Friday, October 24, 2014

የቅዱስ ፓትርያርኩ የጥቅምት 2007 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ መልእክትበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
ምእመናንን በንጹሕ ደሙ የዋጀ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን በቅዱስ መንፈሱ መሪነት እየጠበቀ ከዚህ ጊዜ ስላደረሰን ክብርና ምስጋና ለእርሱ እናቀርባለን ፡፡
እንደዚሁም ሁላችንን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከየሀገረ ስብከታችን በረድኤት ስቦ በሀብት አቅርቦ በዚህ ሐዋርያዊና ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተገናኝተን በእግዚአብሔር ስለተሰጠን ዓቢይ ተልእኮ እንድንመካከር ስለሰበሰበን ስሙ የተመሰገነ ይሁን ፡፡
ወመጺኦ ውእቱ መንፈሰ ጽድቅ ይመርሐክሙ ኀበ ከሉ ፍኖተ ጽድቅ፤ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል   (ዮሐ. 16:13)ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ቃሉና በክቡር ደሙ ከመሠረታት በኋላ በበዓለ ሐምሣ በወረደውና ወደ እውነት ሁሉ በሚመራው በመንፈስ ቅዱስ እንድትመራ ማድረጉ ሁላችንም የምናውቀው ነው ፡፡
ከበዓለ ሐምሣ ጀምሮ እስከ ዛሬ፣ ከዚህ በኋላም እስከ ዕለተ ምጽአት፣ ከዚያም ቀጥሎ ማኅለቅት በሌላቸው አዝማነ መንግሥተ ሰማያት ሁሉ ቤተ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ መሪነትና አስተማሪነት ተጠብቃ ትኖራለች ፡፡
መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያንን የሚጠብቅበት የራሱ የሆነ ጥልቅና ረቂቅ አምላካዊ ጥበብ ያለው ሲሆን፣ ከሚታወቅ የአመራር ጥበቡ አንዱ የሐዋርያት ጉባኤ ወራሽ በሆነው በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አማካኝነት ቤተ ክርስቲያንን የሚመራበት ጥበቡ ነው ፡፡

መንፈስ ቅዱስ በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አማካኝነት በኒቅያ፣ በቁስጥንጥንያና በኤፌሶን ብዙ መናፍቃንን ከቤተ ክርስቲያን ለይቶ በማውጣት ቤተ ክርስቲያንን ከስሕተትና ከውድቀት ታድጓል፡፡ 
በመንፈስ ቅዱስ መሪነት የሚመራው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለትም ሦስትም ሆናችሁ በስሜ በምትሰበሰቡበት እኔ በዚያ አለሁ$ ብሎ ቃል ኪዳን የገባለትና በባለቤትነት የሚገኝበት ዓቢይና ቅዱስ ጉባኤ ነው፡፡(ማቴ.18:20)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት፣ በሁሉም ያለች፣ ቅድስትና አንዲት እንደመሆንዋ መጠን ለሁለት ሺሕ ዓመታት ያህል የተመራችው በመንፈስ ቅዱስ በሚመራው ሲኖዶስ እንጂ በሌላ በማንም አይደለም፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በምሥራቅ አፍሪካ፣ ብሎም በአፍሪካ ምድር በጠቅላላ፣ በማንኛውም ሐዋርያዊ ሚዛን ትክክለኛ ሃይማኖት ያላት ጠንካራና አንዲት ቤተ ክርስቲያን ናት ፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ከጥንታዊው ትምህርተ ሃይማኖት ዝንፍ ሳትል በሚያስደንቅ ሁኔታ የሁለት ሺሕ ዘመናት ዕድሜ ክርስትናን ማስቆጠር የቻለችበት ዓቢይ ምሥጢር በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በሚቃኝ ሲኖዶሳዊ አመራር መመራቷ ነው ፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
ዛሬም እንደጥንቱና እንደትናንቱ የቤተ ክርስቲያናችን ብቸኛ መሪ በመንፈስ ቅዱስ የሚመራ ቅዱስ ሲኖዶስ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡
ሁላችንም የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ይህንን ክርስቶሳዊና ሐዋርያዊ ተልእኮ ጠብቀን እንዳለ ለመጪው ትውልድ የማስተላለፍ ግዴታ አለብን፡፡
    ሉዓላዊውን የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣንና ኃላፊነት በተለያየ ምክንያት በመጋፋት የራሳቸውን ሥውር ዓላማ ለመፈጸም የሚከጅሉ ወገኖች ከስሕተታቸው እንዲመለሱ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ከሁላችንም ይጠበቃል ፡፡
   
ሁላችንም እንደምናውቀው ይብዛም ይነስ፤ ዘመን ያለ ታሪክ አያልፍም፤ በየዘመናቱ ያለ ትውልድ በይበልጥ ደግሞ በኃላፊነት የሚቀመጡ ኃላፊዎች የታሪኩ አካል መሆናቸው አይቀርም፤ እንደሌላው ሁሉ እኛም ከዚህ እውነታ ማምለጥ አንችልም፡፡
ታሪክ አንድን ትውልድ በመልካም ወይም በመጥፎ ሊመዘግብ ይችላል፤ የእኛ ታሪክ እየተመዘገበ ያለው ከሁለቱ በየትኛው ነው? የሚለው ግን የሁላችንም መሠረታዊ ጥያቄ ሊሆን ይገባል፤ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ሩቅ መጓዝና ልዩ ምሁርን መጠየቅ አያስፈልገንም፡፡
ቅዱስ መጽሐፍ እስመ ኢኮነ ርኁቀ እምኔነ፤ ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም እንዳለው የሰው ኅሊና በአካባቢውና በውስጡ ያለውን ለይቶ ማወቅ ይቅርና ከአእምሮ በላይ የሆነውን የረቂቅ አምላክ ህልውና እንኳ በመጠኑም ቢሆን ማወቅ የሚችል ነው፡፡ (ዮሐ.ሥራ.1:27 )
መንፈስ ቅዱስም #ዮም አመ ሰማዕክሙ ቃሎ ኢታጽንዑ ልበክሙዛሬ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ ልባችሁን አታጽኑ›› እያለ የሚጣራበት ጊዜ እንደሆነ ማወቁ አይከብድም$:: (ዕብ. 3$15)
በመሆኑም ራስን በራስ በመጠየቅ የሚገኝ መልስና ራስን በራስ በመወሰን የሚሰጥ ዳኝነት ከሁሉም የበለጠ ፈዋሽ መድኃኒት ነውና በራሳችን ዳኝነት የቤተ ክርስቲያናችንን ሉዓላዊነትና አንድነት እንደዚሁም ምእመናንዋና ሀብቷ የሚጠበቁበት ሥራዎችን መሥራት የቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ተግባር ነው ፡፡

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
    ታላቋና መተኪያ የማይገኝላት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በውስጥም ሆነ በውጭ የተጋረጡባት ግልጽና አደገኛ ፈተናዎች እንዳሉ መገንዘብ አለብን ፡፡
   
በቤተ ክርስቲያናችን ከሚታዩ ፈተናዎች አንዱና ዋነኛው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናን ወደ ሌላ እምነት እየፈለሱ ከመሆናቸው ሌላ፤
• የቤተ ክርስቲያናችን ሀብትና ንብረት አያያዝ አስተማማኝ ሆኖ አለመገኘቱ፤
•   
የሰው ኃይል፣ የገንዘብና የንብረት አስተዳደራችን በዘመኑ ቴክኖሎጂ የተቃኘ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነትን ያሰፈነ አለመሆኑ፤
•    በቤተ ክርስቲያን ስም ቤተ ክርስቲያን የማታውቀውና የማትቆጣጠረው ሀብትና ንብረት የሚሰበስቡ ማኅበራት እየተበራከቱ መምጣታቸው፤
•    በቤተ ክርስቲያን ስም ሀብትን የሚሰበስቡ ማኅበራት በእነርሱ የምትተዳደር ቤተ ክርስቲያን ሳትኖር የቤተ ክርስቲያን ብቸኛ መብት የሆነውን ከምእመናን ገንዘብና ንብረት የመሰብሰብ ሥልጣንን ወደራሳቸው በማዞር ገንዘብና ንብረት ከምእመናን መሰብሰብ መልመዳቸው፤
•   
በዚህም ምክንያት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁለት የተለያዩ ዓሥራትና በኩራት ሰብሳቢዎች እየተፈጠሩ መምጣታቸው፤
•    በቤተ ክርስቲያን እየተፈጠረ ያለው ሁለተኛ ባለሀብት ማኅበር በሂደት ቤተ ክርስቲያንን ወደ ሁለት የመክፈል አዝማሚያ እንዳለው ግልጽ ማስረጃ መገኘቱ፤
•    ማኅበራቱ በመንግሥትና በቤተ ክርስቲያን የማይታወቅ ሀብት የሚሰበስቡ በመሆናቸው ገንዘቡ በሚያስከትለው ሌላ ጉዳት ቤተ ክርስቲያን በአክራሪነት የምትፈረጅበት አጋጣሚ መከሠቱ፤
•   
ማኅበራት በሌላቸው ሥልጣን በቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ ሥራ በቀጥታ ጣልቃ እየገቡ የሰላም ጠንቅ ሆነው መገኘታቸው፤
•    ችግሩን በቀላሉ ለማስተካከል ቢሞከር እንኳ ማኅበራቱ ከቤተ ክርስቲያኒቱ የሚሰጣቸውን መመሪያ ለመቀበል ፈቃደኝነቱና ቅንነቱ ፈጽሞ የሌላቸው ሆነው መገኘታቸው አስቸኳይ መፍትሔ የሚሻ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ችግር ሆኖ ተገኝቶአል ፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
‹‹በይሉኝታ የራስ ዓሊ ቤት ተፈታ›› እንደተባለው ትዕግሥትና ደግነት በዚያም ላይ ይሉኝታ ተጨምሮበት ካልሆነ በቀር እነዚህን ወገኖች የምናስተናግድበት ቤትና የምንዳኝበት ሕግ ሳይኖረን ቀርቶ አይደለም ፡፡
እውነቱን እንነጋገር ከተባለ በሃይማኖታችን ትውፊት ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ጸበልን ቀምሶ የሚኖር የጽዋ ማኅበር ካልሆነ በቀር በቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ ቤተ ክርስቲያንን አህሎ የተደራጀና ቤተ ክርስቲያን አከል የሆነ ገንዘብ ሰብሳቢ ማኅበር ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ፡፡
ስለሆነም በመልካም አስተዳደር፣ በሀብትና በንብረት አያያዝ፣ በመሪ እቅድ እየተመሩ ሥራ መሥራትን አስመልክቶ የተጀመሩ ሥራዎች አጠናክሮና አፋጥኖ ከዳር የማድረሱ ተግባር እንዳለ ሆኖ በተለይም በምእመናን ፍልሰትና በማኅበራት ጉዳይ ላይ በሕገ  ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሕጋዊና ዘላቂ መፍትሔ ማስቀመጡ ቤተ ክርስቲያንን የመታደግ ጉዳይ መሆኑን በአጽንዖት ሳንጠቁም አናልፍም ፡፡

በመጨረሻም
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ግልጽ በሆነ ሁኔታ እያልን ያለነው
1.    የምእመናን ፍልሰት በአሁኑ ጊዜ እየተባባሰ ስለመጣ ሁላችንም ተባብረንና አስፈላጊውን ሥራ ሠርተን ፍልሰቱን እናስቁም፤
2. የቤተ ክርስቲያንን ሀብትና ንብረት በመጠበቅ መልካም አስተዳደርን እናስፍን፤
3.   
በቤተ ክርስቲያን ስም የሚሰበሰብ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን የማታውቀው፣ የማትቆጣጠረውና የማታዝበት ገንዘብና ሀብት ሊኖር አይገባም፤
4.    በቤተ ክርስቲያን መዋቅር ያልታቀፈና ለቤተ ክርስቲያን የማይታዘዝ ማኅበር በቤተ ክርስቲያን ስም ተደራጅቶ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ ለቤተ ክርስቲያን ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ የሚያስከትለው ጉዳት ከባድ ስለሆነ፣ በሕግ ማስተካከል አለብን የሚሉትን ነው ፡፡
ስለሆነም ሕዝበ ክርስቲያኑ ይህንን በግልጽ አውቆ የቤተ ክርስቲያኒቱን ወቅታዊ ችግር በመፍታት ረገድ የበኩሉን እገዛ እንዲያደርግ፣
እንደዚሁም በተሳሳተ መንገድ እየሄዱ ያሉትን ወገኖች በቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት ልትመሩ ይገባችኋል ብሎ እንዲመክራቸው፣
እነዚህ ወገኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው እንዲያገለግሉ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን ተጽዕኖ በመፍጠር ታሪካዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን ፡፡ 

 
እግዚአብሔር አምላክ ጉባኤያችንን ይባርክ፤ ይቀድስ፤ አሜን፡፡
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
 
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም፤ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥቅምት 12 ቀን 2007 .

                            
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ10 comments:

 1. Relevant is now action to demolish those terror organization called himself mk.

  ReplyDelete
 2. ተጠያቂዉ ማቅ ነዉ።

  ReplyDelete
 3. የተቀደሰ አባታዊ መልዕክት ነው።

  ReplyDelete
 4. ማኅበረ ቅዱሳን አስተሳሰብን እንጂ ተቋም ሲገነባ አልኖረም፡፡ (የግል ምልከታ)
  ማኅበረ ቅዱሳን ተቋም ሲገነባ የኖረ የሚመስላቸው ብዙ ሞኛ ሞኞች እንዳሉ እናውቃለን እንረዳለንም፡፡ በዚሁም የተነሣ የባጥ የቆጡን እየቀባጠሩ ለከት በሌለው፣ መንፈሳዊነት በእጅጉ በጎደለው የጎለደፈ አንደበት ወይ የተጫኑትን ወይ ያደቡበትን ሲተነፍሱ እየሰማን እያየን እንገኛለን፡፡
  ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል እንዲሉ በተለያየ መንገድ ሾልከው የገቡ መውጣት ሲገባቸው እንዲኖሩ ስለተደረጉ ብቻ ጊዜ ጠብቀው አንገታቸውን ከፍ ከፍ አደረጉ፡፡ ነቀርሳን (ካንሰርን) በጊዜ መንቀል ካልተቻለ የማይድን ይሆናል፡፡ ሳይቃጠል በቅጠል አልነበር አባባሉ፡፡
  የቅዱሳን ቅድስና የእኩያን አጋንንትን ምስክርነት አይሻም፡፡ እንዲያው የቅድስናቸው ጸጋ በእሳት ዛንጅር ሲጠብሳቸው ራሳቸው ይለፈልፋሉ እንጂ፡፡ ይኽም ቢሆን የእነርሱ ምስክርነታቸው ለቅዱሳን ቅድስና ዋቤ አይደረግም አያስፈልግምም፡፡ የሰሞኑን ልቡሳነ….የሰጡትም ምስክርነት ለቤተ ክርስቲያን አስፈላጊዋ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ይኽ ማኅበር ካለ መላወሻ እያጡ እና ሊያጡ እንደሆነ ስላወቁት ኃያልነቱን ደጋግመው ተናግረዋልና፡፡ ማኅበሩ አገልግሎቱን የሚሰጠው ለመሾም ወይም ለመሸለም አይደለም አልነበረምም፡፡ መነቀፉ ሲያንስው እንጂ አይበዛበትም፡፡ ነቀፋው መልካም ሥራን ተከትሎ እስከመጣ ድረስ እንዲያውም ከዚህ ሊያልፍ እንደሚችል መገመት ይገባል፡፡ ስለመልካም ሥራ ዓለም አትመሰክርም፡፡ ከዓለም የኾኑቱ እኒያ ደግሞ ይነቅፋሉ፡፡ ስለኾነም አይደነቅም፣ ግርምትም አይፈጥርም፡፡
  ይኽ ማኅበር እና አባላቱ ሲገነቡ የኖሩት መንፈሳዊ አስተሳሰብን ነው፡፡ ያላመኑ እንዲያምኑ፣ ያመኑ እንዲጸኑ፣ የጸኑ ደግሞ በጉልበታቸው፣ በዕውቀታቸው እና በገንዘባቸው ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግሉ! ይኽን ሲገነባ ኖሯል፡፡ ለአማንያን በ፵ በ፹ ቀን መጠመቅ ብቻ አይበቃም፡፡ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር እየገቡ አንድም በሰበካ ጉባኤ አንድም በሰንበት ትምህርት ቤት እየተመዘገቡ ትምህርተ ሃይማኖትን፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንዲሁም ትውፊታቸውን ማወቅ እንደሚገባ የድርሻውን ሲያበረክት ቆይቷል፡፡ በዚኽም የሚጨበጥ፣ የሚነካ ወይም የሚዳሰስ አካል የገዛ ለውጥ እንዲመጣ ተጋድሏል፡፡ ይኽን እንኳን ከሳሾች አባታቸውም አይክድም፡፡
  ምእመናን በየአጥቢያቸው ባሉት የሰበካ ጉባኤያት እየታቀፉ ከዳር ተመልካችነት ወደ አገልግሎት ሱታፌ እንዲገቡ እያሳሰበ ለውጥ እንዲመጣ ሠርቷል፡፡ ይኽም አመለካከት ላይ የተሠራ ሥራ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ወደ እናት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር እየገቡ መንታፊዎች እና ሙሰኞች መሰናዘሪያ እንዲያጡ የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡ እነርሱ የፈለጉት ጨው እያላሱ ወደእነርሱ አዘቅት እንዲገባ ነበረ፤ ዓላማ አለውና፣ የራሱን ይሰጣል እንጂ የእናቱን መቀነት አይፈታምና ጥርሳቸውን ነከሱበት፡፡ ሙዳየ ምጽዋት እንዳይገለበጥ ምእመናን እና ደጋግ ካህናት አጥር ቅጥር እንዲሆኑ ጥሯል፡፡ ይኽም እሳቤን ለማልማት የተደረገ ልፋት ውጤት ነው፡፡
  ጉምቱ ጉምቱ ሊቃውንት ወንበራቸው እንዳይታጠፍ ተተኪ እንዲወልዱ፣ የአብነት ት/ቤቶቻችን ማኅፀን እንዳይነጥፍ ትውልዱ ኃላፊነት እንዳለበት ሲያስተምር ቆይቷል፡፡ ጥሪውን የሰሙ በገንዘባቸው፣ በጉልበታቸው እና በዕውቀታቸው እየተራዱ ቤተ ክርስቲያናቸው በአግባቡ ለቀጣዩ ትውልድ እንድትተላለፍ እንዲረባረቡ አድርጓል፡፡ በዚኽም መንገድ ብዙዎች ያለቀስቃሽ ሱታፌ እያደረጉ መኾኑ ነጋሪ አያሻውም፡፡ ይኽም የአስተሳሰብ ለውጥ ነው፡፡ ከእንግዲህ ማኅበረ ቅዱሳን በተቋም ደረጃ ኖረም አልኖረ እነርሱ ግን ይቀጥላሉ፡፡
  አንዲት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን ተሐድሶ ያስፈልጋታል እያሉ በላይ በታች የሚያሙለጨልጩትን ሲከላከል፤ ይኽም አስተሳሰብ የሁሉም የቤተ ክርስቲያን ልጆች እንዲሆን ሲለፋ ኖሯል፡፡ ዛሬ በየአጥቢያው ያለው ሕዝበ ክርስቲያን ያለማንም ጉትጎታ ስውር ዓላማ ያላቸውን እየተከታተለ መረጃ ለአበው እያደረሰ ከቅጽረ ቤተ ክርስቲያን እንዲርቁ የሚያደርገው ምንም ዓይነት መዋቅር ሳያስፈልገው ነው፡፡ ይኽም የእሳቤ ለውጥ ነው፡፡
  እነዚኽ እና ሌሎችም ያልተዘረዘሩት ጉዳዮች ለማን ነው ረመጥ የኾኑበት? እሳት በላኝ ማለታቸው ጠበል እንዳየ ጋኔን የመለፍለፍ እንጂ የመፈወስ ምልክት አይደለም፡፡ ይኽንን ሲባል በጎነቱ ያየለውን ማኅበር ባልዋለበት አታውሉት፣ አሸባሪ ቅብጥርሶ አትበሉት ማለት እንጂ በቅንነት አትተቹት ማለት አይደለም፡፡ ጥፋት ሊኖርበት ይችላል ፍጹምነት የለምና፡፡ ይኽም ሲሆን ወይ አባላቱ እርስ በእርስ ተመካክረው (ያውቁበታልና) አለበለዚያም ደግሞ አባቶች የሚያርሙት እንጂ ለያዙኝ ልቀቁኝ የሚበቃ የሚደርስም አይደለም፡፡ እኒያ ተናዳፊዎች ካሉት መኻል ግን በአንዲቱም አይወቀስም፡፡ ነጭ ውሸት ነጭ ነው፣ ዐይንን በጨው ታጥቦ ስቶ ለማሳሳት መነሳት ትውልድን የመግደል ሕልም እንጂ ሌላ መልክ የለውም፡፡
  ማኅበሩ በደንቡ ላይ እንደገለጠው ሀብት ንብረቱ ሁሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንጂ ስሑታኑ እንደሚሉት የግለሰቦች አይደለም፡፡ ደስ ያላለው ቢኖር ሕንጻውን ሊያፈርሰው ይችላል፤ አስተሳሰቡን ግን ምንም ሊያደርገው አይችልም፡፡ ይኽ አስተሳሰብ አሁን እንደ ንጹሕ ዘር በዓለም ተበትኗል፡፡ ለማጥፋት ከማይቻልበትም ደረጃ ደርሷል፡፡ ተቋሙን ቢያፈርሱት አስተሳሰቡን አያፈርሱትም፡፡ ዘር ሆኗል፣ በዓለም ተበትኗል፣ በእናት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር እየለመለመ ይሄዳል፡፡ እንግዲህ ምኑን ያፈረሱት ይኾን? ማኅበረ ቅዱሳን አስተሳሰብን እንጂ ተቋም ሲገነባ አልኖረምና

  ReplyDelete
 5. እንደዚህ ያስቸገረው ማኅበር የቱ ነው?
  የመልእክቱ መንፈስ ወደ አንድ ማኅበር ያመላከተ ይመስላል….ማኅበረ ቅዱሳንን ይሆን? ማኅበረ ቅዱሳን እንደሆነ እያገለገለ ያለው ከቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መመርያ ነው፡፡
  አሁንም መተዳደርያ ደንቡ እንዲሻሻል ቅዱስ ሲኖዶስ ባዘዘው መሰረት ቅዱስ ሲኖዶሱ በሰየመው ኮሚቴ ታይቶ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ታይቶ…ለማጽደቅ እየጠበቀ ነው፡፡
  ምናልባት ቀዱስነታቸው ይሔንን ጉዳይ አያውቁ ይሆን???

  ReplyDelete
 6. Mk, terror organization elements, have departed to Eritrea to join terrorist that attract Ethiopian gov. The majority of those elements are female. Age between 45 to 65 because most of female elements are old. Kat addicted criminal and sexual predator are unique identity of mk preachers. They have not moral power to engage our church issue. They have spent 989.99 billion Ethiopian birr for gebo to give shermuta papa's to save mk in holy synod. Aba Abraham recived 1.89.69 billion birr gibo to open his shermuta lip to say mk is relevant to our church in the Holy sed meeting.

  ReplyDelete
 7. The trade mark or another secret names of Mk are gin bot seven, save waldeba, Sunday school unity, yetmikettemelash, balwold mahiber, Esat, alshebab, and Eritrea have same objective.

  ReplyDelete
 8. In the Name of the Father, the Son and Holy Spirit, one God Amen
  While i give due respect to our Father His Holiness Abune Mathias Patriarch of EOTC, I have reservation as a member of EOTC in what he has been doing recently! Seeing the tranquility in EOTC at least for one , year, many hoped that EOTC got spiritual leader that will steer to the right direction! But after, group of clergy opposed the reform of church management in Addis Ababa and the ruling party idologues failure to see the difference between አከራሪነተት ና አጥበባቂነት which might be a result of marxist view hangover and protestant apologetic within the party, Our Father is taking a stand that will eventually weaken EOTC by leaving the educated sector as a pray for Tedaiso ( Abba selam and dejebirhan happy about it) and other protestant denominations.


  There is consensus the development plan of our government minus corruption and pur peace should continue so that we shall reach middle income countries as the recent discussion of higher education institution revealed. Hence, the government shall make sure that EOTC memebers and youth are not disaffected by unpopular moves in EOTC! so that all of us are on board to make development of Ethiopia a reality!

  Amen~

  ReplyDelete
 9. May God ricly bless you.Very good statement

  ReplyDelete
 10. ለመሔድ የተዘጋጀ ሰው በተደጋጋሚ ስለጥፋት ያወራል ይባላል......
  ለመሆኑ መቼ የሠራችሁት ጥናት ነው እንደዚህ በሚሊዮን የሚቆጠር አሀዝ ያስቀመጣችሁት .....
  ነው ወይስ የእናንተ የተሐድሶዎች ቁጥር ነው...?????!!!!

  ReplyDelete