Tuesday, September 23, 2014

የኦክላንድ ደብረ ሰላም ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን እና የመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ልዩነት በይቅርታ ተደመደመ።

 Read in PDF
ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በመጨረሻም ቢሆን መልካም ታሪክ እየሰሩ ነው። በየሄደቡት ሁሉ የበድልኋችሁ ይቅር በሉኝ በማለት ማንኛውንም ተቀይሚያለሁ ያለውን ሁሉ እየታረቁ ነው።
  የኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ያስተዳደር በደል ደረሰብን በማለት ባቀረቡት ጩኸት የሚሰማቸው በመታጣቱ ከመድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተለይተው የራሳቸውን ቤተ ክርስቲያን ማቋቋማቸውና በብፁእ አቡነ መልከ ጼዴቅ መወገዛቸው ይታወሳል። ቅዱስ ፓትርያርኩና ሌሎች አንዳንድ ጳጳሳት እንዲሁም ሰባክያነ ወንጌል ውግዙቱን አንቀበልም በማለት ከቤተ ክርስቲያኑ ጋር ቁመው ቆይተዋል። ይህን ሁኔታ እንደ ልዩ መግቢያ በመጠቀም ጠቡን ወደ ቅዱስ ፓትርያርኩ እና ወደ አቡነ መልከ ጼዴቅ ከፍ በማድረግ ከጠቡ የሚገኘውን ፍርፋሪ በኮፌዳቸው ሊለቅሙ ያሰፈሰፉ ሰዎችም ነበሩ። በተለይም በአስታራቂ ኮሚቴው ከተካተቱት አባላት ውስጥ የዳላሱና የሎስአንጀለሱ ዋና ተጠቃሽ ናቸው። 

አንዳንድ የቦርድ ኮሚቴ ነን የሚሉ የፖለቲካና የልዩ ጥቅም ኃይሎችም ከጠቡ ተጠቃሚ ለመሆን ሲሯሯጡ ነበር። የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅን ጠንካራ ወዳጆች ሰባክያነ ወንጌልን በዚህ እያያይዞ መምታት ዋና ተግባራቸው አድርገው ያላሉትን አሉ ያላደረጉትን አደረጉ በማለት ከአቡነ መልከ ጼዴቅ ለይተዋቸው ነበር። ይህን ልዩነት ወደ ሕዝብ ለማውረድ ታስቦም ጽሑፍ ተዘጋጅቶ በጥምቀት በዓል ላይ ሊበተን ሲል እግዚአብሔር ቀድሞ ወጥመዱን አክቸፈው። የታሰበው የጠብ እቅድ ተበላሽቶ ወደ ሰላም እርቅና ፍቅር ተለወጠ አባቶች እርስ በርስ ይቅርታ ተጠያየቁ ጽሑፉን ያዘጋጀው ሰው ኮፒ አድርጎ ሲመጣ ሰላም ወርዶ አገኘው በቁጣ ተሞልቶ ፊቱ ላይ ይታወቅበት ነበር ይላሉ ታዛቢዎች። ምእመናኑ እልል አሉ ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን እያሉ እግዚአብሔርን በመዝሙር አከበሩ። የጠላታችን ቢሆንም ጊዜው፤ ዛሬም እኛው ነን የምናሸንፈው ነገም እኛው ነን የምናሸንፈው። ተብሎ ተዘመረ።

 እርቁ ቀጠለ፤ በኦክላንድ መድኃኔ ዓለም በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ የተጣላው ሁሉ ታረቀ አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናትም ተቀባይነት እንዲያገኙ ተወሰነ ብፁዕነታቸውም ውግዘቱን አነሱ። በዚህም ሌላ የሰይጣን ሥራ ፈረሰ። የላስ ቤጋስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሲመረቅ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ተገኙ። ብፁዕ አቡነ ዮሴፍና አቡነ መልከ ጼዴቅ ወደ ቀደመ ፍቅራቸው ተመለሱ። በዚህ ጊዜ መምህር ተከስተም ተገኝቶ ከአቡነ መልከ ጼዴቅ ጋር ታረቀ። ትቶኝ ስለሄደ እንጂ የምወደው ልጄ ነው ብለው በደስታ ይቅርታ አደረጉለት። በሁለቱ አባትና ልጅ መካከል ገብቶ የነበረው ሰይጣን መግቢያ ያጣበት ጊዜ ነበር። አቡነ መልከ ጼዴቅና መምህር ተከስተ በሎስ አንጀለስ ድንግል ማርያም በአንድ ጉባኤ ተጋብዘው አገለገሉ የሎስ አንጀለስ ሕዝብ በጣም ተደሰተ።  
   እርቁ ቀጠለ የደብረ ሰላም ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ አባላት ቅንነት የተሞላበት ጥበብ ተጠቅመው አቡነ መልከ ጼዴቅን ሄደው አነጋገሩ ይምጡና ይባርኩን ድሮም ጠባችን ለምን ለኛስ አይፈርዱልንም እኛስ ልጆች አይደለንም ወይ በሚል አኮረፍን እንጂ ከእርስዎ ጋር ጠብ የለንም አሁንም እንፈልግዎታለን ሲሉ አረጋገገጡ። ብፁዕነታቸው እኔም ስጠብቃችሁ ነበር እንኳን መጣችሁልኝ እናንተ ተዘጋጁ እኔም ምእመናኖቼን አስከትዬ እመጣለሁ አሉ። ቀኑ መስከረም 21 እንዲሆን ተወሰኖ ልዩ ልዩ እንግዶች ጥሪ ተደረገላቸው። ሊቀ ካህናትና አቡነ ሚካኤል አቡነ ዲሜጥሮስ ከካናዳ ጨምሮ በርካታ ጳጳሳት ተጋበዙ። ይህ በእንዲህ እንዳለ የመድኃኔ ዓለም ቦርዶች እርቁን በመቃወም ተንቀሳቅሰው እንደነበር ምንጮች ተቁመዋል። ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሕዝባቸውን አስከትለው ወደ ኢየሱስ ሄዱ። ከሦስቱ ቦርዶች ማለት ከአቶ ብንያም ከወዘሮ ደብሪቱና ከወይዘሮ ፍቅሬ በስተቀር ሁሉም የመድኃኔ ዓለም ሰዎች ተገኝተዋል የሦስቱ ሰዎች ቅሬታ ግን አጠያያቂ ሆኗል የጠቡ መነሻ እነማን እንደነበሩ ግልጥ ሆኗል የሚሉ አሉ።
  የኢየሱስ ሕዝብ ብፁዕነታቸውን የተቀበለበት ስሜት የሚያስለቅስ እጅግ የሚያስደስትም ነበር። ሰንጋ ሳይቀር አርደው በከፍተኛ ደረጃ ደግሰዋል ። ጸሎት ተደረጎ ብፁዕነታቸው ህዝቡን ባረኩ። ሁሉም ልዩ ደስታና ሐሴት ይታይባቸው ነበር። በዚህ ሁሉ ክብሩ ለጌታ ይሁን አሜን! ሰዎች የሚሉኝን እየሰማሁ በድያችኋለሁና ይቅር በሉኝ ሲሉ የተናገሩት ብፁዕነታቸው ባሳዩት መንፈሳዊነት ትልቅ ፍቅርና ከበሬታን አግኝተዋል። ትሕትና ክብርን ትቀድማለች እንዳለ ጠቢቡ ሰሎሞን የአቡነ መልከ ጼዴቅ ሁኔታ ብዙዎችን እያስገረመ ነው። ከዚህ በኋላ በሰላም እና በፍቅር አብረን እንቀጥላለን ያለፈውን ነገር ከእንግዲህ ተመልሰን አናስበውም ብለዋል።  
  አሁን የሚቀረው የዳላስ ቅዱስ ሚካኤልና የኢየሱስ፣ የዲሲ ቅ/ገብር ኤልና ቅ/ ሚካኤል፣ የዴንበር ሥላሴና ኪዳነ ምሕረት፣ እንዲሁም የስያትል ክብረ ቅዱሳን መድኃኔ ዓለምና ቅ/ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናትን አንድ ማድረግ በመካከላቸው ሰላም መመሥረት ነው። ሆኖም የሁለቱ ማለት የሎስ አንጀለሱ መነኩሴና የዳላሱ ዲያቆን/ቄስ/ የሚያደርጉት እንቅሥቃሴ ሥጋት ላይ እንደጣላቸው ካህናቱ ይናገራሉ። ሁሉም ካህናትና ጳጳሳት አንድ ሆነዋል ነገር ግን እነዚህ ሁለት ሰዎች አቡነ ሳዊሮስንና አቡነ ኤልያስን  ለመገንጠል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በጥብቅ እየተከታተሉት መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል።
 አስቀድመው የነቁና እንቅሥቃሴውን በማክቸፍ ትልቅ ሥራ የሠሩት አንድነትን ለማምጣት ጥረት ያደረጉት አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ አባ ገብረ ሥላሴ ጥበቡ አባ ሀብተ ማርያም ተፋለጥ ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ ሌሎች ጳጳሳትና ሰባክያነ ወንጌል ሁሉ ተሳታፊ ሆነዋል፡። ከየአብያተ ክርስቲያናቱ የተውጣጣው የምእመናን አስታራቂ ኮሚቴም ትልቅ አስተዋጽዖ አድርጓል። ሁሉንም እግዚአብሔር ይባርካችሁ ሲሉ አቡነ መልከ ጼዴቅ አመስግነዋል።
እኛም የኦክላንድ መድኃኔ ዓለም እና የኢየሱስ አብያተ ክርስቲያናት ምእመናን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን። እናንተን ለመለያየት በስውርም ሆነ በግልጥ የሚንቀሳንቀስ ኃይል ቢኖር ተከታትለን እናጋልጠዋለን አይዟችሁ በርቱ። በዚህ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የወንጌል እንቅሥቃሴ በገንዘብ እንድትደግፉ እና አገራችንን ከእስልምና ወረራ እንድንታደግ ስንል በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
በሌላ ዜና ባገር ቤቱ ሲኖዶስ የሚተዳደሩ የአሜሪካ አብያተ ክርስቲያናት በዓላትን በአንድነት ለማክበር እየተሰባሰቡ ነው። በዲሲ አካባቢ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል መሪነት የመስቀልና የጥምቀትን በዓል በጋራ ለማክበር እየተንቀሳቀሱ ነው። በአትላንታ ሦስት አብያተ ክርስቲያናት በዳላስ አምስት አብያተ ክርስቲያናት አንድነትን መሥርተዋል። አጥማቂው አቶ ግርማም ወደ አሜሪካ ሊያቀና መሆኑን ሕብር ራዲዮ ዘግቧል። ወደ ዳላስ ሚካኤል ሊያቀና ነው የሚሉ አሉ እርግጠኞች ግን አልሆንንም። ለማንኛውም ዳላሶች ከመናፍስታዊ አሰራር እራሳችሁን ጠብቁ ስንል ወገናዊ ምክራችንን እንለግሳለን። ጥንቆላው እንዴት እንደሚሠራ እያጠናነው ስለሆነ ወደ ፊት እንገልጠዋለን። አስማቱ የሚገኘው ትክል ድንጋይ (ጎንደር)። ጉም ኢየሱስ (ጎጃም)እና መንዝ አካባቢ መሆኑን አረጋግጠን እየተከታተልነው ነው። የምናውቃቸው ወንበዴዎች ሁሉ ልክ እንደ ግርማ እያጠመቁ ሀብታም ሲሆኑ እያየን የእግዚአብሔር ሥራ ነው ማለት ትልቅ ሞኝነት ነው ተጠንቀቁ!!!!
ዜናውን ለላካችሁልን ሁሉ እናመሰግናለን።       

5 comments:

 1. አባ ሰላማዎች እግዚአብሔር ከእናነተ ጋር ይሁን አፍ እና አይን ስለ ሆናችሁን የምታደርጉት ሁሉ መልካም ነው እራሳችን እንድናይ ያደርገናል በርቱ

  ReplyDelete
 2. የሁለቱ ማለት የሎስ አንጀለሱ መነኩሴና የዳላሱ ዲያቆን/ቄስ/ የሚያደርጉት እንቅሥቃሴ ሥጋት ላይ እንደጣላቸው ካህናቱ ይናገራሉ
  1.አባ ጽጌ
  2 ዲያቆን አንዶዓለም ናቸው እነዚህ ስዎች እርቅ የማይውዱ የመለያየት ስራ በመስራት ሀገር ሁሉ ያውቃቸውል

  እርቁን ላለማየት ዳላስ ሚካኤል ከ ሊቀ ዘማዊያን ቸርነት ጋር ተሸሽገዋል

  ReplyDelete
  Replies
  1. እንደዚህ ያለውን የመናፍቃን ድህረ ገጽ አባ ሰላማ ብሎ መጥራት ሕዝብን ማታለል ከመሆኑም በላይ “መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ” እንደሚባለው አነጋግር መሆኑን አባ ሰላማዎች ልታውቁት ይገባል። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠላት ሆናቸው ማለት መስቀሉን፤ ታቦታቱን፤ አጽዋማቱን፤ ቅዱሳንንና ድንግል ማርያም በመንቀፍና በማዋረድ ሁልጊዜ የምትጽፉትን የስድብ ጋጋታ እያወቃችሁ እንደተቆርቋሪ ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶችና ስለ ስደተኛው ቅዱስ ሲኖድስ ብዙ ጊዜ የምትቀባጥሩት “ጅብ በማያቁት አገር”… እንደሚባለው ነው፡ ለመሆኑ በሰላሙ ዙሪያ ማን ታላቅ ሚና እንደተጫወተ ምን የምታውቁት ነገር አለ? ለአለፉት ሁለት ዓመታት በዲሲ፤ በኦክላንድ በሰያትልና በሌሎችም ቦታዎች ችግር የፈጠረ ማን ነው? የዳላሱ ዲያቆን ወይስ የሎስ አንጀለሱ መነኩሴ? አህያውን ፈርቶ ዱላውን እንደሚሉት ሁሉ እውነቱን መናገር ሲቻል በውሸትና በማስመሰል ሰውን ማወናበድ በአንገት ላይ እባብ እንደመጠምጠም ማለት ነው። አባ ወልደ ትንሳኤና አባ ገብረ ስላሴ አይደሉም እንዴ ይህንን ሁሉችግር የፈጠሩት? ዛሬ ለሰላሙ የታገሉትን እናመሰግናቸዋለን በማለት የመናፍቅነት ዝምድናህን ልታረጋግጥ የወደድከው ለምን ይሆን??? ስለ አቡነ መልከጼዴቅስ ትናትና ምን ስታወሩ ነበር…? ዛሬስ…? አባ ሰላማዎች ህሊናችሁ ምስክር ይሁንባችሁ።ዓለም የሚያውቀውን ታሪክና ሥራ በውሸት አረም ለማልበስ አትሞክሩ፡ የቤተ ክርስቲያን አዋልድ መጻሕፍትን በመናቅ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው በማለት አባ ሰላማዎች ሕዝብን ታወናብዳላችሁ። ሆንም ግን የመጽሀፍ ቅዱስ ምሁራን ብትሆኑ ኖሮ እንዲህ ያለ የውንብድና ሥራ ለመሥራት አታስቡም ነበር። ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት በሉ” ብሎ ያስተምራልና፡ ለማንኛውም እውነቱን እንድትናገሩ እግዚአብሔር የሚያስተውል ልቡና እንዲሰጣችሁ እለምንላችኋለሁ።

   Delete
 3. Andwalem yediyabilosen sira lemesrat yemifaten fetan ....yiker yibleh regmanam neger new.erk yemitela yeneger abat yehone yesw tinish yehone sew new.

  ReplyDelete
 4. እናንተ ክፉወች ባንኖር ምን ታወሩን ነበር ውሽታም

  ReplyDelete