Wednesday, June 4, 2014

ሃያ አራቱ ግዴታዎችና ድንጋጌዎች የአባ እስጢፋ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መነሣት ለማቅ ራስ ምታት የሆኑ ወቅታዊ ጉዳዮች(ክፍል ሁለት)

Read in PDF

የዘንድሮው የግንቦት ሲኖዶስ ስብሰባ ሃያ አራቱ ግዴታዎችና ድንጋጌዎችን መሠረት አድርገው በተነሡ ጉዳዮችና በሌሎችም አጀንዳዎች ሲነጋገር ሰንብቶና ውሳኔዎችን አሳልፎ መጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ ሃያ አራቱን ግዴታዎችና ድንጋጌዎች አስመልክቶ ከስብሰባው ሰዓት ውጪ በማኅበረ ቅዱሳን ሰዎች “እንዲህ በሉ፣ እንዲህ ተከራከሩ…” እየተባሉ እንደተሞሉ ወደስብሰባው አዳራሽ በመግባት ውሳኔ የተሰጠባቸውን አጀንዳዎች ጭምር እየቀሰቀሱ ወደኋላ ሲመልሱ የነበሩ አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ጳጳሳት ነበሩ፡፡ ሆኖም በፓትርያርኩ በሳል የስብሰባ አመራር ችሎታ ወደኋላ ሊመለሱ የታሰቡ አጀንዳዎች ማቅ እንደጠበቀው ወደኋላ ሳይመለሱ፣ ጳጳሳቱ የተሞሉትን ካፈሰሱ በኋላ “ይህን ጉዳይ ስለጨረስን ወደኋላ አንመለስም፤ ወደሌላው ጉዳይ እንለፍ” እያሉ አቅጣጫ በማስያዝ የመሪነት ሚናቸውን እንደተጫወቱ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡ 


በማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ጳጳሳት በኩል “የማቅን መተዳደሪያ ደንብ እንደገና እንየው” ከሚለው “ኢህአዴግ ነገ ይጠፋል፤ ማኅበረ ቅዱሳን ግን ኗሪ ነውና ማኅበራችንን ማንም እንዲነካብን አንፈልግም” እስከሚለው ድረስ ለማቅ ጥብቅና የቆሙ ጳጳሳት ነበሩ፡፡ በተለይ አባ ቄርሎስ፣ አባ ጢሞቴዎስና አባ ሉቃስ ግንባር ቀደሞቹ ናቸው፡፡ በተለይ አባ ሉቃስ ለማቅ ተከራካሪ ሆነው የቀረቡት ባለባቸው ነውር ማቅ አስፈራርቷቸው ነው የሚሉት ምንጮች፣ ከዚህ ቀደም ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳዳሪዎች፣ ጸሃፊዎችና ሌሎችም አገልጋዮች በተዘጋጀ ሥልጠና ላይ አባ እስጢፋ እያስፋፉት ባለው ሙስና ቅሬታቸውን ያሰሙትና “ለእስራኤል ውድቀት ምክንያቶቹ ካህናት ነበሩ ዛሬም ለቤተክርስቲያናችን ውድቀት ተጠያቂዎቹ እኛው ካህናት ነን” ሲሉ ካህናቱ ቆመው ያጨበጨቡላቸው አባ ሉቃስ ዛሬ የተንሸራተቱት ማቅ ይዤብዎታለሁ በሚለው ገበናቸው ተደራድሯቸው ነው ይላሉ፡፡
ይሁን እንጂ ይህን የተቃወሙ ጳጳሳት በፊናቸው ከቤተክርስቲያን ይልቅ ለማቅ ጥብቅና የቆሙትን ጳጳሳት ሐሳብ በመቃወም “ስለአንድ የጽዋ ማኅበር ይህን ያህል ጊዜ ሰጥተን ልንወያይ አይገባም፤ የወሰነውን ነገር እንደገና ወደኋላ ተመልሰን ማየት የለብንም” በሚል ተቃውሟቸውን ማሰማታቸው ታውቋል፡፡ የስብሰባው መሪ ፓትርያርኩም ከአጀንዳ የሚወጡትን ወደአጀንዳ እንዲመለሱ በማድረግ፣ ከዚህ ቀደም በተወሰኑ ውሳኔዎች ላይ ወደኋላ እንመለስ ባዮቹንም ወደሌላው አጀንዳ በማሸጋገር ብቃት ያለው አመራር የሰጡ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡
    

በክፍል አንድ ጽሑፋችን እንደተመለከትነው ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር የተያያዘው ሁለተኛው ለማቅ ራስ ምታት የሆነው ጉዳይ የአባ እስጢፋ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመነሳታቸው ነው፡፡ ፓትርያርኩ አባ እስጢፋ ሊታዘዟቸው እንዳልቻሉና የአንድ ጽዋ ማኅበር አገልጋይ እንደሆኑ ለሲኖዶስ አባላት የገለጹ ሲሆን ይህ የሆነው በጠዋቱ የስብሰባ ጊዜ ነው፡፡ ከማቅ ተሞልተው የገቡት አባ ኤጲፋንዮስ ግን ከሰዓት በኋላ ለአባ እስጢፋ ለመከራከርና ፓትርያርኩን ለመውቀስ ሙከራ አድርገው የነበረ ሲሆን፣ “ለእርስዎ ከእርሳቸው የበለጠ ወዳጅ ማን ይገኛልና ነው አልታዘዝ አሉኝ የሚሉት” ማለታቸው ታውቋል፡፡ በዚህ ንግግራቸውም ጉዳዩን ከቤተክርስቲያን ይልቅ ግለሰባዊ አድርገው ማቅረባቸው፣ በተደረገው የፓትርያርክ ምርጫ ላይ እርስዎ እንዲመረጡ የረዱዎት እርሳቸው ናቸው ለማለት እንደሆነ ተንታኞች ተናግረዋል፡፡ ፓትርያርኩም አተኩረው ካዩአቸው በኋላ “ወደ ሌላው አጀንዳ” እንለፍ በማለት ስብሰባውን ወደ መስመሩ መልሰዉታል ተብሏል፡፡ በቅርቡ በአባ እስጢፋኖስ ላይ ተቃውሞ ሲበረታ አባ ኤጲፋንዮስ “አባ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያኑን አበላሹት የልጆች ቤት አደረጉት” ብለው እንደነበር ምንጮቻችን ያስታውሳሉ፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን ተሞልተው ሲናገሩ ግን ለአባ እስጢፋኖስ ተቆርቋሪ መስለው ነው የቀረቡት፡፡   

ከሃያ አራቱ ድንጋጌዎችና ግዴታዎች በተጨማሪ የአባ እስጢፋኖስ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መነሣት ለማቅ ትልቅ ራስ ምታት ሆኗል፡፡ ማቅ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባረቀቀው ህግ በኩል ያሰበውን ሳያሳካ በአባ እስጢፋ መነሣት ከልቡ ያዘነ ሲሆን፣ ለመነሳታቸውም ውሃ የማይቋጥርና ከሁኔታው ጋር የማይያያዝ ምክንያት በመደርደር አባ እስጢፋን ጀግናው አድርጎ ለማቅረብ ሞክሯል፡፡ “በአዲስ አበባ /ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በመኾን ለመላው አህጉረ ስብከት በአርኣያነት የሚጠቀሰውን የመዋቅር የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ጥናት በቅድመ ግንባር የመሩ” ሲል ሐራ አንቆለጳጵሷቸዋል፡፡  

የማቅ አባት የሆኑት አባ እስጢፋ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመነሣታቸው ዜና ከተሰማ በኋላ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚገኙና ብዙ ያለቀሱባቸውና የታገሏቸው ካህናት ደስታቸውን እየገለጹ መሆናቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡ በግንቦት 20 ዋዜማ መነሳታቸው ደግሞ ልጆቻቸው (የማቅ መሥራቾች የደርግ ርዝራዦች ናቸውና) ከወረዱበት ዕለት ጋር ባለው ግጥምጥሞሽ አወራረዳቸውን ልዩ እንደሚያደርገው በቀልድ መልክ እየተነጋገሩበት ይገኛሉ፡፡ በአባ እስጢፋ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መነሣት ዙሪያ ማቅ እያስወራ ያለው ነገር ግን ከመግለጫውም ከእውነታውም ጋር ይጋጫል፡፡

መግለጫው “በሦስት አህጉረ ስብከት የብፁዓን አባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዝውውር ማድረግ በማስፈለጉ … ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳትነታቸው ተነሥተው በሀገረ ስብከታቸው በጅማ እንዲኖሩ ተወስኗል፡፡” ነው የሚለው፡፡ ሐራ ግን “ለመሥራት ተቸግሬአለኹ ያሉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከፓትርያርኩ ረዳት ሓላፊነት ለመልቀቅ ጠይቀዋል” ሲል ነው ያወራው፡፡ ታዲያ የቱን እንመን? መግለጫውን ወይስ ሐራን፡፡ የለቀቁት ጠይቀው ከሆነ ማቅና ሚዲያው ሐራ ለምን ተቆጡ? “በሀገረ ስብከታቸው በጅማ እንዲኖሩ ተወስኗል” የሚለው ሐረግስ ምን አንድምታ ይኖረው ይሆን? ከዚህ ይልቅ የለቀቁት በፓትርያርኩ በኩልም ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ የአንድ ጽዋ ማኅበር አገልጋይ ስለሆኑና ግፊቱ በተለይ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስተዳዳሪዎችና ካህናት ስለበዛባቸውና በውርደት ከመልቀቃቸው በፊት ሁኔታው ራሳቸው በቃኝ እንዲሉ ስላስገደዳቸው ቢባል ያስኬዳል፡፡ እውነትም ነው፡፡

 

ከዚህ ቀደም እንደ ዘገብነው አባ እስጢፋ ያለባቸውን ነውር ሸፍኖ ስለያዘላቸው ከልብ ሊታዘዙት ቃል የገቡለትን ማቅን ለማስደሰት አዲስ አበባ ሀገረ ሰብከትን ወለል አድርገው ነው የከፈቱለት፡፡ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ቢሮ ከመስጠት ለሀገረ ስብከቱ ካህናት መተዳደሪያ ደንብ እንዲያረቅና በሥርዋጽም ወደሥልጣን ቶሎ እንዲመጣ መደላድሉን እስከማመቻቸት የደረሰ ውለታ ውለውለታል፡፡ ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ እንደሚባለው በረቂቅ መተዳደሪያ ደንቡ ውስጥ ማቅ ለራሱ አመቺ ያለውን ቦታ ቢያመቻችም አስተዳዳሪዎችና ሌሎችም ካህናት በአንድ ድምፅ የተቃውሞ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በማሰማታቸው ረቂቅ ደንቡም እንደታሰበው ሳይሆን ቀርቷል፡፡

 

እንደ እውነቱ ከሆነ የአዲስ አበባን ሀገረ ስብከት ብልሹ አሠራር ለማስተካከል ባደረጉት ጥረት እስካሁን ድረስ ወደር ያልተገኘለትን ተግባራዊ ሥራ የሰሩት ንቡረ እድ ገብረማርያም ናቸው፡፡ አባ እስጢፋ ግን ለእርሳቸው ሥራ ዕውቅና ከመስጠት ይልቅ የእርሳቸውን አሠራር በማፍረስ የሙስናውን መንገድ ይበልጥ ውስብስብ ነው ያደረጉት፡፡ ንቡረ እድ ገብረ ማርያም ሥራ አስኪያጅ ሆነው በሠሩባቸው ጊዜያት የሙስና በሮችን በመዝጋት ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበትን፣ ለስርቆትም የማይመች አሠራር ዘርግተው ስለነበር አስተማማኝ ውጤት ታይቶ ነበር፡፡ ይህ ያልተመቻቸው ሙሰኞች ግን በመልካም ሁኔታ እየሰሩ የነበሩትን ቆራጥ የሥራ ሰው ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት ወደ ቅርስ መምሪያ ሓላፊነት አዛወሯቸው፡፡ ማቅም ቢሆን ለዚያ መልካም ጅምር ዕውቅና ከመስጠትና በዚያው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከማበረታታት ይልቅ ከአባ እስጢፋ ጋር በመመሳጠር ለሌላ ዝርፊያ የሚመችና ከዘረፋው ተካፋይ ለመሆን የሚያስችለውን አሰራር ነው ሲያመቻች የቆየው፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ አባ እስጢፋ የፈጸሙትንና እየፈጸሙ የነበረውን ግልጽ ዝርፊያና ሙስና አንድም ቀን ሲኮንን አለመሰማቱ ነው፡፡

 

በአባ እስጢፋ ዘመን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና የሙስና በር ሆኖ የቆየው ሠራተኛን ያለ አንዳች ምክንያት ከደብር ወደብር የማዘዋወር ሥራ ነው፡፡ ዝውውሩ ገቢ ከሌለው ደብር ጉቦ እየሰጡ ገቢ ወዳለውና ወደሚበላበት ደብር የሚደረግ ዝውውር ነው፡፡ በዚህ የዝውውር ሂደት ብዙዎች ሰለባ ሲሆኑ ጉቦ መስጠት የቻሉ ደግሞ ዝርፊያ ወደሚገኝበት ደብር በመዛወር ለጥቂት ጊዜ የሚቆየውንና እንደ ጥላ የሚያልፈውን ምድራዊ ኑሯቸውን እያደላደሉ ይገኛሉ፡፡ እዚህ ላይ ሠራተኛን ማዛወር እንዳይኖር ከፓትርያርኩ ጥብቅ መመሪያ የተላለፈ ቢሆንም እግዱ ሳይነሣ ግን ዝውውሩ ቀጥሏል፡፡ የጥቅምትና የግንቦት ሲኖዶስ ስብሰባ ሲመጣ ልክ እንደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር መስኮት ተከፍቶ ገበያው እንደሚደራ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ጳጳሳቱ በስብሰባ ስለሚጠመዱ ሥራ አስኪያጆች ከሌሎች የጥቅም ተጋሪዎቻቸው ጋር በመሆን ዝውውሩን ያጧጥፉታል፡፡ ካህናትና ዲያቆናትን ማዛወር የወረዳ ቤተ ክህነት ሥልጣን ሆኖ ሳለ በአሁኑ ወቅት የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ሊቀ አእላፍ በላይ መኮንን ሠራተኞችን በማዛወሩ ሥራ እንደገፉበት እየተነገረ ነው፡፡ ሥራ አስኪያጁ ያለ አንዳች በቂ ምክንያት ሰራተኞችን እያዘዋወሩ ያሉት በጉቦ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ከቀድሞ ጀምሮ ሥራ አስኪያጆች ቢለዋወጡም ጉቦ በማቀባበል የሚታወቀው የደብረ አሚን ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን ጸሀፊ የሆነው ላእከ ሰላም ሽታው እና በአሁኑ ወቀት ደግሞ ሃይሉ ጉተታ እስካሁን ድረስ በጉቦ አቀባባይነት ስማቸው ይጠራል፡፡

 

የመንግሥት ምክር ቤት አባል በመሆናቸው ላይ ሥራ አስኪያጅነት ተደርቦላቸው የሚገኙት የአዲስ አበባ ሥራ አስኪያጅ ሊቀ አእላፍ በላይ ዘመናዊ ትምህርት የተማሩ በመሆናቸው ለውጥ ያመጣሉ ተብሎ ቢጠበቅም የሙስናውን መንገድ እየገፉበት መሆናቸው ከሰሞኑ ከተደረጉት ህገወጥ የሰራተኛ ዝውውሮች መገንዘብ ይቻላል ይላሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ፡፡ አቤቱታና ቅሬታ ያለበትን ሠራተኛ ጥያቄ ባለመቀበል በቢሮአቸው ባለማስተናገድ፣ ነገር ግን በመንግሥት ባለሥልጣናት በኩል የሚመጡትን ግን በመቀበልና ቦታ በመስጠት ስማቸው በስፋት እየተነሣ ነው፡፡

 

ሊቀ አእላፍ በላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ እንዲሆኑ የተደረገው አባ እስጢፋ ከማቅ ጋር ተመካክረው እንደሆነና ዓላማቸውም እርሳቸውን አቅርቦ ስለ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ መረጃ ለመሰብሰብ እንደሆነ ግምታቸውን የሚያስቀምጡት ምንጮች፣ ይህም የሆነው በአቡነ ሳዊሮስና በሥራ አስኪያጁ መካከል ያለውን ቅርበት ስለሚያውቁ ነው ይላሉ፡፡ ሙስናን መዋጋት ፓትርያርክ እንደተሾሙ ይፋ ያደረጉት ዋና ራእያቸው በመሆኑ፣  ዋደኋላ ሲጎትቱት የነበሩትን ማቅንና አባ እስጢፋን ከመንገዳቸው ገለል በማድረግ እንደ ንቡረ እድ ገብረ ማርያም ያሉትን ቆራጥ የሥራ ሰዎች በተገቢው ስፍራቸው በመመደብ ራእያቸውን ከግቡ ማድረስ እንዳለባቸው የብዙዎች ተስፋ ነው፡፡

 

ሌላው በስብሰባው ላይ የተነሣው አጀንዳ የኤጲስ ቆጶሳትን ሹመት የተመለከተው ጉዳይ ሲሆን፣ ለኤጲስ ቆጶስነት ይመረጣሉ የተባሉ እንደ ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል ያሉ አባቶች እንዳይመረጡ ለማድረግ ብዙ ሤራ ሲሸረብ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚህ ሤራ በስተጀርባ ማኅበረ ቅዱሳን ያለ ሲሆን፣ አባ ሳሙኤልም አባ ሠረቀ እንዳይመረጡ ከፍተኛ ሥራ ውስጥ ውስጡን ሲሠሩ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ በዕውቀት ስለሚበልጧቸው ከቀድሞ ጀምሮ ካላቸው ጭፍን ጥላቻ እንደሚመነጭ ይነገራል፡፡ ማቅ በአንድ በኩል ከፍተኛ ገንዘብ ለአባ ሳሙኤል እንመድብና በአስመራጭ ኮሚቴ ሰብሳቢነታቸው አባ ሠረቀ ብርሃን እንዳይመረጡ እናድርግ ሲሉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ አባ ሳሙኤልን በያዝንባቸው ነውር እናስፈራራቸውና እንዳይመረጡ እናስደርግ ያሉ አሉ ተብሏል፡፡ ያሸነፈው ሐሳብ ግን ገንዘብ መመደብ አያስፈልገንም፤ አባ ሳሙኤል የአባ ሠረቀ ጠላት ስለሆኑ አያስመርጧቸውም የሚለው ነው፡፡ በማቅ በኩል እንደተገመተውም አባ ሳሙኤል በአባ ሠረቀ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ የከፈቱ ሲሆን “አባ ሠረቀን ጳጳስ ማድረግ ማለት የአቡነ መርሐን ዓይነት ሰው ሲኖዶስ ውስጥ መጨመር ነው” ሲሉ መናገራቸውን ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በዚህም አነጋገራቸውም የአባ ሠረቀን ምሁርነትና ጠንካራ ሰብእና ሳይወዱ በግድ ገልጸዋል፡፡

 

በአባ ሠረቀ ላይ ከከፈቱት ዘመቻ ባሻገር የአካባቢያቸውንና በውጭ የሚገኙ ዳጎስ ያለ ገንዘብ ሊከፍሉ የሚችሉትን የአካባቢያቸው ተወላጆች የሆኑና የእርሳቸውን የበላይነት የሚቀበሉ መነኮሳትን መልምለዋል ተብሏል፡፡ በዚህም አባ ጳውሎስ ይታዘዙልኛል ብለው እርሳቸውን ጳጳስ ካደረጉ በኋላ አባ ሳሙኤል ያለ ችሎታቸውና ሰብእናቸው የአባ ጳውሎስ ዋና ተቀናቃኝ ሆነው ለመቅረብ እንደሞከሩት፣ የዘሩትን በጊዜው የሚያጭዱባቸውን ምልምሎቻቸውን የወንዜ ልጅ በሚለውና በገንዘብ ስሌት መልምለዋል ተብሏል፡፡ እንደ አባ ሳሙኤል ሁሉ አንዳንድ ጳጳሳትም የሥጋ ዘመዶቻቸውን ጭምር ለጵጵስና መልምለው አስቀምጠዋል ተብሏል፡፡ አባ ሳሙኤል ከዚህ ቀደምም ስንት ሊቃውንት በቆሎ ት/ቤት ብዙ ደክመው ነገር ግን ሥራ አጥተው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በር ላይ በደጅ ጥናት ሲጉላሉ ከውጭ መጣ የተባለን እንደእርሳቸው ያለ ጨዋ መነኩሴን ግን በቀጥታ በሚፈልገው ቦታ ላይ ይመድቡት ነበር፡፡ እንዲህ የማድረጋቸው ምስጢርም ጉቦ በዶላር መቀበላቸው ነው፡፡ በት/ቤት የደከሙት በዕውቀታቸው ለቤተክርስቲያን ከሚያበረክቱት አገልግሎትና አስተዋፅኦ በቀር ለአባ ሳሙኤል የሚተርፋቸው ቤሳቤስቲ የለም፡፡ ቤተክርስቲያን እንዲህ የወንበዶች ዋሻ ሆና የምትቀጥለው ግን እስከመቼ ይሆን?

 


20 comments:

 1. እናንተ የእፉኝት ልጆች ክቡራን መናፍቃን ሆይ!!!June 5, 2014 at 12:56 AM

  እናንተ የእፉኝት ልጆች ክቡራን መናፍቃን ሆይ!!!
  አባ ሰላማ ወይም ፍሬ ምናጦስ ከሳቴ ብርሃን የተባሉ ት አባት የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ናቸው::
  ነገር ግን እናንተ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቀንደኛ ጠላቶች ናችሁ:: እናንተስ በሀይማኖትም በስራትም ከእሳቸው ፈፅሞ ትለያላችሁ ሁልጊዜ ለጥፋት ትፋጠናላችሁና::
  የቤተክርስቲያን አባል ሳትሆኑ የማታምኑበትን በቅዱስ አባታችን ስም (አባ ሰላማ) ብሎግ በመክፈት ስለ ቤተክርስቲያን መርዝ የተቀለቀለበት ማር ለየዋሆች ታሰራጫላችሁ::
  እናንተ ተኩላዎች!
  አባ ሰላማ በተባለዉ የበግ ለምድ በመደበቅ የክህደት መርዛችሁን ትረጫላችሁ::
  ነገር ግን በዚህ ክፉ ስራችሁ በእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን በኢት ህግ መሰረትም ከተጠያቂነት አታመልጡም::
  ይህ ሁሉ ድክመት ህዝበ ክርስቲያኑን ለማማ ሳሳቴት ነው!!
  በእዉነትእግዚአብሔር አቅማችሁን ያሳውቃችሁ:: አሜን::

  ReplyDelete
 2. In the name of the Father , the Son and Holy Sprit One GOD Men

  Please have fear of GOD! Do not lie! Your difference with Mahibre Kidusan is your objective to change the Dogma of EOTC to that of the Protestants. When the protestant opened "zemtcha Philipos" to stir European like reformation in four direction you have ben fighting as fifth columnist within. Hence, you and your friend have been excommunicated from EOTC by the Holy Synod so that you can join whatever denomination that suits. However, you continued to stir conflict by spreading rumors between Mk and Government, Between MK and the Archbishops and between the Archbishops and the Patriarch. There can be in any meeting difference of opinion and decision will be reached as per regulation of Holy Synod. While Mahibre Kidusan shall work as an arm of EOTC, it shall ask permission for rendering assistance the different Department . With this regard it can be give guidance by the respective authority. But it shall not be chained not to preach the Gospel or to prevent capacity building in EOTC. EOTC shall exploit the potential of its children like its sister the Coptic Orthodox Church and modernize while keeping its Dogma and Cannon.

  In Ethiopia, the Government is composed of people of different religious beliefs, therefore it is not surprising if some might be against MK because of it advocates EOTC is the true apostolic church. This is apologetic view is not bad as long as we live in harmony with our compatriots of other religion if you stop your sinister clandestine activity in our Church from which you are excommunicated..

  I propose all ture believers of EOTC not be provoked by Abba Selma and some other websites that pose as supporter of MK and stop from spreading rumors and pray sothat God give rational judgment for the Patriarch, Holy Synod and the Government in relation to EOTC.

  Amen!

  ReplyDelete
 3. LE YAKOBE , Endi yelale :-- Yematsenanachew Ena ngen , Ena ngen yememotewen sew ende sarem yemetewelgewen yesewen lej tefera zend ante mane neh ? ESAYAS 51:12 Leju ngen !

  ReplyDelete
 4. ወይ ጉድ እግዚአ ......................... ቤተ ክህነት

  እኔ ግን በላየ ላይ ንጉሴን ሹማያለሁ

  ReplyDelete
 5. why do you lie , because you are obedient to your father, devil. why do you talk about the 24 guidlines and directions which have not been accepted and approved by the holy synod. shame!!!!!! do you boost as if they are approved ????????let me tell you (menafik), they are not acceptable and get practicality and mk will not be abide by even if the directions are approved. look the past many directions by the dark team( like mk is urged to apologize the church for it calls 'abenet memhran' without permission, mk is obliged to utilize betkihnet 'modelamodel' ...etc) where is the practicality ???? let the dogs cry and the camels go proud,

  ReplyDelete
 6. You are not correct and what you told us is out off reality. Please in the name of God don't propagate evil things like this. We all now this blog is anti - EOTC.

  ReplyDelete
 7. betam rikashoch nachihu, betam tera. rubbish!!!!!!

  ReplyDelete
 8. Please call him Hagi Mutefa nt Estefa.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ha hahhahhaha h ah ha hah a

   Delete
  2. man this is good. u r reporting nicely

   Delete
 9. Bete kehedet yewenbedwoch washa.fired yemigemedelbet bot.every thing on this blog Is true mk knows its true .

  ReplyDelete
 10. Mk mother killler

  ReplyDelete
 11. ANTE MUTICHA;
  YEHASET/YEMENAFIK- LIJ

  ReplyDelete
 12. One of mk fundmetalist priest who has lived in Ga Erget kale girl friend will be speak out in public regarding to his multi sexual life.

  ReplyDelete
 13. kiss belay lebentu addis abeba hageresebket sayehon yejemerew pawelos colege yetemaren qeleb bemezerefu yetebarer ,.1997 oromia atari comshion bemeret oromia zuria meret sheto yetebarere addis abeba eskebarer zerfiawen yeqetel ,,,,,,,,,,,

  ReplyDelete
 14. Leb yalew leb yibel! Abet fetari! Yihchi betekerestiyan wedeyet yihon eyehedech yalechiw? lenegeru MK yabekalet yemeslal, eskene kotetu ketekebere degmo betekerstiyan telemelemalech!!

  ReplyDelete
 15. እውነት ላይ ያልተመሰረተ ከነስሙ ትርጉም ተቃዋሚ የሆነ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ሰዎችን በስብከት ማሳመን ባልቻለ ጊዜ የእውነተኛይቱን ቤተክረስቲያን ደካማ አገልጋዮችን በመጠቀም ገንዘብ በመስጠት በሙስና ዘመኑ ባፈራው የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ መሳርያ ኢነተርኔት በመጠቀም እዚህ ብሎግ ውስጥ በተከላችው ሰራተኞቹ አማካኝነት ያለማቃረጥ የውሸት ጩኸት በመጮህና በመለፍለፍ በጎ የሰራ እያስመሰለ ቤተክርስትያንን ለማፍረስ ይተጋል። ይህ ብሎግ ለዚህ አላማ ከቆሙት የፕሮቴስታንት መሳርያዎች አንዱ ነው። ይህን ብሎግ የምታዩ ሁሉ በአባ ሰላማ ስም የፕሮቴስታንት ብሎግ እያያችሁ መሆኑን አትርሱት። የዚህ ብሎገ ብሎም የዚህ ጽሁፍ አቅራቢዎች ውሸታሞች መሆናችሁንና አላማችሁን ስለምናውቅ የቤተክርሰትያን ልጆች ሁሉ ይህ ያላችሁት ሁሉ ውሸትና ተራ አሉባልታ መሆኑን እንነግራችዋለን። ብትሰሙና ብትታረሙ መልካመ ነው ባተሰሙ ግን የናነተን ብሎግ ማየት እናቆምና እውነተኛ መረጃ ወዳለበት እንሄዳን።

  ReplyDelete
 16. What about you?????big lier

  ReplyDelete
 17. መንፈሳዊ ማህበር እንደሞሆኑ መጠን መከራና ተግዳሮት ሲደርሰበት መንፈሳዊ ምላሽ ነዉ መስጠት ያለበት ሃዋርያቶች መከራና ስደት ሲደርስባቸዉ መንፈሳዊ ምላሽ ነዉ የሰጡት እሱም ፀሎትና በክርስቶስ ስም መከራዉን መቀበል ነበር ማህበረ ቅዱሳን ግን አላማዉ መንፈሳዊ ያለመሆኑ የሚታወቀዉ መንግስት ክስ ሲያቀርብበት ወደ ግል ሚዲያ በመሄድ ማስፈራራትና አመፅን መጥራትና እንዲሁም ባለዉ መዋቅርና የአባላት ብዛት መታበይን እንደ ቁልፍ ስትራቴጂ ነዉ የሚከተለዉ ስለዚህ ማህበረ ቅዱሳን ሳይሆን መባል ያለበት ማሀበረ ፖሎቲከኞች ነዉ ፡፡፡፡፡ አሁን የተሸፈነበት እርቃን እየወጣ ነዉ አባቱ ዲያብሎስ ሊያድነዉ አይችልም

  ReplyDelete
 18. Aba Estefa picture looks like g angster

  ReplyDelete