Saturday, September 6, 2014

"በክርስቶስ መከራ በምትካፈሉበት ልክ ደስ ይበላችሁ” 1ጴጥ 4፥13

Read in PDF

ይድረስ በናይጀሪያ፣ በቻይና፣ በኢራቅ፣ በሶሪያ፣ በግብጽ፣ በፓኪስታን፣ በሳውዲ አረቢያና በሶማሊያ ለምትገኙ ክርስቲያኖች።
እኛ በኢትዮጵያ የምንገኝ ክርስቲያን ወንድሞቻችሁ ነን። ሁላችን የአንድ አባት ልጆች ነን፣ በተለያየ አመለካከት ስሕተትም ይሁን ትክክል ይሁን እንለያይ እንጂ ሁላችንም በሚመጣው የክርስቶስ መንግሥት እንገናኛለን "በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና” ተብሎ እንደተጻፈ የክርስቶስ የመስቀሉ ሥራ ሁላችንንም ከነድክመታችን በአብ ዘንድ ያገናኛናል። መከራ የሚያሳዩአችሁም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ይቀርባሉ። እናንተ የክርስቶስ አካል ናችሁ እኛም የክርስቶስ አካል ነን። ስለዚህ የናንተ መከራ እኛንም ይሰማናል። የአካላችን አንዱ ክፍል ናችሁና ሕመሙ የጋራችን ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሕመሙ ይሰማዋል እስጢፋኖስ መከራ ሲቀበል ከዙፋኑ ብድግ ብሎ ቆሞ እንደታየ ዛሬም በእናንተ መከራ ጊዜ ዝም ብሎ የተቀመጠ እንዳይመሳላችሁ። ስለስሙ ያቀራባችሁትን የተወደደ መስዋእታችሁን ለመቀበል ቆሞላችኋል።




 አይዟችሁ በርቱ የተስፋችን ፍጻሜ እየቀረበ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ሊመጣ ዓለም የማያውቀው የልጅነት ክብራችን ሊገለጥ እየተቃረበ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ "ለእኛም ይገለጥ ዘንድ ካለው ክብር ጋር ቢመዛዘን የአሁኑ ዘመን ስቃይ ምንም እንዳይደለ አስባለሁ። የፍጥረት ናፍቆት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ ይጥባበቃልና።” ብሎ እንዳስተማረን እግዚአብሔር ስለ ስሙ የተቀበላችሁትን መከራ ዘለዓለማዊ ደስታ አድርጎ ይለውጥላችኋል። 

 እኛ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ብዙ የመከራ ዘመን አሳልፈናልና የናንተ መከራ እጅግ ይሰማናል። ከዮዲት ጉዲት ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬም ድረስ ሰይፍ ካንገታችን ተለይቶን አያውቅም። አንዳድ ጊዜ እርስበርሳችን ካቶሊክና ኦርቶዶክስ በሚል የቤተ ሰብእ ግጭት ውስጥ ገብተን ሰይፍ ተማዘናል። ያንን ግን ጌታ እንደ ሰማእትነት አልቆጠረልንም ምክንያቱም እነርሱ ከኛ ገደሉ እኛም ከነርሱ ገደልን። ወንድም ወንድሙን ገድሎ ጀግና እንደማይባል ሁሉ ክርስቲያን ክርስቲያንን ገድሎ የሚያተርፈው አንዳች ክብር የለም። አብዛኛውን መከራ የተቀበልነው ግን ቁራንን በሚያነቡ ሰዎች ነው። በ1997 ዓ.ም በጅማ ክፍለ ሀገር የሆነብንን ሳትሰሙ አትቀሩም፣ በመሕረቱ ባለጠጋ የሆነው አምላካችን ያዘልን እንጂ በጣም ተጨንቀን ነበር። አሁንም ቁራንን የሚያነቡ ሰዎችን እጅግ በጣም እንፈራለን። ነገር ግን ይህ ስለክርስቶስ ተሰጥቶናልና እግዚአብሔር በወሰነልን መንገድ ማለፋችን የማይቀር ነገር ነው። "በአንድም ነገር በተቃዋሚዎች አትደንግጡ ይህም ለእነርሱ የጥፋት ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው ይህም ከእግዚአብሔር ነው ይህ ስለ ክርስቶስ ተሰጥቷችኋልና ስለ እርሱ መከራ ደግሞ ልትቀበሉ እንጂ በእርሱ ልታምኑ ብቻ አይደለም ” ተብሎ ስለተጻፈለን መከራ የምንቀበልበትን ምክንያት ጠንቅቀን አውቀናል ብቻ እግዚአብሔር ያስችለን!
 እባካችሁ አስተምሩን! እናንተ ለእግዚአብሔር ክብር በክርስቶስ ስም ምስክርነታችሁን በደም እያጸናችሁ ወደማያልፈው ዓለም ስትሄዱ፣ እኛ ግን በዚህ በሚያልፈው ዓለም ማህበረ ቅዱሳንና ተሐድሶ በሚል ተከፋፍለን ልናጨረስ ነው። እነርሱ ተሐድሶ ናችሁ እያሉ እኛን ወንድሞቻቸውን ያሳድዱናል። እኛም የስሕተት አስተማሪዎች ናችሁ እያልን የራሳችንን ወንድሞች እናሳድዳለን። ወንድም በወንድሙ ላይ ይነሳል ማለት ይህም አይደለምን? አባቶቻችን ጳጳሳትም እንኳን ሊያስታርቁን የበለጠ እያለያዩን ነው። እኛም በገንዛ ወንድሞቻችን ተሰደን ነው የምንኖረው። ይህ በእንዲህ እንዳለ እኛ እርስ በእርስ ስንካሰስ የቁራን አንባቢዎች ሰይፋቸውን አንገታችን ሥር አስቀምጠው ጊዜ እየጠበቁ ነው።
ያም ሆነ ይህ ክርስቶስ  የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የምናምን ሁሉ በበጉ እራት ጊዜ አብረን እንደምነበላ እናምናለን። በዚያ እራት የተጋበዝን ሁሉ ዛሬ አብረን መከራውን እየተቀበልን የእምነታችንን እራስና ፍጻሜ የሆነውን ክርስቶስን ተመልከተን አብረን እንሩጥ። ወንጌልን እንስበክ እግዚአብሔር ከፈተናው ጋር መውጫውን ይስጣችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው እምነት ያበርታችሁ። ሩጫችሁን ጨረሳችሁ አእላፍ ወደተሰበሰቡበት ወደ ጽዮን ተራራ የደረሳችሁ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ!
                              ከኢትዮጵያ ክርስቲያን ወንድሞቻችሁ!    

8 comments:

 1. amen amen..geta befikir yikebelachihual..lebetesebochachewum tsinatun yistiln..!!

  ReplyDelete
 2. እናት ገድለህ ወደ ልጅ የምትሸሽ ከሃዲ።

  ReplyDelete
 3. Lets the almighty give strength and unity to all human kind. Few fundamental extremists are now terrorizing our glob, civilization and human being. Actually our glob experienced such evil acts several times in history. From Christianity point of view a human being is not an enemy to another human being. As a Christian we should strongly pray and dismantle devils plan. No Christian is an enemy to Muslim because of the holly Bible and no Muslim is an enemy to Christian because of the holly Quran. Let us focus on our sole enemy--- devile

  ReplyDelete
 4. ግፉዐን ወንድሞቻችን….
  -ውሎ አድሮ እንዲህ አይነት ተጋድሎዎችን “ተረት-ተረት” እያለ ታሪክ ከሚያጠለሽ ፕሮቴስታንት ይሰውራችሁ፡፡
  -የነጆርጅ ቡሽ “አክራሪ ፕሮቴስታንቲዝም” በወለደው ዐለማዊነት እየናወዘች ሙስሊሙን ዓለም አክራሪነት አዘቅት ውስጥ በመክተት ላይ ላለችው ባቢሎኗ አሜሪካ ልቡና ይስጥልን፡፡
  -ዘወተር መልኩን ከዓለማዊነት ጋር እየለዋወጠ ዓለምን ርህራሄና ሞራል-አልባ እያደረጋት ከሚገኘው ሥርዓት አርካሹ መረን ፕሮቴስታንቲዝም ይሰውራችሁ፡፡
  -ፕሮቴስታንት ወለዱ የምዕራባውያን እኩይ ፖለቲካና ድንቁርና የተጫነው የዐረብ ዕቡይነት ፍጥጫ ባመጣው ጣጣ የተጫነባችሁ የመከራ ቀንበር ተነስቶ አብረን “ንሴብሖ” እንድንል እንጸልያለን፡፡

  ReplyDelete
 5. Mk did similar to this in EOTC church father's please post it.

  ReplyDelete
 6. Would you please remove the kids picture from the post? the message is clear and informative with out the kid's picture. furthermore no need to be inhumane to show the inhumane nature of the the day. May God bless you

  ReplyDelete
 7. To accept the unity & diversity in the world, it is best to immitate the unity & diversity in Trinity

  ReplyDelete
 8. አባ ሰላማዎች ስለ አነሳችሁት ድረ ገጾ ተባረኩ

  ReplyDelete