Monday, September 15, 2014

በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሚመራው የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ አስራ ሁለተኛ አመታዊ ጉባኤ ተካሄደ

Read in PDF

በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ስር የሚመራው የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ አስራ ሁለተኛ አመታዊ ጉባኤ “ራእይ ያለው ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በደብረ ቅዱሳን ተከለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን በኦታዋ ካናዳ ተካሄደ፡፡ እንደፈረንጆች አቆጣጠር ከAugust 29 – August 31, 2014 ለሶስት ቀናት የተካሄደው አመታዊ መደበኛ ጉባኤው በተሳካ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን ከካናዳ እና ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ከ150 በላይ ተሳታፊዎች 21 የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናትንና ሰንበት ትምህርት ቤቶችን በመወከል ተገኝተዋል።

ጉባኤው በሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ የቅዱስ ሲኖዶስ የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ጸሎት የተጀመረ ሲሆን ራእይ ያለው ትውልድ በሚለው መሪ ቃል ሥር ልዩ ልዩ ትምህርቶች በተለያዩ መምህራን የተሰጡ ሲሆን በዚሁ መሠረት፦
·        ዓላማ፤ ጥሪና ራዕይ - በቀሲስ ዘገብርኤል አለማየሁ
·        ራእይ በመጽሐፍ ቅዱስ - በቆሞስ አባ መላኩ ታከለ
·        የሕይወት ራዕይ - በቀሲስ መላኩ ተረፈ
·        ራዕይ ለቤተክርስትያን - በቀሲስ መላኩ ተረፈ
·        ራዕይ ለኢትዮጵያ - በአባ ገብረሥላሴ ጥበቡ
·        ራዕይ ለአለም - በቀሲስ ዘገብርኤል አለማየሁ ተሰጥተዋል፡፡
የጉባኤው ተሳታፊዎችም በመምህራን የተሰጠውን ትምህርት በበለጠ ከሕይወታቸው ጋር ማዛመድ እንዲችሉ የሚረዳና ከተመረጡት የትምህርት እርእስት ጋር የሚሄዱ ተግባራዊ መልመጃዎች ቀርበዋል። ከዚህ በተጨማሪም በየክልል ጉባኤ ላይ የየቤተክርስቲያኑ ሰንበት ትምህርት ቤት አባላት በህብረት ሆነው በተመደበላቸው የትምህርት ርዕስ ላይ የቀረፁትን ስምንት ራዕዮች በክልሉ ተወካዮች በኩል አቅርበዋል።

12ኛው አመታዊ ጉባኤ ከመጠናቀቁ በፊትም በአንድነት ጉባኤ ኮሚቴው የሁለት አመት የሰራ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ በተለይም በትምህርት ኮሚቴ የተከናወኑ አዳዲስ ግኝቶች ለጉባኤው ተብራርተዋል፡፡ በተለይም ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የመማሪያ ሰነድንና አዲስ አባል ሆነው መደበኛ ሰንበት ትምህርት ቤትን ለሚቀላቀሉ አባላት መሰጠት ያለበትን መሠረታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት አስተምሮ የሚገልጽ የማስተማሪያ ሰነድ ተጽፎ መጠናቀቁን በተመለከተ በሚመለከታቸው ሃላፊዎች ገለጻ ተድርጓል።

መታዊ ጉባኤው ከመጠናቀቁ በፊት የኮሚቴ ምርጫ የተካሄደ ሲሆን ምርጫው ያተኮረው በአሁኑ ሰአት ከአመራር ኮሚቴ አባላት መካከል በልዩ ልዩ ምክንያት በጎደሉ አባላት ምትክ ፈቃደኛ የሆኑ የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮችን ለመተካትና አሁን ያለው ኮሚቴ የስራ ዘመኑን ሲጨርስ የሚተኩ ሶስት አባሎችን ለማሰልጠንና ዝግጁ ለማድረግ ነው። በዚሁ መሠረት በምላተ ጉባኤው ተሳትፎ ከተለያዩ ሰንበት ትምህርት ቤቶች 11 አገልጋዮች ተመርጠዋል። ቀጣዩ 13ኛው የአንድነት ጉባኤ ኦክላንድ ካሊፎርንያ በሚገኘው በመድኀኔለም ቤተ ክርስቲያን እንዲሆን ተወስኖአል።

በተያያዘም November 22,2014 በዋሺንግተን ዲሲ የሚከበረውን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ፓትርያርክ የ25ተኛ ዓመት በዓለ ሲመትና አዲስ የተገዛው የቤተክሕነት ሕንጻ ምርቃትን ለማክበር ወጣቶች ከአባቶቻቸው ጋር መዘጋጀታቸውን በጉባኤው ላይ ገልጸዋል::

በጉባኤው ላይ የቀረቡ ትምህርቶችና ዝማሬዎች መልካም የነበሩ ሲሆን ዘማሪ ዓለማየሁ ኡርጌ የእግዚአብሔርን ክብር ለተክለ ሃይማኖት ሰጥቶ ተክለ ሃይማኖትን የሚያስመልክ መዝሙር በመዘመር የጉባኤውን መንፈስ የረበሸ ሲሆን ለወደፊቱ መዘምራንን ሲመርጡ እየታየ ቢሆን መልካም ነው የሚል አስተያየት ያላቸው አሉ፡፡ በጉባኤው ላይ የታዩ መልካም ነገሮች የመኖራቸውን ያህል የአንዳንድ እግዚአብሔርን ብለው ሳይሆን እኅቶችን ለማበላሸት ዓላማዬ ብለው የመጡና በዝሙትና በመዳራት መንፈስ የተሞሉ ጥቂት ወጣቶችም ነበሩ፡፡ እነዚህ ለመዳራት የሚመጡ ጥቂት በእጅ የሚቆጠሩ ከአምስት ያልበለጡ ወጣቶች በአዲስ አበባና በሰሜን አሜሪካ የሰንበት ትምርት ቤቶች ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ ሲሆን በእድሜም ከሁሉ ወጣቶች የሚበልጡ እንደሆኑም ታውቋል፡፡ ጉዳያቸውም በመረጃ የተያዘ ሲሆን ይህን ሥራቸውን ካላቆሙ ስማቸውን ለሲኖዶስ ለማቅረብ እንገደዳለን ይላሉ ጉዳዩን በቅርበት የታዘቡ የቤተክርስቲያን ልጆች። ለወደፊቱ እንዲህ ዓይነቱ የቅድስና ጉድለት እንዳይኖሩ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ነጻ የሚያወጣውን እውነተኛ ወንጌል በመስበክና በማስተማር አባሎቻቸውን በእግዚአብሔር ቃል እንዲለወጡና በቅድስና እንዲመላለሱ ሊረዷቸው ይገባል፡፡ አሊያ በቤተክርስቲያን ላይ ትልቅ ጥፋት ይደርሳል፡፡

16 comments:

 1. ማህበረ ቅዱሳን በአሜሪካው ሴኖድ እንዳይካተት መደረጉ ለወንጌል አመቺ ነው

  ReplyDelete
  Replies
  1. Are you trying to say that No MK so it is easy to distorter the wongel and confuse meemenan to convert to protestant??????? neke belenal !!!!!!!!!

   Delete
 2. አዎ ለቀስጣው አይመቻችሁም መናፍቅ ሁላ

  ReplyDelete
 3. ቃሉን በቃል ትምርቱን በትምህርት መመለስ ሲገባችሁ ለምን ስድብና ቁጣ ይቀድማችኋል?
  የቃኤልንና የእግዚአብሔርን ቃል አስተውሉ። ቃኤል፣ ለምን ተናደድህ? መልካም ብሰራ ትናደድ ነበርን? ንዴትና ቁጣ የቃኤል ባህርይ ነው

  ReplyDelete
 4. That is true, also nature and behavior of mk

  ReplyDelete

 5. መጽሐፈ ጤፉት ለኅትመት በቃች

  ReplyDelete
 6. Why you think like evil. Mkd is continuing working you talk .....

  ReplyDelete
 7. Mk work for the devil's. This is very true.

  ReplyDelete
 8. You cry every day. Mk working and working....

  ReplyDelete
 9. Mk work hard to fulfill there father devil's hassab.mk is against gospel and jesus.

  ReplyDelete
 10. I am so disappointed to read this massage . I don’t get why this is posted to begin with. You could have post, if you really have to, where, when and general statement about the Andinet Gubae . Who in the right mind would say such things by accusing people what their intention were. Shame on you!!! I don’t know what you are trying to accomplish and if you really stand by your words, please include your name too. Did you read the last paragraph before you post it? በጣም ነው የሚያሳዝነው። እርስ በርስ መወነጃጀያ መድርክ!

  ReplyDelete
 11. Betam asazagn tsehuf. Gubaywn tesatefyalew menem endih aynet neger alayehum. Ebakachehun yesew sem atabelashu

  ReplyDelete
 12. አሁን በናንተ አባባል የጉባኤውን ጥሩ መንፈስ ሪፖርት ማቅረባችሁ ነው እውነትም እራእይ ያላችሁ ሰወች ራእይ ያለው ሰው አንዱ መሆን ያለበት ነገር ምመናንን መክሮ እና ገስፆ ማስተካከል እንጅ በአደባባይ ፀያፍ ካንድ ክርስቲያን አንደበት የማይጠበቅ ቃላት በሚዲያ አይነገርም ነውር ነው ልጆቹንስ ኣናግራችሁዋል ? ዘማሪውንስ አስተካክል ብላችሁታል? ለምን ልጆችን ታጠፋላችሁ ለምንስ ቤተክርስቲያንን ለጠላት አሳልፋችሁ ትሰጣላችሁ እግዚአብሄር ልቦናችሁን ይመልስ በጣም ታሳፍራላችሁ

  ReplyDelete
 13. ውሸት ውሸት ውሸት። ነበርኩ ጉባኤው ላይ ቪዲዮ ዩቱብ ላይ አለ። እባካችሁ የሀሰት ወሬ አታናፍሱ።

  ReplyDelete
 14. አሁን አወቅን ስው ያላየውን አይናገርም ተሃድሶ ብትባሉም ምክንያቱም የሰውነ ነብስ ለማዳን ሳይሆን የእለት እንጀራችሁን እያበሰላችሁነው የራሳችሁን ጥቅም ለማሳደድ ነው ።ይህ ዌብሳይትም የናነተ መድረክ እንደሆነ ተረዳን

  ReplyDelete