Wednesday, October 8, 2014

‹ሕግና ሥርዓት የማይቆጣጠረው ማኅበር ጽንፈኛና አሸባሪ የመሆን ዕድሉ የሰፋ ነው››

ምንጭ፡-http://www.ethiopianreporter.com
-በአድባራትና ገዳማት የመልካም አስተዳደር እጦት መንገሡ ተገለጸ
- ባለፉት አሥርት ዓመታት የምዕመናን ቁጥር ቀንሷል ተብሏል

ቤተ ክርስቲያን ግልጽ የሆነ መዋቅር ያላት ቢሆንም በቤተ ክርስቲያን ስም የሚደራጁ ማኅበራት፣ ከመዋቅራዊ ቁጥጥር ውጭ በመንቀሳቀስ ሀብትና ንብረት ያከማቹና እያከማቹ በመሆናቸው፣ ሕግና ሥርዓት የማይቆጣጠራቸው ከሆነ አሸባሪ የመሆን ዕድላቸው የሰፋ መሆኑን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አስታወቁ፡፡ 
ፓትርያርኩ ይህንን ያስታወቁት ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልፀግ›› በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 27 እስከ መስከረም 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት መስብሰቢያ አዳራሽ የተጀመረውን ጉባዔ በከፈቱበት ወቅት ነው፡፡ 
በቤተ ክርስቲያን ስም የሚንቀሳቀሱ ማኅበራት ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም ከቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ ቁጥጥር ውጭ የሚንቀሳቀስ ሀብትና ንብረት ማካበት የተከለከለና በከባድ ወንጀል የሚያስጠይቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ይህ ድርጊት እየተስፋፋ መሆኑን የጠቆሙት ፓትርያርኩ፣ እየታየ ያለው የማኅበራት ዝንባሌ ሀብት ማካበት፣ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ የተፈቀደውን ‹‹አሥራት በኩራት›› ለራሳቸው መሰብሰብ፣ ከቤተ ክርስቲያን ዕውቅና ውጪ የአገር ውስጥና የውጭ ሥራዎችን በሌላቸው ሥልጣን እየሠሩ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ 

ፓትርያርኩ እንዳብራሩት፣ ማኅበራቱ በሰበሰቡት ሕገወጥ ሀብት አባቶችን ይከፋፍላሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን ያሾማሉ፣ ያሽራሉ፡፡ እነሱ የሚፈልጉትን የማይፈጽሙትን እያስፈራሩ በመሆናቸው፣ አካሄዳቸው ለቤተ ክርስቲያኗ ጥንካሬና ህልውና ፍጹም አደጋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 
በቤተ ክርስቲያን ስም ያለአግባብ ሀብትና ንብረት ያካበተ ማንኛውም ኃይል ባስፈለገ ጊዜ እንቢተኛ በመሆን ቤተ ክርስቲያንን ሊከፋፍል ስለሚችልና በዓለም ላይ ሃይማኖትን ሽፋን በማድረግ ንፁኃንን እየጎዳ ያለውን ትዕይንት ሊያስከትል ስለሚችል፣ ሁሉም የሃይማኖቱ መሪና ተከታይ መታገልና መቃወም እንዳለበት ፓትርያርኩ አሳስበዋል፡፡ 
ሌላው ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ያነሱት ነጥብ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ቁጥር ባለፉት አሥር ዓመታት ውስጥ መቀነሱን ነው፡፡ ለምሳሌ ያህልም በአዲስ አበባ ሰባት በመቶ፣ በኦሮሚያ አሥር በመቶና በደቡብ 7.8 በመቶ የቀነሰ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ የተጠቀሰው ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አለመሆኑን የገለጹት ፓትርያርኩ፣ የምዕመናኑ ቁጥር መቀነስ በአሉታዊ ጎኑ ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ለውጥ እንደሚያስከትል ጠቁመዋል፡፡ ‹‹ሃይማኖታዊ ተልዕኮአችንን መሠረት አድርገን ብንመለከት ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር የምናቀርበው ሕዝብ እያጣን መሆኑን ያሳያል፤›› ብለዋል፡፡ ምዕመናን ሲቀንሱ የቤተ ክርስቲያን ሀብት እየቀነሰ ስለሚሄድም፣ የሚዘጉ አብያተ ቤተ ክርስቲያናትም እየበዙ እንደሚሃዱ አክለዋል፡፡ 
የቤተ ክርስቲያንና ጥንታዊ እሴቶችም በአገር ደረጃ የነበራቸው ጠቀሜታ እየቀነሰ ከሄደ፣ የሃይማኖቱና የአገሪቱ መሠረታዊና ማኅበራዊ እሴቶች እንደሚጎዱ የጠቆሙት ፓትርያርኩ ባህሉ ከተጎዳ ጭካኔ፣ ስግብግብነት፣ ስንፍናና ወንጀል እንደሚበዙ ገልጸዋል፡፡ ፈሪኃ እግዚአብሔር ከመቀነሱና ከመጥፋቱም በተጨማሪ የትውልዱ ሥነ ምግባር ተጎድቶ የተለየ አደጋ እንደሚያስከትልም አክለዋል፡፡ 
አንዳንድ ሰዎች ችግሮችን ግልጽ በማድረግ ውይይት ለማድረግ ሲጠየቁ፣ ‹‹ሌሎች ሃይማኖቶች በእኛ ላይ ሊዘባበቱ ይችላሉና ዝም ይሻላል ብለው ይመክራሉ፤›› ያሉት ፓትርያርኩ፣ ዝም ማለት በመመካከር ሊገኝ የሚችለውን መፍትሔ እንደሚያሳጣ፣ ለምዕመናንና ለሕዝብ የሚሰጠው የተሻሻለ አገልግሎት እንዳይኖር እንደሚያደርግ፣ የቤተ ክርስቲያኗ አስተዳደራዊ ሥራ በዘመኑ ሥልት እንዳይመራና ሃይማኖቱ እንዳይስፋፋ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ በማከልም በዚህ ዘመን ማናቸውም የሚደረግ ነገር ሁሉ ለሕዝብ ያልተደበቀና ምዕመናን በየቀኑ እያዩት ያለ ጉዳይ በመሆኑ፣ ‹‹ዝም እንድንል የሚመክሩን የቤተ ክርስቲያኗን መሻሻልና መጠናከር የማይፈልጉ ወይም የችግሩን አሳሳቢነት ያልተረዱ ናቸው፤›› ብለዋል፡፡ 
በአድባራት፣ በገዳማትና በቤተ ክህነት ጭምር ብልሹ አሠራር መስፈኑን የሚያሳይ በሁለት ሳምንት ብቻ ከአምስት በላይ ከሚሆኑ አድባራትና ገዳማት የተውጣጡ ምዕመናንና ካህናት በሠልፍ ወደሳቸው መምጣታቸው ማሳያ መሆናቸውን የተናገሩት ፓትርያርኩ፣ መደለያ (ጉቦ) በመስጠት ፍትሕ እንዲጓደል ማድረግ፣ በዘር፣ በአካባቢ በመደራጀት ንፁኃንን መበደልና ያልደከሙበትን ሀብት ያለአግባብ ማባከን ትምህርተ ወንጌልን የሚፃረር ተግባር መፈጸም በመሆኑ፣ ሁሉም ሊዋጋው የሚገባ ተግባር መሆኑን አሳስበዋል፡፡ 
በቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ኃላፊነት ተጠቅመው ለራሳቸው ጥቅም የሚሯሯጡ አንዳንድ ሰዎች መኖራቸውን የገለጹት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በአንዳንድ ቦታ ብቻ ሳይሆን በመዋቅር ውስጥ እንደ ሰንሰለት ተያይዘው ለራሳቸው ጥቅም የሚሠሩ ግለሰቦች መበራከታቸው፣ የላቀ መንፈሳዊ ተግባር ለሚጠብቁ ምዕመናን ክፉኛ የመንፈስ ስብራት እየደረሰባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ይህንንና ሌሎች ችግሮችንም ከምዕመናኑ ጋር በመተባበር በተለይ ከቤተ ክርስቲያኗ አገልጋዮች ጋር ዓመቱን ሙሉ በሚኖረው ውይይትና ምክክር ችግሩ ሊፈታ እንደሚችል ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡ 
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ስለማኅበራት በጎ ያልሆነ አሠራርን ሲናገሩ ‹‹ማኅበራት›› እያሉ በወል ስም ከመጥራት ባለፈ ሙሉ ስም ባይጠቅሱም፣ ከገዳማትና ከአድባራት የተወከሉ አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች ግን ሕንፃውን ጭምር እየገለጹ ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑን በመጥቀስ ዕርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኗ ማንኛውም ገቢ እንደ ገንዘብ ሚኒስቴር በአንድ ቋት ሆኖ በቅዱስ ሲኖዶስ ኃላፊነት እንዲመራ ጠይቀዋል፡፡ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ይቅርታ ጠይቀው ወደ ቀድሞ ቤታቸው እንዲመለሱም እንዲሁ ጠይቀዋል፡፡

24 comments:

 1. Who is abay Selma? The group who are making the white truth black. The group who are against the truth . Aba Selma no one can hear you. You are the father of false.

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሊበላኝ የፈለገን አሞራ ሲዞረኝ ነው የማውቀው አለ አሉ፡፡ በእውኑ ኢህአዴግ በራሱ ሄደ አልሆንልህ አለው ከዚህ በፊትም ከሃድያንንና ለሆዳቸው ያደሩ መነኮሳትና አስተዳዳሪ ነን የሚሉትን አደራጅቶ በስብሰባ ስለማህበረ ቅዱሳን ያለሆነ ነገር አስወራ አልሆን አለው፡፡ ሲኖዶስ ውስጥም ገብቶ በፓትርያርኩ በኩል ለመበጥበጥ ሞከረ አልሆን አለው፡፡ አሁን ደግሞ አደራጅቶ ባሰባሰባቸው የገዳማትና አድባራት ተወካዮች ነን በሚሉ ምርጫ 2007ት ላይ ማህበረ ቅዱሳን መሰረቱ እስከታች ድረስ በመሆኑ እሱን ለመተናኮል ተሰብስበው ተራ በሆነ ውንጀላ ሲወያዬ ታይተዋል፡፡ ትላንትና ስለ ማተብ ሰው እውነተኛ እምነቱን ሲገልጥ እነሱ ዝም ብለው በማይገባ ለሰው ግራ ቢያጋባ ነገር ሲዶልቱ ይታያሉ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ የሰጠውንና እንዲሰራ የተፈቀደለትን ማህበር አንድ ፓትርያሪክ ወንበዴዎችን ሰብስበው አልባሌ ነገር መነጋገራቸው ምን ያክል ህገወት ስራ ፓትርያሪኩ እየሰሩ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ይህ አሰራራቸው መንግስት እጁን ማስገባት ያቃተውን እሳቸው እና ግብረ አበሮቻቸው በማህበሩ ላይ በመዶለት ላይ ይገኛሉ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን አካሄዳቸውን ዝም ብሎ እንደማያልፈው ተስፋ አለኝ፡፡ ኢህአዴግነታቸውን ያስመሰከሩ ታላቅ ፓፓስ ናቸው፡፡ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ እርምጃ ሲወስድ ፓትርያሪኩ ደግሞ በማህበሩ ላይ ከወረበሎች በሚቀርብ አሉባልታ እርምጃ እንዲወሰድ መወያየታቸውና መፈለጋቸው ምንም ልዩ አያደርጋቸውም፡፡ ሲኖዶስ የሰጠውን መመሪያ ልክ እየተሰራ አይደለም ካለም መከልከል ያለበት ሲኖዶስ እንጂ አዲሱ የአመራርና የሂሳብ አሰራር ተግባራዊ እንዳሆን ከሚታገሉ አስተዳዳሪዎች ጋር ተወያየሁ ማለቱ ለፓትርያሪኩ ከድጥ ወደ ማጡ መሆኑን ልብ ሊሉት ይገባል፡፡ ነገ ተጠያቂ ሆነው ጸጸት ውስጥ ከሚወድቁ ቆም ብለው አስበው ከድርጊትዎ ቢታቀቡ መልካም ነው፡፡ ፓትርያሪኩ እራሳቸውን ለማዳን ማህበሩን ማስገደል ነው አላማቸው ፡፡ ሃዋርያት ግን ቅዱሳን ግን እንደዚህ ሳይሆን እራሳቸው ነው መስዋእት የሆኑት፡፡ ረ

   Delete
  2. Aba selama is a blog that expose the truth.
   E.g. Most of the church in addis has built a school, but no one from the poor family can afford the fee so why you named it false blog.

   Delete
  3. "ye ayet miskir denbit " alu.... hey u! u better 2 b shut up u don't know about any truth. U know wht! this blog its not only false, It is z most evil blog I ever seen.

   Delete
 2. wow wow wow, so great and blessed ideology. we are prodding of our true church leader. I never seen, kind of this strong message from our Orthodox Church leader...........Our Lord God turning his face to Tewahedo church members.... Thanks our God..............Everybody must obey church rule and law......no no no more private asset for church leaders................Menokossat habet nebert yelachew , habetachew ye Egizeaberher kal ena memenanau becha newu..............

  ReplyDelete
 3. የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያት ትክክለኛ ዉሳኔ ደስ ብሎናል።ለምጠብቃቸውም ፈተና እግዚአብሄር እንድጠብቃቸው የወላዲት አምላክ ምልጃና ጸሎት አይለያቸው በማለት እንጸልያለን። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስም ከህዝቡ በህገ ወጥ መንገድ እኛ ብቻ ነን ለቤተ ክርስቲያን የቆምን እያሉ ከህገ ቤተ ክርስቲያን ዉጩ ሀብት ንብረት ያካበቱ ማህበራትና ጳጳሳት መነኮሳት ነብረታቸው በህግ ለቅድሰት ቤተ ክርስቲያናችን መመለስና መወረስት አለበት እንላለን። የእዚአብሄርም ቃል ሀብት ንብረት ለራሳችሁ በምድር አታከማቹ በማለት ያግዳል። ወይም አለማዊ ነጋዴ መሆን ካለበዚያ እንደ ቅዱስ ቃሉ መኖር፤ ህዝበ ክርስትያኑን በንጽህና መመራት። ቅድስት ቤተ ከርስትያናችን አንድት ናት።

  ReplyDelete
 4. Mk yesytan mahber.lemen abune matiyasen atawegzwachewom???? Mawgez endehone ye mahber erkusan(mk) sira new awgzwachew.wef awgzoch

  ReplyDelete
 5. mahibere kidusan yesirawun yaggnal...be betekiristan yetedebeke zerafi budin new...yemitechutin sim yemiatefa...yemiarimutin yemikes negade sibisib new...amilak yiferdal!!

  ReplyDelete
 6. Aba Selma no one can hear you. You are the father of false.

  ReplyDelete
 7. Mahibere Kidusan has only brought good things to the faith, unlike Aba Selama and other tedahiso who are shifting our faith towards penete.

  ReplyDelete
 8. kkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkkk...........wey maber kedusan yet yihon megibiyachihu
  demo ketemari dabo eyezerefachihu hita behinta tehonalachihu....
  kkkkkkkkkkkkkkkkk RIP

  ReplyDelete
  Replies
  1. ምንም ደስ የሚያሰኝ ነገር አይደለም:: ደስታ ከተሰማን ደግሞ ራሳችንን አንመርምር:: አንድም ማህበር የዚህን ማህበር ቅንታብዉን ሰራ የሰራን የለንም:: ቤተክርስትያኗም ብትሆን ዛሬ ያሏትን የምዐመን ቁጥር ሊኖራት የቻለው በዚህ ማህበር ሰራ ነዉ:: አኔም ይህችን ቤተክርስትያን ያወክዋት በዚህ ማህበር ሰር ሆኘ ነዉ:: ሰዉ ነዉና የሚያስተዳደረዉ ስህተቶች አንክዋን ቢኖሩ ፍርድና በቀል ከአግዚአብሔር ነዉ አንጂ ማንኛችንም ስልጣን አልተሰጠንም:: ያለአባት ያለ አረኛ የሚመራ መንጋ ለማፍራት አና ቤተክርስትያኗን ለማፍረስ ካልሆን በቀር አንዲህ ዓይነት ዜና ለአንድ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን አያስደስትም::

   Delete
  2. Shut a heel up,You guys are the one &the only one
   To take the responsibility of this mess,as u keep doing what you doing right now since the early 80s until this paired of time they made a lot of Chios,Mess leading the church members,false teachings not only that you guys you don't have Christianity mind and heart,all of you are rot,you doing a lot of bad stuff,but still not to let to surrender your life,u got a chance to wake up and breath,PS don't be foolish this is your day don't hesitate &look what you doing in the past it is sin,&shem how long you live in this world?why you doing all this years?
   Now this is the time to make a difference PS stop standing on their side,every body knows about them the day is so close to buried them,the shovel is up the ground is dig to close the door and to wash out from that church once for last,they lost the battle grounds every where this arrogant selfish venomous.l can't wait to watch them there endings'.soon.

   Delete
 9. ሊበላኝ የፈለገን አሞራ ሲዞረኝ ነው የማውቀው አለ አሉ፡፡ በእውኑ ኢህአዴግ በራሱ ሄደ አልሆንልህ አለው ከዚህ በፊትም ከሃድያንንና ለሆዳቸው ያደሩ መነኮሳትና አስተዳዳሪ ነን የሚሉትን አደራጅቶ በስብሰባ ስለማህበረ ቅዱሳን ያለሆነ ነገር አስወራ አልሆን አለው፡፡ ሲኖዶስ ውስጥም ገብቶ በፓትርያርኩ በኩል ለመበጥበጥ ሞከረ አልሆን አለው፡፡ አሁን ደግሞ አደራጅቶ ባሰባሰባቸው የገዳማትና አድባራት ተወካዮች ነን በሚሉ ምርጫ 2007ት ላይ ማህበረ ቅዱሳን መሰረቱ እስከታች ድረስ በመሆኑ እሱን ለመተናኮል ተሰብስበው ተራ በሆነ ውንጀላ ሲወያዬ ታይተዋል፡፡ ትላንትና ስለ ማተብ ሰው እውነተኛ እምነቱን ሲገልጥ እነሱ ዝም ብለው በማይገባ ለሰው ግራ ቢያጋባ ነገር ሲዶልቱ ይታያሉ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ የሰጠውንና እንዲሰራ የተፈቀደለትን ማህበር አንድ ፓትርያሪክ ወንበዴዎችን ሰብስበው አልባሌ ነገር መነጋገራቸው ምን ያክል ህገወት ስራ ፓትርያሪኩ እየሰሩ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ይህ አሰራራቸው መንግስት እጁን ማስገባት ያቃተውን እሳቸው እና ግብረ አበሮቻቸው በማህበሩ ላይ በመዶለት ላይ ይገኛሉ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን አካሄዳቸውን ዝም ብሎ እንደማያልፈው ተስፋ አለኝ፡፡ ኢህአዴግነታቸውን ያስመሰከሩ ታላቅ ፓፓስ ናቸው፡፡ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ እርምጃ ሲወስድ ፓትርያሪኩ ደግሞ በማህበሩ ላይ ከወረበሎች በሚቀርብ አሉባልታ እርምጃ እንዲወሰድ መወያየታቸውና መፈለጋቸው ምንም ልዩ አያደርጋቸውም፡፡ ሲኖዶስ የሰጠውን መመሪያ ልክ እየተሰራ አይደለም ካለም መከልከል ያለበት ሲኖዶስ እንጂ አዲሱ የአመራርና የሂሳብ አሰራር ተግባራዊ እንዳሆን ከሚታገሉ አስተዳዳሪዎች ጋር ተወያየሁ ማለቱ ለፓትርያሪኩ ከድጥ ወደ ማጡ መሆኑን ልብ ሊሉት ይገባል፡፡ ነገ ተጠያቂ ሆነው ጸጸት ውስጥ ከሚወድቁ ቆም ብለው አስበው ከድርጊትዎ ቢታቀቡ መልካም ነው፡፡ ፓትርያሪኩ እራሳቸውን ለማዳን ማህበሩን ማስገደል ነው አላማቸው ፡፡ ሃዋርያት ግን ቅዱሳን ግን እንደዚህ ሳይሆን እራሳቸው ነው መስዋእት የሆኑት

  ReplyDelete
  Replies
  1. ሊበላኝ የፈለገን አሞራ ሲዞረኝ ነው የማውቀው አለ አሉ፡፡ በእውኑ ኢህአዴግ በራሱ ሄደ አልሆንልህ አለው ከዚህ በፊትም ከሃድያንንና ለሆዳቸው ያደሩ መነኮሳትና አስተዳዳሪ ነን የሚሉትን አደራጅቶ በስብሰባ ስለማህበረ ቅዱሳን ያለሆነ ነገር አስወራ አልሆን አለው፡፡ ሲኖዶስ ውስጥም ገብቶ በፓትርያርኩ በኩል ለመበጥበጥ ሞከረ አልሆን አለው፡፡ አሁን ደግሞ አደራጅቶ ባሰባሰባቸው የገዳማትና አድባራት ተወካዮች ነን በሚሉ ምርጫ 2007ት ላይ ማህበረ ቅዱሳን መሰረቱ እስከታች ድረስ በመሆኑ እሱን ለመተናኮል ተሰብስበው ተራ በሆነ ውንጀላ ሲወያዬ ታይተዋል፡፡ ትላንትና ስለ ማተብ ሰው እውነተኛ እምነቱን ሲገልጥ እነሱ ዝም ብለው በማይገባ ለሰው ግራ ቢያጋባ ነገር ሲዶልቱ ይታያሉ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ የሰጠውንና እንዲሰራ የተፈቀደለትን ማህበር አንድ ፓትርያሪክ ወንበዴዎችን ሰብስበው አልባሌ ነገር መነጋገራቸው ምን ያክል ህገወት ስራ ፓትርያሪኩ እየሰሩ እንደሆነ ያሳያል፡፡ ይህ አሰራራቸው መንግስት እጁን ማስገባት ያቃተውን እሳቸው እና ግብረ አበሮቻቸው በማህበሩ ላይ በመዶለት ላይ ይገኛሉ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን አካሄዳቸውን ዝም ብሎ እንደማያልፈው ተስፋ አለኝ፡፡ ኢህአዴግነታቸውን ያስመሰከሩ ታላቅ ፓፓስ ናቸው፡፡ መንግስት በጋዜጠኞች ላይ እርምጃ ሲወስድ ፓትርያሪኩ ደግሞ በማህበሩ ላይ ከወረበሎች በሚቀርብ አሉባልታ እርምጃ እንዲወሰድ መወያየታቸውና መፈለጋቸው ምንም ልዩ አያደርጋቸውም፡፡ ሲኖዶስ የሰጠውን መመሪያ ልክ እየተሰራ አይደለም ካለም መከልከል ያለበት ሲኖዶስ እንጂ አዲሱ የአመራርና የሂሳብ አሰራር ተግባራዊ እንዳሆን ከሚታገሉ አስተዳዳሪዎች ጋር ተወያየሁ ማለቱ ለፓትርያሪኩ ከድጥ ወደ ማጡ መሆኑን ልብ ሊሉት ይገባል፡፡ ነገ ተጠያቂ ሆነው ጸጸት ውስጥ ከሚወድቁ ቆም ብለው አስበው ከድርጊትዎ ቢታቀቡ መልካም ነው፡፡ ፓትርያሪኩ እራሳቸውን ለማዳን ማህበሩን ማስገደል ነው አላማቸው ፡፡ ሃዋርያት ግን ቅዱሳን ግን እንደዚህ ሳይሆን እራሳቸው ነው መስዋእት የሆኑት

   Delete
 10. I do know who are Aba selma ,where is this absolut false information ,any way GOD Bless our church and Maberekidusan.

  ReplyDelete
 11. God never bless mk.how god can bless the evil mahber???

  ReplyDelete
 12. Leba mahber kalhone lemen hensawon ayasrekbem.Leba leba leba dem afsash mahber ashebari mahber.ahunm egziabher yatfawo.beseferebet mesferita yeseferal.sere
  wongel.sere kirstos.

  ReplyDelete
 13. Think that! the enemy of the church is not only MK. the number one enemies of the our church are the bishops and archbishops. evidence, shows us most of the bishops and archbishops as well as many monks have a lot of money, expensive houses, new brand new cars and so on. that's why the general manager Aba Mattewos stands against his holiness the patriarch
  musegnoch, leboch, nefisegedayoch, Yebezubat betekirstiyan honalech.
  slezih ke patiriariku gon teselfen linadnat ygebal. behig ena bsriat hid weym temera malet tifat aydelm. MK gin alamaw nigdna poletika slehone betekirstiyanit sir lihon ayfelgm.

  ReplyDelete
 14. Mk wedajje ysferachuwo erasers selehone, wedajochwa hulu ye mk degafiwoch yebetekrstiyanena ye Antioch tekawamiwoch nachewo.ye mk abalat bemulu orthodoxawian sayonhu Malawian nachew.

  ReplyDelete
 15. mekotater yenesu sira new mahiberu gin besinodos yesedeke denib alew

  ReplyDelete
 16. kebafew yeketel
  ማኅበረ ቅዱሳን እንዴትስ ተመሠረተ?

  ዘመኑ የኮምዩኒዝም ርዕዮተ ዓለምና አስተሳሰብ የሰፈነበት፤ ስመ እግዚአብሔርን መጥራት አስቸጋሪ የሆነበትና ወደ ቤተ እግዚአብሔር መሔድ እንደ ኋላቀርነት የሚቆጠርበት ዘመን ነበር 1977 ዓ.ም፡፡

  በተለይም በየከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ /ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች/ በሚገኙ ተማሪዎች ዘንድ ቃለ እግዚአብሔርን በግልጽ መነጋገርም ሆነ መሰማት የማይታሰብበት ወቅት ነው፡፡

  ቀደም ባሉት ጊዜያት በተለይም በንጉሠ ነገሥት ዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆች እንዲያስተምሩ ከምዕራባውያኑ ሀገሮች መጥተው የነበሩ ሚሲዮናውያን የኑፋቄ ትምህርታቸውን ያሠራጩ የነበረውም በእነዚሁ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነው፡፡

  በዚህ ሁኔታ ትውልዱ በየአቅጣጫው በሚሲዮናውያኑ የኑፋቄ ትምህርት እንዲሁም በኮምዩኒዝም ርዕተ ዓለምና አስተሳሰብ እየተነጠቀ ከኦርቶዶከሳዊት ተዋሕዶ እምነት የኮበለለበት ከቤተክርስቲያን የራቀበት ዘመን ነበር፡፡

  በዚህ ጊዜ ነው፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ዋናው ግቢ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ይከታተሉ የነበሩ አምስት ወጣቶች ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ በቅዱስ ገብርኤል ስም ተሰባስበው ጽዋ መጠጣት የጀመሩት፡፡ ይህ መንፈሳዊ እንቅስቀሴ በዚሁ ተወስኖ አልቀረም፡፡ በየሳምንቱ እሑድ በመንበረ ­ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ቤተክርስቲያን ግቢ በመጠለያ ሥር እየተሰባሰቡ በተደራጀ መልክ ባይሆንም መንፈሳዊ ትምህርት ይማሩ ጀመር፡፡ ከዚያም በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ ትምህርት መማር ቀጠሉ፡፡

  እንዲህ የተጀመረው መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በሌሎች ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚገኙ የቤተክርስቲያን ልጆች ዘንድ የተዳረሰበት አጋጣሚና ሁኔታ የተፈጠረው ደግሞ በዚሁ በ1977 ዓ.ም ነው፡፡ በወቅቱ በነበረው የመንግሥት ሠፈራ ፕሮግራም በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በሙሉ በመንደር ምሥረታና መልሶ ማቋቋም ዘመቻ ወደ ጋምቤላ፣ መተከል እና ፓ­ዌ እንዲዘምቱ ተደረገ፡፡ በዘመቻው ወቅት ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየመጡ የተገናኙት የቤተክርስቲያን ልጆች ቃለ እግዚአብሔርን በመማር፣ በማኅበር ጸሎት በማድረግ እና ስለቤተክርስቲያን ጉዳይ በመወያየት ጊዜውን ተጠቀሙበት፡፡

  በዚህ ዓይነት የተጀመረው እንቅስቃሴ ከዘመቻው መልስ በ1978 ዓ.ም ተጠናከረ፡፡ ውስን የነበረው የተማሪዎች ቁጥርም ጨመረ፡፡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ፣ አምስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ ግቢዎች እስከ አርባ የሚደርሱ ተማሪዎች በምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ማኅበር አዳራሽ እየተገኙ ትምህርተ ወንጌል ይማሩ ነበር፡፡ የተማሪዎቹን ዓላማና ጥረት የተገነዘቡ አባቶች መምህራነ ወንጌልም በቅርብ ሆነው እየተከታተሉ ሲያስተምሯቸው ቆይተዋል፡፡

  በቀጣዩ ዓመት ከ1979 ዓ.ም እስከ 1980 ዓ.ም ድረስ ተማሪዎቹ በተምሮ ማስተማር ማኅበር አደራሽ ከሚከታተሉት መንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር ጋር ይህ መንፈሳዊ እን ቅስቃሴ ተጠናክሮ በስፋት የሚቀጥልበትን መንገድ ይወያዩ ነበር፡፡ በወቅቱ ትኩረት ተሰጥቶት ውይይት ይደረግበት የነበረው ዐቢይ ጉዳይ ከመካከላቸው ሰባኪ ወንጌል ማፍራት ነበር፡፡ ለዚህም በተለይ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከመግባታቸው በፊት በቤተክርስቲያን አገልግሎት እየተሳተፉ በሰንበት ትምህርት ቤት ያደጉና በመጠኑም ቢሆን ልምድ ያላቸውን ተማሪዎች እንዲያስተምሩ ማድረግ አንድ መፍትሔ ነው፡፡ ለዘለቄታው ግን ከተማሪዎቹ መካከል በወቅቱ ሸዋ ሀገረ ስብከት ዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የካህናት ማሠልጠኛ ገብተው እንዲሠለጥኑ ማድረግ የታመነበት መሠረታዊ ጉዳይ ሆነ፡፡

  ይህንኑ ሐሳብ ተግባራዊ ለማድረግ፤ አስቀድመው በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው ስለስብከተ ወንጌል ሥልጠና የወሰዱ፤ በወቅቱ የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እና የካህናት ማሠልጠኛው የበላይ ጠባቂ ከነበሩት ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ጋር ይቀራረቡ በነበሩ ተማሪዎች አማካኝነት ግንኙነት ተደረገ፡፡

  እንዲሁም በ1980 ዓ.ም አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አራት ኪሎ ግቢ ትምህርታቸውን ሊከታተሉ ከገቡት መካከል እስከ ሃምሣ የሚደርሱ ተማሪዎች በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብር ኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት ተሰብስበው ይማሩ ጀመር፡፡ በዚሁ ዓመት በኮተቤ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎችም ተመሳሳይ መንፈሳዊ መርሐ ግብር ጀምረው ነበር፡፡

  በዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርታቸውን አጠናቀው በ1980 ዓ.ም ከተመረቁት ተማሪዎች ውስጥ በግቢ ቆይታቸው በቤተክርስቲያን ተሰባስበው መንፈሳዊ ትምህርት ሲማሩ የነበሩት የቤተክርስቲያን ልጆችም ለመጀመሪያ ጊዜ ተመረቁ፡፡ የምረቃው መርሐ ግብር የተካኼደው በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ተምሮ ማስተማር ማኅበር አዳራሽ ነው፡፡ በበዓሉ ላይ ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮሰ ካልዕ ጋር ሌሎችም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተው፤ ተመራቂዎቹ ተማሪዎች ለቤተክርስቲያን አገልግሎት እንዲተጉ አስተምረው ባርከው መርቀዋል፡፡

  ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ጋር በተደረገው ግንኙነት መሠረት በዚሁ ዓመት ከተመረቁት መካከል ዐሥራ ሁለት ተመራቂ የቤተክርስቲያን ልጆች በዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው በክረምቱ ወራት፤ ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዓተ እምነት፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ትውፊት እንዲሁም የስብከት ዘዴ ሲማሩ ከረሙ፡፡ ሥልጠናውን የተከታተሉት ተማሪዎች ተመርቀው ከገዳሙ ሲሔዱ፤ ብፁዕ አቡነ ጎርጎር ዮሰ ካልዕ፤ «ከዚህ ስትወጡ ተበትናችሁ እንዳትቀሩ አደራ፤ ስለ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎታችሁ እየተገናኛችሁ መወያያ ይሆናችሁ ዘንድ መሰባሰቢያ አብጁ» በማለት፤ ተመራቂዎቹ በጽዋ ማኅበር ስም በመሰባሰብ፣ በሚሔዱበት ቦታ ሁሉ ስብከተ ወንጌልን እንዲያስፋፉ፣ በየዓመቱም በዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እየተገናኙ ስለ ዓመቱ የአገልግሎት ቆይታቸው ሪፖርት እንዲያቀርቡና እንዲወያዩ አሳስበው አሰናበቷቸው፡፡ ተመራቂዎቹ የቤተክርስቲያን ልጆች የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕን አባታዊ ምክርና መመሪያ አልዘነጉም፡፡ ወደ አዲስ አበባ እንደተመለሱ «ማኅበረ ማርያም» በሚል ስያሜ የጽዋ ማኅበር መሠረቱ፡፡ በአዲስ አበባና በዙሪያው በሚገኙ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በዓውደ ምሕረትና ሌሎች መርሐ ግብሮች ቃለ እግዚአብሔርን እያስተማሩ በየወሩ እየተገናኙ ስለአገልግሎታቸው ይወያዩ ነበር፡፡ በዓመቱ መጨረሻም በዝዋይ ተገኝተው ሪፖርት አድርገዋል፡፡ በ1981 ዓ.ም ክረምት ለሁለተኛ ዙር ሥልጠና በምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ተምሮ ማስተማር ማኅበር እና በግቢ ገብርኤል ዓምደ ሃይማኖት አዳራሾች ይማሩ ከነበሩት መካከል ዐሥራ ሁለት ተማሪዎች ተወክለው በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ በአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ አማካኝነት ሥልጠና ተሰጠቷቸዋል፡፡

  ReplyDelete
 17. ke balfew yeketele

  በዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች መንፈ ሳዊ እንቅስቃሴው እየተጠናከረ ቀጥሎ በተለይም በ1982 ዓ.ም በብዙ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ተዳረሰ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ፋኩልቲዎች፤ በጥቁር አንበሳ ሕክምና ፋኩልቲ፣ በልደታ ሕንፃ ኮሌጅ፣ በደ ብረ ዘይት እንስሳት ሕክምና ፋኩልቲ እንዲሁም በጅማ ጤና ሳይንስ፣ በዓለ ማያ ዩኒቨርሲቲ፣ በወቅቱ በአሥመራ ዩኒቨርሲቲ ወዘተ ተስፋፋ፡፡ በዓመቱ የክረምት ወራት ከየዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጆቹ የተውጣጡ አርባ አምስት ተማሪዎች ዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው ሥልጠና ወስደዋል፡፡ በሥል ጠናው በአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ከሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ አርባ የሚደርሱ ተማሪዎችም ተሳትፈዋል፡፡ በዚህ ሥልጠና ወቅት ነበር ባልታሰበ ሁኔታ ታላቅ ኃዘን የደረሰው፤ ብፁዕ አቡነ ጎርጎር ዮስ ካልዕ በድንገተኛ የመኪና አደጋ ነዐረፉ፡፡

  በ1983 ዓ.ም በወቅቱ በነበረው መንግሥት በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች በሙሉ ወታደራዊ ሥልጠና እንዲወስዱ ሲታዘዝ፤ በሀገሪቱ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲ፣ ኮሌጆችና ተቋማት የሚማሩ አሥራ አንድ ሺሕ ያህል ተማሪዎች በብላቴ አየር ወለድ ማሠልጠኛ እንዲገቡ ተደረገ፡፡ ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ በዩኒቨርሲቲና ኮሌጆቹ ግቢዎች ተጀምሮ ቀስ በቀስ የተስፋፋው መንፈሳዊ እንቅስቃሴም የበለጠ የሰፋበትና የተጠናከረበት ጊዜ ሆነ፡፡ ተማሪዎቹ ቀን ከሚሰጣቸው ወታደራዊ ሥልጠና መልስ ማታ ማታ እየተገናኙ መንፈሳዊ ትምህርት መማር በጋራ መጸለይ ጀመሩ፡፡ መንፈሳዊ ትምህርቱና ጸሎቱ በኅብረት የሚካኼደው በወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፑ በሚገኝ በሌላ አገልግሎት ያልተያዘ አዳራሽ /ኬስፖን/ ውስጥ ነበር፡፡ ትም ህርቱ ከዚህ ቀደም በዝዋይ ካህናት ማሠልጠኛ ገብተው በሠለጠኑ እና ሌሎችም በቤተክርስቲያን ትምህርትና አገልግሎት በቆዩ ተማሪዎች እየተሰጠ በየቀኑ ምሽት መርሐ ግብሩ ሳይታጎል ለሁለት ወራት ቀጥሏል፡፡ በዚህ ጉባኤ እስከ አምስት መቶ የሚደርሱ ተማሪዎች ያለማቋረጥ ይከታተሉ ነበር፡፡

  በወቅቱ በብላቴ አየር ወለድ ማሠልጠኛ ካምፕ ለወታደራዊ ሥልጠና የገቡት ተማሪዎች ማታ ማታ እየተ ሰበሰቡ በአንድነት ከሚያደርጉት ጸሎት እና ከሚማሩት የቤተክርስቲያን ትምህርት በተጨማሪ፤ በአካባቢው ወደሚገኘው ብላቴ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን እየተደበቁም እያስፈቀዱም በመሔድ ምስጢራተ ቤተክርስቲያንን ይሳተፉ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰባሰቡት ተማሪዎች ኅብ ረት እየጠነከረ መንፈሳዊ እንቅስቃሴው እየሰፋ መጣ፡፡ እነዚህ የቤተክርስቲያን ልጆች በወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፕ በነበሩበት ጊዜ የ1983 ዓ.ም የእመቤታችንን የልደት በዓል /ግንቦት ልደታ/ ለጸሎትና ለመንፈሳዊው ትምህርት በሚሰበሰቡበት አዳራሽ በደመቀ ሁኔታ አክብረዋል፡፡

  በብላቴ አየር ወለድ ማሠልጠኛ ካምፕ የነበረው የተማሪዎቹ ወታደራዊ ሥልጠና የሁለት ወር ቆይታ በመን ግሥት ለውጥ ምክንያት ሊበተን ግድ ሲሆን፤ ተማሪዎቹ በወታደራዊ ካምፑ ቆይታቸው የነበረው መንፈሳዊ እንቅስቃሴና ኅብረታቸው ዕጣ ፈንታ አሳሰባቸው፡፡ ይህ መንፈሳዊ አንድነት እንዴት መቀጠል እንዳለበት ተነጋገሩ፡፡ ከብዙ ውይይት በኋላም ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ በየዩኒቨርሲቲና ኮሌጆቻቸው ሲመለሱ በቅዱስ ሚካኤል ስም ተሰባስበው ቤተክርስቲያንን ለማገልገል በመስማማት ቃል ገብተው ተለያዩ፡፡

  በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ዕረፍት ዓመታዊ መታሰቢያ ላይ የተገኙ ደቀመዛሙርትና መምህራን ነሐምሌ 22 ቀን 1983 ዓ.ም፤ በወቅቱ የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ የገዳሙና የካህናት ማሠልጠኛው የበላይ ጠባቂ በነበሩበት በብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገብርኤል ሰብሳቢነት ጉባኤ ተደርጎ ነበር፡፡ በጉባኤው ላይ «በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ተምራችሁ በማኅበረ ማርያም የታቀፋችሁ፣ በየቦታው ያላችሁ፣ በገዳሙም የምትኖሩ መነኮሳት እንዳትበታተኑ በአባታችን ስም ማኅበር አቋቁሙ» በማለት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ሐሳብ አቀረቡ፡፡ በሐሳቡ ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ለጊዜው «የዝዋይ ደቀመዛሙርትና መምህራን ማኅበር» በሚል ስያሜ እንዲጠራ ተወስኖ ማኅበር ተመሠረተ፡፡
  ከዚህ ቀደም በ1981 ዓ.ም በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም በተምሮ ማስተማር ማኅበር እና በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት የሚማሩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች ጉባኤ አንድነት በመፍጠር የተጠናከረ እንቅስቃሴ ባያደርግም «ማኅበረ እስጢፋኖስ» የሚባል ማኅበር መሥርተው ነበር፡፡ ከዚያ በኋላም ቢሆን እንቅስቃሴአቸው የተጠናከረ ባይሆንም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕክምና ፋኩልቲ ተማሪዎች «ማኅበረ ሥላሴ» በሚል ስያሜ፤ በሌሎችም ፋኩልቲዎችና ኮሌጆች ግቢዎች የሚገኙ ተማሪዎች በተለያዩ ቅዱሳን ስም በሰየሟቸው ጽዋ ማኅበራት ተሰባስበው ነበር፡፡

  በጥር ወር 1984 ዓ.ም በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ዓምደ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም ጠቅላላ ጉባኤውን ያደረገው «ማኅበረ ሚካኤል» የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ አጽድቆ አመራሩንም መርጧል፡፡ ሆኖም በቅዱሳኑ ስም ማኅበር መሥርተው የተሰባሰቡት አባላት፤ «ዓላማቸው፣ አገልግሎታቸውም ሆነ ታሪካቸው አንድ ነው፡፡ ለምን አንድ ስያሜ ይዘው በአንድነት አይንቀሳቀሱም?» የሚል ሐሳብ በውስጣቸው እየተነሣ በተለያዩ አጋጣሚዎች በጉዳዩ ሲወያዩበት ቆይቷል፡፡

  በዝዋይ ለተመሠረተው ማኅበር ስያሜ ለመስጠት አዲስ አበባ በብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቤት በዚሁ ዓመት በየካቲትና መጋቢት ወራት በተካኼደው ስብሰባ ላይ ሐሳቡ ቀርቦ ውይይት ተደረገበት፡፡ በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል «ሁላችሁም የያዛችሁት አገልግሎት የቅዱሳን ክብር የሚገለጽበት ነው፡፡ ስለዚህ የማኅበራችሁም ስም 'ማኅበረ ቅዱሳን' ይባል፡፡» በማለት ባቀረቡት ሐሳብ መሠረት፤ የ«ማኅበረ ማርያም»፣ «ማኅበረ ሚካኤል» እና «የዝዋይ ደቀመዛሙርትና መምህራን ማኅበር» ተዋሕደው የሁሉም ማኅበራት የጋራ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን ተመሠረተ፡፡

  አባላቱም መንፈሳዊ አገልግሎታቸው የቅድስት ቤተክርስቲያንን ሥርዓትና መዋቅር ጠብቆ በቤተክርስቲያን አስተዳደር ዕውቅና ማግኘት እንዳለበት አምነው፤ «በጠቅላይ ቤትክህነት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ሆነን እናገልግል» በማለት መተዳደሪያ ደንባቸውን ይዘው ወደ መምሪያው ጽ/ቤት ቀረቡ፡፡ በዚህ ዓይነት ማኅበረ ቅዱሳን ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተክርስቲያኒቷ መዋቅር ዕውቅና አግኝቶ ግንቦት 2 ቀን 1982 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተክህነት በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር መደራጀቱ ይፋ ሆነ፡፡

  ReplyDelete