያለበት ለእግዚአብሔር ብቻ ነውና በዝማሬያችን እግዚአብሔርን ብቻ እናክብር፣ እርሱንም ብቻ እናምልክ፡፡

33 comments:

 1. እኔ የሚገርመኝ አንዳንድ ዘማሪያን ወቅቱንና ቢዘነሱን እያዩ ይዘምራሉ : ለእግዚአብሄር ክብር ብቻ አይዘምሩም ካሴታቸው ወይም ሲዳቸው የሚሸጥበትን መንገድ ብቻ ይዘምራሉ

  ReplyDelete
 2. ላንቀላፉ ቅዱሳን!!!!!!! Alk???? Geta kezih Qidusanin kemmitela ganen yigelaglih

  ReplyDelete
  Replies
  1. This comment has been removed by the author.

   Delete
 3. temeheretu ewnet new mekebel yisala elalehu

  ReplyDelete
 4. ዝማሬ ለእግዚአብሔር ብቻ ለእግዚአብሔር ብቻ ለእግዚአብሔር ብቻ ለእግዚአብሔር ብቻ ለሌላ ለማንም መሰጠት የለበትም
  እልልልልልልልልልልለልልልልልልልለልልልለልልልል

  ReplyDelete
 5. ለቅኖች ምስጋና ይገባል

  ReplyDelete
 6. መጀመሪያ አስተያየት ለሰላማ ብሎግ!!!በምታቀርቡዋቸው ጽሁፎች ላይ አስተያየት ስንሰጥ በፍጥነት ከማውጣት ይልቅ አፍናችሁ እያቆያችሁ ማሰቀየሻ ጽሁፍ ካዘጋጃችሁ በሁዋላ መልቀቅ ወዳጅነታችንን ይጎዳዋል፡፡ስለዚህ አስተያየቶቻችንን በፍጥነት ለማውጣት ሞክሩ፡፡አሁንም ስለመስተንግዶአችሁ በኢ/ዊ ጨዋነት አመሰግናለሁ!!ወደ ሀታቴ መዝሙራቱ ጽሁፍ……..
  1. ከጽሁፉ እንነሳ፡ ጽሁፉ የሚያቀርባቸው ጥቅሶች እና የጸሀፊው መደምደሚያ የተዋሀደ አይደለም፡፡ለእ/ር ዘምሩ ማለት ለቅዱሳን አትዘምሩ ማለት እንደሆነ ለማስረዳት ብዙ ይታትራል፡፡ነገር ግን አንድም ለቅዱሳን አትዘምሩ የሚል ጥቅስ አላቀረበም፡፡ሐዋርያትን ጠቅሶ ያቀረበው ማብራሪያም ሐዋርያት የተቃወሙት የአምልኮ መልክ ያላቸውን ውዳሴዎችንና አክብሮቶችን እንጅ እንደ ሐዋርያ የቀረቡላቸውን የጸጋ ምስጋናዎችና ስግደቶች ስላልሆነ ጥቅሶችን ለጥጦ በመተርጎም አጉዋጉል ወደ ራስ ሀሳብ ለማስጠጋት መሞክር ከንቱ ድካም ነው፡፡ ሲጀመር ለእ/ር የምናቀርበው ዝማሬ ለቅዱሳኑ ከምናቀርበው ጋር አንድ ስላልሆነ በምንም መለኪያ የእ/ርን ክብር መጋፋት ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡እናንተ እንደዛ ከመሰላችሁ የምታመልኩትን መርምሩ፡፡“ቅዱሳን ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።” መዝ. 30፡4 ሲል ጸሀፊው ለክርክሩ አስረጅነት የጠቀሰውን ጥቅስ ብንወስድ እንኳ ቅ/ዳዊት “ቅዱሳን ሆይ” እያለ መልእክት የሚያስተላልፈው በህይወት ላሉ ቅዱሳን ብቻ ለይቶ ባለመሆኑ ያረፉ ቅዱሳን እኛን አይሰሙም የሚለውን መከራከሪያ የሚያፈርስ እንጅ የሚያጠናክር አይደለም፡፡
  2. መጽሐፍ ቅዱሱንም እንየው፡፡ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር በተባለው መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን….ርግቤ…ሱላማጢስ….ወዳጄ….ውበቴ በሚሉ ቃላት ተውቦ በሴት አንቀጽ(ጾታ) የቀረበው መዝሙር እንዴትም ቢተረጎም ምስጋናውና ውዳሴው ለእግዚአብሄር የቀረበ ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ሊቃውንቱም የሚተረጉሙት አንድም ለወንጌል፣አንድም ለቤ/ክ፣አንድም ለእመቤታችን የቀረበ ውዳሴ ነው እያሉ ነው፡፡እርግጥ የእናንተን ትርጉም አናውቀውም፡፡ግን ለእግዚአብሄር ብቻ የቀረበ መዝሙር ነው እንደማትሉን ተስፋ እናደርጋለን፡፡እ/ር በሴት አንቀጽ ሲመሰገን አይተን ስለማናውቅ፡፡ለቤ/ክ ነው ካላችሁም ዞሮ ዞሮ ምስጋና የሚቀርበው ለእ/ር ብቻ ነው የሚለው መከራከሪያ መፍረሱ አይቀርም፡፡
  3. በመሰረቱ መዝሙር የሚለው ቃል ዘመረ ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ማመስገን ማለት ነው፡፡ምስጋና ደግሞ እንደውለታው አይነትና እንደውለታ አድራጊው ክብርና ማእረግ ይለያያል፡፡ለአምላክ የምናቀርበው ምስጋና የባህርዩ ነው፡፡ፈጥረህ የምትገዛ፤አብቅለህ የምትመግብ፣ከሶስቱ አካለት አንዱን አካል ልከህ ከዘለዓለማዊ ሞተ-ነፍስ ያዳንከን ብለን ነው፡፡ ለቅዱሳኑና ለመላእክት ስንዘምር ግን አምላካቸውን ታምነው ያደረጉትን ተጋድሎና ያገኙትን አክሊለ ክብር እያስታወስን እነሱን ለእኛ አርዓያ እንዲሆኑ የፈቀደ አምላከ በመዝ 88 ቁ 3 መሰረት ከመረጣቸው ጋር ያደረገውን ቃል እንዲያስብ በስማቸው እየዘመርን ተማለደን ነው የምንለው፡፡ልመናችን ሲደርስም በአማላጅነታቸው ስለተደረገልን እነሱን ለመጽናኛ የሰጠንን መልሰን እናመሰግናለን፡፡ስለጸጋቸው እናወድሳቸዋለን፡፡ደግሞ እንኳን ለጻድቃን ለምድራዊ አርበኞችም ይዘመራል፡፡እነሱማ ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ….ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም…የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል እየተባለ በመዝ 111 የተነገረላቸው ናቸው፡፡ስለዚህ መንፈሳዊ አርበኞቻችንን በመዝሙራት ስራቸውን እያነሳን እንዘክራለን-እናስባቸዋለን-አሳስቡልን እንላቸዋለን፡፡
  4. ስለ መላእክት በመዝ 102 ቁ 20…ባርክዎ ለእ/ር ኩልክሙ መላእክቲሁ-መላእክት ሁሉ እ/ርን ባርኩ…ተብሎ ተጽፎልሀል፡፡እና ቅ/ዳዊትን ያህል ነቢይና መዘምር መላእክትን እንዲህ በመዝሙሩ ሲያናግራቸው ለጣኦት ምስጋና እያቀረበ ነበር ልትለን ነው???ባርክዎ ያለው ዳዊት ሰአሉ ለነ--ለምኑልን እንዳይል የትኛው ጥቅስ ነው የሚከለክለው??
  5. ስለ እመቤታችን የምስጋና(የመዝሙራት) ምንጮች
  ሀ. ትንቢት፡ ቤ/ክ ዳዊት በመዝ 44 ቁ 16….ለልጅ ልጅ ስምሽን ያሳስባሉ…ሲል የተናገረው ትንቢት እመቤታችን በሉቃ 1 ቁ 48….እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል…ስትል በተናገረችው ቃል ፍጻሜ አግኝቱዋል ብላ ታስተምራለች፡፡የምድራዊቷን ቅ/ኤልሳቤጥ እና የሰማያውይውን ቅ/ገብርኤል ምስጋናም እንዳትረሳው፡፡ይሄው እኛም ለፈጽሞ ትንቢት ሰአሊ ለነ ቅድስት እያልን ስሙዋን እንጠራለን-ለትውልድ እናሳስባለ፡፡የለም፡፡ የዳዊት ትንቢት ለኢየሩሳሌም የተነገረ ነው የሚል ካለም ጌታ ተመላለሰባት ተብሎ ከምትወደሰው ግኡዝ ምድር ጌታን ወልዳ፣ተሰዳ፣አጥብታ፣ከቀራንዮ እስከ ጰራቅሊጦስ ያልተለየቸው ወላዲተ አምላክ ምስጋናም ሲያንሳት ነዋ እንላለን!!
  ለ. ቀደምት አበው፡እነ ቅ/ኤፍሬም፣እነ አባ ህርያቆስ፣እነ ቅ/ያሬድ፣እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣እነ ዮሐንስ አፈወርቅ እረ ስንቱ…..አወድሰዋት፣ቅድስናዋን አማላጅነቱዋን ተናግረው አይጠግቡም፡፡እነዚህ ቅዱሳን ስለ ብሉይና ሐዲስ ያላቸው እውቀት ደግሞ አይጠረጠርም፡፡በምስጋናዋ የሚደረድሩት የነቢያት ትንቢትና አምሳል፣የሐዋርያት ስብከት ምጥቀታቸውን ያሳያል፡፡ትምህርቱን ፈጥረው፣አመንጭተው ሳይሆን ከሐዋርያት ሲወርድ ሲዋረድ እናዳገኙም እናውቃለ፡፡እኛም የእነሱ ልጆች ስለሆንን አርዓያነታቸውን ተከትለን ...ተፈስሂ ኦ ማርያም እም ወአመት-እናትነትን ከአገልጋይነት ያስተባበርሽው ብቸኛዋ እመቤት ሆይ ደስ ይበልሽ… እያልን በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንላታለን፡፡እናወድሳታለን፡፡ሆኖም አናመልካትም!!

  ሐ. ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ እውቅና ከምትሰጣቸው ጉባኤያት መካከል በ431 ዓ.ም 200 ሊቃውንት ተሰብስበው ሁለት አካል፣ ሁለት ባህርይ ባዩን ንስጥሮስን ያወገዙበት ጉባኤ-ኤፌሶን አንዱ ነው፡፡በዚህ ጉባኤ ላይ ንስጥሮስ እመቤታችን የወለደችው መለኮትነት የሌለው ወልድን ብቻ (እሩቅ ብእሲ) እንጅ መለኮት የተዋሀደው ስጋን አይደለም በማለቱ “ታዲያ ሰብዐ ሰገል አምኃ አቅርበው የአምልኮ ስግደት የሰገዱት ለሩቅ ብእሲ ነው እንዴ” ተብሎ ተረታ፡፡የእመቤታችን ወላዲተ-አምላክነትም በጉባኤው ዳግም በአጽንኦት ተነገረ፡፡በመጨረሻም በውሳኔው አንቀጸሃይማኖት “….የእውነተኛ ብርሃን እናት ሆይ እናከብርሻለን፣መጥቶ ነፍሳችንን ያዳነውን የዓለምን ሁሉ መድኃኒት ስለወለድሽልን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆይ እናመሰግንሻለን….” ሲሉ የቀደሙ አባቶችን ትምህርት አጽንተው ከ1500 አመት በፊት በዶግማ ደንግገውልናል!!ዶግማ ደግሞ አይሻሻልም፣አይጨመርበትም፣አይቀነስበትም!!ስለሆነም በመላው ዓለም ይሄን ጉባኤ በሚቀበሉ የምእራብና የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ከሉተራውያን በቀር እመቤታችንን ‘ሰአሊ ለነ ቅድስት’ ሳይል የሚውል ክርስቲያን የለም!!በነገራችን ላይ ደቀመዛሙርቱ እንጅ ሉተር የእመቤታችንን ምስጋና አይቃወምም ነበር፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. “….የእውነተኛ ብርሃን እናት ሆይ እናከብርሻለን፣መጥቶ ነፍሳችንን ያዳነውን የዓለምን ሁሉ መድኃኒት ስለወለድሽልን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆይ ….” ብሎ ይህንን ያደረገልሽ ጌታችን የተመሰገነ ነዉ፡ ማለት ይገባል፡፡ ምሥጋና ራሱ የፈጠረዉን ሰዉነት አንጽቶ ማደሪያዉ ላደረገ ጌታ ብቻ ነዉ፡፡ እመቤታችን በመታዘዝ ያደረገችዉ ሁሉ እንደሰዉ የሚያስመሰገናትና ብጽዕት ቅድስት የሚያሰኛት ቢሆንም የአምልኮና ቅዳሴ ዝማሬ አካል መሆን የለበትም፡፡ ከጅምሩ በእስዋ ፍላጎት የመጣ ጸጋ ስላልሆነ ይህንን ጸጋ ለሰጣት ጌታ ራስዋ በትህትና ባሪያህ ብላ እንደገለጸችዉ መቀበል እንጂ የጥንት የዛሬ አባቶች ይህን አሉ ያን አሉ ማለት አይገባም፡፡ሉተር ያለዉ ነገር ሁሉ ትክክል አልነበረም ማለትም ተገቢ አይደለም፡፡ ብዙ የሉተር ልጆች የሚነቀፋት አመቤታችን ከጌታ ልደት በሁዋላ ድንግልናዋ ተገርስሱዋል ልጆችም አሉዋት የሚለዉና ለመቃወም ያህል የኛን ጤናማ የሆኑትን የቤተክርስቲያናችንን ሥርዐት ሲያጥላሉ ነዉ፡፡ አለበለዚያ በክርስቶስ ቤተሰብ ዉስጥ የሚካሄደዉን ሽኩቻ አይቀበለዉም፡፡ እሱ ለሁላችንም በቂ ቦታ አለዉና የክርስቶስን አካል መገነጣጠል ትተን መቻቻልና በድህነት አንድ መሆናችንን በማሰብ ጌታን እናስደስተዉ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

   Delete
  2. እኔ የጌታ ባሪያMay 3, 2014 at 2:04 AM

   ህሩይ ሆይ! ከዚህ ቀደም መላልሼ ስለምልጃና የተደራራቢ አምልኮ መሰል ሥርዐታችን ብጠይቅህ ዝም አላለክምን አሁንም ልጠይቅህ ጌታችን ምን እሳጥቶን ነዉ ለልመና
   ቅዱሳንና መላዕክትን የምንጠራዉ? ዮሐ 14 13 እስከ14 የሚለዉን ተመልከት ደግሞም ጌታችን በሌላ ቦታ በስሙ ባለመለመናችን ምን ያህል እንደተጎዳን ይናገራል፡፡ እርሱ ወንደሞቼ ሲለን ያለፈረብንን ጌታና አባት እነደሩቅና ጨካኝ አለቃ እየቆጠርነዉ በየቅዱሳኑ ገደማት የምንከራተተዉ አያሳዝንም ትላለህ፡፡ እዉነቱን ስንናገር ወይም ስንጠይቅ ፐሮቴስታንት ትላላችሁ ይህ አግባብ አይደለም በቅንነት ጠይቀን አንድም ቀን በቅንነት የሚመልስ (አንተን ጨምሮ) አላየሁም፡፡ እኔ በራሴ ቤተክርሰቲያናችንን ለማወቅ የምጥር ሰዉ ነኝ እንደአቅሜ የቤተክርስቲያንን መጽሐፍት አነባለሁ፡፡ ተአምረ ማሪያምን አንብቤ ስጨርስ አለቀስኩ፡፡ ሌሎቹን ገድላት ለማንበብ ስሞክር ሁሉም ዉሸት ነዉ ባልልም አብዘኛዉ ዘግናኝ ነዉ፡፡ ለልባችን ሀዘን ስትል አንዳንዴ እንክዋን ያፈጠጡና አሳፋሪ ታሪኮቻችንን የማታወግዝበት ምክንያት ጦምህን እንዳታድር ነዉን ጌታችን እኮ ለዕለት እነጀራ አይታማም ወፎች አኔ ግቢ መጥተዉ የተከልከዋቸሁን ፈራፍሬ ሙልጭ አድርገዉ ሲበሉ ሳይ ደስ ይለኛል፡፡ ለካ ጌታ ያስተከለኝ እነሱን ለመመገብ ነዉ አላለሁ ለአንተ ለሊቁ ታድያ ከወፎቹ ያነሰ የሚያስብ ይመስለሃልን፡ መክሊትህን ዛሬ ብትቀብር ነገ የሚጠይቅህ ጌታ አለና በጊዜ አስብበት፡፡

   Delete
  3. ምንም ጥያቄ የማያስነሳ ጉዳይ ሆኖ ሳለ አቶ ህሩይ ለምን እንደምትዘላብድ አይገባኝም፡፡ ሐዋሪያት አንድም ቀን ስለ ቅድስት ማሪያም ስለ ሌሎች ቅዱሳን እና ስለ መላዕክት አንስተው እንዲህ ያለ ትምህርት ያላስተማሩን ለምን ይመስልሀል? ወይስ ረስተው እና ተሸደው ነው? ከመጀመሪያው በአምልኮ ጥማት ተነሳስቶ ራሱን ከልዑል የመሰለው ዲያብሎስ (የወደቀው መልዓክ) ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ የአምልኮ ጥማቱን ለማርካት በተለያዩ ቅዱሳን ስም ሽፋንነት ሲመለክ ስንት ዘመን ኖረ መሰለህ በኢትዮጵያ! ዛሬ ዛሬ ዘማሪዎቻችን መዝሙር ቢቻ ቢዘምሩ መናፍቃን እየተባሉ እየኮበለሉ ነው:: ቢያንስ የገባቸውን ቢቻ እንዲዘምሩ ቢፈቀድላቸው ምን አለበት? የግድ ካለቀላቀሉ ለምን እንደሚባል በፍጹም ሊገባኝ የማይችል ጉዳይ ነው:: ወይስ እነርሱ (ቅድስት ማሪያም ሌሎች ቅዱሳን እና መላዕክት) እንዳይከፋቸውና እንዳይቆጡን ነው? ይገርማል!!!

   Delete
  4. @hiruy your comment is too long but there is no relevance with the issue

   Delete
 7. ewinet new...zimare le fetari bicha new...chigiru yewengel birihan libn kalabera hulum neger ayigebam...yikir yibelachihu..zemen ametash sebakiwochm zemariwcohm leewinet enji lebusiness bead neger atikelakilu!!!

  ReplyDelete
 8. የባሰ አታምጣ !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!ታዲያ አዳራሽ ገብተን በጌታ ስም የዘፈን ሀራራችንን እንወጣ ። እኛስ መድህን አለም ክርስቶስን እናመልካለን እናቱንም ፣መላክቱንም ፡ቅዱሳኑንም በፍቅርና በትህትና ዛሬም ለዘለአለም እንዘምርላቸዋለን !!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 9. በመጽሀፍ ቅዱስ ለድንግል ማርያም፣ ለመላዕክቱ ፡ለቅዱሳኑ የዘመረ ማነው ? ማን ም የለም ዝማሬ ለእግዚአብሔር ብቻ ነው

  ReplyDelete
 10. እኔ የጌታ ባሪያMay 3, 2014 at 2:05 AM

  ለዘወትር ታዳሚዉ ህሩይ ከዚህ ቀደም መላልሼ ስለምልጃና የተደራራቢ አምልኮ መሰል ሥርዐታችን ብጠይቅህ ዝም አላለክምን አሁንም ልጠይቅህ ጌታችን ምን እሳጥቶን ነዉ ለልመና
  ቅዱሳንና መላዕክትን የምንጠራዉ? ዮሐ 14 13 እስከ14 የሚለዉን ተመልከት ደግሞም ጌታችን በሌላ ቦታ በስሙ ባለመለመናችን ምን ያህል እንደተጎዳን ይናገራል፡፡ እርሱ ወንደሞቼ ሲለን ያለፈረብንን ጌታና አባት እነደሩቅና ጨካኝ አለቃ እየቆጠርነዉ በየቅዱሳኑ ገደማት የምንከራተተዉ አያሳዝንም ትላለህ፡፡ እዉነቱን ስንናገር ወይም ስንጠይቅ ፐሮቴስታንት ትላላችሁ ይህ አግባብ አይደለም በቅንነት ጠይቀን አንድም ቀን በቅንነት የሚመልስ (አንተን ጨምሮ) አላየሁም፡፡ እኔ በራሴ ቤተክርሰቲያናችንን ለማወቅ የምጥር ሰዉ ነኝ እንደአቅሜ የቤተክርስቲያንን መጽሐፍት አነባለሁ፡፡ ተአምረ ማሪያምን አንብቤ ስጨርስ አለቀስኩ፡፡ ሌሎቹን ገድላት ለማንበብ ስሞክር ሁሉም ዉሸት ነዉ ባልልም አብዘኛዉ ዘግናኝ ነዉ፡፡ ለልባችን ሀዘን ስትል አንዳንዴ እንክዋን ያፈጠጡና አሳፋሪ ታሪኮቻችንን የማታወግዝበት ምክንያት ጦምህን እንዳታድር ነዉን ጌታችን እኮ ለዕለት እነጀራ አይታማም ወፎች አኔ ግቢ መጥተዉ የተከልከዋቸሁን ፈራፍሬ ሙልጭ አድርገዉ ሲበሉ ሳይ ደስ ይለኛል፡፡ ለካ ጌታ ያስተከለኝ እነሱን ለመመገብ ነዉ አላለሁ ለአንተ ለሊቁ ታድያ ከወፎቹ ያነሰ የሚያስብ ይመስለሃልን፡ መክሊትህን ዛሬ ብትቀብር ነገ የሚጠይቅህ ጌታ አለና በጊዜ አስብበት፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Mothers day is to be celebrated tomorrow ,May 11.If we celebrate a day for our human mothers,how much is expected from Christians to celebrate CHRIST's Mother,emanating from the deep love for CHRIST?

   Delete
 11. erasihin chileh zemera tadiya, silelelaw min agebah. Yefelege lefelegew yizemir. Antem lemartin luther zemir

  ReplyDelete
 12. ለምን ቤተክርስቲያናት በመላዕክት እና በቅድስት ማርያም ስም ይከፈታል?

  ReplyDelete
 13. You guys don't realize that no Saint on Earth lives the life to self alone, though you reakly live to yourself.

  ReplyDelete
 14. ahun ahun eko protestantochum silewengel silu mekeran yetekebelu eyalu yemizemirulachewu alu.tadiya ABA SELAMAWOCH yihe tinish kenesu gar ayararikachihum?

  ReplyDelete
 15. አምልኮ ዝማሬ ለቅዱሳን አምላክ ብቻ ማለት በየትኛዉ የትርጉም መጽሐፍ ነዉ የቅዱሳን ጥላቻ ማለት ነዉ የሚለዉ? አምልኮ ባዕድ የተለማመደ ሰዉ ቅዱሳንን ማምለክ አንድ እርምጃ ወደፊት የተሻሻዐ ይመሰለዋል፡፡ ነገር ግን ቀልቀሎ ስልቻ ስልቻ ቀልቀሎ ነዉ ነገሩ እንደ ቅዱስ ሚካኤል ይህንን መንፈስ እኔም ጌታ የገስጸዉ እላለሁ

  ReplyDelete
 16. ሕይወት
  “….የእውነተኛ ብርሃን እናት ሆይ እናከብርሻለን፣መጥቶ ነፍሳችንን ያዳነውን የዓለምን ሁሉ መድኃኒት ስለወለድሽልን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆይ ….” ብሎ ይህንን ያደረገልሽ ጌታችን የተመሰገነ ነዉ፡ ማለት ይገባል፡፡ ምሥጋና ራሱ የፈጠረዉን ሰዉነት አንጽቶ ማደሪያዉ ላደረገ ጌታ ብቻ ነዉ፡፡ እመቤታችን በመታዘዝ ያደረገችዉ ሁሉ እንደሰዉ የሚያስመሰገናትና ብጽዕት ቅድስት የሚያሰኛት ቢሆንም የአምልኮና ቅዳሴ ዝማሬ አካል መሆን የለበትም፡፡ ከጅምሩ በእስዋ ፍላጎት የመጣ ጸጋ ስላልሆነ ይህንን ጸጋ ለሰጣት ጌታ ራስዋ በትህትና ባሪያህ ብላ እንደገለጸችዉ መቀበል እንጂ የጥንት የዛሬ አባቶች ይህን አሉ ያን አሉ ማለት አይገባም፡፡ሉተር ያለዉ ነገር ሁሉ ትክክል አልነበረም ማለትም ተገቢ አይደለም፡፡ ብዙ የሉተር ልጆች የሚነቀፋት አመቤታችን ከጌታ ልደት በሁዋላ ድንግልናዋ ተገርስሱዋል ልጆችም አሉዋት የሚለዉና ለመቃወም ያህል የኛን ጤናማ የሆኑትን የቤተክርስቲያናችንን ሥርዐት ሲያጥላሉ ነዉ፡፡ አለበለዚያ በክርስቶስ ቤተሰብ ዉስጥ የሚካሄደዉን ሽኩቻ አይቀበለዉም፡፡ እሱ ለሁላችንም በቂ ቦታ አለዉና የክርስቶስን አካል መገነጣጠል ትተን መቻቻልና በድህነት አንድ መሆናችንን በማሰብ ጌታን እናስደስተዉ፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

  ReplyDelete
 17. every day,I am sure that many peoples including you,say "thank you very much" for human beings,this is sin according to your explanation,it is adoration.plus Hiruy gives blessings for you(he said'amesegenalehu',you didn't opposed it.someone asked that why we open church in the name of saints is that Issayas56:4-10

  ReplyDelete
 18. When I wrote this paragraph I was sure that you will not post it. I knew how to challenge you than my brothers who wrote opposing your belief. You and your kind do not need scriptural references so as to clear the points mentioned.You need simple answer, very simple metaphor. It is such metaphor easily destroy your delusion and intellectual pride. Cowards! ፈሪ ሁላ!!!
  ደግሜ እላለሁ
  በእንዳንተና በእንደኔ አይነት ጭራቅ ድምጽ ሳይሆን

  ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ስህተት ለባህርዩ በማይስማማው በእግዚአበሔር ተመረጠች! ምን ይዋጥህ!? ምርጫውን አትሰርዘው ፣ኮሮጆውን አትገለብጠው ነገር ምርጫው የልዑል እግዚአብሔር ነው ። በቃ- ተኝተህ ተኩስ።
  ኦርቶዶክሳዊያን በናታችሁ ነገረ ሃይማኖት በሚገባው ሰው ደረጃ ከፍ አድርጋችሁ አትመልሱለት። ከመጽሐፍ ቅዱስ አትጥቀሱለት። በደረ ጃው አነጋግሩት። ልክ እንደዚህ!
  'የአባ ሰላማው' አመሰግንሃለሁ ። ዋ! አመለከኝ እንዳትለኝ።

  ፖስት ባታደርጉት ስቄም አላባራ!

  መንቲሮ ነኝ

  ReplyDelete
 19. ለመሆኑ የሰራ ስለመልካም ስራው አይወሳ አይወራለት የሚል ማን ነው፡፡ ጌታ መልካም የሰሩ ሰዎችን ሲያወሳ ሲናገርላቸው እንደነበረ ሁሉ እኛስ መልካም የሰሩትን ብንናገርላቸው፡፡ ለምሳሌ ሁለት ሳንቲም ያላትን መበለት ጌታ ከጉድለትዋ ሰጠች ብሎ እንዳመሰገናት በህዝቡ ፊት እንደተናገረላትና እንደመሰከረላት እኛ ደግሞ ያውም መንፈሳዊ ተጋድሎ የተጋደሉትን ብናወራላቸው ብናመሰግናቸው ምን ችግር አለው፡፡ መግደላዊት ማርያም ሽቶ ብትረጨው ደቀመዛሙርቱ ተቃወሙ ጌታ ግን ስለምን ታደክሙዋታላችሁ መልካም ሰርታልኛለች እስዋ ያደረገችው በአለሙ ሁሉ ይህ ወንጌል በሚነገርበት ሁሉ ለመታሰቢያዋ ይነገርላታል እንዳለ ታዲያ ታላላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ያደረጉት ቢነገርላቸው ምን ያስከፋል፡፡ ማሰብ ማለት ነገረ ስራቸውን አይቶ በቃላት መናገር መዘመር ሊሆን ይችላልና ክፋት የለውም፡፡ የሚባርኩህን እባርካለው ብሎ ለአብርሃም ቃል ሲገባ ከሞትክ በሁዋላ ይቀራል አላለም እስከመጨረሻው እንጂ፡፡ እመቤታችንም ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል መንፈስ ቅዱስ ተናገረ ታዲያቅዱሳንን ብንባርክ እንባረካለን እስዋንም ብናመሰግን እንመሰገናለን ይህንንም በግጥምም ይሁን በቃላት መግለጥ እንችላለን፡፡ የሌላቸውን ክብር አንሰጥም ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውንም ክብርና ጸጋ አናሳንስም ፡፡
  ነቢዩ ዳዊት ጎልያድን ገድሎ ሲመለስ ህዝቡ ሳኦል ሺ ዳዊት እልፍ ገደለ ብለው ተቀብለውታል ቢወደስ በውስጥ ለውስጥ እግዚአብሔር ተመሰገነ እንጂ ያውም የእግዚአብሔር መንፈስ ያደረበትን እልፍ በማለት ስለዚህ አባቶችም በሰሩት ቢመሰገኑ ችግር የለውም፡፡ አንድን ሰው በጣም ጎበዝ የምንለው ሰውየውን ለማበርታት ምስጋና ለሰራውም እውቅና ለመስጠት ነው፡፡ ስራዎችን እግዚአብሄር እንደሚሰራው እናውቃለን ፡፡ የእግዚአብሔርን ምስጋና ለሰው መስጠት አለመስጠት መሆኑን እንረዳ፡፡ አንድን ሰው አመሰግናለው ስንልና እግዚአብሔርን አመሰግናለው ስንል የተለያዩ መሆናቸውን እንወቅ፡፡ ለመናፍቃን ይህ ነገር ይከብዳል ግን እራሳችሁን ታካብዳላችሁ ታተልቃላችሁ፡፡

  ReplyDelete
 20. Ahun minfiknachuhin yifa awotachuhat....gobezoch

  ReplyDelete
 21. Which devision of protestant is yours? Muluwongel, Mekaneeyesus or Only Jesus

  ReplyDelete
 22. ሰላም አባ ሰላማዎች ! ይሄን የምተይካቺሁ በርግጥ ጥያቄው እንዲሁ ወደ አአምሮዬ ስለመጣ አንጂ አሁን ፖስት ካደርጋቺሁት ፅሁፍ ጋር የሚያያዝ ሆኖ አይደለም:
  ጥያቄየም በምእራባዉያኑ ዘንድ ነገ ሜይ ፩፩ የ እናቶች ቀን ተብሎ ይከበራል: :ሁሉም እንደ አቅሙ ለ አናቱ ስጦታ ያቀርባል : ለ እናቱ ያለዉን ፍቅር በ አክብሮት (በ አምልኮ አይደለም) ይገልፃል:: አሁን አሁን አንደዉም በ እነኚህ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንም ይሄን አየለመዱት ነዉ ::ፕሮቴስታንቶቺንም ጨምሮ mallet ነው::
  ታዲያ እንዲሁ ለወደደን ለ አምላካቺን ለ ክርስቶስ እናት ለ እመበታቺን ለ ድንግል ማርያም አክብሮታቺንን እና ፍቅራችንን ለመግለፅ በ ወር አንዴ መታሰቢያ ብናደርግ አምልኮ ሆነ ይባላል እንዴ?
  መልሳችሁን እጠብቃለሁ::

  ReplyDelete
 23. funny enes semwan eteralhu

  ReplyDelete
 24. እናንተ ታዲያ ለምን “አባ ሰላማ” ተባላችሁ? የትኛዉን አባ ሰላማ ማለታችሁ ነዉ?

  ReplyDelete