Monday, May 19, 2014

በብጹእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የሚመራው የውጩ ሲኖዶስ ሰላሣ ስምንተኛ መደበኛ ጉባኤውን አጠናቀቀ፡፡


Read in PDF
 •        አዳዲስ ጳጳሳትን ሊሾም ነው።

በኦክላንድ መድኃኔ ዓለም ከ may 14 እስከ may 16 2014 ድረስ ሲካሄድ የቆየው ቅዱስ ሲኖዶስ አንዳንድ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል። ከመላው አሜሪካና ካናዳ ካህናትና ምእመናን በብዛት የተገኙበትና በሰላም እና በፍቅር የተካሄደ ጉባኤ ነበር ተብሏል። የኦክላንድ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ውግዘት መነሣትና ሲኖዶሱን ለመከፋፈል ሾልከው የገቡ ሰዎችን ለይቶ የማወቅ ሁኔታ በመፈጠሩ በሰላም የተካሄደ ጉባኤ ሆኗል። ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ እስከ ዛሬ ድረስ በስሕተት ስላደረጉት ነገር ሁሉ ይቅርታ በመጠየቅ ከወንድሞቼ ጋር እየተማከርሁ እሰራለሁ፤ ሽምግልናውም እየጨመረ ስለሆነ ሌላ ሰው ያስፈልገኛል ብለዋል።
የሕጻናት ወጣቶች ትምህርት በአግባቡ የሚካሄድበት ሥርዓት እንዲዘረጋ፣ የአብያተ ክርስቲያናት መተዳደሪያ ደንብ አንድ ወጥ እንዲሆን በቀረበው አጀንዳ ላይ ሁሉም የተስማማ ሲሆን ነገር ግን ሕጉ እንደገና እንዲጠና ምእመናንን ያካተተ ኮሚቴ ተቋቁሟል፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጋር የሚሠራ የሰበካ ጉባኤ መምሪያ እንዲኖር ተወስኗል። የቦርድ አስተዳደር ወደ ሰበካ ጉባኤ እንዲለወጥ የሚያበረታታ ሕግ እንዲሆን አጽንዖት ተሰጥቶበታል። የሲኖዶሱ ስብሰባ ከዛሬ ጀምሮ መንበረ ፓትርያርክ በሚገኝበት በዲሲ ብቻ እንዲሆን የተወሰነ ሲሆን የጥቅምቱ ጉባኤ ግን በዚያው በኦሐዮ እንዲቀጥል ተወስኗል። የቅዱስ ፓትርያርኩ ቤት እንደ መንበረ ፓትርያርክ ሆኖ በነሐሴ 29 እንዲመረቅ ተወስኗል። በአሜሪካና በሌላው ዓለም የሚያገለግሉ አዳዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ለመሾም ታቅዷል።

 አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትን በተመለከተ የተያዘ አጀንዳ አልነበረም። ይህም ጉባኤውን ይከፋፍላል ተብሎ ስለተፈራ ነው። ነገር ግን ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ስለ ዳላስ ኢየሱስ ያነሱት ጥያቄ ብዙ ያነጋገረ ነበር። ዳላስ ኢየሱስ በሲኖዶሱ ሥር ልጠቃለል ብሎ ያቀረበው ጥያቄ መልስ ሳያገኝ ምንም ጥያቄ ላላቀረበው ለዳላስ ሚካኤል መልስ መሰጠቱ ስሕተት መሆኑን ጉባኤው አምኖበታል። ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ዳላስ ኢየሱስን "ጥቂት ስለ ሆኑ ተጣልተው ስለወጡና የእምነት ችግር ስላለባቸው‚ ሲኖዶሱ አይቀብልም ሲሉ ለዳላስ ሚካኤል ጽፈው ነበር፤ የሚካኤል ቤተ ክርስቲያንም ይህን ደብዳቤ ተቀብሎ ለሕዝብ አንብቧል። ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ስለ ዳላስ ኢየሱስ ሲኖዶሱን የጠየቀው ነገር ሳይኖር ለምን ይህ ሆነ የሚለው ጥያቄ ብዙዎችን ሲያነጋግር ቆይቶአል።
ዳላስ ኢየሱስ ስለ ሆኔታው ማብራሪያ ጠይቆ ከሲኖዶሱ የመጣ ደብዳቤ አነበብን እንጂ እኛን የሚያገባን ነገር የለም የሚል መልስ ሰጥቷል። ነገሩ በመጨረሻ ሲጣራ ዲ. አንዷለም እራሱ ጽፎ አቡነ መልከ ጼዴቅን አስፈርሞ ያመጣውና ቦርዱ ያልወሰነበት ጉዳይ መሆኑ ተረጋግጧል። የሚካኤል ቦርድ መምህር ተከስተን እንዲያስተምር ጋብዘነው ነበር ዲ.አንዷለም ግን እንዳይመጣብኝ በማለቱ ዝም ብለን ስንከታተል ቆይተናል ደብዳቤውንም ያመጣው ራሱ ነው እኛ የምናውቀው ነገር የለም፣ አሁን ግን ችግሩን እየተረዳነው መጥተናል ሲል ምስክርነት ሰጥቷል።
በዚህ አጋጣሚ ሲኖዶሱ ሁሉንም አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት ያለ ቅድመ ሁኔታ ተቀብለን ሂደቱን መቆጣጠር አለብን በሚለው ወስኗል። የዳላስ ኢየሱስንም አቡነ ዮሐንስ እንዲከታተሉ ታዘዘዋል። ዲ. አንዷለም በጉባኤው ላይ ባይገኝም ኪሩቤል የተባለው የመድኃኔለም ሰንበት ተማሪ መምህር ተከስተን በመናፍቅነት ከሷል። ነገር ግን አባቶችና ወንድሞች በአንድነት ይህ ሰው በሌለበት ጉባኤ መከሰስ የለበትም ማስረጃ ካላችሁ አቅርቡ እርሱም ተጠርቶ ይጠየቅ ይህ የዘመኑ የማጥቂያ ስልት ስለሆነ ጥንቃቄ ይጠይቃል በሚለው አስተያየታቸው ዝም አሰኝተውታል።
ብጹእ አቡነ መለከ ጼዴቅም ከኔ ጋር ሲኖር በትምህርቱ ምንም ነገር አግኝቼበት አላውቅም ሲሉ መስክረዋል። ከሳሾች የመምህር ተከስተን የኮንፈረንስና የጉባኤ ስብከቶች ስህተትን ለማግኘት ሲመራመሩ ቢከርሙም ምንም ሊያገኙ ባለመቻላቸው ወሬ ከማውራት ማለፍ አልቻሉም ተብሏል። እነ ኪሩቤል አንብበውት የማያውቁት ወይም የማይገባቸው ከሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ቢሆንም የመናፍቅ ነው ማለት የለመዱ ሥራ ፈቶች ናቸው ሲል አንድ በቅርብ የሚያውቃቸው ሰው ተናግሯል።
 በጠቅላላው ሲኖዶሱ በመልካም መንፈስ የተካሄደ ነበር አንድነቱንም እንደገና አጠናክሯል። በመካከል የተፈጠረው ጥላቻና መለያየት በይቅርታ ተደምድሞ በአዲስ መንፈስ ወደ ፊት ለመጓዝ አዲስ ጉዞ የጀመረ መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ አባቶች በግል ባደረጉት ውይይት ዲ.አንዷለም ከውስጡ ሲኖዶስ አንድ ሊቀ ጳጳስ ሰርጉ ላይ እንዲገኙ  የጋበዘ ሲሆን የድንግል ማርያም ምእመናንን እንዳያለያይ ጥንቃቄ እንዲደረግ፣ እርሳቸውንም በመንፈሳዊ ወንድምነት በጥንቃቄ ማስተናገድ እንደሚገባ መክረዋል። የውስጡን ሲኖዶስ ዜና እንደደረስን እናቀርባለን።   

·     

23 comments:

 1. God is great what a news, Long live Abba Woldetensai, Abatachen and others who working hard to bring peace around Bay area but in the same time there are cancers here in our church Medhanialm and i'm sure in Iyesus specially the name Kirubel who is one of our mezemeran he has no knowledge about Christianity please give him some advise not to bothers other mezemeran in medhanialm.
  Concerned Medhanialm Mezemeran

  ReplyDelete
  Replies
  1. Aye, wela abatachen wela aba Woldetenasai all they are working for is to take total control of all the church in all its dealings,church members will not have any say so except paying all the finance of the church, In return we will get once a week, kedasse for about 2 hours. Who are they fooling? Woldetensai, why do you not go get a real job and earn an honest living? instead of flying from city to city spreading your empty sermon, let me give you advise, go drive a cab, be an example to your compadres, to sit and earn a living is a sin, God does not like lazy, freeloading on church members. please answer me, what are you doing? shame on you all of you who sit 6 days week and work on sunday for about 2 hours.

   Delete
  2. The cancer is within the clergy not with the church members, please do not put the blame on none other but the church leaders who are envious of each other, fighting, and dividing. they need to love, and forgive each other before they come out and preach to us. Start doing charity work, praying, kidase is not enough, go back to enat Ethiopia and help your people, particularly, monks who claim that their life is all to christ and the poor, what in the world are you doing in the USA?

   Delete
 2. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
 3. Aye kirubael lemayawekeh. anten belo degmo kesash. menafiks ante rasek neh. yeoaklanden saytoch yemetadergewen sew yemaywek meslek enday. sewn kemekeseseh befit rashen astekakel. menafkes endant saytoch lay yemichawet balegay ena wendumun yemiks new

  ReplyDelete
 4. Whose website is this. Full of bulshit.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Wizero Gunet lebesh meles yebel weana tenkolishen akumi tenkol yastemarechish Meseret natna lebesh wede egziabeher yemelese

   Delete
 5. This comment has been removed by the author.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Genet Asrat (Albo gift shop) like a true believer do not full yourself we talk a lot about our church board members and you know what we are doing to save our church from those butchers Benyam and Asrat. I know how you respect Abatachen in the same time you know what i'm saying any way Mamye give some advice for your friend Meseret Yilma. The time is not far to see our church love and peace coming back soon might be after Abatachen passed away.

   Delete
 6. ዲ. አንዷለም ስልታዊ ማፈግፈግ ላይ ነው : ተስፋም እየቌረጠ ነው :

  ReplyDelete
 7. አባ ሰላማ: ዜናውን መዘገባችሁ ጥሩ ነው። መቼም ለሕዝብ መረጃ መስጠት መልካም ነገር ነው። የሚገርመው ግን የሆነውንና ያልሆነውን አደባልቃችሁ ማቅረባችሁ ነው። ከሆነው ስትቀንሱ ካልሆነው ደምራችኋል። በጉባኤው የተገኙትን ብትፈሩ ጥሩ ነበር። ይቅር ተባባሉ ማለቱ መልካም ነው። የግለሰቦችን ስምም መጥቀስ አያስፈልግም። ከጠጠቀሰም በትክክል መጠቀስ አለበት። ለመሆኑ ይቅርታ ሲጠይቅ የሰነበተው ማነው? መልሱንእንድሰጣችሁ ከፈለጋችሁ አባ ወልደትንሳኤ ናቸው። ሌሎችም እንዲሁ ጠይቀዋል። እናንተ ይቅርታ ጠየቁ ያላችኋቸው አባትማ ይቅርታ ተጠያቂ ናቸው። አንባቢያን በሞቴ በጉባኤው የነበሩ የምታውቋቸውን ተሳታፊዎች ጠይቋቸው። በእርግጥ ሌሎች የሆኑ ነገሮችንም ጽፋችኋል። ስለዚህ በእግዚአብሔር ፊት ላለመዋሸትና የህሊናችንም እስረኛ እንዳንሆን ብንጥር ጥሩ ነው። ከዜና ምንጩ ስህተት ነው ከተባለም ማስተካከያ አድርጉበት።

  ReplyDelete
  Replies
  1. My dear friend forgiveness is for your self not for the person who betrayed. Abba Wodetensai always the first person asking forgiveness every body knows who did what.

   Delete
  2. You are right, Abba Woldetensae was the one that was asking for forgiveness, among others; not because he was guilty of anything or he sinned against anybody, but because he is following what Jesus taught him through His word. "FORGIVE THOSE THAT DO WRONG AGAINST YOU"

   READ Mathew 6:14-15
   14"For if you forgive others for their transgressions, your heavenly Father will also forgive you. 15"But if you do not forgive others, then your Father will not forgive your transgressions.

   Delete
 8. andualemi maleti eiko yemariam amilaki mariam feterechingi kemaleti yemayimelesi gudenga menafiki eiko newi yesu degree eina Doctorate ye English language chilota maregagecha kalihone besitekeri hayimanotawi eiwiketu einidehoni be-MK wochu chinikilati temetino yetesefa newi berigiti atalayi actor silehone abune melikestedekin biyatalilachewi ayidenikimi lehulumi metenikeku ayikefami eina abatochi liyasibubeti yigebali,.

  ReplyDelete
 9. መምህር ተከስተ is one of the few outstanding Orthodox Church preachers. Jesus Christ’s last words to His disciples before His ascension are instructive for all preachers for all times. He stressed at least two principal issues: (1) Jesus commanded His ministers to go to all people with the purpose of preaching the gospel (Matthew 28:18–20; Mark 16:15). (2) He stressed the need for being filled with the power of the Holy Spirit before commencing the task of preaching the gospel (Luke 24:49; Acts 1:4).መምህር ተከስተ fulfilled both principles, I personally blessing by his sermon and preaching. God Bless Him!

  ReplyDelete
  Replies
  1. There are a handful of GOD's servants that teach and preach the true Gospel to the flock as was the ministry commanded by Jesus. Deacon Tekeste is one of the few that is reaching the many for Jesus. This has been the thorn in the eyes and in the souls of the wolves in sheep's clothing, every time they hear the name Tekeste, it pokes on them so much, it is like they hear the name JESUS, it stirs their soul deep into the core of their being. Too many Sauls, too few Pauls! REPENT FOR THE DAY OF THE SECOND COMING IS AT HAND!!

   Delete
 10. tenesh ewnet safu. weshet betam beza. lemedebachew. aweknachew.

  ReplyDelete
  Replies
  1. wnedene zeme belhe yetesemahene atezebarke. weshet kale safewena egame anbabiwochu enewekew. minu new weshetu? sebesebawe altederegeme? weyes min?

   Delete
 11. ዲ. አንዷለም አዳጋ ላይ ነው

  ReplyDelete
 12. aba selamawoch minew dimtsachihu tefa sile A.A synodos tenfsu enji

  ReplyDelete
 13. The report was biased as usual. for example, it mentioned the apology of Aba Melke Tsedek incorrectly. But the main apology was from others to Aba Melke Tsedek. It didn't say anything about it purposely to mislead the readers.

  ReplyDelete