Friday, October 31, 2014

ከቅዱስ ሲኖዶስ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የተዘረጋው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ማሻሻያ ረቂቅ በሙሉ ድምጽ ጸደቀ።

Read in PDF

  • ·        ቅድስት  ቤተ  ክርስቲያን  እንኳን  ደስ  አለሽ!  
  • ·        ብፁዕ  ወቅዱስ  አባታችን  እንኳን  ደስ  አለዎት!  
  • ·        ብፁዓን  ሊቃነ  ጳጳሳት  እንኳን  ደስ  አላችሁ!  

   በቅዱስ  ፓትርያሪኩ   ብርቱ  አሳሳቢነትና  ጠንካራ  አቋም  የቀረበውና   የቅዱስ  ሲኖዶስ   ምልዓተ  ጉባኤ  በሰፊው  የተወያየበት  ሕገ  ቤተ  ክርስቲያን   ማሻሻያ   በሙሉ  ድምጽ   ጸደቀ።  ሕገ  ቤተ ክርስቲያኑ  አንድ  ወጥ  የሆነና  ከቅዱስ  ሲኖዶስ  እስከ  አጥቢያ  ቤተ   ክርስቲያን  የተዘረጋ መዋቅራዊ  አሠራርን  ያካተተ  መሆኑ ታውቋል።  
ሕጉ  እንዳይጸድቅ  የነበሩ አንድ   አንድ  እንቅፋቶች  ሁሉ ታልፈው በስተመጨረሻ ግን መሳካቱ አልቀረም  ከብዙ  ውጣ  ውረድና  የጊዜ   መባከን  በኋላም  በቅዱስ  ፓትርያሪኩ  ጽኑዕ  አቋምና  በሊቃነ  ጳጳሳቱ  ጥልቅ  ውይይት  ሕገ   ቤተ  ክርስቲያኑ  በትላንትናው  ቀን  በሙሉ  ድምጽ  ሊጸድቅ ችሏል።   

Wednesday, October 29, 2014

የሲኖዶሱ ስብሰባ እና የማቅ ዘገባዎች

read in PDF

ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በሐሰትም የሚናገር አያመልጥም. (ምሳ.19:5) 
ሰሞኑን ማቅ ስለገባበት ለሕግ ተገዛ አጣብቂኝ አስመልክቶ በሐራ ብሎግ ስለሚናፈሰው የሐሰት ወሬ አንድ ለማለት ፈለግን። ቅዱስ ሲኖዶስ 3ኛውን ዓመታዊ ስብሰባ ከማድረጉ ቀደም ብሎ የጠቅላላ ሰበካ ጉባኤ ስብሰባ እንደነበር ይታወቃል። በዚህ ጉባኤ ላይ ማቅ ሕገ ወጥነቱ በሰፊው የተነሳ ሲሆን ከቅዱስ ፓትርያሪኩ ጀምሮ በብዙዎቹ የጉባኤው  ተሳታፊዎች ጠንካራ ተቃውሞ የደረሰው መሆኑ ታውቋል። ይኽንን ተከትሎ ማቅ ጉዳዩ በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ እንዲነሳለትና የጳጳሳቱን ድጋፍ አግኝቶ በቀላሉ ለማምለጥ እንድችል ያላደረገው ጥረት የለም። ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉት አባቶች እንደሚናገሩት በብዙ የሚቆጠር ብር ለእያንዳንዱ ሊቀ ጳጳስ በመበተንና እንዲሁም በተለያየ መንገድ ድጋፋቸውን ለመሰብሰብ አጥብቆ መሯሯጡ የአደባባይ ምሥጢር ነበረ።  
ይኽ በእንዲህ እንዳለ በሐራ ተዋሕዶ በኩል ማቅ የሚያወናጭፈው የሐሰት ወሬ ግን ቀደም ሲል ከነበረው በዓይነቱም ሆነ በይዘቱ እጅግ የከረፋ ሆኗል። ነገሩን በውል ስናየው ከወንጀሉ ለማምለጥ በሚያደርገው ጥረት የአንባቢ ግንዛቤ መኖሩን  እንኳ ዘንግቶታል። ወይም የተፈለገውን ያክል ብዋሽ ሥራዬ ስለሆነ ልቀይረው አልችልም የሚል ይመስላል። በእኛ ዘንድ እውነቱ ግን ,ያዳቆነው.....ሳያቀስ አይቀርም. እንደሚባለው ከጅምሩ የተዋሐደው የሐሰት መንፈስ ወደዳር እያወጣው መሆኑ ነው። የቆየውን ወደኋላ እንተወውና አሁን ሰሞኑን ,ሐራ ተዋሕዶ. ብሎግ የተለጠፈውን ውሸት እንመለከት፦ 

Friday, October 24, 2014

የቅዱስ ፓትርያርኩ የጥቅምት 2007 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ መልእክትበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
ምእመናንን በንጹሕ ደሙ የዋጀ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን በቅዱስ መንፈሱ መሪነት እየጠበቀ ከዚህ ጊዜ ስላደረሰን ክብርና ምስጋና ለእርሱ እናቀርባለን ፡፡
እንደዚሁም ሁላችንን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከየሀገረ ስብከታችን በረድኤት ስቦ በሀብት አቅርቦ በዚህ ሐዋርያዊና ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተገናኝተን በእግዚአብሔር ስለተሰጠን ዓቢይ ተልእኮ እንድንመካከር ስለሰበሰበን ስሙ የተመሰገነ ይሁን ፡፡
ወመጺኦ ውእቱ መንፈሰ ጽድቅ ይመርሐክሙ ኀበ ከሉ ፍኖተ ጽድቅ፤ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል   (ዮሐ. 16:13)ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ቃሉና በክቡር ደሙ ከመሠረታት በኋላ በበዓለ ሐምሣ በወረደውና ወደ እውነት ሁሉ በሚመራው በመንፈስ ቅዱስ እንድትመራ ማድረጉ ሁላችንም የምናውቀው ነው ፡፡
ከበዓለ ሐምሣ ጀምሮ እስከ ዛሬ፣ ከዚህ በኋላም እስከ ዕለተ ምጽአት፣ ከዚያም ቀጥሎ ማኅለቅት በሌላቸው አዝማነ መንግሥተ ሰማያት ሁሉ ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ መሪነትና አስተማሪነት ተጠብቃ ትኖራለች ፡፡
መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን የሚጠብቅበት የራሱ የሆነ ጥልቅና ረቂቅ አምላካዊ ጥበብ ያለው ሲሆን፣ ከሚታወቅ የአመራር ጥበቡ አንዱ የሐዋርያት ጉባኤ ወራሽ በሆነው በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አማካኝነት ቤተ ክርስቲያንን የሚመራበት ጥበቡ ነው ፡፡