Tuesday, May 27, 2014

ይድረስ ለእሕታችን ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ

Read in PDF

የአምላካችን የክርስቶስ ሰላም ይድረስሽ! በእግዚአብሔር መንግሥት የተጠራነው መጀመሪያ ለመዳን ነው ከዚያም እርሱንና የፈቃዱን ምሥጢር በማወቅ እንድናገለግለው ነው። አገልግሎት ሰው ሲያደርግ አይተን የምናደርገው፣ ለከንቱ ውዳሴ ወይም ለጥቅምና ለዝና የምናደርገው ነገር አይደለም። እግዚአብሔር ስላደረገልን መልካም ነገር የምንሰጠው ምላሽ ነው እንጂ። ስለዚህ አስቀድመን እርሱን ማወቅ ይገባናል። ጥሪው ሲደርሰን ደግሞ እሺ ብለን ባሰማራን እና በወሰነልን ሁኔታ በፍርሐትና በመንቀጥቀጥ ልናገለግለው ይገባል።
  የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያስጠነቅቀን ማንም ተነሥቶ አስተማሪ ወይም ተናጋሪ እንዳይሆን ነው። "ወንድሞች ሆይ ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃላችሁና‚ ይላል ያዕ 3፥1። በሌላ ሥፍራም "ማንም ሰው የሚናገር ቢሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር የሚያገለግልም ቢሆን እግዚአብሔር በሚሰጠኝ ኃይል ነው ብሎ ያገልግል ክብርና ሥልጣን እስከ ዘለዓለም ድረስ ለእርሱ በሚሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ‚ ይላል 1ጴጥ 4፥11። በዚህ ቃል መሠረት ሁሉም አስተማሪ ሊሆን አይችልም ካስተማረም እንደ እግዚአብሔር ቃል ብቻ መሆን አለበት፤ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይከብር ዘንድ የሚለውን ቃል እናስተውለው። 


አንቺ በውኑ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ በመዝሙሬ ከብሯል ብለሽ ታስቢያለሽ? ክብሩን ለሌላ አልሰጠሁም ትያለሽ?  እኛ ይህን ጽሑፍ የጻፍንልሽ በመዝሙርሽ ውስጥ እግዚአብብሔር በነገር ሁሉ ሲከብር ማየት ባለመቻላችን ነው ይልቁንም የእግዚአብሔርን ሥልጣንና እርሱ ብቻ ሠርቶ የሚከበርበትን ለሌላ ስትሰጪ የሚያሳይ መዝሙር አገኘን። አንዳድ ጥሩ መዝሙሮች አሉሽ ግን በዚያው ባንዱ ሲዲ ውስጥ ቀላቅለሽ ስታመልኪ ትሰሚያለሽ፤ ይህ ከጌታ መንፈስ ነው ወይስ ከራስሽ አእምሮ ወይስ ከሰይጣን? እስኪ ራስሽን መርምሪና እንደገና እግዚአብሔር በምሕረቱ እንዲያስብሽ ይቅርታ ጠይቂው። እራስሽን ለማየት ይረዳሽ ዘንድ ከዘመርሽው መዝሙር ለምሳሌ አንዳዶችን እንጠቁምሽ፣
 ከሊባኖስ ከልጅስ ጋራ ነይ፤
እመ አዶናይ ከሊባኖስ ወደ እኛ ነይ፣
ጥበቃሽ ዘወትር እንዳይለየኝ፣ ከሊባኖስ---
በሄድሁበት ሁሉ ማረፊያ ሁኚኝ፣
  እኔን ባሪያሽን ድንግል አትርሽኝ፣
በጽድቅ ሰሌዳ ስሜን ጻፊልኝ፣
    ነፍሴና ሥጋዬን አደራ እልሻለሁ፣
በልጅሽ ጽኑ ፍቅር ተማኝጽኜሻለሁ፣
    ከመሞቴ በፊት ለንስሐ አብቂኝ፣
ለነፍሴ ማረፊያ አዘጋጅልኝ፤
  ከአንበሶች መኖሪያ ከነብሮች ተራራ፣
መጥተሽ አስደስቺኝ እህቴ ሙሽራ፤
  የልብስሽ መዓዛ የሊባኖስ ሽታ፣
ሮማን ናርዶስ ነሽ እናቱ ለጌታ፤
  እመቤቴ ስልሽ ስምሽን ስጠራ፣
ፈጥነሽ ድረስሺልኝ ከቅዱሳን ጋራ፤
ከሚካኤል ጋራ ፈጥነሽ ድረሽልኝ ከገብርኤል ጋራ።

(ያሬድ አዳመ ካሳተመው ቁጥር አንድ የመዝሙር መጽሐፍ የተወሰደ ገጽ 18-19)
እያንዳዱን አባባልሽን ሕያውና እውነት ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃል ጋር እናስተያየው።
"ከሊባኖስ ከልጅስ ጋራ ነይ፤
እመ አዶናይ ከሊባኖስ ወደ እኛ ነይ‚
እመቤታችን በሊባኖስ መወለዷን ትውፊታችን ይናገራል። አሁን ግን እርሷ በሊባኖስ የለችም እርሷ በአጸደ ነፍስ በሰማይ አለች፤ ለምን ወደ ሊባኖስ ሄድሽ? ከመኃልየ መኃልይ መዝሙር ወስደሽው እንደሆነ እንገምታለን ያንን መዝሙር ለማስታወስ ነው ካልሽን እንስማማለን እኛም በስብሐተ ነግህ ሁልጊዜ እንዘምረዋለን። ወደ እኛ ነይ ስትይ ግን ምን ማለትሽ ነው? ወደ እኛ መምጣት ካለባት አሁን ካለችበት ከዚያው ከሰማይ እንጂ ከሌለችበት ከሊባኖስ ለምን ነይ አልሻት? ሌላ ጥያቄ የማርያም መምጣት ግን ለምን አስፈለገ? ከልጅሽ ጋራ ነይ ብለሻል፤ ልጇ ወደ አንቺ ከመጣ አይበቃሽም ወይ? ማንኛውንም ጥያቄሽን ለመመለስ እርሱ ታማኝ ነውና። ጌታ "እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከናንተ ጋር ነኝ‚ ብሏል ማቴ 28፥20 ። እኔና እናቴ ካናንተ ጋር ነን አላለም፣ ጌታን ካመንሽው ሁልጊዜ ካንቺ ጋር ነው። ታዲያ ይህን ቃል ለምን ተጠራጠርሽው እርሱ እኮ እንደቃሉ ነው የሚሠራው! ጌታ ሲመጣ ከማን ጋር እንደሚመጣ በቃሉ ተናግሯል እንዲህ ሲል "የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን በእርሱም መኖሪያ እናደርጋለን‚ ዮሐ 14፥23። ጌታችን የሚመጣው ወደሚወደውና ቃሉን ወደሚጠብቅ ነው ሲመጣም ካባቱ ጋር ብቻ ነው። እናም ማርያምን ነይልኝ ማለትሽ ትክክል አይደለም የሚያስፈራሽ ነገር ካለ በእርሱ እመኚ እርሱ ጋንቺ ጋር ነው።
"ጥበቃሽ ዘወትር እንዳይለኝ፣
በሄድሁበት ሁሉ ማረፊያ ሁኚኝ
ጥበቃሽ ዘወትር እንዳይለኝ ስትይ ምን ማለትሽ ነው? ጠባቂሽ ማን ነው? ዳዊት "እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው‚ ይላል መዝ 23፥1 ሲዘምርለትም "እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው በእርሱም እታመናለሁ ጋሻዬና የርድኤቴ ቀንድ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ መድኃኒቴ ሆይ ከግፍ ሥራ ታድነኛለህ‚ እያለ ነበር 2ሳሙ 22፥3 በመጨረሻው ዘመን ለተገኘነው ለኛም ሥጋን ተዋሕዶ መልካም እረኛ የሆነን የድንግል ማርያም ልጅ ኢየሱስ ነው።"መልካም እረኛ እኔ ነኝ፣ መልካም እረኛ ነፍሱን ስለበጎቹ ያኖራል‚ ብሏል ዮሐ 10፥11። የዕብራውያን ጸሐፊ "በዘለዓለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ ለርሱ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ክብር ይሁን አሜን‚ ይላል ዕብ 13፥20።
  ኢየሱስ ክርቶስ በዘለዓለም ደሙ ትልቅ እረኛችን ነው ለዳዊት መሸሸጊያ እና መጠጊያ ጋሻ የሆነው ጌታ ለኛም በደሙ የሚሸፍነን ትልቅ እረኛችን ሆኗል። ታዲያ አንቺ ማርያምን ጠብቂኝ እያልሽ የምትጮሂው የክርስቶስን ጥበቃ ንቀሽ ነውን? ወይስ ተጠራጥረሽ? ወይስ ሁለቱም ካልጠበቁሽ ደህንነት አይሰማሽም? የትኛው ሰው ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ የሌሎችን ጥበቃ ሲማጸን ያነበብሽው?
  በሄድሁበት ሁሉ ማረፊያ ሁኚኝ ያልሽውም ትክክል አይደለም። እግዚያበሔር ማረፊያ ነው። ወደ እረፍት የሚመራም እርሱ ነው "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው በለመለመ መስክ ያሳድረኛል በእረፍት ወሃ ዘንድም ይመረኛል ‚ ይላል ዳዊት መዝ 23፥2 ውሃ የተባለው የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። ሰው ከእርሱ ሲጠጣ ያርፋልና። አምላካችንም "እረፉ እኔም አምላክ እንደሆንሁ እወቁ‚ ይላል መዝ 45፥10። እግዚአብሔር ብቻውን አምላክ እንደሆነ ብታውቂ ታርፊ ነበር። ሁለት ማርፊያ የለም። ስለዚህ እህታችን በአንዱ አሳራፊ በክርስቶስ እረፊ።
"እኔን ባሪያሽን ድንግል አትርሽኝ፣
በጽድቅ ሰሌዳ ስሜን ጻፊልኝ‚
  ይህ ከሁሉም በጣም የሚያሳፍር ግጥም ነው። እኔን በሪያሽን ድንግል አትርሽኝ ብለሻል። እናታችን ማርያም እኔ የጌታ ባሪያው ነኝ ስትል ትሕትናዋን አሳይታናለች ከዚህ ባሕርያዋ አንጻር እንቺ የርሷ ባሪያ መሆንሽን አትቀበለውም የልጇ ባሪያ ብትሆኚላት የበለጠ ደስ ይላታል። በክርስቶስ ብታምኚ ስምሽ በሕይወት መጽሐፍ ይጻፋል እርሱ አይረሳሽም፤ ስማችን በጽድቅ ሰሌዳ የሚጻፈው በእርሱ በመለኮት እንጂ በማርያም አይደለም። ስሜን ጻፊልኝ ስትይ የመለኮትን ስልጣን ለማርያም መስጠትሽ ነው እህቴ እንዴት እንደተሳሳትሽ ማን  በነገረሽ? በታረደው በግ ያመኑ ሁሉ ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ የተጻፈ ነው በዚህ የሕይወት መጽሐፍ ደግሞ ማንም ጣልቃ የማይገባበት የመለኮት ሥራ ነው። ራእ 21፥27። ይህ ግጥም ከባድ ክህደት የሚገኝበት ነው። በጣም ያሳዝናል
"ከመሞቴ በፊት ለንስሐ አብቂኝ፣
ለነፍሴ ማረፊያ አዘጋጅልኝ‚
ከመሞቴ በፊት ለንስሐ አብቂኝ የሚለው ግጥምሽ ከባድ ስሕተት አለበት። ከመሞትሽ በፊት ንስሐ መግባት እንዳለብሽ ማወቅሽ ጥሩ ነገር ነው ምክንያቱም ከሞት በኋላ እነክርስቶስ ሰምራን የመሳሰሉ ጻድቃን ከሲዖል ያወጣሉ የሚለውን የስሕተት ትምህርት ወይም ተዝካርና ዓመታት ደግሰው ደብተራ ስላበሉ ከሲኦል ወደ ገነት መዛወር አለ ብለው የሚያምኑ ሰዎችን አለመቀበልሽ ጥሩ ጎንሽ ነው።ነገር ግን ለንስሐ የሚያበቃ እግዚአብሔር ነው እንጂ እናታችን ማርያም አይደለችም። መንፈስ ቅዱስ ለልድያ እንዳደረገላት ልብን ሲከፍት የሚመጣ የሕይወት ለውጥ ነው ንስሐ። ይህን ለውጥ ያለ መንፈስ ቅዱስ ማን ሊሰጥ ይችላል? "እንኪያስ እግዚአብሔር ለአሕዛብ ደግሞ ለሕይወት የሚሆን ንስሐን ሰጣቸው እያሉ እግዚአብሔርን አከበሩ‚ ይላል ቃሉ የሐዋ 11፥18። ስለዚህ ማርያምን ስትጠብቂ ጌታ በሩ ላይ ቆሞ እያንኳኳ ነውና በርሽን ክፈችለት እርሱ የሕይወት ንስሐን ይሰጥሻል። አንቺ ንስሐ የምትይው አርባ ጊዜ ሰግዶ መመለስን ከሆነ እርሱንስ እነ መምህሬ እንደሻውም ይሰጣሉ።
  ለነፍሴ ማረፊያ አዘጋጅልኝ ብለሻል፤ ወይ ጉድ! ጌታ ወደ አብ እንደሚሄድና ማረፊያ ሥፍራ እንደሚያዘጋጅልን ዳግመኛ መጥቶም ወደ እርሱ እንደሚወስደን ቃል ገብቷል። ዮሐ 14፥3። ታዲያ ጌታ ያዘጋጀው ሥፍራ እያለ ሌላ ምን አስፈለገሽ? በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ ይላል ከዚህ ሁሉ መኖሪያ ላንቺ የሚሆን ጠፍቶ ነው? ማርያምን አዘጋጂ እያልሽ የምትለምኛት? ወይስ ወደ ግሸን የምትሔጂ መሰለሽ? ወደ ግሸን ሲሄድ ቦታ እንደማይገኝ አውቃለሁ ስለዚህ አስቀድመን በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ቦታ አዘጋጁልን ብለን እንናግራለን? ካልተገኘም የራሳችንን ድንኳን ይዘን እንሄዳለን። መንግሥተ ሰማያት ግን ግሸን አይደለም ላመኑት ሁሉ የሚበቃ ቦታ ነው ያለው።
እህታችን ሆይ! እንዲህ ዓይነት መዝሙር የምትዘምሪው አንቺ ብቻ አይደለሽም፣ በአምሳለ በለስ ረገማ ለኃጢአት እንደተባለው ባንቺ በኩል ዘማሪዎቻችንን ሁሉ መገሰጻችን ነው እንጂ። ሆኖም ያንቺና የእንግዳ ወርቅ መዝሙር  አገር ያጠፋ ነው። ባንቺ መዝሙር የተሳሳተው ሰው ብዙ ነው አንቺ ንስሐ ብተገቢና ይቅርታ ብትጠይቂ የተሳሳተው ሊመለስ ይችላል። ሰውን ከማሳሳት የወፍጮ ድንጋይ ባንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር መስጠም እንደሚቀል ጌታ ተናግሯል። ማቴ 18፥4። በገላትያ ም 6 ቁ 7 ላይ "አትሳቱ እግዚአብሔር አይዘበትበትም‚ ይላል። ለጥቅም እና ለሰው ስሜት እየተባለ የሚገጠም ግጥምና የሚካሄደው እልልታ ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ መዘበት ነው። እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ማርያም አደረገችው እያሉ መዘመር መዘባበት ነው። እናም በዚህ ትውልድ ላይ ለሚመጣው እርግማን አንቺም ተጠያቂ ነሽ፣ የጥንት ደብተራዎችን ዕዳ ከፍለን ሳንጨረሽ ሌላ ዘመናዊ ከሃዲ ደብተራዎችን ስናይ በጣም እናዝናለን። ስለዚህ ንስሐ እንድተገቢና ቤተ ክርስቲያኒቱን ይቅርታ እንድትጠይቂ ስንል ስለእኛ በተሰቀለው ስም እንማጸንሻለን።
                              ተስፋ ነኝ


85 comments:

 1. Responsible comment. May God Bless You. I am waiting for her response. "Dej tenahu koyichie kidane mihretin yemilew ye Engida Work mezmurs?"

  ReplyDelete
  Replies
  1. I don't have to go past end of 3rd paragraph. And I must ask, let me hear how you would put your spiritual songs and see how you put the words. Its easy to see someones fault. I turn everything you have, I mean head to toe into the ugliest thing you ever saw, the worst thing you ever heard. For a starter how about this: You are not "ተስፋ". the only ተስፋ is God, You cant say ተስፋ ነኝ. Just check your EGO! how about?

   Delete
 2. ayi mekari dinkem dibilos tesifa ayikoritm ayi tsefa

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማንም እነ ጳዉሎስ ከሰበኩት ወንጌል ዉጭ ከሰበከ የተረገመ ይሁን፡፡ ተስፋ ጌታ እግዚአብሔር ይባርክህ ሁሉንም ከቃሉ መሰረት ስላደረክ፡፡

   Delete
 3. Ersua yezemerechew ke tenbite Daniel wesda new.fantu anten tesma weys Nebiyu Danielen?anten kemetesema bebiyun betesema teru new.Daniel 10:25"be ewunet metsehaf yetetsafewun enegrehalehu:ke aleqachihu ke Mikael beqer manem ayatsenagnem".ezih lay Egziabheren kade malet new be ante tergum.endezihum,Fantu lek ende tenbite Daniel"ke Dengel Martam wuchi manem ayatsenagnim ayitebeqegnim alech.menafiq malet menfeq(6 wer),gemash yizo teguaj,kelay yalkew andandu tekekel,gemashu gen wushet new;lenafiq endezih new yemiamenew.Melaeket eregnochachen nachewna.yihenem ked,Egziabher metebeq eyechale,Mela'ekten tebaqi eregna endaderege hulu,qedusanem ersu qetetawun messmat eyechale benersu bekul tselotzchenen yisemal,leljachewunyiqebeleal.yihenen new meqebel yaqatachihu.

  ReplyDelete
 4. ወንድሜ ተስፋ በእውነት ይህን በቃሉ ተመስርተህ የሳትነውን ለመመለስ የምታደርገውን ሙከራ የሰማይ አምላክ ዋጋህን በእጥፍ ይክፈልህ፡፡ ለእታችንም ቸሩ ጌታ ማስተዋልን ይስጥሽ፡፡ እባካችሁ ቃሉን ብቻ እንዘምረው ቃሉን ብቻም እንጸልየው እዳ እንዳይበዛብን!!!!!! እባክሀ ጌታ ሆይ ለሕዝባችን ዐይኖቹን ክፈት፡፡ ስለ ስምህ ስትል!!!!!!!!!

  ሰላም ነኝ

  ReplyDelete
  Replies
  1. yante hawaria tesfa, tesfa lerasu yemayawq new

   Delete
  2. ay alemastewal.....ye dabilos lij bicha...ye chele lijoch.....tarikin anbibu....tseliyu......protestants influence is not good. they believe in false jesus,,,,,,prove it after coming to the true church, eotc. ante yeseytan ageligay post endematadergew awukalehu.....yedabilos lij bicha....negerin yemtatamimu....dedeboch

   Delete
  3. if one there is a true and genius christian, he will write on songs influenced by satan protestants. songs prepared for jesus in first person singular possessive pronouns(my, mine) are wrong. saying yene geta or getaye....is wrong. songs like these have come since the time protestant songs has begun flourishing. you could find no song before that time in first person singular possessive pronouns. this expression is linked to protestants teaching that 'accept jesus as your personal/ private savior.' this teaching is the same as saying God has not saved all human beings or Adam. Jesus is king of every human being. He saved human kind. Please.............................even known singers of EOC correct your songs......prepare songs to be sing by mass/congregation. haven't you seen hoe much your new songs are difficult to seen in congregations? please know history and Christianity. God bless EOC, the true phase!!!!! Down with the false jesus....

   Delete
 5. አይ ሰይጣን የማትመጣበት መንገድ የለህ ደግሞ በዚህ መጣህ
  ጸሃፊዉ እግዚአብሄር ልቦና ይስጥህ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከዚህ በላይ አሳዛኝ ክህደት ምን አለ???

   እግዚብሄር አይናቸውን ይክፈት
   ሰይጣን የአምላካችንን የወንጌል ቃል በልባችው እንዳያሥተወሉ፡ በአእምሮአቸው እንዳያስቡ በእንግዳ ትምህርተ አሳወራቸሀው!!አምለክ ይርዳቸው
   ጻሃፊው በእረገጥ በወንጌሉ ቃል እየመዘነ፤አቅርቦታል፡፡በዚህም መሰረት የእግዚያብሄርን ቃል የሚቃረን ፡ የአጋንነዌም ተቀዋሚው ፀረ-ክርሰቶስ በረቀቀ ዘዴ የተጠቀመበት ዘፈን ነው፡፡
   በጭፍን ከመቃወም ይልቅ ልክ ፀሃፊው እንዳብራራው ቁጥርና ምዕራፍ አየጠቀሳችሁ አስረዱንና እንስማችሁ????? አረ ባካችሁ ተረት ይብቃ ክረሰቶስ በሙላት ይሰበክ!!!!
   አባ ስላማዎች እግዜአብሄር አብዝቶ ይባረካቸሁ!!!

   Delete
  2. እመቤታችንን ከልጅሽ ከወዳጅሽ ጋራ አትምጪ አንፈልግሺም ልጅሽ ብቻ ይበቃናል ብሎ መናገር ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን እጅግ በጣም አሳፋሪና ዘግናኝ ከመሆኑም በላይ "ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል" ሉቃስ ፤ምዕ 1ቁ48-49 ብላ የተናገረችውን መካድ ይሆናል ።ይሄ አካሄድ ደግሞ በቀጥታ ከሰይጣን ነው። ለነገሩ እመቤታችን ከልጇ ጋር በመጣች ጊዜ እኮ ነው ውሃው ወደ ወይን ጠጅ የተለወጠውና በዚህም የተ አምሩ መጀመሪያ አድርጎ ስሟንና ክብሯን የገለጸው።ዘማሪ ፋንቱ የዘመረችውን መዝሙር በኦርቶዶክሳዊ ዓይን እያየንና እየሰማን ቢሆን ኖሮ በእውነት ለበረከት ይሆነን ነበር አሁንም በሰላም ንኢ እያልን እመቤታችንን መጥራት አናቋርጥም ላንተም ፍቅሯን እንድታሳድርብህ እንጸልያለን።

   Delete
  3. አረ ሰላማችሁ ይጥፋ አባ ሰላማ ምነድን ነው በውነት ይህ የሰይጣን ብሎግ ነው ላማንኛውም የሰይጣን ማህበርስ ተጀምሮ የል እንዴ በናንተ ሰፈር እስኪ እነዚህን የመፅሐፍ ቅዱስ ቃል አብራርታችሁ ንገሩኝ ፋንቱ በእወነት ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊት ነች ስም አታጥፉ እናንተ ስም አጥፊወች ፡፡   Delete
  4. ማንም እነ ጳዉሎስ ከሰበኩት ወንጌል ዉጭ ከሰበከ የተረገመ ይሁን፡፡ ተስፋ ጌታ እግዚአብሔር ይባርክህ ሁሉንም ከቃሉ መሰረት ስላደረክ፡፡

   Delete
 6. yemin tesfa nehi, muticha
  yematreba tehadiso menafik

  ReplyDelete
 7. Tesfa you must be satan yourself. God bless Fantu keep it up we love you.

  ReplyDelete
 8. bado chenekelat new yaleh! keshem

  ReplyDelete
 9. Abizito yibarikih stegawini yabizalih wenidime le-eihtachinim Masitewaluni yadilati

  ReplyDelete
 10. yemahebere kedusanen sem matefat sew senekabache degemo endhe gemrache nege degemo men tameto yehon maferyweche

  ReplyDelete
 11. ለአባ ሰላማ!
  በመጀመሪያ ይህ አስተያየት "ወደ እኛ መምጣት ካለባት አሁን ካለችበት ከዚያው ከሰማይ እንጂ ከሌለችበት ከሊባኖስ ለምን ነይ አልሻት?" የእግዚአብሔርን ቃል የተከተለ መልስ ነው??? ለምሆኑ ይህንን የእግዚአብሔር ቃሎች ያጤነ ነው?
  1ኛ / 13 " ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው "። ዩሐ. ም3፡ 13
  2ኛ/ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ትንሳኤን አይታለች? ከሆነም ለምንድን ነው የትንሳኤ በኩር ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ብሎ መጽሀፉ የሚያስተምረን?
  20 " አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል "። 1ኛ ቆሮ. ም15፡ 20
  51-52 " እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበት ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ እኛም እንለወጣለን "። 1ኛ ቆሮ. ም15፡ 20
  የእግዚአብሔር መንግሥት በምድር ላይ እንድምትመስረት ያውቃሉ????
  3ኛ / 9-10 " መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል፥ ታርደሃልና፥ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፥ በምድርም ላይ ይነግሣሉ እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ "። ዩሐ. ራ. ም5፡ 9-10
  4ኛ / 27፤ " መንግሥትም ግዛትም ከሰማይም ሁሉ በታች ያሉ የመንግሥታት ታላቅነት ለልዑሉ ቅዱሳን ሕዝብ ይሰጣል፤ መንግሥቱ የዘላለም መንግሥት ነው፥ ግዛቶችም ሁሉ ይገዙለታል ይታዘዙለትማል "። ዳን. ም7፡ 27
  ስለዚህ ከእግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ትንሳኤን ያየ አል ብሎ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሀፍ ቅዱስ ያስተምረናል። ነገር ግን ያ ተስፋ ያደረግነው የእግዚአብሔር መንግሥት ጊዜውን ጠብቆ በኋላ ይመጣል። በዚህም ጊዜ የክርስቶስ ወገኖች ብቻ አስቀድመው በፊተኛው ትንሳኤ እንነሳለን። በዚህም ጊዜ አብርሃም አባታችን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም አብረው ትንሳኤን በምያት በዚህ መንግሥት ተካፋይ ይሆናሉ። እግዚአብሔርም መንግሥቱን ሁሉ በምድር በጽዮን ላይ ያደርጋል። በዚህም ጊዜ 5፤ " ዙፋንም በምሕረት ይቀናል፥ በዚያም ላይ በዳዊት ድንኳን ፍርድን የሚሻ ጽድቅንም የሚያፈጥን ፈራጅ በእውነት ይቀመጣል" ኢሳ. ም16፡ 5። ይላል። ስለዚህ የምናወራውን የእግዚአብሔር ቃል በቃሉ የተምዘገበውን ማውራት በጣም ጠቃሚ ነው። በእግዚአብሔር ጥበብ ውይይታችን ብናደርገው እውቀት ይሆንልናል።
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
 12. አባ ሰላማዎች ቃለ ሕይወትያሰማችሁ። ብትቀበለው የተናገራችሁ እናንተ አይደላችሁም። በእናንተ አድሮ የተናገራት፤ የንሥሐ ዕድል የሰጣት መንፈስ ቅዱስ ነው። ለእህታችን ዘማሪት ፋንቱ ብቻ አይደለም። የእግዚአብሔርን ክብር ለጥቅም እየሸቃቀጡ ለሉት ሁሉ ነው እግዚአብሔር የተናገረው። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ዐይነ ልቦናቸውን አብርቶ ለንሥሐ ያብቃልን። እንዲህ ዓይነቱን የጭለማና የድንቁርና መንፈስ አረ በውነት ይገሥጽልን።
  እባካችሁ ይህን ጽሑፍ በአንድም በሌላ ለማቆች እንዲደርስ ብታደርጉት ደስ ይለኛል። አንድም በዚህ መንፈስ የተጠናወተው ማቅ ነው። በጌታ አምኖ ማረፍ ስላልቻለ ይቅበዘበዛል። መጽሐፍ ቅዱስን ከጋሮ አስቀምጦ በጥቅም መርዝ ስለተለከፈ ቤተ ክርስቲያንን ይበጠብጣል። አባቶችን ይከፋፍላል። በጥቅሜ መጡ ብሎ በተለይ ቅዱስ ፓትርያሪኩን እየዘለፈ ይገኛል። ምክንያቱም ሥርዓት ያዝ ፤ በሃይማኖትና በሥርዓት ሂድ ስለላሉት። መቼም መንፈስ ቅዱስ ያልቃኘው አንደበት ሁሉ የሚቀናው ስድብና እርግማን ነው። ስለዚህ ለማቅ በውነት ተግተን ልንጸልይ ይገባናል።
  ሰላም ይብዛላችሁ።

  ReplyDelete
 13. ይህን ተናገርኩ ብለህ የምትኩራራ ከሆነ ገና ብዙ ነገር ያልገባህ ነገር ስላለ ተመልሰህ ሰንበት ትምህርት ቤት ብትገባ ይሻልሃል::

  ReplyDelete
 14. If that is the case why u pray ye Embetachen tselot after Abatachen Hoy????or like Protestant u don t pray it??????If so Why you bother about Ye Orthodox zemarewoch?????Egnas yeEgziabher Sem belayachewlaye lalu Melaekt kidusan bedenb enzemeralen Zemari Fantu berchi Egziabher keanchi ga yehun. amen

  ReplyDelete
 15. ጉድ በል ውበት ና መምህር ለይኩን ዘኦስተን

  ReplyDelete
 16. ጉድ በል ውበት ና መምህር ለይኩን ዘኦስተን

  ReplyDelete
 17. እረ ጉድ ፈላ ፉንትሽ

  ReplyDelete
 18. እረ ጉድ ፈላ ፉንትሽ

  ReplyDelete
 19. Dejje tenahu koyche kidane mehreten.......
  yemilewos ye simamue sewoye mezmur???yale dengel mariyam amalajjenet alem aydenem yemilwo ye zebene show sibket..fantuma betam yemtegerem ferret nat mela teftobatal.seleyulachewo.eyesusen metrat denigrate lemihonbachw sebakiyanena zemariyan

  ReplyDelete
 20. Fantu degmo manate????

  ReplyDelete
 21. teleku chegere fantuna meselocewa sayemaru agelegelot megemerachew new.

  ReplyDelete
 22. ወንድሜ ተስፋ በእውነት ይህን በቃሉ ተመስርተህ የሳትነውን ለመመለስ የምታደርገውን ሙከራ የሰማይ አምላክ ዋጋህን በእጥፍ ይክፈልህ፡፡ ለእታችንም ቸሩ ጌታ ማስተዋልን ይስጥሽ፡፡ እባካችሁ ቃሉን ብቻ እንዘምረው ቃሉን ብቻም እንጸልየው እዳ እንዳይበዛብን!!!!!! እባክሀ ጌታ ሆይ ለሕዝባችን ዐይኖቹን ክፈት፡፡ ስለ ስምህ ስትል!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 23. ወንድሜ ተስፋ በእውነት ይህን በቃሉ ተመስርተህ የሳትነውን ለመመለስ የምታደርገውን ሙከራ የሰማይ አምላክ ዋጋህን በእጥፍ ይክፈልህ፡፡ ለእታችንም ቸሩ ጌታ ማስተዋልን ይስጥሽ፡፡ እባካችሁ ቃሉን ብቻ እንዘምረው ቃሉን ብቻም እንጸልየው እዳ እንዳይበዛብን!!!!!! እባክሀ ጌታ ሆይ ለሕዝባችን ዐይኖቹን ክፈት፡፡ ስለ ስምህ ስትል!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 24. ጐበዝ በነካ እጃችሁ
  1የእንግዳ ወርቅን
  2የልዑል ሰገድ
  3 የቸርነት
  4 የ ዲ ታዲዩስ መዝሙራትን ፈትሿቸው

  ReplyDelete
 25. melke tifu besm yidegfu

  ReplyDelete
 26. Bicheger new enjji fantu ahun zemari tibalalech??ye emamlak amlakiwoch mahber mesrach .eyesus yemiteru hulu pente nachew
  Yemetel agelgayochen bemekfafel sira ke wendwosen gar betegat yeserach ....endihem hono zemari yelem.wengel astemrwat mejjemeriya.

  ReplyDelete
  Replies
  1. tesfaye gabisos endet new, lelaw manew zefen neger yawetaw

   Delete
  2. Don't pass the line! stay in your messed up Orthodox problem. Pastor Tesfaye is a servant of God!

   Delete
 27. ፋንቱ ያገጠሙላትን ነው ምዘምረው ምንም አታውቀውም እርሷ የምታውቀው መክሰስ ብቻ ነው

  ReplyDelete
 28. ፋንቱ ያገጠሙላትን ነው ምዘምረው ምንም አታውቀውም እርሷ የምታውቀው መክሰስ ብቻ ነው

  ReplyDelete
 29. Bishik!!!!! lenante mezimur malet ke orthodox yezerfe kebede new ayedel?

  Tesfa bis mehonihin tawukaleh? eski min aleh? bado qil wust yale tinish bakele enedemiyasemawu chuhet new yemitichohew. Sewochin lemasamen endet lela zede atah? ante dedeb! ene beakal silemawukih min yakil dekama sew mehonihin eredalehu. Ye antem badonet lemeredat anten be akal mawok ayasifeligim yemititsifew tsihuf rasu masaya new. Yemigermewu degimo bizu sew yanebebew lemasimesel degagimeh comment yemitadergew neger new. ye matireba kef bilo ketesetew 30 comment 17tu bante bersaih yetesete comment new. Keshim. Tesfa ke 12 amet befit yeserahewun tastawusaleh? ene endante aydelehum asfelagi kehone silik tewulignina qetero yizen enaworalen. ahunim yemininorew and akababi silehone malet new.

  You are well come for face to face discussion Tesfish! by

  ReplyDelete
 30. "የጥንት ደብተራዎችን ዕዳ ከፍለን ሳንጨረሽ ሌላ ዘመናዊ ከሃዲ ደብተራዎችን ስናይ በጣም እናዝናለን።"
  በሊቃውንት ጉባኤ የተቀመጡ ሰዎች (ሊቃውንት) ይኽን ያስተውሉ ይሆን ወይስ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚለውን እየዘመሩ ነው? የሊቃውንት ጉባኤ ማለት ቀደም ሲል ወደ ቤተ ክርስቲያንዋ ሰርጎ የገባውን የክህደት ትምህርት እያረሙ፤ እያጣሩ የሚያስተካክሉ ናቸው። ዘመናዊውንም የስህተት ትምህርት የሚከላከሉ ናቸው። የኛዎቹ ግን ይኽ እውቀት ቢኖራቸውም "ሕዝቡ አይቀበለንም" ሲሉ ይሰማሉ። ከዚህ አንጻር ወንጌል ያልገባት፤ ለሥጋዊ ጥቅምዋ በየመድረኩ የምትወራጨውን እህት ብቻ መምከሩ በቂ የሚሆን አይመስለኝም።
  በኃላፊነት ያሉ ሊቃውንት፤ ሊቃነ ጳጳሳት፤ ካህናት፤ የመድረክ ሰባኪዎች ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር መሥራትና መቆም ይገባል። እግዚአብሔር በቃሉ በግልጽ እየተናገረ በእልክ ሕሊናን ሸጦ በክህደት ጎዳና መቀጠል ከባድ መቅሰፍት ነው። ለነገሩማ እነርሱ የእግዚአብሔርን ክብር ጥለው ለራሳቸው ክብርና ጥቅም ሲፋጁ ምን ጊዜ ይኖራቸዋል። ጌታ ሆይ በመንጋህ ፊት የቆሙትን እረኞች አስባቸው።
  ተስፋ የተባልከው ሰው ማንንም ሳትፈራ ለእውነት ስለቆምክ፤ እውነቱን ስለጻፍክ እግዚአብሔር ይባርክህ። ቀጥልበት።

  ReplyDelete
 31. አነተ ስለ ተዋህዶ ኦርቶዶክሰ ምንም እውቀት ስለሌህ ነው ዝም ብለህ የምተቀላምደው፣ እረ ተው እግዚአብሔርን ፍራ 9ኝ ወር በሆዶ የተቨከመችውን አናቱንም አክብር። ግድ የለህም ሀሉም የስራውን ያገኛል አንተ ግን ልብ ግዛ ስምህና ስራህ ይመሳሰል ንስሐ የሚያስፈልገህ አንተ ነህ አንጂ ፋንቱ አይደለችም።

  ReplyDelete
 32. ንስሐ የሚያስፈልገህ አንተ ነህ አንጂ ፋንቱ አይደለችም።
  ላልህው ንስሐ መግባት ያለባት ምክንያት

  1 የእግዚአብሔር ክብር ወስዳ ለፍጡራን ስጥታለች

  2ፋንቱ ከሰሽ ስለሆነች

  3 ፋንቱ ዛሬ አንዳንድ አገልጋዩች ነን ባዩች እንደሚያደርጉት በአገልግሎት ሰበብ (ስማቸውን

  መጠቀስ አይስፈልግም) አንሶላ ታጋፋለች
  ስለዚህ ፉንቱ ንስሐ ያልገባች ማን ይግባ ?

  ReplyDelete
 33. Eski be embete smwat fantun...she can't sing Maryamn new yemelachu.demes yeleyesh amen yele.kebero gobeze nate mezemer gen sedale gobeze tebeltatalch.kelelochu Chaf gen atdersem.tureta tureta and neseha.

  ReplyDelete
 34. Adenegne balweld ...mendaye gin men maletu new??? Hule yemaygebagne mezmur balewoled yewoeld beal malt m eslogne neber.buy and kezih bewhala mezmurochachwon menfesawi biyadergwachew admach yenor yihonal.egziabher yemesgen burden Merton yemensemabet zemen..beyegizewo
  lesmu yemizemeruten esat yehonwo zemariwochen yasnesal.keber lesmu yihun.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማቅ፣ፋንቱ እና መሰሎቿ ንስሃ ይግቡ ምክንያቱም ፀረ ወንጌል ናቸውና?

   Delete
 35. መጀመሪያ አስተያየት ለሰላማ ብሎግ!!!በምታቀርቡዋቸው ጽሁፎች ላይ አስተያየት ስንሰጥ በፍጥነት ከማውጣት ይልቅ አፍናችሁ እያቆያችሁ ማሰቀየሻ ጽሁፍ ካዘጋጃችሁ በሁዋላ መልቀቅ ወዳጅነታችንን ይጎዳዋል፡፡ስለዚህ አስተያየቶቻችንን በፍጥነት ለማውጣት ሞክሩ፡፡አሁንም ስለመስተንግዶአችሁ በኢ/ዊ ጨዋነት አመሰግናለሁ!!ወደ ሀታቴ መዝሙራቱ ጽሁፍ……..
  1. ከጽሁፉ እንነሳ፡ ጽሁፉ የሚያቀርባቸው ጥቅሶች እና የጸሀፊው መደምደሚያ የተዋሀደ አይደለም፡፡ለእ/ር ዘምሩ ማለት ለቅዱሳን አትዘምሩ ማለት እንደሆነ ለማስረዳት ብዙ ይታትራል፡፡ነገር ግን አንድም ለቅዱሳን አትዘምሩ የሚል ጥቅስ አላቀረበም፡፡ሐዋርያትን ጠቅሶ ያቀረበው ማብራሪያም ሐዋርያት የተቃወሙት የአምልኮ መልክ ያላቸውን ውዳሴዎችንና አክብሮቶችን እንጅ እንደ ሐዋርያ የቀረቡላቸውን የጸጋ ምስጋናዎችና ስግደቶች ስላልሆነ ጥቅሶችን ለጥጦ በመተርጎም አጉዋጉል ወደ ራስ ሀሳብ ለማስጠጋት መሞክር ከንቱ ድካም ነው፡፡ ሲጀመር ለእ/ር የምናቀርበው ዝማሬ ለቅዱሳኑ ከምናቀርበው ጋር አንድ ስላልሆነ በምንም መለኪያ የእ/ርን ክብር መጋፋት ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡እናንተ እንደዛ ከመሰላችሁ የምታመልኩትን መርምሩ፡፡“ቅዱሳን ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።” መዝ. 30፡4 ሲል ጸሀፊው ለክርክሩ አስረጅነት የጠቀሰውን ጥቅስ ብንወስድ እንኳ ቅ/ዳዊት “ቅዱሳን ሆይ” እያለ መልእክት የሚያስተላልፈው በህይወት ላሉ ቅዱሳን ብቻ ለይቶ ባለመሆኑ ያረፉ ቅዱሳን እኛን አይሰሙም የሚለውን መከራከሪያ የሚያፈርስ እንጅ የሚያጠናክር አይደለም፡፡
  2. መጽሐፍ ቅዱሱንም እንየው፡፡ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር በተባለው መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን….ርግቤ…ሱላማጢስ….ወዳጄ….ውበቴ በሚሉ ቃላት ተውቦ በሴት አንቀጽ(ጾታ) የቀረበው መዝሙር እንዴትም ቢተረጎም ምስጋናውና ውዳሴው ለእግዚአብሄር የቀረበ ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ሊቃውንቱም የሚተረጉሙት አንድም ለወንጌል፣አንድም ለቤ/ክ፣አንድም ለእመቤታችን የቀረበ ውዳሴ ነው እያሉ ነው፡፡እርግጥ የእናንተን ትርጉም አናውቀውም፡፡ግን ለእግዚአብሄር ብቻ የቀረበ መዝሙር ነው እንደማትሉን ተስፋ እናደርጋለን፡፡እ/ር በሴት አንቀጽ ሲመሰገን አይተን ስለማናውቅ፡፡ለቤ/ክ ነው ካላችሁም ዞሮ ዞሮ ምስጋና የሚቀርበው ለእ/ር ብቻ ነው የሚለው መከራከሪያ መፍረሱ አይቀርም፡፡
  3. በመሰረቱ መዝሙር የሚለው ቃል ዘመረ ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ማመስገን ማለት ነው፡፡ምስጋና ደግሞ እንደውለታው አይነትና እንደውለታ አድራጊው ክብርና ማእረግ ይለያያል፡፡ለአምላክ የምናቀርበው ምስጋና የባህርዩ ነው፡፡ፈጥረህ የምትገዛ፤አብቅለህ የምትመግብ፣ከሶስቱ አካለት አንዱን አካል ልከህ ከዘለዓለማዊ ሞተ-ነፍስ ያዳንከን ብለን ነው፡፡ ለቅዱሳኑና ለመላእክት ስንዘምር ግን አምላካቸውን ታምነው ያደረጉትን ተጋድሎና ያገኙትን አክሊለ ክብር እያስታወስን እነሱን ለእኛ አርዓያ እንዲሆኑ የፈቀደ አምላከ በመዝ 88 ቁ 3 መሰረት ከመረጣቸው ጋር ያደረገውን ቃል እንዲያስብ በስማቸው እየዘመርን ተማለደን ነው የምንለው፡፡ልመናችን ሲደርስም በአማላጅነታቸው ስለተደረገልን እነሱን ለመጽናኛ የሰጠንን መልሰን እናመሰግናለን፡፡ስለጸጋቸው እናወድሳቸዋለን፡፡ደግሞ እንኳን ለጻድቃን ለምድራዊ አርበኞችም ይዘመራል፡፡እነሱማ ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ….ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም…የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል እየተባለ በመዝ 111 የተነገረላቸው ናቸው፡፡ስለዚህ መንፈሳዊ አርበኞቻችንን በመዝሙራት ስራቸውን እያነሳን እንዘክራለን-እናስባቸዋለን-አሳስቡልን እንላቸዋለን፡፡
  4. ስለ መላእክት በመዝ 102 ቁ 20…ባርክዎ ለእ/ር ኩልክሙ መላእክቲሁ-መላእክት ሁሉ እ/ርን ባርኩ…ተብሎ ተጽፎልሀል፡፡እና ቅ/ዳዊትን ያህል ነቢይና መዘምር መላእክትን እንዲህ በመዝሙሩ ሲያናግራቸው ለጣኦት ምስጋና እያቀረበ ነበር ልትለን ነው???ባርክዎ ያለው ዳዊት ሰአሉ ለነ--ለምኑልን እንዳይል የትኛው ጥቅስ ነው የሚከለክለው??
  5. ስለ እመቤታችን የምስጋና(የመዝሙራት) ምንጮች
  ሀ. ትንቢት፡ ቤ/ክ ዳዊት በመዝ 44 ቁ 16….ለልጅ ልጅ ስምሽን ያሳስባሉ…ሲል የተናገረው ትንቢት እመቤታችን በሉቃ 1 ቁ 48….እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል…ስትል በተናገረችው ቃል ፍጻሜ አግኝቱዋል ብላ ታስተምራለች፡፡የምድራዊቷን ቅ/ኤልሳቤጥ እና የሰማያውይውን ቅ/ገብርኤል ምስጋናም እንዳትረሳው፡፡ይሄው እኛም ለፈጽሞ ትንቢት ሰአሊ ለነ ቅድስት እያልን ስሙዋን እንጠራለን-ለትውልድ እናሳስባለ፡፡የለም፡፡ የዳዊት ትንቢት ለኢየሩሳሌም የተነገረ ነው የሚል ካለም ጌታ ተመላለሰባት ተብሎ ከምትወደሰው ግኡዝ ምድር ጌታን ወልዳ፣ተሰዳ፣አጥብታ፣ከቀራንዮ እስከ ጰራቅሊጦስ ያልተለየቸው ወላዲተ አምላክ ምስጋናም ሲያንሳት ነዋ እንላለን!!
  ለ. ቀደምት አበው፡እነ ቅ/ኤፍሬም፣እነ አባ ህርያቆስ፣እነ ቅ/ያሬድ፣እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣እነ ዮሐንስ አፈወርቅ እረ ስንቱ…..አወድሰዋት፣ቅድስናዋን አማላጅነቱዋን ተናግረው አይጠግቡም፡፡እነዚህ ቅዱሳን ስለ ብሉይና ሐዲስ ያላቸው እውቀት ደግሞ አይጠረጠርም፡፡በምስጋናዋ የሚደረድሩት የነቢያት ትንቢትና አምሳል፣የሐዋርያት ስብከት ምጥቀታቸውን ያሳያል፡፡ትምህርቱን ፈጥረው፣አመንጭተው ሳይሆን ከሐዋርያት ሲወርድ ሲዋረድ እናዳገኙም እናውቃለ፡፡እኛም የእነሱ ልጆች ስለሆንን አርዓያነታቸውን ተከትለን ...ተፈስሂ ኦ ማርያም እም ወአመት-እናትነትን ከአገልጋይነት ያስተባበርሽው ብቸኛዋ እመቤት ሆይ ደስ ይበልሽ… እያልን በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንላታለን፡፡እናወድሳታለን፡፡ሆኖም አናመልካትም!!

  ሐ. ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ እውቅና ከምትሰጣቸው ጉባኤያት መካከል በ431 ዓ.ም 200 ሊቃውንት ተሰብስበው ሁለት አካል፣ ሁለት ባህርይ ባዩን ንስጥሮስን ያወገዙበት ጉባኤ-ኤፌሶን አንዱ ነው፡፡በዚህ ጉባኤ ላይ ንስጥሮስ እመቤታችን የወለደችው መለኮትነት የሌለው ወልድን ብቻ (እሩቅ ብእሲ) እንጅ መለኮት የተዋሀደው ስጋን አይደለም በማለቱ “ታዲያ ሰብዐ ሰገል አምኃ አቅርበው የአምልኮ ስግደት የሰገዱት ለሩቅ ብእሲ ነው እንዴ” ተብሎ ተረታ፡፡የእመቤታችን ወላዲተ-አምላክነትም በጉባኤው ዳግም በአጽንኦት ተነገረ፡፡በመጨረሻም በውሳኔው አንቀጸሃይማኖት “….የእውነተኛ ብርሃን እናት ሆይ እናከብርሻለን፣መጥቶ ነፍሳችንን ያዳነውን የዓለምን ሁሉ መድኃኒት ስለወለድሽልን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆይ እናመሰግንሻለን….” ሲሉ የቀደሙ አባቶችን ትምህርት አጽንተው ከ1500 አመት በፊት በዶግማ ደንግገውልናል!!ዶግማ ደግሞ አይሻሻልም፣አይጨመርበትም፣አይቀነስበትም!!ስለሆነም በመላው ዓለም ይሄን ጉባኤ በሚቀበሉ የምእራብና የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ከሉተራውያን በቀር እመቤታችንን ‘ሰአሊ ለነ ቅድስት’ ሳይል የሚውል ክርስቲያን የለም!!በነገራችን ላይ ደቀመዛሙርቱ እንጅ ሉተር የእመቤታችንን ምስጋና አይቃወምም ነበር፡፡

  Reply

  ReplyDelete
  Replies
  1. ከላይ ያለውን የጻፍከው ወንድሜ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልህ።ማስተዋል የተሳናቸውን።
   " እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይ የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።ዮሐንስ ራእይ 13 ፤ 5 )"
   ዘንዶውም ወደ ምድር እንደተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት።ራእ 12 ፤ 13

   Delete
  2. ወንድማ እባክህ ሰውን አታደናግር የ431 ጉባኤ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ነች በሚለው እውነተኛ ነገር ተስማሙ እንጂ ምስጋና ይገባታል አላሉም የቀደሙት እውነተኞቹ የኦርቶዶክስ አባቶች እኮ ማስተዋልና ጥበብ የተሙሉ ነገርን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚመረምሩ እውነተኛ አባቶች ናቸው ወንድሜ በእንሱ እያሳበብክ ሰውን አታደናግር ክብር የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ ነው ምስጋና አምልኮ ነውና፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ በአምልኮቱ ቀናተኛ ነው በዚህ ነግር ይፈርዳል ለምንድን ነው፡፡ እውነትን ትንሽ እውነት ከሚመስል ጋር እየቀየጥን ሰውን የምናደናግረው፡፡ በትክክል ስለእምነታን ማወቅ ከፈለግንና ከቀደመርው አማናዊት ቤ/ክ ጋር መጓዝ ከፈለግን መጽሐፍ ቅዱስ፣የቤ/ክ ትሪክን፣ የኢትዮጵያ ቤ/ክ ታሪክን እናንብብ ለምን ዝም ብለን እንገፋለን እግዚአብሔር እኮ እንድናነብና በእርሱ ተመርተን እንድንድን ነው መጽሐፍ ቅዱስን የሰጠን፡፡ ቅዱሳን አባቶች በብዙ ተግዳሮት ያቆዩልን እምነት ይሔ ነው እግዚአብሔር ብቻ ምስጋና ይገባዋል፡፡ ለዘላለም ምስጉን እሱ ብቻ፡፡

   Delete
  3. ሲጀመራ መጽሐፍ ቅዱስን በአግባቢ ተምርህ ከሆነ መሀሌ መሀሌ የተጻው ሰለድንግል ማርያም ሳይሆን ስለ ቤ/ክ እና ስለ እግዚአብሔር ነው፡፡ሰው ሲጠፋ አዋቂ ነኝ ብለህ ሰውን አታሳስት ፡፡ ይህች ቤ/ክ እንደሆነ ዝም ብላለች እንደ አንተ አይነቱን መናፍቅ ይዛ እውነተኞቹን መናፍቅ ትላላች መናፍቅ ማለት እኮ ነገርን ያለቦታው የሚገልጽ እውነትን ውሸት የሚል ውሸትን እውነት የሚል ነው፡፡ ማስተዋልን ይስጥህ

   Delete
  4. ምስክርህ እውነተኛ ከሆነ ስለ እግዚአብሔር በሰው ፊት የምትመሰክር ከሆነ ለምን
   anonymous ትጠቀማለህ መደበቅ የሚፈልግ የሐሰት ምስክረኛ ብቻ ነው።
   ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል። ያለችው መንፈስ ቅዱስን ተመልታ ነው እኛ ደግሞ
   የእግዚአብሔር መንፈስ እውነተኛ ነው አይሳሳትም።ብለን እናምናለን።

   Delete
  5. @AnonymousJune 9, 2014 at 1:44 AM
   ይሄ የጉባኤ ኤፌሶን ድንጋጌ ቀጥታ በአስራት ገብረማርያም ከተጻፈው ትምህርተ-መለኮት መጽሐፍ የተወሰደ ነው፡፡አልጨመርኩበትም፤አልቀነስኩበትም፡፡እንዳለ በትእምርተ ጥቅስ ውስጥ ነው ያስቀመጥኩት፡፡የምታወራውን ያህል የቤ/ክ ታሪክ አንባቢ ከሆንክ አንብበው፡፡ ውሳኔውን ልድገምልህ….
   “….የእውነተኛ ብርሃን እናት ሆይ እናከብርሻለን፣መጥቶ ነፍሳችንን ያዳነውን የዓለምን ሁሉ መድኃኒት ስለወለድሽልን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆይ እናመሰግንሻለን….”
   እንግሊዝኛው የሚቀናህ ከሆነም Hymns to Mary ወይም Counsel of Ephesus and Virgin Mary እያልክ ጎግልን አስሰው፡፡የ431 ጉባኤ ኤፌሶን ሁኔታ እንዲህ ይገልጽልሃል….Anyone who continues to doubt that affection and veneration for the Mother of God is an ancient and fundamental element of authentic "Christianity" need only observe the reactions of the Ephesians to the decree of the Council. We are told that crowds waited outside while the Council deliberated and, upon hearing its decision, the air was filled with cries of "Praise be to the Theotokos." The famous torch lit procession of Ephesus has been cited often as an example of that special love for Mary which has kindled the hearts of entire cities-----even entire nations-----in former time…
   ከላይ ከተገለጸው የእንግሊዝኛ ፓራግራፍ ውስጥ the air was filled with cries of "Praise be to the Theotokos."የሚለው ይሰመርበት!! ትርጉሙ….አየሩ ምስጋና ለወላዲተአምላክ! በሚል የውዳሴ ቃል ታወደ… ማለት ነው፡፡ Theotokos የሚለው የግሪክ ቃል በእንግሊዝኛው Mother of God ሲባል በግእዝ ወላዲተ አምላክ-በአማርኛ የአምላክ እናት ተብሎ ለእመቤታችን ይቀጸላል፡፡እስከምናውቀው የአምላክ እናት አንድ ናት-ስሟም ቅድስት ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ!!
   እንደ አባ ጊዮርጊስ….ውድስት አንቲ በአፈ ነቢያት፣ወስብሕት በሐዋርያት…በአፈ-ነቢያት የተወደስሽ፣በሐዋርያት ተመሰገንሽ… የምንላት!!እንደ ቅ/ያሬድ…ዮም ንወድሳ ለማርያም በእንተ ዘተወልደ እምኔሃ መንክር ግርማ ኃይለ-ልዑል ጸለላ…ዛሬ ከእሷ ስለተወለደው (ክርስቶስ) ማርያምን እናመሰግናታለን፣ልዩ ግርማ የልዑል ኃይል ሸፍኗታል….እያልን!!ይሄ ቃል ለመናገር ደግሞ እንደ ቅ/ገብርኤል መልአክ መሆን፣እንደ ቅ/ኤልሳቤጥ በመንፈስቅዱስ መሞላት ይጠይቃል!!!!እንግዲህ እኛ ቤት ደግሞ ጸጋ የሚገኘው በእምነት ብቻ ሳይሆን በጾም፣በጸሎት፣በምጽዋት…በመሳሰሉት ትሩፋቶች ጭምር እንጅ እንዲሁ ጌታ ሆይ-ጌታ ሆይ በማለት ስላልሆነ እሷን የማመስገን ጸጋ ካልተሰጣችሁ ምንም ማድረግ አንችልም-ቀረባችሁ እንጅ እሷ አይቀርባትም!!ምን እናርግ!!እኛ እንደ እናንተ በየአዳራሹ በኮንፈረንስ እንደ ቻርጅ የሚሞላ መንፈስ የለን!!
   ታላቋ እህታችን ዘማሪት ፋንቱ ከሴቶች ወገን አንች ቀዳማዊት ኦርቶዶክሳዊት ዘማሪት በመሆንሽ ኦርቶዶክሳውያን እንኮራብሻለን!!አሁንም የአገልግሎት ዘመንሽን ይባርክልሽ-እሱ የድንግል ልጅ!!

   Delete
  6. ይቅርታ!! የጠቀስኩትን መጽሐፍ ከነገጽ ቁጥሩ ለመናገር ስል ነው የተመለስኩት፡፡ትምህርተ-መለኮት፣ሁለተኛ እትም፣ከዓስራት ገብረማርያም፣1991 ዓ.ም፣በንግድ ማተሚያ ድርጅት የታተመ፣ገጽ-81፡፡
   ከመጣሁ አይቀር መጽሐፉ በእጃቸው ለሌለ ወገኖች ትንሽ ልጠቃቀስ…
   …ለኤፌሶኑ ጉባኤ ዋና ምክንያት የሆነው የንስጥሮስ ክህደት ነው፡፡በትምህርቱ የክርስቶስን መለኮትና የእመቤታችንን አምላክ እናትነት ክዷል፡፡የክህደት ትምህርቱም እንዲህ የሚል ነው ‹‹የእግዚአብሄር ቃል ከሁሉ በፊት የነበረ መሆኑን አምናለሁ፤ማርያም የአምላክ እናት ነች የሚለውን አባባል ግን አላምንም፡፡የክርስቶስ እናት መሆኗን አልክድም፤እናትነትዋ ግን ለትስብእት ነው፡፡ማርያም እግዚአብሄርን አልወለደችም፤ነገር ግን ከሥጋ የሚወለድ ሥጋ፣ከመንፈስ የሚወለድ ደግሞ መንፈስ ነው፡፡ፍጡር ሆና የወለደችው የእግዚአብሄር መሳሪያ የሚሆነውን ሰውን እንጅ ፈጣሪን አይደለም፡፡በዚህም መሰረት ጌታ ሁለት ጠባይ፣ሁለት አካልና ሁለት ፈቃድ አለው፡፡ሰብአሰገል ለህጻን ጌታ ኢየሱስ መስገዳቸው ስህተት ነው፤ምክንያቱም(በእርሱ እምነት) ህጻን ጌታ ኢየሱስ መለኮት ያልተዋሐደው ሰው ነውና››፡፡….
   …ከሀዲዎቹንም ከክህደታቸው በመሻርና ከኅብረት በመለየት ፍርዱን የሰጠው ጉባኤ የክርስቶስ መለኮትና ትስብእት ያለ መቀላቀልና ያለመለያየት ከተዋሐዱ በኋላ ጌታ አንድ አካልና አንድ ባሕርይ ያለው መሆኑንና እመቤታችንም የአምላክ እናት መሆኗን በማመን የእምነት ቀኖና መቅድም ውሳኔ አሳልፏል፡፡ይህም የእምነት ቀኖና መቅድም (pre-amble) እንደሚከተለው ነው፡፡
   -የእውነተኛ ብርሃን እናት ሆይ እናከብርሻለን፣መጥቶ ነፍሳችንን ያዳነውን የዓለምን ሁሉ መድኃኒት ስለወለድሽልን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆይ እናመሰግንሻለን፡፡
   -የሐዋርያት መመኪያ፣የሰማዕታት አክሊል፣የቅዱሳን እረፍት፣የቤተክርስቲያን መሰረት የሆንከውና ኃጢአትን የምታስተሰርይ ጌታችንና ንጉሣችን ክርስቶስ ክብር ላንተ ይሁን፡፡
   -ስለ ሥሉስ ቅዱስ እንሰብካለን፤እናስተምራለን፣ለአንድ መለኮት እንሰግድለታለን፤እናከብረዋለን፡፡
   ጌታ ሆይ፣ይቅር በለን፤ጌታሆይ፣ ባርከን፤አሜን፡፡
   ተጨማሪ የመጽሐፍ ጥቆማ ለቤ/ክ ታሪክ አንባቢው ወንድሜ፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታሪክ፣በአቡነ ጎርጎርዮስ(M.A) የሸዋ ሊቀጳጳስ፣በትንሳኤ ዘጉባኤ የታተመ፣ዋጋው ብር-25፣በተለይ ከገጽ-155 ጀምሮ “የአማላጅነት ትምህርት” በሚል ርእስ ስር እስከ ገጽ160 ድረስ ስለ እመቤታችን የተጻፈውን ብታነብ ደስ ይለኛል፡፡
   ማስታወሻ ፡ ተዋሕዶ=ያለመቀላቀልና ያለመለያየት ሰው አምላክ ሆነ፤አምላክ ሰው ሆነ ማለት ነው!!አስቀድሞ ቃል ነበረ፤ቃልም ስጋ ሆነ!!አማኑኤል=እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ሆነ-ከእሷ በነሳው ሥጋ!!

   Delete
  7. brother hiruy
   እንግዲህ እኛ ቤት ደግሞ ጸጋ የሚገኘው በእምነት ብቻ ሳይሆን በጾም፣በጸሎት፣በምጽዋት…በመሳሰሉት ትሩፋቶች ጭምር እንጅ እንዲሁ ጌታ ሆይ-ጌታ ሆይ በማለት ስላልሆነ እሷን የማመስገን ጸጋ ካልተሰጣችሁ ምንም ማድረግ አንችልም-ቀረባችሁ እንጅ እሷ አይቀርባትም!!ምን እናርግ!!እኛ እንደ እናንተ በየአዳራሹ በኮንፈረንስ እንደ ቻርጅ የሚሞላ መንፈስ የለን!!
   Would you compare your writing with the word of God Eph 2:8,, Gela 2:16 , so believe only by Jesus and you will be saved. After born again you can do good deeds because you are created to do good work Eph 2:9

   Delete
  8. ወንድሜ አለማየሁ!!
   እኛም እኮ ጾም፣ጸሎት፣ምጽዋት….የመሳሰሉ በጎ ምግባራት ይሰምራሉ የምንለው አንድ ሰው አምኖ እስከተጠመቀ ድረስ ነው፡፡፡፡አባቶቻችን ምን ይላሉ መሰለህ “…ሃይማኖትሰ መሰረት ይዕቲ ወካልአኒሃ ሕንጻ ወንድቅ እሙንቱ….ትርጉም….ሃይማኖት መሰረት ናት ሌሎቹ ግን ህንጻ/ግደድግዳ ናቸው፡፡” ግን…ነገርግን…ሆኖም….ይሁን እንጅ….እኛ እምነት ብቻውን ያለምግባር በቂ ነው ብለን አንሰብክም፡፡እምነቴ ብቻ ያድነኛል ካልክ እኔ ሳልሆን ሐዋርያው ያዕቆብ ከምዕራፍ 2 ቁጥር 17 ጀምሮ የተናገረውን ልቀንጭብልህ…ማመንማ ጋኔን ያምናል ይልሃል…ሐዋርያው…..ተከተለው…
   17 እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።
   18 ነገር ግን አንድ ሰው። አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል።
   19 እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ አጋንንት ደግሞ ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።
   20 አንተ ከንቱ ሰው፥ እምነት ከሥራ ተለይቶ የሞተ መሆኑን ልታውቅ ትወዳለህን?

   Delete
 36. ayi alemtadel ye emebeitacn sm yaqatlhal

  ReplyDelete
 37. Fantu is my gril friend stop to accuse her I am mk in GA

  ReplyDelete
 38. Embetachenen kegeta gar eyawdaderachu setekerakeru yemdanachenen eras fetarin kefterachew gar setawedaderu .satdenu endatetefu.kiber lemigebawo kiber enest.

  ReplyDelete
 39. ዛሬም ልድገምልህ! አንተና መሰሎችህ ከዚህ በላይ አያስፈልጋችሁም።

  መንቲሮ ነኝ
  When I wrote this paragraph I was sure that you will not post it. I knew how to challenge you than my brothers who wrote opposing your belief. You and your kind do not need scriptural references so as to clear the points you mentioned .You need simple answer, very simple metaphor. It is such metaphor easily destroy your delusion and intellectual pride. Cowards! ፈሪ ሁላ!!!

  ደግሜ እላለሁ
  በእንዳንተና በእንደኔ አይነት ጭራቅ ድምጽ ሳይሆን

  ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ስህተት ለባህርዩ በማይስማማው በእግዚአበሔር ተመረጠች! ምን ይዋጥህ!? ምርጫውን አትሰርዘው ፣ኮሮጆውን አትገለብጠው ነገር ምርጫው የልዑል እግዚአብሔር ነው ። በቃ- ተኝተህ ተኩስ። እንዘምርላታለን !

  የኢትዮጲያ ህዝብ መዝሙር ታውቃለህ ? ቀሽም;። ኃይሌ ኦሎምፒክ አደባባይ ሲዘምር ስታይ ኢትዮጲያን ሲያመልክ ነበር እንዴ? ጽሑፎቻችሁ በሙሉ ግልብ የሆነ አመለካከቶቻችሁን ነው የሚያሳዩኝ።
  You and your kinds have very shallow understanding of orthodox Christianity ........
  ኦርቶዶክሳዊያን በናታችሁ ነገረ ሃይማኖት በሚገባው ሰው ደረጃ ከፍ አድርጋችሁ አትመልሱለት። ከመጽሐፍ ቅዱስ አትጥቀሱለት። በደረ ጃው አነጋግሩት። ልክ እንደዚህ!
  'የአባ ሰላማው' አመሰግንሃለሁ ። ዋ! አመለከኝ እንዳትለኝ።

  ፖስት ባታደርጉት ስቄም አላባራ!

  መንቲሮ ነኝ

  ReplyDelete
 40. I dont like her voice. I dont think she can sing.

  ReplyDelete
 41. አይ ሰይጣን የማትመጣበት መንገድ የለህ ደግሞ በዚህ መጣህ?

  ReplyDelete
 42. ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ እግዚአብሔር ጸጋውን ያብዛልሽ።ባንቺ ዝማሬ እርኩሳን መናፍስትና አገልጋዮቻቸውን የሚያበሳጭ የሚያናድድ ስለሆነ እግዚአብሔርን አብዝተን እናመሰግናለን።

  ReplyDelete
 43. Befantu zemari befesume erkusan menafest Libesachu yaychelum.becos eyesus yemibalewon
  sim lemeterat betam selmikebdat yemiterutenm selemetasaded...endewom abrewat hulu likomu yechilalu.

  ReplyDelete
 44. ay sew yemilew syata emotional hono mesadeb new. yilik zemenu sayalk berum sayizega lik ye eyesus enat Mariam endalechiw esun simut. medan ke eyesus kirstos sim be ker be liela yelemna. ye hawaryat sira 4.12. ke gieta fikr gara
  Samson ke asmera

  ReplyDelete
 45. ወንድማ እባክህ ሰውን አታደናግር የ431 ጉባኤ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ነች በሚለው እውነተኛ ነገር ተስማሙ እንጂ ምስጋና ይገባታል አላሉም የቀደሙት እውነተኞቹ የኦርቶዶክስ አባቶች እኮ ማስተዋልና ጥበብ የተሙሉ ነገርን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚመረምሩ እውነተኛ አባቶች ናቸው ወንድሜ በእንሱ እያሳበብክ ሰውን አታደናግር ክብር የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ ነው ምስጋና አምልኮ ነውና፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ በአምልኮቱ ቀናተኛ ነው በዚህ ነግር ይፈርዳል ለምንድን ነው፡፡ እውነትን ትንሽ እውነት ከሚመስል ጋር እየቀየጥን ሰውን የምናደናግረው፡፡ በትክክል ስለእምነታን ማወቅ ከፈለግንና ከቀደመርው አማናዊት ቤ/ክ ጋር መጓዝ ከፈለግን መጽሐፍ ቅዱስ፣የቤ/ክ ትሪክን፣ የኢትዮጵያ ቤ/ክ ታሪክን እናንብብ ለምን ዝም ብለን እንገፋለን እግዚአብሔር እኮ እንድናነብና በእርሱ ተመርተን እንድንድን ነው መጽሐፍ ቅዱስን የሰጠን፡፡ ቅዱሳን አባቶች በብዙ ተግዳሮት ያቆዩልን እምነት ይሔ ነው እግዚአብሔር ብቻ ምስጋና ይገባዋል፡፡ ለዘላለም ምስጉን እሱ ብቻ፡፡

  ReplyDelete
 46. ሲጀመራ መጽሐፍ ቅዱስን በአግባቢ ተምርህ ከሆነ መሀሌ መሀሌ የተጻው ሰለድንግል ማርያም ሳይሆን ስለ ቤ/ክ እና ስለ እግዚአብሔር ነው፡፡ሰው ሲጠፋ አዋቂ ነኝ ብለህ ሰውን አታሳስት ፡፡ ይህች ቤ/ክ እንደሆነ ዝም ብላለች እንደ አንተ አይነቱን መናፍቅ ይዛ እውነተኞቹን መናፍቅ ትላላች መናፍቅ ማለት እኮ ነገርን ያለቦታው የሚገልጽ እውነትን ውሸት የሚል ውሸትን እውነት የሚል ነው፡፡ ማስተዋልን ይስጥህ

  ReplyDelete
 47. ደጅ ጠናሁ yemilew sewuye አቡበክርን yimeslegnal

  ReplyDelete
 48. joro yalew yisma: Aba selamawoch ewunet tenageru. Bertu teberatu......diabilos besewum be'kam yiseralina....bemegesets enikawomew....

  ReplyDelete
 49. This page is not for Orthodox .I think you are coming to divide us like weyane.

  ReplyDelete
 50. habtamemariammesele@gmail.comAugust 2, 2014 at 2:46 AM

  አንዳንድ ጊዜ ሰይጣን በሰዋች ላይ እያደረ አምላክን የሳደባል ያጥላላል እንዲሁም አምላክነቱን በመተው አማላጅ ነው ይላል የህ አይን ያወጣ ክህደት፡፡ መቸም ቢሆን የትም አያደርስምና እውነትን እወቅ፡፡ ቅዱሳን ስማቸው እንደይነሳ የምተፈልግ ሰይጣንና አበሮቹ ደስ አይበላችሁ ድንግል ገና ትከብራለች ትገናለች አምላክ ከሰዎች በላይ አክብሯተልና ፡፡ አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተበረክሽ ነሽ ሉቃስ 1+18
  ስለ ሰው ልጆች ይለምናሉ ይማልዳሉ፤ይፀልያሉም ፅድቅም እንደውሀ ይፈስሳል ምህረትም በምድር እንደ ጠል ይሆናል በመካከላቸውም ለዘላለም እንዲህ ይሆናል” መፅ.ሄኖክ 9÷23
  እግዚአብሔር ሆይ ሐገራችን ኢትዮጵያን በምህረትህ ይቅር በል ያለ አንተ ይቅር ባይ እና ሀይል የለንምና !!!
  “የሚቃጠልንም ስለራሳችሁ አሳርጉ ባሪያዬም ኢዮብ ስለእናንተ ይፀልያል እኔም እንደስራችሁ እንዳላደርግባችሁ ፊቱን እቀበላለሁ” መፅ.ኢዮብ 42 ÷ 7-8
  “የእግዚአብሔር አይኖች ወደፃድቃን ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸው” መዝ 33÷15
  “የሀጢያት መስዋእት በእግዚአብሔር ዘንድ አፀያፊ ነው የቅኖች ፀሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው” ምሳ 15÷18
  “እግዚአብሔር ኩጥአን ይረቃል የፃድቃን ፀሎት ግን ይሰማል” ያዕ 5÷16-18
  “ሌላም መላክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ በዙፋኑም ፊት በወርቅ መሰዊያ ላይ ከቅዱሳን ፀሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ” ራዕ 8÷34
  “በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ እንግዲህ ከእግዚአብሔር ጋር ካለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን” 2ኛ ቆረ 5÷13-20
  “ሲሰድቡን እንመርቃለን ሲያሳድድኑ እንታገሳለን ፤ ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን” 1ኛ ቆረ 4÷12
  “እውነት አላችኋለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል በምድር የምትፈቱት በሰማይ የተፈታ ይሆናል” ማቴ 18÷18
  “እባርክሃለሁ ስምህንም አከብረዋለሁ ለበረከትህም የሚባርኩህንም እባርካለሁ የሚረግሙህንም እረግማለሁ”ዘፍ 12÷2-3
  “ስለ እኔም ስለባሪያዬም ስለዳዊት ስል ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ”አሳ 37÷33-38
  “እንዳየጠፈቸው ቁጠውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሰፍት ጊዜ በፊቱ ባይቆም ኖሮ ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ” መዝ 105÷23
  “… በኋላኛው ዘመን በ12 ነገድ እንደሚፈርዱ” ማቴ 19÷28
  “በአራቱ ማዕዘን ሰአሊ ለነ ቅድስት ሳይላት የሚውል የለም” ራዕ 21÷25
  “የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር የባህርይ ልጁን ላከ” ገላ 4÷4
  “ብዙዎችን፡ መጻሕፍትን፡ ለጥፋት፡ ወደ፡ ባሕላቸው፡ እንዳጣመሙአቸው፡ያልተማሩና፡ የማያስተውሉ፡ ሰዎችም፡ የመጽሐፍን፡ ቃል፡ ወደ፡ ራሳቸው፡ ሐሳብ፡ ይለውጡታል” ፪ጴጥ.፫፥፲፮
  “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል”ሮሜ 8÷23

  ReplyDelete
 51. what is roung men?this is roung mind man

  ReplyDelete
 52. hahahahahahahae hhaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaaahahahahahhhahhahahahahhahhahahahh....ዲያብሎስ ዲያብሎስ ዲያብሎስ ዲያብሎስ ዲያብሎስ ዲያብሎስ ዲያብሎስ ዲያብሎስ ዲያብሎስ ዲያብሎስ wede tsadekane wusedut...atechekenebetem

  ReplyDelete
 53. እግዚብሄር አይናቸውን ይክፈት
  ሰይጣን የአምላካችንን የወንጌል ቃል በልባችው እንዳያሥተወሉ፡ በአእምሮአቸው እንዳያስቡ በእንግዳ ትምህርተ አሳወራቸሀው!!አምለክ ይርዳቸው
  ጻሃፊው በእረገጥ በወንጌሉ ቃል እየመዘነ፤አቅርቦታል፡፡በዚህም መሰረት የእግዚያብሄርን ቃል የሚቃረን ፡ የአጋንነዌም ተቀዋሚው ፀረ-ክርሰቶስ በረቀቀ ዘዴ የተጠቀመበት ዘፈን ነው፡፡
  በጭፍን ከመቃወም ይልቅ ልክ ፀሃፊው እንዳብራራው ቁጥርና ምዕራፍ አየጠቀሳችሁ አስረዱንና እንስማችሁ????? አረ ባካችሁ ተረት ይብቃ ክረሰቶስ በሙላት ይሰበክ!!!!
  አባ ስላማዎች እግዜአብሄር አብዝቶ ይባረካቸሁ

  ReplyDelete
 54. DEROM YEMYE SIRA SIW YEMISIRAN SIW B METCHIT ZINENA OR TAWKI MEHON ENDE MIFLEGE ENAWKALEN. ESTI ANTE ANDE MEZMURE AWTA NA ENA ENEYLIK. KUCHI BLO MAWRAT KELAL MEHONUN ENAWKALN!!!

  ReplyDelete
 55. aba selama yemenafikan machiberberiyana yebeg lemd yelebesu tekula yetebalut limeshegubet yemokerube gets new:: hulachinm awkenal degmo ewnet egziabher besiwur teguazu alalem be birhanina beglts enji,lemin machiberber asfelege enate achiberbariwochi,lenegeru minm silelelachu beleloch tila lemetelel new,egziabher ewnet new menafikan atachiberbru atasmeslu

  ReplyDelete
 56. As soon as I read 3 sentences I knew who you you are; you use the name orthodox, but you are not. What can I say, God is patient for His children; you have some time to ask apology from God and to be his child again. you are on wrong way

  ReplyDelete
  Replies
  1. EBAKACHIHUN BEMANAWKEWU ANZEBARK ENASTEWUL MESTEHAF KIDUS MIN ENDEMIL ENASTEWUL YEABATOCHIN TIRGAUMIE YEGLESTELIN AMEN

   Delete
 57. ተስፋ ነኝ

  you are very funny . The way you are trying to criticise the teaching of Ethiopian Orthodox Tewahedo church is illogical. I should say: you are tehadiso and real menafic, heretic.

  We the laity of EOTC plead & pray befor St Mary in order to get mery from her So, God the Son & incarnated Word of God.

  Repent and cry before our Mother St Mary if you really neeed salvation from the King of the Wodl, Almighty God.

  ReplyDelete
 58. ተስፋ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክህ፡፡

  ReplyDelete
 59. በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ይሰራ የነበረው ዘንዶው አብቅቶለታል፡፡ ከዚህ በሁዋላ የእግዚአብሔርን ክብር ማንም ፍጡር አይወስድበትም፡፡ ክብር ለኃያል ስሙ ይሁን! አሜን!

  ReplyDelete
  Replies
  1. አያችሁ ዲያቢሎስ የድንግልን ምስጋና ሲቃወም እግዚአበሔር ሊያድን የወደደውን የእናቱን ፍቅር ያሳድርበታል ቅድስት ቤተክርስያን እንዳስተማረችን ልቦና ይስጣችሁ ፋንቱ ግን ምስጋናሽ ይቀጥል

   Delete
 60. አያችሁ ዲያቢሎስ የድንግልን ምስጋና ሲቃወም እግዚአበሔር ሊያድን የወደደውን የእናቱን ፍቅር ያሳድርበታል ቅድስት ቤተክርስያን እንዳስተማረችን ልቦና ይስጣችሁ ፋንቱ ግን ምስጋናሽ ይቀጥል

  ReplyDelete
 61. Aba Selamawoch, Min ayinet nachihu...endet endetebarekachihu..Yigebachihual!!?? May God....You are so blessed. You are doping great. I know it is because of God our father. Beritu Beritu...teberatu....MenifesKidus Yaberitachihu.........Owwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwwww I really Loved and Love youuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuuu..

  ReplyDelete