Wednesday, July 16, 2014

ግብረ ሰዶማዊነት የጊዜው የቤተ ክርስቲያን ፈተና

ምንጭ፡- ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ብሎግ

የክርስቶስ ሙሽራ የሆነችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚህ ዓለም ስትኖር በልዩ ልዩ መከራ ውስጥ ታልፋለች፡፡ መከራዋ ከውጭ ከአጽራረ ወንጌል ሃይላት ብቻ ሳይሆን ከውስጥ ከራሷም የሚነሣ ነው፡፡ ከውስጥ ፈተናዎቿ መካከል አንዱ በአገልጋዮቿና በምእመናኗ ዘንድ የቅድስና መታጣት ነው። እግዚአብሔር እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ ሲል አዟል፡፡ ያለ ቅድስና እርሱን ማገልገል እንደማይቻል ግልጽ ጉዳይ ነው፡፡
ቅድስና ብዙ ነገር ነው። በጥቅሉ ቅድስና ከኃጢአት መራቅ እና ጽድቅን እያደረጉ መኖር ተብሎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ በዚህ ክፍል የምንመለከተው ግን ከጾታዊ ግንኙነት ጋር የተያያዘውን የቅድስና ጉድለት ይሆናል፡፡ በዚህ ረገድ ቅድስና የሚባለው አንድ ወንድ በአንዲት ሴት ተወስኖ እግዚአብሔርን እያከበሩ ከእርሱ ጋር መኖር ነው፡፡ ከዚህ ውጭና ተቃራኒ በሆነ አኗኗር መመላለስ ማለትም ከጋብቻ ውጪ የሚፈጸም ማንኛውም ጾታዊ ግንኙነት ሁሉ ርኩሰት ነው፡፡ ይልቁንም ከተፈጥሮ ባሕርይ ውጪ ወንድ ከወንድ ሴት ከሴት ጋር የሚፈጽሙት አስጸያፊ ድርጊት ሌላ ገላጭ ቃል ስለሌለ እንጂ ከርኩሰትም በላይ ነው፡፡
እግዚአብሔር ቅዱስ አምላክ ነው፡፡ ለቅድስናው ተስማሚ በሆነ አኗኗር እንድንኖርም ይፈልጋል፡፡ ጋብቻን ሲመሰርት ለአዳም ሔዋንን እንደፈጠረና ጋብቻ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚፈጠር ህብረት እንደሆነ ግልጽ ሆኗል፡፡ ሰው በኃጢአት ከወደቀ በኋ ግን ይህን የእግዚአብሔር ሐሳብ የሚፈጸምበትን ቅዱስ ሕብረት ጋብቻን ለማበላሸት በወንድና ሴት መካከል የዝሙት ሃጢአት እንዲፈጸም በማድረግ ጠላት ዲያብሎስ ሲሰራ ኖሯል፡፡ ከዚያም የጥፋቱን መጠንና ዐይነት በማስፋት ሰው ከተፈጥሮ ባሕርዩ ውጪ በሆነ መንገድ ከተመሳሳዩ ጾታ ጋር  አስነዋሪ ድርጊት እንዲፈጽም አደረገ፡፡ ይህም አስጸያፊ ርኩሰት የተጀመረው በቅርቡ ሳይሆን ጥንት ነው፡፡ 

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን አጸያፊና ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ የሆነውን ርኩሰት ሲፈጽም የምናየው ከነዓን የተባለው የካም ልጅ ነው፡፡ እርሱ አያቱ ኖህ ገበሬ ሆኖ ካመረተው የወይን ጠጅ ጠትቶ በሰከረ ጊዜ ግብረ ሰዶም እንደፈጸመበት የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ “ኖኅም ከወይን ጠጁ ስካር ነቃ፥ ታናሹ ልጁ ያደረገበትንም አወቀ። እንዲህም አለ፦ ከነዓን ርጉም ይሁን ለወንድሞቹም የባሪያዎች ባሪያ ይሁን።” ሲል ረገመው፡፡ “ያደረገበትንም አወቀ” የሚለውም ግብረ ሰዶም የፈጸመበት መሆኑን እንዳወቀ ያሳያል ይላሉ፡፡ (ዘፍ. 9፡24-25) እርሱ እንዲህ ቢያደርግም የአባቱን ራቁትነት አይቶ ለወንድሞቹ ለሴምና ለያፌት ነግሮ ራቁትነቱን እንዲሸፍኑለት ያደረገው የከነዓን አባት ካም ነው፡፡ ይህም የሚያሳየን ግብረ ሰዶም የሚል ስያሜ የተሰጠው ርኩሰት በኖህ ዘመንም የነበረ አስጸያፊ ርኩሰት እንደሆነ ነው፡፡ ምድር በጥፋት ውሃ እንድትጠፋ አንዱ ምክንያት የነበረውም ይህ ርኩሰት ሳይሆን አይቀርም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ከኖህ በኋላ በዚህ አስጸያፊ ርኩሰት ውስጥ ሆነው የምናገኛቸው የሰዶምን ሰዎች ነው፡፡ የሰዶም ሰዎች ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በዚህ አስጸያፊ ርኩሰት ውስጥ የሚመላለሱና የሚኖሩ ነበሩ፡፡  ወደ ሎጥ የገቡትን ሁለት ሰዎች (መላእክት) ካልተገናኘን ብለው ቤቱን ከበው እንደነበርም ተጽፏል፡፡ መጽሐፉ እንዲህ ይላል “ገናም ሳይተኙ የዚያች ከተማ የሰዶም ሰዎች፥ ከብላቴናው ጀምሮ እስከ ሽማግሌው ድረስ በየስፍራው ያለው ሕዝብ ሁሉ፥ ቤቱን ከበቡት። ሎጥንም ጠርተው እንዲህ አሉት፦ በዚህ ሌሊት ወደ ቤትህ የገቡት ሰዎች ወዴት ናቸው? እናውቃቸው ዘንድ ወደ እኛ አውጣቸው።” (ዘፍ. 19፡4-5) ሎጥ ግን እንግዶቹን እንዲተዉአቸው በማለት ሴቶች ልጆቹን ልስጣችሁና የፈለጋችሁትን በእነርሱ ላይ ፈጽሙባቸው ብሎ ነበር፡፡ እነርሱ ግን አይሆንም ብለው የዘጋውን ደጁን ለመስበር ተቃርበው ነበር፡፡ በመጨረሻም መላእክቱ ይህን ርኩሰት ለመፈጸም የሎጥን ደጅ የከበቡትን ሰዎች አሳወሯቸው፡፡ ይህ አስጸያፊና ከተፈጥሮ ባሕርይ ውጪ የሚፈጸም ርኩሰት ግብረ ሰዶም የሚል ስያሜ የተሰጠውም የሰዶም ሰዎች ከታላቁ እስከ ታናሹ በዚህ ወራዳ ተግባር ውስጥ ስለነበሩ እንደሆነ ይታመናል፡፡
በሙሴ ዘመን በኦሪት ሕግ ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ ያለምሕረት እንዲገደሉ ተደንግጓል፡፡ “ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል ፈጽመው ይገደሉ ደማቸው በላያቸው ነው።” ዘሌ 20፡13
መጽሐፍ ቅዱስ በሐዲስ ኪዳን ክፍል እንደሚያስተምረን ሰዎች በዚህ አስጸያፊ ርኩሰት ውስጥ የሚገኙት እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የእርሱንም ክብር ለፍጡራን ስለሰጡ የእግዚአብሔርንም እውነት በውሸት ስለለወጡ፣ በእነርሱ ላይ ያመጣው አሳልፎ የመስጠቱ ውጤት ነው፡፡ ቃሉም እንዲህ ይላል
 “ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤ … ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ስራ ለባሕሪያቸው በማይገባው ለወጡ፡፡ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሮሜ 1፡18-28
ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን የጻፈው እንደ አይሁድ ሁሉ የአሕዛብንም ኃጢአተኛነት በገለጠበት ክፍል ነው፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት እግዚአብሔርን የማያውቁ የአሕዛብ ርኩሰት ነበር፡፡ ዛሬ ግን ወደቤተክርስቲያን ገብቶ ክርስቲያኖችም የሚፈጽሙት ርኩሰት ሆኗል፡፡ ይህም አዲስ አይደለም፡፡ ቀድሞ በእስራኤል ልጆች መካከልም እስራኤል ከእግዚአብሔር ሲርቁና ከመንገዱ ሲስቱ  ማለትም እግዚአብሔርን ትተው ጣኦታትንና ባእድ አማልክትን ሲያመልኩ ክፉ መንፈስ ያድርባቸውና ግብረ ሰዶምን ይፈጽሙ ነበር፡፡ መሳ. 19፡22፣ 1ነገ. 14፡24 ርኩሰቱን በእግዚአብሔር ቤት ጭምር ይፈጽሙት ነበር፡፡ ንጉስ ኢዮስያስ በይሁዳ ላይ ተሐድሶን ሲያመጣ ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የነበረውን የሠዶማውያንን ቤት ማፈራረስ ነበር፡፡ “ሴቶቹም ለማምለኪያ ዐፀድ መጋረጃ ይፈትሉባቸው የነበሩትን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያሉትን የሰዶማውያንን ቤቶች አፈረሰ፡፡” ይላል ቃሉ። (2ነገ. 23፡7) ዛሬም በቤተክርስቲያን እየሆነ ያለው ተመሳሳይ ድርጊት ነው፡፡ በርካታ ሰዶማውያን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ መሽገዋል፡፡ ይህን አስጸያፊ ርኩሰት ለማስወገድ እንደኢዮስያስ ተሐድሶ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ዛሬ በግብረ ሰዶማዊነት የማይታማ የክርስትና ክፍል የለም። ኦርቶዶክሱ ካቶሊኩ፣ ፕሮቴስታንቱና ቤተ ክርስቲያን ለውጥ ያስፈልጋታል ብለው በእውነት ከሚታገሉት አገልጋዮች ጋር ተመሳስለው የገቡና ራሳቸውን ለግብረ ሰዶም ርኩሰት አሳልፈው የሰጡ እንዳሉም እየታየ ነው፡፡ በዚህ ርኩሰት ውስጥ ከተራው ምእመን አንስቶ እስከ መሪው ድረስ ብዙዎች በርኩሰቱ እየተዳደፉ ነው ይባላል፡፡ በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ የፕሮቴስታንት ክፍሎች የግብረ ሰዶማውያንን ጋብቻ እስከ መፍቀድና እስከመባረክ የደረሱ ሲሆን ይህን ያዩ የሌሎቹ የክርስትና ክፍሎች አንዳንድ አገልጋዮችና ተከታዮችም እየተበረታቱ ርኩሰቱን እየተቀላቀሉት ይገኛሉ፡፡ ብዙ ገዳማውያንና መነኮሳት የዚህ ርኩሰት ተጠቂዎች ሆነዋል፡፡ እግዚአብሔር የፈጠረውን መልካም ነገር ማበላሸት ልማዱ ለሆነው ለሰይጣን ሐሳብ እየተገዙም ነው፡፡
አንዳንዶች ይህን ርኩሰት እየፈጸሙ ለዓመታት በሕይወት መቆየታቸው ነገሩ ችግር ስለሌለው ነው ብለው እንዲያስቡ ያደርጋቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን በሕይወት የቆዩት ይህን ርኩሰት እግዚአብሔር ስለፈቀደላቸው ሳይሆን ከላይ በጠቀስነው በሮሜ መልእክት ውስጥ እንደተጻፈው በእግዚአብሔር ላይ በፈጸሙት ኃጢአት ምክንያት እርሱ ከተፈጥሯቸው ውጪ የሆነውንና የማይገባውን ነውረኛ ሥራ እንዲያደርጉ አሳልፎ ስለሰጣቸው ነው፡፡ ከዚህ የበለጠ የእግዚአብሔር ቁጣ የለም፡፡
ግብረ ሰዶማዊነት የሰይጣን አሰራር የሆነ ትልቅ እስራት ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው ከተፈጥሮ ባሕርዩ ውጪ የሆነውንና እንኳን ሊያደርገው ሊያስበውም የማይገባውን ጸያፍ ድርጊት ከተመሳሳዩ ጾታ ጋር መፈጸሙ በሰይጣን ኃይል ስር የመውደቁና ማሰቢያ ህሊናውን የመጣሉ ውጤት ነው፡፡ በማንኛውም መስፈርት ቢታይ ሰው በሌላ ኃይል ቁጥጥር ስር ካልዋለ በቀር ሊፈጽመው የማይችለው ትልቅ አጋንንታዊ እስራት ነው፡፡ ከዚህ ሰይጣናዊ እስራት ለመፈታትና ነጻ ለመውጣት ደግሞ በዋናነት የእግዚአብሔር እርዳታ ያስፈልጋል፡፡ አሊያ በግብረ ሰዶም ርኩሰት ውስጥ የገባ ሰው በቀላሉ ለመውጣት አይችልም፤ ስለዚህ ከዚህ እስራት ለመፈታት የእግዚአብሔርን እርዳታ በጸሎት መጠየቅና ራስን ከሃያሉ ከእግዚአብሔር እጅ በታች ማዋረድ ብቸኛው መፍትሔ ነው፡፡ 
የሚገርመው በዚህ ርኩሰት ውስጥ እየኖሩ ማገልገልና ሰዎችን ማስደነቅ ይቻላል፡፡ አንዳንዶችም  ግብረሰዶምን እየፈጸሙና እያገለገሉ በአገልግሎት አገኘን የሚሉትን “ስኬት” እንደ ሽፋን ለመጠቀም ይሞክራሉ፡፡ እንደ ሽፋን በሚጠቀሙበት “አገልግሎት” ላይ እንጂ ቅድስና ላይ ትኩረት አያደርጉም፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ያለበት አገልግሎት በቅድስና የሚቀርብ አገልግሎት ነው፡፡ ቅድስና በተለየው አገልግሎት ግን እግዚአብሔር ሊኖር አይችልም፡፡ እግዚአብሔር በተለየው አገልግሎትም መንፈሳዊ የሚመስል ነገር እንጂ እውነተኛ መንፈሳዊ ነገርና መንፈሳዊነት አይገኙም። በዚህ ርኩሰት ውስጥ ያሉ አገልጋዮችም ራሳቸውን እንጂ እግዚአብሔርን አያገለግሉም፡፡ እግዚአብሔር በሚጠላውና አጋንንታዊ በሆነ አስጸያፊ ርኩሰት ውስጥ ስላሉ ለራሳቸው ስምን ዝናን ማትረፍ ሀብትንና ንብረትን ማጋበስ እንጂ ሌላ መንፈሳዊ ፍሬ የላቸውም፡፡ በሰይጣናዊው ርኩሰት ውስጥ መኖራቸውን ያላወቁትን ሰዎች መንፈሳዊ የሚመስሉ ነገሮችን እያከናወኑ በማታለል ይሰራሉ፡፡ ከዚህ የተነሳ በግብረ ሰዶማዊነት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ርኩሰታቸውን በሌሎች ጤናማ ክርስቲያኖች ላይ የማስተላለፍ እድላቸውም ሰፊ ነውና ራስን እንዲህ ካለው ርኩሰት በንቃት መጠበቅ ይገባል፡፡
የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ያለው ርኩሰት በመካከላችን እንዳይገኝ ያዘናል፡፡ እንዲህ ያለው ርኩሰት ባለበት ጉባኤ ትልቅ አደጋና መንፈሳዊ ክስረት አለ፡፡ ቅዱስ ቃሉም “የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ፥ ሴሰኛም የሚሆን እንዳይገኝ፥ ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ከዚያ በኋላ እንኳ በረከቱን ሊወርስ በወደደ ጊዜ እንደ ተጣለ ታውቃላችሁና፤ በእንባ ተግቶ ምንም ቢፈልገው ለንስሐ ስፍራ አላገኘምና።” ሲል ከባድ ማስጠንቀቂያ ይሰጣልና እንደዚህ ካለው ርኩሰት ራሳችንን መጠበቅ መራራ ስር እንዳይኖርም እርስ በርስ መጠባበቅ  የያንዳንዳችን ኃላፊነት ነው፡፡ (ዕብ. 12፡15-16)
 እንደዚህ ካሉት ሰዎች ጋር ንሰሃ እስካልገቡና ወደ እግዚአብሔር ጽድቅ እስካልተመለሱ ድረስ መንፈሳዊ ነገሮችን  አብረን መካፈል እንዳይማይገባን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ከሰው ጋር ያለን መግባባትና ፍቅር የእግዚአብሔርን እውነት እስኪያስጥለን ድረስ መታለል የለብንም፡፡ ግብረ ሰዶማዊነት ትልቅ ኃጢአት ነው፡፡ ለማይረባ አእምሮ ተላልፎ መሰጠትና ከእግዚአብሔር ጽድቅ የመለየት ውጤት ነው፡፡

በመጨረሻም ተሃድሶ ዘኦርቶዶክስ ይህን ከአሕዛብ ወደ ክርስትና በሚገርም ፍጥነት እየተዛመተ የሚገኘውንና ቤተክርስቲያንን እጅግ እየጎዳ ያለውን ርኩሰት አጥብቃ ታወግዛለች፡፡ ግብረ ሰዶማዊነትን ስናወግዝ እኛ ኃጢአት የለብንም በሚል ለመመጻደቅ አይደለም፡፡ ሁላችንም ልዩ ልዩ ድካም እንዳለብን ግልጽ ነው፡፡ “ኃጢአት የልብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፤ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም” ተብሎ ተጽፏል፡፡ እንዲሁም “ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።” ተብሏል 1ዮሀ. 1፡8፤ ያእ. 3፡2፡፡ ነገር ግን ግብረ ሰዶማዊነት ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ብቻ ሳይሆን ቤተክርስቲያን ውስጥ እያደረሰ ያለውን ጥፋት ሁሉም እንዲያውቀውና ከዚህ ርኩሰት ራሱንና ቤተክርስቲያንን ለመጠበቅ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የበኩላችንን አስተዋፅኦ ለማበርከት ነው፡፡ ርኩሰቱ ከአጋንንታዊ አሰራር ጋር የተገናኘ ከባድ እስራት ነውና በዚህ ርኩሰት ውስጥ ያሉ አገልጋዮች በቀላሉ የሚላቀቁት አይሆንም፡፡ ስለዚህ ከፍተኛ የጸሎት ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ስለሆነም በዚህ እስራት ውስጥ ለሚገኙና ከዚህ ርኩሰት መውጣት ለሚፈልጉ የጸሎት ድጋፍ ልናደርግላቸው ይገባል፡፡

28 comments:

 1. Thank you guys, great spiritual education. Lord God bless you.............

  ReplyDelete
 2. እግዚአብሄር አምላክ ይባርካችሁ..........በቃሉ ኖረን ህይወት ብናገኝ ዘላለማዊ መንግስቱን ያለ ጥርጥር እንወርሰዋለን.። ብትወዱኝ ትዕሳዜን ጠብቁ። ዮሐ 14፤15 ።

  ReplyDelete
 3. Yihun Meches min enelalen. Negeru kebad new; begziabher qal kemewagat beqer lela amarachi Yelenim. Thank u.

  ReplyDelete
 4. ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ያለውን ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎች ላይ በቁጣ ይገላጣል።

  ReplyDelete
 5. yihe negere betam eyasazenege nebere ene aba... dn.... zemari .... sehafi... ena lelocheme gebere aberecachewe. endihe bale erkuset teyezew eyayen new. egiziabehere yitebeken.

  ReplyDelete
 6. ምንድን ነው ነገሩ የሚወራው እውነት ነው ማለት ነ

  ReplyDelete
 7. I completly agree still I am not agree those who giving service without marriage they are in doubt . I f you want give spritual spritual service you should marry.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Please read 2timotios 2:4

   Delete
 8. what is going on? why don't you tell us clearly? are you better than God? if someone committed this sin you should tell us who he is. aren't you bother for innocent victims? this peoples are very dangerous if they are in the church they will destroy the institution. you should think about more about the glory of God. i heard that one the so called famous deacon is practicing this thing. well if you know it say it. because he is one of the tehadeso persons you shouldn't hide it. if he is mk you spoke about him day and night. be the truthful people not the conditional ones.

  ReplyDelete
 9. አንዳንድ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያንት ፈቅደዋል ብለሀል ታዲያ በኢትዩጵያ ፈቅደዋል ያሳዝናል ለምን ጥላቻ ትፈጥራለህ ኦርቶዶክስ የሆነ ጌይ የለምን በብዛት ስ ኦርቶደክሳዊ የሆነ አይደለም ,በአገራችን የሚፈፅመው

  ReplyDelete
 10. Why you leave about gay Pappas?

  ReplyDelete
 11. Egeziabhier yebarkachew legeziew yemihon kal new benger hulu Geta yerdan bezi west lalachew Amelakachen yekrta aderagi new qen sichemerlachew kehatiyatachew gar tesmameto endayemslachew lenseha new fetnachew ke Egeziabhier gar tarku be etet berket yanesachewal.Geta hulachenem yerdan beteten enthley telat be Egeziabhier beat lay be hayel wotol ermejawen be Eyesus sem enmeta wendemochachen ehtochachen enasemelet.

  ReplyDelete
 12. Egeziabhier yebarkachew le giziew yemihon kal new.

  ReplyDelete

 13. 1
  በአጭር ቃል በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ይወራል የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብስ እንኳ የማይገኝ ነው፥ የአባቱን ሚስት ያገባ ሰው ይኖራልና።
  2
  እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ።
  3-4
  እኔ ምንም እንኳ በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን፥ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፥ ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን እንደዚህ በሠራው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ፤ እናንተና መንፈሴም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር ተሰብስበን፥
  5
  መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።
  1ቆሮ 5 1-5

  ReplyDelete
 14. For which church. Our orthodox tewahido church she is holly . She doesn't have any problem

  ReplyDelete
  Replies
  1. are bakehe lela yeleheme? endet aynetu defar nehe? betam berkata menekosatna diyakonat sedomaweyan mehonachewene atezenga. yilekese mihertu keendezihe ayenetu hatiyat endisewerene meseley yisaleal.

   Delete
  2. I agree with you that our orthodox priests, bishops, monks what have you are the worst example to the people who follows them, they are fooling them, by giving them lip service. Their teaching is hypocritical, all their message is empty with no substance to show for it. I can not think of a single good samarawit act done in my city by our orthodox church in my city, and I have been a member for over 20 years. Yes I do get lip service, nothing to show for. Shame on you!! especially you Menokses who left enat Ethiopia for your comfort. please write and explain your roll in life. I would like a menokse to explain what menokse means?

   Delete
 15. How dear are you?this is the biggest mistake.Don't cover up,yes the Ethiopian church is playing a big role in her backyard,know no one keeps' this secret,Here the day comes u got face it.Shem on u

  ReplyDelete
 16. In orthodox church yes.kelayesketach mk and
  Mk kalhonutem chemer. hatiystegna yalhone yewgerachewo.but every body is a sinner. Amlak degmo yikerta adragi mehari new.beselot merdat yasfelgal enjji sem kaltetera yemilu hamet yetemachew lewere yemotu yerasachewon gudefsayawetu yesew
  yemitayachew nachew.yehn yeteregeme erkuset yemiyaderguten yezih sehuf akrabi yemiyawokwachw kehone anam ergetegna kehonu lemerdat bimokeru.egxiabher b crstiyanen yitebkat.asferi gize new.lejochachenen kezih arena yitebkelen.

  ReplyDelete
 17. You sure our church is holy ? No. If. You closer to the bishops, monks, priests, preachers. Deacons &zemarian you will see. A lot of bad things sin

  ReplyDelete
 18. egziabehere yiker yibelene

  ReplyDelete
 19. eshi min yitebes tadiya

  ReplyDelete
 20. እነደዚህ ዓይነቱ ነገር እንደተባለዉ ዕድሜዉ ብዙ ነዉ፤ ነገር ግን ሳር ቅጠሉ ሁሉ እንደዚያ ነዉ ማለት አዲስ መጤ ዘይቤ ከመሆኑም በላይ ሰዉን ለማሰበርገግ ወይም ማጥቂያ ዓይነተኛ ሚሳኤል ነዉ። አሁን ይህንን ማዉጣታችሁ ምዕመናን እርስ በርስ እንዲፈራሩና ወንጌል ሜዳ ላይ እንዲቀር ነዉን? የዚህ ጸሐፊ የደረሰብህ ነገር ካለ ወይም በዓይንህ ያየሀዉ ካለ ልምድህን ማካፈል ነዉ፤ ለዚያዉም ስም በመጥራት ሳይሆን ለዚያ ለተለከፈዉ ወንድም ወይም እህት እንዲጸለይ፤ አንተም ደግሞ በመገሰጽና በቅርብ መንፈሳዊ ወንድሞች በማስመከር እንዲድን ማድረግ ነዉ እንጂ የስሚ ስሚ አሉባልታ ማስተላለፉ ስራ ፈትነት ነዉ፤ እኔ ብዙ ሰዎች በእንደዚህ ዓይነት ያልተጨበጠ ወሬ አእምሮአቸዉን የሳቱ እንዳሉ አዉቃለሁና እባካችሁ እንደከርስቲያን ሁኑ፤ የሃጢአት ትንሽና ትልቅ የለዉም ሁላችንም በአንድ ወይም በሌላ እንወድቃለንና መረዳዳት ያስፈልጋል፤ ጥርጣሬ በመርጨት ሰይጣንን ማገልገል የባሰ ሃጢያት ነዉ።ጌታ ይርዳንና ከዚህ ዓይነቱ ወጥመድ እንደዚሁም አማረልን ብለን ብለጎችን ከማጣበብ ይሰዉረን።

  ReplyDelete
 21. ምዕመናን ከእንደዚህ አይነቱ ድርጊት እንዲጠበቁ ማስገንዘቢያና ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገቢ ነው፡፡ ኃጢአት ይሸፋፈን ማለት ተገቢ አይደለም፡፡ ኃጢአተኛም በተገኘበት በድንጋይ ይወገር ማለትም ክርስትና አይደለም፡፡ የግብረ ሰዶም ችግር ያለባቸው ሰዎች እርዳታ ሊደረግላቸው፡፡ ሊማሩ እና ንስሃ እንዲገቡ ሊመከሩ ይገባል፡፡ ኃጢአቱ ከባድ መሆኑን እና የእግዚአብሔር ቃል ለማይረባ አእምሮ ተላልፎ የመሰጠት ውጤት ነው ማለቱን መዘንጋት አይገባም፡፡ ታድያ ሰዎቹን እንዴት እንርዳቸው መሰረታዊ ጥያቄ ሊሆን ይገባል፡፡ ኃጢአቱ ላይ መጨከንና ለኃጢአተኛው መራራቱም ያስፈልጋል፡፡ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ማነው ይገለጥልን ትላላችሁ፡፡ ምን ይረባችኃል ይልቅስ እንዲህ ያለው ሰው ንስሀ እንዲገባ መጸለይ አይሻልም፡፡ ሌሎች ደግሞ ኃጢአተን ለማኮሰስ ትሞክራላችሁ ይህም ተገቢ አይደለም፡፡ እኔ በበኩሌ ይሄ ነገር ለምን ተጻፈበት አልልም ሊጻፍበት ይገባል፡፡ የመጨረሻው ዘመን ምልክቶች መካካል ይህ ኃጢአት አንዱ እንደመሆኑ በቸልታ ልናልፈው አይገባም፡፡ ለሁሉም ግን የእግዚአብሔርን ምህረትና ፍርድ በማሰብ የምናደርገውን ነገር ሁሉ ማድረግ ይገባናል፡፡ በዚህ ኃጢአት ያለ ሰው ንስሀ ሊገባ ከፈቀደ የአግዚአብሔር ምህረት ታገኘዋለች፡፡ ያን ለማድረግ ካልፈለገ ግን የእግዚአብሔር ፍርድ ታገኘዋለች፡፡ በወደቀው ሰው ላይ ጭካኔ ማሳየት አይገባም፡፡ ለወደቀውም ሰው አጉል የሆነ እና የእግዚአብሔር ቃል የማይደግፈውን ርህራሄ ማሳየትም አይገባም፡፡ ጠንካሬ አቋም ቢኖር አሊያም ርህራሄ ቢኖር ሁለም ሰውየውን ለንስሃ እንዲያበቃው ለማድረግ ቢሆን ይበጃል፡፡ የራራን መስለን ሰይጣንን እንዳናግዘው እንጠንቀቅ፡፡ ስለዚህ በቅን ልብ ሆነን የችግሩ ተጠቂዎችን ለንስሃ እንጋብዝ፡፡ እምቢ ካሉም የእምቢታቸው ውጤት ምን እንደሆነ እናስገንዝብ፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር ምህረት አሊያም ደግሞ ፍርድ ሊያመልጥ አይችልም፡፡

  ReplyDelete
 22. Mekro astemro alemeles kalu awogezo meleyet enezihen new.wengelen yemisebkuten kemawogez.

  ReplyDelete
 23. ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።
  ወደ ገላትያ ሰዎች 6 : 1

  ReplyDelete
 24. ይቅርታ የሚያስከለክሉ በሚል በረቂቅ የይቅርታ ሕጉ የተዘረዘሩት ወንጀሎች ተሰረዙ ፤ ከተሰረዙት መካከል ‹‹ግብረ ሰዶም›› ይገኝበታል፡፡በሕጉ መሰረት መንግሥት ወደፊት የግብረሰዶም ፍርደኞችን በይቅርታ ሊፈታ ይችላል፡፡
  ‹‹ግብረ ሰዶም ወንጀል ይቅርታ የማያሰጥ ተደርጎ መግባቱ ከሕገ መንግሥቱና ከሕዝብ ሞራል አንፃር ትክክል ነበር፤›› የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ
  ‹‹የተዘረዘሩት ይቅርታ የማያሰጡ ወንጀሎች እንዲወጡ የተደረገው ይቅርታ የማያሰጡ በማለት ዝርዝር ከተጀመረ መቆሚያ ስለማይኖረው ነው›› የፓርላማው የሕግ፣ የፍትሕና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፍትሕ አስተዳደር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አስመላሸ ወልደ ሥላሴ

  (አንድ አድርገን ግንቦት 3 2006 ዓ.ም)፡- የይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ ሥርዓት ረቂቅ አዋጅ ውስጥ ይቅርታ የማያሰጡ የወንጀል ዓይነቶችን የሚዘረዝረው አንቀጽ ሙሉ በሙሉ በሕግ አውጪው አካል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሰረዙ ተሰማ፡፡ ሌሎች ማስተካከያዎች የተካተቱበት ይህ የይቅርታ አዋጅ ባለፈው ሳምንት ፀድቋል፡፡ የረቂቅ አዋጁ ክፍል ሦስት አንቀጽ 14 ንዑስ 1 በሕገ መንግሥቱ ይቅርታ የሚያስከለክሉ ተብለው ከተቀመጡት ወንጀሎች በተጨማሪ ይቅርታ የሚያስከለክሉ ወይም የማይጠየቅባቸው በማለት ከአሥር በላይ ወንጀሎችን ዘርዝሮ አስቀምጧል፡፡ ከእነዚህ መካከል ግብረ ሰዶም፣ ሙስና፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ ሽብርተኝነት መሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸም ወንጀል የመሳሰሉ ይገኙበታል፡፡ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተደረጉት ማሻሻያዎች መካከል የይቅርታ ዓላማን የተመለከተው አንቀጽ አንዱ ነው፡፡ ‹‹የይቅርታ ዋና ዓላማ፣ የመንግሥትና የታራሚዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል መንግሥት ጥፋተኞች በጥፋታቸው የተፀፀቱና የታረሙ መሆኑን በማረጋገጥ ወደ ኅብረተሰቡ ተቀላቅለው አምራች ዜጋ እንደሆኑ ማድረግ ነው፤›› በሚል ተተክቶ አዋጁ ጸድቋል፡፡

  በዚህ መሰረት ወደፊት በአዲስ ዓመት ዋዜማም ሆነ በተለያዬ ሕዝባዊ በዓላት ወቅት መንግሥት ይቅርታ ከሚያደርግላቸው ፍርደኞች መካከል ግብረ ሰዶማውያን ፍርዳቸው እንደ ተራ ወንጀል በመቁጠር ሊለቀቁና ይቅርታም የሚደረግበት የሕግ አግባብ ሊኖር ይችላል ተብሏል፡፡ ይህ መንግሥት በግብረሰዶም ወንጀል ላይ የያዘውን አቋም ምን ደረጃ ላይ እንዳለ ያመላክታል፡፡

  ReplyDelete
 25. www.eotc-mkidusan.org

  ReplyDelete