Monday, June 9, 2014

ይህ ነው ተሐድሶ!

Read in PDF

(ተሐድሶ፣ ሰኔ 2 ቀን 2006 ዓ.ም.)ጥያቄ ፩፡ ተሐድሶ፣ ተሐድሶ ሲባል እሰማለሁ፤ አንዳንዶች ደግሞ ተሐድሶ እውነተኛውን ትምህርት ለመለወጥ የመጣ አዲስ ትምህርት ነው ይላሉ፤ በእርግጥ ተሐድሶ አዲስ የመጣ እንግዳ ትምህርት ነውን? ለመሆኑ የሚታደሰው ምኑ ነው?
መልስ፡
፩) ተሐድሶ እንግዳ ትምህርት ሳይሆን የእግዚአብሔር አሳብና የማይቋረጥ መንፈሳዊ ሂደት ነው፡፡

ተሐድሶን እንደመናፍቅነት የሚያዩ ራሳቸውም ቢሆኑ ዘወትር በሕይወታቸው ተሐድሶ የመሚከናወንባቸው እንጂ በአሳብ እንደሚቃወሙት ሁሉ በተግባር በሕይወታቸው እንዳይፈጸም ሊያደርጉት የሚችል ነገር አይደለም፡፡ ልዩነቱ እኛ ተሐድሶ በእግዚአብሔር ጸጋ የሚከናወን ፈቃደ እግዚአብሔር መሆኑን ስናምን ተቃዋሚዎቹ ደግሞ በመሰላቸው መንገድ የእግዚአብሔርን አሳብ ሲቃወሙ እግዚአብሔር ግን በቸርነቱ ባለጸጋ ስለሆነ የተሐድሶ ተግባሩን ሳያቋርጥ የሚፈጽም መሆኑ ነው፡፡ 
ለምሳሌ ለ1600 ዓመታት በግብፅ አስተዳደር ሥር የነበረችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ፈቃድ ስለሆነ ራሷን ማስተዳደር መቻልዋ የቤተ ክርስቲያኗ ተሐድሶ መሆኑን ማንም ይረዳዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ራሷን ማስተዳደር መቻልዋ እንግዳና እግዚአብሔር የማይወድደው ነገር ሳይሆን ቀድሞም እግዚአብሔር የሰጣትን መብት በተንኮል ግብፃውያን ከልክለዋት ሲኖሩ እግዚአብሔር ያለው (የፈቀደው ነገር) በሰው ተንኮል ከመፈጸም የማይከለከል በመሆኑ ቤተ ክርስቲያኗ እግዚአብሔር የወደደውን ነገር ማድረግ መቻልዋ ተሐድሶዋ ነው፡፡ ተንኮለኞች ፈቃደ እግዚአብሔርን አፈረሳችሁ፤ የሃይማኖት ሥርዐትን ለወጣችሁ ብለው ኢትዮጵያውያንን ቢያወግዙ እንኳን ሐሰተኞች እነርሱ እንጂ ኢትዮጵያውያን ሊሆኑ አይችሉም፡፡ 

በተሐድሶ ጥያቄም ነገሩ ተመሳሳይ ነው፤ “ወደ እውነተኛው እምነት እንመለስ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ የታሪክ ሂደት ውስጥ  በእውነተኛው ትምህርት ላይ የተጨመሩ አዳዲስና የሐሰት ትምህርቶች በእግዚአብሔር ቃል እየተመዘኑ ይወገዱ”  ስላልን ሐሰተኞች ብንባል፣ ትምህርታችንም አዲስ የመጣ እንግዳ ትምህርት ቢባል አይገርመንም፡፡ እኛ እያልን ያለነው ሐዋርያት የሰበኩት የጸጋ ወንጌል ያለምንም መሻቃቀጥ ይሰበክ፤ ሰዎችን ሁሉ ሊያድን የተገለጠው የእግዚአብሔር ጸጋ በሰው ሠራሽ ሥርዐቶችና ተጥባበ-ነገር አይሸፋፈን ነው፡፡ ይህ የምንፈልገው ተሐድሶ ነው፡፡  
) ስለወጋችሁ የእግዚአብሔርን ቃል አትሻሩ
እኛ እያልን ያለነው “ስለወጋችሁ የእግዚአብሔርን ቃል ሻራችሁ” (ማቴ.156) ሲል ጌታችን ለፈሪሳውያን እንዳስጠነቀቃቸው ስለወግና ሥርዐታችን ስንል (በወግና በሥርዐት ስም) የእግዚአብሔርን አሳብ ቸል እያልን ስለሆነና ይህም እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ተግባር ስለመሆኑ እርግጠኞች ስለሆንን ወደ እግዚአብሔር ቃል እንመለስ ነው፡፡ ይህ የምንፈልገው ተሐድሶ ነው፡፡ ይህን አሳብ መናፍቅነት ብሎ ክፉ ስም በማውጣት ማጥላላት የሰይጣን እንጂ ክርስቲያን ነን የሚሉ ሰዎች ተግባር ሊሆን አይችልም፡፡ ሰዎች ይህን አሳብ መቃወማቸው ራሱ ኀጢአት ስለሆነ ንስሓ ሊገቡበት ይገባል እንላለን፡፡
፫) የቆምንለት ተሐድሶ በሦስት ዋና ዋና ነጥቦች ላይ ያተኮረ  ነው፡፡
 “ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ” የቆችለት ተሐድሶ በሚከተሉት ሦስት ነጥቦች ላይ ያተኩራል፡፡ እነዚህም (1) የትምህርተ ሃይማኖት ተሐድሶ (2) የክርስቲያናዊ ሕይወት ተሐድሶ እና (3) የሥርዐትና የአስተዳደር ተሐድሶ ናቸው፡፡
የትምህርተ ሃይማኖት ተሐድሶ ማለት እግዚአብሔር በነቢያት ባናገረው ትንቢት ፣ በክርስቶስ ልደት፣ ትምህርት (ወንጌል) ፣ ሞት፣ ትንሣኤ፣ ዕርገት፣ ዳግም ምጽአትና ማዳን፣ በሐዋርያት ስብከት፣ በሦስቱ ዓለም አቀፍ ጉባኤያት (የኒቂያ ጉባኤ 325 ዓ/ም፣ የቁስጥንጥንያ ጉባኤ 381 ዓ/ም፣ የኤፌሶን ጉባኤ 431 ዓ/ም) በተወሰነው እምነት ላይ የተጨመረና የጸናውን ትምህርተ ሃይማኖት እንዲሁም  እውነተኛውን የመዳን መንገድ የሚቃወም ማንኛውንም ትምህርት በእግዚአብሔር ቃል መሠረትነት እያጠኑ መቃወምና እውነተኛው ትምህርት እንዲሰበክና እንዲጸና ማደረግ ነው፡፡ ይህን እኛ ተሐድሶ እንለዋለን፤ ለተቃዋሚዎቻችን ይህ መናፍቅነት ከሆነባቸው እኛ ክርስትናቸውን እንጠራጠራለን፡፡
ቀሪዎችን ሁለት ነጥቦች ለሌላ ጊዜ እናቆያቸወና እስኪ ለዛሬ በትምህርተ ሃይማኖት ሊደረጉ ከሚገባቸው ተሐድሶዎች አንዱን እንመልከት፡፡ የክርስትና እምነት የመገለጥ እምነት ነው፤ ይህም ማለት በእግዚአብሔር አስተርእዮ ላይ የተመሠረተ እምነት ነው ማለት ነው፡፡ (ስለ አስተርእዮ ዝርዝር ትምህርት በሌላ ጊዜ ይዘን እንቀርባለን) የእግዚአብሔር ፍጹም አስተርእዮም ክርስቶስ ነው፤ የእግዚአብሔር ቃል  ሰው ሆኖ በሥጋ ሲገለጥ የእግዚአብሔር ፍጹም አስተርእዮ ተሰጠ፡፡ የዚህ አስተርእዮ እውነተኛ ትምህርት ተመዝግቦ የሚገኘው ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡  ከመጽሐፍ ቅዱስ የተሻለ ይህን ትምህርት መዝግቦ የያዘ የእውነት መጽሐፍ የለም፡፡
የእግዚአብሔርን አውነት የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ይህን መጽሐፍ ገልጦ ማነበብና በመልእክቱ መታደስ (መለወጥ) ነው፡፡ ሰዎች ኀጢአተኞች ስለሆንን የመጽሐፉን አሳብ የሚቃረን ሕይወት እንኖራለን፤ ቅዱስ መጽሐፍን በማነበብና በመማር ወደ እውነት መመለሳችን አንዱ ተሐድሶ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች የሚያደርጉት ነገር ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ ነው፤ መጽሐፉ እንዳይነበብ ለመጽሐፍ ቅዱስ የተመደበውን የትምህርትና የንባብ ጊዜ በገድላትና በድርሳናት በማባከን የሰውን የተሐድሶና የመዳን ጊዜ ያዘገያሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያተኮሩ ስብከቶችን የተሐድሶ መናፍቃን ትምህርቶች ናቸው በማለት ሰዎች ወደ ክርስቶስ መንግሥት እንዳይገቡ ይከለክላሉ፡፡
፬) ተሐድሶ የሚጀምረው ለመጽሐፍ ቅዱስ ያለንን አመለካከት ከማስተካከል ነው፤
እንግዲህ ተሐድሶ የሚጀምረው ለመጽሐፍ ቅዱስ ያለንን አመለካከት ከማስተካከል ነው፤ ይህም የትምህርተ ሃይማኖት ተሐድሶ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ከገድልና ከድርሳን ጋር እኩል የሚያከብርና የሚያነበብ፣ የሃይማኖት ጥያቄ ሲነሣ በመጽሐፍ ቅዱስ ከመዳኘት ይልቅ በድርሳናትና በገድላት የተሰበኩ ተረቶችን በመደርደር እውነትን የሚገዳደሩ ሁሉ የሃይማኖት ችግር አለባቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በትምህርታቸው ውስጥ ይህን አይነት አመለካከት እስካስተናገዱ ድረስ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር መጣላታቸው አይቀርም፡፡
ይህን ስንል ገድላትና ድርሳናት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ይጣላሉ ወይ? የሚል ጥያቄ ሊነሣ ይችላል፤ መልሱ አዎን ነው፡፡ አንድ ምሳሌ እናቅርብና ነገሩን ግልጥ እንድርግ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “መዳን በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን፣ ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና” (የሐዋ.412) የሚል እውነት  ተጽፎ ይገኛል፡፡ በድርሳናትና በገድላት ደግሞ የሚያድኑ ኀይላት ተብለው የሚሰበኩ ቅዱሳን ብዙ ናቸው፤ እነርሱ ዛሬ ተገኝተው ቢዳኙን “እንኳስ ሌላ ልናድን እኛም ራሳችንን ማዳን አቅቶን ያዳነን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሆነ መላ ዘመናችን እርሱን ስንሰብክ ኖረን አልፈናል፤ ይህን በእኛ ስም የምትሰብኩትን የሐሰት ወንጌል በፍጹም አናውቀውም፤ አዳኞች ተብለን በጌታችን ስም እንጠራ ዘንድ ከእኛ ይራቅ” ብለው ባባረሩን ነበር፡፡ ምን ይሆናል ልናገኛቸው አልቻልንምና ተቃዋሚዎቻችን በማይገኙና ተጠይቀው እውነት/ሐሰት ብለው ክርክሩን ሊበይኑ በማይችሉ አካላት ስም የጌታን ወንጌል ይቃወማሉ፡፡ ቃሉ “መዳን በሌላ በማንም የለም” ካለ እነርሱ ከጌታ ቃል በላይ ሊሆኑ ስለማይችሉ እንኳንስ በእነርሱ ስም የሚሰብኩ ሐሰተኞችን ራሳቸውን ቅዱሳንን አግኝተናቸው የሐሰት (እንግዳ) ወንጌል ከሰበኩልን እንዳንቀበላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዝን ተቀብለናልና ወደኋላ የምንልበት ምክንያት የለም፡፡     
የምንናፍቀው ተሐድሶ ሩቅና እንግዳ ነገር ሳይሆን ቀላል ነው፤ ትምህርታችን ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊና በመጽሐፍ ቅዱስ ስልጣን ሥር የሚዳኝ ይሁን የሚለው ትምህርት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ በልዩ ልዩ ቋንቋዎች ሊተረጎም፤ ሊታተምና ሊሰራጭ እንዲሁም ሁሉም ሊያነብበውና ሊመራበት ይገባል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ቋንቋ ብቻ ሊነበብ፣ በተወሰኑ ሰዎች ብቻ ሊታወቅ የሚገባው መጽሐፍ አይደልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለሕዝቡ የላከው የመዳን ቃል ስለሆነ ለሁሉም ሰው ሊዳረስ ይገባል፡፡ የተሐድሶ ዋና ትምህርት ይህ ነው፡፡ ይህን ማድረግ ከተቻለ ተሐድሶ በመሥመሩ ላይ የሚሽከረከር ባቡር ሆነ ማለት ነው፡፡ ይህን ማድረግ አለመቻል እግዚአብሔር በምድሪቱ ላይ እንዲመጣ የሚፈልገውን ተሐድሶ ማዘግየት ነው፡፡
) መጽሐፍ ቅዱስን ለሕዝቡ በቋንቋው መተርጎምና ማቅረብ የተሐድሶ ሥራ ነው፡፡
አማኑኤል ካንት የተባለው ታዋቂ የነገረ መለኮት ምሁር እንዲህ ብሏል “መጽሐፍ ቅዱስ  በቋንቋው ስለተተረጎመለትና ስለታተመለት የሰው ዘር በሙሉ እድለኛ ነው፡፡” የእኛም አባባል ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ በቋንቋው የታተመለት ሕዝብ እድለኛ ነው ባዮች ነን፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፤ የቆምንለት አንዱ የተሐድሶ አላማ መጽሐፍ ቅዱስ ለሰዎች ሁሉ በቋንቋቸው ተተርጉሞ ይቅረብ የሚለው ነው፡፡  አማኑኤል ካንት ይህን በተናገረበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ በላቲን ቋንቋ ካልሆነ በቀር በሌሎች የአውሮጳ ቋንቋዎች ተጽፎ አይገኝም ነበር፤ የላቲን ቋንቋ ደግሞ ሕዝቡ የማይጠቀምበት የቤተ ክርስቲያን ቋንቋ ብቻ ነበር፤ ልክ ግእዝ በአሁኑ ወቅት እንዳለበት ሁኔታ ማለት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የእኛ አዋቂዎች እግዚአብሔርና አዳም የተነጋገሩበት ቋንቋ ግእዝ ነበረ በሚል ተረት እየተመሩ በግእዝ ካልተጸለየ፣ በግእዝ ካልተቀደሰ እግዚአብሔር እንደማይሰማ የሚያስቡትን ያህል ያን ጊዜም ካህናቱ የላቲን ቋንቋን ከእግዚአብሔር በልዩ መንገድ የተሰጠ በማስመሰል ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በቋንቋቸው እንዳያነብቡ  ያደርጉ ነበር፡፡ አማኑኤል ካንት ግን እውነቱ ሕዝቡ መጽሐፍ ቅዱስን በቋንቋው ያነብበው ዘንድ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፤ ይህ የሆነለት ሕዘብ ደግሞ እድለኛ ነው እያለ ይሰብክ ነበር፡፡
በአገራችን ታሪክ ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስ ሕዝቡ በሚሰማው ቋንቋ  ተተርጉሞ እንዲቀርብ ይመኙ የነበሩና ይህን በማየታቸው የተደሰቱት የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ የተቀኙትን የአማርኛ ግጥም ላስነብባችሁና የተሐድሶን ምንነተ ተረዱ፡፡
ስለ ሃይማኖት በመሞት ፈንታ
መግደል መሰየፍ የቁራን ዛንታ
ረቂቁማ የወንጌል ፍርድ
መታረድ ነበር መቼ ማረድ
ዛሬ ግን አፍራ እንደ ነጮች (አትዮጵያን ነው)
የቀድሞ ግብሯን ስለተወች
መጋረጃዋም በታምራት
ከላይ እስከ ታች ተቀድዶላት
ወደ ነጻነት ዐይኗን አሻግራ
ሁሉን ታያለች እንዲቦራ
ቅዱስ መጽሐፍም በእርሷ አማርኛ
ከግዜር ተልኮ መጣ ዳግመኛ
የትምህርቷን ወንዝ አለወረፋ  
ሁሉ እንዲቀዳ እየተስፋፋ  (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ ገጽ ፻፹፭)  
ይህ ነው ተሐድሶ! ይህ ግጥም የሚያሳየን የሕዝቡ መጎዳት የገባቸው የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት መጽሐፍ ቅዱስ በሕዝቡ ቋንቋ ተተርጉሞ እንዲቀርብ ሲመኙና የበኩላቸውን ጥረት ሲያደርጉ የነበረ መሆኑን እንዲሁም አሳባቸው እውን ሆኖ ሲያዩት ደግሞ በጣም የተደሰቱበት መሆኑን ነው፡፡ ከዚህም አልፈው እንደ ነፃነት ቆጥረው ያከብሩታል፡፡ እውነት ነው የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብና መማር ካለመቻል የበለጠ ባርነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ከመጎብኘት የበለጠስ የበረከትና የነጻነት ሕይወት የት አለ? ተሐድሶስ ከዚሕ የተለየ ምንድን ነው? በወርቁ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ላይ የተከመረውን የሐሰት ቆሻሻ አስወግዶ መጽሐፍ ቅዱስን ግልጥልጥ አድርጎ ከመስበክና ሰዎችን ሁሉ በእግዚአብሔር ቃል ነጻ ከማውጣት የተለየ ምን ተሐድሶ  አለ? ይህን ቅዱስ ተግባር ክፉ ስም በመስጠት የቤተ ክርስቲያንን ፈውስ ከማዘግየት የበለጠስ በደል የት ይገኛል? እንወዳታለን የሚሏትን ቤተ ክርስቲያን በገድልና በድርሳን ተረት ተብትበው ሕዝቡን በባርነት ሥር ይዘውት ለመኖር የሚፈልጉ ሰዎች አንድ ቀን ዐይናቸው ሲገለጥና ኀጢአታቸውን ማየት ሲችሉ እጅግ አድርገው እንደሚጸጸቱ እናምናለን፡፡ እኛም የቤተ ክርሰቲያን ተሐድሶ እውን እስኪሆን ድረስ እግዚአብሔር በሰጠን ዘመንና አእምሮ ለቤተ ክርስቲያን እየተጋደልን ለመኖር በእግዚአብሔር ጸጋ ወስነናል፡፡

ይቀጥላል!17 comments:

 1. "እውነት እውነት እላችኋለሁ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ
  ሌባ ነው ወንበዴም ነው በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።"(ዮሐ 10 ፦ 1)
  ከ 2000 ዓመት በላይ በእግዚአብሔር ቸርነት የቆየችውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናድስ ስትሉ ትንሽ አይከብዳችሁም።በኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት ነፃነት አለ እውነተኞች ከሆናችሁ የራሳችሁ
  ቤተ ክርስቲያን አቋቁማችሁ የራሳችሁን ዶክትሪን ይዛችሁ ማስተማር ስትችሉ ከመሐል ገብቶ
  እንደ ተኩላ በጎቹን ማተራመስ ምንድን ነው።
  ገድላትን ትቃወማላችሁ እስኪ አባ ጊዮርጊስ ዘ ጋስጫ በ14ተኛው ክ/ዘ የጻፈውን መጽሐፈ አርጋኖን
  ኢየሱስ ክርስቶስን እንዴት እንዳወደሰው እንዳመሰገነው ለእናቱ ማርያምን እንዴት እንዳመሰገናት አንብቡ። 600 ዓመት ሆኖታል እስኪ እናንተ የተሐድሶ መጽሐፍ ወይም የአባ ሰላማ ብሎግ ክርስቶስን መች አመሰገናችሁ ።መንፈስ ቅዱስን ተመልታ እኮ ነው ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል ያለችው የእግዚአብሔር መንፈስ ደግሞ አይሳሳትም።
  "መዳንም በሌላ በማንም የለም እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።(ሐዋ 4 ፦ 12)"ይህንን ጥቅስ አስቀምጣችሁታል።
  ታዲያ አዶናይ ኤልሻዳይ ያሕዌሕ ቅዱስ ጸባዖት አማኑኤል አልፋና ኦሜጋ የሚለው ስም አያድንም መስሏችሁ ነው።
  "ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ።" (ማቴ 24 ፦5)
  ሚስጥር ገላጭ የሆነ ምህረቱ የበዛ አምላክ ከስህተት ይመልሳችሁ አሜን።

  ReplyDelete
  Replies
  1. endehawariaw tomas teteratari atihun.. geta yirdah!!

   Delete
 2. ante yalamenkibet, lante yalteredah neger mels yelelew adirgeh silemitay new

  ReplyDelete
 3. የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የድንግል ማርያም ወዳጆች!!!!
  በዚህ ላይ ተጨማሪ አስተያየት የምሰጠው በመጀመሪያ በቅዱስ ሰለሞን ላይ አድሮ እግዚአብሔር የሚናገረን ነገር እናስተውል። " ጆሮህን አዘንብለህ የጠቢባንን ቃላት ስማ፥ ልብህንም ወደ እውቀቴ አድርግ፤ እነርሱን በውስጥህ ብትጠብቅ፥ በከንፈሮችህም ላይ የተዘጋጁ ቢሆኑ፥ የተወደደ ነገር ይሆንልሃልና። እምነትህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ ለአንተ ዛሬ እነሆ አስታወቅሁህ። የእውነትን ቃል እርግጥነት አስታውቅህ ዘንድ፥ ለሚጠይቅህም እውነትን ቃል መመለስ ይቻልህ ዘንድ፥ በምክርና በእውቀት የከበረን ነገር አልጻፍሁልህምን?" ምሳ. ም22፡ 17-21። ብሎ እግዚአብሔር የዘላለም ሕይወት የሚሰጠንን ቃሉን በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ መዝግቦ እንድንማረው ይመክረናል። በዚህም የእርሱ ደቀ መዛሙርቶቹና አይሁዳውያን ወገኖቹ እንዲረዱት ወይም ሕይወት የሚሰጠው የእርሱ ቃል መሆኑን እንዲህ ሲል ነግሯቸዋል።" ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ምንም አይጠቅምም፤ እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው። ብሏቸዋል። ዩሐ. ም6፡ 63። ስለዚህ ሕይወት የሚሰጠን ቃሉ በመጽሀፉ የተመዘገበው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው። ይህንን ተረድተን ወደ መጽሀፉ ልቦናችንን ማዘንበል ይገባናል። አለበለዚያ ያ ተስፋ አድርገን የምንጠብቀውን የእግዚአብሔርን መንግሥት መግኘት በጣም ያስቸግረናል። ምክንያቱም ሕይወት የሚገኘው በመንፈስ ነው። መንፈስም ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል ነው። ቃልም ደግሞ ክርስቶስ ነው። ይህንን ቃል ወይም መንፈስን የምንመገበው ደግሞ ከመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ይሆናል። በዚህም እግዚአብሔር በነቢዩ ኢሳያስ ላይ አድሮ ፦ " ማዕዱ ሁሉ ትፋትንና ርኵሰትን ተሞልቶአታል፤ ንጹሕ ስፍራ እንኳ የለም።፤ እውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን?፤ ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ነው።፤ በባዕድ አፍ በልዩም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይናገራል፤ እርሱም። ዕረፍት ይህች ናት፥፤ የደከመውን አሳርፉ፤ ይህችም ማረፊያ ናት አላቸው፤ እነርሱ ግን መስማትን እንቢ አሉ።፤ ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ እንዲሰበሩም ተጠምደውም እንዲያዙ የእግዚአብሔር ቃል ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል "። ኢሳ. ም28፡ 8-13 ብሎ ይህንን የእግዚአብሔርን መንፈስ ተመግበን የመንፈስ ፍሬ እንድናፈራ ይምክረናል። በዚህም መታደስ ይገኛል። መታደስ በሌላ አይደለም በእግዚአብሔር ቃል ነው። ለዚህም ነው ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ የነገርኳችሁ ቃል መንፈስም ነው ሕይወትም ነው ብሎ የሚመክረን። ለአዳም በሕይወት ዛፍ ተመስሎ ለእስራኤል በዓለት ውኃ ሆኖ ዛሬም ለእኔና ለእናንተ በመጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ተመዝግቦ ሕይወት የሚሰጥ አንድ ቃል ነው። ቃልም ሥጋ የለበሰው " ኢየሱስ" ነው። ኢየሱስም እግዚአብሔር ነው። በዚህም ይህንን ሕይወት የሚሰጠንን ቃል የምንመገበው ደግሞ በጆሮአችን ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር እኛን ሊያአድሰን የምንችልበትን ምግብ እንድናገኝ ጆሮአችንና ልቦናችንን ወደ ቃሉ ያዘንብልልን! አሜን!
  ወስብሐት ለእግዚአብሔር

  ReplyDelete
 4. Tehadisowu kelay yejemer abatochachi yesatefubet

  ReplyDelete
 5. You see, this is the problem. Since you learned all these stuff from your foreign agents, you cite them in your articles. I don't find any point in this article which requires explaination - bemenafikan betedegagami sibal yenor new. Let me pose a simple question you, who prevented you not to translate and distribute the bible in any language you would like to?

  ReplyDelete
  Replies
  1. sigerm! betam mihur neh bakih.....1 tikis abirara bitibal gin mekelakel tijemir neber...yikir yibelh!!

   Delete
 6. " 1 እግዚአብሔርም አብራምን አለው። ከአገርህ ከዘመዶችህም ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ። 2 ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤ 3 የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤..." ኦሪት ዘፍጥረት - 12

  ReplyDelete
 7. ጅብ “ጥጆቹን ጠብቅ” ቢሉት “ይጠፉብኛል” አለ ይባላል፤ደግሞም በማያውቁት ሀገር “ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” አለ ይባላል፡፡

  ReplyDelete
 8. ስማ ትምህርተ ሃይማኖት አይለወጥም፡፡ እናንተ ዝም ብላችሁ ትቀባጥራላችሁ፡፡ አላማቸሁም ቤተክርስቲያንን ማሳደግ ሳይሆን ለ ፕሮቴስታንት አጋልጦ መስጠት ነው፡፡ ይልቅ የሚከተለውን ቅኔ አበርክቸልሃለሁ፡፡ ይቺ አንዲቷ አባቶቻችን ጠብቀው ያቆዩአት ሃይማኖት እንዴት ጠላቷ እንደበዛ ተመልከት፡፡ ግን ጠባቂዋ አይተኛም፡፡
  ጉባኤ ቃና፡
  እስኩ ለብው ድኩማን አግብርተ ሉተር ሀካይ፡
  እፎኑ ትትሔደስ ቃለ-ተዋህዶ ፀሐይ ?
  ትርጉም፡
  ሰነፍ የሆነ የሉተር አገልጋዮች ደካሞች ሆይ ፣ እስኪ አስተዉሉ፡ የተዋህዶ ቃል ፀሐይ እንዴት ትታደሳለች ?
  ምሥጢር፡
  ፀሐይን አረጀች ብሎ ማደስ እንደማይቻል እና እንደማይሞከር ኦርቶዶክስ ተዋህዶም እንደ ስሟ ርትዕት ስለሆነች ልትታደስ አትችልም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ልቡና ካላችሁ ራሳችሁን አድሱ፡፡
  ኩልክሙ መወድስ (አንድ ሊቅ ለሐራ ካበረከተው)
  ማእረረ ሰላማ ስርናይ ፡ቃለ-ተዋህዶ፡ እፎኑ ፈድፈዱ ፡ወበዝኁ ጸላዕትኪ፤
  እለ ይትሜነዩ ወትረ፡ ከመ ያጥፍዑኪ፤
  ውስቴትኪ፡ ዕፄ-ተሐድሶ ፡እስመ ወጽአ ፡ብኪ፤
  ወወጠነ አማስኖ፡ እንዘኬ ይመትር፡ ምሥጢራተ ወንጌል ሥረወኪ፤
  ሦክሂ አማሌቃዊ፡ እንተ በቆለ ድኅሬኪ፤
  ሠጠጠ ወረገዘ ፡ ምዕመናነ አቁፅለኪ፤
  ወዝንቱሰ ይትርፍ ፡ እንተ በሙስና የአኪ፤
  መንግሥተ ብሔር በረደ-ጊሜ፡ ያንሶሱ በላዕሌኪ፤
  እስመ ከመ ሃሎ ኢዖቀ ፡ እም አምላከ ራማ ኃይልኪ፤
  መንግሥተ ብሔር በረደ-ጊሜ፡ ያንሶሱ በላዕሌኪ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. aye ene hod amilaku kine hod memuya ena silitan maggna aregachihut adel...tenekitobachihual!!

   Delete
  2. ቅኔ ሆድ መሞያ ሳይሆን አእምሮን መሙያ ነው አንተ፡፡ ሆድ ለመሙላትማ እነ ” ከርሶሙ አምላኮሙ” እናነተ አላቹህ አይደል፡፡ ሃይማኖት በማጥፋት የምትበለጽጉ መስሏችሁ፡፡ የዘመኑ ባንዳዎች ማለት እናንተ ናችሁ፡ አገር ሻጭ፡፡

   Delete
 9. ተባረኩ አባ ሰላማዎች ጥሩ መልዕክት

  ReplyDelete
  Replies
  1. Yaaaa tiru seytanawi melekt

   Delete
 10. ቃለ ሕይወት ያሰማልን። ዘሩ ተዘርትዋል የማብቀልና የማሳደግ ድርሻው የሌላው ነው። በተቃውሞና በአለማወቅ ሐሩር ብዛት የደረቀችው የሰው ልብም በዝናብ ወንጌል እንድትረሰርስ እንጸልያለን።
  በርቱ!!!!!!!!!

  ReplyDelete
 11. ANTE MANAFIK! HIWOT KEFELEK ANTE RASI TADES ENJI BETEKIRISTIANITUWA YEMILEWET YEMITADES NEGER YEMATIM

  MESERETUWA FITSUM SILEHONE, ESUAM FITSUMT NAT

  TADISO MENAFIK

  ReplyDelete
 12. በውስጣችሁ ታደሱ እንጅ ይህን አለም አትመሰሉ ያለው ጳዎሎስ ቤተክርስቲያን ትታደስ ብሎ አደለም ዝም ብላችሁ አትቀባጥሩ ቤተክርስቲያን ሁሌም አዲስ ነች ነባርም ነች በክርስቶስ ደም ተመስርታለችና፡፡ ሁለት ምንገድ አለ አሱም ጠባብ ሰፊ መንገድ ፡ ውሐ እሳት ደስ ባለህ መሔድ ተችላለህ ፡፡ ግን ትክክለኛ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞችን ለማደናገር ሞሞከር ግን ትልቅ በደል ነው !!!

  ReplyDelete