Thursday, June 19, 2014

ማቅ ፖለቲካዊ ሥልጣንን ለመጨበጥ በሚያደርገው እንቅስቃሴ “ቅምጥ ኃይሌ” እያለ ሲኩራራበት የነበረው ማኅበር ታገደየማቅ ሰዎች ለክፉ ቀን ያስቀመጥነው ቅምጥ ኃይል እያሉ ሲመኩበት የነበረው ከጥምቀት ተመላሽ ወጣቶች ማኅበር መታገዱ ተሰማ፡፡ ኅብረቱ የታገደው ከቋሚ ሲኖዶስ በተጻፈ ደብዳቤ ነው፡፡ ኅብረቱ ፈቃድ አግኝቶ የነበረው ከማቅ ጋር በሚገባ እየተናበቡ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን የግል ጥቅማቸውን ለማካበትና ለማቅ ሲሰሩ በነበሩት የቀድሞው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በአባ እስጢፋ አማካይነት ነው፡፡ ቋሚ ሲኖዶስ ፈቃዱ የተሰጠው ከቃለ ዐዋዲውና ከሕገ ቤተክርስቲያን ውጪ በመሆኑ የተሰጠው ፈቃድ እንዲነሣና ሀገረ ስብከቱ በአስቸኳይ ሪፖርት እንዲያደርግ ውሳኔ መስጠቱን ሀገረ ስብከቱ ይዲድያ ለተባለውና በሕገወጥ መንገድ ዕውቅና ለሰጠው ማኅበር በጻፈው ደብዳቤ ላይ የገለጸ ሲሆን ፈቃዱም የተሰረዘ መሆኑን ጨምሮ አስታውቋል፡፡

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ከማቅ ጋር እየተመጋገቡ የሚሰሩት የግል መጽሔቶችና ጋዜጦች ግን የታገደው ይዲድያ የጠባለ አንድ ማኅበር ሳይሆን የብዙ ማኅበራት ኅብረት እንደሆነና በኅብረቱ ውስጥ የሚገኙ ማኅበራትም ከ2 መቶ ሺህ በላይ አባላት እንዳሏቸው በመዘገብ ይህን ህብረት ማገድ ቤተክርስቲያን ላይ ትልቅ አደጋ እንደሚደቅን ተቀባብለው ዘግበዋል፡፡ ለምሳሌ ፋክት የተባለው መጽሄት ህብረቱ በስሩ 86 ማኅበራትን ያቀፈና ከ2 መቶ ሺህ በላይ አባላትም በስራቸው እንዳሉ አድርጎ ዘግቧል፡፡ 

የማኅበሩ ተወካይ የሆነችው ፌቨን የተባለች ወጣት ወደጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ቀርባ ስለጉዳዩ ብትጠይቃቸው ሰጡ የተባለው ምላሽ [እንኳን 2 መቶ ሺህ] “አንድ ሚሊዮን ወጣትም ቢሆን የፈለገበት ይድረስ፡፡ ምንጣፍ አነጠፈም አላነጠፈም የፈለገበት ይድረስ” አሉ ሲል ፋክት ዘግቧል፡፡ ይሁን እንጂ የማቅ ብሎግ የሆነውን ሐራን ጨምሮ የግል ጋዜጦቹና መጽሄቶቹ ዜናውን በሚፈልጉት መንገድ አዛብተው ጻፉት እንጂ ደብዳቤውን እንኳ በዋቢነት ለማቅረብ አልፈለጉም፡፡     
ይዲድያ የተባለው ማኅበር መታገድ እንዲህ አነጋጋሪ የሆነው ለምን ይሆን ብለን ብንጠይቅ መልሱ ብዙ ጥናት አይጠይቅም፡፡ ከዚህ ቀደም እንደዘገብነው የማቅ ሰዎች እነ ታደሰ ወርቁ እና ብርሃኑ አድማስ ከላይ የደረቡትን ሃይማኖታዊ ካባቸውን አውልቀው በፖለቲካዊ አቋማቸው በመገለጥ የጥምቀት ተመላሽ ወጣቶችን (ይዲድያ የተባለው ማኅበር ማለት ነው) ከግብጽ ሙስሊም ወንድማማቾች ኅብረት ወጣቶች ጋር በማነጻጸር መንግሥትን ለመገልበጥ በሚደረገው አመጽ በማቅ በኩል ዋናዎቹ ቅምጥ ኃይሎች መሆናቸውን መናገራቸውን ዘግበን የነበረ መሆኑ ይታወሳል፡፡ እነዚህ የራሳቸው አጀንዳ የሌላቸው፣ ማቅ ለፖለቲካዊ ውጤት ይበቃ ዘንድ በራሱ አምሳል ጠፍጠፎ የሰራቸውና ያደራጃቸው ወጣቶች አቋቁመውታል የተባለው ማኅበር መታገዱ በማቅ መንደር ከፍተኛ ቁጭት ማሳደሩ አልቀረም፡፡ ማቅ የሚደጉማቸውና ከማቅ ጋር የሚመጋገቡት ጋዜጦችና መጽሄቶች የማህበሩን መታገድ እንደ ትልቅ ዜና ይዘው መውጣታቸው የማቅ መንደር በጉዳዩ ምን ያህል እንደ ተሸበረና በአባ እስጢፋ አማካይነት የገነባቸው ህገወጥ ሥራዎቹ እየፈራረሱ ለመሆናቸው አንድ ትልቅ ማሳያ እንደሆነ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡
በጥምቀት በዓል ምንጣፍ ማንጠፍ የተጀመረው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሲሆን ይህ ጉዳይ በሲኖዶስ ተወስኖ የተሰራ ስርዓት ሳይሆን እነዚሁ ማቅ ያደራጃቸው ወጣቶች በግል ተነሳሽነት የጀመሩት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ነገሮች በዚህ መንገድ የሚሄዱ ከሆነና ማንም እየተነሳ እርሱ የሚፈልገውን አንድ ነገር ያለሲኖዶስ እውቅና ወደቤተክርስቲያን የሚጨምር ከሆነ ቤተክርስቲያን ወደስርዓተ አልበኝነት መሸጋገሯ አይቀርም፡፡ እስካሁንም በርካታ የተሳሳቱ ትምህርቶችና ልምምዶች ወደቤተክርስቲያን የገቡት በዚሁ ህገወጥ መንገድ እንደሆነ ይታወቃልና ማኅበሩን ከማገድ ባሻገር በዚህ ጉዳይ ላይ የሚታየውን ሕገወጥ አካሄድ ቅዱስ ሲኖዶስ ሊቆጣጠርና ሊያስቆም ይገባል እንላለን፡፡
        

12 comments:

 1. Replies
  1. Seytan የኢሉሚናቲ ዓይን ያለዉ ነዉ ምነዉ ማሩ ይህንን ዓይን ተዉ አላልኩህም እግዚአብሔር ይገስጸዉ!

   Delete
 2. What about Mk army training in Eriteia???

  ReplyDelete
 3. very good job, we need stronger rule for our church to control the issues. no t only writing the church rule , must need to obey every order to apply and practice in the daily life. we seen so many church leaders and members were our of law and rule of church. we have to learn good law and rule from other sisters church............MK every day and time never obey church law and rule.

  ReplyDelete
 4. ማኅበረ ቅዱሳን በኦሮምኛ ቋንቋ የድረ - ገጽ አገልግሎት ሊጀምር ነው አትም ኢሜይል  ሰኔ 13 ቀን 2006 ዓ.ም.

  በእንዳለ ደምስስ

  በማኅበረ ቅዱሳን የኅትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ዋና ክፍል የኦሮምኛ ድረ ገጽ አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀምር የዋና ክፍሉ ሓላፊ ዲያቆን ዶ/ር መርሻ አለኸኝ ገለጹ፡፡


  ማኅበረ ቅዱሳን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶችን በኦሮምኛ ቋንቋ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኀን ዘዴዎች ለምእመናን ለማሰራጨት እቅድ ከያዘ መቆየቱን ዋና ክፍሉ አስታውቋል፡፡


  በዚህም መሠረት “በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የኦሮምኛ ድረ ገጽ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር ሲሆን፤ ወደፊት የኅትመትና የብሮድካስት ዝግጅቶችን ለምእመናን ለማዳረስ ማኅበሩ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ ተግባራዊ ያደርጋል” ሲሉ ዲያቆን ዶ/ር መርሻ ተናግረዋል፡፡


  የኦሮምኛ ዝግጅት ንዑስ ክፍል አስተባባሪ ዲ/ን መዝገቡ ከፍያለው ለኦሮምኛ ድረ ገጽ መከፈት ምክንያት ናቸው ያሏቸውን ሲገልጹ “በኦሮሚያ ክልል ምእመናን ስለ እምነታቸው በቋንቋቸው መማር አለመቻላቸው፤ በቋንቋው የተዘጋጁ ሃይማኖታዊ የኅትመትና የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ ውጤቶች አለመኖር እና ምእመናን በሌሎች የእምነት ተቋማት መወሰዳቸው ነው” በማለት ጠቅሰዋል፡፡


  እነዚህን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመፍታት እና ያሉትን ምእመናን ለማጽናት፤ የጠፉትንም ለመመለስ እንዲቻል ከዐውደ ምሕረት ስብከት በተጨማሪ በመገናኛ ብዙኀን ዘዴዎች ወደ ምእመናን ለመድረስ አዲስ የተዘጋጀው ማኅበራዊ ድረ ገጹ አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ታምኖበታል፡፡


  በድረ ገጹም ትምህርተ ሃይማኖት፤ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ፤ ነገረ ቅዱሳን፤ ስብከት፤ ለጥያቄዎች ምላሽ /ከምእመናን ለሚጠየቁ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥበት/፤ መዝሙር እና ኪነጥበብ ወዘተ. . . የተካተቱበት ሥራዎች እንደሚቀርቡ ዲ/ መዝገቡ ጨምረው ገልጸዋል፡፡


  የድረ ገጹ አድራሻ፡- www.eotcmk.org/afaanoromo


  በተያያዘ ዜና ከዚህ ቀደም ተቋርጦ የነበረው የእንግሊዝኛ ድረ ገጽ በቅርቡ የሚጀምር ሲሆን፤ የድረ ገጹ አድራሻ፡- www.eotcmk.org/site-en መጎብኘት ይቻላል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. ጥሩ ነዉ በተለያየ ቆንቃ ቢያስተላልፍ በአርብኛም ቢጀመር መልካም ነዉ ግን የሚያስተላልፈዉ መልእክት ነዉ ቁም ነገሩ ማቅ ያዉ የታወቀ ተልእኮ አለዉ እሱም የክርስቶስን ድህንነት ስራ መሸፈንና ሰዎች የዘላለም ሂወትን እንዳያገኙ ያባቱን የዲያብሎስን ስራ በትጋት መስራት ነዉ ግን መቼም አይሰካለትም ለምን መድሃኔአለም ለልጆቹ ይራራልና

   Delete
  2. ክርስቶሰን ታዉቀዋለህ??????
   አታዉቀዉም!!!!!!! ለምን ብትል ኦርቶዶክስ ስላልሆንክ አለማዊ እንጂ መንፈሳዊ ሂወት ስለሌለህ ነዉ::ክርስቶስ በፍጹም ልብህ አታውቀዉም :: እግዚአብሄር ልቦናችሁን ይመልስ::
   ኦርቶዶክስ እውነተኛ ሀይማኖትናት
   "የቀደመዉን መንገድ ጠይቅ በእሱም ላይ ሂድ"

   Delete
 5. Yemimrka be egziabher yimeka.mk yetedegefewo bebezw hatiyategnoche tekesha lay selehone esekemechershawo erasu mefresu aykerem .b betecrsti yan
  meseret bekerstos lay yaltesera
  mahber.sebakiwochachew hullu kwengel
  yilek hametena mekefafelen yemisebku
  betam yemeseyefewo mahber new.
  yilke
  Hametena sideb bicha Yetemola

  ReplyDelete
 6. please check credential before called them Mk. Dr. Most of them held. fake degree from Kenya. Fbi start in g investigation most credential here in USA given by Mk element.

  ReplyDelete
 7. mahiber kidusan beretu serach kegezabehar ga selehon setan hulam yechohal!!

  ReplyDelete
 8. MK Be kerestose hulun dile yadergal bertu teberatu MK Ende Abaselamawechi Dehire getse weregna ena sewer deba yalew ye seyetan mahber aydelm . DEL LEKIDUSANU DIablos gin ahunim neger ke AFu ende wenzi siweta yenoral.

  ReplyDelete
 9. Abaselamawoch neger kemitabezu menafikan gar and astemro silalachihu ena sileteneqabachihu mengedun cherk yadirgilachihu mebitachihu new degmo yemigermew asteyayet ymisetewum yemitechewum yaw rasu andsew new. Yeethiopia orthodox amagnoch beegziabiher fetarinet bemebetachin amalajinet btsadiqan , besemaetat endihum bemelaekitan teradaynet enamalen enji enante mahiber mesrtachihu betikim mekanat bemitadergut poletica aniketelachihum

  ReplyDelete