Tuesday, August 12, 2014

እንክርዳዱን ማን ዘራው?

Read in PDF

ምንጭ፡-ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብሎግ

ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ ስናጠና ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን የሠራበት እውነት “ኢየሱስ እርሱ የሕያው እግዘአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነው” (ማቴ.16፥16) የሚለው በእግዚአብሔር አብ የተገለጠ እውነት ነው፤ ማንም ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲጨመር ይህን እውነት በልቡ አምኖ በአፉ ሊመሰክር ይገባዋል (ሮሜ 10፥9-10)፡፡
በክርስቶስ መሠረትነት የተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር የዘለዓለም ሕይወትን የሚሰጥባት የሕይወት እርሻ ናት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና” (1ቆሮ.3፥9) ሲል የገለጣት ቤተ ክርስቲያንን ነው፡፡ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 13 በተለያዩ ምሳሌዎች ቤተ ክርስቲያንን ገልጧታል፤ ከእነዚህ ምሳሌዎች አንዱ እርሻ ነው፡፡ የእርሻው ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር (ክርስቶስ) ነው፡፡ ይህ ጽሑፍ በተለይ በማቴዎስ ወንጌል 13፥24-30 የተመዘገበውን ምሳሌና በዚሁ ምዕራፍ ከቍጥር 36-43 ያለውን ትርጓሜ መሠረት ያደረገ ነው፡፡ማቴዎስ 13፥24-30 “ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች። ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ። ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ። የባለቤቱም ባሮች ቀርበው። ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት። እርሱም፦ ጠላት ይህን አደረገ አላቸው። ባሮቹም። እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን? አሉት። እርሱ ግን፦ እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም። ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን። እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ።”  

ትርጉም፡ ማቴዎስ 13፥36-43 “በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው። የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት። እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው። እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል። የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”
እግዚአብሔር ንጹሑን ዘር በእርሻው ላይ ዘርቷል
ክርስስቶስ ያስተማረው ወንጌል በዚህ ዓለም የዘራው ንጹሕ የሕይወት ቃል ነው፤ የተዘራው ቃል እንደ በቀለ፣ እንዳፈራ፣ ፍሬም ለእግዚአብሔር ክብር እንደዋለ ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንማራለን፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ክርስቲያኖች ዐላውያን ነገሥታት፣ መናፍቃንና ከሐድን በበዙበት ጊዜ ሁሉ የክርስቶስን ወንጌል እየሰበኩ በትውልዱ መካከል እንደ ብርሃን እያበሩ ኖረዋል፡፡ ዘመነ ሰማእታትን ስናስብ ይህን እውነት በእርግጥ እንረዳለን፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን የመሠረተበትን እውነት ስናይ እንደ ወርቅ የጠራ እውነት ነው፡፡ በእግዚአብሔር እርሻ ላይ ከእግዚአብሔር የተዘራ እንክርዳድ ፈጽሞ አልነበረም፤ሊኖርም አይችልም፡፡
ባለቤቱ እርሻውን እንዲጠብቁ ለሠራተኞቹ አደራ ብሎ ነበር፡፡
ሠራተኞች አደራቸውን ስላልተወጡ ቤተ ክርስቲያንን የሚጎዳ እንክርዳድ በቤተ ክርስቲያን ላይ ተዘራ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶ፣ መንጋውን ሰብስቦ፣ ለሐዋርያት አገልግሎቱን አደራ ሰጠቷል፤ እንክርዳዱ የተዘራው ሰዎቹ (ሠራተኞች) ተኝተው ሳለ ነው፤ ይህም ማለት የቤተ ክርስቲያን ጠላት ዲያብሎስ በቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ትምህርት የሐሰት ትምህርትን የዘራው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ተኝተው ሳለ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ተኝተው (ቤተ ክርስቲያንን በእግዚአብሔር ቃል የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን መወጣት ሳይችሉ ቀርተው) ወደ ቤተ ክርስቲያን የሐሰት ትምህርትን ያስገቡት መቼ ነው? ይህን ጥያቄ ለመመለስ እውነት መቼ ተሰበከ? እውነት ምንድን ነው? ወዘተ የሚሉትን ጥያቄዎች አስቀድሞ መመለስ ያሰፈልጋል፡፡
እውነት በእግዚአብሔር ገላጭነት አስቀድሞ በነቢያት በኋላም በክርስቶስ ሥጋዌና ባስተማረው ወንጌል፣ ሐዋርያት በሰበኩት ወንጌል የተገለጠ ነው፤ ይህን ቤተ ክርስቲያን ጠብቃ ስታስተምረው ቆይታለች፡፡ ከክርስቶስ ዕርገት፣ ከሐዋርያት ስብከት፣ በእግረ ሐዋርያት ከተተኩ ቅዱሳን አባቶች አገልግሎት በኋላ አንዳንድ ጊዜ በመከራ ፅናት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በምቾትና በሥልጣን ፍላጎት ብዛት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የመንጋው እረኞች አንቀላፉ፤ በዚህ ወቅት የቤተ ክርስቲያን ጠላት ዋና ዋና የሚባሉ የክርስትና ትምህርቶችን የሚለውጥ፣ የሚያንቅና የሚያቀጭጭ፣ ፍሬ እንዳያፈሩ ብሎም ጨርሶ እንዳይኖሩ የሚያደርጉ የስሕተት ትምህርቶችን በቤተ ክርስቲያን ዘራ፡፡ ዋናው የስሕተት ትምህርት ሰለባ የሆነው ደግሞ የመዳን ትምህርት ነው፤ ክርስቶስ በትምህርቱ እርሱ እውነት፣ ሕይወትና መንገድ እንደሆነ፣ ከእርሱ በቀር በሌላ መንገድ (በኩል) ወደ አብ መድረስ እንደማይቻል አስተማረ (ዮሐ.14፥6)፡፡ ሐዋርያትም  “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና፡፡” (የሐዋ.4፥12) ሲሉ የክርስቶስን ወንጌል ሰበኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ በአጠቃላይ ሲታይ ዋናው መልእክቱ የሰው ልጅ በኀጢአቱ እንደተፈደበት፣ ራሱን ማዳን እንዳልቻለ፣ ሌላ ፍጡርም ሊያድነው እንደማይችል ማረጋገጥና ሰዎች ለመዳንና የዘለዓለም ሕይወትን ለማግኘት እግዚአብሔርን ብቻ ተስፋ ማድረግ እንዳለባቸው ማስተማር ነው፡፡ ይህን እውነት ነቢያት፣ ሐዋርያትና እውነተኞች የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያውቁታል፤ ሰብከውታል፤ ለእኛም አስረክበዋል፡፡
እንክርዳዱ ከፍጡር መዳንን መጠበቅ፣ ፍጡራንን አድኑኝ ብሎ መማጸን፣ በአምልኮት ውስጥ ፍጡራንን ስማቸውን መጥራትና እንደፈጣሪ በሁሉም ቦታ ተገኝተው የሚሰሙ አስመስሎ ማነጋገር፣ በመንፈስና በእውነት የሚመለከውን እግዚአብሔርን በሚያመልኩበት ቦታና ሥርዐት ፍጡርን ማወደስ፣ ለፍጡር መንበርከክ፣ ለማይሰማ ታቦት፣ በሰው እጅ ለተሠራ፣ ሰዎች ተሸክመውት ለሚያንቀሳቅሱት ነገር፣ ምንጣፍ በየመንገዱ እያነጠፉ፣ እየወደቁና እየተነሡ፣ ሆ! እልልልል! እያሉ ማወደስ ይህ ሁሉ በእግዚአብሔር እውነት ላይ የተዘራ የጠላት እንክርዳድ ነው፡፡ ይህን ሁሉ የዘራው ጠላት የእግዚአብሔርን ክብር የማይወድድ ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ ይህ ጠላት በቤተ ክርስቲያን ይህን ሁሉ እንክርዳድ የዘራው መሪዎችዋን በትምህርተ ሃይማኖት ክርክር፣ በስልጣን ፍላጎት፣ በፖለቲካ ጡንቻ ሥር ካስተኛ በኋላ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ነቅተው ቤተ ክርስቲያንን ቢጠብቁ ይህ ሁሉ እንክርዳድ ሊኖር አይችልም ነበር፡፡

የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለጠላት እድል ሰጥተውታል፤ ለእውነት ባለመቆማቸው ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ ለራሳቸው ክብር ቅድሚያ በመስጠታቸው ቤተ ክርስቲያን የእንክርዳድ ማሳ (እርሻ) ሆናለች፤ ይህ የቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ልጆችን የሚያንገበግብ እሳት ነው፡፡
የመሪዎቹ እንቅልፍ የእግዚአብሔርን የንስሓና የተሐድሶ ድምጽ መስማት እስከማይችሉበት ደረጃ ድረስ ከብዶባቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ለምድሪቱ ቃሉን ላከ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት የገለጠውን እውነት እንዳይጠፋ ጠበቀ፤ በትውልድ መካከል የቃሉን ሐውልት አቆመ፤ ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከክርስትና ይልቅ ምንኩስናን፣ ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ በብልሐት የተፈጠረውን ተረት (2ጴጥ.1፥16)፣ ከንጽሕና ይልቅ ርኩሰትንና ሙስናን፣ ከትሕትናና እውነትን ከመፈለግ ይልቅ ትዕቢትንና እውነተኞችን መግፋትን፣ በእግዚአብሔር ድምጽና ክብር ላይ መታበይን፣ ቤተ ክርስቲያንን በእነርሱ ሲኖዶስ ውሳኔና ብልሹ አስተዳደር ሥር ጠምዝዞ በመጣል እንደ ፍሪዳ አርዶ ሥጋዋን መብላት፣ አጥንቷን መጋጥ እንጂ እግዚአብሔርን መፍራት የለም፡፡

እንክርዳዱ ግን እያደገ፣ ስንዴውን እያነቀ፣ እያቀጨጨና እያመነመነ እንዲያውም ስንዴው እንደ እንክርዳድ እንክርዳዱ ደግሞ እንደ ስንዴ እንዲታይ እያደረገ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት “አዳኝ ክርቶስ ብቻ ነው” የሚለው ንጹሕ ስንዴ እንክርዳድ ሆኖ “የዓለም ቤዛ ድንግል ማርያም ናት” “ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንድም” የሚለው “ወፍዘራሽ” (ዲያብሎስ የዘራው) እንክርዳድ ሀገራችን ኢጥዮጵያን ሁሉ እየሞላ ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ተሐድሶ አገልግሎት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በቤተ ክርስቲያናችን እውነተኛ ትምህርት ውስጥ ተዘርቶ ያለው ወፍ-ዘራሽ የስሕተት ትምህርት እንዲለይና እንዲወገድ፣ ቤተ ክርስቲያንም ምእመናንን ወደ እግዚአብሔር እውነት የማድረስና የሰው ልጆችን የመዳን መንገድ የማሳየት አምላካዊ አደራዋን በአግባቡ እንድትወጣ ለንስሓና ለተሐድሶ በመቀስቀስ የበኩላችን ማበርከት ነው፤ እግዚአብሔር ነፍስን ይመልሳል፤ ሰዎችን ሁሉ ወደ እውነት ይመራል፤ ይህን የሚያደርገው ደግሞ በቃሉና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ነውና ቤተ ክርስቲያን ይህን አምላካዊ ኀላፊነት ልትዘነጋውና ለጠላት እድል ልትሰጥ አይገባም እንላለን፤ ይህን የተማርነው ከእግዚአብሔር ቃል ነው፤ የእኛ የሆነ ከራሳችን ያመጣነው እውነት የለም፤ እውነትን በእውነት እናገለግላለን እንጂ በእውነት ላይ አንዳች ነገር አንጨምርም፡፡ ተሐድሶ የምንለውም ይህን ለእውነት መሰጠትን፣ እውነትን ማገልገልን፣ በእውነት ጸንቶ መኖርን ነው፡፡ እግዚአብሔር ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በተሐድሶ ወደ ክብሯ እንድተመለስ ያድርግልን፤ አሜን፡፡

ምንጭ፡-http://www.tehadeso.com/

ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ ስናጠና ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን የሠራበት እውነት “ኢየሱስ እርሱ የሕያው እግዘአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነው” (ማቴ.16፥16) የሚለው በእግዚአብሔር አብ የተገለጠ እውነት ነው፤ ማንም ሰው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲጨመር ይህን እውነት በልቡ አምኖ በአፉ ሊመሰክር ይገባዋል (ሮሜ 10፥9-10)፡፡
በክርስቶስ መሠረትነት የተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር የዘለዓለም ሕይወትን የሚሰጥባት የሕይወት እርሻ ናት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “የእግዚአብሔር እርሻ ናችሁ፤ የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ፤ ከእርሱ ጋር አብረን የምንሠራ ነንና” (1ቆሮ.3፥9) ሲል የገለጣት ቤተ ክርስቲያንን ነው፡፡ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 13 በተለያዩ ምሳሌዎች ቤተ ክርስቲያንን ገልጧታል፤ ከእነዚህ ምሳሌዎች አንዱ እርሻ ነው፡፡ የእርሻው ባለቤት ራሱ እግዚአብሔር (ክርስቶስ) ነው፡፡ ይህ ጽሑፍ በተለይ በማቴዎስ ወንጌል 13፥24-30 የተመዘገበውን ምሳሌና በዚሁ ምዕራፍ ከቍጥር 36-43 ያለውን ትርጓሜ መሠረት ያደረገ ነው፡፡
http://4.bp.blogspot.com/-E1fLnxTxfg0/U-NAVag1sBI/AAAAAAAAAD4/72_1IaGg2HQ/s1600/seeds.jpg
ማቴዎስ 13፥24-30 “ሌላ ምሳሌ አቀረበላቸው እንዲህም አለ፦ መንግሥተ ሰማያት በእርሻው መልካም ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች። ሰዎቹ ሲተኙ ግን ጠላቱ መጣና በስንዴው መካከል እንክርዳድን ዘርቶ ሄደ። ስንዴውም በበቀለና በአፈራ ጊዜ እንክርዳዱ ደግሞ ያን ጊዜ ታየ። የባለቤቱም ባሮች ቀርበው። ጌታ ሆይ፥ መልካምን ዘር በእርሻህ ዘርተህ አልነበርህምን? እንክርዳዱንስ ከወዴት አገኘ? አሉት። እርሱም፦ ጠላት ይህን አደረገ አላቸው። ባሮቹም። እንግዲህ ሄደን ብንለቅመው ትወዳለህን? አሉት። እርሱ ግን፦ እንክርዳዱን ስትለቅሙ ስንዴውን ከእርሱ ጋር እንዳትነቅሉት አይሆንም። ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ፤ በመከር ጊዜም አጫጆችን። እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ልቀሙ በእሳትም ለማቃጠል በየነዶው እሰሩ፥ ስንዴውን ግን በጎተራዬ ክተቱ እላለሁ አለ።” 

ትርጉም፡ ማቴዎስ 13፥36-43 “በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው። የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት። እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው። እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል። የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”
እግዚአብሔር ንጹሑን ዘር በእርሻው ላይ ዘርቷል
ክርስስቶስ ያስተማረው ወንጌል በዚህ ዓለም የዘራው ንጹሕ የሕይወት ቃል ነው፤ የተዘራው ቃል እንደ በቀለ፣ እንዳፈራ፣ ፍሬም ለእግዚአብሔር ክብር እንደዋለ ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንማራለን፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች ክርስቲያኖች ዐላውያን ነገሥታት፣ መናፍቃንና ከሐድን በበዙበት ጊዜ ሁሉ የክርስቶስን ወንጌል እየሰበኩ በትውልዱ መካከል እንደ ብርሃን እያበሩ ኖረዋል፡፡ ዘመነ ሰማእታትን ስናስብ ይህን እውነት በእርግጥ እንረዳለን፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን የመሠረተበትን እውነት ስናይ እንደ ወርቅ የጠራ እውነት ነው፡፡ በእግዚአብሔር እርሻ ላይ ከእግዚአብሔር የተዘራ እንክርዳድ ፈጽሞ አልነበረም፤ሊኖርም አይችልም፡፡
ባለቤቱ እርሻውን እንዲጠብቁ ለሠራተኞቹ አደራ ብሎ ነበር፡፡
ሠራተኞች አደራቸውን ስላልተወጡ ቤተ ክርስቲያንን የሚጎዳ እንክርዳድ በቤተ ክርስቲያን ላይ ተዘራ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን ሠርቶ፣ መንጋውን ሰብስቦ፣ ለሐዋርያት አገልግሎቱን አደራ ሰጠቷል፤ እንክርዳዱ የተዘራው ሰዎቹ (ሠራተኞች) ተኝተው ሳለ ነው፤ ይህም ማለት የቤተ ክርስቲያን ጠላት ዲያብሎስ በቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ትምህርት የሐሰት ትምህርትን የዘራው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ተኝተው ሳለ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ተኝተው (ቤተ ክርስቲያንን በእግዚአብሔር ቃል የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን መወጣት ሳይችሉ ቀርተው) ወደ ቤተ ክርስቲያን የሐሰት ትምህርትን ያስገቡት መቼ ነው? ይህን ጥያቄ ለመመለስ እውነት መቼ ተሰበከ? እውነት ምንድን ነው? ወዘተ የሚሉትን ጥያቄዎች አስቀድሞ መመለስ ያሰፈልጋል፡፡
እውነት በእግዚአብሔር ገላጭነት አስቀድሞ በነቢያት በኋላም በክርስቶስ ሥጋዌና ባስተማረው ወንጌል፣ ሐዋርያት በሰበኩት ወንጌል የተገለጠ ነው፤ ይህን ቤተ ክርስቲያን ጠብቃ ስታስተምረው ቆይታለች፡፡ ከክርስቶስ ዕርገት፣ ከሐዋርያት ስብከት፣ በእግረ ሐዋርያት ከተተኩ ቅዱሳን አባቶች አገልግሎት በኋላ አንዳንድ ጊዜ በመከራ ፅናት፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በምቾትና በሥልጣን ፍላጎት ብዛት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የመንጋው እረኞች አንቀላፉ፤ በዚህ ወቅት የቤተ ክርስቲያን ጠላት ዋና ዋና የሚባሉ የክርስትና ትምህርቶችን የሚለውጥ፣ የሚያንቅና የሚያቀጭጭ፣ ፍሬ እንዳያፈሩ ብሎም ጨርሶ እንዳይኖሩ የሚያደርጉ የስሕተት ትምህርቶችን በቤተ ክርስቲያን ዘራ፡፡ ዋናው የስሕተት ትምህርት ሰለባ የሆነው ደግሞ የመዳን ትምህርት ነው፤ ክርስቶስ በትምህርቱ እርሱ እውነት፣ ሕይወትና መንገድ እንደሆነ፣ ከእርሱ በቀር በሌላ መንገድ (በኩል) ወደ አብ መድረስ እንደማይቻል አስተማረ (ዮሐ.14፥6)፡፡ ሐዋርያትም  “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና፡፡” (የሐዋ.4፥12) ሲሉ የክርስቶስን ወንጌል ሰበኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ በአጠቃላይ ሲታይ ዋናው መልእክቱ የሰው ልጅ በኀጢአቱ እንደተፈደበት፣ ራሱን ማዳን እንዳልቻለ፣ ሌላ ፍጡርም ሊያድነው እንደማይችል ማረጋገጥና ሰዎች ለመዳንና የዘለዓለም ሕይወትን ለማግኘት እግዚአብሔርን ብቻ ተስፋ ማድረግ እንዳለባቸው ማስተማር ነው፡፡ ይህን እውነት ነቢያት፣ ሐዋርያትና እውነተኞች የቤተ ክርስቲያን አባቶች ያውቁታል፤ ሰብከውታል፤ ለእኛም አስረክበዋል፡፡
እንክርዳዱ ከፍጡር መዳንን መጠበቅ፣ ፍጡራንን አድኑኝ ብሎ መማጸን፣ በአምልኮት ውስጥ ፍጡራንን ስማቸውን መጥራትና እንደፈጣሪ በሁሉም ቦታ ተገኝተው የሚሰሙ አስመስሎ ማነጋገር፣ በመንፈስና በእውነት የሚመለከውን እግዚአብሔርን በሚያመልኩበት ቦታና ሥርዐት ፍጡርን ማወደስ፣ ለፍጡር መንበርከክ፣ ለማይሰማ ታቦት፣ በሰው እጅ ለተሠራ፣ ሰዎች ተሸክመውት ለሚያንቀሳቅሱት ነገር፣ ምንጣፍ በየመንገዱ እያነጠፉ፣ እየወደቁና እየተነሡ፣ ሆ! እልልልል! እያሉ ማወደስ ይህ ሁሉ በእግዚአብሔር እውነት ላይ የተዘራ የጠላት እንክርዳድ ነው፡፡ ይህን ሁሉ የዘራው ጠላት የእግዚአብሔርን ክብር የማይወድድ ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ ይህ ጠላት በቤተ ክርስቲያን ይህን ሁሉ እንክርዳድ የዘራው መሪዎችዋን በትምህርተ ሃይማኖት ክርክር፣ በስልጣን ፍላጎት፣ በፖለቲካ ጡንቻ ሥር ካስተኛ በኋላ ነው፡፡ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ነቅተው ቤተ ክርስቲያንን ቢጠብቁ ይህ ሁሉ እንክርዳድ ሊኖር አይችልም ነበር፡፡

የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለጠላት እድል ሰጥተውታል፤ ለእውነት ባለመቆማቸው ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ ለራሳቸው ክብር ቅድሚያ በመስጠታቸው ቤተ ክርስቲያን የእንክርዳድ ማሳ (እርሻ) ሆናለች፤ ይህ የቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ልጆችን የሚያንገበግብ እሳት ነው፡፡
የመሪዎቹ እንቅልፍ የእግዚአብሔርን የንስሓና የተሐድሶ ድምጽ መስማት እስከማይችሉበት ደረጃ ድረስ ከብዶባቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ለምድሪቱ ቃሉን ላከ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት የገለጠውን እውነት እንዳይጠፋ ጠበቀ፤ በትውልድ መካከል የቃሉን ሐውልት አቆመ፤ ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ከክርስትና ይልቅ ምንኩስናን፣ ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ በብልሐት የተፈጠረውን ተረት (2ጴጥ.1፥16)፣ ከንጽሕና ይልቅ ርኩሰትንና ሙስናን፣ ከትሕትናና እውነትን ከመፈለግ ይልቅ ትዕቢትንና እውነተኞችን መግፋትን፣ በእግዚአብሔር ድምጽና ክብር ላይ መታበይን፣ ቤተ ክርስቲያንን በእነርሱ ሲኖዶስ ውሳኔና ብልሹ አስተዳደር ሥር ጠምዝዞ በመጣል እንደ ፍሪዳ አርዶ ሥጋዋን መብላት፣ አጥንቷን መጋጥ እንጂ እግዚአብሔርን መፍራት የለም፡፡

እንክርዳዱ ግን እያደገ፣ ስንዴውን እያነቀ፣ እያቀጨጨና እያመነመነ እንዲያውም ስንዴው እንደ እንክርዳድ እንክርዳዱ ደግሞ እንደ ስንዴ እንዲታይ እያደረገ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት “አዳኝ ክርቶስ ብቻ ነው” የሚለው ንጹሕ ስንዴ እንክርዳድ ሆኖ “የዓለም ቤዛ ድንግል ማርያም ናት” “ያለ ድንግል ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንድም” የሚለው “ወፍዘራሽ” (ዲያብሎስ የዘራው) እንክርዳድ ሀገራችን ኢጥዮጵያን ሁሉ እየሞላ ነው፡፡ የኦርቶዶክስ ተሐድሶ አገልግሎት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በቤተ ክርስቲያናችን እውነተኛ ትምህርት ውስጥ ተዘርቶ ያለው ወፍ-ዘራሽ የስሕተት ትምህርት እንዲለይና እንዲወገድ፣ ቤተ ክርስቲያንም ምእመናንን ወደ እግዚአብሔር እውነት የማድረስና የሰው ልጆችን የመዳን መንገድ የማሳየት አምላካዊ አደራዋን በአግባቡ እንድትወጣ ለንስሓና ለተሐድሶ በመቀስቀስ የበኩላችን ማበርከት ነው፤ እግዚአብሔር ነፍስን ይመልሳል፤ ሰዎችን ሁሉ ወደ እውነት ይመራል፤ ይህን የሚያደርገው ደግሞ በቃሉና በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ነውና ቤተ ክርስቲያን ይህን አምላካዊ ኀላፊነት ልትዘነጋውና ለጠላት እድል ልትሰጥ አይገባም እንላለን፤ ይህን የተማርነው ከእግዚአብሔር ቃል ነው፤ የእኛ የሆነ ከራሳችን ያመጣነው እውነት የለም፤ እውነትን በእውነት እናገለግላለን እንጂ በእውነት ላይ አንዳች ነገር አንጨምርም፡፡ ተሐድሶ የምንለውም ይህን ለእውነት መሰጠትን፣ እውነትን ማገልገልን፣ በእውነት ጸንቶ መኖርን ነው፡፡ እግዚአብሔር ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በተሐድሶ ወደ ክብሯ እንድተመለስ ያድርግልን፤ አሜን፡፡

6 comments:

 1. Well said. The truth is always hard to swallow because we have been thought one way for so long traditionally. We should only worship in spirit and truth. I wounder if people will say on judgment day that the leader of the church didn't tell them the truth.

  ReplyDelete
 2. Thank you! keep it up! we want the revival of our Church.

  ReplyDelete
 3. wedet, wedet, be ewunet enkrdadu ye Luther nufake aydelmen??????

  ReplyDelete
 4. Wedet wedate mk newa enkerdad yezerawo .men tetake slew degmo.

  ReplyDelete
 5. ENKIRDADUN YEZERAW YEHASET ABAT DEYABELOS NEW.ENKIRDADUM ENNANT LEJOCHU NACHU.YORTODOX TEWAHIDO TELATOCH.

  ReplyDelete
 6. Yewngel telat diyabilos yemitekembachwo lijjochwo bemenfesem ersunu yemimeslu mkwoch nachew bezich kidist b krstiyan ersha mehal enkerdad yezerut.

  ReplyDelete