Friday, September 26, 2014

ከብዙዎች ልብ የጠፋውን መስቀል ማን ይፈልገው?

Read in PDF

በየዓመቱ የደመራ በዓል ይከበራል፡፡ በዓሉ የሚከበረው በትውፊታዊው ትረካ መሠረት አይሁድ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ተአምራት እየሰራ ስላስቸገራቸው ጉድፍ መጣያ አድርገውት ለብዙ መቶ ዓመታት ከቆየና የተራራ ክምር ከሆነ በኋላ በንግስት እሌኒ አማካይነት ከተቀበረበት መውጣቱ ስለሚዘከርበት ነው፡፡ ይህ ታሪክ እውነተኛ መሆኑ ግን በጣም አጠራጣሪ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ በተለይም ይህ ታሪክ ሊዘከርበት በሚገባው በሐዋርያት ሥራ ውስጥ ይህ ጉዳይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ፈጽሞ አለመወሳቱ ሲሆን፣ ሐዋርያትም ዛሬ ብዙዎች እንደሚሉት የመስቀል ቅርጽን ይዘው ወይም እያማተቡ ምንም ሲያደርጉ አይታይም፡፡ ይህም የሚያሳየው የመስቀልን ቅርጽ መጠቀምም ሆነ ማማተብ በሐዋርያት ዘመን የሌለና በኋላ ዘመን ምናልባትም ከቈስጠንጢኖስ ዘመን ወዲህ የተጀመረ ልማድ እንደሆነ ነው፡፡


በሐዋርያት ስራ ውስጥ እንደምናነበው አይሁድን ያስቸገራቸው የኢየሱስ ስም ሃያልነትና ፈዋሽነት እንጂ ዕፀ መስቀሉ አልነበረም፡፡ ሐዋርያት መመኪያ የእግዚአብሔር ኃይል እያሉ የጠሩት መስቀል ጌታችንንና መድሃኒታችን ኢየሱስ የተቀበለውን መከራ እንጂ የተሰቀለበትን እጸ መስቀል አልነበረም፡፡ ታዲያ የኢየሱስን ስም ሃያልነትና የመከራውን ስፍራ እንዲቀማ የተደረገው የእፀ መስቀል መቀበርና በንግሥት እሌኒ ከተቀበረበት የመውጣት ታሪክ ደራሲ ማን ይሆን?

ይህን ጥያቄ መመለስ ቀላል አይደለም፡፡ የመስቀል በዓል ታሪክ በኢትዮጵያ ብቻ እንጂ በቀረው ዓለም የማይታወቅ “ክስተት” በመሆኑ ግን የበዓሉ ትረካ አገራዊ እንጂ መጽሐፍ ቅዱሳዊም ዓለማቀፋዊም አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ ታሪኩ ለዓመታት ሲነገርና ሲተረክ ስለኖረና የአደባባይ በዓል ስለሚከበርለት አሁን ደግሞ በዩኔስኮ የተመዘገበ ቅርስ ስለሆነ እውነት እንጂ ሐሠት አይመስልም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ሲፈተሽ ግን የክርስቶስን መከራ መስቀል የሸፈነ ገፋ ሲልም እርሱን ቀብሮ በመቃብሩ ላይ የራሱን ሐውልት ያቆመ አደገኛ ትምህርት ነው፡፡ አሁን ትልቁ ጥያቄ በክርስትና ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የሚያድነው መስቀል የክርስቶስ መከራ ነው ወይስ እርሱ የተሰቀለበት መስቀል ነው የሚለው ነው፡፡ ለብዙዎች ይህ ተደበላልቆባቸዋል፡፡ መስቀል ሲባል የሚያስቡት ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል ወይም የቅርጻ ቅርጽ ባለሞያ ከተለያዩ ቁሳቁሶች የሰራውን የመስቀል ምልክት ነው፡፡ እውነተኛውና የሚያድነው መስቀል ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለብዙዎች ቤዛ የተቀበላቸው ልዩ ልዩ መከራዎች ናቸው፡፡ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ እንደሚል መጽሐፍ ቅዱስ የዳነው በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ በተቀበለው መከራ እንጂ  በዕንጨቱ መስቀል በራሱ አይደለም፡፡ የመስቀል ምልክት ዋና ተግባርም የተሰቀለውን ክርስቶስን ማመላከት ነው፡፡ ዛሬ ግን እጸ መስቀሉ ይህን ተግባር በመወጣት ፋንታ የመከራ መስቀሉን ስፍራ ቀምቷል፡፡ መከራ መስቀሉ እንዲቀበርና ሰዎች አምነው እንዳይድኑበት አድርጓል፡፡ ታዲያ የምንድንበትን ይህን ክቡር መከራ መስቀሉን ከተቀበረበት ማን ያወጣው?

ይህን የምንድንበትን መስቀል ማለትም ክርስቶስ ስለእኛ መዳን የተቀበለውን መከራ ከተቀበረበት ለማውጣት በትውፊታዊው ትረካ መሰረት እንደእነእሌኒ የጉልበት ሥራ አይጠይቅም፡፡ ህልም ማለምም ሆነ ራእይ ማየት አይጠበቅም፡፡ ወንጌልን ብቻ የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ መስበክ ነው መፍትሄው፡፡ ወንጌል ሲሰበክ የተሰቀለው ክርስቶስ ሲሰበክ መከራ መስቀሉ ከተቀበረበት ወጣ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን እውነተኛውና የሚያድነው መስቀል ከተቀበረበት እንዳይወጣ መከራ መስቀሉ እንዲቀበር ያደረገውና እጸ መስቀሉን በስፍራው የተካው ሰይጣን ተግቶ ይሰራል፡፡ ልባቸው የጨለመ ሰዎችም ይህን ባለማስተዋላቸው የተሰቀለውን ክርስቶስን ሳይሆን እርሱ የተሰቀለበትን መስቀል ይሰብካሉ፤ ያመልካሉ፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ግን እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን ይላል እንጂ ክርስቶስ የተሰቀለበትን መስቀል እንሰብካለን አይልም፡፡ የተሰቀለውን ክርስቶስን ትተው እርሱ የተሰቀለበትን መስቀል የሚሰብኩ፣ የሚያመልኩ የሚዘምሩለትና የሚሰግዱለት ሰዎች እንዴት የከሰሩ ናቸው? እነርሱ በክርስትና ስም ሊጠሩ የማይገባ አማልከተ ብዙ አረማውያን ናቸው ቢባል ድፍረት አይሆንም፡፡

ከዕጸ መስቀሉ ጋር ተያይዞ መስቀሉን የጉድፍ መጣያ አደረጉት ተብለው ዘወትር የሚብጠለጠሉት አይሁድ ናቸው፡፡ አይሁድ እፀ መስቀሉን ሳይሆን የኢየሱስን ስም ለምን ጠራችሁብን በሚል ሐዋርያትን ሲያሳድዱ እንደነበር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ የታወቀ እውነት ነው፡፡ ስለእፀ መስቀሉ የሚነገረው የፈጠራው ታሪክ ግን ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሐቅ የሚያስተባብል ነው፡፡ እፀ መስቀሉ አሁን እየተሰጠው ያለውን አምልኮና ክብር ተቃውመው እንደተባለው ጌታ የተሰቀለበትን መስቀል የጉድፍ መጣያ ካደረጉት ሊመሰገኑ እንጂ ሊነቀፉ አይገባም፡፡ ምክንያቱም ለእፀ መስቀል እየተሰጠ ያለው አምልኮ አምልኮተ እግዚአብሔርን የሚቃረንና አምልኮ ባእድ ነውና፡፡

ሐዋርያት ያላስተማሩትንና ያላደረጉትን አስተምረዋል አድርገዋል እየተባለ በስማቸው ብዙ ይነገዳል፡፡ ከሚባለው ውስጥ አንዱና ዋናው ሐዋርያት አጋንንትን ያወጡት በመስቀል አማትበው ነው የሚል ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ትረካ በብዙ አዋልድ መጻህፍት ውስጥ ይገኛል፡፡ ይህ ግን ከጊዜ በኋላ የመጣ ትምህርት እንጂ በሐዋርያት ዘመን ያልነበረ ነው፡፡ እርሱ ጌታችን የሚያምኑትን “እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል” ብሎ እንደተናገረውና በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ እንዳለው ሐዋርያት አጋንንትን ያወጡት በኢየሱስ ስም ብቻ ነው እንጂ በመስቀል ምልክት በማማተብ አይደለም፡፡ የመስቀል ቅርጽ ለክርስትና እምነት ምልክት የተደረገው የተሰቀለውን ክርስቶስን ማእከል በማድረግና እርሱን ለማሰብ እንጂ ለሌላ ጉዳይ አልነበረም፡፡ አሁን ግን ሁሉ ነገር መልኩን ቀይሮ የመስቀል ምልክት ወደመመለክ ተሸጋገረ፡፡ አጋንንትን በስሙ ከማውጣት ይልቅ በብረት መስቀል በመደብደብ ለማውጣት ከሚሞከርበት ሥጋዊ አሰራር ላይ ከደረስን ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

የመስቀል በዓል የተሰቀለውን ክርስቶስን የማናስበብት በዓል ከሆነ ትልቅ ኪሳራ ነው፡፡ በመስቀሉ ላይ የተሰቀለውን ትቶ እርሱ ለተሰቀለበት ቁስ ክብር ዝማሬ አምልኮ የሚቀርብበት በዓል በመሆኑ እግዚአብሔር የሚያዝንበት ነው፡፡ ምክንያቱም እንዲህ እንድናደርግ ፈጽሞ አልታዘዝንም፤ እንዲያውም ተከልክለናል፡፡ የተቀረጹ ምስሎችን ለአንተ አታድርግ የሚለው ትእዛዝ ስሙ ጣኦት ለተባለ ነገር ብቻ የተሰጠ አድርገን ከወሰድን እንሳሳታለን፡፡ ስሙ ጣኦት ያልሆነና እየተዘመረለትና እየተሰገደለት ወደእርሱም እየተጸለየ የሚገኝ ማንኛውም ቁስም ሆነ ሕያው ነገር በዚህ ሁኔታ የሚመለክ ከሆነ ስሙ ሌላ ቢሆንም በገቢር ግን ጣኦት ሆኗል፡፡ ሙሴ በምድረ ባዳ የሰቀለው የናስ እባብ ጣኦት የሆነው ከመጀመሪያው ጣኦት ስለነበረ ሳይሆን የኋለኛው ዘመን ትውልድ እንደ ጣኦት እያጠነለት ስለተገኘ ነው፡፡ ንጉስ ህዝቅያስም ነሁሽታን ብሎ አስወገደው እንጂ ጣኦት ሆኖ እንዲቀጥል አልፈቀደም፡፡ እፀ መስቀልም ዛሬ ጣኦት ሆኖብናልና ጣኦታዊ ግብሩ መወገድ አለበት፡፡ ስፍራውን ለመከራ መስቀሉም መልቀቅ አለበት፡፡ ምልክት የተደረገበትን ዓላማ ሊፈጽምና የተሰቀለውን ክርስቶስን ሊያሳይና ሰዎችን ሁሉ ወደተሰቀለው ሊመራ ይገባል፡፡

እፀ መስቀሉን ስንል መከራ መስቀሉን ወደጎን ገፍተን ከመዳን መንገድ ወጥተናል፡፡ መስቀል ሲባል ቁሱን እንጂ መከራውን የሚያስብ አለ ለማለት አያስደፍርም፡፡ ነገሩ ሁሉ ከላይ የተመለከትነው ከሆነ ተቀብሮ መቅረት የነበረበትን እፀ መስቀል በፈጠራ ታሪክ ከተቀበረበት አውጥተን አምልኮተ ጣኦትን እያስፋፋን ነውና ነገሩ አንድ ካልተባለ የመስቀል ቅርጽ በክርስትና ምልክት መሆኑ ቀርቶ ጣኦት ሆኖ መቅረቱ ነው፡፡ ለዘላለም ሕያው ሆኖ ብዙዎች ይድኑበት ዘንድ ጌታ የተቀበለውን መከራ መስቀሉን ግን ቀብረናል፡፡ በዚህም የመዳንን መንገድ ስተናል፡፡ በማያድነው መንገድ ላይም ወደ ሲኦል እየነጎድን ነው፡፡ ስለዚህ እንመለስ፡፡ እፀ መስቀሉን አለአግባብ ለማንገስ የተቀበረውን መከራ መስቀሉን ከተቀበረበት እናውጣ፤ ሰዎች ሁሉ አምነው ይዳኑበት፤ ለነፍሳቸውም ዕረፍትን ያግኙበት፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይህ ነውና፡፡

ከአፈወርቅ

27 comments:

 1. Indeed! God bless you!

  This is the truth !Glory to be for Jesus!

  ReplyDelete
 2. I donot have word...Abaselamawoch..amilake abizito yibarikachihu...wushet silemedina zemn siyasikotir ewunet yemimesilachew bizuwoch nachew...yebizu sew ayin yemesikel kirtsu lay enji bemesikel yetesekelew kiristos lay alemehonu behiwotim beeminetim endayadig adirigotal...lezih new mesikel beejachew yeyazu wenjelegnoch..beangetachew yateleku negadewochina sekayoch yebezut....geta lehizibu masitewalin yabizalin! tnku abaselamawoch be blessed!!!

  ReplyDelete
 3. ወንድም በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የምንገኝ ሰዎች መሆናችንን ረሳኸው?አሁን በምትጠቀምበት ኮምፒተር" ቅድስት ሄለና" ብለህ እስቲ ፈልግ በለው፣ብዙ የጥንት ታሪክ ጸሐፊዎች በደንብ ይዘረዝርሩልሀል፤መስቀሉንና ሌሎችን ቅርሶች በማውጣቷ ቅድስናዋን "የሉተራንና የአንግሊካን አብያተ ክርስቲያናት" ግንቦት 21(እ.ኤ.አ) በዓሏን ያከብራሉ፤ከኦርቶዶክስ፣ከካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ ማለቴ ነው፤ስለዚህ አንተ ማነህ?እንዳነበብኩት እስላሞችና ወንጌሉ ያልገባቸው ብቻ ናቸው መስቀሉንና ኤሌኒን ንግሥት የማያከብሩት።ቅ ጳውሎስ እኮ "ብዙዎች የመስቀሉ ጠላቶች ሁነው ይመላለሳሉ ብሎናልና"ፍልጵ3፥18 የናንተ አለመቀበል አይገርመንም።

  ReplyDelete
  Replies
  1. ወንድማችን ኮምፒዩተሩ/ኢንተርኔቱ ስለ ንግሥት እሌኒና ተገኘ ስለተባለው የመስቀል ጉማድ ሲያስቀምጥ ያቀረበው ምንጭ በአፈታሪክ/legend/traditionally..ብሎ ነው እንጂ ከመጽሐፍ ቅዱስ አልጠቀሰም። ስለዚህ ዋቢ መጽሐፍ የሚሆነን የአባ እንትና ወይም ቅድስት እንቶኒ ታሪክ ኢንተርኔቱ ላይ ስለተፃፈ ሳይሆን የክርስትና ሁሉ መሠረት ስለሆነው ጌታ ኢየሱስ ታሪክ የተጻፈበት ቅዱስ መፅሐፍ ብቻ መሆን አለበት።

   Delete
 4. ወይስ እንግሊዘኛ ማንበብ አትችልም?ካልቻልክ ሌሎችን ከኮምፒተሩ ፈልጉልኝ ብለህ ይተርጉሙልህ፤ይህ ነው የሚሻልህ አለማወቅ ኃጢአት አይደለም።ሳያውቁ አውቃለሁ ብሎ እነደዚህ የወረደ ጽሑፍ መጻፍ ነው ነውር

  ReplyDelete
 5. while the dogs bark, the camels go up. it is same old, boring 'nufake' from the protestant menafkan ( yemeskelu telatoch woyem terefe-ayhud). who cares for your devil-led 'netela zema' which you release every year for NOTHING?????orthodox WILL continue to celebrate 'the finding of the TRUE cross' which was buried by your brothers( the enemies of JESUS )
  it is laughable that according to protestants, every truth is not considered as truth unless it is written in bible, but when needed, they twist every words of the bible to their interest. finally we pray for you to join us to celebrate 'meskel' like the wise Catholics are doing recently. YOUR PROTEST/NUFAKE WILL BRING NOTHING

  ReplyDelete
 6. አፈ ወርቅ ሳትሆን አፈ ዲያብሎስ ደንቆሮ ነህ።

  ReplyDelete
 7. ቃለ ሂወት ያሰማልን ወንድማችን።ለእፁዋት መስገድ በእግሃብሄርም ሆነ በሰዉ ዘንድም አምልኮተ ጣኦት ነዉ።

  ReplyDelete
 8. may GOD bless you!!!!

  ReplyDelete
 9. ደራሲው ዘርዐ ያዕቆብ እንዳይሆን? ከእሱ እራስ ስለማትወርድ ማለቴ ነው፡፡ ዲያብሎስ ለምን ይሆን መስቀልን የሚፈራው፣ ገና ምልክቱን ሲያይ ይረበሻል፡፡ ነገሩ ወዲህ ነው፡፡ ጌታቸን እፀ መስቀሉን ዙፋን አድርጎ ደሙን አፈሰሰ ሥጋውን ቆረሰ ለእኛም ቤዛ ሆኖ ከዲያብሎስ ቁራኝነት አዳነን፤ ከሞት ወደህይወት መለሰን፡፡ ለዚህም ነው ዲያብሎስ መስቀል ሲያይ የሚጮኸው ድል የተረታበት ባዶ የቀረበት ስለኾነ፡፡ መስቀል በአደባባይ ወጥቶ በዓሉ ሲከበር አጋንንት ቢንጫጩ አይግረማችሁ፣ መስቀሉን ሲያዩ የሚታወሳቸው ድል አድራጊው ጌታ የድንግል ማርያም ልጅ የይሁዳ አንበሳ ኢየሱስ ክርስቶስ እኮ ነው፡፡
  ወሶበ ርእዮሙ እግዚእ ኢየሱስ ለእሙ ወለረድኡ ዘያፈቅር ይቀውሙ፤ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደውን ደቀ መዝሙርና እመቤታችንን ከእግረ መስቀል ቁመው ባያቸው ጊዜ፣ ወይቤላ ለእሙ ኦ ብእሲቶ ነዋ ወልድኪ፤ አንቺ ሆይ ልጅሽ ይርዳሽ ያጽናናሽ አላት፡፡ ውሉድኪ ሲል ነው በዮሐንስ እኛን ለርስዋ መስጠቱ ነውና፡፡ ወይቤሎ ለውእቱኒ ረድ ነያ እምከ፣ ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ታጽናህ አለው እምክሙ ሲል ነው፡፡ በዮሐንስ እርስዋን ለኛ መስጠቱ ነውና፡፡(ዮሐ. 19: 26-27)
  ክርስቶስ ተሰቅሎ ዓለምን ያዳነበት፣ ደሙ የነጠበበት እውነተኛው መስቀል ለዓለም ብርሃኑን ያበራበትን የምናከብርበት ይህ ቀን ነውና፡፡ ምክንያቱም፡-
  • መስቀል የፍቅር ዙፋን ነውና፤ ቅዱስ ዮሐንስ ጌታ በመስቀል ላይ ሳለ እስከመጨረሻው ሳይለይ የፍቅሩን መጠን ተረድተዋል፡፡ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ የጌታን ሕማሙን በዚያች ሌሊት የአዳሩንና የውሎውን ለሰው ልጆች ፍቅር ሲል በሰው ልጆች እጅ የተቀበለውን ጽኑ መከራውን አይተዋልና፤ በመልእክቱም ”ፍቅርም እንደዚህ ነው፣ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደወደደን ስለ ኀጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደላከ እንጂ እኛ እግዝአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም” (1ዮሐ. 4: 10) ያለው፡፡ የሰቀሉትን እንኳ ወደዳቸው፣ ይቅርም አላቸው፡፡ በመስቀሉ ዙፋን በፍቅሩም ድነዋልና ”አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ” እንዲል፡፡
  • መስቀል የጥበብ ቤት ነውና፤ ጠቢቡ ሰሎሞን ” ጥበብ ቤትዋን ሠራች ... ፍሪዳዋን አረደች ... ማድጋዋን አዘጋጀች ... ሁሉን ጠራች ... ኑ እንጀራዬን ብሉ ... አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፣ በማስተዋል መንገድ ሂዱ ... ”(ምሳሌ 9፥ 1-10) ሲል፤ በቅዳሴ መጽሐፍ ላይ ጥበብ መድኀኒታችን ነው በማለት የሚሥጢሩን ባለቤትን ያመሠጥራል፤ በመስቀል ላይ ጥበብ የተባለ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወት እንጀራ ሆኖ ዓለም ሁሉ ተመግቦት ድኖአልና፡፡ ለእኛ በመስቀል ጥበብ ቤት ላይ የተሰቀለው ጥበብ መድኀኔዓለም በዛሬው በምናከብረው የጥበብ ምሥጢር መገኛ በሆነው የመስቀል በዓል ራስ እርሱ ክርስቶስ ነው፡፡ በዚህም እርሱን የዓለምን መድኅን እንሰብክበታለንና፡፡ ”አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ፣ የግሪክ ሰዎች ጥበብን ይሻሉ፣ እኛ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን” (1ቆሮ. 1፥22-23) እንዲል፡፡
  • መስቀል የክርስቲያኖች ሁሉ አርማ ነውና፤ በምድራውያን ልማድ የሀገር ነጻነት በሰንደቅ ዓላማ አርማነት መውለብለብ እንዲታወቅ ሁሉ፣ ዛሬ የሰማያውያን ተስፋና የሕይወት አርማ በዓለም ላሉ ክርስቲያኖች ሁሉ ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ መውጣት በክርስቶስ የታወጀበት ሰንደቅ ዓላማ መስቀል ነው፡፡ በሀገራችን ከአደይ አበባ ውበት ጋር አንድ ሆኖ የሚውለበለብበት መስከረም 16ና 17 ልዩ ክብረ በዓሉ ነው፡፡ ልዩ የሚያደርገው ከአርማ ጋር የእግዚአብሔር ኀይል መሆኑ ነው፡፡ ቅዱስ መስቀል ምንኛ ድንቅ ነው? ዕፅነት/መስቀሉ የተቀረጸበት እንጨት/ ከመለኮት ኀይል ጋር አንድነት፣ ድንቅ ተዋሕዶ፣ አጋንንት የሚርዱለት የክርስቲያኖች ቤዛ ልዩ ምልክት፣ ለመረጣቸው ብቻ ኀይልን ያደርጉበት ዘንድ የታደሉት ግርማ ሞገስ ቅዱስ መስቀል ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ”የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ነው፣ ለእኛ ለምንድነው ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው (1ቆሮ 1፥18) እንዲል፡፡
  የመስቀል ፍቅር ሰው፣ ልዩ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ ”ወሶበ ርእዮሙ እግዚእ ኢየሱስ ለእሙ ወለረድኡ ዘያፈቅር ይቀውሙ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደውን ደቀ መዝሙርና እመቤታችንን ከእግረ መስቀል ቁመው ባያቸው ጊዜ ሲል፣ ድንግል ልብዋ በሀዘን ጦር ተወግቶ የልጅዋን መከራ መቻል ጭንቅ በሆነባት ጊዜ ልጅዋ መሪር ሃዘንዋን ተመለከተ፤ እንዲሁም ከአጠገቧ ካሉት በእንባ ከሚራጩት የኢየሩሳሌም ሴቶች ጋር ከወንድ ወገን የሚያጽናናት አንድ ሰው ቅዱስ ዮሐንስን አየው፡፡ ወይቤላ ለእሙ ኦ ብእሲቶ ነዋ ወልድኪ፤ አንች ሆይ ልጅሽ ይርዳሽ ያጽናናሽ አላት፡፡ ውሉድኪ ሲል ነው በዮሐንስ እኛን ለእርስዋ መስጠቱ ነውና፡፡ ወይቤሎ ለውእቱኒ ረድ ነያ እምከ፣ ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ታጽናህ አለው እምክሙ ሲል ነው፡፡ በዮሐንስ እርስዋን ለእኛ መስጠቱ ነውና”፡፡ (ዮሐ.19፥26-27)ብሎዋል፡፡ እነሆ ተመልከቱ፣ ለቅዱስ ዮሐንስ የባሕሪያችን መመኪያ የሆነችውን የተወደደች ድንግል እመቤት እናት ትሆነው ዘንድ ከአምላኩ ፈጽሞ ተሰጠችው፡፡ ድንግልን ከመስቀሉ ፍቅር ለይቶ ማየት ከቶ አይቻልም፡፡
  መስቀል ፍጹም ፍቅር፣ ርኅራሄ፣ የዋህነት እንደሆነ ሁሉ፣ ድንግልም እንዲሁ ፍጹም ፍቅርን የተሞላች የፍጡር ሁሉ ፍቅር ቢደመር የእርስዋን ፍቅር ይደርስ ዘንድ ሊታሰብ አይችልም፤ ርኅራሄዋ እንኳን ለሰው ልጅ ለፍጡር ሁሉ የምታዝን አዛኝት ናት እንጂ፤ በየዋህነትዋ የዋሂት ርግብ የተባለች ፍጹም ናት እንጂ፡፡ድንግል በዚህ ዓለም ሳለች ልጅዋ እንደተሰቀለ ሆኖ በኅሊናዋ ተስሎ፣ ልብዋ በሕማሙ ጦር ተወግቶ፣ ሃዘንዋ ጸንቶ፣ በሰቆቃ ተውጣ፣ እጅዋን ወደ ላይ ዘርግታ አንድም ስለልጅዋ ኀዘን እንባዋን ስታዘራ በሌላም ልጅዋ ይምረን ዘንድ ስለእኛ ስለ ሰው ልጆች ምልጃ ታደርግ ዘንድ ከቀራንዮ ከስቅለቱ ቦታ እንዲሁም ከመቃብሩ ጎልጎታ አንድም ቀን ተለይታ አታውቅም ነበር፡፡ ሕማሙን እንደ እርስዋ ማን ተረዳ? ድንግልን የመስቀሉ ፍቅር እንዲገባን አማልጂን ብለን እንማጸናት፣ በአምስቱ ኀዘናትሽ ቃል ኪዳን አስቢን እንላት ዘንድ የዚህ ዓለም ፈተና ግድ ይለናልና፡፡ ልጅዋን ወዳጅዋን፣ እስዋንም ደስ እናሰኝ ዘንድ ፍቅርዋን፣ ርኅራሄዋን፣ የዋህነትዋን እንምሰል፡፡ ወገኖቼ ቂም በቀል፣ ክፋት፣ተንኮል፣ ምቀኝነት፣ ዘረኝነት፣ወዘተ እንተው፣ ለዚህ ዓለምም ለወዲያኛውም አይጠቅሙምና፡፡

  ReplyDelete
 10. መጀመሪያ ወንድም አፈወርቅ “አፉ” እንድትል ይሄን ልበል….1
  1-የመስቀል መገኘት በዐል ዓለምአቀፋዊ ብሂል ሳይሆን የመንደር ወሬ ነው ማለትህ ዓለምን ካለማወቅ ወይም አንተ የምተወቀው ዓለም ፕሮቴስታንቶች ብቻ የሚኖሩበት ቢሆን እንጅ ብታውቅ --ጥቂት እንግሊዝኛ ቃላትን ወደ ጎግል ጨምረህ ብትመረምር የመስቀሉ በንግሥት እሌኒ መገኘት በእርግጥም በዓለም የክርስትና ታሪክ የተመዘገበ ሀቅ መሆኑን ትረዳ ነበር፡፡ከበረታህ http://www.catholiceducation.org/articles/religion/re0816.html የሚለውን ሊንክ ወይም ደግሞ http://en.wikipedia.org/wiki/True_Cross የሚለውን ተመልከት በፈረንጆች አቆጣጠር እለቱ በየአመቱ መስከረም 14 ቀን በካቶሊኩም፣በኦርቶዶክሱም፣በአንግሊካኑም ሳይቀር በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ እንደሚውል እና በእለቱም ልክ እኛ ቅ/ያሬድን አብነት አድርገን በመስቀሉ ወበቃሉ ገብረ ሰላመ ለኩሉ እንደምንለው እነሱም በፊናቸው "We adore Thee, O Christ, and we praise Thee, because by Thy Holy Cross Thou hast redeemed the world." እያሉ እንደሚያከብሩት ትገነዘባለህ፡፡እና እባክህ አንብብ፡፡በል አሁን የቤት ስራ ልስጥህ…St. Helena and True Cross, Feast of finding of True Cross, Veneration of True Cross …የሚሉ ቃላትን ወደ ጎግል ቋት ዱለህ ከዘመናዊው ፕሮቴስታንት ውጭ ያለው የዓለም ክርስቲያን ስለመስቀልና ስለክብሩ ምን እንደሚል አጣርተህ ትመጣለህ፡፡
  2-ለነገሩ ዓለም ተቀበለው አልተቀበለው እኛ ጉዳያችን አይደለም፡፡ለሃይማኖታችን ትክክለኛነት የዓለም ምስክርነት አያስፈልገንም፡፡እንደሱ ከተባለማ-ዓለማቀፋዊነት መለኪያ የሃይማኖት ሚዛን ከሆነማ በዘመነ-ኦሪት አባቶቻችን አክሱማውያን ከቤተ-አይሑድ ተባብረው “አንድ እግዚአብሔር አለ” ብለው ሲያመልኩ በአሕዛባዊ መንገድ ይራመድ ከነበረው ዓለም ባለመስማማታቸው ትክክል አልነበሩም ልንል ነው፡፡በነገራችን ላይ የእናንተ ዓለም ተብየ ምዕራባውያን መሆናቸው ነው፡፡እነሱ ደግሞ ክርስትናን በፕሮቴስታንት ፈረስነት ምን ያህል ወደ ክህደትና የሥጋ መንገድ ይዘውት እንደነጎዱ ዛሬ በምዕራቡ ያለው ልቅ የኑሮ ዘይቤ ምስክር ነው፡፡
  3-እኛ መስከረም 17ትን የምናከብረው መስቀሉ ወደ ኢ/ያ የገባበት እለት ብለን በመሆኑና ሌላው ዓለም ደግሞ በፊናው ከእኛ በተለየ ቀን ማክበሩ በአደባባይ የሚነገር ሀቅ ስለሆነ ሀገርህን በማታውቀው የፈረንጅ ዐይን ለመመልከት ባትደክም ጥሩ ነው፡፡
  4- “መጽሐፍቅዱስ ላይ የሌለ ሁሉ ውሸት ነው” አካሄድህ ደግሞ ያስቃል፡፡መስቀሉ የወጣው በ4ኛው ክፍለ-ዘመን ነው፡፡በዚህ ጊዜ ደግሞ መጽሐፍቅዱስ ተጽፎ አልቋል፡፡ስለዚህ ታሪኩ በቤ/ክ ታሪክና በትውፊት ስር ሆኖ ይዘከራል፡፡በሞቴ ግን የእኛንስ መስቀል ሐዋርያት አልተጠቀሙበትም አልከን ለመሆኑ የእናንተን ኦርጋንና ጊታር፣ስፒከር፣ሲዲና ካሴት፣የቲቪ ቻናል፣የትንቢት ኮንፈረንስ፣ወዘተ…ባህሎች ሐዋርያት ተጠቀሙበት ሲባል አልሰማንም እኮ!!እንደ ሐዋርያቱ እንደ ጴጥሮስና ዮሐንስ መጎናጸፊያ በመልበስ፣በምኩራብ በማስተማር፣የምትበሉትንና የምትጠጡትን ቀላቅላችሁ በማኅበር በመኖር ከሆነ ይሄን የምትሉን ደስ ይላል፡፡ግን አይመስለኝም፡፡የሐዋርያት ግብር ከእናንተ ቤት ይልቅ እኛ ቤት ይታያል፡፡
  5-እንግዲህ እኛ አንድ ትውፊት (1) ከመጽሐፍቅዱስ ወይም ከሌላ ትውፊት ጋራ እስካልተጋጨ (2) ለመንፈሳዊ ሕይወት መቃናት እስከረዳ (4) አባቶች በቀኖና ደንግገው እስካስረከቡን ወይም ይሄ አይሆንም ብለው እስካልከለከሉን ድረስ የግድ ሌላው ዓለም አልተቀበለውም፤በመጽሐፍ ቅዱስ አልተጻፈም ብለን አናጣጥለውም፡፡ስለመስቀል ክብር፣በዓልና የፀጋ ስግደት ያለን አመለካከትም በዚህ መነጽር ሊታይ ይችላል፡፡
  6-የእናንተ የፕሮቴስታንቶች ችግር ነባር የኦርቶዶክስና የካቶሊክ አብያተ-ክርስቲያናት የዐላውያን ነገሥታትንና የሙስሊም ካሊፌቶችን ተዋግተው፣መሀይሙን ሕዝብ ፊደል አስቆጥረው፣ክርስትናውን በትውፊትና በስእል ጭምር ታግዘው ለማያነቡና ለማይጽፉ ሰዎች ጭምር እንዲገባ ካደረጉት በኋላ በዘመነ-ወረቀት እና ዲሞክራሲ መጥታችሁ ለ2ሺህ አመታት የእ/ብሔር ድንቅ ስራዎች የተገለጹበትን የክርስትና ታሪክ ደምስሳችሁ ታሪክን እንደ አዲስ ለመጻፍ፣ምጥ ለእናት ማስተማር መሞከራችሁ ነው፡፡የሚያሳዝነው በዚህ የእናንተ የሃይማኖት ፍልስፍና ክርስትና እንደ እብድ ጨርቅ በየእለቱ ስትተረተርና ለዓለማዊነት መሥዋእት ስትሆን እንጅ አንድም ሞራላዊ ተምሳሌትነት ያለው ሀገር ስትገነባ አይተን አናውቅም፡፡

  ReplyDelete
 11. ንግባእኬ ኀበ-ነገረ-መስቀሉ…….2
  7-በዓልን በድርጊት፣በቁስ፣በአምላክ ወይም በፍጡር ስም አንዳንዴም በቦታ ሰይሞ ማክበር በሁሉም ቦታ በሁሉም ጊዜ ያለ ባህል ነው--በሃይማኖታዊውም በሥጋዊውም መንገድ፡፡ታዲያ ምንጊዜም የበዓሉ ማጠንጠኛ በዓሉ የሚከበርበት መነሻ ምክንያት እንጅ ስያሜው ብቻ አይደለም፡፡ለምሳሌ የባንዲራ ቀን ሲባል የምንነጋገረው ባንዲራው ስለወከለው ዓላማ እንጅ ስለተሰራበት ጨርቅ ብቻ አይደለም፡፡የአድዋን ቀን ስናከብርም ስለተገኘው ድልና ስለድሉ ትርጉም እንጅ ስለ ግዑዙ ተራራ ብቻ አይደለም፡፡የነጭ ሪባን ቀን ብለን የምናከብረው ስለቁራጭ ጨርቅ ለማውራት ብቻ ሳይሆን ይበልጥ ስለ ሴቶች ጥቃት በስፋት ለመነጋገር ነው፡፡የቂጣ በዐል ተብሎ በኦሪት ዘፀኣት 12 ቁ 19 ጀምሮ ስለተጻፈው በዓል ስንነጋርም ከኋላው ያለውን የእስራኤል ከግብፅ ባርነት የመውጣት ዐላማ እናስባለን እንጅ ስለሚበላው ቂጣ ብቻ አይደለም፡፡በሌላ አነጋገር የጨርቅ፣የተራራ፣የቂጣ በዐል እያልን ዐላማውን የወከሉትን መገለጫዎች አናጣጥልም፡፡
  8-መስቀልንም ስናከብር በመስቀሉ በዐል ውስጥ ጠላት ዲያብሎስ በጌታ ሞት የተሸነፈበትን ለመዘከር እንጅ መስቀሉ ከእፀዋት መገኘቱን ዘንግተነው አይደለም፡፡እኛም እኮ ስናከብረው ከምን እንደተሰራ አውቀን “እፀ-መስቀል” እያልን ነው፡፡ነገር ግን ባንዲራን ጨርቅ ብሎ ማጣጣል ከጀርባው የወከለውን ሉዐላዊ ሀገር የማንኳሰስ ፀያፍ ድርጊት እንደሆነ ሁሉ መስቀልንም “እንጨት” እያሉ መጽረፍ የዛኑ ያህል ነውር ነው እንላለን፡፡ጥቂት ቲፎዞዎችን ለማስጨብጨብ ካልሆነ በቀር እንዲህ ያለው አነጋገር በእኛ ኦርቶዶክሳውያን ቀርቶ በጨዋ ፕሮቴስታንቶች ዘንድም ትዝብት ላይ የሚጥል ነው--ቢያንስ እነሱም በየቸርቾቻቸው በር ወይም አናት ላይ መስቀሉን ለምልክትነት ይጠቀሙበታልና፡፡
  9-በመሰረቱ መስቀል ትንቢት የተነገረለት፣ዓለም ለ2 ተከፍሎ የተዋጋበት--ክርስትናና እስልምና፣የክርስትና ምልክትና ዐርማ ነው፡፡እድሜ ለዐለማዊው ፕሮቴስታንት ይሁንና ወደ ኢ-አማኒነት ጎረፉ እንጅ ቀደም ሲል በአውሮፓ ክርስቲያኖችም መስቀል ትልቅ ትርጉም እንደነበረው በብዙ የአውሮፓ ሀገሮች ባንዲራ ላይ ያለውን የመስቀል ምልክት ማየት በቂ ነው፡፡እስኪ በህሊናችሁ የስካንዲኒቪያን ሀገሮችን ባንዲራ አስቡ!!ለትንቢቱ ደግሞ መዝሙር 43ን እና 59ን አንብቡ….ብከ ንወግኦሙ ለኩሎሙ ጸርነ…ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ….ሲል ታገኙታላችሁ፡፡
  10-መስቀልን ማክበርም ሆነ ለመስቀል መስገድ ከፕሮቴስታንት ውጭ ባለው የምስራቅም ሆነ የምእራብ ክርስትና የተለመደ ነው፡፡እኛ …ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ… ስንል ነሱ ደግሞ በዚሁ ቃል We bow down for thee Holy Cross O Lord ይላሉ፡፡መነሻችንም…ወንሰግድ ውስተ መካን ኀበ ቆመ እግረ-እግዚእነ…የሚለው የመዝሙር 131 ኃይለ ቃል ነው፡፡
  11-እዚህ ላይ አንድ ነገር ይሰመርበት፡፡ለመስቀል የምንሰግደው ክቡር ደሙ የተንጠባጠበበት መሆኑን በማሰብ የጸጋ ስግደት እንጅ አምልኮ አይደለም፡፡ዘዳግም 4 የሚያወራው ስለ አምልኮ ስግደት እንጅ ስለጸጋ ስግደት አይደለም፡፡ይኸውም…ኢትስግድ ሎሙ ወኢታምልኮሙ…አትስገድላቸው፤አታምልካቸውም…በሚለው ትኩረቱን አምልኮ ላይ ያደረገ የአጻጻፍ ዘይቤ መረዳት ይችላል፡፡ስለዚህ አምልኮ ያለበት ስግደት ነው የተከለከለው፡፡መስቀልን ደግሞ እናከብረዋለን እንጅ አናመልከውም፡፡
  12-በዚሁ አስተሳሰብ ውስጥ ሆነን በእለተ-መስቀል ኦርቶዶክሳውያን የምንዘምረውን ምልጣንና እስመለዓለም እንየው--እንምራው፡፡(1) ምልጣኑ መሪጌታው መስቀል አደባባይ ላይ የመራው እንዲህ ይላል…ይቤሎሙ ኢየሱስ ለአይሑድ እመኑ ብየ፣ወእመኑ በአቡየ፣ዮምሰ ለእሊኣየ፣አበርህ በመስቀልየ…ትርጉም..ኢየሱስ አይሑድን አላቸው፡ በእኔ እመኑ፣በኣባቴም እመኑ፣ዛሬ እኔ በመስቀል ላይ አበራለሁ፡፡” (2) እስመለዓለሙንም እንቃኘው ይሄው…ብከ ንወግኦሙ ለኩሎሙ ጸርነ፣ይቤ ዳዊት በመንፈሰ-ትንቢት በእንተ-ዝንቱ እፀ-መስቀል ዘተሰቅለ ዲቤሁ ቃለ-አብ፣ወበስምከ ነኀስሮሙ ለእለ ቆሙ ላእሌነ፤ወካእበ ይቤ ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ከመ ያምስጡ እምገጸ-ቅስት ወይድኃኑ ፍቁራኒከ፤ወንህነኒ ንትፈሳህ ዮም ወንግበር በዓለ በዛቲ እለት በዓለ-እግዚእነ….ትርጉም…ዳዊት በትንቢት መንፈስ ሆኖ፡ ባንተ ጠላቶቻችንን እንወጋለን፣በስምህም እላያችን ላይ የቆሙትን እናስራቸዋለን (መዝ 43) ያለው ስለዚህ እፀ-መስቀል ነው፤ዳግመኛም ከቀስት ፊት ይድኑ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሀቸው(መዝ 59) ይላል፤እኛም በዚህ እለት እንደሰት የጌታ በዐል ነውና(መዝ 117)፡፡” እንግዲህ እንዲህ እያልን የምንዘምር ሰዎችን ጣኦት አምላኪና የተሰቀለውን ከተሰቀለበት የማንለይ አድርጎ ለማቅረብ ድፍረቱ ላላቸው ወንድሞቻችን አምላከ ቅ/ያሬድ ማስተዋሉን ይስጣቸው ከማለት በቀር ምን እንላለን!!
  የራሳችን ኣላዋቂዎች ሲያጣጥሉት እውቅና ለሰጠውና ምእራባውያን የደነገጉትን ብቻ ሳይሆን ከደሃ አፍሪካውያንም ዓለምአቀፋዊ ቁሳዊ ያልሆነ (መንፈሳዊ) ቅርስ እንደሚገኝ ለመሰከረው ዩኔስኮ ክንብንባችን አውርደን በኦርቶዶክሳዊ ትህትና እጅ እንነሳለን፡፡በኢኦተቤክ ኮርተናል!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. Hiruy please continue your contribution. I really thank you, I usually visit this blog to read your response and to check if there is something bad around the church coz this blog will post immediately anything bad that happened on EOTC and true EOTC chirstians.

   Delete
  2. Memhir Hiruy - thank you and God bless.

   Delete
 12. "Afe-kus"...You think every thing is wrong unless you proved it. If you wanna see,go and visit the monasterys how our Fathers heal the bad spirits like yours!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete

 13. ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንደሚያስተምሩን ጌታችን የተሰቀለበት መስቀል የተዘጋጀው ከሰባት ዓይነት ዕፅዋት ነው፡፡
  1. ሳኦል ከገነት ያስመጣው ዕፅ
  2. ሰሎሞን ቤተ መቅደስን በሠራበት ወቅት ሠረገላ አድርጎ የተጠቀመበት ዕፅ
  3. ከመቃብረ አዳም የበቀለ ፅፀ ሕይወት
  4. ሎጥ በእንባው ያለመለመው ፅፀ ከርካዕ
  5. ታቦተ ጽዮንን ይሸከሙበት የነበረው ሠረገላ
  6. ጌታችን በቢታንያ የረገማት ዕፀ በለስ
  7. ዘኬዎስ ጌታችንን ለማየት የወጣበት ዕፀ ሠግለ /ሾላ/ ከእነዚህ ሰባት ዕፅዋት በተዘጋጀ መስቀል ነው ጌታችን የተሰቀለው /መጽሐፈ ኪዳን ትርጓሜ ተመልከት/


  ጌታችን ከእነዚህ ዕፅዋት የተዘጋጀ መስቀሉን ተሸክሞ በቀራንዮ አደባባይ በመስቀሉ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍሶ ቀድሶታል በዚህ የተነሣ መስቀል ነዋይ ቅዱስ ነው መስቀል በሐዲስ ኪዳን ሁለት መሠረታዊ ትርጉሞች አሉት፡፡
  1. ጌታችን የተሰቀለበት ከሰባት ዕፅዋት የተዘጋጀውን መስቀለኛ እንጨት /ቅዱስ መስቀል/
  2. ጌታችን ዓለምን ለማዳን የተቀበለው መከራ መስቀል ይባላል መስቀል ስንል እነዚህን ከላይ ያነሳናቸውን ሁለት አበይት ትርጉሞች ማስታወስ የግድ ይላል፡፡

  ስለ መስቀል የክርስቶስ ትምህርት
  ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ደጋግሞ ነገረ መስቀልን አስተምሯል፡፡ “ዘኢጻረ መስቀለ ሞትየ ኢይክል ይጸመደኒ” መስቀሉን የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ የእኔ ሊሆን አይገባውም” ማቴ.10፡38፣ 16፡24፣ ማር.8፡34፣ ሉቃ.9፡23፣ 14፡27፡፡


  ጌታችን ይህንን ያስተማረው ከመሰቀሉ በፊት መሆኑ ግልፅ ነው በቃል ካስተማረው በኋላ በተግባር ፈጸመው መስቀሉን እንድንሸከም መከራውን እንድንቀበል አስቀድሞ አስጠነቀቀን መስቀሉ የሌለው የክርስቶስ ሊሆን እንደማይችል አስረግጦ ነገረን፡፡


  ከዚህ የተነሣ ክርስቶስ ራሷ የሆነላት ሐዋርየዊት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መስቀሉን በየዓመቱ በየወሩ ታከብረዋለች ትሸከመዋለች፡፡ በመስቀሉ የሚገኘውን መከራ ትቀበላለች በመስቀሉ የሚገኘውን በረከት ታድላለች ክርስቶስን በግብር ትመሰለዋለች በእግር ትከተለዋለች የእርሱ መሆኗ መልክት መስቀሉ ነው፡፡


  “በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ” ማቴ.16፡24፡፡ “የሰው ልጅ /ክርስቶስ/ ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል ሊዘባበቱበትም ሊገርፉትም ሊሰቅሉትም ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል” ማቴ.20፡18፡፡ መስቀል ስንል ይህን ሁሉ መከራ ያጠቃልላል ይህ ሁሉ መከራ የተፈጸመበት ነዋይ ቅዱስም መስቀል ይባላል፡፡


  “ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንዲሆን ታውቃላችሁ የሰው ልጅ ሊሰቀል አልፎ ይሰጣል” ማቴ.26፡1፡፡ ይህ እስከ አሁን ጌታችን በቃል ያስተማረውን ተመልክተናል ተግባሩ እነሆ፡-“የአይሁድ ንጉሥ ሰላም ላንተ ይሁን እያሉ ዘበቱበት ተፉበትም መቃውን ይዘው ራሱን መቱት ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት ልብሱንም አለበሱት ሊሰቅሉት ወሰዱት ሲወስዲትም ስምዖን የተባለ የቀሬና /ሊቢያ/ ሰው አገኙ እርሱንም መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት ትርጓሜው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሆን ጎልጎታ ወደሚባለው ሥፍራ በደረሱ ጊዜ ሰቀሉት” ማቴ.27፡29፡፡ መስቀል ማለት ይህን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡


  ሰሎሞን የወይን ሐረግ መድኀኒቴ ሆነ ከሀሲሦን ይቆረጣል በጎልጎታ ይተከላል” ያለው ተፈጸመ መድኃኒት መስቀል መድኃኒት ክርስቶስን ተሸክሞ ታየ መድኃኒት ክርስቶስ የሚሰቀልበትን መስቀል ተሸክሞ ደፋ ቀና ብሎ መከራን ሲቀበል ተመለከትን መስቀሉን እርሱ ብቻ አይደለም ተከትዮቹ እነስምዖን ቀሬናዊም ተሸከሙት የድካሙ ተካፋይ ሆኑ፡፡ ልዩነቱ እነ ስምዖን ተገደው እኛ ግን ወደን ነው፡፡ እነ ስምዖን በአጋጣሚ እኛ ክርስቲያኖች ግን በዓላማ ክርስቶስን እንመስለው ዘንድ መስቀሉን የማይሸከም ለእኔ ሊሆን አይገባውም ብሎ አስተምሮናልና በተግባርም ፈጽሞ አሳይቶናልና፡፡
  ከሰቀሉትም በኋላ እንዲህ ዘበቱበት “የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ አሁን ከመስቀል ይውረድ እኛም እናምንበታለን” ማቴ.27፡40-42


  “ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት መስቀሉንም ተሸክሞ በእብራይስጥ ጎልጎታ ወደተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ በዚያም ሰቀሉት” ዮሐ.19፡17፡፡ ራስ ቅል ስፍራ ማለት የአዳም የራስ ቅል የተቀበረበት ቦታ ነው መስቀሉ የተተከለበት ቦታም ይህ ነበር ለአዳምና ለልጅ ልጆቹ የተፈጸመ ካሳ ነውና፡፡


  “እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር” እግዚአብሔር ከዓለም በፊት ንጉሥ ነው በምድር መካከል መድኀኒትን አደረገ” መዝ.73፡13፡፡ ይህ መድኃኒት ዓለም የዳነበት ቅዱስ መስቀሉ አይደለምን?


  “ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል” የአበው ተስፋ በድንግል ማርያም ተፈጸመ በቀራንዮም መድኃኒት መስቀል ተተከለ” እንዲል ስለሆነም መስቀልን ስናስብ ለእኛ የተከፈለውን የአምላካችንን የቤዛነት ሥራ የተቀበለውን መከራ የተገረፈውን ግርፋት የታሰረበት ሀብል የተሰቀለበትን መስቀል የጠጣውን መራራ ሐሞት እደቹ እና እግሮቹ የተቸነከሩበትን ቅንዋት /ችንካሮች/ ጎኑ የተወጋበትን ጦር የፈሰሰውን ደሙን የተቆረሰ ሥጋውን በጠቅላላው ለእኛ ሲል አምላካችን የተቀበለውን ጸዋትወ መከራ እናስባለን፡፡

  ReplyDelete
 14. ስለ መስቀል የሐዋርያት ትምህርት
  ስለ ቅዱስ መስቀል ከክርስቶስ ቀጥሎ ያስተማሩት ቅዱሳን ሐዋርያት ናቸው፡፡ ርዕሰ ሐዋርየት ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ በማለት ያስተምራል፡፡ “ወበእንተ ኃጣውኢነ ውእቱ ተሰቅለ ዲበ ዕፀ በሥጋሁ ከመያውጽአነ እምኃጣውኢነ” ስለ ኃጢአታችን እርሱ በእንጨት /በመስቀል/ ላይ ተሰቀለ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ” 1ጴጥ.1፡24 በማለት በመስቀሉ ክርስቶስ የከፈለልንን ዋጋ ነገረን፡፡
  “ወንገረ መስቀሉሰ እበድ ውእቱ በኃበ ህጉላን ወለነሰ ለእለ ድኅነ ኃይለ እግዚአብሔር ወጥበበ እግዚአብሔር ውእቱ” 1ቆሮ.1፡18፡፡


  “የመስቀሉ ቃል /ትምህርቱ/ ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚብሔር ኃይል ነው በማለት እግዚአብሔር ኃይሉን የገለጠበት ማዳኑን ያሳየበት ትድግናው የተከናወነበት መሆኑን ያስረዳናል፡፡ ይህን ዓለም አልተቀበለውም አላወቀምና፡፡


  “እኛስ የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን” 1ቆሮ.1፡2 ሲል የክርስቶስ መገለጫው መስቀሉ ነው፡፡ ዙፋኑ ነውና ዲያብሎስን የቀጣበት ኃይሉን የሻረበት ነውና ሰው ይህን መቀበል ካልቻለ ሰው መሆኑ ያጠራጥራል፡፡


  “እስመ ይቤ መጽሐፍ ርጉም ውእቱ ኩሉ ዘስቁል ዲበ ዕፅ ወለነሰ ተሣሃለነ እመርገማ ለኦሪት” መጽሐፍ በእንጨተ የተሰቀለ ሁሉ ርጉም ይሁን ይላልና እኛን ግን ከኦሪት ርግማን በእንጨት ተሰቅሎ ዋጀን” ገላ.3፡12፡፡


  የኦሪትን ርግማን ተቀብሎ በእንጨት መስቀል ተሰቅሎ መርገሙን ወደበረከት ለወጠልን መስቀል የእርግማን ምልክት ሳይሆን የድል፣ የነጻነት፣ የበረከት ምልክት መሆኑን አወጀልን፡፡ እኛም ይህን ተቀብለን መስቀል ኃይላችን ነው መስቀል መድኃኒታችን ነው እንላለን፡፡ በመስቀሉ እንመካለን ጥግ አድርገን ጠላታችንን እንዋጋበታለን፡፡


  “በሥጋ መልካም ሆነው ሊታዩ የሚወዱ ሁሉ እንድትገረዙ ግድ አሏችሁ ነገር ግን ስለ ክርስቶስ መስቀል እንዳይሰደዱ ብቻ ነው ገላ.5፡12፡፡ ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት /ከኃጢአት/ የተለየበት እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት /ከኃጢአት የተለየሁበት/ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ”


  እዚህ ላይ ቅዱስ ጳውሎስ ከኃጢአት የተለየበት ከእግዚአብሔር ጋር የታረቀበት መመኪያው መስቀል እንደሆነ ከመሰከረ እኛስ ከእርሱ አንበልጥም እኔን ምሰሉ ብሎናልና” 1ቆሮ.11፡1፡፡ ስለዚህ ነው በመስቀሉ የምንመካው የምናከብረው ኃይላችን ብለን የምንጠራው መስቀሉን መስቀል የሰላም መሠረት ነው ጥልን /ዲያብሎስን/ የገደለ /ድል የነሣ/ ለሰው ሰላም የተደረገበት ነው፡፡


  “ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን /ሕዝብና አሕዛብን/ በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው” ኤፌ.2፡16፡፡ “ወገብረ ሰላመ በደመ መስቀሉ ለእለ ውስተ ሰማይ ወእለ ውስተ ምድር ወዘታህቴሃ ለምድር በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ለራሱ /ከራሱ ጋር/ እንዲያስታርቅ ፈቅዷልና ቆላ.1፡20፡፡ ለዚህ ነው መስቀል ሰላም ነው የሰላም ምልክት ነው የምንለው ሰውና መላእክት ሰውና እግዚአብሔር ሕዝብና አሕዛብ ነፍስና ሥጋ የታረቁበት ነውና፡፡


  “በትዕዛዛት የተጻፈውን የእዳ ጽሕፈት ደመሰሰው እርሱንም በመስቀል ጠርቆ አስወግዶታል ቆላ.2፡14፡፡ እንግዲህ የዕዳ ደብዳቤያችን የተሻረበት እኛ ጸጋና ክብርን የተጎናጸፍንበት የዕርቅ የሰላም የመዳን ምልክት ነው መስቀል፡፡


  ስለዚህ ብዙዎች መስቀልን ይወዱታል በአንጻሩም ብዙወች ባለማወቅና በክፋት ይጠሉታል ሊቀብሩት ፈለጉ ለምን? ተአምራት በማድረጉ ድውይ በመፈወሱ ሙት በማስነሣቱ፣ እውር በማብራቱ ባለቤቱን ክርስቶስን እንደጠሉት ሁሉ መስቀሉን የጠሉ አይሁድ መስቀሉን ለ300 ዓመታት ቀበሩት መስቀል ገቢረ ተአምራት የሚያደረግ ተቀብሮ ይቀር ዘንድ የማይቻል ነውና በእሌኒ ንግሥት አማካኝነት ከተቀበረበት ወጣ መስቀል በጎልጎታ ብቻ አይደለም የተቀበረው በክርስቶሳውያን ልቡና ጭምር እንጂ ስለሆነም ቀብሮ ማስቀረት አይቻልም ይልቁንም ቤዛነቱን ኃይሉን ተአምራቱን አምኖ መቀበል ነው፡፡


  በጥንታውያን ክርስቲያኖች መስቀል ተቀብሮ ከወጣበት ጊዘ ጀምሮ እሌኒ ንግሥት ቤተ መቅደስ ከሠራችለት ጊዜ ጀምሮ በመስከረም አሥራ ሰባት ቀን አሁን በኢትዮጵያ እንደሚከበረው ይከበር ነበር፡፡ ዛሬ ግን በኢትዮጵያ ብቻ በደማቅ ሁኔታ ሲከበር በሌሎች ታስቦ ይውላል፡፡ ይህም የሚያሳየው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቱያን ታሪክን በመጠበቅ ከሌሎች ይልቅ ምን ያህል ብርቱ እንደሆነች ያሳያል፡፡


  ለመስቀሉ ጠላቶች የተሰጠ ተግሳጽ
  ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና ብዙ ጊዜ ስለ እርሱ አልኳችሁ አሁንም እንኳ እያለቀስኩ እላለሁ መጨረሻቸው ጥፋት ነው ሆዳቸው አምላካቸው ነው ክብራቸው በነውራቸው ነው አሳባቸው ምድራዊ ነው” ፊል.3፡18፡፡


  ReplyDelete


 15. 1. መስቀል የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጫ ነው፡፡

  “መስቀል” የሚለው ቃል ክርስቶስ የተሰቀለበትን ዕፀ መስቀል፣ ክርስቶስ የተቀበለውን መከራ፣ እንዲሁም ምእመናን ክርስቶስን አምነው እግዚአብሔርን ለማገልገል የሚቀበሉትን መከራ ያስተረጒማል፡፡
  2. መስቀል የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጫ ነው፡፡

  መስቀል ከሦስቱ አካላት (አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ) አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድ ሰው የሆነበት ዓላማ ነው፡፡ መስቀል የክርስቶስ ሕማምና ሞት ምሥጢር ነው፡፡ “ፍቅር ሰሐቦ ለወልድ ኀያል እመንበሩ ወአብጽሖ እስከ ለሞት” ትርጒም፡- “ኀያል ወልድን ፍቅር ሳበው፤ እስከሞትም አደረሰው” (አባ ሕርያቆስ፡ቅዳሴ ማርያም) ተብሎ እንደ ተጻፈ እግዚአብሔር ወልድ ሰው የሆነበት ምክንያት ሰውን መውደዱ መሆኑ ግልጽ ነው፤ ስለዚህ መስቀል ሰውን ወደ ቀደመ ክብሩ፣ ወደ ቀደመ ቦታው ለመመለስ እግዚአብሔር የፈጸመው ሰውን የመፈለግ ጉዞ ነው፡፡


  በተስእሎተ ቂሣርያና በደብረ ታቦር “ኢየሱስ እርሱ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ” (ማቴ16፥16፤ 17፥5) እንደሆነ በግልጽ ከተነገረ በኋላ ክርሽጾሽ ወደ ኢየሩሳሌም ስለ መውጣቱና በሊቃነ ካህናት፣ በጸሐፍትና በፈሪሳውያን እጅ ተይዞ እንደሚሰቀል ገልጦ ለደቀ መዛሙርቱ ሲያስተምር ቅዱስ ጵጥሮስ “አይሁንብህ” በማለት ተናገረው፤ ሆኖም ክርስቶስ የመስቀልን ነገር አለመቀበል የእግዚአብሔርን አሳብ መቃወም ስለሆነ “የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ከኋላየ ሂድ፤ እንቅፋት ሆነህብኛል” በማለት ገሠጸው (ማቴ.16፥21-28)፡፡

  ክርስቶስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ የሚጠብቀው ነገር መስቀል እንደሆነ እያወቀ የመጣለት ዓላማ ነበርና ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፤ በዮሐንስ ወንጌል ክርስቶስ “ጊዜዬ ገና አልደረሰም”፤ ዮሐንስ ደግሞ “ጊዜው ገና አልደረሰም ነበርና” በማለት የተናገሩት ጊዜ የመስቀል ጊዜ እንደ ነበረ እናውቃለን፤ በመጨሻው ሳምንት ግን ክርስቶስ ወደኢየሩሳሌም ወጥቶ ሳለ የሞቱ ሰዓት ሲቃረብ በጊዜ ፈንታ “ሰዓቱ” በማለት ተናገረ (ዮሐ.12፥23፡27፣13፥1፣17፥1)፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማያት ወርዶ፣ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ የተጓዘው የሕይወት ጉዞ የመስቀል መንገድ፣ ሰውን የመፈለጉ የፍቅር ጉዞ መሆኑን በዚህ እናያለን፡፡

  መሰቀል የፍቅር ፍጻሜ መሆኑን ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ይመሰክራሉ፤ ጌታችን በዮሐንስ ወንጌል “አልቦ ዘየዐቢ እምዝ ፍቅር ከመ ዘይሜጡ ነፍሶ ቤዛ ነፍሰ ቢጹ” ስለ ወዳጆቹ ቤዛ ነፍሱን አሳልፎ ከመስጠት ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም” (ዮሐ.15፥13) ሲል እንደተናገረው ከመስቀል የበለጠ የእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጠበት በሰማይም ሆነ በምድር ሌላ ነገር የለም፡፡

  ReplyDelete
 16. 3. መስቀል የትንቢተ ነቢያት ፍጻሜ፣የተስፋ አበውም መድረስ ነው፡፡

  መስቀል የትንቢተ ነቢያት ፍጻሜ፣ ለዘመናት ሲጠበቅ የነበረው የመዳን ተስፋ መድረስም ነው፡፡ መስቀል የሚለው ቃል በብሉይ ኪዳን ተጽፎ ባይገኝም ክርስቶስ በመስቀል ላይ ስለተቀበለው መከራ በትንቢትና በምሳሌ ብዙ ነገር ተነግሯል፤ በእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውስጥ ምሥጢረ ድኂን (ነገረ መስቀል) በግልጽም ሆነ በምሥጢር ተነግሯል፤ ለምሳሌ ያህል ለማየት በኦሪት ዘኁልቍ ምዕ.21፥8፡9) እንደተጻፈው ሙሴ በእስራኤል አደባባይ የሰቀለው አርዌ-ብርት በቀራንዮ በመስቀል ተሰቅሎ ዓለምን ያዳነው የወልደ እግዚአብሔር ምሳሌ መሆኑ በዮሐንስ ወንጌል ተገለጾአል (ዮሐ.3፥14)፡፡ “ወበከመ ሰቀሎ ሙሴ ለአርዌ ምድር በገዳም ከማሁ ሀለዎ ለወልደ እግዚአብሔር ይሰቀል ከመ ኵሉ ዘየአምን ቦቱ ኢይትሐጐል አላ ይሕየው ሕይወተ ዘለዓለም” ትርጒም፡- “ሙሴ በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ሊሰቀል ይገባዋል” ተብሎ፡፡ በነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ ም.53 “መስቀል” የሚለው ቃል ባይጻፍም ሕማመተ መስቀሉ በዝርዝር በመንፈሰ ትንቢት ለነቢዩ ታይተው፣ በመጽሐፍ ተጽፈው ከትውልድ ትውልድ ሲሰበኩና ሲነገሩ ቆይተዋል፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ከተናገራቸው ሰባት አጽራሐ መስቀል አንዱ “ተፈጸመ ኵሉ” ማለትም “ሁሉም ነገር ተፈጸመ” (ዮሐ.19፥30) ሲል የተናገረው ቃል መስቀል የትንቢተ ነቢያት መፈጸምን፣ የተስፋ አበው መድረስን፣ ለሰው ልጆች መዳን አስፈላጊ የሆነው ነገር ሁሉ በክርስቶስ ሞት የተፈጸመ መሆኑን ያሳያል፡፡

  4. መስቀል የእግዚአብሔር ልዩ ጥበብ ነው፡፡

  መስቀል ከሰው አእምሮ በላይ የሆነ የእግዚአብሔር ጥበብ ነው፤ በዘመነ ሐዋርያት የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ከኢየሩሳሌም ጀምራ በይሁዳ፣ በሰማርያና በልዩ ልዩ የአሕዛብ ከተሞች የክርስቶስን ሞትና ትንሣኤ፣ እንዲሁም በመስቀሉ የተገኘውን መዳን ስትሰብክ ለዓለም ይህ ጥበበ እግዚአብሔር እንደ ጥበብ ሳይሆን እንደሞኝነት ይታይ ነበር፤ በሌላ በኩል አይሁድም ቢሆኑ ስለሙሴ ሕግና ስለ አባቶቻቸው ሥርዐት የቀኑ በመምሰል የመስቀልን ሥራ ይቃወሙ ነበር፤ እንዲህ አይነቶችን ተግባራትና ሰዎች ቅዱስ ጳውሎስ “የመስቀል እንቅፋቶች (ገላ.5፥11 እና “የመስቀል ጠላቶች (ፊል.3፥18) በማለት ተቃውሟቸዋል፡፡

  ይህ ተሠውሮ የነበረ አሁን ግን በእግዚአብሔር ፍቅር የተገለጠው ምስጢር በኢትዮጵያውያን የአንድምታ ትርጓሜ መምህራን ሐተታ “እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል” በማለት “እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ የበለጠ ጥበብ” ተብሎ ይጠራል፡፡ ምክንያቱንም ሲገልጡ ዓለምን መፍጠር የባሕርይ ገንዘቡ ነው፤ ሰው መሆን ሥጋ መልበስ፣ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መሞት ግን በፈቃዱ የፈጸመው አስደናቂ ሰውን የማዳን ጥበብ እንጂ የባሕርዩ አልነበረምና ይላሉ፡፡ የግሪክ ጠቢባንም በራሳቸው አእምሮ ልክ የተሰፋ፣ በምርምር ሊደረስበት የሚችል ጥበብ አለመሆኑን ሲያውቁ ለእግዚአብሔር ጥበብ ከመሸነፍና ለአግዚአብሔር ከመገዛት ይልቅ እንደሞኝነት ይቆጥሩት እንደ ነበረ ቅዱሳት መጻሕፍትና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳሉ (1ቆሮ.1፥18) ፡፡

  5. መስቀል ክርስቶስን የምናገለግልበት የመከራ ሕይወት ነው፡፡

  መስቀል ክርስቶስን በእምነት መከተልና ማገልገል ነው (ሉቃ.9፥23)፡- መስቀልን ተሸክመው እንዲከተሉት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተምራቸው ደቀ መዛሙርቱ ስለእርሱ መከራን መቀበልና እርሱን ማገልገል እንደሚገባቸው ማስተማሩ ነበር፡፡

  መስቀል ክርስቶስን እንደ ተሰቀለ ሆኖ በእምነት ዐይን ዘወትር የምናይበት ምሥጢር ነው (ገላ.3፥1)፡፡ ሞቱን አምነን እርሱን የምንመስለው በእምነታችንና እምነታችንን ለማስተማር በምናደርገው ተጋድሎ ነው፤ ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች “ ክርስቶስ በመካከላችሁ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር” ማለቱ በርኅቀት ያሉ ነገሮችን ማየት የሚችል የእምነትን ኀይል ለመግለጽ ነው፤ ጌታችን በኢየሩሳሌም እንጂ በገላትያ አልተሰቀለምና፡፡ ገላትያንና ቀራንዮን ያገናኘ የእምነት ድልድይ የክርስቶስ መስቀል እንጂ የግሪክ ፍልስፍና ወይም የሮም ስልጣኔ አልነበረም፤ በእርግጥ መስቀል ቀራንዮንና ገላትያን ብቻ ሳይሆን ሰማይንና ምድርን፣ ሰውንና እግዚአብሔርን፣ ሰውንና መላእክትን፣ ነፍስንና ሥጋን፣ ሕዝብንና አሕዛብን አንድ ያደረገ የአንድነት ምሥጢር ነው፡፡

  6. መስቀል በሊቃውንት ትምህርት

  የነቢያት ትንቢት፣ የክርስቶስ ወንጌል፣ የሐዋርያት ስብከት፣ የሊቃውንት ምሥጢር መስቀልን ማእከል ያደረገ ነበር፤ በኢትዮጵያውያን ሊቃውንት ትምህርትም ሲታይ ነገረ መስቀል የቅዱስ ያሬድ የምሥጢር መሠረት፣ የዜማው ጣዕም እንደሆነ ማየት እንችላለን፤ ስለ ቅዱስ ሥጋው፣ ስለ ክቡር ደሙ፣ ስለሞቱ ስለ ትንሣኤው፣ ስለ ቅዱሳን መንፈሳዊ ሕይወት፣ ወዘተ በተናገረበት ቦታ ሁሉ መስቀል የምሥጢር ማሰሪያው ነበር፡፡ ለዚህ ጽሑፍ ርእስ ያደረግነው “መስቀልከ እግዚኦ ተሰብሐ” የሚለው ድርሰቱም መስቀል የሙታን ትንሣኤ፣ የሕሙማን ፈውስ፣ የዕውራን ብርሃን፣ የቤተ ክርስቲያን መሠረት እንደሆነ ያስተምራል፡፡

  ሌላው ከኢትዮጵያውያን ሊቃውንት አንዱ የሆኑት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫም ስለ መስቀል የሚከተውን ጽፈዋል፤ “ተተክለ ዕፀ መስቀል በእደ አይሁድ፤ ወተነድቀት ቤተ ክርስቲያን በእደ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ ተጠብሐ በግዑ ለእግዚአብሔር ዲበ ዕፀ መስቀል በእደ ሰቃልያን ወተሠርዐ ማእደ በረከት ለመሃይምናን፤ ተረግዘ ገቦሁ መድኀኒነ፤ በተቀብዓ ኀዋኅዊሃ ለቤተ ክርስቲያን በደመ መረዓዊሃ” ትርጒም፡- “ዕፀ መስቀል በአይሁድ እጅ ተተከለ፤ ቤተ ክርስቲያንም በኢየሱስ ክርስቶስ እጅ ተመሠረተች፤ የእግዚአብሔር በግ በሰቃልያን እጅ በዕፀ መስቀል ላይ ታረደ፤ የበረከት ማእድም ለምእመናን ተዘጋጀ፤ የመድኃኒታችን ጎኑ ተወጋ፤ የቤተክርስቲያን ደጆች (በሮችዋ) በሙሽራዋ ደም ተቀቡ” (የቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫና የአባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም (2001)፡ መጽሐፈ ምሥጢር ምዕራፍ 5 ቁጥር 6፣ ገጽ140) ፡፡

  መስቀል ተነግሮ የማያልቅ፤ ተሰብኮ የማይጠገብ የቤተ ክርሰቲያን ምሥጢር ነው፤ ስለዚህም በቤተ ክርስቲያን በሁሉም መንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ መስቀል አለ፤ ያለ መስቀል የሚፈጸም የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን በሁለት ሺህ ዓመታት ታሪኳ ውስጥ ከዐላውያን ነገሥታት፣ ከመምለክያነ ጣኦት አሕዛብ፤ ከአጽራረ ቤተ ክርስቲን መናፍቃን ጋር ባደረገቻቸው ተጋድሎዎች ሁሉ መስቀል ምርጉዘ ቤተ ክርስቲያን፣ ተስፋ ቅቡፃን ሆኖ ኖሯል፡፡ ዛሬም መስቀልን ማክበር ሃይማኖትን መመስከር፣ የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ መግለጥ ነውና ቤተ ክርስቲያን እስካሁን ድረስ ጠብቃው እንደ ኖረች ሁሉ በዓለ መስቀልን ታከብረዋለች፤ ለነገ ትውልድም በአግባቡ ታስረክባለች፡፡
  ምንጭ፡ መስቀል ከጎልጎታ እስከ ግሸን ደብረ ከርቤ፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፡ የ2006 ዓ/ም የመስቀል በዓልን አስመልክቶ የወጣ መጽሔት፡፡

  እኛም ቤተ ክርስቲያን የመስቀለ ክርስቶስን እውነተኛ መልክ የያዘ በዓለ መስቀልን ለመጠበቅና ለትውልድ ለማስተላለፍ በምታደርገው ጥረት እያገዝን መስቀልን የተመለከተ የስሕተት ትምህርት ሁሉ እንዲስተካከል እንሠራለን፡፡

  እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅ!

  ReplyDelete
 17. ዲያብሎስ የሚፈራው ኢየሱስን እንጅ መስቀልን አይደለም:: ሐዋርያት አጋንንትን ያውጡት በኢየሱስ ስም ነው በመስቀል የሚል ማስረጃ የለም አሁንማ ግርምሽም
  በመቁጠሪያ አወጣለሁ ይላል :: ጐበዝ አንሳሳት መጽሀፍ ቅዱስ ያልተናገረውን ሐዋርያት ያላስተማሩትን አባቶች ብለዋል የሚለው ማስረጃ አይደለም

  ReplyDelete
 18. Aba Selama ke Cinodocu begiltse ketewegedut tehadisowoch mehal andu selehonk aygermim yehe ye tehadiso ena ye minfikina timhrtihin ezaw lerasih egna wengelin keman endetemarin enawkalen

  ReplyDelete
 19. ከአፈወርቅ ምን ይደረግ በቅርስነት በአለም ተመዘገበ ውይ እናንት መናፍቆች መቃወም ከተባለ ሁሉንም መቃወም ነው ወደድህም ጠላህም ትጋተዋልህ ሬት ሬት እለህ ድሮም መናፍቅ እኮ የተቋቋመው ስራው ባህልን ሀይማኖትን ለመበረዝ ጥርጣሬን ለመንዛት ነው አፈወርቅ የመደር ወሬ ለቃቃሚ ነህ

  ReplyDelete
 20. አትሳሳት፣ ዲያብሎስ እኮ መስቀልን የፈራው በመስቀሉ ውስጥ ድል ነሺውን ኢየሱስን ስለሚያየው እኮ ነው፣ ግርምሽ ላልከው…ግርማ ጠንቋይ መሆኑን ከቤተክርስቲን እንዲወጣ የተደረጉት ጥረቶች አመላካች ናቸው፡፡ እኛም አልተቀበልነውም ለነገሩማ እንደ አንተ ፍቅረ ነዋይ ያደረባቸው አገልጋይ ነን ባዮች እና ቀሳጮች ፊት ሰጡት እንጂ አኛ ጥንቱንም ግርማ ጠንቋይ እንደሆነ አላጣነውም …መስቀል ይዞም ታይቶ አይታወቅም…መቁጠሪያዋን እረሳሃት፡፡ ብዙዎች ለመስቀሉ ጠላት ሆነው ይመላለሳሉ እንዲል መጽሐፍ ትንቢቱ በእናንተ እየተፈጸመ ነው፡፡ መስቀልን ምልክታችን ማድረጋችን የተከፈለልን መስዋእትነት ምን ያህል ልዩ እንደነበረ ዘወትር በዐይነ ሕሊናችን እንዲሳል ነው፡፡ አሁንም እልሃለሁ ዲያብሎስ መስቀልን ይፈራል ከፈለክ መንፈስ ያለበት ሰው መስቀል ሲያይ እንዴት እንደሚሆን ናና ተመልከት….ይቅርታ ለካ አንተም ያ እርኩስ መንፈስ ሰፍሮብሃል …. እንዳያስጮህህ ብዬ ነው፡፡ መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንነ መስቀል ቤዛነ መስቀል መድኀኒተ ነፍስነ አይሁድ(መናፍቃን/ተሃድሶአውያን) ክህዱ ንህነሰ አመነ ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ፡፡ እግዚአብሔር አላውያንን፣ መናፍቃንን ከቤተክርስቲያን ላይ ያስታግስልን አሜን፡፡

  ReplyDelete
 21. You do not have moral power to curse Afework. Look, you will be go to the city or school to improve your damp Bala ger Amaharic.

  ReplyDelete