Sunday, June 22, 2014

ይህ ነው ተሐድሶ! (ክፍል ሁለት)

                                   ምንጭ፡-ተሃድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብሎግ
በክፍል አንድ ጽሑፍ “ይህ ነው ተሐድሶ” በሚል ርእስ የተሐድሶን ትምህርት መግለጥ መጀመራችን ይታወቃል፤ተሐድሶ፣ ተሐድሶ ሲባል እሰማለሁ፤ አንዳንዶች ደግሞ ተሐድሶ እውነተኛውን ትምህርት ለመለወጥ የመጣ አዲስ ትምህርት ነው ይላሉ፤ በእርግጥ ተሐድሶ አዲስ የመጣ እንግዳ ትምህርት ነውን? ለመሆኑ የሚታደሰው ምኑ ነው?”  በሚል ጥያቄ መነሻነትም የምናገለግለው ተሐድሶ (1) የትምህርተ ሃይማኖት ተሐድሶ (2) የክርስቲያናዊ ሕይወት ተሐድሶ እና (3) የሥርዐትና የአስተዳደር ተሐድሶ እንደሆነ ተመልክተናል፡፡ ከሦስቱ ዋና ዋና የተሐድሶ መስኮች አንዱን በመውሰድ ተሐድሶ ምን እንደሆነ ለማሳየትም ሞክረናል፤ ከዚያው የቀጠለው እነሆ!   

1.    ዋናው ነገር አንድ ነው፡፡
1.1. ማርታን ወደ ማርያም የመቀየር ተሐድሶ
ሰዎች ወደ እግዚአብሔር ቃል ካልተመለሱ ወደ እግዚአብሔር አይመለሱም፤ ጌታ እንዳለው  “የሚያስፈልገው ግን ጥቂት ወይም አንድ ነገር ነው፤ ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች፤ ከእርስዋም አይወሰድባትም አላት።” (ሉቃ.10፥42)፡፡ እነማርታ ቤተ ክርስቲያኑን ሞልተውታል፤ ዳቦ ጋግሩ፤ ወጥ ሥሩ፤ልብስ እጠቡ፤ከበሮ ምቱ ሲባሉ አይሰለቻቸውም፤ የክርስቶስን ወንጌል ተማሩ ሲባሉ ግን እንኳንስ ሊማሩ የሚማሩ እኅቶችና ወንድሞችን እንኳን ማየት አይፈልጉም፡፡ በዓመት አንድ ቀን የጥምቀት በዓል ሲመጣ ለማይሰማ ታቦት መንገድ ይጠርጋሉ፤ ምንጣፍ ያነጥፋሉ፤ ጉልበታቸውን ሳይሰስቱ ያገለግላሉ፤ የሚሰሙት ወንጌል ግን የለም፤ የእነዚህ ሰዎች አገልግሎት የቅናት እንጅ የእምነት አይደለም፡፡
 ለእግዚአብሔር ቃል ቅድሚያ ካልሰጡ ደግሞ ለማይሰማና ለማያይ ታቦት ምንጣፍ እንዳነጠፉ፣ ግብር እንደገበሩ ይኖራሉ እንጅ ዕረፍትን አይገኙም፡፡ እነዚህ ሰዎች ለጊዜው ደስተኞች ናቸው፡፡ ዐሥር ዐመት በዚህ መልኩ ካገለገሉ በኋላ “አሁን ለመዳናችሁ እርግጠኞች ናችሁን?” ብለን ብንጠቃቸው  እንኳንስ እርግጠኞች ሊሆኑ እንዲያውም ፍርሐታቸው ጨምሮ እናገኛቸዋለን፤ ስንጠይቃቸው የሚሰጡን መልስ “ማንም ከመሞቱ በፊት ለመዳኑ እርገጠኛ መሆን አይችልም” የሚል ነው፡፡
እነዚህ ሰዎች ይንም አይነቱን ወንጌል ከየት እንዳገኙት እናውቃለን፡፡ አዲሱ ትምህርት ነው፤ ሐዋርያት ያወገዙት፣ “ማንም እኔ ካስተማርኋችሁ የተለየ ወንጌል ቢያስተምራችሁ የተወገዘ ይሁን” (ገላ.1፡8) ብለው ያስጠነቀቁን ትምህርት ይህ ነው፡፡
ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ክርስቶስ ለመሄድ መናፈቅ አልሰሙም ማለት አንችልም፤ የሰሙትን እንዳላመኑት ግን እናያለን፡፡ ክርስቶስ በቃሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጅ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወድዶአልና፤ በእርሱ የሚያምን አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመን አሁን ተፈርዶበታል” (ዮሐ.3፡16-17) ያለው ቃል ዕረፈት ካልሰጠና እርግጠኛ ካላደረገን በምን እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን?  ከዚህ ከጸና እውነት ያንሸራተተንና ከዓለቱ ነቅሎ በአሸዋ ላይ የሠራን ማነው? ይህን ከእግዚአብሔር እውነት የሚነቅል ትምህርት በእግዚአብሔር ቃል መዋጋት ተሐድሶ ነው፡፡
ብዙዎቻችን “የአገልግሎት ማኅበራት አባላት ነን” እያልን ከበሮ ለመምታት፣ ለመዘመር፣ ታቦት ለማክበር፣ ምንጣፍ ለማንጠፍ፣ የቤተ ክርስቲያን ቅጥረ-ግቢ ለማጽዳት፣ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ታቦት የሚሄድባቸውን መንገዶች ተከትሎ ለማጽዳትና ሰንደቅ ዓላማ ለመስቀል እንጅ የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ጊዜ የለንም፡፡ ቃለ እግዚአብሔርን መስማት እግዚአብሔርን ማገልገል ነው ብለን የምናምን ስንቶቻችን ነን?  ማርታ ማርያምን ለምን ተቃወመቻት?  ቃለ እግዚአብሔርን መስማት እግዚአብሔርን ማገልገል እንደሆነ ስላልገባት ነበር፡፡ ክርስቶስ ግን ለሁሉ የሚበቃውን አንድ ታላቅ አገልግሎት አከበረ፤ እርሱም ቃሉን መስማት ነው፡፡ ተሐድሶ የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት የመታደስ አገልግሎት ነው፡፡
የጸጋ ስጦታዎቻችን የተለያዩ ናቸው፤ ለአንዱ የተሰጠው ለሌላው ላይኖረው ይችላል፤ የሚዘምር ላይሰብክ፣ የሚሰጥ ላያስተምር ይችላል፤ ለሁላችንም የተሰጠን ጸጋ ግን የእግዚአብሔርን ቃል የመስማት አገልግሎት ነው፤ በዚህ አገልግሎት ውጤታማ ያልሆነ ሰው ደግሞ በሌላ አገልግሎት ውጤታማ መሆን አይችልም፡፡ እግዚአብሔርን ስለማያውቀው የሚያገለግለው የሚያውቀውን ራሱን፣ አለቃውን፣ ታቦቱን፣ ገንዘብን፣ ክብርንና እውቅና መፈለግን፣ ተቃውሞን፣ ሥርዐትንና ታሪክን፣ እኔ ብቻ ትክክል ነኝ ማለትን እንጂ እግዚአብሔርን ሊያገለግል አይችልም፡፡ ተሐድሶ ከዚህ አይነት እስራት ነጻ ወጥቶ እግዚአብሔርን እንደቃሉ በእውነትና በመንፈስ ማምለክ (ማገልገል) ነው፡፡  
1.2. የሚያስፈልገን ጸበል ወይስ ወንጌል?
ለነማርታ እነርሱ ካልደከሙ የእግዚአብሔር ጸጋ አይበቃም፡፡ የእነርሱ ማሰሮ የምትሞላው የእግዚአብሔር ጸጋ ሲፈስስባት ሳይሆን እነርሱ የፈጩት ዱቄት ሲጨመር ብቻ ነው፡፡ ቃሉን መማር መሥዋዕት አይደልም፤ ጸበል ካልጠጡ፣መክፈልት ካልበሉ እግዚአብሔርን አላገለገሉትም፡፡ ቃሉን ካልሰሙ ቤተ ክርቲያን መሳለም ምንድን ነው? ጸበል ውሃ አይደለምን? ህሊናችንን ከሞተ ሥራ ሊያነጻ የሚችል መለኮታዊ ጸበል የእግዚአብሔር ቃል ነው፤(ዕብ.9፡14) ዲያቆናት በኩስኩስት ጸበል ከሚቀዱ ይልቅ ከመለኮታዊው ጸበል ከቃሉ ለምእመናን የማጠጣት አገልግሎት ቢጀምሩ ምናለበት? እስከመቼ ምእመናን በውሃ እየተታለሉ ይኖራሉ? የሕይወት ውሃ መጽሐፍ ቅዱስ ተከድኖ ወይም አልባሌ ቦታ ተጥሎ ዘወትር የውሃ መቅጃ ኩስኩስት ስናጥን የምንኖረው እስከ መቼ ነው? ኧረ ተዉ ጎበዝ የእግዚአብሔር ፍርድ ሳይገለጥ ወደ ቃሉ እንመለስ! ተሐድሶ ከውሃና ከመክፈልት ወደ ሕይወት ውሃ ወደ እግዚአብሔር ቃል መመለስ ነው፡፡
እግዚአብሔር የሕይወት ምግብ አዘጋጅቶ እየጠበቀን እኛ እግዚአብሔር የሰበሰበውን ሕዝብ የሚያልፍ ምግብ ያውም ውሃ አጠጥተን የምንልከው እስከመቼ ነው? ወደ እግዚአብሔር ቃል ከመመለስ የበለጠ ምን ተሐድሶ አለ? ሰውን ወደ እግዚአብሔር ቃል ከመመለስ የበለጠ አገልግሎትስ የት ይገኛል? ተሐድሶ አዲስ ነገር አይደልም፤ እግዚአብሔር ተረስቷልና ይታሰብ፤ እግዚአብሔር ክብሩንና ቦታውን ተነጥቋልና ወደ ክብሩ ይመለስ የሚል ተጋድሎ ነው፡፡ ክብሩን ለማንም እንደማይሰጥ የተናገረው እግዚአብሔር ያስነሳው አገልግሎት እንጂ አንዳች የሰው ፍላጎት የለበትም፡፡ እናውቃልን ስንዴ፣ ሰልባጅ፣ ብር ፈልገው የሚሠሩ፣ የፕሮቴስታንት ተላላኪዎች እንደምንባል፡፡ እኛ ግን የቤተ ክርስቲያኒቱ መቆሳቆል፤ የነገሮች ቅጥ ማጣት፣ በእግዚአብሔር ቦታ የማይሰሙና የማያዩ ታቦታት መቀመጥና መክበር፣ ንስሓ መግባት አለመቻላችን ቤተ ክርስቲያናችንን እየጎዳ ያለ መሆኑ፣ ያሳሰበን የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንጂ በምንም ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ላይ ክፉ አሳብ ያለን ሰዎች አይደለንም፡፡ እንዲውም በአመንነው እውነት ምክንያት ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር የሚጠቅም ልዩ ሸክም (ራእይ) ያለን ሰውች ነን፤ ራእያችን እንዳይዘገይ፣ መባረካችን እንዲፈጥን በመንገዳችን እንቅፋት አትሁኑብን እንላለን እንጂ በፍጹም እግዚአብሔር የማይፈልገው፣ ቤተ ክርስቲያንንም ሆነ ሀገርን የሚጎዳ አጀንዳ የለንም፡፡ አገልግሎታችን ሰማያዊና የከበረ መሆኑን እናውቃለን፤ ለዚህም ነው በነገር ሁሉ ስንፈተን “የማምነውን አውቀዋለሁ” ብለን ጸንተን እየተጓዝን፣ በየጊዜው ደግሞ እየበዛን ያለነው፡፡ የሚያበዛን የሕይወት ቃል የሆነው የእግዚአብሔ ቃል ነው፡፡ በተሐድሶ ያለ ሕዝብ በውሃ ዳር የተተከለ ዛፍ ነው፤ ቅጠሉ አይጠወልግም፤ ዘወትር ያፈራል እንጂ የመድረቅ ሥጋት የለበትም፡፡ ተሐድሶ ይህ ነው!
1.3. የምንሰብከው እግዚአብሔርን ወይስ የእኛን ሥነ ምግባር?
የሚያስፈልገው ነገር አንድ ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል፡፡ የእኛ ገድልና ድርሳን፣ የእኛ አመለካከትና ዕወቀት፣ የእኛ ቅኔና ትርጓሜ በቦታው ጠቃሚ ቢሆንም በእግዚአብሔር ክብር ላይ መጋረጃ ሲሆን ግን ጉዳት እንጂ ጥቅሙ አይታየንም፤ የሕይወት መንገድ የተገለጠበት መጽሐፍ “መጽሐፍ ቅዱስ” ነው፡፡ ይህን እውነት ማንም ማስተባበል እንደማይችል እናምናለን፡፡ ወደ እግዚአብሔር ቃል እንመለስ! (Back to the word of God!) ምንም ብንሰብክ፣ ምንም ብንቀኝ፣ ምንም ብናከማች የእግዚአብሔር ቃል ካልሆነ ይበተናል፡፡
ይህ ነገር ለምን ያሳስበናል? ሰዎች እንዲለወጡ፣ ንስሓ እንዲገቡ፣ እንደእግዚአብሔር ቃል እንዲመላለሱ እግዚአብሔር ይፈልጋል፤ ይህ ሊሆን የሚችለው ደግሞ እግዚአብሔርን በቃሉ መሠረት ስናውቀው ብቻ ነው፡፡ የግብፅ ፓትርያርክ የነበሩት አቡነ ሺኖዳ የተናገሩትን ምሳሌ አድረገን እንመልከት፤ “I confess before You, O Lord that I ought to have changed my trend of writing. I confess-in shame-that I often talked to people about virtue but little did I talk to them about you, though you are all in all” (The release of the spirit p.14) መልእክቱ ወደ አማርኛ ሲመለስ እንዲህ የሚል ነው፡፡ “ከአሁን በፊት ስጽፍበት የነበረውን ልማዴን መለወጥ እንደነበረብኝ አቤቱ በፊትህ እናዘዛለሁ፤ ለሕዝቡ ስለ ምግባራት (ስለመልካም ምግባር) ዘወትር ብዙ እንደ አስተማርሁ፣ ብንም እንኳን አንተ ሁሉ በሁሉ ብትሆንም ስለአንተ ግን ጥቂት እንደነገርኋቸው በሐፍረት እናዘዛለሁ፡፡” ስለ እግዚአብሔር ሳይሆን ስለ ሥነ ሥርዐት ስንሰብክ ከኖርን የምናልመውን ለውጥ ማምጣት አንችልም፤ የሚለውጠው እግዚአብሔር እንጅ የእኛ ቃል አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ በቃሉ እንጅ በእኛ የስብከት ጥበብ አይሠራም፡፡ እግዚአብሔር በቃሉ እንጂ በእኛ ተረት ለመጽናት ቃል ኪዳን የለውም፡፡
ዛፉን እየነቀልንና እያደረቅን ፍሬ የምንፈልገው ከየት ነው? እስኪ ልብ በሉ! እግዚአብሔርን ከሰው ልብ የሚያፈናቅል (እንደዛፍ ተክል የሚነቅል) ትምህርት እያስተማርን በጎ ምግባር የምናገኘው ከምኑ ነው? አቡነ ሺኖዳ እንዳሉት ስለ እግዚአብሔር ሳይሆን ስለ በጎ ሥራ ስንሰብክ የምንኖረው እስከመቼ ነው? መቼም ቢሆን የሰይጣንን አሳብ አንስተውም፤ ዛሬስ ብሎ ብሎ ተሐድሶ መልካም ሥራን መቃወም ጀመረን? ተመልከቱ! ተሐድሶ ለየለት! የሚል ሰው አይጠፋም፡፡ እያልን ያለነው በዛፉ የማይኖር ፍሬ አያፈራም፤ ሰውን ከዛፉ የሚቆርጥና የሚያደርቅ ለመጥፋትና ለመቃጠል የሚያዘጋጅ የሐሰት ትምህርት ከቤተ ክርስቲያን ይራቅ፤ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት ትታደስ ነው፡፡ይህ ነው ተሐድሶ!
በክርስቶስ የምንኖረው በቃሉ ስንኖር ብቻ ነው፤ ቃሉን እየተቃወምን ወይም ቃሉን ከአትሮንስ አውርደን የእኛን ተረት አትሮንስ ላይ የምንሰቅል ከሆነ፣ ዐውደ ምሕረቱን እንደ ስሙ የምሕረት ማወጃ አደባባይ ሳይሆን የሚያስር ትብትብ መስበኪያ ካደረግነው፣ እግዚአብሔር በቃሉ ነጻ ሊያወጣው የሚፈልገውን ሕዝብ የበለጠ የእስራት ቀንበር ከጫንንበት የት አለ የእኛ የክርስቶስ መልእክተኞች መሆን?  የምንሟገተው ለማን ነው?  ለራሳችን ወይስ ለክርሰቶስ?  ለክርስቶስ ከሆነ ቃሉን ለምን አናጠናም/አንሰብክም?  ዓለምን መቃወም የምንችለው በቃሉ ብቻ ነው፡፡ ለእኛ የተለየ ጥበብ የለንም፤ያለን ማረጋገጫ ቃሉ ብቻ ነው፡፡ ተሐድሶ ይህ ነው! ወደ እግዚአብሔር ቃል መመለስ! እግዚአብሔር ይመልሰን! የቤተ ክርስቲያናችንን የተሐድሶ ተስፋ በቃሉ እንደገና ወደ ክብሯና ቅድስናዋ የመመለስዋን ትንሣኤ ለማየት ያብቃን!

  ይቀጥላል!

19 comments:

 1. Is this"tehadso"??? and what is Protestantism??? What is the difference between the two??? i need some one who gonna elaborate this.......

  ReplyDelete
 2. Let me tell you in simple language: Thadso (reform) and protest have two different meaning. I won’t going to elaborate about protest, but let me say some about Thadso (reform)— first let me tell u that God Apostles didn’t create a religion, religion were created after them by protesting each other. Orthodox and catholic were the first denominations their after thousands emerging just by protesting their own denomination. When we come to in our point, thados is not protesting it is all about reform, which means demanding the church to go the right direction, even in my age I am looking a lot wrong doing in our church. I am afraid to say that but I will see – Lord Jesus is not presence in our church but presence in those Orthodox Christians truly believing and accepts that He is the Son of Lord, and he is Lord. It is all about learning the bible that thadso are moving and fire up!
  Please open your heart to Lord Jesus; he loves you the best evidence was his payment for your sin in behalf of you at Keranio in the cross. Read the bible, start from John.
  God bless you!

  ReplyDelete
 3. አባ ሰላማ የመናፍቃን ብሎግ ነው!!June 23, 2014 at 11:36 PM

  በ Hiruy
  እነዚህ ስመ-ቅዱሳንን ጠርተው በሚሰብኩ ሰባክያን ላይ የተሰነዘሩ “…..ወግና ልማድን ይጠርቃሉ፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ቃል ሳይሆን ያልተዋሃዳቸውን የትርጓሜ ብሂልን ያወለካክፋሉ፡፡ የተሰቀለውን ክርስቶስን ሳይሆን እርሱ የተሰቀለበትን ዕንጨት (እፀ መስቀልን) ይሰብካሉ፡፡….” የሚሉ እና ተገልብጠው ሲነበቡ ኦርቶዶክሳዊ ሰባኪዎቻችንን ጠራቂ፣አወላካፊ፣እኛ የምናከብረውን መስቀል እንጨት የሚሉ የሰላማ ጸሐፊ አገላለጾች ምርቃት አልመሰሉኝም፡፡medirek yelemede sew awaki new ayibalim የሚለው ያንተ አገላለጽም እኔን አላዋቂ ለማለት የተሰነዘረ እንጅ ቡራኬ አልመሰለኝም፡፡ በበኩሌ የፕሮቴስታንቶችን ያልተገባ እና ኢ-መጽሐፋዊ የሆነ የልሳንና የትንቢት ዘይቤ ገልጫለሁ፡፡የገለጽኩትም ስድብ ሳይሆን ሀቅ ነው ብየ አምናለሁ፡፡ድርጊቶቹ መጽሐፍቅዱሳዊ ናቸው ካልክ ማብራሪያህን ልጠብቅ!!
  ወደ ጥያቄህ ስመጣ፡ መጀመሪያ ነገር የጽሁፉ ማጠንጠኛ ክርስቶስን እንስበክ በሚል ሽፋን ስለቅዱሳን አትናገሩ የሚል መንፈስ ያለበት እንጅ ስለ ኢየሱስ አማላጅነት/ፈራጅነት ስላልሆነ ጭብጡ ላይ ብታተኩር ደስ ይለኝ ነበር፡፡የነ ማርያም መገደላዊት ምግባር ከወንጌሉ ጋር ሊሰበክ ግድ እንደሆነ ጌታ የተናገረውን ጠቅሼ ያስቀመጥኩትን ካመንክም እሰየው፡፡
  ስለ ሮሜ 8 ቁ 34 ብዙ ተጽፏል፡፡አንተም ያነበብከው ይመስለኛል፡፡አላድክምህ!!ይሁን ግዴለም ካልከኝ ግን በጥቂቱ ልናገር….ምን ገዶኝ….
  1. ‘አማላጅ’ የሚለውን ቃል እንደወረደ ሳይሆን ለምስጢሩ በተስማማ መልኩ ፈራጅ ብለን እንተረጉመዋለን፡፡ “የሚማልድ” የሚለው ዘይቤ መጻኢ ጊዜን/ድርጊትን (future time/tense) የሚያመለክትን ነው እያልከኝ ይመስለኛል፡፡እሱን ቃል በመስቀል ላይ አንድ ጊዜ “…የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው….ተፈጸመ…” ተብሎ በጌታ የሥጋዌ ወራት የታወጁ ቃላት የተፈጸመውንና እስከ እለተ-ምጽአት ለሚነሱ ምዕመናን የተደረገ የማዳን ስራ ዘለዓለማዊነት የሚገልጽ ብለን እንጅ በየዕለቱ የሚደረግ መለማመን ብለን ክርስቶስን ወደ አማላጅነት በሚያወርድ መልኩ አንተረጉመውም፡፡ደግሞም አንተ እንዳልከው ኢየሱስ አማላጅ ነው ቢባል እንኳ ይህ አገላለጽ ‘ቅዱሳን አያማልዱም፣ገድላቸውን መናገር አያስፈልግም’ ማለት ተደርጎ ተለጥጦ መተርጎም ያለበት አይመስለኝም፡፡
  2. አንተ ያልካት “በመለኮቱ ፈራጅ፣በለበሰው ሥጋ አማላጅ” የምትለዋ በሰማያት ያለውን ክርስቶስ የሰው ልጆችን ወርዶ፣ተወልዶ፣ተሰቅሎ የማዳን የቤት-ስራውን ያልጨረሰ እና በዚህ ወቅትም በአብ ቀኝ ስር ሆኖ ሲለማመን የሚውል ፍጡር የምታስመስል ኑፋቄ ታስገርመኛለች፡፡በራሳችሁ ትርጓሜ እንሂድ ቢባል እንኳ እሱ ያለመለኮቱ በሥጋው ብቻ ካማለደ ሥጋውያኑ ቅዱሳን መለኮታዊ ባህሪ ባይኖራቸውም በለበሱት ስጋ በሰማያት ሆነው እንደሚያማልዱ አለማመናችሁ የእምነቱን ከሎጂክም መራቅ ይበልጥ ያመላክተኛል፡፡ለማንኛውም ፕሮቴስታንቶች ችክ ካለው ያማልዳል/አያማልድም ክርክር ወጥታችሁ ምስጢረ-ሥጋዌ ላይ ያላችሁን አቋም ስትገልጹልን ይበልጥ እንነጋገራለን፡፡ስለ ባሕርየ-ክርስቶስ ያላችሁ አቋም እጅጉን ሲበዛ ግልጽነት የጎደለው፣ በየሴክታችሁ የሚራመደው አቋም እጅጉን የተምታታ ነው፡፡አጥሩት!!
  3. የክርስቶስን በመስቀል ላይ ደሙን በማፍሰስ የተፈጸመ የማዳን ስራ አማላጅነት ብለን ከተረጎምነው በዚሁ በሮሜ 8 ቁ 26 እና 27 ያለውን መንፈስቅዱስ ስለእኛ ይማልዳል የሚል ቃልስ እንዴት እንተርጉመው???እንግዲህ መንፈስቅዱስ አልተሰቀለ!!
  4. የግድ ቃሉን እንደ አገባቡ እያየን ካልተረጎምነው በፊደላዊነት ገደል መግባታችን ነው፡፡አንዳንድ በቁማቸው ከሚተረጎሙ ይልቅ በትርጓሜ መቃናት የግድ የሚላቸው ቃላት አሉ፡፡ለምሳሌ፡ ያንተ ከእናትና አባትህ መወለድ ‘ልደት’ ይባላል፣የጌታ ከእመቤታችን ያለ አባት(ያለ ወንድ ዘር) መወለድም ‘ልደት’ ይባላል፡፡በሁለታችሁ ልደት መሃል ትልቅ ልዩነት እንዳለ ብናውቅም በትርጉም የማቃናት መብታችንን ጠብቀን የሁለታችሁንም መወለድ ልደት እንለዋለን፡፡የሚማልድ ተብሎ ለጌታ ፈራጅነት በተነገረው ቃል እና እኛ በምንለው የቅዱሳን አማላጅነት መሃል ያለውን በቃል ተመሳስሎ በምስጢር መለያየትም እንዲሁ ከቃላት ድኩማን መሆን የመጣ እንደሆነ አስበህ ብትረዳው!!
  5. ኦርቶዶክሳዊ ከሆንክ “…ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሄር…በአብ እሪና (በመተካከል) ይኖራል፡፡ወይትዋቀስ በእንቲአነ…ስለእኛ ይከራከራል፡፡መከራከርስ የለም፡፡ስለኛ በዕለተ ዐርብ ባደረገው ተልእኮ ፍጹም ዋጋችንን የምናገኝ ስለሆነ…..” በማለት እንግሊዝኛ ክርስትና ከመነሳቱ በፊት አባቶች ወደ ግእዝ የተረጎሙትን የሐዋርያው ቅ/ጳውሎስ ወደ ሮሜ ሰዎች 8 ቁ 34 የአንድምታ ትርጓሜ ገጽ-68 ተመልከት፡፡አንተም ታውቀዋለህ ብየ እንደምገምተው ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ ሁሉም ሰው መጽሐፍቅዱስን እንዲያነብ ታበረታተለች እንጅ ሁሉም እንደየስሜቱ እንዲተረጉመውና በየእለቱ ሁልቆ-መሳፍርት የሌለው ዝርው ድርጅት በውስጧ እንዲበቅል ስለማትፈቅድ በጠዋቱ የወንጌሉን ትርጓሜ ከትውፊቷ እና ከሚስጥራቱ አስማምታ አስቀምጣለች፡፡ስለዚህ መጽሐፉ ላይ ግርታ ሲኖር አንድም አንድምታውን ማገላበጥ እንዲያም ሲል አባቶችን መጠየቅ እንጅ “….መገለጥ ሆነልኝ….ጌታ ተናገረኝ… “ እያሉ ስሜትን መንፈሳዊነት አላብሶ ያለሥርዓት መንጎድ የለም፡፡ዋዋዋዋይ…. አሁንም ሰው ላስቀይም ነው መሰለኝ!!እሺ!! ለሰላማ ብሎግ ትእግስት አመስግኘ፣ለማስረዘሜ ይቅርታ ጠይቄ በምርቃት ልሰናበት፡፡
  የሥርዓት አምላክ በሥርዓት ለመራመድ ይርዳን!!

  ReplyDelete
 4. አባ ሰላማ የመናፍቃን ብሎግ ነው!!June 23, 2014 at 11:36 PM

 5. ተባረኩ ፀጋውን ያብዛላሁ፡፡ የእግዚአብሔርን ሀሳብ ለማስፈጸም ፍቅር ይቀድማልንና እርስ በእርሳችሁ ያላችሁ ፍቅር ይብዛ ይጨምር ስለሚል ቃሉ በፍቅር እንተያይ ጌታ ይረዳናል፡፡

  ReplyDelete
 6. ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች እንደመከራቸው፡ ኤፈ. ም4፡ 4-6 4" በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤5 አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤" 6 ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ" ። ብሎ አስተምሯቸዋል። ሌላ ነገር እከሌ እከሌ የሚባል ሐይማኖት በእግዚአብሔር ዘንድ የለም። ነገር ግን ሁሉም በራሱ ጥበብ ስለሚመራ እግዚአብሔርን አይውቁትም። በዚህም ዓለማችን በብዙ ሥጋዊ ጥበብ የተሞላች ስለሆነ እኔ የዚህ ወግን ነኝ በማለት በእርግማን ቦታ የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው። ለዚህም ነው እሥራኤል እንዴት ከእግዚአብሔር ዘንድ ርቃ በራሷ ጥብበ በመስዋእትና በቁርባን ሕግ ወይም ደምን በማፍሰስ ህግ ብቻ ጽድቅ ይገኛል ብላ ሕይወት የሚሰጣትን ክርስቶስን በማግለሏ ምክንያት ወይም በራሱ ጥበብ በመጉዟ ምክንያት ሕይወትን እንዳጣች እንዲህ ሲል መክሯቸዋል። ሮሜ ም10፡ 1-4፡ 1" ወንድሞች ሆይ፥ የልቤ በጎ ፈቃድና ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ልመናዬ እንዲድኑ ነው።2 በእውቀት አይቅኑ እንጂ ለእግዚአብሔር እንዲቀኑ እመሰክርላቸዋለሁና።3 የእግዚአብሔርን ጽድቅ ሳያውቁ የራሳቸውንም ጽድቅ ሊያቆሙ ሲፈልጉ፥ ለእግዚአብሔር ጽድቅ አልተገዙም"።4 የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና። በዚህም ይህንን ቃል ባለመረዳታቸው ደግሞ በዘመናችን ክርስቶስ ሕግን ፈጽሙኦታል ከእንግዲህ ወዲያ ሕግ የለም ብለው በእምነት ድነናል እሙን ብቻ እየጠራን እንኖራለን ብለው ኃጥያትን የሚበዙ እንዚህ ሁሉ መንፍቃን ወይም ፕሮተኤስታንት ወይም ሌላ ሰም ይዘው ይጓዛሉ። ነገር ግን ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነው ያለው ስለ ደም ማፍሰኡ በርሱ ደም እርሱ ይህንን የደም ማፍሰሱን ሕግ አቁሞታል ፈጽሞታል። በዚህም ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነው። የሞራል ሕጉ ግን ሁልግዜም ጥበበኞች የሚአስተውሉት የእግዚአብሔር ሕግ ነው። በዚህም ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች እንደመከራቸው ሮሜ ም7 ፡ 12 12 "ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት"። ብሏቸዋል። ሰዎች የእግዚአብሔር ትበብ ሰለጎደላቸው ሃይማኖትን ያበዛሉ በዚህም በእኛ መካከል መከፈፈል የበዘበት ምክንያቱ ይህ ነው፡፡
  ወስብሃት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
 7. It the end of the day, the Gospel conveys one message: accept Jesus and be a good person in his name. Unlike your statement, reading and learning the Gospel is not the ultimate objective, it is the work you do in his. Forgive me, adelem legzier lesewum tegonbiseh/akibireh selamsela maletikin egzier ayiresam. Trust me, your message is another form of protestantism. ..

  ReplyDelete
 8. ምግባር ያለው ሃይማኖት እንጂ ማወቅ ብቻውን ኤአጸድቅም። አዲስ እውቀት ያመጣጭሁ ይመስል ያኦርቶዶክስ ምዕመናንን አላዋቂ ለማስመሰል የማትፈጥሩት ማደናገርያ ወሬ የለም። ምነው አሉባልታ ትታችሁ ወንና ወንድ መጋባት ሴትና ሴት መጋባት ሃጥያት አይደለም ብለው ግብረ ሰዶማውያንን በቤተ ጸሎታቸው ባርከው ስለሚያጋቡት እናንተ ስለምታደንቃቸው ፕሮቴስታንቶች የገደል ጉዙ ለምን አትናገሩም። ንገሩን ካላችሁ አገር ቤት ጻድቅ ምትመስሉ አነዳንድ ፕሮቴስታንቶች ሁሉ በገንዘብ የሚረድዋችሁ የዚህ ዓላማ አራማጅ ፕሮቴስታንቶች መሆናቸውን ያደባባይ ምስጢር ነው። አገር ቤት መልአክ የምትመስሉ መናፍቃን በበርካታ ጉዳዮች ውጭ አገር ስትታዩ ሃይማኖት ያላችሁም አትመስሉም። ማታለል እራሱ አንድ ትልቅ ሓጢያት ነው ይህነ ብሎግ በትክክለኛ ማንንነታችሁ በፕሮቴስታንትነታችሁ ግልጽ አድርጋችሁ ቢሆን ባታላይነት ባልጠየከችሁ ነበር ነገር ግነ ኦርቶዶከስ ሳትሆኑ ኦርቶዶከስ እያስመሳላችሁ በፈጠራና ባሉባለታ ወሬ ቤተክርስትያናችን ህዝባችን እያላችሁ ይህቺን ሃይማኖት መተቸታችሁ ምዕመናኑን ማንቃሸሻችሁ የናነተን አታላይነት ነው የሚያንጸባርቀውና ወደ እውነቱ ብትመጡ ነው ሚሻላችሁ። ጠቃቅን ነገር እየለቃቀማችሁ የሰው አይምሮ አታድክሙ።

  ReplyDelete
 9. "ስለ እግዚአብሔር ሳይሆን ስለ ሥነ ሥርዐት ስንሰብክ ከኖርን የምናልመውን ለውጥ ማምጣት አንችልም፤ የሚለውጠው እግዚአብሔር እንጅ የእኛ ቃል አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ በቃሉ እንጅ በእኛ የስብከት ጥበብ አይሠራም፡፡ እግዚአብሔር በቃሉ እንጂ በእኛ ተረት ለመጽናት ቃል ኪዳን የለውም፡፡ "Dear brother may God blessing be upon you

  ReplyDelete
 10. መልካም ለመሆኑ የሚታደሰው ማነው? ለምን አሰፈለገ? አባተቶቻችን የሚያረጅ የሚያልቅ ስር የሌለው በየጊዜው የሚታደስ እምነት ከሆነ ያስቀመጡል እነርሱ ምኑን አድሰው አስረከቡን?አሮጌውስ ምን ነበር?የመጀመሪያው ፈጣሪ ማን ነበረ አሁንስ ማን አደረጋችሁት?የተት ነበረ አሁንስ ከዙፋኑ ለቆ የት ሄደ? እባክዎ ሙሉ መልስ ይስጡኝ

  ReplyDelete
 11. tehadso=Protestantism. I think the only difference is that the tehadso community wants to use the Orthodox Tewahedo Church as their platform. My proposal is that no one should stand against them as long as they stay outside of the Orthodox church. However, they work day and night to take over the church.

  ReplyDelete
 12. Hiruy, God bless!!

  ReplyDelete
 13. "ኦሪትና ነቢያት የተናገሩትን ልፈጽም መጣሁ እንጂ ልሽር አልመጣሁም" ባለው መሠረት መቅደሷን በደብተራ ኦሪት ቅርጽ ሠርታ ምስጢራትን ስታከናውንበት ኑራለች፡፡ መስዋዕተ ኦሪትን በሐዲስ በክርስቶስ ክቡር ሥጋና ቅዱስ ደም ትሠዋለች ታሳርጋለች በጥምቀት የሥላሴ ልጅነት ታድላለች በቅዳሴ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ብላ የቅድስት ሥላሴን አንድነት ሦስትነት ታውጃለች በአበው ማኅበረ ነቢያት ፤ በማኅበረ ሐዋርያት ፤ በማኅበረ ጻድቃን ሰማዕታት ፤ በማኅበረ ደናግል ወመነኮሳት በአጠቃላይ በማኅበረ ቅዱሳን ሰማያውያን እግዚአብሔር የገለጸውን ኃይሉን የገባውን ኪዳኑን አምልታ አስፍታ ታጎላለች፡፡ “ክብር ለሚገባው ክብር ስጡ መታዘዝ ለሚገባው ታዘዙ” በተባለው አምላካዊ ቃል መታሰቢያቸውን ሳታጠፋ ታከብራቸዋለች እንጂ በዘመናቸው ሰይጣነ ቅናት አድሮባቸው እንደገፏቸውና እንደተጣሏቸው ሰዎች በመዋዕለ እረፍታቸው አትገፋቸውም፡፡ በአጸደ ሥጋ ከዚህ ዓለም ስላለፉ አይረቡም አይጠቅሙም አትልም፡፡ የሚጠሏቸውን በምድር ከበረከቱ በሰማይ ከመንግሥቱ እንደሚለያቸው አጠንክራ ታስተምራለች፡፡....
  ሰይጣንና የግብር ልጆቹ ቢወዱም ቢጠሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት

  ReplyDelete
 14. bertu bertu bertu tehadiso letesadabiwochm yasifeligal!!!

  ReplyDelete
 15. i can conclude that protestants do not worship the true Jesus

  ReplyDelete
 16. Let me tell you in simple language: Thadso (reform) and protest have two different meaning. I won’t going to elaborate about protest, but let me say some about Thadso (reform)— first let me tell u that God Apostles didn’t create a religion, religion were created after them by protesting each other. Orthodox and catholic were the first denominations their after thousands emerging just by protesting their own denomination. When we come to in our point, thados is not protesting it is all about reform, which means demanding the church to go the right direction, even in my age I am looking a lot wrong doing in our church. I am afraid to say that but I will see – Lord Jesus is not presence in our church but presence in those Orthodox Christians truly believing and accepts that He is the Son of Lord, and he is Lord. It is all about learning the bible that thadso are moving and fire up!
  Please open your heart to Lord Jesus; he loves you the best evidence was his payment for your sin in behalf of you at Keranio in the cross. Read the bible, start from John.
  God bless you

  ReplyDelete
 17. ስህተታችሁ እንደ ምድር አሰዋ በዛ

  ReplyDelete
 18. በእውኑ ቤተክርስትያናችን ወንጌልን አትሰብክም?በስራተ ቅዳሴ ከመዝሙረ ዳዊት ይሰበካል ወንጌል ይነበባል ከሃዋርያት ስራ ይነበባል ከ ጳውሎስ መልእክት ይነበባል ከሌሎች መልእክት
  ይነበባል በመጨረሻ ስብከት ይሰበካል።ይህ አምልኮ በተለይ በጾም ወራት በየእለቱ ይከናወናል።ብየእለቱ ደግሞ አውደምህረት ላይ በሰርክ ጉባኤ ስብከት ይሰጣል።በየሰንበት ትምህርት ቤቱ ወንጌል ይሰበካል።በየጊዜው ጉባኤ ይዘጋጃል።መዘርዘሩ ይከብዳል።እና አሁንም ይህች ቤተክርስትያን ወንጌል አትሰብክም ሲባል አያሳፍርም።ታድያ ሰባኪዎቹ በሳምንት አንዴ አዳራሽ ውስጥ ጩኸው የሚለያዩት ነው የሚሰብኩት?

  ReplyDelete
 19. tehadiso is the new version of protestant why you are lying on my beloved religion true orthodox tewahido orthodox ???????????????????
  tehadiso==protestant

  ReplyDelete