Wednesday, September 3, 2014

ይድረስ ለዘማሪ ታዴዎስ ግርማ።እግዚአብሔር ታላቅ ነው ነገር ግን ማንንም አይንቅም መዝ 51፥17፤
ኃያል ነው ግን በጣም ታጋሽ ነው ኢዮ 36፥5።
ስሜን በከንቱ አትጥራ በማለት ክብሩን የተናገረው አምላካችን ዘፍ 20፥4 እንዲህ በድፍረት የምንዘባበትበት አይደለም። ለመዘመር ያነሣሣን ምንድር ነው? እግዚብሔርን ስላወቅነው? ወይስ በሌላ ስሜት? መዝሙር አምልኮ ነው እግዚአብሔር ስላደረገልን የምንሰጠው የደስታ ምላሽ ነው። ማርያም እሕተ ሙሴ ለእግዚአብሔር እንጂ ለሙሴ አልዘመረችም ዘጸ 15፥1። እመ ሳሙኤል ሃና ለእግዚአብሔር ዘመረች 1ሳሙ 2፥1። ቅዱስ ዳዊት ለእግዚአብሔር ዘመረ። ድንግል ማርያም ለእግዚአብሔር ዘመረች ሉቃ 1፥47። በመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኛቸው ቅዱሳን ሁሉ ለእግዚአብሔር ብቻ እንቺ አንዱ ለሌላው ሲዘምር አናይም። እኔ እንደተማርኩት ቅዱስ ያሬድም ለእግዚአብሔር ብቻ ነው የዘመረው። የኋላ ሰዎች አዋልድ በሚል ጨመሩበት እንጂ። ቅዱሳንንም ሲያነሳ ተጋድሏቸውንና እሩጫቸውን መጨረሳቸውን በማድነቅ የእግዚአብሔር ክንድ እንዴት እንዳገዛቸው ይናገራል እንጂ እነርሱን ከጌታ በላይ አስቀምጦ የእርሱን ሥራ ለነርሱ አይሰጥም። መጽሐፍም "ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ ለንጉሣችን ዘምሩ እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና በማስተዋል ዘምሩ‚ በማለት ለማን መዘመር እንዳለብን ይነግረናል። መዝ 46፥6-7።


ይህን ማስታወሻ የጻፍኩልህ አንደኛ ዝማሬ ለጌታ መሆኑን ልነግርህ ሲሆን! በተጨማሪም አንተን ተከትሎ የተሳሳተውን ሕዝብ ወደ ትክክለኛው አምልኮ ለመመለስና አንተም ንስሐ እንድትገባ ለመምከር ነው። በዚህ ሃያ ዓመት ውስጥ የኢትዮጵያን ሕዝብና ቤተ ክርስቲያንን ከበደሉና ይቅርታ መጠየቅ ከሚገባቸው ሰዎች መካከል አንዱ አንተ መሆንህን ልነግርህ እወዳለሁ።

አንተ በመዝሙርህ ያሰራጨሃቸውን የስሕተት ትምህርቶች እስከዛሬም የቤተ ክርስቲያን መድረኮችን ተቆጣጥረው የሚገኙትን በእግዚአብሔር ቃል ቅኝት ላሳይህና እራስህን እንደገና እይ።

አድኚኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና፣
ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አልራቀምና፣
ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ፣
አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ።


   ያአማኑኤል እናት የተዋሕዶ አክሊል፣
   አትጥፊ ከመሐል እንድትሆኚን ኃይል፣
   ምንም ቢበዛብሽ የእኛ ጉስቁልና፣
   ከእኛ ጋራ ከሆንሽ አለን ቅድስና።

ተስፋዬ ነሽና እመካብሻለሁ፣
ግራ ቀኝም አልል ምርኮኛሽ ሆኛለሁ፣
ስቅበዘበዝ አይቶ ተስፋ የሰጠኝ፣
እግዚአብሔር ይመስገን ካንቺ ያስጠጋኝ።

   በስጋ ደክሜ በነፍሴ እንዳልጠፋ፣
   እማጸንሻለሁ ድንግል የኔ ተስፋ፣
   የመንግሥቱ ወራሽ እንድሆን አድርጊኝ፣
   መልካም ሥራ መሥራት እኔን አስተምሪኝ።

አንቺ የሌለሽበት ጉባኤው ባዶ ነው፣
በቁም የደረቀ ሕይወት የተለየው፣
ከመካከል ገብተሽ ሙይ የጎደለውን፣
ሰርጉ ተደግሷል ጎብኝልን ጓዳውን።

ያሬድ አደመ ካሳተመው የመዝሙር መጽሐፍ ቁጥር 1 ገጽ 117 ላይ የተወሰደ፤

መዝሙሩ በእግዚአብሔር ቃል ሲመረመር ሌሎችን አማልክት ከሚያመልኩ ሰዎች የተረጨ መንፈስ መሆኑን ያረጋግጣል።


አድኚኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና፣
ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አልራቀምና፣

ማርያምን አማልጅን ጸልይልን እንላታለን እንጂ አድኚን አንልም የሚለው ማምለጫ የሚመስል ገደል እዚህ ላይ ተጋልጧል። የሥጋ ፈተና በመሥቀሉ ኃይል የሚሸነፍ ነው። "የክርስቶስ የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ምኞቱ ጋር ሰቀሉ‚ ይላል። በክርስቶስ ሞት አምነን በጥምቀት በሞቱ የተባበርን ሁሉ ሥጋ ከክፉ መሻቱ ጋር በእግዚአብሔር መንፈሳዊ አሰራር እንደሚሰቀልና አዲስ ሕይወት አግኝተን እንደምንመላለስ የጌታ ቃል ይናገራል። ገላ 5፥25። ጳውሎስ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ ያለው ለዚህ ነው። ገላ 2፥21። በክርስቶስ ሞት ስናምን ሥጋዊነታችንም ይሞታል። ከዚያም ኃይል በሚሰጠን በክርስቶስ ሁሉን እንችላለን እንደተባለ በመስቀሉ ኃይል ድል እየነሳን እንጓዘለን። ስለዚህ ከሥጋ ፈተና የምንድነው ኃይልን በሚሰጠን በክርስቶስ ነው። ማዳን የእርሱ ነውና። አንተ ግን ማርያምን ከስጋ ፈተና አድኚኝ ስትል የለመንኸው ማርያም አዳኝ ናት ወይ? አዳኝ ማን ነው? የእግዚአብሔር ቃል ማርያም የአዳኛችን እናት እና የተከበረች ቅድስት መሆኗን ይናገራል እንጂ አዳኛችን ናት አይልም።

"ሥጋየ ከኃጢአት ከቶ አልራቀምና‚ ይህን ትክክል ብለሃል። ግን እኮ ሥጋህ ከኃጢአት ያልራቀው አዳኝህ ማን እንደሆነ ባለማወቅህ ነው። "ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ‚ 1ጢሞ 1፥15። እያለ ቃሉ አንተ ግን ማርያምን አድኚኝ እያልክ ትጮካለህ እንዴት ሆኖ ሥጋህ ከኃጢአት ሊርቅ ይችላል? ብቸኛው የኃጢአት መድኃኒት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በእርሱ ብታምን ትድናለህ። አድነኝ ብለህ አስተካክል።


ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ፣
አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ።

"እናንተ ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ እኔ አሳርፋችኋለሁ‚ ማቴ 11፥28። ይላል ጌታ ለምን ወደ ክርስቶስ አትመጣም? እርሱ ወደ እኔ ኑ ላሳርፋችሁ እያለ አንተ ግን ወደ ማርያም ትሮጣለህ። ድንግል ማርያም የሚላችሁን አድርጉ ብላለች ዛሬም ቢሆን የሚልህን አድርግ ነው የምትልህ። እርሱ አትምጣብኝ ቢልህ፤ እሺ ወደ እርሷ ሄደህ ትለምን ነበር ግን መቼ አትመጣብኝ አለህ? ና! እያለህ ነውኮ! ድንግል ማርያም ልጄ አትምጣ ያለህ ይመስል ለምን ወደ እኔ ትመጣለህ? ትልሃለች።   አትጥፊ ከመሐል እንድትሆኚን ኃይል፣

እንዲች ናት ባዕድ አምልኮ! ማርያምን እናከብራታለን እንጂ አናመልካትም የሚለው ፕሮፓጋንዳ እዚህ ላይ ተጋልጧል። ኃይል የእግዚአብሔር ነው ኃይል መጠጊያ ጉልበት የሚሆነን ጌታ ነው ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ አለ "በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ጽድቅና ኃይል አለ ወደ እርሱም ሰዎች ይመጣሉ‚ ኢሳ 45፥24። ኃይል የእግዚአብሔር ብቻ ነው። ማርያምን ኃይል ሁኚን በማለት መዘመር ሌላ ሁለተኛ አምላክ መፍጠር ስለሆነ መታረም አለብህ።


ምንም ቢበዛብሽ የእኛ ጉስቁልና፣
   ከእኛ ጋራ ከሆንሽ አለን ቅድስና።

ቅድስና በክርስቶስ ደም ስንነጻ የምናገኘው የጌታ በረከት ነው። "የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል‚ ዮሐ 1፥7 እንዲሁም በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሚሰጠን መንፈስ ቅዱስ ቅድስናን እናገኛለን

"ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፣ ተቀድሳችኋል፣ ጸድቃችኋል‚ ተብሎ ተጽፏል 1ኛ ቆሮ 6፥11። ስለዚህ የቅድስናችን ምክንያት መንፈስ ቅዱስ በኛ ሲያድር የሚመጣ እንጂ ማርያም በመካከላችን ስትሆን አይደለም። ማርያም መንፈስ አይደለችም እንደኛ ፍጡር ስለሆነች በመካከላችን አትገኝም። እርሷ በጌታ ክብር በሰማይ አለች። እንደ መንፈስ ቅዱስ በሁሉ ሥፍራ ግን አትገኝም። ስለዚህ የጉስቁልና መፍትሔው ንስሐ መግባት ብቻ ነው።

ተስፋዬ ነሽና እመካብሻለሁ፣
ግራ ቀኝም አልል ምርኮኛሽ ሆኛለሁ፣
ስቅበዘበዝ አይቶ ተስፋ የሰጠኝ፣
እግዚአብሔር ይመስገን ካንቺ ያስጠጋኝ።
በስጋ ደክሜ በነፍሴ እንዳልጠፋ፣
   እማጸንሻለሁ ድንግል የኔ ተስፋ፣


በምን መልኩ ነው ማርያምን ተስፋ ያደረግኸው? በመዳን ከሆነ መዳን በክርስቶስ ነው። እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ "በልጁ የሚያምን ይድናል በልጁ የማያምን ግን ይፈረድበታል የሚል ነው‚ ከዚህ ውጭ ማርያምን ተስፋ አድርጎ መስጠቱን የሚናገር መጽሐፍ የለም። ወይስ ላንተ የተለየ ተስፋ ሰጥቶህ ይሆን? ኤፌ 4፥3 ባአንድ ተስፋ ተጠርታችኋል ይላል እርሱም ክርስቶስ ነው። አንተ ሁለተኛውን ተስፋ ከሄት አመጣከው?

አንቺ የሌለሽበት ጉባኤው ባዶ ነው፣
በቁም የደረቀ ሕይወት የተለየው፣
ከመካከል ገብተሽ ሙይ የጎደለውን፣
ሰርጉ ተደግሷል ጎብኝልን ጓዳውን።

አቤት ክህደት! የትኛው ጉባኤ? ሁለት ወይም ሦስት ሆናችሁ በስሜ በምትሰበሰቡበት በዚያ በመካከላችሁ እገኛለሁ ማቴ 18፥20። በስሜ የሚለውን ቃል አትርሳው። ስሜ ያለው ኢየሱስ የሚለውን ዋና መጠሪያ ስሙን ነው። በጌታ በኢየሱስ ስም ተሰብስበን እርሱ በመካከላችን እንደሚገኝ ቃል ኪዳን አለን። ይኸውም በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው። እንግዲህ ጌታ በቃሉ መሠረት በመካከላችን ከተገኘ እንዴት ጉባኤው ሕይወት የሌለው ይሆናል? እርሱ እውነት መንገድና ሕይወት አይደለምን? በእርግጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከኔ ጋር የማያከማች ይበትናል እንዳለው በአርሴማ በተክልዬ በገብርዬ የሚሰበሰብ ጉባኤ ደረቅና ሕይወት አልባ መሆኑን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የበቀለውን አመጸኛ እና እምነት የጎደለው ትውልድ በማየት ማረጋገጥ ይቻላል። ለዚህም አንተና እንግዳ ወርቅ፣ ፋንቱ ወልዴ፣ ጸዳለ ጎበዜ፣ ቸርነት ሰናይ፣ መኩሪያ ጉግሳ፣(ገጣሚ) ልዑል ሰገድ፣ ዋና ዋና ተጠያቂዎች ናችሁ። ንስሐ ካልገባችሁ የመዝሙራችሁን ይዘትና አንዳንድ ታሪካችሁን ለማስተዋስ መገደዳችን አይቀርም።

ታዴዎስ አንተ በጣም የምትገርም ዓይነት ዘማሪ ነህ። ስለ ላሊበላ በዘመርኸው መዝሙርህ ላይ እንደሚከተለው ብለሃል

 "ቅዱስ ላሊበላ ጻድቁ መነኩሴ፤
 አደራ ጠብቀኝ በሥጋ በነፍሴ‚ አቤት! አቤት! የመዝሙር መጽሐፍ ቁ 1 ገጽ 119

ማርያምን አደራ ጠብቂኝ ስትል እንደነበር ካላይ ባየነው ግጥም አስተውለናል። አሁን ደግሞ ላሊበላን በምድር በሥጋህ፤ በሰማይ በነፍስህ፤ አደራ ጠብቂኝ ብለሃል። ነፍስህ ነገር እንዴት ነው? በሰማይም ጠባቂዋ ላሊበላ ሆነ እንዴ?። ዳዊት ግን የነፍሴ ጠባቂዋ እግዚአብሔር ነው ይላል ። ቆይ! ቅይ! ምን ነው ማርያምን ተጠራጠርሃት? ማርያም ከጠበቀችህ አይበቃህም? ወይስ ለሁለት ካልጠበቁህ ሰላም አይሰማህም?

ነገሩ የገንዘብ ጉዳይ ነው። መስከረም 21 ሲደርስ ያን አድካሚ ተራራ "ግሸን ማርያም ሲሄዱ፤ አልጋ ባልጋ ነው መንገዱ‚ እያላችሁ ሕዝብን ትበዘብዛላችሁ። ለነገሩ ይህን መዝሙራችሁን የተረጎመ አስተዋይ "አልጋ ባልጋ ነው መንገዱ‚ የሚሉት ግሸን ሄድን ብለው ከወጡ በኋላ ደብረ ብርሃን፣ ኮንቦልቻ፣ ደሴ፣ እዚያው ግሸንም አልጋ ይዘው የሚሰነብቱ ስለሆነ ነው ብለዋል። ለዚህ አባባሉ በየመንገዱ ወድቆ የምናየው ኮንዶም ምሥክር ነው። የላሊበላ በዓል ሲደርስ ስለላሊበላ ትዘምራላችሁ፣ ስለ ጻድቃኔ ስለ ሸንኮራም ዘምራችኋል። ታዴ! አንተ ደግሞ በማህሌት ይዘላል ለተባለው ለመርቆርዮስ ፈረስ ስእል ዘምረሃል። ምን አለበት ለጥቅም ብለህ እግዚአብሔርን ከምትሳደብ ሰርተህ ብትበላ!!!!

አሁንም አልረፈደም ንስሐ ግባ፣ አለባለዚያ ከተጠያቂነት አትድንም፣ መታሰቢያህም ከባዕድ አምላኪዎች ጋር ይሆናል።

                              ተስፋ ነኝ    

27 comments:

 1. አንቺ የሌለሽበት ጉባኤው ባዶ ነው፣
  በቁም የደረቀ ሕይወት የተለየው፣
  ከመካከል ገብተሽ ሙይ የጎደለውን፣
  ሰርጉ ተደግሷል ጎብኝልን ጓዳውን። this is a fact for protestant menafkan organization. the conference of menafkan is void without her involvement

  ReplyDelete
 2. ወዳጀ ተስፍ ምነው አለማየሁ የተባለውን እረሳህው በክፋ መንፈስ ተይዞ የሚዘምረውን ተስፋ እግዚአብሔር የአገልግሎትህን ዘመን ይባርክ

  ReplyDelete
 3. ቁጣየን ላስቀድም!!
  ወንድም ተስፋ መገረብ አመጣህሳ…አንዱን ሀሳብ ደጋገምከው!!ለነገሩ የሰላማ ማጠንጠኛ አንድ ነው--እግዚአብሄርን ለማወደስ እሱ ያከበራቸውን ቅዱሳንን ለማንኳሰስ መፋጨር(ሊቁ መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ‘ማፋቸል’ ይሉታል)!! እዚህ ጽሁፍ ላይ ያሬድን በእማኝነት ለመጥቀስ ተሞክሯል--ገና ሲጀምር …ብፁዕ አንተ ዮሐንስ…ብሎ የቅ/ዮሐንስን ስም የሚጠራውና ከገጹ ጅማሬ እስከ ፍጻሜው ሰአሊ ለነ/ሰአል ለነ/ሰአሉ ለነ በሚሉ የአማልጅነት ተማጽኖዎች የተሞላው መዝገብ ድጓ!!ይሄን ስናይ…ስሜ አይጠሬ ላመሉ መጽሐፍቅዱስ ይጠቅሳል…እንተርታለን፡፡እንጨምራለን…በአይቴ ሀሊፈኪ ድጓ ተምህርኪ!!ለማንኛውም የእልፍ አእላፍ ኦርቶዶክሳዊ ዘማርያንን መዝሙር ከመነቃቀስ…ግልባጭ…የሚል ጨምሩበት፡፡በቃ፡፡ሲደጋገም ስለሚያታክት!!
  እናንተንም…አታልፍም ብሎ…ከሚለው ከቴዲ አፍሮ “አበባይሆሽ” ዜማ ተሰርቆ ከተሰራው እስክስታ አስወራጅ የኤፍሬም አለሙ ሆታ ስለሚያስተጓጉላችሁ!!ለማንኛውም ከተከሳሹ በቀር ይዘቱን ላልቀየረው ክሳችሁ አዲስ መልስ ለማዘጋጀት አልደክምም፡፡የዘወትር ትብብራችሁን ተማምኜ የቀደመውን ከመድገም በቀር!!
  ብቻ ግን ተስፍሾ ማስፈራራትህ ገርሞኛል!!ባል እያፋቱ የሚያገቡ፣የተሻለ ከፋይ ሲያገኙ የተፈረመ የህትመት ውል የሚቀዱና ክርስትናው ቀርቶ ሰብአዊነት የራቃቸው፣ከዘመናዊ እስከ ባሕላዊ ዘፈን እየሰረቁ በስመ-ኢየሱስ የሚያላግጡ፣ባንድ ቀን 10 ቦታ ላይ እንገኛለን ብለው የውሃ ሽታ ሆነው የሚቀሩ፣የቢዮንሴና የክሪስ ብራውን ቅጂ የመሰሉ መንፈሰ-ቀሊላን ባለ ታይት፣ባለሚኒ፣ባለራፐር መሀረብ የፕሮቴስታንት ዘማሪ ተብየዎች እኮ እኛም እናውቃለን--ቅሉ የሰውን ነውር መዝራት ስለማያንጽ እየተውነው እንጅ!!እረ ተወኝ--ክፉ አታናግረኝ!!ደግሞ እመነኝ!!የእናንተ ወፋፍራም ድልብ ፓስተሮችና ዘማሪ ተብየዎች ፖስተር ያልከለለው ጌታ “ምስለ-ፍቁር ወልዳ” በሚለው እመቤታችንን ከተወዳጅ ልጇ ጋር የሚያሳይ ምስል አይከለልም!!
  ወደፍሬ ነገሩ….
  1. ከጽሁፉ እንነሳ፡ ጽሁፉ የሚያቀርባቸው ጥቅሶች እና የጸሀፊው መደምደሚያ የተዋሀደ አይደለም፡፡ለእ/ር ዘምሩ ማለት ለቅዱሳን አትዘምሩ ማለት እንደሆነ ለማስረዳት ብዙ ይታትራል፡፡ነገር ግን አንድም ለቅዱሳን አትዘምሩ የሚል ጥቅስ አላቀረበም፡፡ሐዋርያትን ጠቅሶ ያቀረበው ማብራሪያም ሐዋርያት የተቃወሙት የአምልኮ መልክ ያላቸውን ውዳሴዎችንና አክብሮቶችን እንጅ እንደ ሐዋርያ የቀረቡላቸውን የጸጋ ምስጋናዎችና ስግደቶች ስላልሆነ ጥቅሶችን ለጥጦ በመተርጎም አጉዋጉል ወደ ራስ ሀሳብ ለማስጠጋት መሞክር ከንቱ ድካም ነው፡፡ ሲጀመር ለእ/ር የምናቀርበው ዝማሬ ለቅዱሳኑ ከምናቀርበው ጋር አንድ ስላልሆነ በምንም መለኪያ የእ/ርን ክብር መጋፋት ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡እናንተ እንደዛ ከመሰላችሁ የምታመልኩትን መርምሩ፡፡“ቅዱሳን ሆይ፥ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።” መዝ. 30፡4 ሲል ጸሀፊው ለክርክሩ አስረጅነት የጠቀሰውን ጥቅስ ብንወስድ እንኳ ቅ/ዳዊት “ቅዱሳን ሆይ” እያለ መልእክት የሚያስተላልፈው በህይወት ላሉ ቅዱሳን ብቻ ለይቶ ባለመሆኑ ያረፉ ቅዱሳን እኛን አይሰሙም የሚለውን መከራከሪያ የሚያፈርስ እንጅ የሚያጠናክር አይደለም፡፡
  2. መጽሐፍ ቅዱሱንም እንየው፡፡ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር በተባለው መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን….ርግቤ…ሱላማጢስ….ወዳጄ….ውበቴ በሚሉ ቃላት ተውቦ በሴት አንቀጽ(ጾታ) የቀረበው መዝሙር እንዴትም ቢተረጎም ምስጋናውና ውዳሴው ለእግዚአብሄር የቀረበ ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ሊቃውንቱም (ቅ/ያሬድን ጨምሮ) የሚተረጉሙት አንድም ለወንጌል፣አንድም ለቤ/ክ፣አንድም ለእመቤታችን የቀረበ ውዳሴ ነው እያሉ ነው፡፡እርግጥ የእናንተን ትርጉም አናውቀውም፡፡ግን ለእግዚአብሄር ብቻ የቀረበ መዝሙር ነው እንደማትሉን ተስፋ እናደርጋለን፡፡እ/ር በሴት አንቀጽ ሲመሰገን አይተን ስለማናውቅ፡፡ለቤ/ክ ነው ካላችሁም ዞሮ ዞሮ ምስጋና የሚቀርበው ለእ/ር ብቻ ነው የሚለው መከራከሪያ መፍረሱ አይቀርም፡፡
  3. በመሰረቱ መዝሙር የሚለው ቃል ዘመረ ከሚለው ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ማመስገን ማለት ነው፡፡ምስጋና ደግሞ እንደውለታው አይነትና እንደውለታ አድራጊው ክብርና ማእረግ ይለያያል፡፡ለአምላክ የምናቀርበው ምስጋና የባህርዩ ነው፡፡ፈጥረህ የምትገዛ፤አብቅለህ የምትመግብ፣ከሶስቱ አካለት አንዱን አካል ልከህ ከዘለዓለማዊ ሞተ-ነፍስ ያዳንከን ብለን ነው፡፡ ለቅዱሳኑና ለመላእክት ስንዘምር ግን አምላካቸውን ታምነው ያደረጉትን ተጋድሎና ያገኙትን አክሊለ ክብር እያስታወስን እነሱን ለእኛ አርዓያ እንዲሆኑ የፈቀደ አምላከ በመዝ 88 ቁ 3 መሰረት ከመረጣቸው ጋር ያደረገውን ቃል እንዲያስብ በስማቸው እየዘመርን ተማለደን ነው የምንለው፡፡ልመናችን ሲደርስም በአማላጅነታቸው ስለተደረገልን እነሱን ለመጽናኛ የሰጠንን መልሰን እናመሰግናለን፡፡ስለጸጋቸው እናወድሳቸዋለን፡፡ደግሞ እንኳን ለጻድቃን ለምድራዊ አርበኞችም ይዘመራል፡፡እነሱማ ዝክረ ጻድቅ ለዓለም ይሄሉ….ወጽድቁኒ ይነብር ለዓለም…የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል እየተባለ በመዝ 111 የተነገረላቸው ናቸው፡፡ስለዚህ መንፈሳዊ አርበኞቻችንን በመዝሙራት ስራቸውን እያነሳን እንዘክራለን-እናስባቸዋለን-አሳስቡልን እንላቸዋለን፡፡
  4. ስለ መላእክት በመዝ 102 ቁ 20…ባርክዎ ለእ/ር ኩልክሙ መላእክቲሁ-መላእክት ሁሉ እ/ርን ባርኩ…ተብሎ ተጽፎልሀል፡፡እና ቅ/ዳዊትን ያህል ነቢይና መዘምር መላእክትን እንዲህ በመዝሙሩ ሲያናግራቸው ለጣኦት ምስጋና እያቀረበ ነበር ልትለን ነው???ባርክዎ ያለው ዳዊት ሰአሉ ለነ--ለምኑልን እንዳይል የትኛው ጥቅስ ነው የሚከለክለው??

  ReplyDelete
  Replies
  1. Kal hiywot yasmalen ...gen ayegbachweim

   Delete
  2. Tebarek tiru mels setehewal ega esketesmamanin beagbabu kalun esketetekemnebet deres lemisegana gedeb yelewum menafekanoch ende ashen feltewal mewagat yenorbenal Egzeabher yegesesachewu.

   Delete
 4. 5. ስለ እመቤታችን የምስጋና(የመዝሙራት) ምንጮች
  ሀ. ትንቢት፡ ቤ/ክ ዳዊት በመዝ 44 ቁ 16….ለልጅ ልጅ ስምሽን ያሳስባሉ…ሲል የተናገረው ትንቢት እመቤታችን በሉቃ 1 ቁ 48….እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ይሉኛል…ስትል በተናገረችው ቃል ፍጻሜ አግኝቱዋል ብላ ታስተምራለች፡፡የምድራዊቷን ቅ/ኤልሳቤጥ እና የሰማያውይውን ቅ/ገብርኤል ምስጋናም እንዳትረሳው፡፡ይሄው እኛም ለፈጽሞ ትንቢት ሰአሊ ለነ ቅድስት እያልን ስሙዋን እንጠራለን-ለትውልድ እናሳስባለ፡፡የለም፡፡ የዳዊት ትንቢት ለኢየሩሳሌም የተነገረ ነው የሚል ካለም ጌታ ተመላለሰባት ተብሎ ከምትወደሰው ግኡዝ ምድር ጌታን ወልዳ፣ተሰዳ፣አጥብታ፣ከቀራንዮ እስከ ጰራቅሊጦስ ያልተለየቸው ወላዲተ አምላክ ምስጋናም ሲያንሳት ነዋ እንላለን!!
  ለ. ቀደምት አበው፡እነ ቅ/ኤፍሬም፣እነ አባ ህርያቆስ፣እነ ቅ/ያሬድ፣እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፣እነ ዮሐንስ አፈወርቅ እረ ስንቱ…..አወድሰዋት፣ቅድስናዋን አማላጅነቱዋን ተናግረው አይጠግቡም፡፡እነዚህ ቅዱሳን ስለ ብሉይና ሐዲስ ያላቸው እውቀት ደግሞ አይጠረጠርም፡፡በምስጋናዋ የሚደረድሩት የነቢያት ትንቢትና አምሳል፣የሐዋርያት ስብከት ምጥቀታቸውን ያሳያል፡፡ትምህርቱን ፈጥረው፣አመንጭተው ሳይሆን ከሐዋርያት ሲወርድ ሲዋረድ እናዳገኙም እናውቃለ፡፡እኛም የእነሱ ልጆች ስለሆንን አርዓያነታቸውን ተከትለን ...ተፈስሂ ኦ ማርያም እም ወአመት-እናትነትን ከአገልጋይነት ያስተባበርሽው ብቸኛዋ እመቤት ሆይ ደስ ይበልሽ… እያልን በገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንላታለን፡፡እናወድሳታለን፡፡ሆኖም አናመልካትም!!

  ሐ. ኦርቶዶክሳዊት ቤ/ክ እውቅና ከምትሰጣቸው ጉባኤያት መካከል በ431 ዓ.ም 200 ሊቃውንት ተሰብስበው ሁለት አካል፣ ሁለት ባህርይ ባዩን ንስጥሮስን ያወገዙበት ጉባኤ-ኤፌሶን አንዱ ነው፡፡በዚህ ጉባኤ ላይ ንስጥሮስ እመቤታችን የወለደችው መለኮትነት የሌለው ወልድን ብቻ (እሩቅ ብእሲ) እንጅ መለኮት የተዋሀደው ስጋን አይደለም በማለቱ “ታዲያ ሰብዐ ሰገል አምኃ አቅርበው የአምልኮ ስግደት የሰገዱት ለሩቅ ብእሲ ነው እንዴ” ተብሎ ተረታ፡፡የእመቤታችን ወላዲተ-አምላክነትም በጉባኤው ዳግም በአጽንኦት ተነገረ፡፡በመጨረሻም በውሳኔው አንቀጸሃይማኖት “….የእውነተኛ ብርሃን እናት ሆይ እናከብርሻለን፣መጥቶ ነፍሳችንን ያዳነውን የዓለምን ሁሉ መድኃኒት ስለወለድሽልን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆይ እናመሰግንሻለን….” ሲሉ የቀደሙ አባቶችን ትምህርት አጽንተው ከ1500 አመት በፊት በዶግማ ደንግገውልናል!!ዶግማ ደግሞ አይሻሻልም፣አይጨመርበትም፣አይቀነስበትም!!ስለሆነም በመላው ዓለም ይሄን ጉባኤ በሚቀበሉ የምእራብና የምስራቅ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ከሉተራውያን በቀር እመቤታችንን ‘ሰአሊ ለነ ቅድስት’ ሳይል የሚውል ክርስቲያን የለም!!በነገራችን ላይ ደቀመዛሙርቱ እንጅ ሉተር የእመቤታችንን ምስጋና አይቃወምም ነበር፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Endzhu astmerut ...yeh yedabelos fers

   Delete
 5. ቃለ ሕይወት ያሰማህ ።እውነትን እየቀበሩ በሕዝቡ ላይ አዚም የጣሉ፣ ሕዝቡን ከፈጠራቸው አምላክ የለዩ፣የቀራንዮ ፍቅሩን እየጣሉ የአለት እንጀራቸውን የሚያበስሉ።እንዲሁ አይቀርም ፍርድ ይመጣል።

  ReplyDelete
 6. Next will be engdawork ..yesum yegude new kihedet yemelabet mezmuroch.orthodoxawiyan mariyam selemnewdat ..metekemiya new yaderegen ..mewegez yalebachew betam kehedet yehonu mezmurochen new yemizemerew.mereten kef adergo asbareke menamen yemilewo ewonet yemaymesel mezmure...men lay komo new mereten Kef adergo yasbarekew????

  ReplyDelete
 7. ታዴዎስ: እንግዳ ወርቅ፣ ፋንቱ ወልዴ፣ ጸዳለ ጎበዜ፣ ቸርነት ሰናይ፣ መኩሪያ ጉግሳ፣(ገጣሚ) ልዑል ሰገድ፣ ዋና ዋና ተጠያቂዎች ናችሁ
  ጐበዝ ምነው ምንዳዬ ተረሳ ? ወንዶሰን በቀለስ ሌሎችም አሉ ንስሐ ገብተው ካልተመለሱ የግል ማህደራቸውን መክፈት ነው ከመጋረጃ በሰተጀርባ የሰሯትን ነውራቸውን እነዚህ የኢትዬጵያን ህዝብ በስህተት ጐዳና የመሩ ሆድ አደሮች የ ኢየሱስን ክብር ለፍጡራን የሰጡ የ አውሬው በኢትዮጵያ ምድር መንገድ ጠራጊዎች ናቸው

  ReplyDelete
  Replies
  1. Lemin ene tiztaw, zerfen, begashawin askeriteh enezihn becha tekeskachew? enesum eko sele dingel mariyam zemirewal/ sebkewal. Ketechu ayker hulunim metechet new, lemin tezebarikaleh

   Delete
  2. thank you whoever wrote this comment. This site is being run by one specific group. like the priest and bishops have their own groups the mezmuran have their own groups. the true believers of the faith and then the FAKE group

   Delete
 8. hahaha what a funny menafik you are?????? why do not you first regret to your sin (nufake) before advising others. SIMA!! ANTE BE NUFAKE MAEBEL EYETENAWETK SLEHONE BENSEHA WEDE TEKEKELEGANAW HAIMANOT TEMELES. DO NOT KID US.

  ReplyDelete
 9. ያላዋቂ ሳሚ…… ሆኖብሃል፡፡ ሂድና ተማር ከመጠምጠም መማር ይቅደም እንዲሉ አበው፡፡ ለአንተ አትሆን እናትህ አይደለችምና ክደሃታልና እሷ ግን አሁኑም ብትመለስ በፍቅር ትቀበልሃለች፡፡ ምንም እንኳ ክብሯን ባትቀንሰውም ብታዋርዳት፣ ብትንቃት… እንደ አንተ ጨካኝ አይደለችምና ታማልድሃለች፡፡ እኛ ልጆቿ ነን እሷ እናታችን ናት ስለሆነም እናት ለልጇ አስፈላጊውን ሁሉ ታደረግለታለች፡፡ ከአምላኳ በተሰጣት ቃል ኪዳን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ታድናለች፡፡
  እድኝኝ እናቴ ከስጋ ፈተና…… ከእና ጋር ከሆንሽ አለን ቅድስና
  ታዴዎስ ታላቅ ክብር አገኘህ .. ስለስሟ ተተችተሃልና
  ያላዋቂ ሳሚ…… ሆኖብሃል፡፡ ሂድና ተማር ከመጠምጠም መማር ይቅደም እንዲሉ አበው፡፡ ለአንተ አትሆን እናትህ አይደለችምና ክደሃታልና እሷ ግን አሁኑም ብትመለስ በፍቅር ትቀበልሃለች፡፡ ምንም እንኳ ክብሯን ባትቀንሰውም ብታዋርዳት፣ ብትንቃት… እንደ አንተ ጨካኝ አይደለችምና ታማልድሃለች፡፡ እኛ ልጆቿ ነን እሷ እናታችን ናት ስለሆነም እናት ለልጇ አስፈላጊውን ሁሉ ታደረግለታለች፡፡ ከአምላኳ በተሰጣት ቃል ኪዳን ከመከራ ስጋ ከመከራ ነፍስ ታድናለች፡፡
  እድኝኝ እናቴ ከስጋ ፈተና…… ከእና ጋር ከሆንሽ አለን ቅድስና
  ታዴዎስ ታላቅ ክብር አገኘህ .. ስለስሟ ተተችተሃልና

  ReplyDelete
 10. enante gibrachu kesimachu yettaresebachu ayhudoch!!!!!

  ReplyDelete
 11. You wonderful may God bless you. You have a credit with God you will be awarded in the heaven. I know you write this in good intention not to criticize others. Revealing the truth needs courage and Love to God the source of truth and life. The devil abuse and control their mind, unless Lord let them free from the bandage what can you do? But your message surly helps many to shift the truth please continue this wonderful service.

  ReplyDelete
 12. ማስተዋልንንና መንፈሳዊውን ጥበብ ከልቡናው በሰይጣን ምክር ተቀምቶ አእምሮውን ለብዎውን ካጣ ሰው የሞተ አስከሬን ይሻላል፡፡ ባንድ ስሙ ዕውቀት ሊኖረው የሚችልበት ዕድል የለውምና፡፡ ነቢዩ ዳዊት “ሰው እናታችን ጽዮን ይላል፤በውስጧም ሰው ተወለደ::” ብሎ የተናገረላትን ጌታችንን እናት ከሰውነት ያልወጣንና ሰይጣናዊ ከሆነው የሞት ትምህርት ያልቀመስን እኛ ምን ጊዜም እመቤታችንን እናታችን ጽዮን እንላታለን፡፡ፅዮን ማለት አምባ መጠጊያ ነውና እሷም ለኛ አምባችን መጠጊያችን ናትና፡፡ እንዲያው ግን እናንተ መናፍቃን የእሷ መመስገን እንዲህ እርር ድብን የሚያደርጋችሁ “በዘርህና በዘርዋ መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ” ያለው የጌታ ቃል እየተፈጸመባችሁ ነው አይደል ግን እናንተ መች ታውቁታላችሁ ልብ ይስጣችሁ እንጂ፡፡ ዮሀንስም በራእዩ ዲያብሎስ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት ሲያሳድዳት ያየው ዲያብሎስ የእሷ የሆኑትንና የልጇም ምስክርነት ያላቸውን ይዋጋ ዘንድ በባህር አሸዋ መካከል ቆመ የተባለለት የዲያብሎስ መቆሚያ መሰረት የሌላችሁ አሸዋዎች ስለሆናችሁ አይደል በናንተ እየተመሰለ እውነተኛ አማኞችን በመሠረት አልባ ጭቅጭቃችሁ ስትዋጉ የምትኖሩት፡፡ ደግሞ አንተን ብሎ መካሪ ቂቂቂቂቂ!!!!!!!!!!! ለራስህ ተመከር ይልቅ፡፡ ዕኛስ የምናደርገውን እናውቃለንና ሰይጣን ምክር አያሻንም፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. Wow I am happy kal hiywot yasemalen

   Delete
 13. Replies
  1. This blog is a tehadio blog. they should just call it Zetehadiso

   Delete
 14. አስተያየት ለመስጠት ጽሁፍ ከጀመርኩ በኋላ ለማን መናገር እንዳለብኝ ቆም ብዬ ማሰብ እንዳለብኝ ተገነዘብኩ፡፡ ሰው በተፈጥሮ ወይንም በሌላ ምክንያት የመስማት ችግር ከገጠመው የሚግባባው በምልክት ቋንቋ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ግን አይኑ ማየት ሲችል ነው፡፡ አለበለዚያ በመጻፍም ሆነ በቃል ለእንደዚህ አይነቱ ሰው ማስረዳት ነፋስን እንደመጨበጥ ይሆንበታል፡፡
  የአባ ሰላማ የጡመራ መድረክ ሰዎች ሆይ የጠፋውን ዓይናችሁን የሚያበራና የደነቆረውን ጆሯችሁን የሚከፍት አምላክ ከክፉ መንፈስ እንዲገላግላችሁ፣ የቅዱሳን ምልጃ አሁንም ኢትዮጵያን አይረሳትምና በምድሯ ለምትመላለሱ አሁንም የንስሃ ዕድሜ ይስጣችሁ፡፡
  ዖርቶዶክሳውያን ደግሞ እንደዚህን ሰዎች እንዲመልሳቸው እንለምን!

  ReplyDelete
 15. 2. መጽሐፍ ቅዱሱንም እንየው፡፡ከመዝሙሮች ሁሉ የሚበልጥ መዝሙር በተባለው መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን….ርግቤ…ሱላማጢስ….ወዳጄ….ውበቴ በሚሉ ቃላት ተውቦ በሴት አንቀጽ(ጾታ) የቀረበው መዝሙር እንዴትም ቢተረጎም ምስጋናውና ውዳሴው ለእግዚአብሄር የቀረበ ነው ለማለት አስቸጋሪ ነው፡፡ሊቃውንቱም (ቅ/ያሬድን ጨምሮ) የሚተረጉሙት አንድም ለወንጌል፣አንድም ለቤ/ክ፣አንድም ለእመቤታችን የቀረበ ውዳሴ ነው እያሉ ነው፡፡እርግጥ የእናንተን ትርጉም አናውቀውም፡፡ግን ለእግዚአብሄር ብቻ የቀረበ መዝሙር ነው እንደማትሉን ተስፋ እናደርጋለን፡፡እ/ር በሴት አንቀጽ ሲመሰገን አይተን ስለማናውቅ፡፡ለቤ/ክ ነው ካላችሁም ዞሮ ዞሮ ምስጋና የሚቀርበው ለእ/ር ብቻ ነው የሚለው መከራከሪያ መፍረሱ አይቀርም፡፡

  ReplyDelete
 16. tiz yilegnal..studiyo wusit mezemer yelebetim yetebale yegitim singn...ay tadiwos ewunet yemitimerabetin menfes tawukew yihun? yikir yibelh..band wekit mezimur lisera studyo gebito
  '"mekoms lanchi new mekemet lelijish.."" bilo lizemir neber...yikir yibelew..bekirikir new singnu endiweta yetederegew....min yidereg medireku benegadewoch siletemola man yarim..man ewunet yinager...yikir yibelachihu!!

  ReplyDelete
 17. Keber semayena medren sadkanen semaetaten melaekten emebetachenen lefetere amlak.kibrun amlkowon lersu yihun sadkanm sedkewal semaetatem kibrachewonn yikebelalu kersu zend..yegnan tibkena ayeshumna lerasachen enwek.mamlek yemigebanen bicha enamelk .melkamochun degmo beserachew enmselachew.enkberachew enjji anamlkachew.

  ReplyDelete
 18. Go heel with your followers.There is no way except him,All your roads they drug u to hell,it's dead end.

  ReplyDelete
 19. Yadanegne awokewalhu
  yemotelegne eyesuse new
  selelelegne yemekefelew
  serotype misgana new.
  Happy new year

  ReplyDelete