Thursday, July 24, 2014

ሐሰትን ሲናገር ከእራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና። ዮሐ.8:44

Read in PDF

ይነብብ ሐሰተ እምዚአሁ…….ወአቡሃ ለሐሰት

ከጥዑመ ልሳን ፈረደ!
ይኽ ቃል በሰዎች ዘንድ በጣም የተለመደና ሰዎች በቦታውም ያለቦታውም የሚጠቀሙት ነው። ቃሉ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቃል ሲሆን የተነገረው በክፉ መንፈስ ተሞልተው ሐሰትን ይዘሩ ለነበሩ አይሁድ ነው። ዛሬ ዛሬ ሐሰት የጊዜው ፋሺን በሆነበት ዘመን ሐሰትን መዝራት ለብዙዎች ኃጢአት የማይመስልበት ጊዜ ነው። ምክንያቱም በዚህ ዘመን ሐሰት እንደ ነውር የሚታይበት ሳይሆን ሐሰት ጥበብ፤ ሌላውን ማጥቂያ መሣሪያ፤ የሰውን ልብ መግዣና ስውር ደባን ወደሰዎች አእምሮ ለማስገባት ዓይነተኛ ዘዴ ሆኖ የሚታይበት ዘመን ስለሆነ። ሐሰት ያልሆነውንና ያልተደረገውን ነገር ከራስ አፍልቆ መናገር ብቻ ሳይሆን ዋና ዓላማው በጀርባ ላለው ስውር ደባ የኋላ መግቢያ በር ነው።

በነ “ሐራ” መንደር ሐሰት መናገር በጣም ቀላል ሲሆን የዕለት ዕለት ሞያዊ ተግባርም ነው። ማቅ የቆሻሻ መድፊያ አድርጎ ያቆማት “ሐራ” በየጊዜው በሬ ወለደ ወሬን ታስነብበናለች። ምን አልባት አንባቢ በሐራ ዘንድ ሐሰትን መዝራት ምን አዲስ ነገር አለው? ምንስ ያስደንቃል? ሊል ይችላል። እርግጥ ነው አዲስ ነገር ሆኖብን ሳይሆን አያውቅብንም ተብሎ እየተዋሸና እየተወናበደ ያለው ወገን እንዲነቃ ብለን እንጂ ሐሰት ለሐራ መነሻና መድረሻ መሆኑን እኛም አሳምረን እናውቃለን።

ሰሞኑን “ሐራ” ካናፈሰቻቸው በሬ ወለድ ወሬዎች በጣም የተደመምንበትን አንዱን ለመዳሰስና እውነተኛውን ክስተት ለአንባቢዎች ለማስጨበጥ ፈለግን። ለምሳሌ ያክል የሚከተለውን እነሆ፦

v “ቋሚ ሲኖዶስ ለፓትርያሪኩ ማስጠንቀቂያ ሰጠ” ስለተባለው

የንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሐና የአቶ ታምሩን የሥራ ዝውውር አስመልክቶ ማቅ ዝውውሩ በቅዱስ ፓትርያሪኩ ብቻ እንደተካሔደና በዚህ ያልተደሰተው ቋሚ ሲኖዶሱ ለፓትርያሪኩ ማስጠንቀቂያ እንደሰጠ ሳያፍር፤ ዓይኑን በጨው ታጥቦ አስነብቦናል። እኛ ግን ሐራን ስለማናምናት ጠይቀንና አጣርተን የደረስንበትን እውነተኛ ታሪክ እነሆ ይዘን ቀርበናል።

አቶ ታምሩ ከልዩ ጽ/ቤት የተነሱበት ታሪክ እንዲህ ነው። አቶ ታምሩ ፎርጅድ ደብዳቤ በቅዱስ ፓትርያሪኩ ስምና ፊርማ አዘጋጅተው በአውስትሪያሊያ ለሚገኘው አንድ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ይሰጣሉ። በዚህ ቤተ ክርስቲያን ያሉ ምዕመናን ቤተ ክርስቲያኑ ይሸጥ አይሸጥም በሚለው ለሁለት ተከፍለው በመከራከር ላይ እያሉ ይሸጥ የሚሉት ወገኖች አቤት ለማለት ወደ መንበረ ፓትርያሪክ ሲመጡ በአቶ ታምሩ በኩል የጓሮ በር ያገኛሉ። አቶ ታምሩም ደጎስ ያለ እጅ መንሻ ሲያገኙ በፓትርያሪኩ ፊርማ የሐሰት ደብዳቤ ለማብረር ምንም አልሰቀጠጣቸውም። ቤተ ክርስቲያኑ ይሸጥ ባዮች  “አቦ-ሰጠኝ” የሆነውን ደብዳቤ የፓትርያሪኩ የአዎንታ ማስረጃ አድርገው ሲያቀርቡ፤ አይሸጥም ባዮች ደግሞ በበኩላቸው አቤት ለማለት ወደ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ይመጣሉ።

በዚህ መንገድ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ነገሩን ከተረዱ በኋላ አቶ ታምሩ እንዲጠየቅ ሲደረግ አቶ ታምሩ ይክዳሉ። በተደረገው ክትትልና ማጣራት በቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የቀድሞ ልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩ መጋቤ ሠናይ አሰፋ ለአቶ ታምሩ ደብዳቤውን አርቅቀው የሰጡ መሆናቸውን አቶ ታምሩ ባሉበት ይመሠክራሉ። ይኽንን ያረጋገጠው ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ከፓትርያሪኩ ጋር ሆኖ አቶ ታምሩ ከቦታቸው እንዲነሱ ይወስናል። በፓትርያሪኩ ፈቃድ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሐ ለልዩ ጽ/ቤት ሲመደቡ፤ አቶ ታምሩ ደግሞ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ፊርማ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ኮለጅ ተመድበው ይላካሉ። አባቶች በጉባኤ የወሰኑት፤ ፋይል ይዞ የሚገኘው እውነተኛ ታሪክ ይኽ ነው። 

እውነተኛው ታሪኩ ይኽ ሆኖ ሳለ የሐሰት መርዝን ከራሱ አመንጭቶ በሐራ የሚያርከፈክፍ ማቅ ግን የሚያወራው ያልተደረገና ያልሆነውን ነው። ለምን ስንል በአገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቅዱስ ፓትርያሪኩን ስም ማጥፋትና በቅዱስነታቸው ዙሪያ አድማን ማነሳሳት፤ በቤተ ክርስቲያን ሰላም እንዲታጣ ማድረግ በወቅቱ የያዘው ቋሚ አጀንዳው ስለሆነ ነው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በማቅ ጥርስ ውስጥ እንዴት ገቡ ብለን ስናስብ ለማቅ የውንብድና አካሔድ ስለአልተመቹ ነው። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በቤተ ክርስቲያንዋ ታሪክ ክብርና ጥቅም የማይገዛቸው፤ ለእውነት የቆሙና ሙስናን ከሥሩ ነቅለው ለመጣል በቁርጠኝነት የሚታገሉ የመጀመሪያው አባት ናቸው ብንል ማጋነን አይሆንም።

ስለዚህ የ5 ኪሉ ሕንፃ ባለቤት ማኅበር ቅዱስ ፓትርያሪኩን ነክሶ የያዘው እስከአሁን በጥቅም እንደሚያሽከረክራቸው አባቶች ሆነው ስላልተገኙ፤ የውንብድናውን በር ስለዘጉበት ጥቅሜ ተነካ፤ በአካሔዴም ተነቃብኝ ብሎ እንደሆነ የሚስተዋል እውነት ነው።

ሌላው የምናነሳው ጥያቄ ማቅ ይኽን ያክል ውሸት በሚዲያ ሲረጭ እውነቱ ተጣርቶ ይደረስብኛል ብሎ ለምን አላሰበም? የጐመጀው በሬ ሣሩን እንጂ ገደሉን ስለማያይ ይሆን? ወይስ ጥዋት ማታ ያለሐፍረት የሚያናፍሰው ሐሰት ስለሆነ ሐሰትነቱ አይታወቀውም ይሆን? ውሸት ሲበዛ እውነት ይመስላል እንዲሉ። ወይንስ እኛን አንባቢዎቹን አንብበው አይረዱም፤ ጠይቀው አይደርሱበትም ብሎ ስለምንቀን ይሆን? እርሱማ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ብላ ሰይማ የቀባችውን አባት ያለምንም ምክንያት የሚያዋርድ የ5 ኪሉ የሕንፃ ባለቤት ማኅበር ስለእኛ ምንም አይገደውም።
                                                                                  
ታሪኩን ከላይ እንደአየነው ማቅ የአቶ ታምሩን ነውር ከማንሳት ይልቅ ነውሩን ከድኖ ነውር የሌለበትን አባት መወንጀል ማንነቱን በትክክል ገልጦ ያሳየናል። ነውርና ሙስና ለማቅ ዕድል ፋንታው በመሆኑ እውነተኞችን አባቶችና ወንድሞች በሐሰት መክሰስ ገና ሲወለድ የተጠናወተው ክፉ መንፈስ ስለሆነ የቤተ ክርስቲያን አምላክ አንድ ቀን ይፈውሰዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ያለማቋረጥም እንጸልያለን።

 ማቅ ሕዝቡን በማታለልና የተሳሳተ መረጃን በማሰራጨት፤ የአዲስ አበባ አድባራትን በማወክ ቅዱስ ፓትርያሪኩን በሕዝብ ዘንድ አስጠልቼ ተሰሚነት አገኛለሁ ብሎ ቢያቅድም ገመዱ እያጠረበት መምጣቱ ግልጽ እየሆነ ነው።

በቤተ ክርስቲያንዋ ሞያ አሉ ከሚባሉት ሊቃውንት ቀዳሚ ሥፍራን የሚይዙ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃን የጥላቻና የስም ማጥፋት ጥላሸት ሲቀባቸው የቆየ ቢሆንም በሰዎች የተጣሉትን ከፍ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን የተሻለ እድገት ሰጣቸው። ማቅ የእግዚአብሔርን አሠራር መቀበል ባይችልም ከእንግዲህ ከልዩ ጽ/ቤት ወሬ አቀባይ ሰው ማጣቱን ይረዳል።

ሌላው “ውሻ በቀደደው ጅብ…” እንዲሉ የማቅን በህገ ወጥነት ሀብት ማካበትና በቤተ ክርስቲያንዋ ነጻ ገበያ እንደልቡ መቧረቅን የተመለከቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ በርካታ ማኅበራት ለእኛም ፈቃድ ይሰጠን ሲሉ አመልክተዋል። ይኽም የበርካታ ማኅበራት የማቅን የውንብድና ፈለግ ተከትሎ የመጣው “ለእኛም የይገባናል” ጥያቄ ቅዱስ ሲኖዶስን በእጅጉ እንዳሳሰበው ብዙዎች ይናገራሉ። ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያንን ልጆች በእኩል ከማየት አንጻር ለአንደኛው ወገን ፈቃድ ሰጥቶ ሌላኛውን ወገን መከልከል ስለማይቻል። ማቅ እንደመዥገር ተጣብቆ የቤተ ክርስቲያንዋ ደም መጣጭ መሆኑ ለብዙዎች የገባቸው ይመስላል። የማኅበራቱ ጥያቄም ማቅ ለመንግሥት ታክስ የማይከፍል፥ ሂሳቡ ኦዲት የማይደረግ፤ በቀላሉ ብልጽግና የሚገኝበት ነጻ ገበያ ስለሆነ እኛስ ምን ያግደናል የሚል ነው። ምክንያቱም በማቅ መንደር ለመስበክም፤ ለመነገድም ምንም መስፈርት የለም። ምንአልባት መስፈርቱ ሊሆን የሚችለው በወንድሞች መካከል ጠብን መዝራትና ጥቅም አገኝበታለሁ ያለውን የሐሰት ወሬዎችን ያለምንም ሀፍረት ማናፈስ ነው። ማቅ በስሙ መንፈሳዊ  በተግባሩ ግን ሕገ-ወጥ ነጋዴና ፖለቲካዊ ስለሆነ ሊነቃበት ይገባል።

በዚህ አጋጣሚ ቤተ ክህነቱ ለታወቀው ቫይረስ(ተስቦ) ፈውስ ሳያገኝለት ሌላ መቶ ቫይረስ እንዳይፈጠርና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕይወት እንዳያውክ የማኅበራቱን ጥያቄ በተመለከተ ከወዲሁ ሊያስብበት ይገባል እንላለን።

በተጨማሪም እኛ ለማቅ ያለን ምክር የሚከተለው ነው፦

1)    እግዚአብሔር የቀባቸውንና ያከበራቸውን አባቶች ማክበር፤ እግዚአብሔርን በመፍራት መመላለስ የክርስትና ጠባይ ነው።
2)    ወንድሞችን በሐሰት መክሰስ የክፉ መንፈስ ተግባር ስለሆነ በንሥሐ ታጥቦ ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት ሕይወት ነው።
3)    አባቶችን በጥቅም፤ ምዕመናንን በአድማ ከፋፍሎ ከማወክ፤ ለእግዚአብሔር መንግሥት እንቅፋት ከመሆን በአባቶች እግር ሥር ተቀምጦ መማር፤ ከአባቶች ጋር ተስማምቶ መሥራት ፍኖተ ጽድቅ ነው እንላለን።

                                  =====ይቆየን=====

9 comments:

 1. The source is Fakt Metsihet not Hara Zetewahido

  ReplyDelete
  Replies
  1. ,The source is Fakt Metsihet not Hara Zetewahido.

   ፋክት የማቅ ቅምጥ፤ የሐራ የሐሰት ወሬ ሽልፍ መሆንዋን አሳምረን እናውቃለን።
   ከዚህም ጋር ፋክት የሐሰት ወሬ ብትፈበርከውም ሐራ አሰራጭተዋለች። ቃሉ የሚለው ደግሞ ሐሰትን ፈጥሮ ያወራ ብቻ ሳይሆን የዘራም በእግዚአብሔር የተጠላ እንደሆነ ይመሠክርልናል።
   ,እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች……………….በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።. ስለዚህ ይኽ የአባ ሰላማ ጉዳይ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል የመቀበልና ያለመቀበል ውሳኔ ነው። ሐራ ከፋክት ትስማም፤ ከክሷም ታውጣ ለዘራችው የሐሰት ወሬ ተጠያቂ ናት።

   (ከጊዜሽወርቅ ደብረ ማርቆስ)

   Delete
 2. Ante wshetam meregawin yawetaw hara sayehon Fakt metsehat new.demo hulunim neger ke mk new bilachu techelutalachu.

  ReplyDelete
  Replies
  1. The source is Fakt Metsihet not Hara Zetewahido.

   ፋክት የማቅ ቅምጥ፤ የሐራ የሐሰት ወሬ ሽልፍ መሆንዋን አሳምረን እናውቃለን።
   ከዚህም ጋር ፋክት የሐሰት ወሬ ብትፈበርከውም ሐራ አሰራጭተዋለች። ቃሉ የሚለው ደግሞ ሐሰትን ፈጥሮ ያወራ ብቻ ሳይሆን የዘራም በእግዚአብሔር የተጠላ እንደሆነ ይመሠክርልናል።
   ,እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች……………….በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።. ስለዚህ ይኽ የአባ ሰላማ ጉዳይ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ቃል የመቀበልና ያለመቀበል ውሳኔ ነው። ሐራ ከፋክት ትስማም፤ ከክሷም ታውጣ ለዘራችው የሐሰት ወሬ ተጠያቂ ናት።   (ከጊዜሽወርቅ ደብረ ማርቆስ)

   Delete
 3. Gebrekidane ze DireDawaJuly 26, 2014 at 12:11 PM

  አባ ሰላማዎች በእውነቱ ትልቁ ከእናንተ የተጠቀምነው ነገር ቢኖር ስለ ሐራ በምታወሩልን እናንተን ከነሱ እንድንለይ ሐራዎች እናማናቸው እንድንል ምክኒያት በመሆናችሁ ነው፡፡ እግዜር ይስጣችሁ ተዋኅዶን አውቃታለሁ ለማስመሰል የምትወሻክቱትን ስመለከት ደግሞ አስመሳዮች እና ተኩላዎች መሆናችሁ ገባኝ፡፡ ተስፋ ቆርጬ ባለሁበት በእናንተ የሚብጠለጠለውን ማኅበርን እና ሐራን እንዳውቅ ረዳችሁኝ በእውነቱ ከሆነ ማኅበረ ቅዱሳኖች እና ሐራ የምትባለዋን ዌብሳይት ስመለከት ቤተክርስቲያናችንን ባግባቡ የተረዱ ከአማናዊው ምንጭም የተቀዳውን ቃለ እግዚአብሔር እና የተዋኅዶን አስተምህሮ የሚያደርሱን ትክክለኛ ክርስቲያኖች መሆናቸውን ተረድተናል፡፡ ተኩላነታችሁን ለማወቅ ካባችሁን እስክታወልቁ መጠበቅ አላሻንም፡፡ ከክፋታችሁ ተመለሱ !!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ,ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤ ከነዚህም የወጣ ከክፉው ነው. (ማቴ.5:37)

   ,እናንተስ እረ እፈሩ ማንም ከማንመ አትሻሉ አናንትስ ለቤ/ክ ተሐድሶ አሰራለን እያላችሁ ወንድሞቻችሁን በጥቅም ለውጣችሁ ስማ የምታጠፉ. ለሚለው መልስ፦

   ወንድሜ/እህቴ, የቅንነት፤ የማስተዋል ልብ ካለ አንብቦ መረዳት ቀላል ነው። አሊያም ,አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱትም አይሰማ. እንደሚሉት አበው። ማነው ስም አጥፊ? የሌለ ታሪክን ፈጥሮ የሰዎችን ስም ማጉደፍ ወይስ ለተሳሳተ ጽሑፍ መልስ መስጠት? አባ ሰላማዎች ,ስትክክለኛ ታሪኩ ይኽ ሆኖ ሳለ በሐራ የተገለጠው የተሳሳተ ነው. ብሎ ነው የጻፈው። ከዚያን በኋላ የአንተ/የአንቺ እና የእኔ ድርሻ ሁለቱን አመዛዝነን መረዳት ነው። ቀጥለን እግዚአብሔር በልባችን ያስቀመጠውን እውነት መናገር ነው። በደፈናው መሳደብ ግን ,ከክፉ ነው. ከሚለው ወገን መሆን ነው።

   እግዚአብሔርን የምትፈራ ከሆነ/ከሆንሽ አስተውል/ይ፦ ,ቃላችሁ አዎን አዎን ወይም አይደለም አይደለም ይሁን. የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ለዚህ አባባልህ የሚደግፊህ/ሽ ይመስልሃል/ሻል? እውነት የሚናገረውን ስም አጥፊ፥ ስም አጥፊውን እውነተኛ ማድረግስ የእግዚአብሔር ቃል የማይዳኝህ/ሽ ይመስልሃል/ሻል?

   አባ ሰላማ ዌብሳይት ብዙ አስተምሮኛል። እውነትን መናገርና የጨለማውን ሥራ መግለጥ ለእኔ ወንጌል ነው። ወንጌል ማለትም ለእውነትና እውነት ነው። (ዮሐ.18:37) ሐራም በበኩሉ በቤተ ክርስቲያኔ ያለውን ችግር ብዙ እንዳውቅ አድርጎኛል። ሆኖም እያወኩኝ በመጣሁ ቁጥር ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንቱ በውሸትና በፖለቲካ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ከመንፈሳዊነት ጎራ በጣም ርቆብኛል። ድርጅትን ከድርጅት ጋር ከማነጻጸር ይልቅ እውነትን ከሀሰት መለየት፤ በሁሉም የሚጻፉትን በእግዚአብሔር ቃል መዳኘት በረከት ነው። እውነተኛ መረጃን ለአንባቢያን ማቅረብም የሰማዕያንን ልብ መግዛት ነው።

   (ከብርሃነ ሕይወት አዲስ አባባ)

   Delete
 4. “በዚህ መንገድ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ነገሩን ከተረዱ በኋላ አቶ ታምሩ እንዲጠየቅ ሲደረግ አቶ ታምሩ ይክዳሉ። በተደረገው ክትትልና ማጣራት በቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የቀድሞ ልዩ ጽ/ቤት ኃላፊ የነበሩ መጋቤ ሠናይ አሰፋ ለአቶ ታምሩ ደብዳቤውን አርቅቀው የሰጡ መሆናቸውን አቶ ታምሩ ባሉበት ይመሠክራሉ። ይኽንን ያረጋገጠው ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ከፓትርያሪኩ ጋር ሆኖ አቶ ታምሩ ከቦታቸው እንዲነሱ ይወስናል። በፓትርያሪኩ ፈቃድ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሐ ለልዩ ጽ/ቤት ሲመደቡ፤ አቶ ታምሩ ደግሞ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ፊርማ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ኮለጅ ተመድበው ይላካሉ። አባቶች በጉባኤ የወሰኑት፤ ፋይል ይዞ የሚገኘው እውነተኛ ታሪክ ይኽ ነው።”

  ቃለ ሕይወት ያሰማችሁ

  ReplyDelete
 5. እናንተስ እረ እፈሩ ማንም ከማንመ አትሻሉ አናንትስ ለቤ/ክ ተሐድሶ አሰራለን እያላችሁ ወንድሞቻችሁን በጥቅም ለውጣችሁ ስማ የምታጠፉ፡፡ እነሱ እሺ ወንጌል አልገባቸውም እንደበል እናንተስ የጌታ ቃል ሞልቶ የነበረባችሁ የምንላችሁ ግን ማስተዋላችሁ ተወስዶ የምታደርጉት እስኪጠፋባችሁ ድረስ ለድፍረት ክስ ተላልፋችሁ የተሰጣችሁት አታፍሩም እኔማ ከአሁን በኋላ ለእናነተ ያለኝ ነገር አብቅቷ /ማሊ ቲቄል ፋሪስ/ ማጣም ነው የምታሳዝኑት ይልቁልንም የተሰውን ሐጥያት ስትገልጡ ከመኖሩ ተመለሱና በንስሐ የሚየምርባችሁን ክብር የሚሆናቸውን የጌታን ነገር ለመግለጥ ትጉ፡፡ ማስተዋልን ይስጣችሁ፡፡

  ReplyDelete
 6. መጀመሪያ ለምትጠቀሙት አማርኛ ተጠንቀቁ እግዚአሔር የሚሳደብለት ተከታይ ኖሮት አያውቅም በህይወት የሚኖርለት እንጂ ይልቁልም ለማያውቃችሁ ይህንን በሉ እስከዛሬ ባለማወቅ እናንተን አከባበርን ሀሳባችሁን ተከተል ግን እስኪ እንደክርስቲያን አውሩ ጥርስ ላለቀ ጥርስ አትኑ፡፡

  ReplyDelete