Friday, May 30, 2014

በአቡነ ጳውሎስ ላይ ሲፈጸም የቆየው የሊቃነ ጳጳሳቱ አድማና የማኅበረ ቅዱሳን ጣልቃ ገብነት በአቡነ ማትያስ ላይም ቀጥሏል!

Read in PDF

ምንጭ፡- ደጀ ብርሃን
ከሊቃነ ጳጳሳቱ ግማሾቹ የራሳቸውን የጉባዔ ላይ የድምጽ ጡንቻ በማፈርጠም ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ከሚመስሏቸው ጋር የመቀናጀት ጠባያቸው ከምንኩስና ጀምሮ የተዋረሳቸው እንጂ ድንገት የተከሰተባቸው ዐመል አይደለም። ገሚሶቹ ሊቃነ ጳጳሳት ደግሞ ከዚህ ፈርጣማና  ጠንካራ የቡድን  አቅም መፍጠር ከቻሉት ጋር መለጠፍ የሚፈልጉት አንድም ብቻቸውን መዝለቅ እንደማይችሉ ስለሚያውቁ፤ በሌላ መልኩም ሊመጣ ይችላል ከሚሉት ጥቃት ራሳቸውን ለመከላከል ከመፈለግ ራስን የማዳን ዘዴ የተነሳ ነው። ጥቂቶች ቢሆኑም አንዳንዶቹ ደግሞ ያልሆነ ንትርክና ጭቅጭቅ እንዲነሳ የማይፈልጉ፤ ዝም ብለው በመመልከት ታዛቢ የሚመስሉ በእድሜ የገፉ ሲሆኑ በጣት የሚቆጠሩት ደግሞ ስለቤተክርስቲያን የሚገዳቸው ነገር ግን ድምጻቸው ብዙም የማይሰማላቸው ናቸው።

 የቡድን ኃይል መፍጠር የቻሉት አብዛኛዎቹ ሊቃነ ጳጳሳት የወጣትነት ዐመል ብዙም ያልራቃቸው፤ በቂ ኃብት ማከማቸት የቻሉ፤ ለተሸከሙት ማዕርግ ሳይሆን ለስምና ለዝና የሚጨነቁ በተለይም ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ንክኪ ያላቸው ናቸው። እነዚህኞቹ ለቤተ ክርስቲያን የሚታይ፤ የሚጨበጥ፤ ለትውልድ የሚተላለፍ ቋሚ ቅርስና ሀብት መፍጠር ያልቻሉ ነገር ግን በምላስ የሰለጠኑ፤ እምቢተኝነትና ቡድንተኝነት እውቀት የሚመስላቸው ናቸው። ቤተክርስቲያን መታመስ የጀመረችው እነዚህኞቹ ቅዱስ ወደተባለው ሲኖዶስ የመቀላቀል እድል ካጋጠማቸው በኋላ ነው።  ማኅበረ ቅዱሳንም ከሀገር ቤት እስከ ውጪ ሀገር ድረስ በቤተ ክርስቲያኒቱ መልክና ቁመና ስሩን የሰደደው በእነዚህኞቹ ጀርባ ታዝሎና ተንጠላጥሎ ነው።
የቀድሞውን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ እግር ተወርች አስረው አላሰራ ሲሉ የነበሩት እነዚህ ቡድንተኞች ዛሬም አንድ ግንባር ፈጥረው እድሜ ካላስተማራቸው አረጋውኑ መካከል ጥቂቶቹን አሰልፈው ማኅበረ ቅዱሳንን ከጀርባቸው አቁመው ፓትርያርክ ማትያስንም በተመሳሳይ መልኩ አላሰራ፤ አላንቀሳቅስ፤ አላላውስ እያሏቸው ይገኛል። በዚህ መልኩ የት ድረስ መጓዝ እንደሚቻል ለመገመት አይከብድም። ነገር ግን «ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም» እንዲሉ አበው መላ መፈለግ ፓትርያርክ ማለት «ርእሰ አበው» ማለት እንደመሆኑ መጠን የተሰጠውን ሥልጣን ለቡድንተኞች አስረክቦ የተነገረውን የሚቀበል ተላላኪ ማለት ባለመሆኑ ሥልጣኑ ሙሉዕ መሆኑን ማመን የግድ ይሆናል። ስለዚህ በአድመኝነት፤ ለማኅበሩ ወግነው አላሰራ ለሚሉ ምን መደረግ አለበት?  ነገሮች እየጠሩ፤ የችግሩም ገፈት ከላይ ካልተወገደ በስተቀር ተለባብሶ የትም አይደረስም። ቤተ ክርስቲያንም አትድንም፤ ባለማዕርጎቹም በዘመናቸው ንስሐ አይገቡም። ስለዚህ የማያወላዳ እርምጃና ውሳኔ ያለምንም ማቅማማት መውሰድ የግድ ይላል። ጥቂት ነጥቦችን እናንሳ።

1/
ከአድመኞቹ ሊቃነ ጳጳሳት መካከል ብዙዎቹ ቃል የገቡበትን መሃላ አፍርሰው የቤተ ክርስቲያኒቱ ተጠሪ ነን ካሉ በኋላ ደመወዝተኛ፤ አበልተኛና የጥቅሟ ተከፋይ ሲያበቁ መንፈሳዊነቱን ክደው፤ ሀብት ንብረት አፍርተው እንደዓለማውያኑ የሚሊዮን ብር ቤቶችን የገነቡ፤ በባንክ ያከማቹ ስለመሆናቸው መረጃና ማስረጃ የሚቀርብባቸው ስለሆነ በሊቀ ጳጳስነት ማዕርግ የእግዚአብሔርን መንግሥት ብቻ ለማገልገል  ብቃት የሚጎድላቸውና «ለሁለት ጌቶች መገዛት አትችሉም» ያለውን የወንጌል ቃል ያፈረሱ ስለሆነ ከያዙት ማዕርግ ተሰናብተው ወደዓለማዊ ሀብታቸው እንዲሄዱ ሊሸኙ ይገባል።

2/ ገሚሶቹ ሊቃነ ጳጳሳት ቃለ መሃላ ከፈጸሙበት «ኩሎ ኀደግነ» ሁሉን ትተን ተከተልንህ ካሉ በኋላ በቀጥታ ያለሰማንያ ጋብቻ በትዳር ወልደው ከብደው የሚኖሩ፤ ገሚሱም በአዲሱ የቤተሰብ ህግ እንደተመለከተው « ትዳር በሚመስል ሁኔታ አብሮ መኖር ራሱ ጋብቻ እንደተፈጸመ ይገመታል» በሚል የህግ መንፈስ መሰረት አግብተው ዓለሙም፤ ሊቀጵጵስናውም ሁሉም ሳይቀርባቸው አጣምረው የያዙ ስለሆነ በእነዚህኞቹ «ጸሊማን አርጋብ»  ላይ በቂ ማስረጃ መቅረብ ስለሚችል በማያወላዳ ውሳኔ ለሌሎች ትምህርት ሊሆን በሚችል መልኩ ለትዳራቸው ታማኝ ሆነው እንዲኖሩ በክብር መሸኘት አለባቸው።
3/ ለዚህ ጥሩ አብነትና ምሳሌ ሊሆን የሚችለው በግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከዚህዓለም በሞት የተለዩት የአቡነ ሺኖዳ አስተዳደር ተጠቃሽ ነው። ሊቃነ ጳጳሳት የራሳቸውን ሀብት ማፍራት አይችሉም። መነኮሳት ከመነኮሱበት ገዳም ውጪ ሌላ ገዳም በፍጹም አይቀበላቸውም። ከገዳሙ ከወጣ ምንኩስናውን እንደተወ ይቆጠራል። በሴት የተጠረጠረ መነኩሴ በቀጥታ ተጠርቶ ይጠየቃል እንጂ እንደኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተሸፋፍኖ ያሻውን እንዲፈጽም እድል አይሰጠውም። መረጃና ማስረጃ ከቀረበበት ቀሚሱን ከታች አንስቶ፤ እስከ አንገቱ ድረስ መሃል ለመሃል በመቀስ ቀደው መቋቋሚያ ገንዘብ ሰጥተው ሕዝባዊ እንዲሆን ያሰናብቱታል። ይህ ለሌላው ትምህርት፤ ለቤተ ክርስቲያንም ክብር ይሆናል። ነገር ግን በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ያለው ነገር በዚህ ዘመን አሳፋሪ ሆኗል። ከሊቃነ ጳጳሳቱ ትዳር የመሰረቱ ሞልተዋል። የመነኮሳት ነጋዴ መሆናቸው ሳይታወቅ ሚሊየነር ሆነዋል። ዝሙትና ስርቆት ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደነቀዝ እየበላት ነው። በዚህ መልኩ ከቀጠለች የቤተ ክርስቲያኒቱ ኅልውና አስጊ ነው። እዚህ ላይ ከነጋ ድራስ ገብረሕይወት ባይከዳኝ መጽሐፍ ጥቂት ቃል እንዋስ። «እግዚአብሔር መንግሥታችንን፤ ቤተክርስቲያናችንን ለባዕድ አሳልፎ አይሰጣትም እያለ ሕዝባችን በስንፍና ያለሥራ ይኖራል» እውነትም ብዙ ጊዜ እግዚአብሔር ከጥፋት ተከላከለን፤ ነገር ግን እኛ ለቸርነቱ የተገባውን ሥራ ሠርተን በተግባር አላሳየንም» ብለዋል ነጋድራስ በጽሁፋቸው ከዛሬ ሰማንያ ዓመት በፊት።  ይሁን እንጂ ዛሬም ከስንፍናችን ፈቀቅ አላልንም። እግዚአብሔር ራሱ ይጠብቅ ብለን እኛው ያጠፋናትን ቤተ ክርስቲያን እንደባለእዳ ትተንለታል። 

4/ ማኅበረ ቅዱሳን ማነው? የማነው? ምንድነው? ብዙ የሚያጠያይቅ ጉዳይ ነው። የጠራና የማያሻማ መልስ ያስፈልገዋል። ተለባብሶ በበግ ለምድ ተሸሽጎ አይዘለቅም። ስለማኅበረ ቅዱሳን ጥብቅና የሚቆም ማንም ቢኖር የማኅበሩ አባል የመሆን መብቱ የተከበረ ነው። ነገር ግን ሊቀጳጳስ ከሆነ በኋላ ቤተ ክርስቲያን የሰጠችውን የሲኖዶስ አባልነት ሥልጣን ይዞ የማኅበረ ቅዱሳን አባል መሆን አይችልም። መሆን ከፈለገ ጵጵስናውን ማስረከብ አለበት።  አንድ ሚኒስትር የኢህአዴግ ምክርቤት አባልና የሰማያዊ ፓርቲ አባል በአንድ ጊዜ መሆን አይችልም። አንዱን ይተዋል፤ ወደአንዱ ይጠጋል እንጂ። ይህንን ለማስተካከል የፓትርያርኩ ሥልጣን ምሉዕ ነው። እነዚህ በሁለት ልብ ሲኖዶሱን የሚያውኩ ጳጳሳት በህግ አግባብ ካልተወገዱ የሲኖዶስ ሕውከት ማብቂያ አይኖረውም። ስለማኅበረ ቅዱሳን የሚከራከር ሊቀጳጳስ ከሲኖዶስ አባልነቱ ወደታች ወርዶ የተራ ማኅበር ደጋፊ ከሆነ ማዕርጉን ተገፎ  በማኅበር አባልነቱ እንዲቀጥል ከሲኖዶስ ሊባረር ይገባዋል።
5/
ፓትርያርክ ማትያስ ቆምጨጭ ያለና እርምት የሚሰጥ እርምጃ ከመውሰድ ውጪ በእንደዚህ ዓይነት የአድማና የቡድን ጭቅጭቅ እየተሰላቹ የትም አይደርሱም። ሊቀጳጳስ የሚባለው ማዕርግ ሊከበር የሚችለው ራሱ ማዕርጉን የተሸከው ሰው አክብሮ፤ የሚያስከብር ሥራ ሲሰራበት ብቻ ነው። ሹመትማ ይሁዳም ከሐዋርያት አንዱ ነበር። ነገር ግን ጥፋት እንጂ ልማት አልሰራበትምና ሐዋርያ መባሉ ቀርቶ «ሰያጤ እግዚኡ» ከመባል አልዳነም። ስለዚህም ቤተ ክርስቲያንን ከመሸጥ የማይመለሱ እነዚህ አድመኞች ሊቃነ ጳጳሳት ሻጮች ቢባሉ ምንም አያስነውርም። ስም መጥቀስ አያስፈልግም እንጂ እነማን ማናቸው? ምን አደረጉ? ምንሰሩ? በደንብ ይታወቃል። 
6/ ቤተ ክርስቲያንን ከውድቀት ለማዳን፤ ማዕርጋት ዋጋና ክብር እንዲኖራቸው ለማድረግ ሲባል ያልተፈለገ ነገር ግን አስገዳጅ እርምጃ እስከመውሰድ የሚዘልቅ ክስተት መፈጠሩ አይቀርም።  ፓትርያርክ ከሆኑ በኋላ ከሚቆጠቁጠው የመንፈሳዊ ኅሊና ቁጭትና ከታሪክ ወቀሳ ለመዳን መስራት የሚገባውን ሁሉ ካልሰሩበት ማዕርጉን ተሸክሞ መቀመጥ በቤተክርስቲያን ውድቀት ላይ መተባበር በመሆኑ ሹመቱን አስረክቦ የራስን ነጻነት ማወጅ የተሻለ ነው።
በአቡነ ጳውሎስ ላይ ሲፈጸም የቆየው የሊቃነጳጳሳቱ አድማና የማኅበሩ ሴራ በአቡነ ማትያስም ላይ የሚቀጥለው  እስከመቼ ነው?
 አቡነ ማትያስ አርፈው የማኅበሩ አባል ሊቀ ጳጳስ ሌላ ፓትርያርክ እስኪሆን ድረስ ይህ ውጊያ አያቆምም።

42 comments:

 1. nice point. really really

  ReplyDelete
 2. Oh my God. .betam yasferal.

  ReplyDelete
 3. በአዲስ አበባ ያለችሁ የቅዱስ ስኖዶስ ሊቃነ ጳጳሳት ልብ ገዝታችሁ ከስደተኛው ስኖዶስ አባቶች ተማሩ። ጉባኤያቸው ደስ ያሰኛል ።ማቅን ነቅለው በማዉጣት የተቀደሰ ጉባኤ በሰላም በመጀመር በሰላም ጨርሰዋል። አጅግ ደስ ያሰኛል። በሀገር ቤት ያለችሁ አባቶቻችን ግን የማህበረ ቅዱሳን ስጦታ አይኖቻችሁና ልቦናችሁ ደንድኖዋል። ከእግዚአብሔር ይልቅ ማህበርን በማስቀደምና በማምለክ ላይ ናችሁ፡፤ እጅግ አሳዛኝ አሳፋር ስራ እየሰራችሁ ናችሁ። ትላንትና በአቡነ ጳዉሎስ ላይ ማቅ ያደረገውን የከፋት ስራ አሁን ጀምሮዋል። እባካችሁ ሀብቱም ሁሉ ይበቃችዋል። ለእግዚአብሔር ክብር ቁም ። ጠላቶቻችሁን ውደዱ። እንደ ቃሉ መናገር ብቻ ሳይሆን ክእናንተም ምሳሌነት እንጠብቃለን።ቤተ ክርስቲያናችንን በሌሎችን ዘንድ አሳፈራችሁ; በመናፊቃን ዘንድ ተመልክቱ የኦርዶክስ አባቶች በጥምና በስልጣልን ስጣሉ ስሰዳደቡ እያሉ ማስተማርያ አድርገዉናል። ይበቃል ይበቃል ይበቃል ከማህበር ይልቅ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ፍሩ።!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማህበረ ቅዱሳን የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጅ ነው!June 3, 2014 at 3:50 AM

   አይ መናፍቅ እንዲሁ ሀሰት ታወራለህ። ማህበሩ ምን እንደሚሰራ ማህበሩን የሚደግፉት ጳጳሳት ማን እንደሆኑ ታወቃለህ። ሀሰት የአባትህ የዳቢሎስ ነው

   Delete
 4. አይ መናፍቅ እንዲሁ ሀሰት ታወራለህ። ማህበሩ ምን እንደሚሰራ ማህበሩን የሚደግፉት ጳጳሳት ማን እንደሆኑ ታወቃለህ። ሀሰት የአባትህ የዳቢሎስ ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማኅበሩ የዲያቢሎስ ቀኝ መሆኑን እና አባቱም ዲያቢሎስ መሆኑን አሳምረን እናውቃለን፡፡

   Delete
  2. ማቅን ጠንቅቀን እናዉቀዋለን ። መንፈሳዊ ቃል እየተናገር ግን የፓለትካ አላማ ያለው በቅዱሳንና በአምላክ እናት ስም የምነግድ ድርጅት እንድሆ ማንም የተዋህዶ እውነተኛ ክርስትያን ያውዋል።ከቅዱስ ስኖዶስ ፈቃድን ስርዓት ዉጪ በመርካቶና ራጉኤል ቤተ ክርሰቲያን የከፈተቸው የንግድ ደርጆቾች በራሱ ነጋዴ መሆን እንጅ መንፈሳዊ ማህበር መሆኑን ይገልጻል።ቅዱስ ስኖዶስና ፓትርያርኩን አንኳን አያምንባቸውም አያከብራቸውም ። ስለዚህ ማቅ በቅዱስ ስም ተደብቆ የተዋህዶ ልጆች ተሐድሶ እያለ ሰላም እንዳይፈጠር መለያየት እንድሰፋ እያደረገ ነው። ማቅ በዚህ አማጹ እናውቀዋለን።

   Delete
  3. ባታዉቁት ነበር የሚደንቀዉ። ኑፋቄያችሁን እንደፈለጋችሁ እንድታሰራጩ እንቅፋት እንደሆነባችሁአለቆቻችሁ በዉጭ እየጮሁ እየነገሩን ነዉ። ይህ ደግሞ ለማኅበሩና ለኛ ለአላማዉ ደጋፊዎች የበለጠ ብርታት ነዉ። መስላችሁ ነዉ እንጂ እግዚያብሔር ያስነሳዉን ማንም አያቆመዉም። ይልቅ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ ዛሬም አልረፈደም....

   Delete
 5. ጥሩ እይታ ነው

  ReplyDelete
 6. እዉነት ያሸንልMay 30, 2014 at 11:48 PM

  መናፍቃን! መናፍቃን! መናፍቃን! መናፍቃን! መናፍቃን! መናፍቃን! መናፍቃን! መናፍቃን!
  እግዚአብሄር ቤተክርስቲያንን ይጠብቃል::
  በበግ ለምድ ተሸፍናችሁ ትናገራላችሁ:: ግን አይሳካላችም ::
  እግዚአብሄር ልቦና ይስጣችሁ::

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማነህ ደግሞ አንተ ማፈሪያ ጽኁፉን መዝነህ አስተያየት እንደመስጠት የፈሪ ዱላህን ታስወነጭፋለህ። እንደ አንተ አይነቱ ትክክለኛ መልዕክትን አጣሞ የሚያነብ ነው የበግ ለምድ ለባሽ ተኩላ። አትድረቅ ትንሽ ወዝ ይኑርህ

   Delete
  2. እውነት ያሸኝፋል? እውነት ግን ምንድን ነው? ለመሆኑ ገብቶሀል። እውነት ኢየሱስ ነው እሱን ተቀበልና ዳን

   Delete
 7. አይ የዲያቢሎስ ምክር ዝናርህን እስክጨርስ ተዋጋ ማህበሩ ስለ እውነት ስለሚሰራና እውነተኛ የኦርቶዶክስ ጠበቃ ስለሆነ ጌታ አብሮት አለ ለክደታችሁ መግቢያ አጣችሁ

  ReplyDelete
 8. አይ መናፍቅ እንዲሁ ሀሰት ታወራለህ። ማህበሩ ምን እንደሚሰራ ማህበሩን የሚደግፉት ጳጳሳት ማን እንደሆኑ ታወቃለህ።

  ReplyDelete
 9. ምን አይነት አሉባልተኛ ናችሁ???

  ReplyDelete
 10. ደፋር ዝም ብለህ ትለፈልፋለህ፡፡ ለመሆኑ አንተስ ምን እየሰራህ እንደሆነ ልብህ ያውቅ የለም፡፡
  ሁሉም እንደ ሰው ፈቃድ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሆናል፡፡

  ReplyDelete
 11. Yewochiwo sinodos westem yemibetebet mk aleko....andwalem yemibal...semonoun berasu serg layem sibetebet neber.

  ReplyDelete
 12. ይህ ሁሉ ሲሆን አቡነ ማትያስ ባገር አሉ እንዴ ካሉስ የድረሱልኝ ጥሪ አያሰሙም?ሰው ዓይኑ እያየ
  እንዴት ዕኮ ዕመቅ ይወርዳል። ሀይ ባይ ከሌለ ዕኮ ወፎችም ብዙ አዝመራ ያወድማሉ።እናም እያንዳንዱ
  እያናወዘ አስተዳደር ሲበላሽ ዕርማት ካልሰጠ ስንኳን ለሌላው ለራሱም ባለመሆን ከገደል አፋፍ ላይ ነው
  አይጣል!!!

  ReplyDelete
 13. በትክክል ተገልጿል። በመንግስት የደኅንነት ኃይል ትብብር የእያንዳንዱን ሊቀጳጳስ ታሪክ የሚያጠና ቡድን አቡነ ማትያስ በምስጢር አዋቅረው የተገኘውን መረጃ መነሻ በማድረግ ትምህርት ሊሆን በሚችል መልኩ ዱርዬ ጳጳሳት ተገፈው ወደመነኮሱበት ገዳም ለንስሐ መላክ አለባቸው። እንደደካማ የሚቆጠሩት አቡነ ተክለሃይማኖት እንኳን አቶ ኢያሱ ብለው አባ ገብርኤልን አባረው አልነበር? ኋላ ንስሐ ገብቻለሁ፤ ተጸጽቻለሁ ብለው በምህረት ተመለሱ እንጂ። ዱርዬና አድመኛ ለማባረር አቡነ ማትያስ የማንም እርዳታ አያስፈልጋቸውም። መረጃው ካለ በቂ ስልጣን አላቸው። ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተም ከአቅሜ በላይ ስለሆነ መቆጣጠር አቅቶኛል ብለው ለመንግስት ደብዳቤ መጻፍ ብቻውን በቂ ነው። ይሄ ማፊያ ድርጅት የእውነት ሁሉ ጠላት!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Mk Enquan beMatias(Sliper) BePawlos(wardiya) altechalem. kezih behuala Lemengistim Ayichalim.Diro neber Enji...

   Delete
  2. Mk is already matured, just it is out of the control of Aba Matias(EPRDF pupit) even EPRDF itself couldn't Control.The Senod members, All church futhers, sundayschool, parish council, university students are with MK. hereafter no one can tach his hand. chaw tehadiso,chaw EPRDF, chaw Matias(Pupit) long live Tewahido.

   Delete
 14. yihin hulu yemiseraw tinish Diablos, hager kehadi CIA, BAYABL endehone sintu yawikal.Abatochin andun bedilela lelawn bedula eyasferara papasat yemiridulet mela bifelegilet senodos selam yihon neber. yemigermegn yeabune matias & yepapasat wodaj mesay tamagn memiselu new, seytan.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Bayabl enquan senodosin, Mkn yiselilal,but he likes MK & ready to give every thing even his life for TEWAHIDO. I know him, He hate untitewahido forces aggressively specially Tehadiso & idiot poletical forces which are trying to interfere in the cherch matters.

   Delete
  2. Mk minlemalet new? Mk tabot & Woyane-dagon/ MK -God& woyane-satan lemalet new? tewu

   Delete
  3. yegziabherin sira leand9bayabl0 baiseti, Egziabher sew bilo yakeberewin diablose maletu min yitekimal, Aba Matiasen Ena Bayablin Meleyayet Yemichal ayimesilegnim mikiniyiatum lezih kibir yabekachewin Keegziabher ketilo mechem yemiresut ayimesilegnim, bayabl endehone minim belut keasebew ayimelesim minim bibal ayiberdew /ayimokew.Entseliy.

   Delete
 15. Mk killer of our true church father's now will plan to kill Aba Mathias. Death to Mk and their supporters. Erget kale the leader of mk church in Atlanta GA was slept in Motel six with one of mk wife. Attached pictures of both.

  ReplyDelete
 16. The truth never die. yes Patiraric Mattas have a fully power to make decision. he is the leader of our great church. simple question, why our archbishops worry about MK ? MK is not God , not holy angles, not senodos, not government and not united nation . so MK is nothing nothing nothing. just business and hiding political group. that is it........

  ReplyDelete
 17. Tera wore. Any layman can easily decrypt the secrete agenda you trying to propagat. I'm afaird for you because MK will continue to flourish despite the challenges.

  ReplyDelete
 18. sorry , I know Mahbere Kedusan is anti protestant inside the Orthodox church . Devil will crud . no matter GOD will keep our church or his house.

  ReplyDelete
 19. ማኅበረ ቅዱሳን ማነው? የማነው? ምንድነው? ብዙ የሚያጠያይቅ ጉዳይ ነው። የጠራና የማያሻማ መልስ ያስፈልገዋል። ተለባብሶ በበግ ለምድ ተሸሽጎ አይዘለቅም። ስለማኅበረ ቅዱሳን ጥብቅና የሚቆም ማንም ቢኖር የማኅበሩ አባል የመሆን መብቱ የተከበረ ነው። ነገር ግን ሊቀጳጳስ ከሆነ በኋላ ቤተ ክርስቲያን የሰጠችውን የሲኖዶስ አባልነት ሥልጣን ይዞ የማኅበረ ቅዱሳን አባል መሆን አይችልም። መሆን ከፈለገ ጵጵስናውን ማስረከብ አለበት። አንድ ሚኒስትር የኢህአዴግ ምክርቤት አባልና የሰማያዊ ፓርቲ አባል በአንድ ጊዜ መሆን አይችልም። አንዱን ይተዋል፤ ወደአንዱ ይጠጋል እንጂ። ይህንን ለማስተካከል የፓትርያርኩ ሥልጣን ምሉዕ ነው። እነዚህ በሁለት ልብ ሲኖዶሱን የሚያውኩ ጳጳሳት በህግ አግባብ ካልተወገዱ የሲኖዶስ ሕውከት ማብቂያ አይኖረውም። ስለማኅበረ ቅዱሳን የሚከራከር ሊቀጳጳስ ከሲኖዶስ አባልነቱ ወደታች ወርዶ የተራ ማኅበር ደጋፊ ከሆነ ማዕርጉን ተገፎ በማኅበር አባልነቱ እንዲቀጥል ከሲኖዶስ ሊባረር ይገባዋል።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ማህበረ ቅዱሳን የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጅ ነው!June 3, 2014 at 11:46 PM

   menafqqqqqqqqqqqqqqqq!!!

   Delete
 20. Abaselama is the voice of voiceless, and also the true source of information in regarding to EOTC. When I saw the gangster picture of
  Aba Abrham just reminded me his back ground. He is totally not priest because a biological father of two kids. Here in GA , he was appointed Kesis Yacob ,he from Gojam, as priest. Kesis yacob was married in Canada and father of two in his first wife. After all, he moved to USA and remarried another woman and father of three daughter. Criminal Aba Abrham if you are Gojam blood, he will give kehinet in Muslem. He will be fire from EOTC NOT ONLY IN HOLY SYNOD. Death to MK, and Idiot papas such like Aba Abrham.

  ReplyDelete
 21. የዚህ ጽሁፍ አቅራቢ አላዋቂነቱን የገለጠበት የቤተክርስቲያንን ስርዓት ልክ እንደካድሬ እንዲመራ የሚፈልግ ይመስላል፡፡ ፓትርያሪኩ የሚሉትን እሺ ብሎ ያልተቀበለ ከስልጣኑ ይሻር አይነት ትዕዛዝ
  ተጠሪነታቸዉ ለቅዱስ ሲኖዶስ የሆኑት ፓትርያሪክ በአንባገነንነት የራሳቸዉን እና የላካቸዉን አካል አጀንዳ በግድ ተቀበሉ ብሎ ማስገደድ ምን የሚሉት መሪነት ነዉ፡፡ በአንባገነኖችስ የቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚደናቀፈዉ እስከመቸ ነዉ? አባቶቻችን ሆይ ለቤተክርስቲያን ሥርዓት መንፈሳዊዉን ተጋድሎ ተጋደሉ፡፡ አቤቱ ለቤተክርስቲያን ቅን እና አርቆ አናቢ መሪን ስጥልን

  ReplyDelete
 22. Mk yelelewo meangeste. semayat worst bicha new.except in heaven you will find them every where. Siyamesuna betun sibetebet siyasademu beye sira botawo Yesewo
  sim siyatefu.

  ReplyDelete
 23. Mr. Mesfin who was fired from eotc with violation of church rule in addition to acted as gay with Aba Abrham came Atlanta to preach bible. It is shame on him morally no more power to do any thing in EOTC. Some AIDS carriers mk elements married in GA that was violated in USA law. Mesfin came to preach in this wedding ceremony.

  ReplyDelete
 24. I know MK has done so many blunders, but it does nto deserve to die or be destroyed. Aba Mathias is tryingt to destroy MK to please the Weyane regime and the racists around them.

  Having said that, MK needs to apologize to all folks whom it has attacked, blackmailed and tarnished without any objective ground in the name of defending the EOTC. Again, MK has to repent and correct itself from the kind of mistakes it has committed over the last 23 years, like for example the numerous groundless defamation of innocent folks. Then, after the self corrective measures and reconcilation with chruch elements, MK can them become a very positive element in the church and continue to play important roles in advancing/modernizing the chruch and spreading the word of God. The idea of eliminating MK is not a good idea. How long are we going to continue to believe "annihilation" is the solution. I say to you that "reconciliation" is the only and best solution for the problem that the EOTC is facing.

  ReplyDelete
 25. እናንተ መናፍቃን ማህበረ ቅዱሳን ማን እንደሆነ ታዉቃላችሁ!
  ጀርባችሁንና ሰራችሁን ስለሚያዉቅ/ስለሚያጋልጥ የቤተክርስቲያኒቱ አባል ሳትሆኑ ቤተክርስቲያናችን እያላችሁ ህዝቡን ማደናገር እንደትችሉ ስለአደረገ እርሱን ለመፍረስ የምትፈነቅሉት ድንጋይ የለም
  ማህበሩ በስራዉ ሁሉ እግዚአብሔርን ስለምያስቀድም አመናቸሁም አለመናችሁን ማህበሩ በእናንተ(በመናፍቃን) የፈጠራ ስም ማጥፋት ወሬ አይፈርስም

  ReplyDelete
 26. Ahun ende mk menafek ale????? Sime mawotat lelilawo setawokubet!!! Menafk ye mk lela semu new.yewengel sheftoch .yodabisinya drama siru .mata yemtchefrubet
  bota ken ya drama lemiserawo sewoye eyekeflachu sherbet feteru.

  ReplyDelete
 27. Most mk women suffering from Aids and Tb. Atlanta couple may be victomized same as mr. Mesfine.

  ReplyDelete
 28. ጀግናው ማህበረ ቅዱሳን ለነፍሳችን መዳን ስለቆምክልን በጣም እንወድሀለን

  ReplyDelete
 29. Patriarch Mathias is unique hero in Eotc history. Almost 99% of Ethio American supporting him. Because he standing to the church not for Mk.

  ReplyDelete
 30. Kemahberkidusan lay wredu manim Aysemachihum! if u are christian uwill never talk such bad thigs on spritual fathers ! kenanteHatiyat yelelebet....

  ReplyDelete