Sunday, June 29, 2014

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቀጳጳስ በብፁዕ አቡነ ዳንኤል ላይ የገዳሙ መነኮሳት አድመው በረሃብ እየቀጧቸው መሆኑ ተሰማ

Read in PDF

በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ በሆኑት በብፁዕ አቡነ ዳንኤል ላይ አባ ገብረ ወልድ በተባሉ መነኩሴ አሳዳሚነት ሊቀጳጳሱ ላይ ልዩ ልዩ የአድማ እርምጃዎች እየተወሰዱ መሆናቸውንና ሊቀጳጳሱ ላይ አደጋዎች መደቀናቸውን ከስፍራው የደረሰን ዜና አመለከተ፡፡ ብፁዕነታቸው የሲኖዶስን ስብሰባ ለመካፈል ከመጡ ወዲህ ተመልሰው ቢመጡ አናስገባቸውም በሚል የተጀመረው አድማ ምግብ እንዳይቀርብላቸው፣ ሾፌራቸውም መኪናቸውን እንዳያንቀሳቅስ እስከ ማሳደም የደረሰ አሳዛኝ እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑን ምንጮቻችን የገለጹ ሲሆን ይህም ድርጊት በአንዳንድ ክፉ ቀን ግብጻውያን መነኮሳት ኢትዮጵያውያን መነኮሳት በበሽታና በረሃብ እንዲያልቁ ለማድረግ በራቸውን ዘግተውባቸው እርዳታ ሳያገኙ እንዲሞቱና ገዳማቶቻችን ያለ ሰው እንዲቀሩ ለማድረግ ከሚጠቀሙባቸው በጭካኔ የተሞሉ ስልቶች ጋር ተመሳሳይነት አለው፡፡ ከዚህ እርምጃ በስተጀርባ የማን እጅ እንዳለ ለጊዜው የታወቀ ነገር ግን የለም፡፡
ብፁዕ አቡነ ዳንኤል የስኳር በሽተኛ ከመሆናቸው አንጻር በረሃብ እንዲቀጡ አድማ መመታቱ እጅግ አሳዛኝ ተግባር መሆኑ እየተነገረ ሲሆን፣ በብፁዕነታቸው በኩል እስካሁን ነገሩን በትዕግስት ማሳለፋቸው የቤተክርስቲያን ስም በዚህ መንገድ እንዳይነሣ ከማሰብ እንደሆነ የተናገሩት ምንጮች፣ ብፁዕነታቸው የዲፕሎማት ፓስፖርት ያላቸውና እንደዲፕሎማት ስለሚታዩ ለሚመለከተው አካል አቤት ቢሉ ይህን ባደረጉት መነኮሳት ላይ ሕጋዊ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ስለጉዳዩ የሚያውቁ ይናገራሉ፡፡
በአባ ገብረወልድ የተመራው የአድማ ማኅበር እንዲህ ለማድረግ ያነሳሳው ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር ባይኖርም ብፁዕነታቸው የኢየሩሳሌም ሊቀጳጳስ ሆነው ከተሾሙ በኋላ በዚህ ወቅት ሊሆን የማይችለውን በጎልጎታ ምዕራፍ ስምንት የተባለውን ቦታ ለቤተክርስቲያናችን በመግዛት ትልቅ ስራ መስራታቸው ይነገራል፡፡ የመነኮሳቱ ቅናትና አድማ የተነሳው ከዚህ መልካም ስራ ሳይሆን እንደማይቀር አንዳንዶች ይገምታሉ፡፡ የመነኮሳቱ ማኅበርም አይዟችሁ ያላቸው አካል ሳይኖር አይቀርም የሚል ግምት አለ፡፡

23 comments:

 1. አባ ሰላማዎች ወደ አንድ ወገን ያደላ ዘገባ ባታቀርቡ ጥሩ ነው። ሌላው አቡነ ዳንኤልን ለረዥም ጊዜ አሜሪካን ሀገር እንደማውቃቸው ምንም ከሰው ጋር የሚያኖር ጠባይ የሌላቸው አስቸጋሪ ሰው ሲሆኑ፣ የገዳሙ መነኮሳትም ጋር ችግር የለም ለማለት አልደፍርም ግን ከሊቀ ጳጳሱ በላይ የከፋ አይሆንም ገዙ የተባለውም መሬት እርሳቸው ከመምጣታቸው በፊት ብዙ የተደከመበት መሆኑን ለማሳወቅ እወዳለሁ ።

  ReplyDelete
 2. አይ አቡነ ዳንኤል በሌላ ሊቀ ጳጳስ ሀገረ ስብከት ጣልቃ ገብተው ስልጣነ ክህነቱ ለተያዘ ደብተራ በወገንተኝነት ሽፋን በመስጠት በቤተ ክርስቲያን ስርዓት ላይ የፈጸሙት ስህተት ውሎ ሳያድር በረሀብ ተቀጡ የእግዚአብሔር ፍርድ ይገርማል፣ በሉ አለአግባብ የሚያጠራቅሙትን የአሜሪካን ሀገር ጡረታዎትን መመንዘር ይጀምሩ ለመቼ ሊሆኖት ነው? ነው ወይስ እርስዎም እንደነ አቡነ ……… የሚያሳድጉዋቸው አሜሪካን እያሉ ያፈሯቸው (የእህትና የወንድም ልጆች) አሉዎት እንዴ ዛሬ ማን ይታመናል።

  ReplyDelete
 3. Aba Selamoch ye semau geta yerdachu betam betam yasazenal Aba Gebrewelde megabew new endihum Aba Tesfa yetebale Lemadena ale kezehe befitem endehu sibetebit yenore leba ye emahoye Sebele Bal yenbere sew new andega asadame. lenegeru tefatu ezehu bet christian new. beye sowest amte bekyru noro yhe balhone neber. Ambasader Helawe mesmat alebachew. Aba Daniel le Israel mengest kalasaweku adega alew.

  ReplyDelete
 4. እናንተ መናፍቃን ሙታን ፕሮቴስታንቶች ምን አገባችሁ ቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ?

  ReplyDelete
 5. ከዘህ ጉዳይ በስተ ጀርባ ረጅሙ የማሕበረ ቅዱሳን እጅና ምላስ አለበት ምንም መደበቅ አያስፈልግም። እነሆ ሰሞኑን እንደ ምንሰማዉ ማህበረ ቅዱስ ሊቃነ ጳጳሳቱን በህክምና በርዳታ ስም ወደ አሜሪካ በማምጣት እርሱ በተቆጣጠራባቸው ቤተ ከርስቲያን እያሽከረከራቸው ገንዘብ እንድለምኑለት በማድረግ ላይ ይገኛል ። ይህ ክፉ ማህበር በኢትዮጵያ መንገዱ ስዘጋበት በአሜሪካ ቀዳዳ እያበጀ ነው። እነዝህ ወደ አሜርካ በህክምናና በእርዳታ ሰበብ የመጡት ሊቃነ ጳጳሳት እጅ እግራቸው በየስፍራው ከመሰንዘራቸው በፊት ጥንቃቀ ብያደርጉ መልካም እንደሆነ እንመክራቸዋለን። ካለ በለዚያ በማስረጃ የተደገፈ ጉዳቸውን በአደባባይ እንድ ወጣ ይደረጋል ።ጠንቀቅ መልካም ነዉ። ቅዱስ መጽሐፉም እንደ እባብ ብልህ ሁን ይላልና ። አሜሪካን ያሉት የማቅ ካህናትና አባላቱ በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ ሩጫ በማድረግ ላይ ናቸው። የገንዘብ ከረጥታቸው እጅግ ስለጎደለቸው። በዙ መዘምራን የአስራት ገንዘባቸው ለማቅ መስጠት በማቆማቸውና ከእርሱ እስራት ራሳቸው በመፊታት ነጻነታቸው በማወጃቸው ነው።

  ReplyDelete
 6. የማቅ ከፉ ሥራ መቸውም አይቆም። እርሱን ለማይደግፉት ጳጳሳት ለማጥፋት ከቶ አያቀላፋም። የእርሱ ደጋፊዎች ለሆኑት ጳጳሳት በህክምና በርዳታ ምክንያት በማድርግ ወደ አሜሪካ በማስመጣት በኢ/ ስኖዶስና አገረ ስብከት በማይመሩ አብያተ ክርስቲያናት በድብቅ እየላክ ገንዘብ እንድለምኑለት በማድረግ ላይ ይገኛል ። እነዚህ ሊቃነ ጳጳሳት የምመክራቸው ሰዉ ምነዉ ጠፋ? በአሜሪካ ያሉት የማቅ ካህናት በየስፊራው እየበሩ ናቸው። ህዝበ ከርስቲያኑ ሳይነቃባቸው የገንዘብ ልመናውን ለማፋጠን ሌት ከቀን እየተጉ ናቸው። እስካሁን ጳጳሳቱ እየተራመዱ ያሉት ማቅ አባለት ብቻ ወደ ምጋብዙአቸው ቤተ ከርስቲያን ብቻ ነው። በአሜሪካ ያለው የተዋህዶ ህዝብ ገንዘቡን በቀላሉ አያስረክብም ። ሁል ግዜ ሰዉን ማሞኘት አይቻል። ሁሉም ነቅቷዋል። ኤረ ይበቃል አባቶች..........ማቅ የትም አያደርሳችሁ። ምናልባት እንደ አቡነ ጳዉሎስ ወደ መቃብር ካልሆነ.....

  ReplyDelete
 7. Hi maru kebede do you know the sign of eye ? Do not use it it is devil sign of course you comment is from devil sprit

  ReplyDelete
 8. እኔን ግን በጣም ግርም የሚለኝ እነዚሁ ለማቅም ይሁን ለራሳቸው ገንዘብ ለመለመን በየቤተክርስቲያኑ ቲኬት ተቆርጦላቸው፣ አበል ታስቦላቸው፣ ልዩ አቀባበል እየተደረገላቸው የሚሄዱ " ሊቃነ ጳጳሳት" የፓትርያርኩን ስም፣ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ስም በፀሎት ሳያነሱ የራሳቸውን ስም ብቻ እያስጠሩ ቡራኬ ሰጠን ህዝቡን መከርን፣ አረጋጋን እያሉ የሚሰሩት ድራማ ነው።
  እስኪ እንደው እነርሱ ያላከበሩትን ስርአት ማን እንዲያከብረው ነው መድረክ ላይ ቆመው የሚቀላምዱት ምዕመናኑ እንደሚታዘባቸው ዘንግተውት ይሆን እስኪ በሁለት የተለያዩ ስቴቶች የተፈፀመውን የስርዓት መጣስ እንመልከት ያው " በሊቃነ ጳጳሳቱ" ማለቴ ነው።
  1ኛው/ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ወደ ሚኒሶታ " ደብረ ሰላም መድኃኔ ዓለም" ሰኔ ሚካኤልን አስታከው ለገንዘብ ልመና መጡ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ለአገልግሎትም ሆነ ለቡራኬ ከመሄዳቸው በፊት በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በቦታው ያለዉ ችግር፣ እናገለግላለን የሚሉት ካህናት ሥልጣነ ክህነታቸው የተያዘባቸው መሆኑ፣ የእርሳቸው እዚያ ቦታ መገኘት ህገ ወጥ የሆነውን "ገለልተኝነትን" ማጠንከር እንደሆነ፣ በስልክ በተደጋጋሚ እና ለታሪክም በመረጃ እንዲቀመጥ በደብዳቤ እንዲያውቁት ተደረገ እርሳቸው ግን "የፓትርያርክም፣ የሊቀ ጳጳስም ስም አይጠራ፣ የተወገዘ ካህንም ይኑር አይመለከተኝም እኔ የመጣሁት ገንዘብ ለመለመን ነው" በሚል ከአንድ አንጋፋ ሊቀ ጳጳስ በማይጠበቅ አሳዛኝ እና አሳፋሪ ድርጊት ከተወገዙ ካህናት ጋር ቀድሰው፣ባርከው፣ገንዘብ ለምነው ሄዱ።
  2ኛው/ በላስቬጋስ እንዲሁ የሰኔ ሚካኤልን በዓል ለማክበር በሚል ሽፋን ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ለልመና ፕሮግራም ተይዞላቸው ወደዚያው አመሩ ይሄን ደግሞ ለየት የሚያደርገው በኢትዮጵያ ሲኖዶስ እንመራለን የፓትርያርኩን ስም እንጠራለን የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ ስም አንጠራም አንቀበላቸውም የሚባልበት የአዲስ ሥርዓት ባለቤቶች መሆናቸው ነው "ከስጋው ጾመኛ ነኝ ከመረቁ አውጡልኝ" አይነት ነገር ብቻ ያም ሆነ ይህ ጳጳሱ ተገኙ ሁሉንም ሳያውቁ እንበል በቤተክርስቲያኒቷ ሥርዓት መሰረት የፓትርያርኩንም፣ የሊቀ ጳጳሱንም ስም በፀሎት መጥራት ጀመሩ በቦታው ያሉ የማቅ ደቀ መዛሙርት ለሊቀ ጳጳሱ መመሪያ ሰጡ/ ልብ በሉ ወደ ላይ/ "የመጡበት የገንዘብ ልመና እንዳይደናቀፍ የሊቀ ጳጳሱን ስም አይጥሩ ተባሉ" አይ ፂም አልባው አባ ገብረ………! ግን እስከ መቼ ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓት አፈንግጠው??? ወደ ሀሣቤ ልመለስ በዚህ ዙሪያ በተደገፈ መረጃ ወደፊት እመጣበታለሁ።
  ታዲያ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሄኖክም ልክ እንደ አቡነ አትናቴዎስ የሊቀ ጳጳሱ ስም ቢጠራ ባይጠራ እኔ የመጣሁት ገንዘብ ለመለመን ብለው መጥራት ያቆማሉ በዚሁ ሁኔታ ቀድሰው፣አቁርበው፣ገንዘባቸውን ለምነው ተመለሱ።
  ልብ በሉ ቤተ ክርስቲያን ተዘጋ በሚል ሽፋን የቤተ ክርስቲያኒቷን ሥርዓት እየናዱ የሚሰበሰበው ገንዘብ እውነት ለቤተ ክርስቲያን ይሆን? ደግሞስ ሊቃነ ጳጳሳቱ ፓትርያርኩንና፣ ሊቃነ ጳጳሳቱን እንደ ቤተ ክርስቲያኒቷ ሥርዓት ቢያከብሩ ክብሩ የራሳቸው መሆኑን ሳይገነዘቡት ቀርተው ይሆን ወይስ ገንዘብ ልብን ይሰውራል እንደተባለው ይሆን አይ የዘመናችን ጳጳሳት…………… ግን አንድ ነገር ልበል ገንዘቡን የሚሰጣችሁ ምዕመን በሚሰጠው ገንዘብ መጠን እየታዘባችሁ እና ለቤተ ክርስቲያኒቷ እያዘነላት መሆኑን የሚያስተውል ልቡና ይስጣችሁ።

  ReplyDelete
 9. ኤረ ምን አይነት ጉድ ነው።ጳጳሳቱ እስከ መቼ ነው በማቅ እስራት የምገዙት ? ለማይጠፋ ምግብ ብሰሩ ይሻላቸዋል። የነ አባ ገ/ኪዳን የላስቨጋሱ በሰሜን አሜርካ የማህበረ ቅዱሳኑ የስብከት ክፍል ሀላፍው ካህን የትም አያደርሳችሁን ። እበርሴ እኮ የሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከት አንቀበልም በማለት አዋጅ ያወጁ ቤተ ከርስቲያን ኛቸው ፡፤ ምነው እነ አቡነ ፊልጶስ ከእነርሱ ደጅ አለመለየታቸው ከእነርሱ ጋር መተባበራቸው አሳዛኝ ነው። ስኖዶሱንም ሀበረ ስብከቱን የማይቀበል የማቅ ቤተ ከርስቲያን ነው የላስቨጋስ ቅ/ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ። እናዝናለን አቡነ ፊልጶስ.............

  ReplyDelete
 10. one important message I want to share to all is that we can talk to God directly without the help of Abunes, priests, and all the jazz they preach to drag you to their churches and drain money out of you. If you have noticed, their lip service that the kingdom of god is earned by becoming a member of their church and attending their service is all to brainwash you with their philosophy of fear, and that you will be doomed to hell if you do not give all what you have. Have you wondered why our church officials do not teach or speak of charity work to the needy, to the seek to the mentally sick?? No!! Do you know why? they are too busy giving you lip service. My advice to you is to stop them in their tracks, and say when are you going to practice what you preach??

  ReplyDelete
 11. Thanks to all of our brothers and sisters in the name of our Holy God. amen.እንነዚህ የማቅ ሊቃነ ጳጳሳትን ወደ አማሪካ ለገንዘብ ልማና የተለቀቁትን በአሜሪካ ያሉት የየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳስ ማስቆም አለባቸው። እነ አባ ሔኖክ ሊቀ ጳጳስ የማቅ መልእክተኞች ስለሆኑ የኢ/ቅዱስ ስኖዶስ በአስቸኳ ወደ ቀደመው ስራቸው እንድመለሱ ማድረግ አለበት ። ዓላማቸ የኢት ቅዱስ ስኖዶስ የማይወክል ስለሆነ። ማቅ የጀመረው የእጅ አዙር እየተጠቀመባቸው ነው። እኛ የኢትዩጵአ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች በማቅ ጳጳሳት ላይ ቅረታ አለን ።

  ReplyDelete
 12. ማኅበራችን የአገልግሎት ማኅበር ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር አስፈላጊነቱን አምኖ ፤ የአገልግሎት መስመሩንም በደንብና መመሪያ አስምሮ በመፍቀድ ያቋቋመውም ከዚህ አገልጋይነቱ የተነሳ ነው፡፡ በመኾኑም ማኅበሩ በይፋ ከተመሰረተበት 1984 ዓ.ም ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኗን በአባላቱ ሞያ ፤ ጉልበትና ገንዘብ እያገለገለ ለዛሬ ደርሷል፡፡ ሕዝቡን ለአገልግሎት በሚጠራና በሚያተጋ አምላክ ፈቃድም ወደፊት አገልግሎቱን እንደሚቀጥል ያምናል፡፡

  ሐዋርያዊት በኾነችው ቤተ ክርስቲያን ሥር ለአገልግሎት የቆመው ማኅበራችን ፤ አገልግሎት የጋራና በምትገለገለው ቤተ ክርስቲያን ዕቅፍ ሥር ያሉ ሁሉ ሊተባበሩት የሚገባ መኾኑን በአፅንዖት ያምናል፡፡ ይህንንም ከምስረታው ጀምሮ በተግባር ሲገልጥ ቆይቷል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ዕቅፍ ውስጥ በመኾኑ ከሚመስሉትና ዓላማውን ከሚጋሩት ማኅበራትና አካላት ጋር ልዩ ልዩ ቅንጅቶችን በመፍጠር እያገለገለ ከዛሬ ደርሷል፡፡ ወደፊትም ይቀጥላል፡፡


  የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ ዛሬም እንደ ትላንቱ በሀገር ብሎም በዓለም ደረጃ ካለባት መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሓላፊነት አንጻር ቤተክርስቲያን ብዙ አገልጋዮችን ትፈልጋለች፡፡ አገልግሎት ለቤተክርስቲያን ጥቅም የጋራ በጋራ በመኾኑ አንጻርም ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ሊሰጥ የሚገባው አገልግሎት በአገልጋዮች አንድነት ላይ የተመሠረተ ፤ በጋራ መክረውና አቅደው ሊሰጡት የሚገባ መኾን ይገባዋል፡፡

  ከዚህ አንጻር ዛሬ በእግዚአብሔር ፍቃድ በልዩ ልዩ ኅብረት በቤተ ክርስቲያኗ ቅጽር የተሰበሰቡ ማኅበራት በቂ ናቸው ብሎ ባያምንም ያሉት ጥቃቅን ልዩነታቸውን ወደ ጎን በመተው ለመንፈሳዊ አገልግሎታቸው መቀራረብ ፤ መመካከርና አብሮ አቅዶ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው በእጅጉ ያምናል፡፡ ማኅበራቱ አብረው ሲያገለግሉ የተበታተነው ኃይል ይሰበሰባል፡፡ በዚህ የጋራ ኃይልም በቁጥርም በይዘትም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና እየተወሳሰበ የመጣው የቤተክርስቲያናችን ችግር በአግባቡ መፍትሔ እያገኝ ይሄዳል፡፡ የተጣመመው ይቃናል ፤ የመረረው ይጣፍጣል ፤ የራቀውም ይቀርባል፡፡

  በዚህ አጋጣሚ በአምላክ ፍቃድ 22 የአገልግሎት ዓመታትን የዘለቀው ማኅበራችን አሁንም አንዷን ቤተ ክርስቲያን በቅንነት ለማገልገል ያለው ዝግጁነትና ጉጉት ለመግለጽ ይወዳል፡፡ብእሴ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት እንዳለው (መዝ 133 ፤ 1) መንፈሳዊ ቅንአትን ስንቅ አድርገው በልዩ ልዩ መንገድ ለማገልገል የተሰበሰቡ ማኅበራት እንዲገናኙ ፤ እንዲወያዩ ፤ እንዲያቅዱና እንዲሰሩ ለማድረግ የቻለውን ሁሉ ለማድረግ የበለጠ ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ የማኅበራችን ጥሪ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ተግባራዊ ይኾን ዘንድ ለመተባበር ለሚመጣ ማንኛውም አካልም በሩ ክፍት መኾኑን ይገልጻል፡፡

  የቤተ ክርስቲያን ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ የአገልጋዮቿን ኅብረት አይፈልግም፡፡ በመኾኑም ምንም እንኳን ማኅበራችን ከላይኛው እስከ ታችኛው መዋቅሩ ሁሉ ሲተጋበት የቆየ ቢኾንም ፤ የበለጠ አንቀናጅ ፤ አብረንም እንሥራ ስንል ጥንተ ጠላት ልዩ ልዩ እንቅፋቶችን በመንገዳችን ላይ እንደሚያስቀምጥ ያለፉት ልምዶቻችን ሁሉ ይነግሩናል፡፡ የቤተክርስቲያን አገልግሎት ትጋትን ፤ ፍቅርን ፤ አንድነትን ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም አገልግሎት ከትጋት ፤ ትጋትን ከፍቅር ፤ ፍቅርን ከአንድነት ጋር አስተባብረን በመያዝ ማገልገል ይገባናል፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ አንድነቱን ስለማይፈልግ ፈተና ያበዛል፡፡ ፍቅርንና ትጋትን ለማሳጣት ይንቀሳቀሳል፡፡ ነገር ግን ይህንኑ የዲያቢሎስ የተንኮል ሴራ ጠብቀን እስከተንቀሳቀስን ድረስ ፤ ከማንም በላይ ደግሞ ከላይ ጀምሮ በተዋረድ ያሉ የአበው ምክርና መመሪያ እንዲሁም ጸሎት አጋዥ አድርገን እስከተጓዝን ድረስ እንቅፋቱን ሁሉ አልፈን ሐዋርያት የሰበሰቧትን የሰበኳትን እናት ቤተ ክርስቲያንን እናገለግላለን፡፡ ለዚህም አበው ዛሬም መመሪያ ምክራቸውን እንዳይርቀን ፤ ጸሎታቸውም እንዳይለየን እንጠይቃለን፡፡V

  ReplyDelete
  Replies
  1. what are you talking about? you are talking nonsense to us, why do you not start doing something about those who are need, after all you are in the buisness of good deed. what service have you given for 22 years?you are losing the youth of your people because of your lie and deceit. Young Ethiopians do not believe you as you are not doing anything worthy to society..

   Delete
  2. when you talk about the service that the church is giving in the community, I am puzzled and appauled that members believe that you are actually doing something to help the community. please let me know one good deed you have done, such deeds as feeding the hungry, fundraising to the needy, going door to door in your community to see how people are coping. where is your outrage on how many young people are on the street(Ethiopians) As priests, monks and bishops, your concern, drive and ambition should be looking after human beings who need salvation. You are too drawn to monetary gain and worldly comfort, bigger church and talking about rank in file of church politics. when are you going to change the doctrine of lying to people. Time has changed, you should inspire to change. I am not suggesting to switch the religion, or the readings of the bible, however your laws and your doctrines are absolutely outdated. You are preaching the same doctrine that was used in the Mesafent zemen!!

   Delete
 13. af lela tegibar lela....lemehonu mahiberu beandinet yaminal? fikir yemilewunis betegibar yikebelal? yih hulu liyunet..bitibit..gichit...sim atifinet..kesashinet sew erisberisu endayitemamen..ageligayochn keabatoch..abatochn keabatoch ga yemiagachew man honena?lelaw kerito besew guday sint zemen tsebesebachihu?sewn lematikat sint gize teselefachihu? bemeseretu hawariat yesebesebuat betekiristian hizbun bemagachet yemitimera alineberechim.simlela gibir lela....behawariat sim atinegidu....hawariat wengelin sebeku enji wenjeln alasayum....hawaria hono silekiristos yalisebekena yalitsafe andm yelem...yikir yibelachihu...yeteyazachihubetin silematawuku lib yisitachihu!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ለነገሩ ስለ ማኀበረቅዱሳንም ሆነ ስለቤተክርስቲያን ጉዳይ መናገር የሚቻለዉ አይነ ለቦናዉ ለበራለት ምድራዊ ክብር እና ዝና ሳይሆን ሰማያዊ ሃገርን ለሚናፍቅ ነው እናም ማኀበራችን ማኀበረ ቅዱሳን የአገልግሎት ማኀበር ነው በመሆኑም ብዙዎችን የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ከእሳት እየነጠቀ ለሰማያዊ ሰርግ ሙሽራ አድርጎአቸዋል፤ብዙ ገዳማትን አድባራትን ሊቃዉንተ ቤተክርስቲያንን በራሱ በጎ ፈቃድ ገንዘቡን ጉልበቱን እዉቀቱን ተጠቅሞ ደግፏል ከመዉደቅ ከመፍገምገም ተድጓል፡፡ቤተክርስቲያንም በመናፍቃን እና በአላዊያን ተጽዕኖ አገልግሎቷ ሳይደበዝዝ አሁን ካለችበት እንድትደርስ የልጅነት ድርሻውን አበርከቷል፡፡እና ጥቅሙ የተነካበት ዲያብሎስ እና አጋሮቹ ስለማኀበረ ቅዱሳን ብዙ ቢያወሩ ቢያስወሩ አይደንቅም!!!

   Delete
 14. Yemenafekan sera alubalta new enanete menafekan ye beg lemdachihun aweleku be Aba Selama semei meserat akumu.

  ReplyDelete
 15. ለነገሩ ስለ ማኀበረቅዱሳንም ሆነ ስለቤተክርስቲያን ጉዳይ መናገር ሚቻለዉ አይነ ለቦናዉ ለበራለት ምድራዊ ክብር እና ዝና ሳይሆን ሰማያዊ ሃገርን ለሚናፍቅ ነው እናም ማኀበራችን ማኀበረ ቅዱሳን አገልግሎት ማኀበር ነው በመሆኑም ብዙዎችን የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ከእሳት እየነጠቀ ለሰማያዊ ሰርግ ሙሽራ አድርጎአቸዋል፤ብዙ ገዳማትን አድባራትን ሊቃዉንተ ቤተክርስቲያንን በራሱ በጎ ፈቃድ ገንዘቡን ጉልበቱን እዉቀቱን ተጠቅሞ ደግፏል ከመዉደቅ ከመፍገምገም ተድጓል፡፡ቤተክርስቲያንም በመናፍቃን እና በአላዊያን ተጽዕኖ አገልግሎቷ ሳይደበዝዝ አሁን ካለችበት እንድትደርስ የልጅነት ድርሻውን አበርከቷል፡፡እና ጥቅሙ የተነካበት ዲያብሎስ እና አጋሮቹ ስለማኀበረ ቅዱሳን ብዙ ቢያወሩ ቢያስወሩ አይደንቅም!!!

  ReplyDelete
 16. hulachenenem egeziyabeher yiqer yibelen....

  ReplyDelete
 17. Begbi gubae make yastemarew wengel sayhon deserve sedebna teaches sihone yazgjachewom Lagrange esat enjji lemengeste semayat enslaving mk erasu
  yawekewal.yebetekrstiyan telatoch wenbede
  enesanet mahber.betam trkit. Yewahan besteker.

  ReplyDelete
 18. ዓለም የውሸት ዱለት እየተበላ ይኖርባታል።
  ዱለቱ ሲያከትም ሕይወት ያከትማል።አንድ ሰው ላንድ ነገር ተቆርቋሪ መስሎ የሰውን ስም በሐሰት ማጥፋት ከባድ ኃጢአት ነው የቁም ፍዳም አይቀርለትም (ያልካደ ከምኩራብ ተሰደደ)ብዙ ሐሰት
  አንድ እውነትን ሊጋርድ ይችላል ጊዜውን ጠቆ ግን ግርዶሹን ነፋስ ይገረስሰዋል ከዚያም ዋሾና ውሸት
  እንዳልነበሩ ይሆናሉ። አዬ ኢየሩሳሌም ምነውኮ???

  ReplyDelete
 19. Mk egziabher yatfachu .yehe hulu brain wash yadergachut swe yrmikerakrrew l mk enjji lekdist b krstiyan alemohonu berasu min eyeserachu endalhone yasredal.

  ReplyDelete