Saturday, August 23, 2014

በጾመ ፍልሰታ ሲመለክ የሠነበተው ማነው?የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ድንግል ማርያምን አከብራታለሁ እንጂ አላመልካትም ስትል በተደጋጋሚ ተደምጣለች፡፡ ይህ አባባል ትክክል ነው፡፡ በዚህ በኩል ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚስማሙ ይመስለናል፡፡ ድንግል ማርያምን የማያከብር ክርስቲያን ሊኖር አይችልምና፡፡ ሆኖም ልዩነት የሚፈጠረው አክብሮት የሚባለው ጉዳይ አምልኮት ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ ድንግል ማርያም ጌታ ለእናትነት የመረጣት ብትሆንም ከቅዱሳን አንዷ ናት እንጂ ወደአምላክነት ደረጃ ከፍ ያለች ሌላ አካል አይደለችም፡፡


 በኦርቶዶክስና በካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ግን እርሷን በማክበር ስም ድንግል ማርያም እየተመለከች ትገኛለች፡፡ በዚህ ሐሣብ ብዙዎች እንደማይስማሙ ይታወቃል፡፡ የማይስማሙትም የድንግል ማርያም ክብር የተነካና እርሷ የተዋረደች ስለሚመስላቸው ነው፡፡ እውነታው ግን እነርሱ እንደሚያስቡት አይደለም፡፡ ድንግል ማርያም በአክብሮት ስም እየተመለከች ነው ማለት እየታየ ያለውን እውነታ መግለጽ እንጂ እርሷን ማዋረድ ሊሆን በፍጹም በፍጹም አይችልም፡፡ ይህ ከቶም የማይታሰብ ነውና፡፡
በተጠናቀቀው በጾመ ፍልሰታ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን በየገዳማቱና አድባራቱ ሱበኤ ገብተው እንደሰነበቱ ይታወቃል፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ሱባኤ ገብቶ መጸለይ መልካም ነው፡፡ ችግሩ በሱባኤ ስም በእግዚአብሔር ፊት ሳይሆን በማርያም ስም መገኘቱ ነው፡፡ እስኪ እውነቱን እንነጋገር! ሰዉ በዚህ የጾም ወቅት ሱባኤ የገባው ወደማን ለመጸለይ ነው? ወደእግዚአብሔር ወይስ ወደ ማርያም? በሱባኤው ሲመለክና ሲወደስ የሰነበተው ማነው? እግዚአብሔር ወይስ ማርያም? በሱባኤው ውዳሴው ቅዳሴው ሲተረጎምለት ሲቀደስለት የነበረው ማነው? እግዚአብሔር ወይስ ማርያም? መልሱ ቀላል ነው፡፡ ማርያም ናት፡፡ 

ሰው ወደ እግዚአብሔር ካልጾመና ካልጸለየ ሱባኤ ቢይዝ፣ ሽንበራና ውሃ እየተመገበ መሬት ላይ ተኝቶ ቢሰነብት፣ የጾም ጸሎቱ አድራሻ እግዚአብሔር ካልሆነ ከስሯል፡፡ በጾመ ፍልሰታ ሕዝቡ ሲጾምና ሲጸልይ የነበረው ወደእግዚአብሔር ነው ይባል እንጂ በአብዛኛው ሲጾምና ሲጸልይ የነበረው ወደ ማርያም ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ ይህ ጾም ለእግዚአብሔር ብቻ መቅረብ የነበረበት ውዳሴና ቅዳሴ እንዲሁም አምልኮ ለማርያም የቀረበበት፣ እርሱን ደስ በማሰኘት ፈንታ ምስጋናውንና ክብሩን ለማርያም በመስጠት እግዚአብሔርን ያስቀናንበት ወቅት ነው፡፡ እስከ መቼ ይሆን እግዚአብሔርን ብቻ ወደማምለክ፣ ክብርን ውዳሴንና አምልኮትንም ለእርሱ ብቻ ወደመስጠት የማንመለሰው? እውነት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል የማያውቀውን ተረት ፈጥረን በሐሰት ማርያም ሞታ አልቀረችም ተነስታ አርጋለች ማለታችን ሳያንስ ወደ እግዚአብሔር ሳይሆን ወደ ማርያም እንጸልያለን ብለን አምልኮተ ባእድን የምንለማመደውስ እስከ መቼ ይሆን? 

ብዙዎቻችን ማርያምን ወደማምለክ የተሸጋገርነው በኢየሡስ ክርስቶስና በእናቱ መካከል የእናትና ልጅ ግንኙነት አለ በሚልና አምልኮውን ቤተሰባዊ በማድረግ ነው፡፡ ነገር ግን እንዲህ ያለው ነገር በአሕዛብ አማልክት ዘንድ እንጂ በእውነተኛው አምላክ በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ ከቶ የለም፡፡ ይህ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፡፡ ድንግል ማርያም እግዚአብሔርን ከሚያመልኩት ቅዱሳን መካከል ነች እንጂ በአክብሮት ስም አምልኮትን የምትቀበል ሌላ አካል አይደለችም፡፡ ስለዚህ በማርያም ስም የተደረሰው ውዳሴና ቅዳሴ ሁሉ ተገቢነት የሌለው አምልኮ ባእድ ነው፡፡ በክርስትና ትምህርት ሊመለክና ሊወደስ የሚገባው ሁሉን የፈጠረ የሁሉ ጌታና አምላክ የሆነው እግዚአብሔር ብቻ ነው እንጂ ከእርሱ ጋር አምልኮትን የሚጋራ ሌላ አካል የለም፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እያስተማረ ሳለ አንዲት ሴት ተነሥታ ድምጽዋን ከፍ በማድረግ ውዳሴ ማርያምን አቅርባ ነበር እንዲህ በማለት “የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው”  ውዳሴ ማርያምን ለመጀመሪያ ጊዜ የደገመችው ይህች ሴት ሳትሆን ትቀራለች?  የጌታችን መልስ ምን ነበር?  “አዎን፥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው አለ።” (የሉቃስ ወንጌል 11፡27-28) የጌታ ምላሽ ግልጽ ነው፡፡ በዚህ ምላሽ መሰረት ሰው ብፁዕ የሚሰኘው የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ በመፈጸሙ ነው እንጂ በሌላ አይደለም፡፡ የሴትየዋን ውዳሴ ማርያም ጌታ እንዳልተቀበለ ግን ግልጽ አድርጓል፡፡ እኛም ከዚህ ምላሽ ትምህርት መውሰድ ካልቻልንና አከበርን ብለን ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለሌላ ብንሰጥ ተሳስተናል፡፡ ስለዚህ በጾመ ፍልሰታ ያሳዘነውንኛ አምልኮቱን ለፍጡር በመስጠት ያስቆጣነውን አምላካችንን በንስሐ እንታረቀው፡፡

23 comments:

 1. lebe yalew leb yibel

  ReplyDelete
 2. This is definetly false idea!

  ReplyDelete
 3. Yilq antena anten yemeselu denaqurt lib yibelu getama melsun sete bitsu nachew yetebalut yedinglin widassie "awon "bilo new mels yesetew lante ledenqoro gin awon malet aydelem malet honebih

  ReplyDelete
  Replies
  1. በጣም የምታዛዝን ማስተዋል የጎደለክ ነክ፡፡ ምክንያቱም ግልፅ ተደርጎ የተነገረክን የማታስተውል መሆንክን ለማንም ይታያል፡፡ ለስድብ የመጋበዝክም ምክንያት ሰይጣን የሀየማኖት ካባ አስለብሶክ የሸወደክ መሆኑን ያሳያል፡፡ የሚሻልክ በጭፍን መቃወም ሳይሆን በቅንነት ነገሮችን ማየት ነው፡፡ ሰው ደደብ የሚባለው አንተን ሲመስል መሆኒን አትዘንጋ፡፡ ይሆንን ያልኩክ እያዘንኩኝ ነው ግን “ሰይጣን እዳያስተውሉ አይምሮአቸውን አሳወረ” የተባልከው ላንተ መሆኑን ለሚያስተውል ይገባዋል ፈጣሪ ይድረስልክ

   Delete
 4. ERSUNEN EKO CHER HOY SILEW ENE AYDELEEHUM YALEWEN MEN BELEH LETEREGUMEW NEW

  ReplyDelete
 5. Leka Tsehafiwim honu abaselama blog orthodox aydelachihum. Lezenedochachu gira letegabutina letegabachihut lenante tiru fez yizachihuwal. Lib yistachu - awkachu motachual. Ye egziabherin kal yetebekech bitsit gin emebetachin Nat. Endekalih yihunilign bila yamenech. Pente tehadiso hula zim bileh tafezaleh aydel. ..

  ReplyDelete
 6. this is the alert bell.pls people come to the truth,the truth shall set u free.

  ReplyDelete
 7. It is false article! There is only one God Orthodox and catholics worship but respect St. Mary

  ReplyDelete
 8. Kiber hulu amleko for father son holy spirit .yihun.ene yemamenew yemamelkew hatiyateh teszersolhal lilegne yemichelewom Nefsenena segayen liyaden yeichelewon getta
  bicha new.

  ReplyDelete
 9. Adegegna bozene kelawach pente

  ReplyDelete
 10. 1-እመቤታችንን እነደማናመልካት ካወቃችሁ ጥሩ ነው!!
  2-የእኛን ኦርቶዶክሳዊ ድርጊቶች ሁሉ ጓዳሰራሽ ኋላቀር ባህል አድርጎ ከመመልከት እመቤታችንን ማክበር ዓለምአቀፋዊ ይዘት ያለው መሆኑንና በቢሊዮን በሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳውያንን እና ካቶሊካውያን ጭምር በአማላጅነቷና በወላዲተ-አምላክነቷ ሰዐሊ-ለነ እያሉ እንደሚያከብሯት ከተረዳችሁ መልካም ነው፡፡የእመቤታችንን አማለጅነት ማመን ከዘርዐ-ያዕቆብ ወዲህ የመጣ ለማስመሰል መማሰናችሁን መተዋችሁም ተመስገን ነው፡፡
  3-የፍልሰታው ሰዓታት “…ሰአሊ ለነ ማርያም ኀበ ወልድኪ ኄር መድኃኔዓለም…ማርያም ሆይ የዓለም መድኃኒት ከሆነው ቸር ልጅሽ ለምኝልን፣ትእምርተ-ሰላምነ ዘኪያሁ ንትአምን እብነ ሕይወት ወርእስ-ማዕዘንት ውዕቱ ኢየሱስ ክርስቶስ….የሰላማችን ምልክት የምናምንበት ሕይወት ድንጋይ(መሰረት) የማዕዘን ራስ እሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው….” ይላል፡፡
  4-የጠዋቱ ውዳሴ ማርያም “….ፈቀደ እግዚእ ያግእዞ ለአዳም ኅዙነ ወትኩዘ-ልብ ወያግብኦ ኀበ-ዘትካት መንበሩ ሰአሊ ለነ ቅድስት….ያዘነ አዳምን ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ ከወደደ ልጅሽ ድንግል ለምኝልን…” ይላል፡፡
  5-ቀን በቅዳሴ ማርያም “…ኦ ድንግል እንተ-ወለድኪ ለነ መብልዓ-ጽድቅ ዘበአማን ወስቴ-ሕይወት ዘበአማን…እውነተኛውን የጽድቅ መብል፣እውነተኛውን የሕይወት መጠጥ የወለድሽልን ድንግል…” እንላታለን፡፡
  6-ከዛም ቅዳሴውን “…ቁርባን በመቀበል እግዚአብሔር ምስለ ኩልክሙ…እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን” ተብለን ሰርሖተ ሕዝብ ይሆናል፡፡
  7-እመቤታችንን ማክበር ማለት ከላይ የተተቀሱትን አይነት በሥርዓተ-ቤተክርስቲያን የተደነገጉ ቀኖናዎችንና ያሬዳዊ መዝሙሮችን የተከተሉ ድርጊችን በመፈጸም የእሷን አማላጅነት፣የልጇን መድኃኔዓለምነት (ይሄ “የግል አዳኝ” ምትሉትን በመጽሐፍ ቅዱስ ያልተጻፈ ካፒታሊስታዊና ግለሰብ ተኮር ሊበራሊዝም መርህ እርሱት!!) አምኖ መከተል ነው፡፡
  8-“አዎን፥ ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው አለ።” (የሉቃስ ወንጌል 11፡27-28…ጥሩ ጥቅስ ነው፡፡ግን በሞቴ!!ይሄ ሲተረጎም እመቤታችንን አታክብሩ ማለት ነው እያላችሁን መሆኑ ነው??አይይይ!!!
  ተመየጢ፣ተመየጢ…ተሐድሶ ቀሳጢ!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ያልከው ሁሉ ምንም ረብ የለውም አውነት ሌላ ጭፍን ሀይማኖተኛ መሆን ሌላ ጌታ ያብራልክ

   Delete
 11. Sewuye"bitsuan yemibalut qalun semtew yemifetsemu nachew"yalew Emebetachin qalun semta yideregelegn bila qalun yefetsemech mehonuan eyayew,awuqeh wede lela teteregumaleh. Emebetachin qalun semta endalfetsemech bitsehet atebalem setel ye Amlaken kalun mekadeh new.Mezmur32:1"le qenoch mesgaba yigebal"

  ReplyDelete
 12. Betsuhanes Ye Egziabhern Kal Semetew Yemeyadergu Nachew Lik new Egna ORTODOXSAWEYANOCH kekalu saneweta Dengel Weladite Amelakin Enamesgenalen Enawedesalen Enakeberalen mikeneyatum kalu yazenal Tewled hulu betsehet yelugnal yamesgenugnal kalech egna teweled ayedelenem ende wedaje??? ke Qidus Gebreal enbeletalen ende ?Elesabet endamesgenechat enamesgenatalen negestitu bekegnhe tekomalech yalew lemehonu manin yihon??? meles setugn Bemabezat Ayedel Bemasater endalew Qidus Heryakos Ye Emebetachen Fikerewa Amalajenetewa Enatenetewa Yebezalet sew new yemigebaw Teyeku likawenet alun bedereja kemetemetem memar yikedem emebete hoy habete neshena bamesgenesh diyabilos bikena gena ale gena Addis mesegana yeketelal....

  ReplyDelete
 13. ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከማሪያም መወለዱ እኛን ከሃጥያት ለማዳን ነዉ እንጂ ዓለም በድንግል ማርያም አማላጅነት እንዲድን አይደለም። እኔ ቀናተኛ አምላክ ነኝ እያለ እግዚአብሄርን ለማስቀናት መሞከር ሃጢያት ነዉ። የሚመለከዉ የሚሰበከዉ የሚለመነዉ የሚታመነዉ አንዱ ኣምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነዉ።

  ReplyDelete
 14. i will advise the protestants to learn Amharic language to properly distinguish 'AMLKOT' VS 'AKBROT'. still you are confused or purposely want to confuse others.

  ReplyDelete
 15. Protestants are dying out following the teachings of santan,their forefather.We tewahidos worship St. Marry for she pray for us.Now she is in heaven as St.John writes in raiy12:1.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Orthodoxy doesn't teach to worship Mary. You're the one following satan's teaching

   Delete
 16. እንግባባ…ቃሉ ግልጽ ነው!!
  1. ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽእት ይሉኛል!!!…..እንዴትም ቢተረጎም “በመገረም” የሚቆም አይደለም!!ያለፈውም፣ያለውም፣የሚመጣውም ትውልድ ያመሰግኑኛል ማለት ነው!!....ትውልድ ሁሉ….የሚለው ቃል ይሄን ይገልጻል!!
  2. ድርሰቱም ….ሰዐሊ ወጸልይ ለነ ምህረተ ሀበ ፍቁር ወልድኪ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይስረይ ለነ ኃጣውኢነ- ኃጢአታችንን ይቅር ይለን ዘንድ ከጌታችን ከመድሀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን…ከሚለው ቃል ውጭ ሙሉ ጸሎቱ በሉቃስ ወንጌል ምእራፍ 1ቁ 26 እስከ 56 ውስጥ የሚገኝ ቅ/ገብርኤልና ኤልሳቤጥ ለእመቤታችን ካቀረቡት ምስጋና የተወሰደ እንጅ እናንተ እንደምትሉት የንጉሥ ዘርዐያዕቆብ ድርሰት አይደለም!!
  3. የእሱ(የዘርዐያዕቆብ) ድርሰት ቢሆንማ ሁሌም እንደምንለው እመቤታችን የምትመሰገነው በኢትዮጵያ ብቻ ሆኖ ይቀር ነበር!!ግን አደለም!!የምስራቅ ኦርቶዶክሱም፣ካቶሊኩም፣ኦሪየንታሉም ከሉተር ልጆች በቀር አማናዊውን መድህን ያስገኘችውንና በመ/ቅዱስ ውስጥ በመልአክ ቃል ብጽእት ተብላ ከሴቶች ሁሉ ተለይታ የተጠራቸውን ወላዲተአምላክ ሰአሊ ለነ ቅድስት ሳይሉዋት አይውሉም!!የእሱዋ ምስጋና በሀገር ብቻ ሳይሆን በአህጉራትም የታወቀ ነው!ወንዝ ይሻገራል!!
  4. ስለ መላእክት በመዝ 102 ቁ 20…ባርክዎ ለእ/ር ኩልክሙ መላእክቲሁ-መላእክት ሁሉ እ/ርን ባርኩ…ተብሎ ተጽፎልሀል!!እና ቅ/ዳዊትን ያህል ነቢይና መዘምር መላእክትን እንዲህ በጸሎቱ ሲያናግራቸው ለጣኦት ምስጋ እያቀረበ ነበር ልትለን ነው???ባርክዎ ያለው ዳዊት ሰአሉ ለነ-ለምኑልን እንዳይል የትኛው ጥቅስ ነው የሚከለክለው??እስኪ ጨምረህ በመዝሙር 148 የተጻፈውን አንብበው!!መዝሙር 32 ቁ 1…..ተፈስሁ ጻድቃን በእ/ር-ጻድቃን በእ/ር ደስ ይበላችሁ…..ይላል ቅ/ዳዊት ያሉትን በሞተ ስጋ ከተለዩት ሳይለይ ነው…ደስ ይበላችሁ…የሚለው!!እኛም እሱን አብነት አድረገን ቅድስት ድንግል ማርያምን ደስ ይበልሽ ስንላት ልባችን ሀሴት ያደርጋል!!
  5. ደጋግሜ እንደምለው የሞቱ ቅዱሳንና መላእክት አያማልዱም የሚል የመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ የለም!!ወፍራሞቹ ፓስተሮች ያማልዳሉ እየተባለ በክርስቶስ ህያው የሆኑት እነ ቅ/ጳውሎስ አያማልዱም ማለት የክርስቲያንን ሞት ከአረማዊ ሞት ለይቶ ካለማወቅ የተነሳ የሚመጣ አመለካከት ይመስለኛል!!
  ለማንኛውም ስለ እመቤታችን ምስጋና ስላነሳችሁ መዝሙረኛውን ደጋግሜ ብጠቅስም የልቤ ስላልደረሰ መመለሴ እንደማይቀር ገልጨ ሀሳቤን ልግታ!!
  ሰዐሊ ለነ ቅድስት!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. yetemolahewun eyafesesik kemitinor wede kalu bitimeles melkam new...lerejim gize balemawe ahun yemitilewun..kemitilewum belay tikis eyederederin metalelachnn sasib yegetan tigist adenikalehu. esu masitewaln kalisete ewuket yemimesilh hulu yigodahal.tikis metikes ewuket adelem.tikisun wede rasih hasab mewusedim bisiletihn ayasayihim.yebizu sew dikimetim tikisun metsehafu endemilew sayihon rasaqchew endemifeligut meterigomachew new...Geta yikir yibelih!!

   Delete
 17. ሰይጣን በእባብ አካል ተሰውሮ ሔዋንን፤ በእርሱዋም አዳምን በማሳት በእነርሱ ላይ ሞት እንዲሠለጥንባቸው ስላደረገ “በአንተና በሴቲቱ መካከል፣ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደረጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኮናውን ትነድፋለህ” በማለት የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር ፈረደበት፡፡ “በአንተ” የተባለው ሰይጣን ሲሆን፣ “በሴቲቱ” የተባለችው ቅድስት ድንግል ማርያም ናት (ገላ.4፡4)፣ “በዘርህ” ሲል የዲያብሎስ የግብር ልጆችን ሲሆን(ዮሐ.8፡49)፣ “በዘርዋ” የተባለው ክርስቶስ ነው(ገላ.3፡16)፡፡ ትርጉሙ እንዲህ አንደሆነም ወንጌላዊው ዮሐንስ “ዘንዶው በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የጠበቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ”አለን፡፡(ራእ.12፡17) እባብ የተባለው ሰይጣን ስለመሆኑም “ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ”(ራእ.12፡9) ብሎ ጻፈልን፡፡
  "አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ሰዳዴሆሙ ለአጋንንት ስድዶሙ እግዚኦ ለአጋንንት እምየማንነ ወእምጸጋምነ ወእምዛቲ መካንነ ይርኃቁ እምኔነ ለእለ ይጸብዕዋ ለነፍስነ" መጽሐፈ ሰዓታት
  ሲተረጎም እንዲህ ይላል
  "አቤቱ አጋንንትን የምታሳድዳቸው አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ከግራ ከቀኛችን ከዚህችም ቦታችን ከእኛም ይርቁ ዘንድ ሰውነታችንን የሚዋጓት አጋንንት አሳዳቸው፡፡"

  ReplyDelete
 18. አብ ያከበራት ወልድ ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስ የነሳባት መንፈስ ቅድስ ያከናወነባት ታላቅ እናት........ስለሷ.........................

  ReplyDelete
 19. በመጽሀፍ ቅዱስ
  ዲያብሎስ ሴቲቱን እነዳላገኘ ባወቀ ጊዜ ከዘሩአ የቀሩትን ሊዋጋና ሊያጠፋ በባህር አሸዋ ላይ ቆመ ይላል ምናልባትም ዲያብሎስ የቆመበት አሸዋ አንተና መሰሎችህ ሳትሆኑ አትቀሩም
  ቅድስት ድንግል ማርያም አትመለክም ልጁአ የመለካል እንጅ እርሱአ ትመሰገናለች የዘመርላታል ትከበራለች ከአምላክ ቀጠሎ ያለዉ ክብር ሁሉ ይሰጣታል እንጅ

  ReplyDelete