Friday, May 23, 2014

“የኮሌጁ ችግር “ረቡዕ ስለማይጾም ነው” ያለው አዲሱ አሜሪካዊ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ከኮሌጁ ተሰናበተ

Read in PDF

 • በፎርጅድ ማስረጃ ሲማር የተገኘው አንድ የማቅ አባል ተማሪም ተባሯል
ማኅበረ ቅዱሳን በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ያለውን ፍላጎት ለማስጠበቅ በተለመደ ስልቱ አስርጎ ያስገባውና በከፍተኛ ደመወዝ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ሆኖ እንዲሠራ የተመደበው ቀሲስ ኸርበርት ጎርደን የተባለው ግለሰብ ከኮሌጁ መሰናበቱ ተሰማ፡፡ ይህ በዜግነት አሜሪካዊ፣ በእምነት ካቶሊካዊ፣ በሚስቱ ደግሞ ማህበረ ቅዱሳን የሆነው ግለሰብ ማኅበረ ቅዱሳን የሰጠውን ተልዐኮ በአግባቡ ሳይወጣና የአራት ወር ደሞዙን ሳይበላ በቋሚ ሲኖዶስ ትእዛዝና እርሱም ማመልከቻ በመፃፍ የተሰናበተ መሆኑ ታውቋል፡፡
የሚገርመው ነገር የኮሌጁ አንዱና ዋና ችግር ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ እየታወቀ ለማቅ ያደረው ግለሰቡ ግን የኮሌጁ ችግር ረቡዕና ዓርብ ስለማይጾም ነው ማለቱ ለብዙዎች አስገራሚ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ምክንያቱም በትምህርትና በጥናት ላይ ያሉ ሰዎች እንዲጾሙ መገደድ የሌለባቸው መሆኑ በእስራ ምእቱ መጽሐፍ ላይ የተገለጸ ሆኖ እያለ ማቅ ግን መጽሐፉንም ይህን ማሻሻያ ባለመቀበልና መጽሐፉም እንዳይሠራጭ በመቀስቀስ ሲሰራ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በተለይም በደብረ ማርቆስ ይህ መጽሐፍ ኑፋቄ አለበትና እንዳትገዙ እያለ ሲቀሰቅስ እንደነበር ምንጮቻችን ይናገራሉ። ምንም እንኳ ፆም አስፈላጊ ቢሆንም ለአንድ ዲን ነኝ ለሚል ሰው የማይመጥን ሐሳብ አንስቶ የኮሌጁን ትልልቅ ችግሮች በአርብ ሮብ ጾም ለመሸፈን መሞከሩ ብዙዎችን ሲያሳዝን የቆየ ድርጊት ነው፡፡ ይሁንና በእነዚሁ ቀናት ማለት ረቡዕ ማመልከቻ አስገብቶ አርብ መሰናበቱ በነገሩ ግጥምጥሞሽ ብዙዎች ተገርመዋል፡፡ ማቆች ግን እንደ ተአምር ሳይቆጥሩት እንደማይቀር ብዙዎች ይገምታሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ ሲማር የነበረው “ቄስ” ደነቀ ገብረ መስቀል የተባለ ቀንደኛ ማኅበረ ቅዱሳን ተማሪ በፈጸመው የማጭበርበር ወንጀል ከኮሌጁ እንዲባረርና ስለፈጸመው የማጭበርበር ወንጀል በሕግ የሚጠየቅ መሆኑ ከተጻፈለት ደብዳቤ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የኮሌጁ ዲን በተሰናበተ በአንድ ቀን ልዩነት ኮሌጁን ሲበጠብጥና ማቅ የሰጠውን ተልእኮ ሲያራምድና እናት ቤተክርስቲያንን ሲያደማ የነበረው ተማሪ ደነቀ ገብረ መስቀል መባረሩ ተገቢና ከሕግ አንጻርም ጉዳዩ በወንጀል ድርጊት የሚያስጠይቅ ስለሆነ፣ ሌሎችን ሊያስተምር የሚችል አስፈላጊው የሕግ እርምጃ ሊወሰድበት እንደሚገባ የብዙዎች እምነት ነው፡፡ ከተማሪ ደነቀ በተጨማሪ የሚጠረጠሩና ማቅ አስርጎ ያስገባቸውና የመለመላቸው ሌሎች ተማሪዎች እንዳሉም ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡
ለእናት ቤተ ክርስቲያን ቆሜያለሁ የሚለውና በሚፈጽማቸው አስነዋሪ ተግባራት እናት ቤተ ክርስቲያንን ዘወትር አንገት ሲያስደፋ የኖረው ማኅበረ ቅዱሳን አባላቱ ፎርጅድ ማስረጃ ተይዞባቸው ሲባረሩ ይህ የመጀመሪያ አይደለም። ዘንድሮ ተመራቂ የነበረው ተማሪ ደነቀ በፎርጂድ ማስረጃ ይህን ያህል ዓመት እናት ቤተክርስቲያን ደክማ አስተምራው፣ የምግብ፣ የመኖሪያ ወጪውን ሸፍና መቆየቷ ትልቅ ኪሳራ ሲሆን በእርሱ በጀት ሕጋዊ ተማሪ እንዳይማር ማድረጉም አሳዛኝ ነው፡፡ ኮሌጁ ከዚህ ቀደም በፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ እነ መምህር ምህረተ አብ አሰፋን፣ እነጳውሎስ መልክአ ሥላሴን የመሳሰሉ ሰዎች እንዲመረቁ ማድረጉን ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ ስለዚህ ኮሌጁ በነካ እጁ ሌሎቹንም መርምሮ ኮሌጁን በፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ ማጽዳት ይኖርበታል፡፡ በቀጣይም የትምህርት ማስጃዎችን እየመረመረና በሚመለከተው አካል እያረጋገጠ ተማሪዎችን መቀበል የሚችልበት ጠንካራ አሰራር መዘርጋት እንዳለበት ምንም አያጠራጥርም፡፡
ከዚህ ቀደም በፎርጂድ ማስረጃ የተመረቁም ቢሆኑ በፎርጂድ ማስረጃቸው ፎርጂድ እስከሆነ ድረስ የትምህርት ማስረጃቸውን መሠረዝና ዲፕሎማና ዲግሪያቸውን መንጠቅ የሚቻልበት አሠራር እንዳለ ይታወቃል፡፡ በፎርጂድ የትምህርት ማስረጃ ገብተው እንዲማሩ በር የከፈተው አንዱ ሁኔታ አስቀድሞ የነበረው አሰራር እንደ አሁኑ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የብሔራዊ ፈተና ውጤት ወደ ሀገር አቀፍ የፈተናዎች ማረጋገጫ ኤጀንሲ ተወስዶ ትክክለኛ ለመሆኑ ማረጋገጫ አይሰጥ ስለነበር እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ አሁን ግን ኮሌጁ በዚህ መንገድ የማጣራት ስራ ሠርቶ ነው  ተማሪ ደነቀ የትምህርት ማስረጃ ሐሰተኛ ሆኖ ያገኘው፡፡
ማህበረ ቅዱሳን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አንገት የሚያስደፋ ታሪክ ከእለት ወደ እለት እየፈፀመ ይገኛል፡፡-በዚህ ዓይነት ከዚህ በፊት በሦስቱም የቤተ ክርስቲያን ኮሌጆች ዓላማውን የሚያስፈጽሙለት አባላቱ በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እንዳለስገባና እንዳላስመረቀ ምንም ዋስትና የለም፡፡ በተመሳሳይም በመንግሥት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለፖለቲካዊ አላማው ያስገባቸውና ያስመረቃቸው ጥቂት የማይባሉ ናቸው፡፡ ስለዚህ አሁንም ቢሆን በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ኮሌጆችና በተለይም በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የማታ መርሐ ግብር ያሉ የማቅ አባላት የትምህርት ማስረጃቸው ቢፈተሽ ጥሩ እንደሆነ መጠቆም እንወዳለን፡፡ የኮሌጁ ሊቀጳጳስ አባ ጢሞቴዎስም በዚህ አቅጣጫ እየወሰዱት ያለው እርምጃ የሚደነቅና መቀጠል የሚገባውም ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዲን የነበረውን ኸርበርት ጎርደን  መሰናበት ተከትሎ ማቅ የመለመለው፣ የእርሱን ቦታ እንዲይዝለት የሚፈልገውና በእነ ወ/ሮ ዘውዴና በእነ ቸሬ አበበ የሎቢ ሥራ እየተሰራለት የሚገኘው ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሣ በቶሎ ቢጠናና ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይከሰት ቢደረግ ጥሩ ይሆናል እንላለን፡፡

24 comments:

 1. MAHIBERE KIDUSAN IS NOT LIKE U R SAYING!

  ReplyDelete
 2. God is Great!!! Gena ye MK YETEBELASHE taric yewtal!!!!!! Aba selaman
  thankyou Enlalen.

  ReplyDelete
  Replies
  1. አዎን ይውጣ

   Delete
  2. Amazing! The collaboration between protestants and thieves and wizards in EOC is not yet clear to mahiber kidusan even. MK, please know that there are people serving in EOC who work deliberately and sometimes due to lacking know-how for protestants.

   Protestants are devil's troops. That is why they do cheat to 'preach.' They are protestants but use the name aba selama for this website.

   Leba bicaha!

   you are fighting not against MK but against God and saints. Lusifer, don't you know how many saints defeated you!

   Delete
 3. kolajochi wede sera MK wede mekera!
  kolajochi wede keber MK wede hasar!
  kolajochi wede ewnet Mk wede haset!
  kolajochi wede kristos Mk wede dyablos!!!!!!!!

  ReplyDelete
 4. ይህንንስ እንኳን ሰው ሰይጣንም አያውቀውም አይጠራጠረውም ፤ ክፉ ክፉን ለማኅበረ ቅዱሳን ስትሰጡ ክፉዎች ሆናችሁ ቀራችሁ ማኅበረ ቅዱሳን ግን በቅዱሳን ጸለትና ልማና መእግዚአብሐየር ቸርነት መልካም የሆነውን አገልግሎቱን ይቀጥላል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አሁን ይሔ ምን አይነት አስተያየት ነው። ማኅበሩ ጣዖት ካልሆነብህ በቀር የሰራውን ስህተት ስህተት ነው ብሎ መቀበል ያስፈልጋል። እውነተኛ የማህበሩ ወዳጅ ከሆንክ ይሄን አድርግ

   Delete
  2. መናፍቃን አሁን በእናንተ ቤት ኦርቶዶክሳዊ ሆናችሁ እና ለዚህች ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ናችሁ ብሎ ህዝበ ክርሰቲያኑን ያታለላችሁ መስሏችሁ ከሆነ በእውነት ተታጅላችኋል፡፡ መሐል አዲስ አበባ ባማረ ቤትና መኝታ ሆኖ የሚማረው መንፈሳዊ ኮሌጅ ገብቶ ተምሮ ኋላም ህዝበ ክርስቲያኑን አርዓያ ሆኖ ወንጌልን ሊሰብክለት የሚማር ተማሪ በትጋቱ እንዳይጎዳ እንዳይጾም የሚያዝ መጽሐፍ አወጣችሁልን እና ማኅበረ ቅዱሳን ደበቀው ስትሉ ትንሽ እንኳን ሀፍረት አይሰማችሁም? ሰውን ባትፈሩ ፈጣሪን አትፈሩም? እርግጠኛ ነኝ በፈጣሪ መኖር ስለማመናችሁ ጥያቄ አለኝ፡፡

   Delete
 5. wedeme yargeseh mk.

  ReplyDelete
 6. እልልልለልልልልልል ውይ አጭበርባሪውና የትቅል ጸር የሆነው ማቅ እንዲህ መጋለጡ ደስ ብሎኛል

  ReplyDelete
 7. ኧረ ተዉ እናተ ቢስተዋል ይሻላል። ማኅበሩ ዕኮ ከሰው ጋር መዋል ጀምሯል።
  ሌላው አካል የጓዳ ሆኖ እንዳይቀር ያስፈራል። እናም ይታሰብበት (ኀሊ ቅድመ ትንብብ)

  ReplyDelete
 8. Abet difin tilacha yiluhal yihe new .Aba selamawoch lemehonu betekrstiyanua baluat kolejoch gebtew yemimarutn dekemezamurtoch yemimelemlew MK new? ene eskemawukew dires beye wereda beteknet behagere sibket etc eyetemelemelu new yihen keyet amttachihu ke MK gar endagenagnachihu yigermal.


  ReplyDelete
 9. Hi aba selama temari Denke be haset ye temhert masereja tesenabet!!!
  "KESNAWS" Ye Haset mehonu kolaju beyatara! bezuwachu the M.k diacons, priests, monks,and bishops are real forged!!!

  ReplyDelete
 10. weye mk min eyehoneseh new are bakeseh rasehen ateri. yaderebeshe menfese eko asacena sache newe. yihe hule wesetena maceberebere mon yadegelacehuwal? mk yitadese

  ReplyDelete
 11. ye Hara zegabi menew sele forged sinesa meshesheg!!
  MENEW ende aba selame lehager ENA le Betekrstian yematkomi blog!! ende dejeslame letzegi mehonu EWEKIi!!! BLOG HARA WEDE MEKERA

  ReplyDelete
  Replies
  1. What? Ante jilajil aba selama blog new lehager ena lebetekirstiyan yekomew? Wey alemawok! Betekiristiyann lematfat qorto yetenesaw man honena geta ayine libunahn yabralh

   Delete
 12. lehul gez seat weket alewu. Thanks to our Lord God for his great work.Nothing hiding from God eyes. The truth is never died. O MK how long do you cheat and play game behind of our church? Thank you Aba Selam.for good and truth info.

  ReplyDelete
 13. በአንድ ድንጋይ ሶስት ወፍ ለመምታት መሞከር!!
  በዚህ ዘገባ ሶስት ዒላማዎችን ለመምታት ተሞክሯል፡ (1) ሥርዓተ ጾምን ማፋለስ፣(2) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታሪክ ከልደተክርስቶስ እስከ ፳፻(2000) ዓ.ም የሚለውን በሚሊኒየሙ በታላላቅ ሊቃውንት የወጣ መጽሐፍን ማስጠላት፣(3)ማኅበረቅዱሳንን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ማጥቃት፡፡
  መጽሐፉን ያነበበ ሰው ግን ከሶስቱም ስህተቶች ይተርፋል፡፡መጽሐፉ ግንቦት 7 ቀን 1961 ዓ.ም በቅ/ሲኖዶስ ስለአጽዋማትና በዐላት አከባበር መመሪያ(ቀኖና) እንዲወጣ ትእዛዝ ተሰጥቶ ጥናት ቀርቦ የነበረ ቢሆንም ጥናቱ ተግባራዊ እንዳልሆነ የሚያመላክት እንጅ መጽደቁን አያሳይም፡፡
  ይኼው ሙሉ ንባቡ ከገጽ 36 ጀምሮ……
  “ግንቦት 7 ቀን 1961 ዓ.ም በተደረገው ቅ/ሲኖዶስ ስለአጽዋማትና በዐላት አከባበር መመሪያ የሚሆነውን ጽሁፍ
  -ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ
  -ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
  -ብፁዕ አቡነ አብርሃም
  -ክቡር ንቡረ ዕድ ድሜጥሮስ ገ/ማርያም እንዲያዘጃጁ ታዘው አቅርበዋል፡፡
  …….በጥናቱ መሰረት 7ቱን አጽዋማት ለመጾም ቦታና ጊዜ ለማይፈቅድላቸው (1) ለፖሊስና መከላከያ ሠራዊት አባላት፣(2)ለመንገደኞች፣(3)ለፋብሪካ ሰራተኞች፣(4)ከፍተኛ ጥናት በሚጠይቅ የት/ት ገበታ ላይ ለሚገኙ ተማሪዎች ከጥሉላት ምግብ በቀር ጠዋት ቁርስ ቢበሉና ሻይ ቢጠጡ ….
  በጊዜው… ቅ/ሲኖዶስ ይህን አስተያየት ተመልክቶ…. ጉዳዩ ካህናቱን ብቻ ሳይሆን ሕዝበ ክርስቲያኑንም በቀጥታ የሚመለከት በመሆኑ ይኸው ተጠንቶ የቀረበው ሓሳብ በጋዜጦች፣በሬዲዮና በቴሌቪዥን ከተገለጠ በኋላ ሕዝቡ ይተችበት የመጨረሻውም ውሳኔ የሚደረገው የቤ/ክ ሊቃውንት መምህራንና ካህናት ምዕመናንም አውቀት አስተያየታቸውንና አሳባቸውን ከገለጡበት በኋላ ይሆናል በማለት ተስማምቶ እንደነበር የሚገልጥ ጥናት አለ፡፡……”
  ስለዚህ ከላይ የቀረበው ጽሁፍ የሚያሳየው ረቂቅ ጥናት እንጅ የቅ/ሲኖዶስ ውሳኔን አይደለም፡፡እናንተ ግን ለዒላማዎቻችሁ መምቻ ያመቸናል በሚል መልኩ መቆንጸሉን ሙያ አደረጋችሁት፡፡የእናንተስ ይሁን ይበልጥ የሚያበሳጨው እናንተ የቆነጸላችሁት መጽሐፍ ሁሉ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ እንደሆነ ለመደምደም የሚፋጠኑት ያሳዝናሉ፡፡አንብቦ ከመናገር ይልቅ ገምቶ መፈረጅ ነውር ነውና ኦርቶዶክሳዊ ነን የምንል ሰዎች መጽሐፉን ሳናነብ ሌላው በራሱ መንገድ ቆንጽሎ ስላቀረበው ብቻ የእኛ አይደለም ለማለት መሯሯጥ ነውር ነው፡፡ማኅበሩም ቢሆን በየልሳናቱ መጽሐፉን ለማጣቀሻ ከመጠቀም በቀር እንዳይሸጥ ሲያጥላላ አላየንም፡፡ማኅበሩ መጽሐፉን ተቃወመ መባሉ ሐሰት ነው፡፡ስለሆነም ሰዎች የያዝነውን ለማስጣል ሲሞክሩ ለመጣል መሞከር ያለጦርነት በቆረጣ መማረክ ነው፡፡ወይም ርስትን መልቀቅ ነው፡፡እንዲህ ከሆንማ ነገ ደግሞ ድጓውን ጠቅሰው የእኛ ነው ሲሉ ድጓውን ልናጣጥል ነው፡፡
  ወደ ጥናቱ ዘገባውና ጥናቱ ስንመለስ፡ የቲዎሎጅ ተማሪዎች ከዐለማዊው ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሆነ ከአብነት ተማሪዎች በተለየ መልኩ ከፍተኛ ጥናት የሚጠይቅ ትምህርት ውስጥ ናቸው ማለት አይቻልም፡፡ስለሆነም የቲዎሎጅ ደቀመዛሙርት አይጾሙም የሚለው ዘገባ አጠራጣሪነት እንዳለ ሆኖ አንዳንድ የሚሽሩ ካሉም ገና ባልጸደቀ ጥናት ተሳቦ ጾም የሚሽሩበት ምክንያት የለም፡፡ከሚጠብቃቸው ኃላፊነት አንጻርም ይሄ የሥርዓት ጥሰት ከእነሱ አይጠበቅም፡፡እንዲህ አይነት ሰበብ እየፈጠሩ ጾምን የማስገደፍ አካሄድ ከምዕመናኖቿ በአብላጫው በግብርና ተሰማርቶ ለሚገኘው ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ነገ ደግሞ ገበሬውም ከተማሪና ከፋብሪካ ሰራተኛ በባሰ መልኩ ስለሚለፋ ሊጾም አይገባም ወደሚል አፍራሽ መንገድ ወስዶ እንደተቋም ስርዐተ-ጾምን ስለሚያናጋ መበረታታት አለበት ብየ አላምንም፡፡


  ReplyDelete
 14. YOU ARE NOT CORRECT ,MK HAS NO SUCH TRASH OBJECTIVE LIKE YOUR FRIENDS.THE PROTESTANT WE WILL CONTINUE FOR THE FLOWERINESS OF ORTHODOX TEWAHIDO FOR EVER..........GOD IS WITH US.

  ReplyDelete
 15. HODAM HULU LEMIN ZIM BILACHIHU ATIBELUM??????

  DIROM DIYABILOS YADEREBET SEW SIBELANA SITETA KEMEWAL BEKER LELA MIN YAWUKAL. KE GETA YEHONE SEW ENDEGETA HAWARIYAT YISTOMAL.

  HOD AMLAKU YEDIYABILOS LIJI HULA

  ReplyDelete
 16. Oh, paulos merew (dukla )the turist buden
  Oh, mehretab (felflu the london)
  Gezeh kerbal be forged letetaden
  Ke coIIege endetesenabetw Dean
  The semu Harebert Gorden
  YE MK RESA YE 4 KILO BEDEN!!!!

  ReplyDelete
 17. Mk seraw eyeseranew.yenanet ende gedel mameto machoh kabatach 666 yeweresachet new.viva mk

  ReplyDelete
 18. ማህበረ ቅዱሳንን ለቀቅ አድርጉት.. ወሬኛ ሁሉ..

  ReplyDelete