Wednesday, August 27, 2014

ማርያም ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም ብትባል ችግሩ ምንድነው?

Read in PDF

ማኅበረ ቅዱሳን የተባለው ስብስብ ለኦርቶዶክሳዊት ትምህርት ዋና ጠበቃ ነኝ በማለት ከእኔ በላይ ለአሳር የሚል የግብዞች ስብስብ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት የሚለውም ምርቱና ግርዱ ያለየውን አሰስ ገሰሱን ሁሉ ነው እንጂ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሰረተውንና ከእርሱ ጋር የማይጣላውን ትውፊታዊ ትምህርት ብቻ አይደለም፡፡ ለማቅ መጽሐፍ ቅዱስ ከቤተክርስቲያን መጻሕፍት አንዱ እንጂ ዋናው አይደለም፡፡ ይህን አስተያየት ከዚህ ቀደም የማቅ አንዱ አውራ የሆነው ዳንኤል ክብረት ለዕንቁ መጽሔት በሰጠው አስተያየት መናገሩ ይታወሳል፡፡ እርሱ እንዲህ ነበር ያለው “የብዙ መጻሕፍት ባለቤት የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን እንዴት በአንድ መጽሐፍ ቅዱስ ተሳስተሻል ትባላለች?” ይህ የአላዋቂ አስተያየት ነው፡፡ ለዳንኤልና ለመሰሎቹ መጽሐፍ ቅዱስ የክርስትና ትምህርት ሁሉ ምንጭ ሳይሆን ከቤተክርስቲያን መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡ ያሳዝናል!! እንዲህ ከሚያምንና ከሚያስተምር ስብስብ የጠራ የክርስትና ትምህርት ማግኘት ዘበት ነው፡፡ ታዲያ ማርያም ቤዛዊተ ዓለም ብትባል ምን ችግር አለው ቢሉ ምን ይደንቃል፡፡
የማህበረ ቅዱሳን ሰዎች ያላቸውን የዘመናዊው ትምህርት ዕውቀት መጽሐፍ ቅዱስን ለማጣመምና እንደ አሰስ ገሰስ ለሚቆጠረው የስህተት ትምህርታቸው ቃሉን እየጠመዘዙና እያጣመሙ ሽፋን ለማድረግ ነው የሚጠቀሙበት፡፡ ማርያም ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም ትባላለች የሚለውን ዓይን ያወጣ የስሕተት ትምህርት ከማውገዝ ይልቅ ሊስማማው ቀርቶ አብሮት ሊሄድ የማይችለውን ጥቅስ በግድ እየለጠፉበት ድጋፍ ይሁነን ይላሉ፡፡  

ከሰሞኑ ማርያም ቤዛዊተ ዓለም ብትባል ችግር እንደ ሌለው የተናገረው የማቅ ሰባኬ ወንጌልና ዲ/ን ሄኖክ ሃይሌ ነው፡፡ ይህን ያለውም ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ በማኅበሩ የአየር ሰዓት ላይ በሰጠው “ስብከት” ነው፡፡ ስብከቱ ሁሉ ስለማርያም ሲሆን በዚህ ላይ በተለይ ቤዛዊተ ዓለም ብትባል ምንም ችግር የለውም ባለው ላይ አስተያየት መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ሄኖክ እራቀቃለሁ ብሎ ኢትዮጵያውያን ለልጆቻቸው ቤዛ፣ ቤዛዊት እያሉ ስም በሚያወጡበት አገር “ማርያም ቤዛዊ ዓለም” ብትባል ምን ችግር አለው ሲል ትንሽ እንኳን አፉን አላነቀፈውም፡፡ እውን ማርያምን ቤዛዊተ ዓለም ለማለት ይህ በቂና አሳማኝ ምክንያት ነውን? ቤዛ ዓለም ክርስቶስ ብቻ ሆኖ ሳለ ማርያምን ቤዛዊተ ዓለም ለማለት የደፈረች ቤተክርስቲያን ለሕዝቡ ምን መልካም ነገር ልታስተምር ትችላለች? ከዚህ አንጻር ሕዝቡ ልጁን ቤዛ ወይም ቤዛዊት ቢል ምን ይደንቃል? ደግሞስ ቤዛ ወይም ቤዛዊት የሚለውን ደህና ስም አወጣሁኝ ብሎ እንጂ ማርያም ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም በተባለችበት መንገድ ነውን? ከምንም በላይ ግን ሰዉ ልጁን በዚህ ስም መሰየሙ ማርያምን ቤዛዊተ ዓለም ለማለት ማስረጃ ተደርጎ ለመቅረብ ምን መነሻ ይኖራል? ይህ ስህተትን በእግዚአብሔር ቃል ከማረም ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል ለስህተት መሸፈኛ አድርጎ እንደመሰዋት ይቆጠራል፡፡
ማርያምን ቤዛዊተ ዓለም ለማለት ማስረጃ ተደርጎ የተጠቀሰው ሌላው ጥቅስ “ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው።” (ምሳ. 21፡18) የሚለው ነው፡፡ በዚህ ጥቅስ መሰረት ኃጥእ የጻድቅ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ከተባለ ታዲያ ማርያም ቤዛዊተ ዓለም ብትባል ችግሩ ምንድነው ይላል የማቁ ሰባኬ ወንጌል ሄኖክ፡፡ ይህ ጥቅስ ማርያምን ቤዛዊተ ዓለም ለማለት በቂ ማስረጃ ነውን? ኃጥእ የጻድቅ በደለኛ የቅን ሰው ቤዛ ነው ማለት ምን ማለት ነው? ጻድቅ የሚድነው በኃጥእ ቤዛነት ነው ማለት ነውን? በፍጹም፡፡ ስለዚህ ለኃጥእና ለበደለኛ የተሰጠው ቤዛ የሚለው ስያሜ ከክርስቶስ ቤዛነት ጋር የሚያያዝ ስያሜ እንዳልሆነ መረዳት ማስተዋል ነው፡፡
ሌላው ሄኖክ ቤዛ ተብሏል ብሎ የጠቀሰው ሙሴ ነው፡፡ “ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።” (የሀዋርያት ስራ 7፡35) የሚለውም ሙሴ የእስራኤል ነጻ አውጪ ሆኖ መላኩንና እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ነጻ ማውጣቱን የሚያስረዳ እንጂ ሙሴ የእስራኤል ቤዛ ነው የሚል ትርጉም የለውም፡፡ ሙሴም በዘመኑ ይህን ከመፈጸም በቀር ለእስራኤል ቤዛ ሆኖ ስለመለወጡ ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም፡፡ 
ከምንም በላይ ግን ማርያምን ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም ከማለት በቀር እንዲህ የተባለችው በምን ምክንያት እንደሆነ ሄኖክ ለማብራራት አልሞከረም፡፡ ቢሞክር ከማይወጣው ችግር ውስጥ እንደሚወድቅ ያውቀዋልና ቤዛ መባሏ ብዙ እንደማያስደንቅ ብቻ ጠቁሞ ማለፍን ነው የመረጠው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይሆን ሌሎች የቤተ ክርስቲያን መጻህፍት ማርያምን ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም በማለት ይጠሯታል፡፡ የዓለሙ ሁሉ ቤዛ ማለት ነው፡፡ እውን ይህ ስያሜ ለማርያም ይስማማታል ወይ? ማርያም ለዓለሙ ሁሉ ቤዛ የሆነችው መቼ ነው? በምንስ ጉዳይ ነው? ለማርያም የክርስቶስን ስፍራ ካልሰጠን በቀር ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት የሚቻል አይደለም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቶስ ራሱን ለሁሉ ቤዛ አድርጎ እንደሰጠ ይናገራል፡፡ “አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤” (1ጢሞ. 2፡5-6)፡፡ እንግዲህ ራሱን ለሁሉ ቤዛ አድርጎ የሰጠው እርሱ ብቻ ከሆነ ማርያምን ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም ብሎ መሰየም ለምን አስፈለገ? ይህ የክርስቶስን ቤዛነት ማቃለል አይሆንምን? ስለዚህ ማርያም ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም የተባለችበትን አውድ በሚገባ መፈተሽ ይገባል፡፡ ማርያም ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም መባል የለባትም የምንለው ቤዛ ኩሉ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ስለሆነና እርሱ ቤዛነትን ያልከፈለለት ሰው ስለሌለ ነው፡፡ ምክንያቱም “ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ” ነው የሚለው፡፡ በዚህ ውስጥ ማርያምም ትካተታለች፡፡ ክርስቶስ ስለእርሷም ሞቶላታል፡፡ ቤዛዋ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ለእርሷ ቤዛ መባል ፈጽሞ አይስማማትም፡፡ ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም የሚለው ስም በልኳ ያልተሰፋ ስም ነው የሚሆነው፡፡ ቤዛ ናት የሚል ካለ ግን በትክክል ቤዛ የሆነችበትን ምክንያት፣ ቤዛ የሆነችለትን ሰው ወዘተርፈ ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡
እንዲህ ማድረግ ስለማይቻል ግን አንዳንዶች ቀድሞ “ነይ ነይ እምዬ ማርያም ቤዛ ነሽ አሉ ለአዳም” ሲሉ ይዘምሩ የነበረውን ተሐድሶ አድርገውበት “ነይ ነይ እምዬ ማርያም ልጅሽ ቤዛ ነው ለአዳም” ወደማለት ተሸጋግረዋል፡፡ ይህ መልካም ነው፤ ነገር ግን በእኛ ጥሪ ላትመጣ ማርያምን ነይ ነይ ማለቱም ከንቱ ጩኸት ስለሆነና ትክክልም ስላይደለ ይህም ሀሳብ ሌላ ተሐድሶ ያስፈልገዋል፡፡ “በመከራ ቀን ጥራኝ አድንህማለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ” ያለው ፈጥኖ የሚደርስልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን ብቻ ልንጠራው ይገባል፡፡ (መዝ. 50፡15)፡፡

27 comments:

 1. Endiyaw yih MK yegon wugat honebachihu aydel? Eyecheferachihu tselyubet.

  ReplyDelete
  Replies
  1. እግዚአብሄር ብርሃን ሆኖ ሳለ ቅዱሳንን እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ ካለ ልንከለክለው ነው፡፡ ማቴ. 5፡14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። አለም የሚጣፍጠው በጌታ ነው ግን እሱ እራሱ ቅዱሳንን የዓለም ጨው ናችሁ አለ ማቴ 5፡13 እናንተ የምድር ጨው ናችሁ ታዲያ የናነተ መቅናት የት ለመድረስ ነው፡፡
   እመቤታችንን አረጋዊ ስምዖን አንቺ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል ብሎ ስደት መከራ እንደሚያጋጥማት ነግሮዋታል ሉቃ. 2፡34-35 ስምዖንም ባረካቸው እናቱን ማርያምንም። እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት። ታዲያ ከዚህ በላይ ቤዛነት ምን አለ፡፡ ሰዎች ሌሎችን ለማዳን የሚከፍሉት መስዋእትነት ቤዛነት ነው፡፡ እመቤታችንም ስለኛ ወደዚህ ዓለም የመጣውን ጌታ ለማሳደግ መከራ አይታለች መስዋእትነት ከፍላለች፡፡ ቅዱሳን ብዙዎች ይድኑ ዘንድ እስከሞት ደረስ የታመኑ ሆነዋል ቤዛ ሆነዋል፡፡ እመቤታችንም ሴት ስትሆን ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ ተብላለች ፡፡ ሙሴም እስራኤል ዘስጋን ከምድረ ግብጽ ለማውጣት ባደረገው መሰዋትነት ቤዛ ተብሎዋል ታዲያ እመቤታችን ጌታን ይዛ ወደ ምድረ ግብጽ ያደረገችው ስደትና መመለስ ለምን ቤዛ አያስብላትም ያውም ለኛ ለእስራኤል ዘነፍስ፡፡

   35 ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።
   36 ይህ ሰው በግብፅ ምድርና በኤርትራ ባሕር በምድረ በዳም አርባ ዓመት ድንቅና ምልክት እያደረገ አወጣቸው።
   37 ይህ ሰው ለእስራኤል ልጆች። እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል፤ እርሱን ስሙት ያላቸው ሙሴ ነው።
   ስለዚህ አትቅኑ መናፍቃን በአባ ሰላማ ስም አትነግዱ፡፡ ሰይጣን ገና ያብዳል፡፡

   Delete
 2. lemenkef yemtkenutn yakil lemastemar erasachihun azegaju bergit lemawok yaltadele chinklat lenekefa tewodadari yelewum

  ReplyDelete
 3. እግዚአብሄር የባርክህ አንተን የመሰለ ሰው እግዚአብሄር ስለሰጠን እጅግ ደስ የለናል በቆራጥነት ለመልካም ነገር ለጌታ ነገር እየሰጠከው ያለውን ዋጋ ጌታ ያየዋል፡፡ በርታ ለእውነት መኖር ደስ የላል ካለማወቅ የገላገለክን እግዚአብሄር ተናገርለት በርታ በርታ

  ReplyDelete
 4. ስሟ ሲጠራ የሚንቀጠቀጥ ዲያብሎስ ነው፡፡ የእርሱ የግበር ልጆች፡ ተንገብገቡ፡፡ ክብሯን አትቀንሱት፡፡ ምክንያተ ድኂን ናትና ይህ ስም ይገባታል፡፡ ስሟ ሲጠራ የሚንቀጠቀጥ ዲያብሎስ ነው፡፡ የእርሱ የግበር ልጆች፡ ተንገብገቡ፡፡ ክብሯን አትቀንሱት፡፡ ምክንያተ ድኂን ናትና ይህ ስም ይገባታል፡፡

  ReplyDelete
 5. እኔ የአለም ብርሃን እንደሆንኩ እናንተም የአለም ብርሃን ሁኑ ያለው ጌታ መድሃኒአለም ነው ።እኔን የወደደ እኔ ካደረግሁት በላይ ያደርጋልም ብሎአል።እንዳው እምዬ ማርያምን የተቃወማችሁ መስሎአችሁ የክርስቶስን ቃል አትካዱ።please take your time and read the holy bible from the beginning to the end. .Please don't repeat what Luther said. and yetesenakelebeten. for your information MK is the back bone of Ethiopian orthodox church .A lot of people miss understood before but things are changing and we know who they are and what they stand for real orthodox Christian religion unlike you Abaselam who you try to pull us to be protestant.

  ReplyDelete
 6. አቡነ ጎርጎርዮስ ‹ሥራህን ሥራ፤ አንበሳው ሲያጓራ ፍንክች አትበል፤ የሰይጣንን ውሻዎች ለመውገር አትቁም፤ ጥንቸሎቹን በማባረር ጊዜህን አታጥፋ፤ ዝም ብለህ ሥራህን ሥራ› ሲሉ የመከሩት ለዚህ ብሎግ ሳይሆን አይቀርም፡፡

  ReplyDelete
 7. Awo mk lebetekrstiyanachen yegon wogat honebatte.medahniyalem layenessa yigdelewona yihenen yeseytan mahber.dem kalteta yemayereka nahber...kesash mahber leba mahber yaferselen.teller bkerstos wengel
  yafersulen.welaite amlak betehetenawa tafersewo mahbere erkusan.bekerstos mot yedanewon alem yalemebetachen amalajenent aydenem yemil kehadi mahber
  yenesu guides meche alkali.

  ReplyDelete
 8. Thank you brothers for you guys gave (thought) us what the great difference between Lord God Jesus and his mother. when need to know who we have to believe or worship. Holy God or his mother virgin Mary. All christian believer virgin Mary chosen by Lord God to be his mother, but she is not a God. Because she was created by Holy Almighty God....

  ReplyDelete
 9. ተጻፈ …ማርያም ቤዛዊተ-ኩሉ ዓለም በሚለው ቃል ለሚሳለቁ!!!
  በፊደል….በፊደል….አንጫወት….2
  4- እስራኤል-ዘሥጋ የእኛ--እስራኤል-ዘነፍሥ የተባልነው ውሉደ-ጥምቀት ክርስቶሳውያን ሁሉ ምሳሌ መሆናቸውንም እንረዳለን፡፡ለምሳሌ፡ “…ልባቸው ለቀና ለእስራኤል እግዚአብሔር እንዴት ቸር ነው።” የሚለውን የመዝ 71 ቁ 1 ጥቅስ ለእስራኤል ብቻ የተነገረ ቃል አድርገን አንወስደውም ለሁላችንም እንጅ!!ለእስራኤላውያን የተነገረው እስራኤላውያን ላልሆኑም እንደተጠቀሰ የበለጠ ማየት የሚፈልግ፡ ሮሜ 9 ቁ 6፣12 ቁ 8፣4 ቁ 12፣ሉቃ 19 ቁ 8፣ገላ 3 ቁ 6፣6 ቁ 15፣1ኛ ቆሮ 5 ቁ 17፣ኢሳ 56 ቁ 8….ወዘተ ይመልከት፡፡ስለሆነም በብሉይ ኪዳን እስራኤላውያንን እየፀለየ፣ድንቅና ምልክት እያደረገ ያሻገራቸው ሙሴ “ቤዛ” ከተባለ በአማላጅነቷ ላመንን (ለእኛ) ከሚደረግልን ድንቅና ምልክት ተነስተን እመቤታችንን ቤዛ ብንላት ምንድነው ድንቁ እና ብርቁ??!!ዋናው ነገር እሷን ቤዛ ስንልና ጌታን ቤዛ ስንል ያለው የቃሉን አንድምታና ትርጉም መረዳት ነው፡፡ከዚህ ውጭ ቤዛ የሚለውን ቃል ይዞ በአንድ ወንዝ ለሚፈስ፣ክርስቶስን በማክበር ስም ክብረ-ቅዱሳንን ለሚያቃልል፣ዐውዳዊ ተርጉምን (context) ለመሻት ከመጣር ይልቅ ፊደል አንጠልጥሎ እመቤታችን “ቤዛ፣ፋሲካ መድኃኒት፣ወዘተ…” ተባለች እያለ ዘወትር ለሚከስ ስሑት ትውልድ ስንል መጻሕፍቶቻችንን አንበረዝም፡፡፡፡፡፡
  5- እመቤታችን በጌታ የማዳን ጉዞ ውስጥ ያልሆነችው የለም፡፡ተመልከቱ!!ሉቃ 2 ቁ 34 “…ስምዖንም ባረካቸው እናቱን ማርያምንም። እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥ በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት።” ይቺ እመቤት ከግብፅ በረሃ እስከ ቀራንዮ ከዛም እስከ እለተ ጰራቅሊጦስ በጌታ የማዳን ጉዞ ውስጥ ነበረች፡፡በነፍሷ ሰይፍ አልፏል!!ሰይፍ የምንለው መከራና ስደቷን ነው፡፡በተሸከመችው መድኅን የተነሳ የደረሰባትን!!ስለዚህ በስመ-ኀዳሪ ይፄዋዕ ማኅደር(ባደረው ያደረበት ይጠራል) ስንል ቤዛዊተ-ዓለም እንላታለን፡፡ህጹጽ ምሳሌ ከሆነ ላቅርበው!!ያሸነፈው አንድ ኃይሌ ገ/ሥላሴ ሆኖ ሳለ እሱ የተገኘባት ኢ/ያ አሸነፈች እንደሚባለው ማለት ነው፡፡በስመ ኀዳሪ…ማለት ይሄ ነው፡፡
  6- መጽሐፍቅዱስን ካነበብነው ቤዛ የሚለው ቃል ከጌታ ማዳን በተጨማሪ እንደየአገባቡ ለብዙ ትርጉም ይውላል፡፡ለማሳያ እንጥቀስ፡ (1) ሀብት ቤዛ ተብሉዋል…ምሳሌ 13 ቁ 8 “…ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።” (2) ኃጥዕም ቤዛ ይባላል…ምሳሌ 21 ቁ 18 “…ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፤ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው።” (3) ãረ ግብፅም ቤዛ ተብላለች …ኢሳ 43 ቁ 3 “…እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።” (4) የቦታ ካሳም ቤዛ ይባላል…ዘሌዋ 25 ቁ 24 “…በርስታችሁም ምድር ሁሉ መቤዠትን ለምድሪቱ አድርጉ። ወንድምህም ቢደኸይ ከርስቱም ቢሸጥ፥ ለእርሱ የቀረበ ዘመዱ መጥቶ ወንድሙ የሸጠውን ይቤዠዋል።” (5) የኃጢኣት ማስተስረያ ቤዛ ይባል ነበር “…ዘፀ 30 ቁ 12…አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር ተቀብለህ፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ መቅሰፍት እንዳይሆንባቸው፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ።” ብዙ መጥቀስ ይቻላል፡፡ዋናው ነገር ቤዛ ለሚለው ቃል ተቆርቋሪ መስሎ ከማደንቆር ቃሉን እንደአግባቡ መረዳት ይገባል ለማለት ነው፡፡ በፊደል…በፊደል አንጫወት!!!
  7- ስደመድም፡ (ሀ)እውን ይህ ስያሜ ለማርያም ይስማማታል ወይ?---አዎ እንደአገባቡ ከተጠቀምነው ቃሉ ለእመቤታችን ይገባል፤ቃሉን አማላጅ ለሚለው ቃል ተለዋጭ በማድረግ ብቻ ማለትም ከጌታ ልዩ የሆነ የማዳን ስራ ጋር ሳንቀላቅል እስከተጠቀምንበት ድረስ ቃሉ ይስማማታል፤ (ለ) ማርያም ለዓለሙ ሁሉ ቤዛ የሆነችው መቼ ነው?---እመቤታችን የዓለም ቤዛ የሆነችው ማማለድን በደም ዋጅቶ አንዴ በቀራንዮ ከተፈጸመ የማዳን ስራ በመለየት በእሷ አማላጅነት፣በልጇ አዳኝነት ካመንበት ቀን ጀምሮ ነው፤ (ሐ) በምንስ ጉዳይ ነው?---የክርስቶስን አዳኝነትና ቸርነት አምነን በጠየቅናት በማንኛውም ጉዳይ እሷ ቤዛ ናት-ዋስ-ጠበቃ፤(መ) ለማርያም የክርስቶስን ስፍራ ካልሰጠን በቀር ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ይቻላል ወይ?---ቃሉ ለእነሙሴ፣ለእነ ግብጽ ሲውል እነሱ በክርስቶስ ቦታ መቀመጥ እንዳላስፈለጋቸው ሁሉ እመቤታችንም ቤዛ-ዋስ-ጠበቃ ለመባል በጌታ መንበር መቀመጥ አያስፈልጋትም፣አማላጂቱ በፈራጁ ቦታ አትቀመጥም እንዲሁም ፈራጁ በአማላጂቱ ቦታ አይቀመጥም፡፡፡፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Dear selama why omitting this??
   በፊደል….በፊደል….አንጫወት….1
   1-መጀመሪያ ቤዛዊተ-ዓለም የሚለውን ቃል ነጥለን ትርጉሙን እንይ!! “ቤዛ” እና “ዓለም”!!ቤዛ የሚለው ቃል በመዝገበ-ቃላት ትርጉሙ ቤዘወ-ተቤዠ ከሚል የግእዝ ቃል እንደሚመዘዝና ግሳዊ ትርጉሙም፡መቤዠት፣ማዳን፣መታደግ፣ማስጣል፣ከጭንቅ ከባርነት ነጻ ማውጣት፣ከባለዕዳ እጅ መግዛት፣መዋጀት፣ ለውጥ መስጠት…ተብሎ በአለቃ ኪዳነወልድ ክፍሌ መዝገበቃላት ገጽ-265 ተተርጉሟል፡፡ቤዛ የሚለው ስያሜም፡ የተያዘን ወይም የተወሰደን ነገር ለማስመለስ የሚከፈል ዋጋ፣ካሳ፣ለውጥ፣ምትክ፣ዐላፊ፣ዋስ፣መድን፣ተያዥ፣…እያለ ይሄው መዝገበቃላት ያፍታታዋል፡፡ዓለም ስንልም የግድ መላውን ዓለም ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ዓለመ-መላእክት፣ዓለመ (ብሔረ) ብፁዐን እንዲሉ አባቶች፤ዓለም የሚለው ቃል የተለየ መኖሪያን ወይም ቡድንን ሊወክል ይችላል፡፡የዳኑት ያመኑትና የተጠመቁት ብቻ ሆነው ሳለ ያልተጠመቁትን ቀላቅለን በክርስቶስ ደም ዓለም ዳነ እንደምንለው፣ክርስቶስን ያልተቀበሉት እስራኤላውያን ብቻ ሆነው ሳለ እስራኤልን እንደ ዓለም ቆጥረን ጌታን ዓለም አልተቀበለውም እንደምንለው፣ወዘተ….
   2- ወደ ጉዳያችን እንምጣ፡፡እመቤታችንን ቤዛዊተ-ዓለም ስንል ቤዛነቷ እንደጌታ ደም አፍስሶ፣በቀራንዮ ተሰቅሎ፣በአዳም ምክንያት የመጣብንን መርገመ-ነፍስ የጥል ግድግዳ ማፍረስ ማለት አይደለም፡፡እሱማ በጌታ ደም ብቻ መሆኑን በትምሕርተ ኅቡአትም…እሙታን ተንሲኦ ሲኦለ ከይዶ በሞቱ ለሞት ደምሰሶ…ከሙታን ተነስቶ፣ሲኦልን ረምርሞ፣በሞቱ ሞትን ደመሰሰው…እያልን ነው ያደግነው፡፡ እመቤታችንን ቤዛ ስንልም እንደ ክርስቶስ የምትዋጅ ማለታችን ሳይሆን ቤዛ ከሚለው ቃል ውስጥ በክርስቶስ አዳኝነት እና በእሷ አማላጅነት ካመንን በኋላ ለሚደርስብን የኃጢአት (ው)ድቀት በአማላጅነቷ “እንድታስጥለን፣ዋስ፣መድን፣ተያዥ” እንድትሆነን ማለታችን ነው፡፡ “ዓለም” የተባለውም በልጇ አዳኝነትና በእሷ አማላጅነት ያመነው ክርስቱን (ክርስቶሳዊ) ማኅበረሰብ እንጅ በልጇ አዳኝነትና የባሕርይ አምላክነት ያላመነ፣የእሷን አማላጅነትና ወለዲተአምላክነት ያልተቀበለ ሁሉ አይደለም፡፡ስለዚህ እመቤታችን ቤዛዊተ-ዓለም ስንል በአማላጅነቷ ላመኑ ክርስቶሳውያን የዓለም ሕዝቦች ዋስ-ጠበቃ ማለታችን እንጅ እንደ ክርስቶስ ተሰቅላ የምትቤዠን ማለታችን አይደለም፡፡እሱን የሚሉት ከእኛ ለእኛ ሳይሆኑ ስለእኛ መናገር የሚፈልጉ ወገኖች ናቸው፡፡ዐይነ-ልቡናቸውን ያብራላቸው--እምነት ቢለየንም ሰብአዊነትና ዜግነት ያገናኘናልና ስለ እነሱም እንጸልያለን፡፡
   3- በፀሐፊው እንዳይሆን ሆኖ የተተረጎመውን የሐዋ ስራ 7 ቁ 35 በፊቱና በኋላው ያሉትን ኃይለቃሎች ጨምረን እንየው፡፡እንዲህ ይላል “…በግብፅ ያሉትን የሕዝቤን መከራ ፈጽሜ አይቼ መቃተታቸውንም ሰምቼ ላድናቸው ወረድሁ፤ አሁንም ና፥ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ አለው። ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ብለው የካዱትን፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው። ይህ ሰው በግብፅ ምድርና በኤርትራ ባሕር በምድረ በዳም አርባ ዓመት ድንቅና ምልክት እያደረገ አወጣቸው።” ይህ ኃይለ-ቃል የሚያሳየው ሙሴ እስራኤልን ለማዳን ሹምና ቤዛ ተደርጎ በመልአኩ እጅ መላኩንና ድንቅ ምልክት ማድረጉን ነው፡፡አስተውል!! “...አርባ አመት ድንቅና ምልክት እያደረገ አወጣቸው…” የተባለው “ቤዛ” ተብሎ የተሾመው ሙሴ ነው፡፡እልኸኛው ፀሐፊ ጥቅሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተገኘ ሆኖበት እንጅ ከሌሎች የቤ/ክ አዋልድ መጻሕፍት ቢሆን ኖሮ “ቤዛ” የሚለውን ለሙሴ ከጌታ የተሰጠ ስያሜ ነቅሶ እንደሚያብጠለጥለው እናውቃለን፡፡እኛ ግን ሙሴ ቤዛ ቢባል አንድም ቅድስናው በአምላኩ ታውቆለት መሆኑን በማሰብና የእሱ ቤዛነት ለእስራኤል ዘሥጋ መሆኑን ስለምናውቅ፣አንድም ምንም እንኳ ሙሴ ድንቅና ምልክት አደረገ ቢባል ዋናው የድርጊቱ ባለቤት እሱ ባለቤቱ እግዚአብሄር መሆኑን ስለምንረዳ በፊደላዊነት አንርድም፡፡በፊደል…በፊደል አንጫወትም---በትርጉም…እና…በአበው ትርጓሜ እንጅ!!

   Delete
 10. mk degmo beyetgnaw akmu new yemihonew? Ye ahyasibsb

  ReplyDelete
 11. be blessed aba selamawoch...letekawamiwoch bota atisitu....ewunet yeminager tekawamiw bizu new...bertu abaselamawoch.wagachihun kegeta enji kesew atitebiku.yemitiserut endichebechebilachihu balemehonu metamenachihun gifubet!!!

  ReplyDelete
 12. GREAT CLARIFICATION BETWEEN GOD AND HIS MOTHER, WONDERFUL UNDERSTANDING REGARDING OUR WORSHIP. THANK BROTHER................

  ReplyDelete
 13. Mk betebetu. Woyane Wogaw dirtu

  ReplyDelete
 14. የእርሷን ሥጋ የለበሰው መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ እኮ ነው ቤዛ ኩሉ ዓለም የተባለው… አረ ቅናታችሁ ልክ ይኑረው….

  ReplyDelete
 15. Nisgid Le Meskel We Le Mariyam Dingil lay bitisifubbet tsifachihu kehone alanebebkum mallet new

  ReplyDelete
 16. why do you confuse others purposely? bible is not compared with other 'awaled metsahifts' . awalds are born from bible, they can not conflict with the bible as you think. however, in orthodox church, the bibile is the most respected and above all awalds. it is not equal with others. in earthly state administrations, policies and guidelines are born from state constitutions with out conflicting with the latter or to support the latter. awald metsahfits is like that. they are facts which describe seemingly vague truths from the bible or they are facts which are not obtained in the bible. accordingly protestants, there is no truth unless recorded in the bibile. this is poor thinking, but what is laughable is they believe what the pastors dictate which is not related with facts.

  ReplyDelete
 17. Erasu yefeterewon siga new melso yelebesewo .sewoch enastewol.

  ReplyDelete
 18. will come back hiruy

  ReplyDelete
 19. Hiruy I always show up to read your comments... Kale hiywot yasemalign..

  ReplyDelete
 20. Marriyamin merto lemn tewoledebat? Yihn tiyake melis. neger gin lememeles libhin aswosdehewal! Minalbat yemimeles kehon, kidist dingil marriam nitsihit,rihirit,bezawit,& kidist Nat!!! Ersu yekedesewn be manim fukera&jinjena ayilewotim! Erasachihun ewoku egizabeher and new ayilewotim

  ReplyDelete
 21. Kidist Dingil Marriam :nitsihit, rihirit,woladite amlak, bezawite kulu nat! kinat keseyitan new, atikinu! begonet ye egzeabher new, bego hunu! mahbere kidusan betekirstianin atibetibitu. sewn wodechelema atisdedu, wode birhan new enj yalu lela minalu kifu tiwlid ye egzeabherin neger yikawomal yitelal!

  ReplyDelete
 22. Ye dingilin Bezanet lemeredat be Geta Ende hawariyat temerto Orthodox mehon yasfeligal Menafikan ena Tehadisowoch yetunim yahil bitelefelfu ena bitedekimu ye Dingil mariam Bezayte kulu Alem kibir yisefal Mahibre Kidusan yisfafal enante gin ende Ariwos titefalachu

  ReplyDelete
 23. Aba Selama ye seytan dekemezmur yetehadiso group no one hear u

  ReplyDelete