Friday, June 13, 2014

የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ እንስበክ

Read in PDF

ሁሉም ወንጌል እሰብካለሁ ይላል፡፡ ወንጌልን መስበክ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቀው ግን “ወንጌልን እሰብካለሁ” የሚለው ሁሉ አይደለም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ውስጥ ያላለፈ ሰው የሚመላለሰው በልማድ ስለሚሆን ወንጌልን መስበክ ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ በቅጡ አይረዳውም፡፡ ወንጌል እሰብካለሁ እያለ የሚሰብከው ግን ወንጌል አይደለም፡፡ ሌላ ወንጌል ነው፡፡ ልዩ ወንጌል ነው፡፡ ያልተቀበልነው ወንጌል ነው፡፡ ወንጌል ስለኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የሚሰበክ የምሥራች ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም መሰበክ ያለበት ለሰዎች ሁሉ የምሥራች የሆነው የተሰቀለው ኢየሱስ ብቻ እንደሆነ አስረግጦ ይመሰክራል፡፡ የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንመልከት፡፡

 •   “እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን፤” (የሐዋ. 13፡32
 • እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር “ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።” (የሐዋ. 14፡15
 • “መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥” (1ቆሮ. 1፥23
 •  “ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤ በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ። እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ … እንግዲህስ እኔ ብሆን እነርሱም ቢሆኑ እንዲሁ እንሰብካለን እንዲሁም አመናችሁ።” (1ቆሮ. 15፡1-4፣11
 • “ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥” (2ቆሮ. 4፡5)
ከብዙ በጥቂቱ እነዚህ ጥቅሶች መሰበክ ያለበት የተሰቀለው ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ይመሰክራሉ፡፡ እንዲህም ሲባል እርሱ ስለኃጢአታችን መሞቱንና በሦስተኛው ቀን መነሣቱን ማእከል በማድረግ ነው ወንጌል መሰበክ ያለበት። ምክንያቱም ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቅበት መንገድ፣ ከጭንቀቱና ከትካዜው የሚያርፍበት ዕረፍተ ሥጋ ወነፍስ እርሱ የተሰቀለው ክርስቶስ ብቻ ነውና፡፡ ከእርሱ በቀር ሌላ ይህን ሊያደርግ የሚችል ከሰማያውያን መላእክትም ሆነ ከምድራውያን ደቂቀ አዳም ፈጽሞ አይገኝምና የምንሰብከው ሌላ መልአክም ሆነ ሰው አይኖርም፡፡
በዚሁ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ላይ ተመሥርተው ሊቀ ሥልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህ አሁን ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ “የስብከት ዘዴ” በተባለ መጽሐፋቸው የሚከተለውን ጽፈዋል፡፡
የእግዚአብሔር ቅዱስ ዐላማ ሰው ሁሉ እንዲድን፥ ሰው ሁሉ የመንግሥቱ ወራሽ እንዲሆን የታለመ ነው። ለዚህም ሁሉ መምህር ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ መጣ፣ የስብከቱ ጠባይ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥራ የሚከተል፣ ራሱን ኢየሱስ ክርስቶስን ማእከል አድርጎ የሚሄድ ይሆናል። ስለ ሰው ደኅንነት ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ሞቷል። እንግዲያውስ የስብከቱ ይዘት፣ የስብከቱም ጠባይ የተሰቀለውን ኢየሱስን የሚመለከት መሆን አለበት። ሰባኪው በፈቀደው ርእስ ሊናገር ይችላል። ሆኖም ዋናው ዓላማ የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት ለመናገር መሆን አለበት።
ምንም የስብከት ምንጩ ቅዱስ መጽሐፍ ቢሆንም፣ ጥቅሱም ከእርሱው ቢወጣም ሐተታውና አገላለጡ ስለ አዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆን አለበት። ኢየሱስን ማእከል ያላደረገ፥ የእርሱንም አዳኝነት የማይገልጥ ስብከት ሊሆን ሊባልም አይችልም። (የኢ.አ.ተ.ቤ.ክ የስብከት ዘዴ” 1980 ገጽ 64 ፤67)
ይህ የብፁዕነታቸው መጽሐፍ እንደሚያስረዳው አንድ ሰባኪ በፈለገው ርእስ ሊሰብክ ቢችልም የትምህርቱ አቅጣጫና ግብ ወደሚያድነው ኢየሱስ የሚደርስ መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን ሰባኪው እሰብካለሁ የሚለው ወንጌልን ሳይሆን በወንጌል ስም ሌላ ትምህርት ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ የምናደርግ ሰዎች በወንጌል እሰብካለሁ ስም እየሰበክን ያለውን ጉዳይ ብንመረምር ጥሩ ነው፡፡

ዛሬ በስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተሰማሩ ሰባኪዎቻችን ሁሉ የሚሰብኩት የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ ነው ማለት አይቻልም፡፡ እርግጥ ነው የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ የሚሰብኩ አሉ፡፡ የተሰቀለውን ክርስቶስን መስበካቸው ባይቀርም፣ ወንጌልን በመስበክ ስም ግን ልዩ ወንጌልን የሚሰብኩም አሉ፡፡ ለምን? ... ለዚህ ጥያቄ የሰባኪዎቹን ማንነትና የሚሰብኩበትን ምክንያት በመፈተሽ በአራት ምድብ መድበን ምላሽ ለመስጠት እንሞክራለን፡፡

1.    የወንጌልን ምንነት በቅጡ ያልተረዱ
በዚህ ምድብ ያካተትናቸው ክፍሎች ከተሰቀለው ክርስቶስ በተጨማሪ ሌሎችንና ራሳቸውን የሚሰብኩት የወንጌልን ምንነት በቅጡ ስላልተረዱ ነው፡፡ ወንጌል የክርስቶስ የአዳኝነት ዜና በመሆኑና ከእርሱ በቀር የሚያድን ሌላ ስለሌለ ከእርሱ ውጪ ማንም አይሰበክበትም፡፡ ይህን ያልተረዱ “ሰባኪዎች” ግን “ወንጌልን ይሰብካሉ” ተብለው አውደ ምሕረት ላይ ከተሰየሙ በኋላ የሚሰብኩት ክርስቶስን ብቻ አይደለም፡፡ ያንቀላፉ ቅዱሳንንና መላእክትን፣ ራሳቸውንም ጨምሮ በሕይወተ ሥጋ ያሉትን ሌሎችን ሰዎች ጭምር ይሰብካሉ፡፡ ወግና ልማድን ይጠርቃሉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ሳይሆን ያልተዋሃዳቸውን የትርጓሜ ብሂልን ያወለካክፋሉ፡፡ የተሰቀለውን ክርስቶስን ሳይሆን እርሱ የተሰቀለበትን ዕንጨት (እፀ መስቀልን) ይሰብካሉ፡፡ ሌሎችንም ወንጌል ያልሆኑትንና ምናልባትም ከወንጌል ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ነገሮች ሁሉ ይሰብካሉ፡፡ የዚህ ስሙ ስብከተ ወንጌል ይባል እንጂ በተግባር ሰፈተሽ ሌላ ነው፡፡ በዚህ ክፍል የሚመደቡት እንዲህ የሚያደርጉት ወንጌል ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስላላወቁ ይሆናል፡፡ አለማወቅ ግን ከጥፋተኝነት አያድንም፡፡ ስለዚህ የተሰቀለውን ክርስቶስን ባለመስበክ ስለፈጸሙት ኃጢአት ተጸጽተው ንስሀ መግባትና በቀጣይ የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ መስበክ ይገባቸዋል፡፡

2.   አውቆ አጥፊዎች
እነዚህኞቹ የወንጌሉን እውነትና ሊሰበክ የሚገባው ክርስቶስ ብቻ መሆኑን ያወቁ ቢሆንም፣ ወንጌልን በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ያልተረዱና ሕይወታቸው ያልተለወጠ በመሆኑ ተመሳስለው ለመኖርና ስለክርስቶስ እንዳይሰደዱ ብለው ወንጌልን ይሸቃቅጣሉ፡፡ ለመኖርና ለክብራቸው ሲሉ ያላመኑበትን ልዩ ወንጌል ይሰብካሉ፡፡ እንዲህ የሚያደርጉት ገና ለገና ስማችን በክፉ ይነሳል ብለው ስለስማቸውና ስለጥቅማቸው በመጨነቅ እንጂ በእርግጥም ነገሩ እንደዚያ ስለሆነ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ አድርባዮች በተጠነቀቁላቸው ሰዎች ዘንድ አመኔታን አላተረፉም ሁሌ በጥርጣሬ አይን ነው የሚታዩት፡፡

ሕዝቡ አይቀበለንም ብለው ስለሚያስቡ እውነት የሆነውን ሳይሆን ህዝቡ መስማት ይፈልጋል ብለው የሚያስቡትን ነው የሚሰብኩት፡፡ ይህ ግን ሕዝቡን በእነርሱ አለማወቅ መለካትና የደረሰበትን ደረጃ ዝቅ አድርጎ ከመመልከት የሚመነጭ ነው፡፡ ህዝቡ የትና የት ጥሏቸው እንደሄደ ከቶ አላወቁም፡፡ ሕዝቡ በሚሰበክለት ወንጌል ሊያዝን አይችልም ይደሰታል እንጂ፡፡ ከዚህ ይልቅ እነርሱ በሚዘበዝቡለት ተረታተረት ምን ያህል ልቡ እንደሚያዝን አላወቁም፡፡ በዚህ ጉዳይ ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርም ያዝናል፡፡ “የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል፤” (ሉቃስ 12፡47) እንደ ተባለው፥ እንዚህ አባክያን በአውቆ አጥፊነታቸው ተጠያቂነታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ሰውን ደስ ለማሰኘትና በሰው ዘንድ ተቀባይነትን ላላማጣት በሚል ወንጌልን ከመሸቃቀጥ ተመልሰው የእግዚአብሔርን ቃል በቅንነት እንደ እግዚአብሔር ሐሳብና ፈቃድ ሊያስተምሩና ሊሰብኩ ይገባል፡፡

3.   ቃሉን በመነገድ የሚኖሩ  
እነዚህኛዎቹ የሚሰብኩት በስብከት ሥራ ዳጎስ ያለ ትርፍ ለማግኘት ስለሆነ ለገበያ ቢቀርብ ያዋጣል የሚሉትን ነገር ነው ይዘው የሚቀርቡት፡፡ ይዘው የሚቀርቡት ስብከት በሉት ትምህርት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያለያይ፣ በአማኞች መካከል መለያየት እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ጉዳይ ከሌላቸው በስብከት ገበያው ላይ አይታዩም፡፡ እነዚህ ሰዎች ስለተሰቀለው ክርስቶስ ሲሰብኩ አይታዩም፡፡ ሥራቸው የዕቅበተ እምነት ዓይነት ነው ቢባልም እርሱ ማመካኛ ነው፡፡ ዋናው ግብ ገቢ ማግኘት ነው፡፡ በስብከት ስም መነገድ ነው፡፡

በዚህ ጎራ ሊመደቡ የሚችሉ እውነትን እንሰብካለን የሚሉ አንዳንዶችም የልባቸው ዋና ሐሣብ እውነትን መግለጥና ሰዎች በክርስቶስ አምነው እንዲድኑ ሳይሆን በሌሎች ዘንድ ወንጌል የገባው ነው ተብለው ዝናን ለማትረፍና በእርሱ ምክንያት ሀብት ለማጋበስ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች የተሰቀለውን ክርስቶስን ከማሳየት ይልቅ ራሳቸውን የሚያሳዩ፣ የወንጌልን ቃል ወይም ከእግዚአብሔር የተማሩትን ሳይሆን የራሳቸውን ለአቅመ ፍልስፍና ያልደረሰ የቃላት ኳኳታ የሚያሰሙ፣ ከየስፍራው የቃረሙትን ውጥንቅጥ ነገር ቀባብተው የሚያቀርቡ፣ የክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸው ደቀመዛሙርት የሚያፈሩ፣ ተከታዮቻቸውን በረቀቀና መንፈሳዊ በሚመስል ግን ባልሆነ መንገድ እንዲያመልኳቸው የሚጋብዙ፣ ከሚከተላቸው መንጋ የወፈረውንና የደለበውን አሳደው የሚይዙና የሚበሉ፣ የከሳው ግን እንዲጠገን የማያደርጉ፣ የሚናገሩትና የሚኖሩት ለየቅል የሆነባቸው ናቸው፡፡ ስለወንጌልና ስለ ክርስቶስ ሳይሆን በዚህ ክፉ ስራቸው ምክንያት ስማቸው በክፉ የሚነሣ ዋጋ ቢሶች ናቸው፡፡ እነዚህም የተሰቀለውን ክርስቶስን ከመስበክ ይልቅ ራሳቸውንና ለራሳቸው ጥቅም የሚሰብኩ በመሆናቸው ተጠያቂነታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ንስሃ ሊገቡና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ክርስቶስ ብቻ እንዲታይ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ አሊያ መጨረሻቸው ጥፋት ነው፡፡

4.   እውነተኛ ሰባኪዎች 
እነዚህ አገልጋዮች ወንጌል ምን ማለት እንደሆነ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት የገባቸው፣ ወንጌልን ለምን እንደሚሰብኩ የሚያውቁ፣ የማገልገላቸው ምክንያትም ሰዎች እውነት የሆነውን እንዲያውቁና እንዲድኑ መሆኑን የተረዱ ናቸው፡፡ እየተከፈላቸው ሳይሆን ብዙ ዋጋ እየከፈሉ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰባክያን በትክክለኛው ስፍራ ላይ ስላሉ ብዙ ተቃውሞ ይነሣባቸዋል፡፡ ስማቸው በተቃዋሚዎች ዘንድ በክፉ ይነሣል፤ ዙሪያ-ገባቸው ቢመረመር ግን የሚገኘው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ እነዚህ አገልጋዮች በትክክለኛው መሥመር ላይ የሚጓዙ ስለሆነ በአገልግሎታቸው ላይ እምብዛም ነቀፋ አይኖርም፡፡ በብዙ ተቃውሞና ስደት ውስጥም ሆነው እንኳ ዕለት ዕለት ግድ የሚላቸው የሰዎች መዳን ነው፡፡ ስለዚህ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑ የወንጌልን እውነት የመግለጥ ሥራቸውን አያቋርጡም፡፡ እውነተኛ ወንጌል ሰባኪነት ይህ ነው፡፡

ማጠቃለያ
ወንጌልን መስበክ ማለት የተሰቀለውንና ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ክርስቶስን መስበክ፣ ሰዎች ሁሉም በእርሱ እንዲድኑና የነፍሳቸውን ዕረፍት በእምነት እንዲቀበሉ፣ ወደእግዚአብሔርም ዕረፍት እንዲገቡ ማድረግ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ሊያነሣሣን የሚገባው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ስለኃጢአታችን አሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ እንዲሁ ወዶናል፡፡ ይህን ተነግሮ የማያልቅ አስደናቂ ፍቅሩን በመመስከር ሰዎችን የዚህ እውነተኛ ፍቅር ምርኮኞች ማድረግ የተጠራንለት ዋና ተልእኮ ነው፡፡ ሰዎች ወደቤተክርስቲያን ወይም ወደእኛ የሚመጡት ይህን በአንድያ ልጁ ሞት የተገለጠ አምላካዊ ፍቅር ለማግኘትና በእርሱ ለማረፍ ነው፡፡  ከእኛም የሚጠበቀው የተቀበልነውን ወንጌል መስበክና ሰዎችን በሞቱ ከወደዳቸው ከአምላካቸውና ከአዳኛቸው ጋር ማስተዋወቅ ነው፡፡

ይህን ልናደርግበት በሚገባው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ባለማወቃችን ምክንያት ሰዎችን የባሰ የገሃነም ልጆች እንዳናደርግ መጠንቀቅ አለብን፡፡ ንስሃ በመግባትና ወንጌልን ብቻ በመስበክ የእስከዛሬውን ጥፋታችንን ማረም አለብን፡፡ በቃሉ የጀመርነውን ንግድም ማቆምና ያለዋጋ የተቀበላችሁትን ያለ ዋጋ ስጡ እንደተባለው በነጻ የተቀበልነውን ጸጋ በነጻ በመስጠት መንፈሳዊ አደራችንን መወጣት አለብን፡፡ የወፈሩትንና የደለቡት በጎች ብቻ በመጠበቅ ስራ መጠመዳችንን ትተን የከሱትንና የተሰበሩትን በጎች በመጠገን፣ የባዘኑትን በመፈለግ  የተሰጠንን የወንጌል አደራ መወጣት አለብን፡፡ አሊያ አትርፈናል ስንል ከስረናል፡፡ ሁላችንም አንድ ቀን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቆማችንና ስለአገልግሎታችን መጠየቃችን፣ ምላሽም መስጠታችን አይቀርምና፡፡

ለማንኛውም ወንጌል የተሰቀለውን ክርስቶስን መስበክ ነው፡፡
 ሁሉም ወንጌል እሰብካለሁ ይላል፡፡ ወንጌልን መስበክ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቀው ግን “ወንጌልን እሰብካለሁ” የሚለው ሁሉ አይደለም፡፡ በቤተ ክርስቲያን ትምህርት ውስጥ ያላለፈ ሰው የሚመላለሰው በልማድ ስለሚሆን ወንጌልን መስበክ ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ በቅጡ አይረዳውም፡፡ ወንጌል እሰብካለሁ እያለ የሚሰብከው ግን ወንጌል አይደለም፡፡ ሌላ ወንጌል ነው፡፡ ልዩ ወንጌል ነው፡፡ ያልተቀበልነው ወንጌል ነው፡፡ ወንጌል ስለኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት የሚሰበክ የምሥራች ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስም መሰበክ ያለበት ለሰዎች ሁሉ የምሥራች የሆነው የተሰቀለው ኢየሱስ ብቻ እንደሆነ አስረግጦ ይመሰክራል፡፡ የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንመልከት፡፡
·        “እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን፤” (የሐዋ. 13፡32)
·        እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር “ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን።” (የሐዋ. 14፡15)
·        “መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥” (1ቆሮ. 1፥23)
·        “ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤ በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ። እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ … እንግዲህስ እኔ ብሆን እነርሱም ቢሆኑ እንዲሁ እንሰብካለን እንዲሁም አመናችሁ።” (1ቆሮ. 15፡1-4፣11)
·        “ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታ እንደ ሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክምና፥” (2ቆሮ. 4፡5)
ከብዙ በጥቂቱ እነዚህ ጥቅሶች መሰበክ ያለበት የተሰቀለው ክርስቶስ ብቻ እንደሆነ ይመሰክራሉ፡፡ እንዲህም ሲባል እርሱ ስለኃጢአታችን መሞቱንና በሦስተኛው ቀን መነሣቱን ማእከል በማድረግ ነው ወንጌል መሰበክ ያለበት። ምክንያቱም ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የሚታረቅበት መንገድ፣ ከጭንቀቱና ከትካዜው የሚያርፍበት ዕረፍተ ሥጋ ወነፍስ እርሱ የተሰቀለው ክርስቶስ ብቻ ነውና፡፡ ከእርሱ በቀር ሌላ ይህን ሊያደርግ የሚችል ከሰማያውያን መላእክትም ሆነ ከምድራውያን ደቂቀ አዳም ፈጽሞ አይገኝምና የምንሰብከው ሌላ መልአክም ሆነ ሰው አይኖርም፡፡
በዚሁ መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት ላይ ተመሥርተው ሊቀ ሥልጣናት ሀብተ ማርያም ወርቅነህ አሁን ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ “የስብከት ዘዴ” በተባለ መጽሐፋቸው የሚከተለውን ጽፈዋል፡፡
የእግዚአብሔር ቅዱስ ዐላማ ሰው ሁሉ እንዲድን፥ ሰው ሁሉ የመንግሥቱ ወራሽ እንዲሆን የታለመ ነው። ለዚህም ሁሉ መምህር ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ መጣ፣ የስብከቱ ጠባይ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥራ የሚከተል፣ ራሱን ኢየሱስ ክርስቶስን ማእከል አድርጎ የሚሄድ ይሆናል። ስለ ሰው ደኅንነት ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ሞቷል። እንግዲያውስ የስብከቱ ይዘት፣ የስብከቱም ጠባይ የተሰቀለውን ኢየሱስን የሚመለከት መሆን አለበት። ሰባኪው በፈቀደው ርእስ ሊናገር ይችላል። ሆኖም ዋናው ዓላማ የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት ለመናገር መሆን አለበት።
ምንም የስብከት ምንጩ ቅዱስ መጽሐፍ ቢሆንም፣ ጥቅሱም ከእርሱው ቢወጣም ሐተታውና አገላለጡ ስለ አዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ መሆን አለበት። ኢየሱስን ማእከል ያላደረገ፥ የእርሱንም አዳኝነት የማይገልጥ ስብከት ሊሆን ሊባልም አይችልም። (የኢ.አ.ተ.ቤ.ክ የስብከት ዘዴ” 1980 ገጽ 64 ፤67)
ይህ የብፁዕነታቸው መጽሐፍ እንደሚያስረዳው አንድ ሰባኪ በፈለገው ርእስ ሊሰብክ ቢችልም የትምህርቱ አቅጣጫና ግብ ወደሚያድነው ኢየሱስ የሚደርስ መሆን አለበት፡፡ እንዲህ ካልሆነ ግን ሰባኪው እሰብካለሁ የሚለው ወንጌልን ሳይሆን በወንጌል ስም ሌላ ትምህርት ነው፡፡ ስለዚህ እንዲህ የምናደርግ ሰዎች በወንጌል እሰብካለሁ ስም እየሰበክን ያለውን ጉዳይ ብንመረምር ጥሩ ነው፡፡

ዛሬ በስብከተ ወንጌል አገልግሎት የተሰማሩ ሰባኪዎቻችን ሁሉ የሚሰብኩት የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ ነው ማለት አይቻልም፡፡ እርግጥ ነው የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ የሚሰብኩ አሉ፡፡ የተሰቀለውን ክርስቶስን መስበካቸው ባይቀርም፣ ወንጌልን በመስበክ ስም ግን ልዩ ወንጌልን የሚሰብኩም አሉ፡፡ ለምን? ... ለዚህ ጥያቄ የሰባኪዎቹን ማንነትና የሚሰብኩበትን ምክንያት በመፈተሽ በአራት ምድብ መድበን ምላሽ ለመስጠት እንሞክራለን፡፡

1.    የወንጌልን ምንነት በቅጡ ያልተረዱ
በዚህ ምድብ ያካተትናቸው ክፍሎች ከተሰቀለው ክርስቶስ በተጨማሪ ሌሎችንና ራሳቸውን የሚሰብኩት የወንጌልን ምንነት በቅጡ ስላልተረዱ ነው፡፡ ወንጌል የክርስቶስ የአዳኝነት ዜና በመሆኑና ከእርሱ በቀር የሚያድን ሌላ ስለሌለ ከእርሱ ውጪ ማንም አይሰበክበትም፡፡ ይህን ያልተረዱ “ሰባኪዎች” ግን “ወንጌልን ይሰብካሉ” ተብለው አውደ ምሕረት ላይ ከተሰየሙ በኋላ የሚሰብኩት ክርስቶስን ብቻ አይደለም፡፡ ያንቀላፉ ቅዱሳንንና መላእክትን፣ ራሳቸውንም ጨምሮ በሕይወተ ሥጋ ያሉትን ሌሎችን ሰዎች ጭምር ይሰብካሉ፡፡ ወግና ልማድን ይጠርቃሉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ሳይሆን ያልተዋሃዳቸውን የትርጓሜ ብሂልን ያወለካክፋሉ፡፡ የተሰቀለውን ክርስቶስን ሳይሆን እርሱ የተሰቀለበትን ዕንጨት (እፀ መስቀልን) ይሰብካሉ፡፡ ሌሎችንም ወንጌል ያልሆኑትንና ምናልባትም ከወንጌል ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ነገሮች ሁሉ ይሰብካሉ፡፡ የዚህ ስሙ ስብከተ ወንጌል ይባል እንጂ በተግባር ሰፈተሽ ሌላ ነው፡፡ በዚህ ክፍል የሚመደቡት እንዲህ የሚያደርጉት ወንጌል ማለት ምን ማለት እንደሆነ ስላላወቁ ይሆናል፡፡ አለማወቅ ግን ከጥፋተኝነት አያድንም፡፡ ስለዚህ የተሰቀለውን ክርስቶስን ባለመስበክ ስለፈጸሙት ኃጢአት ተጸጽተው ንስሀ መግባትና በቀጣይ የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ መስበክ ይገባቸዋል፡፡

2.   አውቆ አጥፊዎች
እነዚህኞቹ የወንጌሉን እውነትና ሊሰበክ የሚገባው ክርስቶስ ብቻ መሆኑን ያወቁ ቢሆንም፣ ወንጌልን በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት ያልተረዱና ሕይወታቸው ያልተለወጠ በመሆኑ ተመሳስለው ለመኖርና ስለክርስቶስ እንዳይሰደዱ ብለው ወንጌልን ይሸቃቅጣሉ፡፡ ለመኖርና ለክብራቸው ሲሉ ያላመኑበትን ልዩ ወንጌል ይሰብካሉ፡፡ እንዲህ የሚያደርጉት ገና ለገና ስማችን በክፉ ይነሳል ብለው ስለስማቸውና ስለጥቅማቸው በመጨነቅ እንጂ በእርግጥም ነገሩ እንደዚያ ስለሆነ አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ አድርባዮች በተጠነቀቁላቸው ሰዎች ዘንድ አመኔታን አላተረፉም ሁሌ በጥርጣሬ አይን ነው የሚታዩት፡፡

ሕዝቡ አይቀበለንም ብለው ስለሚያስቡ እውነት የሆነውን ሳይሆን ህዝቡ መስማት ይፈልጋል ብለው የሚያስቡትን ነው የሚሰብኩት፡፡ ይህ ግን ሕዝቡን በእነርሱ አለማወቅ መለካትና የደረሰበትን ደረጃ ዝቅ አድርጎ ከመመልከት የሚመነጭ ነው፡፡ ህዝቡ የትና የት ጥሏቸው እንደሄደ ከቶ አላወቁም፡፡ ሕዝቡ በሚሰበክለት ወንጌል ሊያዝን አይችልም ይደሰታል እንጂ፡፡ ከዚህ ይልቅ እነርሱ በሚዘበዝቡለት ተረታተረት ምን ያህል ልቡ እንደሚያዝን አላወቁም፡፡ በዚህ ጉዳይ ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርም ያዝናል፡፡ “የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል፤” (ሉቃስ 12፡47) እንደ ተባለው፥ እንዚህ አባክያን በአውቆ አጥፊነታቸው ተጠያቂነታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ሰውን ደስ ለማሰኘትና በሰው ዘንድ ተቀባይነትን ላላማጣት በሚል ወንጌልን ከመሸቃቀጥ ተመልሰው የእግዚአብሔርን ቃል በቅንነት እንደ እግዚአብሔር ሐሳብና ፈቃድ ሊያስተምሩና ሊሰብኩ ይገባል፡፡

3.   ቃሉን በመነገድ የሚኖሩ  
እነዚህኛዎቹ የሚሰብኩት በስብከት ሥራ ዳጎስ ያለ ትርፍ ለማግኘት ስለሆነ ለገበያ ቢቀርብ ያዋጣል የሚሉትን ነገር ነው ይዘው የሚቀርቡት፡፡ ይዘው የሚቀርቡት ስብከት በሉት ትምህርት ሕዝብን ከሕዝብ የሚያለያይ፣ በአማኞች መካከል መለያየት እንዲፈጠር የሚያደርግ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነት ጉዳይ ከሌላቸው በስብከት ገበያው ላይ አይታዩም፡፡ እነዚህ ሰዎች ስለተሰቀለው ክርስቶስ ሲሰብኩ አይታዩም፡፡ ሥራቸው የዕቅበተ እምነት ዓይነት ነው ቢባልም እርሱ ማመካኛ ነው፡፡ ዋናው ግብ ገቢ ማግኘት ነው፡፡ በስብከት ስም መነገድ ነው፡፡

በዚህ ጎራ ሊመደቡ የሚችሉ እውነትን እንሰብካለን የሚሉ አንዳንዶችም የልባቸው ዋና ሐሣብ እውነትን መግለጥና ሰዎች በክርስቶስ አምነው እንዲድኑ ሳይሆን በሌሎች ዘንድ ወንጌል የገባው ነው ተብለው ዝናን ለማትረፍና በእርሱ ምክንያት ሀብት ለማጋበስ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች የተሰቀለውን ክርስቶስን ከማሳየት ይልቅ ራሳቸውን የሚያሳዩ፣ የወንጌልን ቃል ወይም ከእግዚአብሔር የተማሩትን ሳይሆን የራሳቸውን ለአቅመ ፍልስፍና ያልደረሰ የቃላት ኳኳታ የሚያሰሙ፣ ከየስፍራው የቃረሙትን ውጥንቅጥ ነገር ቀባብተው የሚያቀርቡ፣ የክርስቶስን ሳይሆን የራሳቸው ደቀመዛሙርት የሚያፈሩ፣ ተከታዮቻቸውን በረቀቀና መንፈሳዊ በሚመስል ግን ባልሆነ መንገድ እንዲያመልኳቸው የሚጋብዙ፣ ከሚከተላቸው መንጋ የወፈረውንና የደለበውን አሳደው የሚይዙና የሚበሉ፣ የከሳው ግን እንዲጠገን የማያደርጉ፣ የሚናገሩትና የሚኖሩት ለየቅል የሆነባቸው ናቸው፡፡ ስለወንጌልና ስለ ክርስቶስ ሳይሆን በዚህ ክፉ ስራቸው ምክንያት ስማቸው በክፉ የሚነሣ ዋጋ ቢሶች ናቸው፡፡ እነዚህም የተሰቀለውን ክርስቶስን ከመስበክ ይልቅ ራሳቸውንና ለራሳቸው ጥቅም የሚሰብኩ በመሆናቸው ተጠያቂነታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ስለዚህ ንስሃ ሊገቡና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ክርስቶስ ብቻ እንዲታይ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ አሊያ መጨረሻቸው ጥፋት ነው፡፡

4.   እውነተኛ ሰባኪዎች 
እነዚህ አገልጋዮች ወንጌል ምን ማለት እንደሆነ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት የገባቸው፣ ወንጌልን ለምን እንደሚሰብኩ የሚያውቁ፣ የማገልገላቸው ምክንያትም ሰዎች እውነት የሆነውን እንዲያውቁና እንዲድኑ መሆኑን የተረዱ ናቸው፡፡ እየተከፈላቸው ሳይሆን ብዙ ዋጋ እየከፈሉ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ እነዚህ ሰባክያን በትክክለኛው ስፍራ ላይ ስላሉ ብዙ ተቃውሞ ይነሣባቸዋል፡፡ ስማቸው በተቃዋሚዎች ዘንድ በክፉ ይነሣል፤ ዙሪያ-ገባቸው ቢመረመር ግን የሚገኘው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡ እነዚህ አገልጋዮች በትክክለኛው መሥመር ላይ የሚጓዙ ስለሆነ በአገልግሎታቸው ላይ እምብዛም ነቀፋ አይኖርም፡፡ በብዙ ተቃውሞና ስደት ውስጥም ሆነው እንኳ ዕለት ዕለት ግድ የሚላቸው የሰዎች መዳን ነው፡፡ ስለዚህ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑ የወንጌልን እውነት የመግለጥ ሥራቸውን አያቋርጡም፡፡ እውነተኛ ወንጌል ሰባኪነት ይህ ነው፡፡

ማጠቃለያ
ወንጌልን መስበክ ማለት የተሰቀለውንና ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ክርስቶስን መስበክ፣ ሰዎች ሁሉም በእርሱ እንዲድኑና የነፍሳቸውን ዕረፍት በእምነት እንዲቀበሉ፣ ወደእግዚአብሔርም ዕረፍት እንዲገቡ ማድረግ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ሊያነሣሣን የሚገባው የእግዚአብሔር ፍቅር ነው፡፡ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ስለኃጢአታችን አሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ እንዲሁ ወዶናል፡፡ ይህን ተነግሮ የማያልቅ አስደናቂ ፍቅሩን በመመስከር ሰዎችን የዚህ እውነተኛ ፍቅር ምርኮኞች ማድረግ የተጠራንለት ዋና ተልእኮ ነው፡፡ ሰዎች ወደቤተክርስቲያን ወይም ወደእኛ የሚመጡት ይህን በአንድያ ልጁ ሞት የተገለጠ አምላካዊ ፍቅር ለማግኘትና በእርሱ ለማረፍ ነው፡፡  ከእኛም የሚጠበቀው የተቀበልነውን ወንጌል መስበክና ሰዎችን በሞቱ ከወደዳቸው ከአምላካቸውና ከአዳኛቸው ጋር ማስተዋወቅ ነው፡፡

ይህን ልናደርግበት በሚገባው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ባለማወቃችን ምክንያት ሰዎችን የባሰ የገሃነም ልጆች እንዳናደርግ መጠንቀቅ አለብን፡፡ ንስሃ በመግባትና ወንጌልን ብቻ በመስበክ የእስከዛሬውን ጥፋታችንን ማረም አለብን፡፡ በቃሉ የጀመርነውን ንግድም ማቆምና ያለዋጋ የተቀበላችሁትን ያለ ዋጋ ስጡ እንደተባለው በነጻ የተቀበልነውን ጸጋ በነጻ በመስጠት መንፈሳዊ አደራችንን መወጣት አለብን፡፡ የወፈሩትንና የደለቡት በጎች ብቻ በመጠበቅ ስራ መጠመዳችንን ትተን የከሱትንና የተሰበሩትን በጎች በመጠገን፣ የባዘኑትን በመፈለግ  የተሰጠንን የወንጌል አደራ መወጣት አለብን፡፡ አሊያ አትርፈናል ስንል ከስረናል፡፡ ሁላችንም አንድ ቀን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቆማችንና ስለአገልግሎታችን መጠየቃችን፣ ምላሽም መስጠታችን አይቀርምና፡፡

ለማንኛውም ወንጌል የተሰቀለውን ክርስቶስን መስበክ ነው፡፡
 
24 comments:

 1. Why you go around? Tell us Who is your target Mr sebaki? If you afraid to tell the truth, you need to be stoned because yuo are denying the true God in front of us to fit the crowd

  ReplyDelete
 2. Tebareku abbo..ene betam yemiyastelugne degomo medrek lay sebaktachew ye krstos wedajje mesayoch.hiwotachew nuroachew gen befesum getan yemaymesel..I think be huletegnawo yemedbachwachwo nachwo.beteleye yemiseruten gif enamen atiyat ayaweken medrek lay komew eyesus suddenly mesmat yechenkegnal.

  ReplyDelete
 3. guys, we have many times told you ( the protestants or their servants-tehadiso) that we CAN NOT accept the LAME wongel of menafkans, we preach our JESUS( the son of our lady VIRGIN MARRY) as GOD not only LORD, we still preach the SAYINTS as their deeds are disclosed in the bible, " egziabher bekdusanu endetegelete atawkumin????"------we preach this true wongel, not the menafkans' ento-fento'

  ReplyDelete
  Replies
  1. manim yemiawuk bimesilew liyawuk endigebaw gena alawekem....kegeez wedeamaregna yeteteregomewun anibibeh yihon?alanebebikim."aemiru keme tesebiha egiabiher betsadiku" yilal .tirgumum "egziabher bekidusanu endetemesegene ewuku "malet new.yakeberachewun..yeredachewun..yadanachewun amilak yameseginalu malet new..yilikunm yeadis kidan kidusan kidisinachew fitsum newuna egziabiher beliju yaderegelachewun asibew yameseginalu malet new.chigiru begileseboch tetseeno yadegena yetemaren sew silewengel masiredat fetagn mehonu new.geta yirdah!!

   Delete
  2. "we preach our JESUS( the son of our lady VIRGIN MARRY) as GOD not only LORD"

   What does this even mean? Not only as Lord? Don't you know his Lordship is unique and when you call Jesus "Lord" essentially you're acknowledging his divine nature?
   This shows basic lack of knowledge on the bible

   Delete
 4. WOW! TEBAREKU....EWINETEGNA MELEEKIT NEW...BERTU LETEKAWAMIWOCH BOTA ATISITU..LETESADABIWOCHIM TSELIYU...KIFU YEMIMELISULACHIHU WOYIM YEMINAGERUACHIHU BELELA MENFES YETEYAZU NACHEWUNA TAGESUACHEW!!!

  ReplyDelete
 5. Geta yibarkih tiru new

  ReplyDelete
 6. እውነት ብላችኋል፡፡ ጌታ ይህንን እውነት ህዝቡ እንዲረዳና ከሞት እንዲያመልጥ ልንጸልይ ይገባል፡፡ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፡፡ እኛ ይህ ለውጥ እንዲመጣ በርትተን ልንተራ ይገባል፡፡ስራው የእግዚአብሔር ነውና፡፡ አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ። አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤
  ስለዚህ በድፍረት። ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፤ ሰው ምን ያደርገኛል? እንላለን።የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።
  ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። ዕብ 13:5-8

  ReplyDelete
 7. yeleba sibisib hula !kirstosin atawkutim

  ReplyDelete
 8. ተዘከሩ መኳንንቲክሙ…ዋኖቻችሁን አስቡ…ዕብ 13 ቁ 7!!!
  1.ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ወንጌል የሚተርከውን የአብ አንድያ ልጅ መድኅን ክርስቶስ በመስበክ ረገድ አንዳች ህጸጽ የለባትም፡፡ፍጽምት ናት!!ይሄው ማስረጃየ…
  (ሀ) 18 በዐላትን በጌታ ስም ሰይማ በተለየ ሁኔታ ታከብራለች፡፡9ኙ ማለትም፡ የመጋቢት 29ኙ ብስራት ወይም ትስብዕት፣ልደት፣ጥምቀት፣ደ/ታቦር፣ሆሳዕና፣ስቅለት፣ትንሣኤ፣ዕርገት እና ጰራቅሊጦስ በማንኛውም ቤ/ክ ውስጥ ከፍ ባለና አገራዊ ስሜት ባለው መልኩ ይከበራሉ፡፡የተወሰኑት እንደውም ብሔራዊ በዐላት ናቸው፡፡ከ9ኙ ንዑሳት የጌታ በዐላትም ማለትም ከመስቀል፣ስብከት፣ብርሃን፣ኖላዊ፣ግዝረት፣ልደተ ስምዖን(ጌታ በዘሌዋ 12 መሰረት በኦሪቱ ህግ በ40 ቀኑ ወደ መቅደስ ሲገባ ስምዖን በሉቃ 2 ቁ 29 ጀምሮ ያለውን የጸለየበት ቀን)፣ቃና ዘገሊላ፣ደ/ዘይት እና የመጋቢት መስቀል በተለየ መልኩ ከወንጌሉ ጋር ተሳስረው በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ይዘከራሉ፡፡የቅዱሳን በዐል ሲሆን ግን ቅዱሱ የሚዘከረው በስሙ በታነጸው ቤ/ክ ብቻ ነው፡፡ለምሳሌ ሚያዚያ ጊዮርጊስ የሚዘከረው በቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ ወይም ጽላቱ ባለበት ደብር ብቻ ነው፡፡ጥምቀት ግን የጌታ በዐል ስለሆነ በሁሉም ይከበራል፡፡ልደትም፣ትንሳኤም እንደዛው ነው፡፡በሁሉ ይከበራል፡፡ይሄ ደግሞ ፕሮቴስታንት ከመምጣቱ በፊት ድሮ በጣም ድሮ የተጀመረና አሁንም የቀጠለ ነው፡፡ስለዚህም ነው ክርስቶስን እናስተዋውቃችሁ ስትሉን የምንስቀው፡፡ቀድመን አምላክነቱን አውቀን አክብረነዋላ!!
  (ለ) “ቁማችሁ አዳምጡ!” ሲል ዲያቆኑ አውጆ በካሕኑ የሚነበበውን ቃለ-ወንጌል ጨምሮ በቅዳሴው መሃል ብቻ 4 የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት አሉ፡፡ማኅሌት ያለ እንደሆነ ደግሞ ከእስመለዓለም በፊት ወንጌል መነበቡ ግድ ነው፡፡ያውም በገጠሪቱ ኢ/ያ በተለይም በሰሜኑ የትርጓሜ-ሐዲስ መምር ከተገኘ እስመለዓለም ላይ የሚነበበው ወንጌል በአንድምታ ተተርጉሞ ይሰማል፡፡ለኦርቶዶክሳውያን ወንጌል ብርቃችን ሳይሆን ትጥቃችን ነው የምልህ ለዚህ ነው፡፡
  (ሐ) ገድላትንና ድርሳናትን ማስተማር ተገቢነቱ ባያጠራጥርም አብዛኛው ሰባኪ በማታ የወንጌል መርሐግብሮቻችን ይዞ የሚመጣው መጽሐፍቅዱስ እንጅ እናንተ ከጣራ በላይ እንደምታጮሁት ድርሳናትንና ገድላትን አይደለም፡፡በእኛ ዐውደ-ምህረት ከገድላትና ድርሳናት በቀር እንደማይሰበክ ለማሳመን ስትጥሩ ሳይ ግን ሰዎቹ በጌታ ስም የሚሰራ ኃጢአት ጽድቅ ነው የሚል ወንጌል አላቸው ይሆን እላለሁ!!መጀመሪያ ነገር ወንጌሉን ከአመታት በፊት ማን ወደ አግእዝና አማርኛ ተረጎመውና!!ወይ ምጥ ለእናት ማስተማር!!

  ReplyDelete
 9. 2. የቅዱሳንን ገድልና ተአምር መናገር ወንጌልን ማስረጽ እንጅ ልዩ ወንጌል መስበክ አይደለም፡፡ላስረዳ…
  (ሀ) ክርስቶስን ስበኩ ማለት ቅዱሳን ስለ ስሙ ያደረጉትን ተጋድሎ እና በተጋድሎአቸው ያገኙትን ጸጋ እና አክሊለ ክብር አትናገሩ ማለት እንደሆነ አድርጎ መተርጎም ጌታ ለእነሱ ስለመረጠላቸው ፍሬንድና ስለላከላቸው ፍሪጅ እና አልጋ ተናግረው ከማይጠግቡ ሰዎች አይጠበቅም፡፡እንዴ! ባለፉት የአገራችን የመንግሥት ሥርዓቶች ስለደረሰባችሁ በደል እና ስላደረጋችሁት ተጋድሎ ተርካችሁ-ጠርቃችሁ የማትጠግቡ ሰዎች እኛን ስለ እነ አቡነ ጴጥሮስ አትናገሩ ስትሉን እንታዘባችኋለን!!
  (ለ) የቅዱሳንን ህይወት መተረክ እንደሚገባ ራሱ ባለቤቱ ነው የነገረን ይሄው በማቴ 26 ቁ 13 የሰፈረው ቃሉ እንደወረደ “….እውነት እውነት እላችኋለሁ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በሚሰበክበት በማናቸውም ስፍራ እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ ሊሆን ይነገራል፡፡” ሲል የመግደላዊቷን ገድል ከቃለ-ወንጌሉ አስተሳስሮታል፡፡እሱ ያስተሳሰረውን ማን ይለያያል???መከተል እንጅ!!
  (ሐ) ሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ ወደ ዕብራውያን ሰዎች ምዕራፍ 11ን ሙሉውን የብሉዩን ቅዱሳን ገድል ለመተረክ ነው ያዋለው፡፡አንብበው!!እኛም በተራችን እሱ በጠራቸው ላይ ከእሱ ህልፈት በኋላ የተነሱትን እና ስለ ክርስቶስ መከራ የተቀበሉትን ጻድቃንና ሰማዕታት ጨምረን ዜና-ተጋድሎአቸውን ስንናገር ልዩ ወንጌል ለመስበክ ሳይሆን ጌታን ታምነው ስላገኙት አክሊለ ክብር እየመሰከርን ወንጌል በቲዎሪ ሳይሆን በተግባር እንዴት እንደተተረጎመች በማስረዳት ይበልጥ በምዕመኑ እንድትሰርጽ እያደረግን ነው፡፡
  (መ) ሐዋርያው ይመስጠኛል!!ከእሱ መልእክት ልጨምር!! ዕብ 13 ቁ 7 “….የእግዚአብሄርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፡፡የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው፡፡ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና፣ዛሬ፣እስከ ለዘላለም ያው ነው….”ይላል፡፡አዎ!ትናንት እነ ቅ/ጳውሎስ እነ ቅ/ያሬድ የነገሩን ክርስቶስ፣ዛሬ አባቶቻችን የሚሰብኩት ክርስቶስ፣ነገም መጪው ኦርቶዶክሳዊ ትውልድ የሚመሰክርለት ክርስቶስ ያው ነው፡፡ስለዚህ እንደ አዲስ የሚያሥተዋውቅ አያሻንም!!ዋኖቻችንንም ከነ ገድል ፍሬያቸው እናስባለን፤እነሱን ለአርዓያነት የሰጠንን ክርስቶስንም እንሰብካለን!!
  (ሠ) የሐዋርያት ስራ ስንል የነጳውሎስን እና ጴጥሮስን ስራ ብቻ የሚተርክ ማለታችን ሳይሆን እ/ር በእነሱ አድሮ የሰራው ስራ ማለታችን መሆኑ እርግጥ ነው፡፡ትንቢተ ኢሳያስ/ኤርምያስ፣ሕዝቅኤል…ስንልም እንደዛው ነው፡፡ኦሪቱ እና መጽሐፈ-ነገሥቱም እ/ርን ብቻ እሰብካለሁ ብሎ የቆመ ሳይሆን ስለ ታላላቅ አበው፣ነቢያት፣መሳፍንት፣መኳንንት፣ነገሥታት የሚተርክ ነው፡፡ታዲያ እኛን ገድል አትናገሩ ስትሉን መጽሐፍቅዱስ አንድ ላይ ከተጠረዘበት ጊዜ በኋላ እ/ር በቅዱሳኑ አድሮ ስራውን መስራት አቁሟል ልትሉን ነው??ተመየጢ-ተመየጢ፣ተሃድሶ ቀሳጢ!!

  ReplyDelete
 10. 3. (ሀ) እናንተ የምትነግሩን ክርስቶስ ወይ ገና ከገዳመ ቆሮንቶስ ያልወጣው ወይም በጌቴሴማኔ ብቻውን በለበሰው ሥጋ ምክንያት በጸሎት የሚቃትተው ክርስቶስ ይመስለኛል፡፡የእኛ ክርስቶስ ግን ገዳመ ቆሮንቶስና ጌቴሴማኔ ብቻ የነበረው ክርስቶስ አይደለም፡፡ደብረታቦር ላይ ከነቢያትና ከሐዋርያት ጋር ብርሃነ መለኮቱን የገለጸ፣ብቻውን ነጥለን ጌታ ጌታ የምንለው ሳይሆን ከአብና ከመንፈስቅዱስ ጋር የምንጠራው፣ሰፊ ቤተሰብ ማለትም እንደ እናት እመቤታችን፣እንደወንድም ሐዋርያትና 72ቱ አርድእት፣እንደ እህት 36ቱ ቅዱሳት አንስት ሆነው እሱ ግን የእነዚህ ሁሉ ራስ መሆኑን የምንመሰክርለት ክርስቶስ ነው ያለን፡፡እንጅ በፍጡራን ዜና ተጋድሎ የሚቀና እና የሚከለል አምላክ የለንም፡፡የቤ/ክ ራስ የተባለውን ክርስቶስ ስለ ስሙ መከራ የተቀበለው የቅ/ጊዮርጊስ ገድል ሸፈነው ማለት ክብር ይግባውና ክርስቶስን እንደ ዘኬዎስ ማሳጠር ይሆንብኛል፡፡የወይኑ ግንድ አይሸፈንም!!ይሄ ሀሳብ (ለፈጸምኩት prejudice ይቅርታ የረደረግልኝና) ጌታን ከፍ ከማድረግ የመነጨ ሳይሆን በቀራንዮ ተፈጸመ ካለ በኋላ የማዳኑን ስራ አጠናቆ በአባቱ ቀኝ በክብር የተቀመጠውን ሰማያዊ አባት በየእለቱ እንደሚማልድ ከሚያስብ ጭንቅላት ይመነጫል፡፡
  (ለ) ሐዋርያውማ በኤፌሶን 2 ቁ 20 እንዲህ ነው የሚለው “…በሐዋርያትና በነቢያት መሰረት(ባመኑት እምነት ባስተማሩት ትምህርት) ላይ ታንጻችኋል፡፡የማዕዘኑም ራስ(በኩረ-ምዕመናን/መምህራን)ክርስቶስ ኢየሱስ ነው….” አይ ጳውሎስ! ካንተ ወዲያ ወንጌልን ማን ሊሰብካት??ይሄው እኛ ኦርቶዶክሳውያን መሰረቶቻችንና የማዕዘኑን ራስ ይዘን አንተንም ስለተጋድሎህ በስምህ ቤ/ክ አንጸን እናስብሃለን-ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ እያልን በቅዳሴያችን-ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቦኡ ሊዲያ ሐገሩ ለኤንያ እያልን በዋዜማችን-አሁንም እናንተን ያስነሳልንን ክርስቶስ እናመሰግነዋለን!!
  (ሐ) ለዚህ ደግሞ የባለ መሀረቦቹ የነፓስተር እከሌ ክርስቶስን ከማወደስ ይልቅ ቅዱሳንን በማጣጣል የታጨቀ የስርጭትና የትራንስፎርሜሽን ጉባኤ፣የነነቢይ እከሌ ከስኒ ተመልካች መበለቶች የተቀዳ የሚመስል የትንቢት ኮንፈረንስ፣እንደ ኤልዛቤል ነቢያተ-ጣኦት በመንፈራገጥ የተሞላ የመዝሙር ኮንሰርት፣የፈውስ ምሽት ዝግጅት፣ባለቤት የሌለው ቋንቋ እየፈጠሩ ልሳን በሚል ፈሊጥ መንተባተብ አይስፈልገንም!!
  (መ) “...ንህነሰ ንሰብክ ክርስቶስሀ ዘተሰቅለ በእንተ ኃጥአን….መስቀልከ እፀ-ተነብዮ፣መስቀልከ ለሰይጣን ሞኦ….ዘርዕ ንጹህ ዘይፈሪ ውስተ-ስጋሆሙ ለቅዱሳን ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ…” እያሉ የወንጌሉን ቃል ብቻ ሳይሆን ዜማውን ከነምግባሩ ያወረሱ ዋኖች አሉን፡፡እነ ቅ/ያሬድ፣እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ይባላሉ!!አምልኮ ለሚገባው ክርስቶስ አምልኮ፣የከበረው ላከበራቸው-የተቀደሰው ለቀደሳቸው ቅዱሳን ክብር እየሰጠን እነሱን እንከተላለን!!
  ገና ገና…ውስተ ኩሉ ምድር ወጽአ ነገሮሙ፣ወውስተ-ኩሉ አጽናፈ-ዓለም በጽሀ ነቢቦሙ እንላለን!!2.1 ቢሊዮን የካቶሊክና በኦርቶዶክስነት የሚጠሩ ክርስቲያኖችም ገድለ-ቅዱሳንን በመስበክ ረገድ እንደኛው ስለሚተጉ በዚህ በኩል ብዙም ብቸኝነት አይሰማንም!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. medirek yelemede sew awaki new ayibalim.lemehonu romr 8:34 lante engida ayidelem.yemotew...kemutanim yetenesaw..silegna yemimalidew yilal..kemotena ketenesa behuala be abatu kegn mekemetun tekiso silegna yemimalidew yilal.yihin min bileh lititeregumew yihon? yemetsehaf kidus enat grreku newuna yiferdal bitil antenm lelawunm sihitet lay titilaleh. bemelekotawi bahiriw mefiredu ewunet bihonm besewunetu yimalidal yilal....mels kaleh akirib?sidib kehone yikiribih

   Delete
  2. ለውድ፡ AnonymousJune 18, 2014 at 2:21 AM
   እነዚህ ስመ-ቅዱሳንን ጠርተው በሚሰብኩ ሰባክያን ላይ የተሰነዘሩ “…..ወግና ልማድን ይጠርቃሉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ሳይሆን ያልተዋሃዳቸውን የትርጓሜ ብሂልን ያወለካክፋሉ፡፡ የተሰቀለውን ክርስቶስን ሳይሆን እርሱ የተሰቀለበትን ዕንጨት (እፀ መስቀልን) ይሰብካሉ፡፡….” የሚሉ እና ተገልብጠው ሲነበቡ ኦርቶዶክሳዊ ሰባኪዎቻችንን ጠራቂ፣አወላካፊ፣እኛ የምናከብረውን መስቀል እንጨት የሚሉ የሰላማ ጸሐፊ አገላለጾች ምርቃት አልመሰሉኝም፡፡medirek yelemede sew awaki new ayibalim የሚለው ያንተ አገላለጽም እኔን አላዋቂ ለማለት የተሰነዘረ እንጅ ቡራኬ አልመሰለኝም፡፡ በበኩሌ የፕሮቴስታንቶችን ያልተገባ እና ኢ-መጽሐፋዊ የሆነ የልሳንና የትንቢት ዘይቤ ገልጫለሁ፡፡የገለጽኩትም ስድብ ሳይሆን ሀቅ ነው ብየ አምናለሁ፡፡ድርጊቶቹ መጽሐፍቅዱሳዊ ናቸው ካልክ ማብራሪያህን ልጠብቅ!!
   ወደ ጥያቄህ ስመጣ፡ መጀመሪያ ነገር የጽሁፉ ማጠንጠኛ ክርስቶስን እንስበክ በሚል ሽፋን ስለቅዱሳን አትናገሩ የሚል መንፈስ ያለበት እንጅ ስለ ኢየሱስ አማላጅነት/ፈራጅነት ስላልሆነ ጭብጡ ላይ ብታተኩር ደስ ይለኝ ነበር፡፡የነ ማርያም መገደላዊት ምግባር ከወንጌሉ ጋር ሊሰበክ ግድ እንደሆነ ጌታ የተናገረውን ጠቅሼ ያስቀመጥኩትን ካመንክም እሰየው፡፡
   ስለ ሮሜ 8 ቁ 34 ብዙ ተጽፏል፡፡አንተም ያነበብከው ይመስለኛል፡፡አላድክምህ!!ይሁን ግዴለም ካልከኝ ግን በጥቂቱ ልናገር….ምን ገዶኝ….
   1. ‘አማላጅ’ የሚለውን ቃል እንደወረደ ሳይሆን ለምስጢሩ በተስማማ መልኩ ፈራጅ ብለን እንተረጉመዋለን፡፡ “የሚማልድ” የሚለው ዘይቤ መጻኢ ጊዜን/ድርጊትን (future time/tense) የሚያመለክትን ነው እያልከኝ ይመስለኛል፡፡እሱን ቃል በመስቀል ላይ አንድ ጊዜ “…የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው….ተፈጸመ…” ተብሎ በጌታ የሥጋዌ ወራት የታወጁ ቃላት የተፈጸመውንና እስከ እለተ-ምጽአት ለሚነሱ ምዕመናን የተደረገ የማዳን ስራ ዘለዓለማዊነት የሚገልጽ ብለን እንጅ በየዕለቱ የሚደረግ መለማመን ብለን ክርስቶስን ወደ አማላጅነት በሚያወርድ መልኩ አንተረጉመውም፡፡ደግሞም አንተ እንዳልከው ኢየሱስ አማላጅ ነው ቢባል እንኳ ይህ አገላለጽ ‘ቅዱሳን አያማልዱም፣ገድላቸውን መናገር አያስፈልግም’ ማለት ተደርጎ ተለጥጦ መተርጎም ያለበት አይመስለኝም፡፡
   2. አንተ ያልካት “በመለኮቱ ፈራጅ፣በለበሰው ሥጋ አማላጅ” የምትለዋ በሰማያት ያለውን ክርስቶስ የሰው ልጆችን ወርዶ፣ተወልዶ፣ተሰቅሎ የማዳን የቤት-ስራውን ያልጨረሰ እና በዚህ ወቅትም በአብ ቀኝ ስር ሆኖ ሲለማመን የሚውል ፍጡር የምታስመስል ኑፋቄ ታስገርመኛለች፡፡በራሳችሁ ትርጓሜ እንሂድ ቢባል እንኳ እሱ ያለመለኮቱ በሥጋው ብቻ ካማለደ ሥጋውያኑ ቅዱሳን መለኮታዊ ባህሪ ባይኖራቸውም በለበሱት ስጋ በሰማያት ሆነው እንደሚያማልዱ አለማመናችሁ የእምነቱን ከሎጂክም መራቅ ይበልጥ ያመላክተኛል፡፡ለማንኛውም ፕሮቴስታንቶች ችክ ካለው ያማልዳል/አያማልድም ክርክር ወጥታችሁ ምስጢረ-ሥጋዌ ላይ ያላችሁን አቋም ስትገልጹልን ይበልጥ እንነጋገራለን፡፡ስለ ባሕርየ-ክርስቶስ ያላችሁ አቋም እጅጉን ሲበዛ ግልጽነት የጎደለው፣ በየሴክታችሁ የሚራመደው አቋም እጅጉን የተምታታ ነው፡፡አጥሩት!!
   3. የክርስቶስን በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ የተፈጸመ የማዳን ስራ አማላጅነት ብለን ከተረጎምነው በዚሁ በሮሜ 8 ቁ 26 እና 27 ያለውን መንፈስቅዱስ ስለእኛ ይማልዳል የሚል ቃልስ እንዴት እንተርጉመው???እንግዲህ መንፈስቅዱስ አልተሰቀለ!!
   4. የግድ ቃሉን እንደ አገባቡ እያየን ካልተረጎምነው በፊደላዊነት ገደል መግባታችን ነው፡፡አንዳንድ በቁማቸው ከሚተረጎሙ ይልቅ በትርጓሜ መቃናት የግድ የሚላቸው ቃላት አሉ፡፡ለምሳሌ፡ ያንተ ከእናትና አባትህ መወለድ ‘ልደት’ ይባላል፣የጌታ ከእመቤታችን ያለ አባት(ያለ ወንድ ዘር) መወለድም ‘ልደት’ ይባላል፡፡በሁለታችሁ ልደት መሃል ትልቅ ልዩነት እንዳለ ብናውቅም በትርጉም የማቃናት መብታችንን ጠብቀን የሁለታችሁንም መወለድ ልደት እንለዋለን፡፡የሚማልድ ተብሎ ለጌታ ፈራጅነት በተነገረው ቃል እና እኛ በምንለው የቅዱሳን አማላጅነት መሃል ያለውን በቃል ተመሳስሎ በምስጢር መለያየትም እንዲሁ ከቃላት ድኩማን መሆን የመጣ እንደሆነ አስበህ ብትረዳው!!
   5. ኦርቶዶክሳዊ ከሆንክ “…ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሄር…በአብ እሪና (በመተካከል) ይኖራል፡፡ወይትዋቀስ በእንቲአነ…ስለእኛ ይከራከራል፡፡መከራከርስ የለም፡፡ስለኛ በዕለተ ዐርብ ባደረገው ተልእኮ ፍጹም ዋጋችንን የምናገኝ ስለሆነ…..” በማለት እንግሊዝኛ ክርስትና ከመነሳቱ በፊት አባቶች ወደ ግእዝ የተረጎሙትን የሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች 8 ቁ 34 የአንድምታ ትርጓሜ ገጽ-68 ተመልከት፡፡አንተም ታውቀዋለህ ብየ እንደምገምተው ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ሁሉም ሰው መጽሐፍቅዱስን እንዲያነብ ታበረታተለች እንጅ ሁሉም እንደየስሜቱ እንዲተረጉመውና በየእለቱ ሁልቆ-መሳፍርት የሌለው ዝርው ድርጅት በውስጧ እንዲበቅል ስለማትፈቅድ በጠዋቱ የወንጌሉን ትርጓሜ ከትውፊቷ እና ከሚስጥራቱ አስማምታ አስቀምጣለች፡፡ስለዚህ መጽሐፉ ላይ ግርታ ሲኖር አንድም አንድምታውን ማገላበጥ እንዲያም ሲል አባቶችን መጠየቅ እንጅ “….መገለጥ ሆነልኝ….ጌታ ተናገረኝ… “ እያሉ ስሜትን መንፈሳዊነት አላብሶ ያለሥርዓት መንጎድ የለም፡፡ዋዋዋዋይ…. አሁንም ሰው ላስቀይም ነው መሰለኝ!!እሺ!! ለሰላማ ብሎግ ትእግስት አመስግኘ፣ለማስረዘሜ ይቅርታ ጠይቄ በምርቃት ልሰናበት፡፡
   የሥርዓት አምላክ በሥርዓት ለመራመድ ይርዳን!!
   መድረቅ የለመደው ወንድምህ hiruy!!

   Delete
 11. ብቻ የሚለውን ራስህ ነው የጨመርከው።ክርስቶስ ያለው በወንጌል"እናንተን የተቀበለ እኔን ተቀበለ፤እናንተን የጣለ እኔን ጣለ" ማቴ10፥40፦42 ያለውን የት ትጥለው ?እንደዚህ የሚሉትን የወንጌል ክፍሎች ለእናንተ የእግዚአብሔር ቃል አይደለም?በ12 ዙፋን ተቀምጣችሁ ትፈርዳላችሁ ያለው፤ከአለቃችሁ ከሚካኤል በስተቀር ማንም የሚያፀናኝ የለም፥ይህም በእውነት መጽሐፍ የተፃፈ ነው"ዳን11፥21 ያለው፤እርሱ ነብይ ነውና ይጸልይልህ ትድናለህ(ዘፍ20፥7) ያለው፤ጸሎታቸው በመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ(ራእይ8፥3፦5) ያለው፤በኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ያደርጋል ከዚህም የሚበ ልጥ(ዮሐ14፥12) ያለው፤ወ.ዘ.ተ...

  ReplyDelete
 12. I am just wondering about some of the people who followers of the Ethiopian Orthodox twehdo every time they comments start with cursing (sedebe) why they don’t star with love to tale the mistake somebody made if any instead of saying bad stuff. We supposed be a role model for Christians. How do other people to follow the orthodox if you keep cursing. The writer did not write any bad or wrong thing if you really know the Bible he just taling the truth. Please read the Bible there is no passage to tale us to curse.

  ReplyDelete
 13. Kedusanen beserachewo meselwachew..searches menneber.kerstosen mesebek yalferhat eskemot deres.hawariyat
  bemeseretwat bandit kidest b Kerstiyan enamenalen k alen enesu yemesertwat b krstiyan kerstosen new yesebkechew.

  ReplyDelete
  Replies
  1. የኔ ወንድም ሐዋርያትማ አባቶቻቸውን ገድል እንዲህ ይተርኩታል….አንብብውና ከእኛ ገድለ-ቅዱሳን ልዩነት ካለው ግለጽልን….ይሄውልህ…
   ወደ ዕብራውያን ሰዎች ምዕራፍ 11
   1 እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው።
   2 ለሽማግሌዎች የተመሰከረላቸው በዚህ ነውና።
   3 ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።
   4 አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፥ በዚህም፥ እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል።
   5 ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ወሰደው አልተገኘም። ሳይወሰድ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተመስክሮለታልና፤
   6 ያለ እምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና።
   7 ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፥ በዚህም ዓለምን ኰነነ፥ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።
   8 አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ።
   9 ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤
   10 መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና።
   11 ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደ ሆነ ስለ ቈጠረች፥ ሣራ ራስዋ ደግሞ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች።
   12 ስለዚህ ደግሞ በብዛታቸው እንደ ሰማይ ኮከብ እንደማይቈጠርም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የነበሩት የሞተን ሰው እንኳ ከመሰለው ከአንዱ ተወለዱ።
   13 እነዚህ ሁሉ አምነው ሞቱ፥ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙምና፤ ዳሩ ግን ከሩቅ ሆነው አዩትና ተሳለሙት፥ በምድሪቱም እንግዶችና መጻተኞች እንዲሆኑ ታመኑ።
   14 እንዲህ የሚሉት ለእነርሱ የሚሆነውን አገር እንዲፈልጉ ያመለክታሉና።
   15 ያን የወጡበትን አገር አስበው ቢሆኑ፥ ሊመለሱ ጊዜ በሆነላቸው ነበር፤
   16 አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና።
   17-18 አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ ይስሐቅን በእምነት አቀረበ፥ የተስፋን ቃል የተቀበለው። በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል የተባለለት እርሱም አንድ ልጁን አቀረበ፤
   19 እግዚአብሔር ከሙታን እንኳ ሊያስነሣው እንዲቻለው አስቦአልና፥ ከዚያም ደግሞ በምሳሌ አገኘው።
   20 ይስሐቅ ሊመጣ ስላለው ነገር ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው።
   21 ያዕቆብ ሲሞት በእምነት የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸው ባረካቸው፥ በዘንጉም ጫፍ ተጠግቶ ሰገደ።
   22 ዮሴፍ ወደ ሞት ቀርቦ ሳለ በእምነት ስለ እስራኤል ልጆች መውጣት አስታወሰ፥ ስለ አጥንቱም አዘዛቸው።
   23 ሙሴ ከተወለደ በኋላ ወላጆቹ ያማረ ሕፃን መሆኑን አይተው በእምነት ሦስት ወር ሸሸጉት የንጉሥንም አዋጅ አልፈሩም።
   24 ሙሴ ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ እንዳይባል በእምነት እምቢ አለ፤
   25-26 ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና።
   27 የንጉሡን ቍጣ ሳይፈራ የግብፅን አገር የተወ በእምነት ነበር፤ የማይታየውን እንደሚያየው አድርጎ ጸንቶአልና።
   28 አጥፊው የበኵሮችን ልጆች እንዳይነካ ፋሲካንና ደምን መርጨትን በእምነት አደረገ።
   29 በደረቅ ምድር እንደሚያልፉ በኤርትራ ባሕር በእምነት ተሻገሩ፥ የግብፅ ሰዎች ግን ሲሞክሩ ተዋጡ።
   30 የኢያሪኮ ቅጥር ሰባት ቀን ከዞሩበት በኋላ በእምነት ወደቀ።
   31 ጋለሞታይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው ከማይታዘዙ ጋር በእምነት አልጠፋችም።
   32 እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና።
   33 እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥
   34 የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ።
   35 ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤
   36 ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ፤
   37 በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፥ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤
   38 ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ፥ በዋሻና በምድር ጕድጓድ ተቅበዘበዙ።
   39-40 እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና።

   Delete
  2. ወንድም ህሩይ
   እንደ ዕብራውያን መልክት ከሆነ የእምነት አባቶች አብይ ጉዳይ እግዚአብሔር የሰጣቸው የተስፋ ቃል እርሱም ጌታ እየሱስ ክርስቶስ ነበር:: በ ቁ ፩፪ እንደተገለፀው የምስክርነታቸው አስፈላጊነት ደግሞ: ሸክም የሚሆንብንንና ተብትቦ የሚይዘንን ሀጥያት አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በፅናት እንድንሮጥ አርአያ ስለምሆነን ነው:: ከዚያ በላይ ግን ጳውሎስ በዚሁ ምዕራፍ ዝለን ተስፋ እንዳንቆርጥ የዕምነታችን ጀማሪና ፍፁም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንድንመለከት መስቀሉን ታግሶ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በ እግዚአብሔር ዙፋን ቅኝ የተቀመጠውን እርሱን እንድናስብ ያሳስበናል:: የ አባ ሰላማ ብሎግ ፀሐፊ የሚለውም የነዚህ እምነት አባቶች ገድል አይወራ ሳይሆን “እግዚአብሔር ከ ቅዱሳንና መላእክት ጋር ሌላ አዲስ ቃል ኪዳን ስላደረገ ከዚህ በሁአላ በስማቸው ላበላ ላጠጣ መቃብራቸውን ለጎበኘ ለዝክራቸው የሚሆን ጠላ ሲዘጋጅ የሚቆላ አሻሮ ለሸተተው እስከ ፭ ወይም ፯ ትውልዱ ድረስ ምህረት ያገኛል ወዘተ’’ የሚሉ ሁልቆ መሳፍርት የመዳኛ መንገዶችን የሚያስተምሩ ለምን እንደተፃፉ እንጂ ማን እንደፃፋቸው የማይታወቁ የታሪክ ጊዜና ቦታ (መቼት) የሌላቸው ጳውሎስ የአሮጊቶች ተረት ተረት የሚላቸው ፀረ ወንጌል ድርሰቶች የቤተ ክርስቲያን አጀንዳ አይሁኑ ነው::
   “በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ ነገር እንዳላውቅ ቆርጬ ነበርና..” እንዳለው: ከርሱ ወዲያ ወንጌል ሰባኪነት ያልከው ጳውሎስ ከ ሐዋርያት ሥራ ጀምሮ እስከ ዕብራውያን መልክቱ ድረስ ከ እየሱስ በስተቀር ሌላ ወንጌል አልሰበከም::
   በነገራችን ላይ እየሱስን ነጥላችሁ ጌታ ጌታ ትላላችሁ ላልከው አሁንም ጳውሎስ በ ፊሊ ፪: ፭-፩፩ እንዳለው በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።
   እየሱስ ጌታ ነው

   Delete
  3. Thanks brother. Pls give us more.

   Delete
 14. I stop by this blog to check on Hiruy's comment. God bless your devotion.

  ReplyDelete
 15. ኤፌሶን 2 15÷22
  15 እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥
  16 ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።
  17 መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤
  18 በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።
  19 እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።
  20 በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
  21 በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤
  22 በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ

  ReplyDelete
 16. ሕሩይ እግዚአብሔር ይባርክህ።እባክህ መልስ ከመስጠት እንዳትቦዝን።ለሚጠይቁችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ፣

  ReplyDelete