Sunday, June 29, 2014

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቀጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዳንኤል ላይ የገዳሙ መነኮሳት አድመው በረሃብ እየቀጧቸው መሆኑ ተሰማ

Read in PDF

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ በሆኑት በብፁዕ አቡነ ዳንኤል ላይ አባ ገብረ ወልድ በተባሉ መነኩሴ አሳዳሚነት ሊቀጳጳሱ ላይ ልዩ ልዩ የአድማ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆናቸውንና ሊቀጳጳሱ ላይ አደጋዎች መደቀናቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ፡፡ ብፁዕነታቸው የሲኖዶስን ስብሰባ ለመካፈል ከመጡ ወዲህ ተመልሰው ቢመጡ አናስገባቸውም በሚል የተጀመረው አድማ ምግብ እንዳይቀርብላቸው፣ ሾፌራቸውም መኪናቸውን እንዳያንቀሳቅስ እስከ ማሳደም የደረሰ አሳዛኝ እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑን ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን ይህም ድርጊት በአንዳንድ ክፉ ቀን ግብጻውያን መነኮሳት ኢትዮጵያውያን መነኮሳት በበሽታና በረሃብ እንዲያልቁ ለማድረግ በራቸውን ዘግተውባቸው እርዳታ ሳያገኙ እንዲሞቱና ገዳማቶቻችን ያለ ሰው እንዲቀሩ ለማድረግ ከሚጠቀሙባቸው በጭካኔ የተሞሉ ስልቶች ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ከዚህ እርምጃ በስተጀርባ የማን እጅ እንዳለ ለጊዜው የታወቀ ነገር ግን የለም፡፡

Wednesday, June 25, 2014

ተአምረ ማርያም የተባለው መጽሐፍ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን እናት የቅ/ማርያምን የቅድስና ባህርይ አይወክልም!

Read in PDF

ምንጭ፡-ደጀ ብርሃን
(እዝራ ስነ ጽሁፍ፤ ዘላለም መንግሥቱ)

ተአምረ ማርያም የተባለው መጽሐፍ እንደ ስያሜው ሁሉ ማርያም ንዳደረገቻቸው  የሚነገሩ  የብዙ  ተአምራት  መድብል  ነው።  ከተአምራቱ በጣም  ጥቂቱን  ሕጻኑ  ኢየሱስ  ያደረጋቸው  ሲሆኑ  ብዙዎቹን  ማርያምና የማርያም  የተለያዩ  ስዕሎች  ናቸው  ያደረጉት።  አንዳንዱ  ምዕራፍ  ምንም ተአምርነት  የሌለበት  የተደረጉ  ነገሮች  የተዘገቡበት  ዘገባ  ቢሆኑም በእያንዳንዱና  በሁሉም  ምዕራፎች  መግቢያ  ወይም  አናት  ላይ  ማርያም ያደረገቻቸው  ተአምራት  እንደሆኑ  በቀይ  ቀለም  እየተጻፈ  በአንቀጽ ተቀምጦአል።  ተአምር  ባልሆኑት  ላይ  በአናቱ  ላይ  የማርያም  ተአምር መሆኑን  መጻፉ  የግድ  መሆን  ስላለበት  የተደረገ  ይመስላል።

ለምሳሌ፥ ሁለተኛው  ተአምር  ወይም  ምዕራፍ  ማርያም  ስለ  መጸነሷና  ስለ  ልደቷ የተነገረ  ሲሆን  ያው  የግዴታ  ልማድ  ሆኖ  ክብርት  እመቤታችን ያደረገችው ተአምር ተብሎ ተጽፎአል። ያለዚያ እንደ ምዕራፍ 2 መግቢያ ማርያም  ገና  ከመጸነሷና  ከመወለዷ  በፊትም  ተአምር  ታደርግ  ነበርና ከልደቷ  በፊትም  ቀዳሚ  ኅልውና  ነበራት  ማለት  ይሆንአጻጻፉ ይመስላል። ከሆነ ዘላለማዊት ናት ሊሰኝ ይመስላል።  የመጽሐፉ አሳታሚና ባለቤት ማን ነው? ይህኛውን  (እኔ  ያነበብኩትንእትም  ያተመው  ተስፋ  ገብረ  ሥላሴ ማተሚያ  ቤት  ሲሆን  አሳታሚው  አልተጻፈም።

Sunday, June 22, 2014

ይህ ነው ተሐድሶ! (ክፍል ሁለት)

                                   ምንጭ፡-ተሃድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብሎግ
በክፍል አንድ ጽሑፍ “ይህ ነው ተሐድሶ” በሚል ርእስ የተሐድሶን ትምህርት መግለጥ መጀመራችን ይታወቃል፤ተሐድሶ፣ ተሐድሶ ሲባል እሰማለሁ፤ አንዳንዶች ደግሞ ተሐድሶ እውነተኛውን ትምህርት ለመለወጥ የመጣ አዲስ ትምህርት ነው ይላሉ፤ በእርግጥ ተሐድሶ አዲስ የመጣ እንግዳ ትምህርት ነውን? ለመሆኑ የሚታደሰው ምኑ ነው?”  በሚል ጥያቄ መነሻነትም የምናገለግለው ተሐድሶ (1) የትምህርተ ሃይማኖት ተሐድሶ (2) የክርስቲያናዊ ሕይወት ተሐድሶ እና (3) የሥርዐትና የአስተዳደር ተሐድሶ እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ ከሦስቱ ዋና ዋና የተሐድሶ መስኮች አንዱን በመውሰድ ተሐድሶ ምን እንደሆነ ለማሳየትም ሞክረናል፤ ከዚያው የቀጠለው እነሆ!   

1.    ዋናው ነገር አንድ ነው፡፡
1.1. ማርታን ወደ ማርያም የመቀየር ተሐድሶ
ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ቃል ካልተመለሱ ወደ እግዚአብሔር አይመለሱም፤ ጌታ እንዳለው  “የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች፤ ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።” (ሉቃ.10፥42)፡፡ እነማርታ ቤተ ክርስቲያኑን ሞልተውታል፤ ዳቦ ጋግሩ፤ ወጥ ሥሩ፤ልብስ እጠቡ፤ከበሮ ምቱ ሲባሉ አይሰለቻቸውም፤ የክርስቶስን ወንጌል ተማሩ ሲባሉ ግን እንኳንስ ሊማሩ የሚማሩ እኅቶችና ወንድሞችን እንኳን ማየት አይፈልጉም፡፡ በዓመት አንድ ቀን የጥምቀት በዓል ሲመጣ ለማይሰማ ታቦት መንገድ ይጠርጋሉ፤ ምንጣፍ ያነጥፋሉ፤ ጉልበታቸውን ሳይሰስቱ ያገለግላሉ፤ የሚሰሙት ወንጌል ግን የለም፤ የእነዚህ ሰዎች አገልግሎት የቅናት እንጅ የእምነት አይደለም፡፡

Thursday, June 19, 2014

ማቅ ፖለቲካዊ ሥልጣንን ለመጨበጥ በሚያደርገው እንቅስቃሴ “ቅምጥ ኃይሌ” እያለ ሲኩራራበት የነበረው ማኅበር ታገደየማቅ ሰዎች ለክፉ ቀን ያስቀመጥነው ቅምጥ ኃይል እያሉ ሲመኩበት የነበረው ከጥምቀት ተመላሽ ወጣቶች ማኅበር መታገዱ ተሰማ፡፡ ኅብረቱ የታገደው ከቋሚ ሲኖዶስ በተጻፈ ደብዳቤ ነው፡፡ ኅብረቱ ፈቃድ አግኝቶ የነበረው ከማቅ ጋር በሚገባ እየተናበቡ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን የግል ጥቅማቸውን ለማካበትና ለማቅ ሲሰሩ በነበሩት የቀድሞው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በአባ እስጢፋ አማካይነት ነው፡፡ ቋሚ ሲኖዶስ ፈቃዱ የተሰጠው ከቃለ ዐዋዲውና ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ በመሆኑ የተሰጠው ፈቃድ እንዲነሣና ሀገረ ስብከቱ በአስቸኳይ ሪፖርት እንዲያደርግ ውሳኔ መስጠቱን ሀገረ ስብከቱ ይዲድያ ለተባለውና በሕገወጥ መንገድ ዕውቅና ለሰጠው ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ ላይ የገለጸ ሲሆን ፈቃዱም የተሰረዘ መሆኑን ጨምሮ አስታውቋል፡፡

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ከማቅ ጋር እየተመጋገቡ የሚሰሩት የግል መጽሔቶችና ጋዜጦች ግን የታገደው ይዲድያ የጠባለ አንድ ማኅበር ሳይሆን የብዙ ማኅበራት ኅብረት እንደሆነና በኅብረቱ ውስጥ የሚገኙ ማኅበራትም ከ2 መቶ ሺህ በላይ አባላት እንዳሏቸው በመዘገብ ይህን ህብረት ማገድ ቤተክርስቲያን ላይ ትልቅ አደጋ እንደሚደቅን ተቀባብለው ዘግበዋል፡፡ ለምሳሌ ፋክት የተባለው መጽሄት ህብረቱ በስሩ 86 ማኅበራትን ያቀፈና ከ2 መቶ ሺህ በላይ አባላትም በስራቸው እንዳሉ አድርጎ ዘግቧል፡፡ 

Friday, June 13, 2014

የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ እንስበክ

Read in PDF

ሁሉም ወንጌል እሰብካለሁ ይላል፡፡ ወንጌልን መስበክ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቀው ግን “ወንጌልን እሰብካለሁ” የሚለው ሁሉ አይደለም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ውስጥ ያላለፈ ሰው የሚመላለሰው በልማድ ስለሚሆን ወንጌልን መስበክ ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ በቅጡ አይረዳውም፡፡ ወንጌል እሰብካለሁ እያለ የሚሰብከው ግን ወንጌል አይደለም፡፡ ሌላ ወንጌል ነው፡፡ ልዩ ወንጌል ነው፡፡ ያልተቀበልነው ወንጌል ነው፡፡ ወንጌል ስለኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የሚሰበክ የምሥራች ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም መሰበክ ያለበት ለሰዎች ሁሉ የምሥራች የሆነው የተሰቀለው ኢየሱስ ብቻ እንደሆነ አስረግጦ ይመሰክራል፡፡ የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንመልከት፡፡

  •   “እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን፤” (የሐዋ. 13፡32
  • እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር “ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።” (የሐዋ. 14፡15
  • “መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥” (1ቆሮ. 1፥23
  •  “ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤ በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ። እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ … እንግዲህስ እኔ ብሆን እነርሱም ቢሆኑ እንዲሁ እንሰብካለን እንዲሁም አመናችሁ።” (1ቆሮ. 15፡1-4፣11
  • “ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥” (2ቆሮ. 4፡5)

Monday, June 9, 2014

ይህ ነው ተሐድሶ!

Read in PDF

(ተሐድሶ፣ ሰኔ 2 ቀን 2006 ዓ.ም.)ጥያቄ ፩፡ ተሐድሶ፣ ተሐድሶ ሲባል እሰማለሁ፤ አንዳንዶች ደግሞ ተሐድሶ እውነተኛውን ትምህርት ለመለወጥ የመጣ አዲስ ትምህርት ነው ይላሉ፤ በእርግጥ ተሐድሶ አዲስ የመጣ እንግዳ ትምህርት ነውን? ለመሆኑ የሚታደሰው ምኑ ነው?
መልስ፡
፩) ተሐድሶ እንግዳ ትምህርት ሳይሆን የእግዚአብሔር አሳብና የማይቋረጥ መንፈሳዊ ሂደት ነው፡፡

ተሐድሶን እንደመናፍቅነት የሚያዩ ራሳቸውም ቢሆኑ ዘወትር በሕይወታቸው ተሐድሶ የመሚከናወንባቸው እንጂ በአሳብ እንደሚቃወሙት ሁሉ በተግባር በሕይወታቸው እንዳይፈጸም ሊያደርጉት የሚችል ነገር አይደለም፡፡ ልዩነቱ እኛ ተሐድሶ በእግዚአብሔር ጸጋ የሚከናወን ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑን ስናምን ተቃዋሚዎቹ ደግሞ በመሰላቸው መንገድ የእግዚአብሔርን አሳብ ሲቃወሙ እግዚአብሔር ግን በቸርነቱ ባለጸጋ ስለሆነ የተሐድሶ ተግባሩን ሳያቋርጥ የሚፈጽም መሆኑ ነው፡፡ 
ለምሳሌ ለ1600 ዓመታት በግብፅ አስተዳደር ሥር የነበረችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ፈቃድ ስለሆነ ራሷን ማስተዳደር መቻልዋ የቤተ ክርስቲያኗ ተሐድሶ መሆኑን ማንም ይረዳዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ራሷን ማስተዳደር መቻልዋ እንግዳና እግዚአብሔር የማይወድደው ነገር ሳይሆን ቀድሞም እግዚአብሔር የሰጣትን መብት በተንኮል ግብፃውያን ከልክለዋት ሲኖሩ እግዚአብሔር ያለው (የፈቀደው ነገር) በሰው ተንኮል ከመፈጸም የማይከለከል በመሆኑ ቤተ ክርስቲያኗ እግዚአብሔር የወደደውን ነገር ማድረግ መቻልዋ ተሐድሶዋ ነው፡፡ ተንኮለኞች ፈቃደ እግዚአብሔርን አፈረሳችሁ፤ የሃይማኖት ሥርዐትን ለወጣችሁ ብለው ኢትዮጵያውያንን ቢያወግዙ እንኳን ሐሰተኞች እነርሱ እንጂ ኢትዮጵያውያን ሊሆኑ አይችሉም፡፡ 

Saturday, June 7, 2014

መንፈስ ቅዱስ ግን ለምንድር ነው የተረሳው?


Read in PDF 

የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ በጻድቃን በሰማዕታት፣በመላዕክት፣ በሥላሴ፣ በኢየሱስ፣ በአብ … ሥም “በመታሰቢያነት” የተሰሩ የገጠር አጥቢያ፣ አድባራት፣ ገዳማትና ካቴደራሎች አሏት፡፡ ከእነዚህ እልፍ ሺህ “አብያተ ክርስቲያናት” መካከል የመንፈስ ቅዱስን “መታሰቢያ ህንጻ” ማግኘት በምድረ በዳ መልካም ጥላ የመፈለግ ያህል እጅግ ይከብዳል፡፡ለምን ይሆን? … (በእርግጥ የመንፈስ ቅዱስ አማናዊ ማደርያ ቅዱሱ በጌታ ቤዛነት ያመነ አማኝ ሰውነት ቢሆንም! (1ቆሮ.3፥16፤ሮሜ.8፥9) የንጽጽሩም አላማ ስለመንፈስ ቅዱስ ያለንን ግንዛቤ አናሳነት ለመታዘብ እንጂ ድካምን ለማጉላት ከማሰብ አይደለም፡፡)

  መንፈስ ቅዱስ ለሐዋርያት የወረደበትን ዕለት የክርስቶስን የማስታረቅ አገልግሎት ተንትኖ የጻፈው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “የቤተ-ክርስቲያን የልደት ቀን” ይላታል፡፡ ቤተ-ክርስቲያን የምትባለው የምዕመናን አንድነት የምትወለደው በመንፈስ ቅዱስ ስትጠመቅ ብቻ ነው፡፡የቤተ-ክርስቲያን የመኖር ህልውናዋ ÷ ኢየሱስን ክርስቶስ ነው ብላ የመስበክ ኃይልዋ እርሱ የብርታት መንፈስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡

Wednesday, June 4, 2014

ሃያ አራቱ ግዴታዎችና ድንጋጌዎች የአባ እስጢፋ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መነሣት ለማቅ ራስ ምታት የሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች(ክፍል ሁለት)

Read in PDF

የዘንድሮው የግንቦት ሲኖዶስ ስብሰባ ሃያ አራቱ ግዴታዎችና ድንጋጌዎችን መሠረት አድርገው በተነሡ ጉዳዮችና በሌሎችም አጀንዳዎች ሲነጋገር ሰንብቶና ውሳኔዎችን አሳልፎ መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ ሃያ አራቱን ግዴታዎችና ድንጋጌዎች አስመልክቶ ከስብሰባው ሰዓት ውጪ በማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች “እንዲህ በሉ፣ እንዲህ ተከራከሩ…” እየተባሉ እንደተሞሉ ወደስብሰባው አዳራሽ በመግባት ውሳኔ የተሰጠባቸውን አጀንዳዎች ጭምር እየቀሰቀሱ ወደኋላ ሲመልሱ የነበሩ አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ጳጳሳት ነበሩ፡፡ ሆኖም በፓትርያርኩ በሳል የስብሰባ አመራር ችሎታ ወደኋላ ሊመለሱ የታሰቡ አጀንዳዎች ማቅ እንደጠበቀው ወደኋላ ሳይመለሱ፣ ጳጳሳቱ የተሞሉትን ካፈሰሱ በኋላ “ይህን ጉዳይ ስለጨረስን ወደኋላ አንመለስም፤ ወደሌላው ጉዳይ እንለፍ” እያሉ አቅጣጫ በማስያዝ የመሪነት ሚናቸውን እንደተጫወቱ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ 


በማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ጳጳሳት በኩል “የማቅን መተዳደሪያ ደንብ እንደገና እንየው” ከሚለው “ኢህአዴግ ነገ ይጠፋል፤ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ኗሪ ነውና ማኅበራችንን ማንም እንዲነካብን አንፈልግም” እስከሚለው ድረስ ለማቅ ጥብቅና የቆሙ ጳጳሳት ነበሩ፡፡ በተለይ አባ ቄርሎስ፣ አባ ጢሞቴዎስና አባ ሉቃስ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው፡፡ በተለይ አባ ሉቃስ ለማቅ ተከራካሪ ሆነው የቀረቡት ባለባቸው ነውር ማቅ አስፈራርቷቸው ነው የሚሉት ምንጮች፣ ከዚህ ቀደም ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሃፊዎችና ሌሎችም አገልጋዮች በተዘጋጀ ሥልጠና ላይ አባ እስጢፋ እያስፋፉት ባለው ሙስና ቅሬታቸውን ያሰሙትና “ለእስራኤል ውድቀት ምክንያቶቹ ካህናት ነበሩ ዛሬም ለቤተክርስቲያናችን ውድቀት ተጠያቂዎቹ እኛው ካህናት ነን” ሲሉ ካህናቱ ቆመው ያጨበጨቡላቸው አባ ሉቃስ ዛሬ የተንሸራተቱት ማቅ ይዤብዎታለሁ በሚለው ገበናቸው ተደራድሯቸው ነው ይላሉ፡፡
ይሁን እንጂ ይህን የተቃወሙ ጳጳሳት በፊናቸው ከቤተክርስቲያን ይልቅ ለማቅ ጥብቅና የቆሙትን ጳጳሳት ሐሳብ በመቃወም “ስለአንድ የጽዋ ማኅበር ይህን ያህል ጊዜ ሰጥተን ልንወያይ አይገባም፤ የወሰነውን ነገር እንደገና ወደኋላ ተመልሰን ማየት የለብንም” በሚል ተቃውሟቸውን ማሰማታቸው ታውቋል፡፡ የስብሰባው መሪ ፓትርያርኩም ከአጀንዳ የሚወጡትን ወደአጀንዳ እንዲመለሱ በማድረግ፣ ከዚህ ቀደም በተወሰኑ ውሳኔዎች ላይ ወደኋላ እንመለስ ባዮቹንም ወደሌላው አጀንዳ በማሸጋገር ብቃት ያለው አመራር የሰጡ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡
    

Monday, June 2, 2014

ሃያ አራቱ ግዴታዎችና ድንጋጌዎች እና የአባ እስጢፋ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መነሣት ለማቅ ራስ ምታት የሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ክፍል አንድ
ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ቅዱስ ሲኖዶስ ለስብሰባው ያላሰበውን አጀንዳ በመፍጠር፣ ስብሰባውን በማወክ የሚታወቀው ማኅበረ ቅዱሳን በዘንድሮው የግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ የስብሰባው አንዱ አጀንዳ በመሆን ሲያወያይ ሰንብቷል፡፡ ጀንበር እየጠለቀችበት የመጣ የሚመስለው ማቅ በዚህ ስብሰባ ላይ እየተረቀቀለት ባለው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ሊካተቱ ይገባቸዋል የተባሉ 24 የሚሆኑ ልዩ ልዩ ግዴታዎችና ድንጋጌዎችን ቅዱስ ፓትርያርኩ በረቂቅ መተዳደሪያ ደንቡ እንዲካተቱ ለልዩ ጽ/ቤት የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ ለሆኑት ለብፁዕ አቡነ ገሪማ በጻፉት መመሪያዊ ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡ በደብዳቤው እንደተገለጸው ግዴታዎቹና ድንጋጌዎቹ ህገ ቤተክርስቲያንን፣ ቃለ ዐዋዲንና በ2006 ዓ.ም. በጥቅምቱ አገር አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የወጣውን መግለጫ መሠረት ያደረገ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ይህም መመሪያዊ ደብዳቤው ሕገ ቤተክርስቲያንን መሠረት ያደረገ መሆኑን ያሳያል፡፡


መመሪያውን ማስተላለፍ ያስፈለገበት ዋና ምክንያቶች ሦስት መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ የመጀመሪያው የማኅበሩ ሕገ ደንብ በፍጥነት እንዲዘጋጅና ተጨማሪ ጊዜ በመውሰድ ስራው እንዳይጓተት ለማድረግ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የሚዘጋጀው ደንብ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ እንዲሆን ለማሳሰብ ነው፡፡ ሦስተኛውም ማቅ በሚሰራው መልካም ቤተክርስቲያንን የሚያስመሰግናትን ያህል ስሕተት ፈጽሞ ሲገኝ ቤተክርስቲያንን የሚያስጠይቅና በሕግ እንድትጠየቅ ሊያደርጋት የሚችል አጋጣሚ እንዳይኖር ጥበቃና ጥንቃቄ  ለማድረግ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ በዚህ ምክንያትም ሕገ ቤተ ክርስቲያንን፣ ቃለ አዋዲውንና በጥቅምት 2006 ዓ.ም የጥቅምቱ ሀገር አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ባወጣው መግለጫና እርሱን ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በተላለፈው ውሳኔ መሠረት በፓትርያርኩ መመሪያ ሰጭነት ለማኅበረ ቅዱሳን ሕገ ደንብ አዘጋጅ ኮሚቴ መመሪያው ተሰጥቷል፡፡ ፓትርያርኩ ሕገ ቤተክርስቲያንን የመጠበቅና የማስጠበቅ ሃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ ግዴታዎቹንና ድንጋጌዎቹን የማስተላለፍ ሕጋዊ ሥልጣን አላቸው፡፡