Tuesday, August 5, 2014

ፍልሰታ ለማርያም እውነተኛ ወይስ የፈጠራ ታሪክ?

Read in PDF

“እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱሳን ሐዋርያት ሲተላለፍ በመጣው ትውፊት በተገለጠው መሠረት በ64 ዓመት ዕድሜዋ በጥር 21 ቀን ዐርፋለች፡፡ መላእክት ሥጋዋን አሳርገው በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አኖሩት፡፡ በዚያው ዓመት ሥጋዋ እስከ ነሐሴ 14 ቀን በገነት ከቆየ በኃላ ነሐሴ 14 ቀን መላእክት አምጥተው ለሐዋርያት ሰጡአቸውና በጌቴሴማኒ ቀበሩአት፡፡ በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ተነሥታ በክብር ወደ ሰማይ ዐርጋለች፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ዕረፍት ትንሣኤና ዕርገት ይህን ታምናለች፡፡ በየዓመቱም ነሐሴ 16 ቀን የፍልሰትዋን መታሰቢያ በታላቅ ሥነ ሥርዓት ታከብራለች (ስንክሳር ነሐሴ 16 ቀን)፡፡”

እንዲህ የሚለው “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮትና የውጭ ግንኙነት” የተሰኘው መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ በብፁዓን ጳጳሳትና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በጋራ የተዘጋጀ ሥራ በመሆኑ የቤተክርስቲያኗ ልሳን ነው። ከዚህ አንጻር ተቀባይነቱ ከፍተኛ እንደሆነ ይታመናል። ይሁን እንጂ በአንዳንድ ሁኔታ ለእግዚአብሔር ቃል ታማኝ ሆኖ አይገኝም። በትውፊት ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የሚጣረሱ ትምህርቶችን በቅዱሳን ሐዋርያት ስም “ከቅዱሳን ሐዋርያት ሲተላለፍ በመጣው ትውፊት” መሠረት እያለ ያቀርባል። መጽሐፉ “ትውፊት ከቅዱሳት መጻሕፍት ምስጢርና ትርጉም ጋር የሚቃረን አይደለም” ቢልም (ገጽ 47) መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት የሌላቸውንና ከጊዜ በኋላ የተፈጠሩ ትምህርቶችን በትውፊት ስም ተቀባይነት እንዲኖራቸው ያደርጋል። ትውፊት አስፈላጊ ነገር መሆኑ ባያከራክርም በክርስትና ትምህርትና ሥርዓት ውስጥ ተቀባይነት ያለው ትውፊት ግን ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ የመጣ ብቻ ሳይሆን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይቃረን መሆኑ ነው፡፡

መጽሐፉ ከላይ የተጠቀሰውን የማርያምን “ከሙታን ለይቶ መነሣትና ወደ ሰማይ ማረግ” ከሐዋርያት ሲተላለፍ የመጣ ትውፊት ነው ቢልም ምንጭ አድርጎ የጠቀሰው ስንክሳር የተባለውን መጽሐፍ ነው። ስንክሳር የቅዱሳንን ታሪክ የሚተርክና ከዓመት እስካመት በዓላቸውን የሚያስተዋውቅ መጽሐፍ ሲሆን፣ ግብጻውያን የቅዱሳን መላእክትንና የጻድቃን የሠማዕታትን፣ የእነርሱንም ፓትርያርኮች በዓል ጭምር እንድናከብርና በዓባይ ወንዝ ሳንጠቀም በበዓላት ብዛት ስራ ፈትተን እንድንኖር አስተምህሯቸውን ያሰረጹበት መጽሐፍ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ መንበረ ፕትርክና እንዳይኖረንና የራሳችንን ፓትርያርክ እንዳንሾም ለ1600 ዓመታት ያህል ሲከለክሉንና ሁልጊዜ በእነርሱ ስር እንድንኖር ያደረጉበት መጽሐፍ ነው፡፡ ሚያዝያ 10 ላይ የሚነበበው ኢትዮጵያውያን ለራሳችን ጳጳስ እንሹም በማለታቸው እግዚአብሔር እንደተቆጣና መዓት እንዳወረደባቸው ተጽፏል፡፡ በቅርቡ ከግእዝ ወደአማርኛ በተተረጎመው ስንክሳር ላይ ይህ ውሸት እንዳለ መቀመጡና በግርጌ ማስታወሻ እንኳ ማስተካከያ አለመደረጉ ቤተክህነቱን ትልቅ ትዝብት ላይ የሚጥለው ሆኗል፡፡ ነጻ ከወጣን ከ50 ዓመት በላይ ያስቆጠርን ቢሆንም አሁንም ግን ነጻነታችንን በሚገባ እንዳላከበርነው የሚያሳይም ነው፡፡

ማርያም እንደ ጌታ ከሙታን ተለይታ ተነሥታለች ወደ ሰማይም ዐርጋለች የሚለው ትምህርት ከሐዋርያት ሲተላለፍ የመጣ ነው ተብሏል፡፡ ከነሐሴ 1-16 የሚጾመው ጾመ ፍልሰታም ይህ ታሪክ የሚዘከርበት ነው፡፡ መቼም ይህ ድርጊት ማለትም የማርያም መነሣትና ማረግ ተፈጽሞ ቢሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይመዘገብ ነበር፡፡ ነገር ግን በአንድም ስፍራ አልተመዘገበም፡፡ ለምን ቢባል? መልሱ ያልተፈጸመ ድርጊት በመሆኑ ነው የሚል ይሆናል፡፡ ለነገሩ መጽሐፍ ቅዱስ የማርያምን ትንሣኤና ዕርገት ቀርቶ ሞቷንም አይናገርም፡፡ ከምንም በላይ ጌታ የሰውን ፊት አይቶ የሚያደላና በዘመድ የሚሰራ ባለመሆኑ እመቤታችን ማርያም እናቱ ስለሆነች ከሰው ሁሉ ቀድማ እንድትነሣና እንድታርግ ሊያደርግ አይችልም፡፡ እርሱ ብቻ ከሙታን በመነሳት በኩር ሲሆን ማርያምን ጨምሮ የቀረው የሰው ዘር በሙሉ ግን በመጨረሻው ቀን እንደሚነሳ ነው መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው፡፡ ስለዚህ ማርያም ተነሥታለች አርጋለች የሚለው ትምህርት እውነተኛ ሳይሆን ከጊዜ በኋላ ሰዎች የፈጠሩት ሐሰተኛ ትምህርት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡

አንዳንዶች ግን ይህን ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ለማድረግ ስለማርያም ያልተነገሩ አንዳንድ የብሉይ ኪዳን ጥቅሶችን በመጥቀስ ለማደናገር ይሞክራሉ፡፡ ስለማርያም የተነገሩ ጥቅሶች ቢሆኑ ኖሮ አንዳቸው እንኳ በሐዲስ ኪዳን ተፈጽመውና የማርያም ከሙታን መነሣትን ወደሰማይ ማረግ ተረጋግጦ ይጻፍ ነበር፡፡ ከሚጠቀሱት መካከል፦
·        “አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት” መዝ. 131፡1፡፡
·        ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ። ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ ውበቴ ሆይ፥ ነዪ። እነሆ፥ ክረምት አለፈ፥ ዝናቡም አልፎ ሄደ።” መኃ. 2፡11 የሚሉት ይጠቀሳሉ።

“አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት” የሚለው የመጀመሪያው ጥቅስ የሚናገረው ስለማርያም ከሙታን ተለይቶ መነሳት ነው የሚሉ ክፍሎች ጥቅሱን ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ጋር በማዛመድ ነገሩን እንድንቀበላቸው ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ይኸውም በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስጋውን መቅደስ ብሎ ጠርቶታል (ዮሀ. 2፡19-21)፡፡ ታቦት ደግሞ ማደሪያ ማለት ነው፡፡ እነዚህን ሁለት በተለያየ ቦታ የተነገሩ ሐሳቦችን ከያሉበት ጠርተው አንድ ላይ በማያያዝና  “አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት” ከሚለው ጥቅስ ጋር እንዲገናዘቡ በማድረግ የጌታ ማደሪያ ማርያም ናትና በዚህ ጥቅስ መሰረት ደግሞ የመቅደሱ ታቦት ማርያም ናት፣ ይህም ጥቅስ ስለ ጌታና ስለ ቅድስት እናቱ ትንሳኤ የተነገረ ነው ሲሉ ሐሳባቸውን ይደመድማሉ፡፡

በቅድሚያ መጽሐፍ ቅዱስ መተርጎም ያለበት አውዱን ጠብቆ መሆን አለበት፡፡ በተለያየ ስፍራ ለተለያየ ዓላማ የተነገሩ ቃላትን በተነገሩበት አውድ መሠረት ሳይሆን እኛ ማራመድ የምንፈልገውን አመለካከት እንዲደግፉለን በሚል ሌላ መልክ የምንሰጣቸው ከሆነ ትልቅ ስሕተት ላይ እንወድቃለን፡፡ ስለ ማርያም ትንሣኤ ተብሎ የተጠቀሰው ጥቅስ መልእክት የሚናገረው ስለሌላ ነገር እንደሆነ ጥቅሱ የተነገረበት አውድ ምስክር ነው፡፡ በዚህ የመዓርግ መዝሙር ውስጥ የተነገረው ዳዊት ለእግዚአብሔር ቤት መሥራት የመፈለጉ ነገር ነው፡፡ ዳዊት “ለእግዚአብሔር ስፍራ፥ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያ እስካገኝ ድረስ ብሎ” በመሀላ ጭምር ስእለት መሳሉን ይናገራል፡፡ ከዚያም “ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን።” ይላል፡፡ ይህም ስለ እግዚአብሔር ማደሪያ ስፍራ እየተናገረ መሆኑን ያሳያል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ነው “አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት” የሚለውን ቃል የተናገረው፡፡ ይህ ቃል ለሌላ ትርጉም የሚተርፍ ክፍል የለውም አንተና የመቅደስህ ታቦት ተነሡ ሲል ስለ እግዚአብሔርና ስለ ታቦቱ እየተናገረ ነው፡፡ እንዲህ ከሆነም ታቦት በመቅደስ ውስጥ ይቀመጣል እንጂ መቅደስ በታቦት ውስጥ ሊቀመጥ አይችልም፡፡ የመቅደስህ ታቦት የሚለውም በመቅደስህ ውስጥ ያለው ታቦት ማለቱ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ስለዚህ ቃሉ እግዚአብሔርና የመቅደሱ ታቦት እንዲነሡ ሲጠይቅ “ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ፥ ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው።” ብሎ በማከል ጉዳዩ በቀጥታ ከመቅደሱ ታቦት ጋር እንጂ ከትንሣኤና ከማርያም ጋር የሚያያዝ ነገር እንደሌለው ያሳያል፡፡ ከቃል ኪዳኑ ታቦት ጋር በተያያዘ ታቦቱ ጉዞ ሲጀምር ሙሴ “… አቤቱ፥ ተነሣ ….” ይል እንደነበር ተጽፏል (ዘሁ. 10፡35)፡፡ በዚህ የመዝሙረ ዳዊት ክፍልም የተነገረው በተመሳሳይ ሁኔታ ነው፡፡ ስለዚህ ተፈጽሞ ያልታየን ትንቢት እንደ ትንቢት ማቅረብ ስህተት እንጂ ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡ ሰዎች ከልባቸው አፍልቀው ማርያም ተነስታለች አርጋለች ላሉት የስህተት ትምህርታቸው ልብን ሞልቶ የሚያናገር ማስረጃ ከመጽሀፍ ቅዱስ ስለማያገኙ ከመጽሀፍ ቅዱስ በተወሰዱ ቃላት ላይ ቁማር በመቆመር ማርያም ተነሥታለች አርጋለች ለማለት ይዳዳቸዋል፡፡

ሁለተኛው ማስረጃ ተብሎ የሚጠቀሰው ደግሞ ውዴ እንዲህ ብሎ ተናገረኝ። ወዳጄ ሆይ፥ ተነሺ ውበቴ ሆይ፥ ነዪ። እነሆ፥ ክረምት አለፈ፥ ዝናቡም አልፎ ሄደ።” የሚለው የመኃልየ መኃልይ ቃል ነው፡፡ በዚህም ጥቅስ ውስጥ “ተነሺ” የሚል ቃል ስላለና ክረምት አለፈ ስለተባለ ክረምትን ከመከራና ከሞት ጋር በማያያዝ ተነሺ ማለትንም ከማርያም ትንሳኤ ጋር በማያያዝ ስለማርያም ትንሣኤና ዕርገት እንደተነገረ አድርገው ነው የሚጠቅሱት፡፡ በመሰረቱ ይህ በሁለት ፍቅረኛሞች መካከል የቀረበ ንግግር ነው፡፡ ቃሉ መተርጎም ያለበትም በዚሁ መንገድ ነው፡፡ በመኃልየ መኃልይ ውስጥ ያለውን ቅኔ አባቶች በብሉይ ኪዳን አውድ በእስራኤልና በእግዚአብሔር በሐዲስ ኪዳን አውድ ደግሞ በክርስቶስና በቤተክርስቲያን መካከል ያለውን ኅብረት ያሳያል በሚል እንደሚተረጉሙት ይታወቃል፡፡  ከዚህ አልፎ ግን በተለይ ለማርያም ሊሰጥ የሚችልበት አግባብ አይኖርም፡፡ ይህ ጥቅስ እንደተባለው  ስለማርያም ትንሳኤና እርገት ተነግሮ ቢሆን ኖሮ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተፈጽሞ ባየነው ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን የፈጠራ ታሪክ ተፈጽሞ የምናገኘው በስንክሳር ውስጥ መሆኑ ትምህርቱን መጽሐፍ ቅዱስም ቅዱሳን ሐዋርያትም እንደማያውቁት ያመለክታል፡፡

የማርያም ትንሣኤና ዕርገት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት የሌለው የፈጠራ ትምህርት ስለሆነ በመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ለማስደገፍ መሞከር አደገኛና በእግዚአብሔር ቃል ላይ መዋሸት ይሆናል፡፡ ከዚያ ይልቅ እዚያው አዋልድ መጻሕፍት ውስጥ የትምህርቱን ምንጭ መፈለጉ ይሻላል፡፡ ከሁሉም የሚያሳዝነው ግን ጾመ ፍልሰታ ባልተከናወነ የፈጠራ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ጾም መሆኑ የምንዘክረው ሐሠተኛ ታሪክን ነውና ምንኛ ምስኪኖች ነን!! ጾም መልካም ነገር ነው፡፡ ነገር ግን በምን ምክንያት እንደምንጾም ካላወቅን፣ ጾማችን አላማ ቢስ ይሆናል፡፡

ለሁሉም ግን ጾመ ፍልሰታ የተባለው ጾም እውነተኛ ታሪክ ምንጩ መጽሐፍ ቅዱስ አለመሆኑን ተረድተን የተነገረውን የፈጠራ ታሪክ እያሰብን ሳይሆን እግዚአብሔርን እያሰብን፣ ስለሃጢአታችን ንስሐ እየገባንና የመንፈስ ቅዱስን ሃይል ለመቀበል እየተዘጋጀን በእግዚአብሔር ፊት ብንጾምና ብንጸልይ ብዙ በረከት ወደ ሕይወታችን ይመጣል፡፡ እውነትን ከሐሰት፣ የከበረውን ከተዋረደው፣ የእግዚአብሔርን ከሰይጣን እንድንለይ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጠን፡፡

45 comments:

 1. aba selama yalgebah neger ale ye egziyabher fekad,chernet ejiki bizu new be metsafi kidus keseferew belay .kemetsaf kidus behiola bemidr lay ejik yemidenki neger tedergolinal .ye kidist dingil mariyam menesat ligermachu ayigebam . yashashalachut neger binor mk new tsomun yawejew alemaletachu libachun yekefete egziyabher yimesgen .

  ReplyDelete
 2. Hulem talekisaleh silemayimeleketih neger ewnetu yihe new.

  ReplyDelete
 3. ማስተዋል የጎደለህ አንተ ሰው;ተመልከት ብዙ ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ;ለምሳሌ እኔ የምኖረው አውሮፓ ውስጥ ነው አውሮፓውያን ለምሳሌ እኔ ከምኖርበት ሀገር እመቤታችን ያረገችበት ዕለት ብሔራዊ በዓል ነው።እና እንደ አንተ ድን ቁርና ከሆነ ፈረንሳይ የእመቤታችንን የፍልሰትዋን መታሰቢያ .ብሔራዊ በዓል አድርጋ የምታከብረው ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወስዳ ነው።አይ መናፍቅ ሁሉን እንደተጠራጠራችሁና ከእመባታችን ጋር እንደ ተጣላችሁ ፀሐያችሁ ሊጠልቅ ነው።በመጽሐፍ ቅዱስ እንካዋን እመቤታችን ያደረገችው ይቅርና ጌታችን ያደረገው አብ ዛኛው አንዳልተጻፈ፥ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌል"ጌታችን ያደረገው ሁሉ ቢጻፍ ምድር ዓለም ሊሸከሙት አንደማይችሉ ጽፎልናል"በከንቱ አትድከም ሳንጠራጠር የእመቤታችንን የፍል ሥታ መታፍስቢያ እናከብራለን

  ReplyDelete
 4. Ante Menafik Sitihon Lemin Sele Orthodox eminet menager dadah! Min meseleh tikis eyefelek sitimeramer bizuwoch be eminet Ye egziabherin mengist agegnu. silemariam mekeber abiziteh tikochaleh...orthodox ledingil mariam kibir bitiset belijua yetenesa new....ke hulu merto silakeberat siladerebat...

  ReplyDelete
 5. " ግብፆች በዓባይ ወንዝ ሳንጠቀም በበዓላት ብዛት ስራ ፈትተን
  እንድንኖር አስተምህሯቸውን ያሰረጹበት መጽሐፍ ነው፡፡"

  የግብፅ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ለምን ይሆን ? የእመቤታችንን የቅድስት፣ ንጽሕት፣ ድንግል ማርያም /የወላዲተ አምላክን/ ትንሳኤዋንና በዓሏን የሚያከብሩት? እኮ! ለምን ይሆን? መልሱልኛ!
  አይ ሞኝነትና አላዋቂነት! የድንግል ልጅ ማስተዋሉን ያድለን።

  ReplyDelete
 6. ene haimanotem migbarem endaboteche newu, mela sewuneten bemeskal amsal, amatibalehu zor bel saitan!!!!!!!!

  ReplyDelete
 7. መቼም ይህ ድርጊት ማለትም የማርያም መነሣትና ማረግ ተፈጽሞ ቢሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይመዘገብ ነበር፡፡ ......ለነገሩ መጽሐፍ ቅዱስ የማርያምን ትንሣኤና ዕርገት ቀርቶ ሞቷንም አይናገርም፡፡

  አንተ ከንቱ!!!! ታዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ መሞቷ ስላልተመዘገበ እመቤታችን አልሞተችም ማለት ነው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ብዙ ነገር እንዳለ ሁሉም ቢጻፍ ዓለም ራሷ እንደማትበቃ አልተጻፈም ግን ለምን እንኳን ድንግል ማርያም አንተ ሳይገባህ ድንቅ ታምር ተደረገልኝ እያልክ ባዶ አዳራሽ አፍህን ስትክፍ ትውል የለ እንዴ ምነው ለቤተ ክርስቲያን ውጋት ሆናችሁ! አለማወቅህ የሚታወቀው በራስህ ጽሁፍ ነው፡፡ ድግሞ እኮ ‹‹እመቤታችን›› ትላለህ አያምርብህም፡፡ አየህ ሰው የማያምበትን ሲናገር ወይም ሲጽፍ አፉ ላይ እንደ ዘንጋዳ ቂጣ ሲፈረፈር ይታወቅበታል፡፡ ደካማ!!!!!!አንተ ከንቱ!!!! ታዲያ በመጽሐፍ ቅዱስ መሞቷ ስላልተመዘገበ እመቤታችን አልሞተችም ማለት ነው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ብዙ ነገር እንዳለ ሁሉም ቢጻፍ ዓለም ራሷ እንደማትበቃ አልተጻፈም ግን ለምን እንኳን ድንግል ማርያም አንተ ሳይገባህ ድንቅ ታምር ተደረገልኝ እያልክ ባዶ አዳራሽ አፍህን ስትክፍ ትውል የለ እንዴ ምነው ለቤተ ክርስቲያን ውጋት ሆናችሁ! አለማወቅህ የሚታወቀው በራስህ ጽሁፍ ነው፡፡ ድግሞ እኮ ‹‹እመቤታችን›› ትላለህ አያምርብህም፡፡ አየህ ሰው የማያምበትን ሲናገር ወይም ሲጽፍ አፉ ላይ እንደ ዘንጋዳ ቂጣ ሲፈረፈር ይታወቅበታል፡፡ ደካማ!!!!!!

  ReplyDelete
 8. እክህደከ ሠይጣን ። ጾም ፍስለታ በመጣ ቁጥር አባ ሰላማን የሚያስተዳድረው ሉሲፈር ቁጣው ጣሪያ ይደርሳል ። አስታውሳለሁ ባለፈው አመት በተመሳሳይ ጊዜ በፃም ወቅት ይህ ሰይጣናዊ የሆነ ብሎግ ባወጣው ወላዲተ አምላክን በሚሰድበው ጹሑፉ ላይ በቂ መልስ ተሰጥቶ ነበር። ነገር ግን ያዳቆነ ሠይጣን መች ይለቅና። ይሄው ተመልሶ መጣ። የገሀነም ደጆች አይችሉአትም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. እየምሮው የጨለመበትን ሰው ምንም ሊደረግ አየችልም ከላይ እርዳታ እኪመጣለት ድረስ ዮሀንስ 6 ላይ አየሱስ እንዳለው ህዝቡ ተአምርም ቢያዩ የእግዚአብሄርንም አጀንዳ ቢነግራቸው ትተውት የሄዱት የአብ መሳብእኪሆንላቸው ነበር “ አብ ካልሳበው በቀር ወደ እኔ የሚመጣ የለም፡፡”

   Delete
 9. በደንብ መናፍቅነት ነው::አንተ የምትለው ነው ከመጽሐፍ የወጣ::በአዉሮፓ በፈረንሣይ;በበልጅየም,ወዘተ,የእመቤታችን የፍልሰቷ ቀን ብሔራዊ በዓል ሆኖ ዝግ ነው::እንዳንተ ፈጠራ ከሆነ ይህንን እንዲያከብሩት ያደረጉት አጼ ዘርዓ ያዕቆብ ከኢትዮጵያ በስልክ ደዉለው ነግረዋቸው ነው:በአውሮፓ በአሜሪካ ሁሉ በኛ ነሐሴ 9 በፈረንጆች ነሐሴ 15 ፍልሰታ(Assoption) ተብሎ የሚከበረው?አፍረተ ቢስ ሐሰተኛ ለመሆንህ ይህ ብቻ በቂ መረጃ ነው::እንዲያዉም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀን ተብሎ አልታወጀ;በቤተ ክርስቲያናችን ብቻ ነው የምናከብረው::እንዳተ ፈጠራ ወሬ እነ ኣጼ ዘርዓ ያዕቆብ ከፈረንጆች ጋር ተነጋግረው;እንደ ዉሀ ፈሳሽ እንደ እንግዳ ደራሽ ዛሬ የእመቤታችን ፍልሰታ ብለን እናክብር ብለው አወጁ እያልከን ነው,ያለ ምንም ታሪክ?እምታሞኘውን አሞኝ:ይህ ፈጠራ ወሬ ይቅርብህ::ሌላው ጌታችን"በኔ የሚያምን እኔ የማደርገዉን ያደርጋል ባለው መሠራት"ዮሐ14:12:እርሱ ሙቶ ነፍሳትን ከሲኦል እንዳወጣ;እርሷም ሙታ ነፍሳትን ከሲኦል አወጣች::ሞት በጥር ነሔሴ መቃብር አይደለም 66 ዓመት እንቅልፍ እንዲተኛ የሚያደርግ ልጅ ነው ያላት እመቤታችን::ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ"አባት ሆይ ፈቃድህ ቢሆን ይቺ ጽዋ(ሞት) ከእኔ ትለፍ" እንዳለ እመቤታችንም ሆኑ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይህ የሞት ጽዋ ከእኔ ትለፍ አሉ ቢባል ምኑ ነው ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚጋጨው?ጌታችንም ፈርቶ አይደለም እንዲህ ያለው;እመቤታችንም ፈርታ አይደለም እንዲህ ያለችው::በዚህ መልኩ የአንተ ነው እንጂ ፈጠራ የ እመቤታችን ታሪክ ግን በዓለም ያለው ታሪክ ተመሳሳይ ነው::"ማንም የለም" የሚለው አነጋገር:እመቤታችንን ለመጨመሩ ምንም መርጃ የለህም::እስኪመጣ ድርስም ሞትን የማይቀምሱ አሉና::በቃህ

  ReplyDelete
 10. found this Not only on Ethiopian Orthodox,but all Eastern Orthodox, Oriental Orthodox, certain Anglican Church and yes the Catholic Church believe the physical ascending of saint Mary to Heaven. The assumption of Saint Virgin Mary:By the authority of our Lord Jesus Christ, of the Blessed Apostles Peter and Paul, and by our own authority, we pronounce, declare, and define it to be a divinely revealed dogma: that the Immaculate Mother of God, the ever Virgin Mary, having completed the course of her earthly life, was assumed body and soul into heavenly glory.........More elaborated in the Encyclopedia. I thank the writer for help me dig and read more about it. Now I go by what my church stands. Nevertheless we should encourage people to write if they have different opinion so we can look at it rather than succumb to attacking and labeling

  ReplyDelete
 11. የማያመሰኳ እንስሳ የዋጠውን መልሶ እንደማይደቀው መልሶ መላልሶ እንደማያኝከው ሁሉ መናፍቃንም አንድ ጥቅስን በሆነ መንገድ ጎርሰው ከዋጡት በኋላ ምስጢር አያመላልሱም ፤ ደጋግመውም አያኝኩትም ማለትም የሚመላለሱ ምስጢራትን አያገኙም፡፡ ዳግመኛም ሰኮናቸው ስላልተሰነጠቀ መሬት አይቆነጥጡም፤ ሃይማኖቱንም በምግባር አይኖሩትም፤ እንዲሁ ሲያደናግሩ ይኖራሉ እንጂ፡፡ ይህም ማለት እንደ ገመል ገዝፈው ብናያቸውም ለሰኮናቸው የሚስማማ አሽዋ ( ያልረጋ ልቡና ) ፈልገው በዚያ ይኖራሉ እንጂ እንደ ሌሎቹ ቆንጥጠው ረግጠው ገደልና ተራራ አይሻገሩም፤ ሃይማኖት አቀበትን ሊወጡ ገደላ ገድል ተጋድሎዎችንም አልፈው ለምስጢር ለክብር ሊበቁ አይችሉም፡፡ አሁንም ከላይ የመደንገጥና የመረበሽ ስሜት የታየባቸው አሉ ያልኩት በሃይማኖት ገና ያልረጋና እንደ አሸዋ የሚንሸራተት ልቡና ካለ የመናፍቃን ድፍን ሰኮና ይረግጠዋል የበለጠም ያንሸራትተዋልና ሁላችንም ብንሆን ልቡናችን ለማጽናት እንድንጥር አብሮ ለመጠቆም ነው፡፡

  ከዚሁ ከሚበላውና ከማይበላው ሳንወጣ በባሕር ውስጥ ስላሉት እንድንበላቸው የታዘዙት ቅርፊትና ክንፍ ያላቸውን ነው፡፡ ይህም ማለት ቅርፊት ለባሕር ፍጥረታት ጋሻ መጠበቂያቸው እንደሆነ ሁሉ የሃይማኖት ጋሻ ወይም ከመናፍቃን የኑፋቄ ጦርና የክህደት መርዝ ለመዳን የሃይማኖትና የምግባር ጋሻ ከሌለና በክንፋችው ወደ ባሕሩ ላይኛው ክፍል ድረስ እንደሚንሳፈፉበትና ወደ ታች ብቻ እንደ ድንጋይ እንዳይዘቅጡ እንደሚጠበቁበት በመንፈሳዊነትና በንጽሕና ክንፍ ወደ ከፍተኛው የእግዚአብሔር ምስጢራትና መረዳት የማይወጡ እንደ ድንጋይ በከበደ በዚህ ዓለም ፍልስፍናና ሥጋዊ ሙግት ወደ መሬት መሬታዊነትና ሥጋዊነት የሚዘቅጡት መናፍቃን ‹‹ ርኩሳን›› ከሚባሉት መመደባቸውን አውቆ መጠበቅ ተገቢ ነው፡፡ እንዳልኩት እነርሱ ከዘመን አመጣሽ ሀሳብና ፍጹም ካልተማሩ ሰዎች ሀሳብና ክህደት የሚጠበቁበት ቅርፊት (ጋሻ) የሌላቸው ናቸውና፡፡ እንዲያውም አንዳንዶቹ ሲሉ እንደሚደመጡት‹‹ አስኳሉን እንስጣችሁ ስንላቸው ቅርፊቱን አትንኩብን አሉ›› (በኤግዚቢሽን ማዕከል በተደረገው የተሐድሶዎች ልፈፋ ላይ አንድ አባ ተብየ የተናገረውን ያስታውሱ) እያሉ ቅርፊቱ አስኳሉን የያዘውና የሚጠብቀው መሆኑን እንኳ ማሰብ አቅቷቸው ቅርፊት መጠበቂያ የሌላቸው ብቻ ሳይሆኑ ካላቸውም ላይ መስበር የሚፈልጉ መሆናቸውን ነግረውናል፤ ራሳቸው መሆናቸውንም መንፈስ ቅዱስ አፋቸውን ጸፍቶ አናግሯቸዋል፤ በራሳቸውም ላይ አስመስክሯቸዋል፡፡ ስለዚህ ክርስቲያኖች ነጹሐን የሚበሉ (አምላካቸው የሚቀበላቸው) የሚሆኑት ጥርጥርንና ክህደትን ይህንም የመሰለ የመናፍቃንን የመዘባበትና የክህደት ጦር የሚከላከል በቅርፊት የተመሰለ የሃይማኖት ጋሻ ሲኖራቸው ነው፡፡ ከጋሻዎቻችን ዋናው ደግሞ የሃይማኖታችን ነገር የቅዱሳት መጻሕፍትንም ምስጢር ለብሶ ማለትም አውቆ መገኘት ነውና ጊዜ ወስዶ ቁጭ ብሎ መማር እንኳ ባይቻል በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ልቡናን ከፍቶ በወሬና በአሉባልታ ሳይጠመዱ መማር መጠየቅና እንደተገለጸው እያመላለሱ እያኘኩ እያጠኑ መያዝ ተገቢ ነው፡፡ ከዚህም በላይ በሃይማኖት ልብን ማጽናት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ነገር ነው፡፡ ያ ከሆነ ጠይቀን ያልገባንና የማናውቀውን እስከምንረዳ ድረስ ጊዜ እናገኛለን፡፡ ነገር ግን ብዙዎቻችን ትእግስት የለንም፤

  ReplyDelete
 12. እንደ ይሁዳ ስሙን የሚቃረን ግብር ሁልጊዜም የሚሠራውና ራሱን ‹‹ አባ ሰላማ ›› ብሎ የሚጠራው የተሐድሶዎች ብሎግ አንድ የሚያስደንቅ ጽሑፍ ሰሞኑን አስነብቦናል፡፡ የሚያስደንቅ ያልኩት ራሴን ባስደነቁኝ ሦስት ምክንያቶች ነው፡፡ የመጀመሪያው ለርእስነትና ሐሳቡን ለማስተላለፍ መሪ አድርጎ የተጠቀመው ጥቅስ መልእክቱ ከነገረ ጉዳዩ ያለውን ርቀትና አንድ ሰው ከካደ በኋላ ጥቅሶችን እስከምን ድረስ ሊያጣምም እንደሚችል ሳስብ አሁንም እደነቃለሁ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ ክርስትና ከተመሠረተበትና በይፋ በብዙዎች ተቀባይነት እያገኘ ከመጣበት ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ብዙ የዓይን ምስክሮች አይተው ያስተላለፏቸውን ትውፊቶች ሁሉ ምን ያህል እንደሚጠሉ ሳስብ በዚያ ዘመን የነበሩ አይሁድ በአካለ ሥጋ የመመለስ እድል ገጥሟቸው ቢጠየቁ እንኳ ‹‹ እንዴት ከእኛ በላይ ጠላችኋቸው›› ብለው የሚገረሙባቸው ስለሚመስለኝ እደነቃለሁ፡፡ ሦስተኛውና ሁልጊዜም ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ ተሐድሶዎች የምደነቀው ደግሞ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብና ማኅበረ ቅዱሳን ላይ ባላቸው ጥላቻ ነው ፡፡ አስተውሎ ለሚያይ ሰው ጽሑፍ ነክ ነገር ላይ ከተነሡ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን ወቅታዊ ነገር ላይ ከተነሡ ማኅበረ ቅዱሳንን አንዳንድ ጊዜ ሁለቱንም አንድ ላይ ካላመቼም የሚጽፉበትን ሰው ማኅበረ ቅዱሳን ወይም ዘርዐ ያዕቆብ ነክ አድርገው ካላቀረቡ መንፈሳቸው የሚቀጣቸው ይመስለኛል፡፡ ዓለም አቀፍና ልዩነት የሌለበት የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ነባር ትውፊቶች መካከል አንዱ የሆነውን የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት ለዘርዓ ያዕቆብ መስጠት ማለት ምን ያህል ድፍን ቅልነት ይሆን? እንዲህ የምለውና የምደነቀውም ብዙ ጊዜ የስሕተትና የክህደት ጽሑፍ ቢጽፉም እውነቱ የያዙትና በዚያም እንጸድቃለን ብለው የሚያስቡና ለዚያም ለመሰላቸው የሚተጉ ይመስለኝ ስለነበረ ነው፡፡ ይህን ጽሑፍ ሳየው ግን ‹‹ ኦርቶዶክስን እንዴት እናስጠላለን፤ ሰውንስ ከእምነት እንዴት እንለያለን?›› በሚል መንፈስ ብቻ እንደሚሠሩ ስለተረዳሁ ነው፡፡ አሁን አሁንማ እንደ መሸታ ቤት በየሥርቻው በከፈቷቸው ብሎጎቻቸው ዓይን ያወጣ ስድብና ምንም ዓይነት መሠረት የሌለው የስም ማጥፋት ቅርሻቶቻቸውን በመትፋት ላይ መሆናቸውን ሳይ አውሬው ብስጭቱ እየጨመረ የመጣው ወደፊት ሰማዕትነትን አይቶ እየፈራ ይመስላል ፡፡  በርግጥ ይህ ብሎግ በመኖሩ ‹‹ ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው›› /ራእ 13፤ 5/ ተብሎ የተነገረለት አውሬው ሥራውን እያበረታ መሆኑን እናያለን፡፡ በማያቋርጠው የሐሰትና የጠብ ፤ የስድብና የስም ማጥፋት እንዲሁም የኑፋቄና የክህደት ጽሑፎቻችሁም ‹‹ እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ ›› /ራእ 12 ፤ 15/ የተባለውን አውሬው በገቢር የሚያሳይባችሁ የክሕደትና የኑፋቄ የአውሬው የትፋት ወንዞች መሆናችሁን ታረጋግጡልናላችሁ፡፡ ነገር ግን ‹‹ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው ›› /ራእ 12 ፤16/ ተብሎ እንደተጻፈው ምድር ቤተ ክርስቲያን የእናንተን የክህደት መርዝ ታሰርገዋለች ፡፡ አሁንም እንደተለመደው ሁሉ ስሕተቶቻችሁን ከማሳየት እንጀምር፡፡  አውሬ ያበከተውን አትብሉ  በመጽሐፍ ‹‹በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን አውሬም የሰበረውን አይብላ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ›› /ዘሌ 22 ፤ 8/ ተብሎ እንደተጻፈ አውሬ ያቆሰለው ደሙን መጥጦ ያበከተው የጫረው ሁሉ እንዳይበላ በኦሪቱ ታዝዟል፡፡ በላይኛው አንቀጽ ላይ ደግሞ አውሬው ማን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ነግሮናል፡፡ አንድ ሰው በጉ ወይም በሬው የእርሱ ቢሆንም አውሬ ሊበላው ጭሮ ካቆሰለው ደሙን መጥጦ ከገደለው እንዳይበላው እንደተከለከለው ሁሉ ለሕይወታችን ምግብ በአምልኮታችንም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገን ከምናቀረበው ከመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት አንዱን ለይተው ልክ አውሬ በጉን ከመንጋው ለይቶ እንደሚበላው ወይም እንደሚያቆስለው አውሬ የተባለ መናፍቅም ወይም ከሐዲ ከእናቱ ወይም ከመንጋው ለይቶ በተሳሳተ ትርጉም ያቆሰለውን ወይም የጫረውን ወይም በክህደት አስተምህሮ የገደለውን መብላት ለእኛ የተከለከለ ነው፡፡ በኦሪቱ ትእዛዝ እንዳየነው በጉ ንብረትነቱ የሰው ቢሆንም አውሬ ስለነካው ብቻ እንደተከለከሉት ጥቅሱ የእኛውና ከእኛው መጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደ ቢሆንም አውሬ መናፍቅ በጥርጥርና በክህደቱ መርዙ የወጋውን በልተን እንዳንጎዳ የተከለከለ ነው፡፡ ስለዚህም ጥቅስን እኛ ለነፍሳችን የምንመገበው በአውሬ መናፍቃን ትምህርት ያልተጫረና ያልረከሰ ሲሆን ብቻ መሆኑን ማስተዋል አስፈላጊ ነው፡፡ ስለዚህ መናፍቃን በተሳሳተ መንገድ ያጣመሙትን ሁሉ ለነፍሳችን ማቅረብ ራስን መቅጣት መሆኑን ማወቅና መጠበቅ ተገቢ ነው፡፡

  ለምሳሌ እመቤታችን አልተነሣችም አላረገችም ብሎ ለመካድ የግድ ጥቅስም የሚያስፈልገው አልነበረም፡፡ ‹‹ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም ›› / ዮሐ 3 ፤13/ የሚለውን ጠቅሶ እጂግ በተዛባ መንገድ እመቤታችን አላረገችም ለማለት መጥቀስ ልክ በበጎቹ አውሬ እንደሚያደርገው የበጉን ደሙን ( የጥቅሱን ነፍሱን ምስጢሩን ወይም ዋና መልእክቱን ) መጥጦ ገድሎ አበክቶ መስጠት ነው፡፡ ቀጥታ በዚህ መንገድ እንተርጉመው ካልንማ መጀመሪያውኑ የሚለው ወደ ሰማይ የወጣው ከሰማይ የወረደው ከሆነ ክርስቶስ ያረገው በተዋሐደው ሥጋ ነውና በውኑ ሥጋውን ከሰማይ ይዞ ወርዷልን? እንዲህማ ከሆነ የሰው ልጅ ተብሎስ እንዴት ሊጠራ ይችላል? እንዲህማ ከሆነ የራሱ ትምህርትና ንግግርም ሆነ ስለ እርሱ ሐዋርያትና ሊቃውንት ያስተማሩት ሁሉ ከንቱ ሆነ፡፡ ከሰማይ በውረድማ ከሆነ መላእክቱን እንኳ ብንተዋቸው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ሦስተኛ ሰማይ የተነጠቀው ጥንቱን ከዚያ ቢመጣ ነውን? ወይስ ሔኖክና ኤልያስ ያረጉት ድሮውንም ከሰማይ የወረዱ በመሆናቸው ነው? ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ወርደው ያልተመለሱም አሉ፡፡ ለይስሐቅም ምትክ ሆኖ የተሰዋው ከሰማይ የወረደ ነበር፡፡ ለኤልያስም እንጎቻ በመሶብ ውኃም በማሠሮ ወርዶለት ነበረ፡፡ ጥቅሶችን የምትተረጉሙት እንደዚህ ከሆነ ‹‹ እኔ ስለ እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር ምስክሬ እውነት አይደለም ›› / ዮሐ 5 ፤ 31/ የሚለውንስ ምን ትሉለታላችሁ? በእውነት ጥቅስን እንዲህ ያለ ቦታውና ያለመልእክቱ መጠቀም በገዳመ ቆሮንቶስ ለጌታም ጥቅስ እየጠቀሰ ለመፈታተን ያላፈረውንና አሁንም ይህን ከማድረግ የማያፍረውን የማይሰለቸውንም ዲያብሎስን ያስመስላችሁ ወይም በእርሱ መንፈስ የምትሠሩ ፈታኞች መሆናችሁን ታረጋግጡ ካልሆነ በቀር የምትፈጥሩት ነገር የለም፡፡ ልክ ክፉ አውሬ በጉን ከመንጋው ለይቶ አድክሞ ይዞ ደሙን መጥጦ እንደሚገድለው ጥቅስንም ከመጽሐፍ ቅዱስ ከመንጋውና ከመልእክቱ ለይቶ ምሥጢር ደሙን መጥጦ በማብከት ተሐድሶዎችን የሚተካከል ያለ አይመስለኝም፡፡

  ReplyDelete
 13. ይህ ጥቅስ የተጠቀሰለት ዳግም የመወለድ ምስጢር ረቅቆበት አልገባው ላለው የአይሁድ መምህር ኒቆዲሞስ ነው፡፡ ከጥቅሱ ጌታችን ኒቆዲሞስን ከነበረበትም ዕውቀትና እምነት ከፍ እንዲልና ታላቁን ምሥጢረ ሃይማኖት እንዲረዳ እያደረገው እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ በፊቱ ቆሞ የሚያነጋግረው ጌታ ዕሩቅ ብእሲ ሳይሆን ከሰማይ አካላዊ ቃል መጥቶ በተዋሕዶተ ትስብእት የተገለጠ መሆኑንና በሚያየው ትስብእት ውስጥ የማያየው መለኮት ተዋሕዶ መኖሩን ትስብእትም ለዚህ የበቃው በተዋሕዶ እንጂ እንደ ቀደሙት ነቢያት በጸጋ አለመሆኑንና የባሕርይ አምላክ መሆኑን ነበር ያስረዳው፡፡ በርግጥም ወልደ እጓለመሕያው ጌታ ራሱን አምላክ ያደረገ ፍጡር አይደለም፡፡ አምላክነት ከጥንት ገንዘቡ ነው፤ ነገር ግን ይህን ሰማያዊነት፣ ቀዳማዊነትና፣ ፈጣሪነት፣ ሁሉን ማወቅና ከመወሰን ሳይወጡ መምላት፣ ከመግዘፍ ሳይወጡ መርቀቅ ( ቀድሞ በሰማይ የነበረውን) ትስብእት ወይ ሥጋ የወረሰው በተዋሕዶ ከቃል ነውና ‹‹ ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም›› ሲል እውነተኛ ተዋሕዶውን አረጋገጠልን፡፡ ጥቅሱ ራሱ የሚፈጸመው ‹‹ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው ›› በሚል ሐረግ ነው፡፡ ጌታ ራሱ በኒቆዲሞስ ፊት ሆኖ እያነጋገረው እያለ ራሱን ‹‹ በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው›› ሲል የጠቀሰው በዚያው ቅጽበት ወይም ቃል ሥጋን ከተዋሐደበት ቅጽበት ጀምሮ ሥጋ ቅድመ እርገትም በየማነ አብ በዘባነ ኪሩብ በክብር ያለና ፍጹም አምላክ መሆኑን ሲያስረዳው ነው፡፡ ምክንያቱም ከእርሱ ጋር ሲነጋገር ቢየየው በሰማይ የሌለ እንዳይመስለው ተዋሕዶውንና አምላክነቱን ለማስረዳት የተናገረው መሆኑን በዚህ ማረጋገጥ እንችላለን፡፡ እንደዚህማ ባይሆንና ጥቅሱ ለጌታ ለዕርገቱ የተነገረ ቢሆን ኖሮ ‹‹ አሁን በሰማይ የሚኖረው›› ለምን ይለዋል፡፡ ገና አላረገም ነበርና፡፡ ስለዚህ ጥቅሱ ከእመቤታችን ዕርገት ቀርቶ ከጌታም ዕርገት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ፡፡  ለመሆኑ የእመቤታችን ዕረፍት፣ ትንሣኤና ዕርገትን ያሰተማሩና የሰበኩ እነማን ናቸው? በግእዙ ያለው ታሪካችን ከሆነ ያስጠላችሁ እስኪ በሦስተኛ ክፍለ ዘመን ስለ እመቤታችን ድንቅ ድንቅ ስብከቶች የሰበከውን ጎርጎርዮስ ገባሬ መንክራትን ዘርዓ ያዕቆብ አስተማረህ ትሉታላችሁን? ወይስ የእመቤታችን በዓለ ዕረፍቷ ከበዓለ ዕርገቷ ጋር በአንድ ላይ በጁሊያን አቆጣጠር ኦገስት 15 አንድ ላይ ይከበር ይል ለነበረው ለቁስጥንጥንያው ንጉሥ ለዮስጥንያኖስ ከጥንት ጀምሮ ከኢየሩሳሌም መጥቶ በመንበረ ማርቆስ ካቴድራል ቤተ መጻሕፍት ተቀምጦ የኖረውን የእመቤታችንን የዕረፍቷንና የዕርገቷን ዜና መጽሐፍ ተርጉሞ በመስጠት ዕረፍቷ ጥር 21 ዕርገቷ ነሐሴ 16 መሆኑን በመግለጽ ቢያንስ በዚያ ዘመን ሁለቱም በዓላት በየራሳቸው እንዲከበሩ እንጂ አንድ ላይ መከበሩ እንዳይታወጅ ያደረገው የ33ኛው የእስክንድርያ ፓትርያርክ የቴዎዶስዮስን (535 - 566) ሥራ ምን ልታደርጉት ነው? አትደብቁት በብዙ የዓለም ቋንቋዎች የተተረጎመ ነው፡፡ እንግዲህ እናስተውል ፤ ይህ ቴዎዶስዮስ በጽርእ (ግሪክ) ቋንቋ ተርጉሞ ለንጉሡ የሰጠው መጽሐፍ በዓሉ ከእርሱ ዘመን በፊት ተለያይቶ ይከበር እንደነበርና ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ያሉት የምስራቁ ክፍል አባቶች በዚህ ትውፊት ጸንተው ይጠቀሙበት እንደነበር አሁን ድረስ በጉዳዩ ላይ ምርምር ለሚያደርጉ ማስረጃ ሆኖ ያገልግላል፡፡ በቅርብ ጊዜ አሜሪካን ሀገር ያለው የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የነገረ መለኮት ከፍተኛ ትምህርት ቤት የሆነው የቅዱስ ቭላድሚር ሴሚናሪ ከሚያሳትማቸው እስከ ስምንተኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ አባቶች ስብከቶች (Patristic writings) መካከል አንዱ የእመቤታችንን ዕረፍትና ዕርገት ( Dormition and Assumption) በተመለከተ በዚያ በጥንቱ ዘመን የተሰበኩ ስብከተ ሊቃውንትን አሰባስቦ የያዘ ነው፡፡ ይህ በዓል በጥንታውያኑ አበው ሲያከብሩት የመጣና እመቤታችን ዕረፍቷም ሆነ ዕርገቷ ከሐዋርያት ጀምሮ በኢየሩሳሌም ዙሪያ የነበሩ እጂግ ብዙ ደናግል ሴቶች በአካል በነበሩበት የተፈጸመ እንደሆነ ትውፊቱን የመዘገቡ መጻሕፍት ሁሉ የሚያረጋግጡት እውነታ ነው፡፡ በዚያ የነበሩ ሁሉ አይተው እንዳረጋገጡት ጌታ በሚያስደንቅ ግርማ የእመቤታችንን ነፍስ ሊቀበል በተገለጸ ጊዜ በአንድነት የሰገዱት ሐዋርያትና ደናግል ፍርሐት ርቆላቸው ቀና ሲሉ ሙሴ ከፊት ሆኖ ሌሎች ነቢያትና ጻድቃን ጌታን ከብበው ዳዊት በበገናው ‹‹ ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ፤ አንተ ወታቦተ መቅደስከ›› የሚለውን መዝሙሩን ሲዘምር ሁሉም በአንድነት አይተዋል፤ ሰምተዋል፡፡ ይህ የተረጋገጠ ታሪክ ነው፡፡ የነበሩት ሁሉ መስክረውታልና፡፡ እንግዲህ ሐዋርያትና ከእነርሱ ጋር የነበሩ ሁሉ ነበርን አይተናል ብለው አውርሰውት ከሔዱና ሁሉም እየተቀባበለ ለእኛ ካደረሰው በኋላ እናንተ አንቀበልም በማለታችሁ ከሐዋርያት መንገድ መውጣታችሁን ታረጋግጡልናላችሁ እንጂ እኛ የምንጠራጠር ይመስላችኋልን?የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት ትውፊት ወይም የቤተ ክርስቲያንን ትውፊት የማትቀበሉ ከሆነ ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን ከየት አገኛችሁት? ማን ሰጣችሁ? ምዕራፍና ቁጥሩንስ ከየት ተቀበላችሁት? ነቢያት ሐዋርያት እንደጻፉትስ በምን ታረጋግጣላችሁ? በእነማንስ በኩል ተጠብቆ ደረሳችሁ? ለመሆኑ ተነሣች ዐረገችን ለመቀበል ከቸገራችሁ አልተነሣችም አላረገችምን ለምን አመናችሁት? የተነገረውንና ሲተላለፍ የኖረውን ለማመን የምትቸገሩ እናንተ ልብወላዳሁን ለማመን የሚያፋጥናችሁ ማን ነው? መቼና እንዴት እንደተፈጸመ ወይም የዕረፍቷንና የአቀባበሯ ሌላ ትውፊት እንኳ ሳትይዙ የነበረውን ለማቃለል ብቻ የሚያጣድፋችሁ እንዴት ያለ ክፉ መንፈስ ነው? እናንተ የተረጋገጠ ጽሑፍ ብቻ ነው የምንቀበልስ ካላችሁ ትንሣኤና ዕርገቷ የተመለከተውን ጽሑፍ ማን እንደጀመረው፣ እንዴት እንደተሸጋገረና እንዴት ስሕተት እንደሆነስ ለምን አልመረመራችሁም? ጥላቻ ጊዜ አይሰጥማ፤ ክህደት የእውነተኛ ዐውቀት ጭላንጭል የለውማ፡፡ እንግዲህ እናነተን በምን መርዳት ይቻል ይሆን? ሐዋርያትን ካልተቀበላችኋቸው እኛንማ እንዴታ!በክህደት ትምህርታችሁና በስም ማጥፋታችሁ የምንደነግጥ ይመስላችኋልን? ይህንማ ሥራችሁ እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ እናንተም ሥራችሁን እኛም ሥራችንን እንሠራለን፡፡ በኋላ ዘመን ዋጋችን እንደ ሥራችን እንዲመዘን እናውቃለንና፡፡ ወይስ እንደ ዲያብሎስ ተስፋ ድኅነት የለንም ብላችሁ ተስፋ ቆረጣችሁ?

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ante yeteret a bat! Ye enjera guday honobehe new yemtelefelefew enj ..

   Delete
 14. ትንሣኤዋና ዕርገቷ ለክርስቲያኖች ሊቀበሉት የማያስቸገረው ግን የተረጋገጠ ትውፊት በመኖሩ ብቻም አይደለም፡፡ ትልቁና ዋናው ምሥጢር ያለው ደግሞ እመቤታችን ‹‹ ልዩ ›› መሆኗ ላይ ነው፡፡ ዕድገቷና ሕይወቷ ልዩ ነበር፡፡ በእርሷ የተደረገው የአካላዊ ቃል ጽንስና ወሊድም እስካሁን ሊገልጹት ቀርቶ ሲያስቡትም ይከብዳል፡፡ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው ‹‹ ይህንም ባሰብኩ ጊዜ ኅሊናዬ የልጅሽን የባሕሩን ጥልቅነት ሊዋኝ ይወዳል፤ የወዳጅሽ የመሰወሪያው ማዕበልም ያማታዋል፡፡ ... አሁንም ገናንቱን አንመርምር፤ ጥልቅነቱንም አንጠናቀቅ፤ የገናንቱን መጠን ለማመስገን የነቢያትና የሐዋርያት አንደበት የማይቻለው ነው›› እንዳለው ለማንም የሚቻል አይደለም፡፡ ለዚህ የታደለችው ነገሩን ሁሉ በልቧ ትጠብቀው የነበረችው እራሷ ድንግል እመቤታችን ብቻ ናት፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ገብርኤልም ቅድስት ኤልሳቤጥም ‹‹ ልዩ›› መሆኗን አስቀድመው ምስጋናቸውን ያስከትሉላት፡፡ ታዲያ እመቤታችን ልዩ በሆነ መንገድ ከጸነሰችና ከወለደች ልዩ በሆነ መንገድስ የማትነሣው የማታርገው ለምንድን ነው? መነሣቷና ማረጓ አድሎ ያስመስላል የሚባለው በድንግልና ጸንሳ በድንግልና መውለዷንስ ለምን አድሎ ነው አይባልም? ጽንሱ ልደቱ ሰለ እርሱ ነው የምትሉ ከሆነስ ትንሣኤውና ዕርገቷ ምን የሚያረጋግጥ ይመስላችኋል? የእርሱን ትንሣኤና ዕርገት ተሰርቆ ነው ሲሉ የነበሩ አይሁድ በእርሷ ትንሣኤና ዕርገት ሲያፍሩ ብዙዎቹም ከእነርሱ ወደ ክርስትና ሲመለሱ እናንተ ይህን ከማለት የማትመለሱ የክርስቶስን ትንሣኤም ሳታውቁ ታቃልላላችሁን? የእናንተ ክሳደ ልቡና በእውነቱ እንደምን ከዚያ ዘመን አይሁድ ይልቅ ጸና? በውኑ አድሎን ለእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት የምትጠቅሱት በደብረታቦር በዓል ሙሴን ከሙታን ኤልያስን ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሦስቱን ብቻ ይዞ መውጣቱንስ አድሎ ትሉታላችሁን? በእውነቱ ስንቱን ተመሳሳይ ታሪክ ልንጠቅስ ስንቱንስ ልናስታውሳችሁ እንችላለን? በእውነት የቀደሙትን አበው ትምህርትና ትውፊት እንዳትቀበሉ የእግዚአብሔርንስ የማይታወቅ መንገድ የደረሳችሁበት አስመስሎ ያሞኛችሁ ወይንም ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? የእመቤታችን ልዩ መሆን ካልገባችሁ በትንሣኤዋና በዕርገቷም ልዩ መሆኗን እንዴት ልትረዱ ትችላላችሁ? ማስተዋላችሁን የጋረደውን የስድብና የስም ማጥፋት ግብር ያሰደረባችሁን ከፉን መንፈስ ትቃወሙትና ከዚህም ነጻ ትወጡ ዘንድ በእውነት እግዚአብሔር ይርዳችሁ ከማለት በቀር ምን ልንል እንችላለን፡፡ድንግልማ በእውነት ተነሥታለች ዐርጋለችም፤ ክብር ምስጋና ለተወደደ ልጇ ይሁን፤ አሜን፤ በረከቷም ይደረብን፡፡  አርምሞትኪ ማርያም ኃለፈ እም አንክሮ፤

  እስከ ንሬኢ ሕዝብኪ ለተአምርኪ ግብሮ፤

  ገነትኪ ትጽጊ ሰላመ ወተፋቅሮ፤

  እለያማስኑ ለዓጸደ ወይንነ ወፍሮ፤

  ቆናጽለ ንዑሳነ አፍጥኒ አሥግሮ፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. wendemai kale heyewet yasemalen menegeste semayaten yawereselen AMEN

   Delete
 15. http://en.wikipedia.org/wiki/Assumption_of_Mary
  Protestant views[edit source | editbeta]

  The Protestant Reformer Heinrich Bullinger believed in the assumption of Mary. His 1539 polemical treatise against idolatry[28] expressed his belief that Mary's sacrosanctum corpus ("sacrosanct body") had been assumed into heaven by angels:
  Hac causa credimus ut Deiparae virginis Mariae purissimum thalamum et spiritus sancti templum, hoc est, sacrosanctum corpus ejus deportatum esse ab angelis in coelum.[29] For this reason we believe that the Virgin Mary, Begetter of God, the most pure bed and temple of the Holy Spirit, that is, her most holy body, was carried to heaven by angels.[30]
  Most modern Protestants neither teach nor believe in the Assumption of Mary, as they see no Biblical basis for it. Although most churches within Lutheranism do not teach the Assumption of Mary, August 15 is a Lesser Feast in celebration of "Mary, Mother of Our Lord", according to the Calendar of Saints.[31][32][33

  ReplyDelete
 16. refer this link http://en.wikipedia.org/wiki/Assumption_of_Mary
  The feast of the Assumption is a public holiday in many countries, including Austria, Belgium, Chile, Colombia, Croatia, Ecuador, France, Germany (Bavaria and Saarland only), Greece, Lebanon, Lithuania, Italy, Malta, Mauritius,[34] Poland, Portugal, Romania, Senegal, Slovenia, Spain, Switzerland (8 cantons only) and Vanuatu.[35] In Eastern Orthodox churches following the Julian Calendar, the feast day of Assumption of Mary falls on August 28.

  ReplyDelete
 17. ye GREEK YE RUSIYA YE LATIN ENA BATEKALAY YE ALEM ORTODOX ENA YE CATOLIC CHURCH BE MARIYAM TINSAEA YAMINALU KE PROTESTANT BESTEKER SILEZH YE ETHIOPIA ORTODOX BICHA ENDEMITAMN ADIRGACHIHU ATWASH

  ReplyDelete
 18. bezwochu yefetera tariwoch nachew ande yeethiopiana ye gebche ortodox kechristose weyse kemariam manene tewdhlhe bebale be dersanwa dengel mariam tebltebetalch get gene ..............................

  ReplyDelete
 19. Glory and honor be to God the almighty in Jesus Christ through the Holy Spirit now and for ever.

  Welde-Ab.

  ReplyDelete
 20. እኔ የምለው እንዴት ነው ነገሩ ጎበዝ ለተረት ከመኖር በኢየሱስ መኖር አይሻልህም ተው ተመለስ ንስሀ ግባና ጌታን ተከተል።የምን ተረት ውስጥ ተወሽቖ መኖር ነው!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. @maru kebede egziabeher mastewal yesteh .ye egziabeher eweneten bemenem mekeyer aychalem weyem kalgebah zem malet hateyat aydelem.emebetachenen mewded beweshet ayegeletsem .sele egziabeher enkuan weshet menager hateyat new.egziabeher be haset aykeberemena.degemom mesedadeb yekerestian bahery aydelem.geta mastewalun yesteh!!!!

   Delete
 21. እንዲህ እየሆንን እናንተ ቅድስት ቤተክርስቲያንን እየተራገማችሁ እኛም በእቅፉዋ ውስጥ እየኖርን፣እየተቀደስን፣የዘላለማዊ ህይወት ምግብ እየተመገብን፣ እየተባረክን የአምላካችን ዳግም ምፅአት ይደርሳል።እውነተኛው ዳኛ ይፈርዳል።

  ReplyDelete
 22. Atachiberbiru Ye Germany, Norway, and others Telalakiwoch

  Dormition of the Theotokos

  Main article: Dormition of the Theotokos
  Source Wikipedia, the free encyclopedia

  The Orthodox feast of the Dormition is analogous to what Roman Catholicism calls the Assumption of Mary. According to Orthodox Tradition, Mary died like all humanity, "falling asleep", so to speak, as the name of the feast indicates. (Catholic theologians are divided on the issue of whether Mary died. Today most would favor an actual death before the Assumption.) The Apostles were miraculously summoned to this event, and all were present except Thomas when Mary passed from this life. She was buried. Thomas arrived three days later, and desiring to see her one more time, convinced the other apostles to open her tomb. To their surprise, her body was not there.

  This event is seen as a first symbol of the resurrection of the faithful that will occur at the Second Coming of Christ. The event is normally called the "Dormition", though there are many Orthodox Churches with the name "Assumption". In Greek, "Dormition" is "Kimisis" (Coemesis) -- falling asleep in death—from which the word "cemetery" derives.[12]

  ReplyDelete
 23. Thank you Maru Kebede,you explained clearly how other churches believe and celebrate the Assumption of Our Mother.I was considering to post calendars of Coptic Orthodox Church(exactly the same as Ethiopian Orthodox Church),Syrian Orthodox Church and Indian Orthodox Church on this issue,but Maru, you have given us even far beyond this,and God bless you for sharing the information.
  I think anybody can Google and read about the Assumption of Our Mother and Its Celebration in other Churches.
  Once again,thank you Maru Kebede

  ReplyDelete
 24. በዮሐንስ ራእይ ላይ ስለእናንተ ተፅፏል "በእርሷ ላይ ለመድረስ ሲያቅተው ቀሪ ልጆቿን ሊወጋ በባህር አሸዋ ላይ ቆመ"ይላል የባሕር አሸዋ ማለት እናንተ ያውሬው መንፈስ ያደረባችሁ ናችሁ።ልጆቿ ደግሞ እኛ ነን።

  ReplyDelete
 25. "God was pleased through the foolishness of what was preached to save those who believe." 1 Corinthians 1:21

  Le mayamin teret ne'w le'egna amlak gin yemiyasdestew Haimanot ne'w

  ReplyDelete
 26. Every thing done in EOTC regarding St. Mary has hidden the savior Jesus Christ, that is the ultimate goal of Satan. If the bible does not say any thing, where you get this story?

  ReplyDelete
 27. For a person who closed his eyes to see the truth I know there is no cure or evidence that might change, but for those confused and my want to know some thing I think this will give a glimpse of some little thing out side of Ethiopian Orthodox. Enjoy it, watch this http://myocn.net/orthodox-christian-radio-programs/

  ReplyDelete
 28. አንዳንዲ ይገርመኛል ዮሐንስ "ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤
  ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፎአል።"
  የዮሐንስ ወንጌል 20 : 30-31
  ኢየ ሱ ስ የሰራው ታምር አለ እንጅ ስለ ሌሌች ያልተጻፈ አለ አላለም በእግዚአብሔር ልጅ እንድ ናምን አምነንም ሕይወት እንዲሆንልን ይህ ተጽፏል። የእግዚአብሔር አላማ ወይም አሳብ በሰማይ በምድር ያለውን በክርስቶስ ኢየሱስ ለመጠቅለል ነው እንጅ ስለ ማርያም እንድናወራ አይደለም ኤፊ.1፡10 ወገኔ ተመለስ ዝምብለህ በጨለማ አትጒዝ ማርያም እንደሆነ ማንም የማይቀማትን እድል መርጣለች ይህውም የክርስቶስ ማደርያ በመሆን እኛም የእግዚአብሔር ማደርያ ለመሆን እንሰራ። ይህን ለማድረግ እግዚአብሔር ይርዳን አሜን

  ReplyDelete
 29. ESEKE ALEM FETAMAI BENANETE LAYE ADERU SIYASASETENA SISADEB YEHASETE MELASUN SIZEREGA YENURALE YE AWERAITE TELALAKI KEMEHUN YADENATHU

  ReplyDelete
 30. doma chinkilat yelelochin kidisina kemagudef yalef ewketim hone bikatu yelewm.

  ReplyDelete
 31. መዝ. 131፡8 አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።
  ይህ ሃይለ ቃል አማናዊት ታቦት ለሆነች ለእመቤታችን ትንሳኤ ይነገራል፡፡ አቤቱ ወደ እረፍትህ ተነስ ተብሎ የተነገረው ለእግዚአብሔር አብ ነው፡፡ መቅደስ የተባለው ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ጌታችን እራሱን መቅደስ ብሎ ጠርቶዋል፡፡ ‹‹ ይህንን መቅደስ አፍርሱት በሶስት ቀን አነሳዋለሁ ›› (ዮሀ. 2፡20-21) ጌታ መቅደስ የሚባለው በስጋው ነው፡፡
  ‹‹ የመቅደስህ ታቦት ›› ሲል ‹‹ መቅደስ ›› የተባለውን የባህርይ ልጅህ የወልድን ማኅደር(ማደሪያ) እመቤታችንን ይዘህ ወደ መንግስተ ሰማያት ተነስ የሚል ፍቺ አለው፡፡
  እግዚአብሄር የፈቀደውን እንዳያደርግ ማንም አይከለክለውም፡፡ ምን አልባት ቢኖር ጎዶሎነት ወይም ምንፍቅና ነው፡፡ አንድ መንፈሳዊ አይደረግም እንዴት ይላል፡፡ እግዚአብሄር ሄኖክ አባታችንን ወሰደው ለምን አካሄዱን ከእግዚአብሄር ጋር አድርጎዋልና ነብዩ ኤልያስንም በእሳት ሰረገላ ወሰደው ለምን ለአምላኩ ቀናኢ ነበርና ፡፡ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ከሞቱ ቅዱሳን ተነስተው በከተማው ለብዙዎች ታዩ ይለናል፡፡ መሞታቸውን አይነግረንም፡፡ ማቴ. 27፡52 መቃብሮችም ተከፈቱ፥ ተኝተው ከነበሩትም ከቅዱሳን ብዙ ሥጋዎች ተነሡ፤
  53 ከትንሣኤውም በኋላ ከመቃብሮች ወጥተው ወደ ቅድስት ከተማ ገቡና ለብዙዎች ታዩ። ታዲያ ይህ ድንቅ አምላክ እናቱን አስነሳ ብንል ያስደንቃልን በጭፍኑ ለመካድ ካልሆነ በስተቀር፡፡ የትንሳኤ በኩር ስንልኮ ከሱ ቀድሞ ሞቶ የተነሳ ላለመኖሩ እንጂ ከሱ በሁዋላ የተነሱ ቅዱሳን እንደነበሩ ከላይ አይተናል፡፡ እመቤታችንም ሞታ ተነሳች ያልነው ከሱ በሁዋላ ነው፡፡ ሌሎችን ያስነሳ አምላክ ምነው እመቤታችን ሲባል መናደዳችሁ፡፡ ከክፉው መንፈስ መሆናችሁ በዚህ ያስታውቃል፡፡በቀላሉ ማመን ስትችሉ በማይገባችሁ እየገባችሁ አትዘባርቁ፡፡
  መዝ. 131፡8 አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።

 32. Shudder, O ye heavens! and, O earth, give ear unto these words: God descended once before for our sake; He descends again today for His Mother.

  –from The Lamentations at the Bier of the Mother of God
  Photo: Shudder, O ye heavens! and, O earth, give ear unto these words: God descended once before for our sake; He descends again today for His Mother. –from The Lamentations at the Bier of the Mother of God

  ReplyDelete
 33. ማስተዋል የጎደለህ አንተ ሰው;ተመልከት ብዙ ዝርዝር ውስጥ ሳንገባ;ለምሳሌ እኔ የምኖረው አውሮፓ ውስጥ ነው አውሮፓውያን ለምሳሌ እኔ ከምኖርበት ሀገር እመቤታችን ያረገችበት ዕለት ብሔራዊ በዓል ነው።እና እንደ አንተ ድን ቁርና ከሆነ ፈረንሳይ የእመቤታችንን የፍልሰትዋን መታሰቢያ .ብሔራዊ በዓል አድርጋ የምታከብረው ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወስዳ ነው።አይ መናፍቅ ሁሉን እንደተጠራጠራችሁና ከእመባታችን ጋር እንደ ተጣላችሁ ፀሐያችሁ ሊጠልቅ ነው።በመጽሐፍ ቅዱስ እንካዋን እመቤታችን ያደረገችው ይቅርና ጌታችን ያደረገው አብ ዛኛው አንዳልተጻፈ፥ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌል"ጌታችን ያደረገው ሁሉ ቢጻፍ ምድር ዓለም ሊሸከሙት አንደማይችሉ ጽፎልናል"በከንቱ አትድከም ሳንጠራጠር የእመቤታችንን የፍል ሥታ መታፍስቢያ እናከብራለን

  ReplyDelete
 34. ante satmot gin kemot belay yemoth EGZIABHER YIKIR YIBELH

  ReplyDelete
 35. God bless you brother a truly revealing. the orthodox and chatholics have always been deceived when it comes to the issue of Mary. with a logical but deceitful argument they argue because mary is the mother of Jesus she is special to other humans in her birth, life and death and now ascencion. this is however not supported by the bible. Jesus in his life has never talked about special treatment of Mary or his brothers.

  ReplyDelete
  Replies
  1. …ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ…ከመባል በላይ ምን ትባልለህ? ከድንግል ማርያም ውጭ.. ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል… ያለ/ያለች ፍጡር በመጽሀፍቅዱስ ውስጥ ካለ ወዲህ በል፡፡

   Delete
 36. Bible is a collection of different books/chapters which were written at different time period by different individuals. However, we people collected those books/chapters and made together and said it bible after we reached agreement. Therefore, it is up to us to include others books or reduces whenever an issue is raised. This is the reality. What I don't understand here, some shallow minded people complaining the referring of written facts which are available in different books other than the bible! This is ridiculous!!! You shallow minded people have to convince us (if you can) the bible was sent down from heaven by God at one time in the past as the Muslims believe the Koran sent down by Allah from heaven. Until you justify this way, nobody is listening you anything that comes out from your shallow mind. Or, I suggest you to take time to learn how each chapter in the bible was written (who wrote, when was written, for what purpose and why we agreed to include it in the bible???) Otherwise stay away from the complex religious-political world. You don’t deserve to tell anything to anyone except your shallow so called analysis.

  ReplyDelete
 37. ከሱባኤ(ከ2 ሰባት) መልስ…..ጥቂት ስለፍልሰታ ለማርያም!!!

  የምስራቁ እና የምዕራቡ ክርስትና ወይም በሌላ አነጋገር የምስራቅና የኦሪየንታል ኦርቶዶክሱ ከካቶሊኩ ዓለም ተስማምቶ ያለልዩነት ከሚያከብራቸው በዓላት ውስጥ አንዱ በዓለ-ፍልሰታ ነው፡፡ፈረንጆቹ The Assumption Day ይሉታል፡፡አንዳንድ ምዕራባውያን(ካቶሊኮች) ደግሞ Dormition ይሉታል፡፡ሆኖም ይሄኛው ቃል( Dormition) ከፍልሰታ ይልቅ ለጥር 22ቱ የእመቤታችን በዓለ-ዕረፍት(አስተርዮ) መጠሪያነት ስለሚቀርብ ፍልሰታ ለሚለው ቃል ትክክለኛው የእንግሊዝኛ አቻ ትርጓሜ Assumption ነው፡፡

  ሀ. ለፍልሰቷ (ሥጋዋ ከነፍሷ ተዋሕዶ ከመቃብር ስለመነሳቱ) የምናቀርበው ማስረጃም…

  1-ትውፊት፡፡፡ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ እስከኛ ድረስ እየተከበረ መኖሩ፡፡
  2-ትንቢት፡፡፡ መዝ 131 ቁ 8፣መዝ 44 ቁ 9፣ራዕይ 11 እና 12፣
  3-የአበው ምስክርነት፡፡፡ እምጌቴሴማኔ ፈለሰት ኀበ ዘሉዐሌ መካን… እንዲል መልክዐ-ፍለሰታ፣አእረግዋ መላእክት በስብሐት….እንዲል ቅ/ያሬድ
  4-ዘመነ ሰማዕታት በቆስጠንጢኖስ መነሳት ካበቃ በኋላ አጽመ-ቅዱሳን ሲሰበሰብ የእመቤታችን መቃብር ባዶ ሆኖ መገኘቱ፡፡ባዶው መቃብር አሁንም ይጎበኛል፡፡
  5-ፍልሰተ-ሥጋዋ ከላይ በተጠቀሱት በቢሊዮን የሚቆጠሩ የክርስትና አማኞች በተመሳሳይ መልኩ ለሺህ አመታት መታመኑ፣

  ለ. ፍልሰታና መጽሐፍቅዱስ!!

  1-ከላይ የተጠቀሱት ትንቢቶች እና ራዕይ፡፡(መዝ 131 ቁ 8፣መዝ 44 ቁ 9፣ራዕይ 11 እና 12)፣
  2-የሄኖክና የኤልያስ እርገት እንደመነሻ ሲታይ የእሷ እርገት ከመጽሐፍቅዱስ መርህ ጋር የሚጋጭ ስላልሆነ፣
  3-በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተካተተው የሚበዛው መጽሐፍቅዱስ ከተጻፈ በኋላ ስላረገች ነው ተብሎ የሚታመን ሲሆን መጽሐፉን ከእርገቷ በኋላ የጻፈው ዮሐንስ ግን በራዕዩ ምዕራፍ 11 እና 12 ተናግሮታል--በራዕይ መልክ፣
  4-በብሉይ ኪዳን ውስጥ አንድም ቦታ ተጽፎ የማይገኘው የሙሴ ስጋ በቅ/ሚካኤል መወሰድ በሓዋርያው ይሁዳ መልእክት 1 ቁ 9 ተጽፎ መገኘቱና በጊዜው የነበሩት ምዕመናን ይህ በብሉያችን ስለሌለ አንቀበልም የሚል ተቃውም አለማሳየታቸው ስለ እመቤታችን ፍልሰተ-ሥጋ የሚነገረውንም ትውፊት ስለሚደግፍ (by analogy)፣
  5-እመቤታችን አዳም በበደሉ ካገኘውና ለልጆቹ ከተላለፈው እርግማን (ጥንተ-አብሶ) ነጻ ናት ብለን ለምናም ለእኛ ኦርቶዶክሳውያን አዳም ስለ በደሉ የመጣበት ሙስና-መቃብር በደሉ ባልተላለፈባት እመቤታችን ላይ ይደርሳል ብለን ስለማናምን ዐርጋለች እንላለን፡፡

  ማስታወሻ፡ በሀገራችን እስከ 1966ቱ አብዮት ድረስ ፍልሰታ (ነሐሴ 16 ቀን) ብሔራዊ በዐል ማለትም መ/ቤት ተዘግቶ የሚከበር በዐል ነበር፡፡ነበር፡፡አሁንም The Assumption Day is treated as public holiday in some countries like Austria, Spain, Poland, Portugal, Italy, Greece, Slovenia, Belgium, Chile, Croatia, some parts of Germany and Switzerland, Guatemala etc. - See more at
  http://aglobalworld.com/holidays-around-the-world/assumption-day/

  ReplyDelete
 38. I am wondering who is the Man standing next the body of Mary ,holding small child , Who is the Child???.DO NOT TELL ME ,THAT IS JUSES!!
  I think somebody who sees this picture will write another "twfit" again.

  ReplyDelete
 39. እኔ የምለዉ የማሪያም መሞትና መነሳትን በተለመከተ ሺርፍራፊ ያዉም አብሮ የማይሄድ አዉዱን የለቀቀ ጥቅስ እንደ ሰይጣን (ኢየሱንስን ሲፈትንዉ እንደጠቀሰዉ ጥቅስ ማለቴ ነዉ)እየጠቀሱ የጥቅሱን መንፈስ ሳይረዱ ከሰይጣን በቀዱት የሀሰት ወይንጠጂ የሰከሩ ደብተራዎች በጸፉት የጨለማ ትምህረት ፤ክርስቶስ ኢየሱስን የሚጋርድ የፈጠራ ድርስት የምትከራከሩት ለምንድን ነዉ ?
  ወገኔ መጽሀፍ ቅዱስ እንዴት አዉዱን ጠብቆ እንዴት መተርጎም እንዳለበት ስነ-መለኮት ትምህረት ቤት ግቡና Hermeneutics ተማሩ ቃሉን ከተጻፈበት ዓላማ ዉጭ አጣሞ መተርጎም ሀሰትን እንጂ እዉነት ለማወቅ ለማወቅ አለመፈለግ ነዉ የጸሀፊዉን ዓላማ መሳት ነዉ ፣ይህ ደግሞ እያንገዳገዳችሁ ያለዉ የስህተት ወይን ጠጅ መጨረሻ ባፈጢማችሁ ደፍቶ ለገሀነብ ፍርድ ሊዳርጋችችሁ ይችላል ፣ካንገዳገዳችሁ የስህተት አሰራር ለመዉጣት ጊዜዉ አሁን
  እስኪ ልጠይቃችሁ
  1. ከመዳን ጋር ያለዉ ግንኙነት ምንድን ነዉ ?
  2. ሀዋርያት ለምንጾሙት ?
  3. እኛስ ዛሬ ለምንድን ነዉ የምንጸሞዉ ? እርገቷ እንዲገለጥልን ?

  ReplyDelete
 40. መጋቤ ሀዲስ ላዕከ ነኝJanuary 12, 2015 at 6:59 PM

  እኔ የምለዉ የማሪያም መሞትና መነሳትን በተለመከተ ሺርፍራፊ ያዉም አብሮ የማይሄድ አዉዱን የለቀቀ ጥቅስ እንደ ሰይጣን (ኢየሱንስን ሲፈትንዉ እንደጠቀሰዉ ጥቅስ ማለቴ ነዉ)እየጠቀሱ የጥቅሱን መንፈስ ሳይረዱ ከሰይጣን በቀዱት የሀሰት ወይንጠጂ የሰከሩ ደብተራዎች በጸፉት የጨለማ ትምህረት ፤ክርስቶስ ኢየሱስን የሚጋርድ የፈጠራ ድርስት የምትከራከሩት ለምንድን ነዉ ?