Monday, June 2, 2014

ሃያ አራቱ ግዴታዎችና ድንጋጌዎች እና የአባ እስጢፋ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መነሣት ለማቅ ራስ ምታት የሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች ክፍል አንድ
ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ ቅዱስ ሲኖዶስ ለስብሰባው ያላሰበውን አጀንዳ በመፍጠር፣ ስብሰባውን በማወክ የሚታወቀው ማኅበረ ቅዱሳን በዘንድሮው የግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ የስብሰባው አንዱ አጀንዳ በመሆን ሲያወያይ ሰንብቷል፡፡ ጀንበር እየጠለቀችበት የመጣ የሚመስለው ማቅ በዚህ ስብሰባ ላይ እየተረቀቀለት ባለው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ሊካተቱ ይገባቸዋል የተባሉ 24 የሚሆኑ ልዩ ልዩ ግዴታዎችና ድንጋጌዎችን ቅዱስ ፓትርያርኩ በረቂቅ መተዳደሪያ ደንቡ እንዲካተቱ ለልዩ ጽ/ቤት የውጭ ግንኙነት የበላይ ኃላፊ ለሆኑት ለብፁዕ አቡነ ገሪማ በጻፉት መመሪያዊ ደብዳቤ አስታውቀዋል፡፡ በደብዳቤው እንደተገለጸው ግዴታዎቹና ድንጋጌዎቹ ህገ ቤተክርስቲያንን፣ ቃለ ዐዋዲንና በ2006 ዓ.ም. በጥቅምቱ አገር አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የወጣውን መግለጫ መሠረት ያደረገ መሆኑ ተመልክቷል፡፡ ይህም መመሪያዊ ደብዳቤው ሕገ ቤተክርስቲያንን መሠረት ያደረገ መሆኑን ያሳያል፡፡


መመሪያውን ማስተላለፍ ያስፈለገበት ዋና ምክንያቶች ሦስት መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ የመጀመሪያው የማኅበሩ ሕገ ደንብ በፍጥነት እንዲዘጋጅና ተጨማሪ ጊዜ በመውሰድ ስራው እንዳይጓተት ለማድረግ ነው፡፡ ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የሚዘጋጀው ደንብ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ እንዲሆን ለማሳሰብ ነው፡፡ ሦስተኛውም ማቅ በሚሰራው መልካም ቤተክርስቲያንን የሚያስመሰግናትን ያህል ስሕተት ፈጽሞ ሲገኝ ቤተክርስቲያንን የሚያስጠይቅና በሕግ እንድትጠየቅ ሊያደርጋት የሚችል አጋጣሚ እንዳይኖር ጥበቃና ጥንቃቄ  ለማድረግ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ በዚህ ምክንያትም ሕገ ቤተ ክርስቲያንን፣ ቃለ አዋዲውንና በጥቅምት 2006 ዓ.ም የጥቅምቱ ሀገር አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ባወጣው መግለጫና እርሱን ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በተላለፈው ውሳኔ መሠረት በፓትርያርኩ መመሪያ ሰጭነት ለማኅበረ ቅዱሳን ሕገ ደንብ አዘጋጅ ኮሚቴ መመሪያው ተሰጥቷል፡፡ ፓትርያርኩ ሕገ ቤተክርስቲያንን የመጠበቅና የማስጠበቅ ሃላፊነት ያለባቸው በመሆኑ ግዴታዎቹንና ድንጋጌዎቹን የማስተላለፍ ሕጋዊ ሥልጣን አላቸው፡፡

መመሪያው ሕግንና ሥርዓትን ተከትሎ የተዘጋጀ ቢሆንም ከአቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና አንሥቶ “መታዘዝ ለምኔ” በሚል አቋም ጸንቶ የሚገኘውና ለቤተክርስቲያን ውሳኔዎች እንቢኝ አሻፈረኝ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን አቧራ ማስነሣቱን ቀጥሏል፡፡ ሃያ አራቱ ነጥቦቹ በህገ ደንቡ ውስጥ እንዳይካተቱም በተለመደ ስልቱ ጳጳሳቱን በጥቅማ ጥቅም በመያዝ፣ አንዳንዶቹንም በነውራቸው በማስፈራራት፣ ሲብስም ለጉዳዩ ፖለቲካዊ ይዘት በመስጠት በፖለቲከኛነቱ ከጎኑ እንዲሰለፉ ለማድረግ ሲንቀሳቀስና ጳጳሳትን ሲከፋፈል፣ በዚህም ምክንያት የሲኖዶሱን ስብሰባ በእጅ አዙር ሲያውክ ሰንብቷል፡፡ ሲኖዶሱን ሲያስበጠብጥ የሰነበተው እርሱ ሆኖ ሳለ ግን ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል እንዲሉ ተበደልኩኝ እያለና 24ቱን ነጥቦች በተሳሳተ መንገድ እንዲታዩ በማድረግ በፋክትና በሌሎቹም ማኅበሩ በሚደጉማቸው ሚዲያዎች መረጃዎቹን በማዛባት ጭምር ዘመቻ ከፍቶባቸው ሰንብቷል፡፡
ድንጋጌዎቹ ሕገ ቤተክርስቲያንን መሠረት ያደረጉ ስለሆኑ ሊከበሩና መረን የተለቀቀውን ማኅበረ ቅዱሳንን ሥርዓት የሚያስይዝ ነው፡፡ ከድንጋጌዎቹ መካከል ማኅበሩን ይበልጥ ያንገበገበው ምን እንደሆነ ለማወቅ ቢያስፈልግ ሐራ የተባለው የማኅበሩ ብሎግ የሚከተለውን ጠቅሷል፡፡
1.    የማኅበሩ ፈቃድ በየዓመቱ እንዲታደስ፤
2.   ማኅበሩ ከቅፅረ ቤተ ክርስቲያን ውጭ እንዳይሰበሰብና ቢሮ እንዳይከፍት፤
3.   የሠራተኞቹ ቅጥርና ምደባ በመንበረ ፓትርያርኩ እንዲካሔድ፤
4.   አባላቱ በግልም በቡድንም በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ሥራ፣ በቀኖናዊ የሥነ ሥርዓት ድንጋጌና በሰንበት /ቤቶች ጉዳይ እንዳይገቡ፤
5.   የማኅበሩ አባላት በግል ለሚሠሩትየቤተ ክርስቲያንን አንድነትና የሀገርን ሰላም የሚፃረር ድርጊትማኅበሩ ሓላፊነት እንዲወስድ”
የሚሉት እንደ ተካተቱበት አትቷል፡፡ እውን እነዚህ ድንጋጌዎች እንዴት ነው ትክክል አይደሉም የሚባለው? ቤተክርስቲያን የምታወጣው ሕግና ደንብ ለማቅ የማይስማማ ስለሆነ ብቻ ትክክል አይደለም እንዴት ይባላል? ይህ በራሱ የሚያሳየው ማቅ ሥርዓት አልበኛ ማኅበር መሆኑን ነው፡፡ እስኪ ማቅ እኔን ለማጥቃት ሆን ተብሎ የተረቀቁ ድንጋጌዎች ናቸው ያላቸውን እንመልከት፡፡ 

1/ የማኅበሩ ፈቃድ በየዓመቱ እንዲታደስ፤ አሁን ይህ ድንጋጌ ምን ችግር አለው? የማኅበሩ አካሄድ በሕጋዊ መንገድ ተገምግሞ በየዓመቱ እንዲታደስለት ቢደረግ ይህ በሕግና በሥርዓት ለሚመላለስ ማኅበር አስቸጋሪ እንደማይሆን ጥርጥር የለውም፡፡ በየትም የሚሠራበት የተለመደ አሠራር ነው፡፡ ነገር ግን በሕገወጥ መንገድ መጓዝ ለለመደ ችግር ላለበትና በሥርዓት ለማይሄደው ማቅ አስቸጋሪ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለዚህ ይህን ሕጋዊና ትክክለኛ አካሄድ ወደመቃወም መጣ፡፡ ሀራ እንደጻፈውም “ማኅበሩ በበኩሉ በተለይ በፈቃድ ዕድሳት ረገድ የተነሣው ሐሳብ ‹‹በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ በጸደቀ መተዳደርያ ደንብ የሚመራውን የማኅበሩን አገልግሎት ለማስቆም የሚደረግ አካሔድ ነው፤›› ብሏል፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ የጸደቀ መተዳደሪያ ደንብ የሚመራው ማቅ መተዳደሪያ ደንብ ስላለው ይህ በራሱ ዕድሳት አያድርግ የሚል ነጻ ፈቃድ አይሰጠውም፡፡ ደግሞም ቁጥጥር ማድረግ ለግጽነትና ተጠያቂነትን ማስፈን እንጂ አገልግሎትን ማስቆም ሊሆን አይችልም፡፡ ለማቅ ሕገወጥ አካሄድ ግን በእርግጥም ሕገወጥ አካሄዱን እንደአገልግሎት ከቆጠረው እርሱን ለማስቆም የወጣ ደንብ ይሆንበታልና ቢሰጋ አያስገርምም፡፡
  
2/ “ማኅበሩ ከቅፅረ ቤተ ክርስቲያን ውጭ እንዳይሰበሰብና ቢሮ እንዳይከፍት” የሚለው ነጥብም ሃይማኖተኛ እንጂ ፖለቲከኛ አይደለሁም በሚለው በማቅ ዘንድ ተቀባይነት በኖረው ነበር፡፡ ነገር ግን የሚለውና የሚኖረው ተቃራኒ የሆነበት ማቅ መኖር መሰብሰብም መሥራትም ያለብኝ ከቅጽረ ቤተክርስቲያን ውጪ ነው እያለ ነው፡፡ ለምን? በአንድ በኩል ከቤተክህነቱ እይታ ውጪ ለመሆንና በቤተክርስቲያን ስም ያሻውን ሕገወጥ ተግባር ለመፈጸም እንዲረዳው ይመስላል፡፡ የፓትርያርኩ መመሪያ መሰብሰብ አትችሉም፤ ቢሮም መክፈት አትችሉም ቢሆን ያን መቃወም እውነተኛ ነገር በሆነ ነበር፡፡ የተባለው ግን ያላችሁት በቤተክርስቲያን ሥር ስለሆነ መሰብሰብም ሆነ መሥራት የሚገባችሁ በቅጽረ ቤተክርስቲያን ነው የሚል ትክክለኛ ድንጋጌ ነው፡፡ ይህም የተቀደሰ ሀሳብ ለማቅ አልተዋጠለትም፡፡ ምክንያቱም ማቅ ራሱን የቻለና ከቤተክህነት በላይ ለመሆን የሚንጠራራ ምናልባትም ተገንጥሎ ሌላ ቤተክርስቲያን ለመሆን የሚከጅል ስብስብ ስለሆነ (አስራት መሰብሰቡ፣ ለቤተክህነት መመሪያ አልገዛም ማለቱ ወዘተ… ለዚህ ማሳያዎች ናቸው) በቅጽረ ቤተክርስቲያን መታሰሩ ለድብቅ አጀንዳው ተስማሚ ሆኖ ስላልተገኘ አልተቀበለውም፡፡
3/ “የሠራተኞቹ ቅጥርና ምደባ በመንበረ ፓትርያርኩ እንዲካሔድ፤” የሚለው ነጥብም በሐራ በኩል ተዛብቶ ነው የቀረበው፡፡ ድንጋጌው በተለይ በስብከተ ወንጌል፣ በትምህርተ ሃይማኖትና በክህነት አገልግሎት የሚቀጥራቸውን ሰራተኞች ነው የሚመለከተው፡፡ ሐራ ግን ከእዚህ ውጪ ላለው የሰራተኞች ቅጥር ሁሉ ደንጋጌው አስገዳጅ እንደሆነ ነው ያስቀመጠው፡፡ ለነገሩ የሐራን ዘገባ በግልባጩ ነው መረዳት እንጂ በፊት ለፊት ንባቡማ ሁሌ በተዛባ መረጃ ላይ የቆመ ነው፡፡ ማቅ በሃይማኖት አውድ የሚንቀሳቀስ ማኅበር እንደ መሆኑ ሰባኪዎቹን፣ የትምህርተ ሃይማኖት መምህራኑንና በክህነት የሚያገለግሉትን ከቤተክርስቲያኗ በራሱ ሥልጣን እየመለመለ የሚጓዝበት መንገድ እጅግ አደገኛ መሆኑ ከእስካሁኑ አካሄዱ መታዘብ ተችሏል፡፡ ቤተክርስቲያኗ አስተምራና ደመወዝና ቀለብ ሰፍራ የምታኖራቸውን መምህራንና ልዩ ልዩ አገልጋዮች ማቅ እየመለመለ የእርሱ ተከታዮች ማድረጉና ተጨማሪ ገንዘብ በመክፈልና በጥቅማ ጥቅም በመያዝ ከቤተክህነት ጋር እያጋጨ መጓዙ አደገኛ አካሄድ ነው፡፡ በቅርቡ እንኳ ከፍተኛ ገንዘብ አስገባበታለሁ ብሎ ያሰበውን የአብነት መምህራን ጉባኤ የጠራው በዚሁ መንገድ ነው፡፡ አካሄዱ የቤተክርስቲያንና የማኅበረ ቅዱሳን ተከታዮች በሚል አገልጋዮቿንና ምእመናኖቿን ለሁለት እየከፈለ ስለሆነ ይህን መቆጣጠርና የቤተክርስቲያኗን አንድነት ማስጠበቅ ከቅዱስ ፓትርያርኩ የሚጠበቅ ነውና የወጣው ድንጋጌ ተገቢ እንጂ ስሕተት ሊሆን አይችልም፡፡
4/ “አባላቱ በግልም በቡድንም በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ሥራ፣ በቀኖናዊ የሥነ ሥርዓት ድንጋጌና በሰንበት /ቤቶች ጉዳይ እንዳይገቡ፤” ያለው ሐራ እዚህም ላይ “ጣልቃ” የምትለዋን ወሳኝ ቃል አውጥቶ ማቅና አባላቱ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንዳይገቡ የሚል አንድምታ እንዲሰጠው በማድረግ የድንጋጌውን መንፈስ ለማጭበርበር ሞክሯል፡፡ የተባለው ከላይ በተዘረዘሩት ጉዳዮች ላይ ጣልቃ እንዳይገቡ ነው። በእርግጥም በዚህ ጉዳይ ጣልቃ የመግባት መብት ሲኖዶስ አርቅቆ ሰጥቶናል እያለ በሚፎክርበት መተዳደሪያ ደንብ ውስጥም ቢሆን የተሰጠው መብት አይደለም፡፡ ጣልቃ ለመግባት የሚያስችል ሕጋዊም ሞራላዊም ሁኔታ የለውም፡፡ እስከዛሬ ድረስ ግን እንዳሻው ጣልቃ ሲገባ አስተዳደራዊ ሥራዋን፣ ቀኖናዊ የሥነሥርዓት ድንጋጌዋን ሲጥስ ሰንበት ትምህርትቤቶችን ካልመራሁ ካልተቆጣጠርኩ ሲል ነው የኖረው፡፡ ከአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሀፊዎችና ሌሎችም ሰራተኞች ጋር የተጋጨው በአላስፈላጊ ጣልቃ ገብነቱ ነው፡፡ ከአንዳንድ የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ሃላፊዎች ጋር ሲጋጭ የኖረው በሥራቸው ጣልቃ እየገባና ሥራቸውን እየነጠቃቸው ሲያስቸግራቸው ነው፡፡ ሰንበት ትምህርት ቤቶችንም ቢሆን ካልተቆጣጠርኩ በሚል በሚያደርገው ጣልቃ ገብነት ሲበጠብጥና ሲጋጭ ነው የኖረው፡፡ ቀድሞ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር በነበረ ጊዜ በተለይ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ራሱን ያስተዋውቅ የነበረው እንደማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ሳይሆን እንደመምሪያው አድርጎ ነው፡፡ አሁንም ቢሆን የመፍረስ አደጋ ተጋርጦብኛል በሚል አባላቱ ለቤተክርስቲያን ቀናዕያን በመምሰል በየሰንበት ት/ቤቱ እየተሰገሰጉና ሰንበት ት/ቤቶችን የመቆጣጠር አዝማሚያ እያሳዩ ነው፡፡ በየአውደ ምሕረቱም ለእነርሱ ሐሳብ ተገዢ ያልሆኑትን የቤተክርስቲያን ልጆች “ተሐድሶ ነው” “መናፍቅ ነው” የሚል ክፉ ዘር በምእመናን መካከል በመዝራትና በየሰበካ ጉባኤው ክስ በመመስረት በአንዳንድ ቦታዎች የሠርክ ጉባኤዎችን እያወኩ ይገኛሉ፡፡ ይህ ጣልቃ ገብነት ሊቆም አይገባውም ነው የሚባለው? ያሳዝናል!!
5/ “የማኅበሩ አባላት በግል ለሚሠሩትየቤተ ክርስቲያንን አንድነትና የሀገርን ሰላም የሚፃረር ድርጊትማኅበሩ ሓላፊነት እንዲወስድ” ሐራ ይህን ስትጠቅስ እንዴት አላፈረችም ብለን መጠየቅ እንወዳለን፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው በፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ መሆን ያለበት ራሱ መሆኑ ፈጽሞ ለጥያቄ የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም፡፡ ማቅ ግን አባላቱንና ለወንጀል ድርጊት ያደራጃቸውን ወሮበሎች ተጠቅሞ እየፈጸመ ላለውና ለሚፈጽመው የወንጀል ድርጊት ሓላፊነቱን ቤተክርስቲያን እንድትወስድለት ይፈልጋል፡፡ አሊያም ወንጀል ፈጻሚዎቹን እኔ አላውቃቸውም ብሎ ማምለጥ ይፈልጋል፡፡ እስካሁን እየሄደበት ያለው መንገድም እነዚህን ወገኖች ማቅ የሚፈልገውን እንዲፈጽሙለት ካደረገ በኋላ ሲጠየቅ ይህን ያደረግኩት እኔ አይደለሁም በሚል የማስተባበል አካሄድ ነው፡፡ ይህ ድርጊት ግን እዚህ ላይ ማቆም አለበት፡፡ እንዲህ ካልሆነ የማንን ዕዳ ማን ሊከፍል ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ንጹሕ የሆነ ሰው ይህ ድንጋጌ አያስፈራውም፡፡ ምን ያለበት ምን አይችልም እንደሚባለው ግን ዓላማው የቤተክርስቲያንን አንድነትና የሀገርን ሰላም የሚጻረር ድርጊት ለመፈጸም ሐሳቡ ያለው ግን ይህ ድንጋጌ ክፉ ሥራውን የሚከላከል መጠበቂያ፣ ከፈጸመው በኋላም ተጠያቂ ማድረጊያ ድንጋጌ በመሆኑ ያስፈራዋል፡፡ ማቅም ነገሩ እንዲህ ነው የሆነበት፡፡
በዚህ ጽሑፍ የማኅበረ ቅዱሳን ልሳን ሀራ ሊከራከርባቸው እያዛበ ጭምር የጠቀሳቸውን ብቻ ተመለከትን እንጂ ያልጠቀሳቸው ሌሎቹ ድንጋጌዎችና ግዴታዎች ሁሉ ተገቢነት ያላቸውና ሕገወጡን ማቅን አደብ ሊያስገዙ የሚችሉ በሕገቤተክርስቲያን መሠረት የተደነገጉ ናቸውና የፓትርያርኩ መመሪያ ተግባራዊ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ሕገ ቤተክርስቲያንን የማስጠበቅ ሥልጣን ፓትርያርኩ አላቸውና፡፡ ይህ ተግባራዊ እንዳይሆን ግን የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ የሆኑ ጳጳሳት ቡድን ፈጥረው ሰሞኑን በተጠናቀቀው የግንቦቱ ሲኖዶስ ሲቃወሙት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለመሆኑ ይህን ድንጋጌ የተቃወሙት ጳጳሳት ዓላማቸው ምን ይሆን? ከድንጋጌዎቹ ብዙዎች እነርሱው ጭምር በሌሎቹ ጉባኤዎች የተስማሙባቸውና ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮች ሆነው ሳሉ የተቃወሙት በምን መሠረት እንደሆነ አነጋጋሪ ነው፡፡ ይህ ከቤተክህነት እየጎረሱ ወደማኅበረ ቅዱሳን የመዋጥ አባዜ የወለደው እንጂ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡

ብፁዓን አባቶች ሳያስተውሉት በሲኖዶስ ስብሰባ ወቅት አንድ መጥፎ ባህል እያዳበሩ መሆናቸውን ግን ያጤኑት አይመስልም፡፡ የሲኖዶስ ስብሰባ በእግዚአብሔር መንፈስ መመራት ያለበት፣ ለእግዚአብሔር ክብርን የሚያመጡና ለቤተክርስቲያን ጥቅም የሚያስገኙ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እንጂ በቡድን ተከፋፍሎ አንዱን ቡድን ደግፎ የሚቀርቡ ጠቃሚ ሐሳቦችን በጭፍን በድምፅ ብልጫ ውድቅ የሚደረጉበት ሊሆን አይገባምና ይህ ሁኔታ መስተካከል አለበት፡፡ አሊያ ቤተክርስቲያን የጭቅጭቅ መድረክ ሆና ከመቀጠል አታመልጥም፡፡ ትናንት አቡነ ጳውሎስ ላይ ሲደረግ የነበረው አሁን አቡነ ማትያስ ላይ ከተደገመ ነገ ወደሥልጣን ለሚመጣው ፓትርያርክም እንደባህል ተደርጎ ስለሚወሰድ አደገኛና ነግ በኔ ነውና ብፁዓን አባቶች ሊያስቡበት ይገባል፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቅድሚያ መስጠት ያለባቸው ለቤተ ክርስቲያን እንጂ በኋላ ለመጣ ማኅበር መሆን የለበትም፡፡ ማኅበሩ በሕግና በሥርዓት እንዲሄድ የወጣለትን ድንጋጌ በቅን መንፈስ ከማየትና በድንጋጌው ሕጋዊነትና ኢሕጋዊነት ላይ ተነጋግሮ ከመወሰን ይልቅ ሌላ መልክ ሰጥቶ ማኅበሩ በጀመረው የጥፋት መንገድ እንዲጓዝ መፍቀድ ይሆናልና እነዚህ ጳጳሳት ነገ ዋጋ እንደሚከፍሉበት ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ቢሆንም ፓትርያርኩ በዚህ ጉዳይ ላይ ቁርጠኛ አቋም መያዝና ለድንጋጌው ተግባራዊነት ብስለት የተሞላውና ሕጋዊነትን የተከተለ የማያዳግም ውሳኔ መወሰን አለባቸው፡፡ እንደ አቡነ ጳውሎስ በማቅ ጉዳይ ላይ መለሳለስ ካሳዩ ለአቡነ ጳውሎስ ያልተኛው ማቅ ለእርሳቸውም እንደማይተኛ መታወቅ አለበት፡፡ በሲኖዶሱ ውስጥ እያቆጠቆጠ ያለውን በቡድን ተከፋፍሎ የመራኮት ጎጂ ባህልም ለቤተክርስታየን አይበጅምና ከወዲሁ መቆም አለበት፡፡ ፓትርያርኩን የማያከብር ሲኖዶስ ደግሞ ነገ ከአባላቱ ሌላኛው ቦታውን ሲይዝ ተመሳሳይ ዕጣ እንደሚገጥመው ማወቅ አለበት፡፡ ዛሬ “ለእኔም ለእርስዎም አይሆንም” የሚሉ ጳጳሳት ነገ ወደ ሥልጣን ቢመጡ በዚሁ ጎጂ ባህል መታሰራቸው ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ባህል ለመስበር ለዚህ ባህል መዳበር ዋና ምክንያት የሆነውን ማቅን መስመር ማስያዝ እንጂ እርሱን እሹሩሩ ማለቱ አዋጭ አይደለም፡፡

35 comments:

 1. ማህበረ ቅዱሳን የቅድስት ቤተክርስቲያን ልጅ ነው!June 2, 2014 at 2:19 AM

  እናንተ መናፍቃን ማህበረ ቅዱሳን ማን እንደሆነ ታዉቃላችሁ!
  ጀርባችሁንና ሰራችሁን ስለሚያዉቅ/ስለሚያጋልጥ የቤተክርስቲያኒቱ አባል ሳትሆኑ ቤተክርስቲያናችን እያላችሁ ህዝቡን ማደናገር እንደትችሉ ስለአደረገ እርሱን ለመፍረስ የምትፈነቅሉት ድንጋይ የለም
  ማህበሩ በስራዉ ሁሉ እግዚአብሔርን ስለምያስቀድም አመናቸሁም አለመናችሁን ማህበሩ በእናንተ(በመናፍቃን) የፈጠራ ስም ማጥፋት ወሬ አይፈርስም::

  ReplyDelete
  Replies
  1. weye dinkurena meche yihone sew yimetehonut?

   Delete
  2. weye awakinet

   Delete
 2. ለአባ ሰላማ!!!


  ወሬኛም በማውራቱ፣
  ማቅም በአገልግሎቱ፣
  ይቀጥላል፡፡ ምን ትሆኑ?
  እኔ የምለው ግን ውሸት አይሰለቻችሁም???!!!
  ለነገሩ ከግብር አባታችሁ ከዲያብሎስ የወረሳችሁት አይደል ቢጥማችሁ እንጂ እንዴት ይሰለቻችኃል
  የሚገርመው ግን ውሸት በምንም አግባብ ቢቀርብ…. ለቁጥር እስኪታክት ቢደጋገም…..ያው ቁልጭ ያለ ውሸት እንጂ ወደ እውነት መጠጋት እናካን አለመቻሉ ነው፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. አይ አባ ሰላማ

   በግልፅ ተሀድሶነታችሁን ትሰብኩ ጀመራችሁ??
   ye abatachin abune selama sema lenante mekeleja mehonu berasu yasazinal

   Delete
 3. wawe des yilal makine endihe manketket teru new. des belonal

  ReplyDelete
 4. Man , stop and think ; be with your sense: all you said is rubbish

  ReplyDelete
 5. none of the above two agendas are headaches of mk.because the agendas proposed by the poisoned patriarch , ill -advised by the dark team of the dead bete-khinet, who in turn supported by protestant menafkan government officials are automatically rejected by all members of the holy synod, and not approved. the patriarich is poisoned because he is now implementing the agendas of protestant menafkan government cadres, not the agenda of GOD. WE PITY FOR HIM.OUR CHURCH AND MK WILL NOT HAPPEN ANY THING

  ReplyDelete
 6. Geta hoy eskemeche mk bezihch betecrstiyan lay yefenchal.Becks belen ante Buchanan neh
  kesis kifu mahber yemtglaglen..hayl yante new...ppasatum hodachewo amlakachew kebrachewom beneworachew kehone denbetwal.

  ReplyDelete
 7. አጋንንታሞች ! የቅድስት ቤተክርስቲያን ብርቅዬ ልጆቿ ስብስብ ፡ እናንተን እና አባታችሁ ዲያቢሎስን የሚያንቀጠቅጥ እንደሆነ የሚዘልቅ ነው ማኅበረ ቅዱሳን፡፡ መናፍቃን አዳራሾቻችሁ አልበቃ ብሏችሁ ቤተክርስቲያኒቱን እንዲህ ስታብጠለጥሏት የእርካታችሁ ምንጩ ያባታችሁ የዲያቢሎስ አይነት መሆኑ ለማያውቋችሁ እንኳን ግልጽ ከሆነ ሰነባበተ፡፡ ቅድመ እግዚአብሔር ቆማችሁ ስለማትጸልዩ ወንድሞችን በመክሰስ ውላችሁ የምታድሩ ልቡሳነ ስጋዎች ናችሁ፡፡ ተሃድሶ መናፍቃን፡፡

  ReplyDelete
 8. Pls belive me,(CIA) BAYABL is a very bad gay. he has got trust of Aba Matias & with him in the day, discuss with "aba" samuel in the evining & learn from diablos over nignt. The patriarc should know Bayabl's game.other wise you will see one day he will kll him. b/s i have concret evidence that he is Armed.

  ReplyDelete
  Replies
  1. It is unblivable can a person worship at the same time for Tabot & dagon/ belive in GOD & satan? ur explanation seems like this.some people marginalise bayabl as "woyane", & others catagorised as fanatic MK & others said him CIA..How?

   Delete
  2. Hulachihu Atidikemu, Aba matiasim bayablin Aytelutim, Esun Telitew manin liwodu,tore mesaria(gun) yelewim Binorew Eskezare binorew eskezareyitekus nebere

   Delete
  3. Rasachinin legziaber enasigeza, wishet tiru aydelem, bayable armid aydelem, yigelal yetebalewim tseyaf ababal new,aba Matiasim egziabher yesten abat andafer,yasikesifal, abatina ligin lematalat yihin yahil medikem hatiat new.lemelikam enidikem.

   Delete
 9. Protestantism (tehadiso) is satanism

  ReplyDelete
 10. ዘቦ እዝን ሰሚ'ዐ ለይስማዕ Or may go hell

  ReplyDelete
 11. what the tehadso still did not understand is that , MK, as a SPIRITUAL association, should not work with out various internal and external obstacles, challenges ( IT IS WELL EXPECTED AND A MUST ). if MK is not challenged by different and difficult problems, it WOULD be a doubtful for its spirituality. so, in short the kingdom of GOD(JESUS) will not be achieved without price. keep on MK WE ARE BEHIND YOU. LET DEVIL CRY.

  ReplyDelete
 12. nothing rubbish, everything is right and true. we are proud of all peoples stand against of MK.we know what is going. MK members are wrong and bad dream...........good job Aba Selama blog for your info.

  ReplyDelete
 13. የለበሳችሁት የበግ ለምድ እንጂ ምናችሁም የቤተክርስቲያን መአዛ የለውም፡፡ ይህም በፍሬአችሁ (maletim be fikir-albaw ena nisiha-albaw tsihuf) malete new.
  Fetari yimelketachihu!

  ReplyDelete
 14. You the serpent! You will be judged under his mercy-full eyes.
  Do you feel that your devotions are in the Diabolist spirit? Repent and give life to your frozen heart.
  May God bless you?!

  ReplyDelete
 15. please write the 24 in brief

  ReplyDelete
 16. እኔ የመምለው እነዚህ የማህበረ ቅዱሳን ተቆርቋሪ ነን እያሉ አስተያየት የሚሰጡ ሰዎች የአእምሮ ችግር አለባቸው እንዴ? የተጻፈው ጽሁፍ እኮ ከነማስረጃው ነው የቀረበው፡፡ የሲኖዶሱም ውሳኔ አብሮ ተያይዞዋል፡፡ ምንድን ነው ዝም ብሎ መዘባረቅ? ደረቁን እውነት ውሸት ነው እያሉ አየንን በጨው አጥቦ መምዋገት ምን ይጠቅማቸዋል? የጎድ ቀን አየይመሽም አሉ አባቶቻችን ጉደኛ ሰዎች ደግሞ ተተረማምሰው ሳይጠፉ አያርፉም ማለት ነው፡፡ እኔ የመምለው እነዚህ የማህበረ ቅዱሳን ተቆርቋሪ ነን እያሉ አስተያየት የሚሰጡ ሰዎች የአእምሮ ችግር አለባቸው እንዴ? የተጻፈው ጽሁፍ እኮ ከነማስረጃው ነው የቀረበው፡፡ የሲኖዶሱም ውሳኔ አብሮ ተያይዞዋል፡፡ ምንድን ነው ዝም ብሎ መዘባረቅ? ደረቁን እውነት ውሸት ነው እያሉ አየንን በጨው አጥቦ መምዋገት ምን ይጠቅማቸዋል? የጎድ ቀን አየይመሽም አሉ አባቶቻችን ጉደኛ ሰዎች ደግሞ ተተረማምሰው ሳይጠፉ አያርፉም ማለት ነው፡፡

  ReplyDelete
 17. ወገን ድንጋጌዎቹን በዝርዝር ጻፉልን ኮኔክሽናችን ስስ የሆንን ሰዎች እንዴት አድርገን ፐዲኤፉን እንክፈት ተቸገርን እኮ

  ReplyDelete
 18. ሰላማዎች እስካሁን የማቅ መተዳደሪያ ሆኖ ያገለገለውን ደንብም ጫኑልን.እንወቀው.

  ReplyDelete
 19. thanks God ! now it time of church to preach bible gata ho temesgen simh likeber new

  ReplyDelete
 20. የሀብታም ልጅ ሲታገል የድሀ ልጅ ይሞታል። ማቅና ሌሎቹ ሲታገሉ ድሀዋ ቤተ ክር ድሆቿን ልታጣ ነው
  አይጣል!

  ReplyDelete
 21. mahiberekidusan sijemer jemiro bewenjel yemitawek new....egnam nebern eko...yemiasazinew yewegel fire yehonu abalat sayihon yesebesebew tesedabi...kibirmin endehone yaligebaw tiwuld endifelefelu madiregu new.endewum 1 wedaje min ale...comment yemisetut yemahiberu teketayoch tesadabiwoch nachew yih yemiasayew yalewengel menorachewun new.God forgive mahiberekidusanin and his followers

  ReplyDelete
 22. GUD Gud Gud MK be Ethiopia be Germen Be US Bealem lay Dramaw Tenekabet yalene astemari sebaki heg tebaki askebari zemari ere hulunem ene becha negn yemawekew eyale kersteyan abatoch wendemoch ehetoch sebakiyan zemareyan yehonuten Ande tehadeso eyale seyasadded endihum Tensheuu malet sayechelu dikuna kisena eyachebereberu betekimatikim abatoch papasatin eyedelelu kihenet eyeserku meskel chebetew beteley be europ legud feletewal selezhi ahun macheber yelem abune mateyas bawetut heg yemetemeru kehone teketelalachehu yalebelezhia begelts wede poletikachehu tezewaweru aleke dekeke Chefin degafiwoch weyem erasachehu mk ayenachehun geletuuuu

  ReplyDelete
 23. Mk fired priest called him self as a Doctor oficialy he did not attend adult school to improve his English skill Mr. Mesin Tegegn came Atlanta Sunday to preached in weding cermoney. Acording to Dekalb hospital source Mk couple that married and invited. Mesfin suffering from Aids and Tb.

  ReplyDelete
 24. Betecrstiyan albeka blwoachu adarash geban ale ???? Mk new enjji betecrstiyan albeka bleach yod abisinniya yegebachut.adarash ayshalem??? Kechefera botta?? Mk dem teteto yemaytegeb mahber maqe yalbesachu.

  ReplyDelete
 25. Anonymous June 3 @ 12:, have you been in English school? Check your English before commenting other.

  ReplyDelete
 26. maninetachihu post kemtadergut neger yastawuqibachihual besidib yemijemr blog rasun tikikil adrgo lelawun bikonin man yaminwal

  yemirba tija kegemedu yastawuqal nekitenbachihual yemahibere kidusan guday migib lemblat eskisanachihu dires ras mitat yehonebachih tehadisowoch
  lelawun bemesadeb degafi atagegnum ewunet bemeyaz enj
  amlak libon yistachihu Mahibere Kidusanin Egziabher yibark

  ReplyDelete
 27. lenegeru yeminitsifewun enanten kaldegefe post atadergutim tigermalachihu

  ReplyDelete
 28. Gosh bertu
  abatachehu Diablos

  ReplyDelete