Saturday, October 11, 2014

ማሕሌተ ጽጌ

እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የዘመናት ቀመርና አቆጣጠር ከመስከረም 26- ኅዳር 6 ያለው ጊዜ ‹‹ወርሐ ጽጌ›› በመባል ይታወቃል፡፡ ‹‹ጽጌ›› ማለት ‹‹አበባ›› ማለት ሲሆን በዚህ ወቅት የዱር ዕፀዋት የሚያብቡበት፣ ለዐይን ድንቅ የሆነ ኅብረ ቀለም ያለው የዱር ሳር ልምላሜና ጸደይ የምንመለከትባቸው ወራት ናቸውና በአበባ ጌታችን ኢየሱስን፣ አበባው በተገኘባት  መሬት ድንግል ማርያምን እየመሰሉ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይልቁንም መሪጌቶች ያዜማሉ፤ ይቀኛሉ፤ ይዘምራሉ፤ ማሕሌተ ጽጌና ሰቆቃወ ድንግል የተባለውን እንዲሁም  በእነ ዘርዓያዕቆብ የተደረሰውን መልካ መልክ ሌሊቱን በሙሉ በመደጋገም ያዜሙታል፡፡
ነገር ግን ይህ ‹‹ማሕሌተ ጽጌ›› የተባለው አንስተኛ መጽሐፍ በሊቃውንት ያልታየና ያልተመረመረ ከመሆኑም ባሻገር በፈጣሪና በፍጡራን መካከል ያለውን ልዩነት የማያውቁ እንዲሁም የማርያም ፍቅር አቃጠለን፤ አንገበገበን፤ ያሉ መሪጌቶች የደረሱት አጉል ድርሰት ነው፡፡ከብዙ ጥቂቶቹን
እያነሳን ብንመለከተው ለምሳሌ በዚህ 2007 ዓመት ጥቅምት 2 የሚዜመው እንዲህ ይላል፡- በከመይቤ መጽሐፍ ማዕከል ፈጣሪ ወፍጡራን፣ ለእረፍት ዘኮንኪ ጽላተ ኪዳን ብኪ ይትፌስሁ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ወብኪ ይወጽኡ ኀጥእን እምደይን፡፡ 

ትርጉም፡- መጽሐፍ እንደሚል በፈጣሪና በፍጡራን መካከል መካከለኛ የሆንሺ የኪዳነ ጽላት ማርያም ሆይ በአንቺ የገነት ጻድቃን ደስ ይላቸዋል ኀጥአንም ከደይን ይወጣሉ ማሕለተ ጽጌ

ወብኪ ይወድኡ ኀጥአን እምዲይን
ኀጥአን ከደይን ባንቺ ይወጣሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በሲኦል ለነበሩ ነፍሳተ ሲኦል የምሥራችን ሰብኮ ከሲኦል ያወጣቸው ጌታ ኢየሱስ እንደሆነ አበክሮ ያስተምራል፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ በእርሱም ደግሞ ሄዶ በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው 1ጴጥ.3፥19
ወስበከ ሎመ ግዕዛነ ለእለ ውስተ ሲኦል
ትርጉም፡- በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነጻነትን ሰበከላቸው ጌታ ኢየሱስ ቅዱስ ሥጋው በመስቀል ላይ እንዳለ ቅድስት ነፍሱ ወደ ሲኦል ወረዳ በሲኦል የነበሩ ነፍሳትን እንዳወጣት ሲኦልንም እንደበረበረቻት የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡፡
ከዚህ ውጭ በሲኦል ያሉ ነፍሳት በቅድስት ማርያም ይሁን በሌሎች ቅዱሳን አማካኝነት ከፍዳ ወጡ ብሎ ማስተማር ስህተት ነው፡፡ 
የሲኦልና የገነት መክፈቻ ያለው ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነው፡፡
አምላካን እግዚአብሔር በኀጢአት የወደቀውን የሰውን ልጅ ለማዳን ከፍጡራን መካከል አንድም ሰው እንዳላገኘ በበደሉ ምክንያት ከአምላኩ ጽድቅ የጎደለው ሰውም ሌላውን ለማዳን ቀርቶ ራሱንም ለማዳን በጌታ ፊት እንደማይቆም ቅዱሳት መጻሕፍት በግልጥ ይመሰክራሉ ኢሳ. 64፣6
        በመሆኑም ‹‹በፈጣሪና በፍጡራን መካከል ድንግል ማርያምን ማድረግ ስህተት ከመሆኑም በላይ የኢየሱስ ክርስቶስን ፍጹም መካከለኛነት የሚቃወም የክህደት ድርሰት ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔርነቱ እግዚአብሔርን ወክሎ፣ እንደ ሰውነቱ የሰው ዘሮችን ሁሉ ወክሎ መካከለኛ የሆነ ብቸኛው አስታራቂ ጌታ ኢየሱስ እንጂ ድንግል ማርያም አይደለችም ‹‹አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ እርሱም ሰው የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው››1ጢሞ. 3፣5 እንዲል አባቶችም በኪዳኑ ወአረቀ ትዝም ደስብእ የሰውን ዘር ሁሉ አስታረቅህ›› ብለዋል፡፡
ሊቁ ኪዳነ ወልድ ክፋሌም እንዲህ ብለዋል ፡፡
አምላክና ሰው መካከለኛ
የሰማይ የምድር ምሰሶ ዳኛ
ከመሃል ቆሞ እንደ አምደወርቅ
አባቱን ከእኛ የሚያስታርቅ
ስለ እኛ በደል ሲያቀርብ ካሳ
ወድቆ የሚሰግድ እጅ የሚነሳ፡፡
መጽሐፍ እንደሚል ሊቃውንት አባቶችም እንዳስተማሩን ሰውንና እግዚአብሔርን ያስታረቀ ብቸኛው መካከለኛ ጌታ ኢየሱስ ሆኖ ሳለ ዘርዓያዕቆብና ግብረ በላ ደባትሮቹ ባለማስተዋል የክርስቶስን መካከለኛነት ለተለያዩ የአንቀላፉ ቅዱሳንና መላእክት በመስጠት ጌታን ሲያስቆጡት ኖረዋል፤ እንግዲህ መልእክቱ ፈጽሞ መጽሐፍ ቅዱስ ጋር የማይስማማ ድርሰት ነው  መሪጌቶቻችን ሌሊቱን በሙሉ ሲዘምሩት የሚያነጉት እንደ እውነቱ ከሆነ በዚህ በጽጌ ወራት ወቅት እግዚአብሔር ብቻ የሚመሰገንበት ምስጋና ቢሆን ከረሀብ መዝገብ ላልወጣችው ሀገራችን እንዴት ዐይነት የበረከት ምንጭ በጎረፈላት ነበር
ነገር ግን አምላኮአችን ቅይጥ፣ ምስጋናችን ውሸት፣ ጩኸታችን ከንቱ ጩኸት፣ዝማርያችን አድራሻ የሌለውና ጸሎታችን ድጋም ሆኖብን በበረከት ፈንታ መርገምን ለልጅ ልጆቻችን እያወረሰን እንገኛለን እግዚአብሔር ወደ እውነት ይምራን!! በየሳምንቱ ይቀጥላል፡፡

26 comments:

 1. First who are you? What is your faith? If you have your own faith and if you are not have the sprit of God, just follow your own way. The Ethiomedia orthodox church never comes to you. Why are you doing devils activity. If you not believe, just leave for the believers. Even Jesus didn't say to go you are doing. You are the son of devils. You are collapsing the truth to false.
  God bless you!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እውነትን ሀሰት ሀሰትን እውነት ከሚሉ ከጨለማው ወገን ሰራዊት መካከል ሆነው ሲያበቁ እንዲህ ያለ የድፍረት አስተያየት በመስጠትዎ ታዘብኩዎት።
   ለምሳሌ በዚህ 2007 ዓመት ጥቅምት 2 የሚዜመው እንዲህ ይላል፡- በከመይቤ መጽሐፍ ማዕከል ፈጣሪ ወፍጡራን፣ ለእረፍት ዘኮንኪ ጽላተ ኪዳን ብኪ ይትፌስሁ ዘገነተ ጽጌ ጻድቃን ወብኪ ይወጽኡ ኀጥእን እምደይን፡፡

   ትርጉም፡- መጽሐፍ እንደሚል በፈጣሪና በፍጡራን መካከል መካከለኛ የሆንሺ የኪዳነ ጽላት ማርያም ሆይ በአንቺ የገነት ጻድቃን ደስ ይላቸዋል ኀጥአንም ከደይን ይወጣሉ ማሕለተ ጽጌ

   ወብኪ ይወድኡ ኀጥአን እምዲይን
   ኀጥአን ከደይን ባንቺ ይወጣሉ፡፡
   መጽሐፍ ቅዱስ በሲኦል ለነበሩ ነፍሳተ ሲኦል የምሥራችን ሰብኮ ከሲኦል ያወጣቸው ጌታ ኢየሱስ እንደሆነ አበክሮ ያስተምራል፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ በእርሱም ደግሞ ሄዶ በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው 1ጴጥ.3፥19
   ወስበከ ሎመ ግዕዛነ ለእለ ውስተ ሲኦል
   ትርጉም፡- በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነጻነትን ሰበከላቸው ጌታ ኢየሱስ ቅዱስ ሥጋው በመስቀል ላይ እንዳለ ቅድስት ነፍሱ ወደ ሲኦል ወረዳ በሲኦል የነበሩ ነፍሳትን እንዳወጣት ሲኦልንም እንደበረበረቻት የቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት ይመሰክራሉ፡፡
   ከዚህ ውጭ በሲኦል ያሉ ነፍሳት በቅድስት ማርያም ይሁን በሌሎች ቅዱሳን አማካኝነት ከፍዳ ወጡ ብሎ ማስተማር ስህተት ነው፡፡
   ይህንን እውነት ስህተተት መሆኑን የሚናገር አንድ እንኳን ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ያቅርቡ እስኪ ምንም እንደማያገኙ እመሰክርሎታለሁ ስለዚህ ከእውነት ጋር ቢስማሙ ይመረጣል

   Delete
  2. Ethiomedia is not equivalent to Ethiopia

   Delete
  3. Which one should come first?The Bible or the church?As to me the church is more truthful than the Bible.B/c the Bible is written through agreement of most protestants in the 16th century but the church is living even before Christ has come to this world.Please,read,learn,pray,fast,worship then you understand

   Delete
 2. First, who are you attempted to correct others? Do you have faith in God? If you have just concern and teach your followers. Why you are you against the truth? I read your argument on the ethiopian orthodox church faith. You are nothing know about orthodox. The enemies always against the truth, and you are one those.
  God bless you!

  ReplyDelete
 3. ተባረኩ እንዲህ ህዝብን ወደ እውነት መምራት ያስደስታል

  ReplyDelete
 4. misteru gelts newu mechem ateredutem

  ReplyDelete
 5. ከጨለማዉ አጋንንት ጋር ተባብረዉ በጨሌማ መንገድ ሰመሩን የነበሩን ዘረያሀቆባዊያን ማሀበረ እርኩሳኑ ዛሬም ለባሀድ አምልኮያቸዉ ሂዝቡን ግራ እያጋቡ ሰለሆነ ጠንቅቀን ለሰሂተታቸዉ መሰመር ማዘጋጀት አለብን። እዉነት ትቀጥናለች እንጅ አትበጠሰም።

  ReplyDelete
 6. good...wey ayiteyiqu.. ayanebu..ayimaru lesidib gin yemiderisibachew yelem...abaselamawoch bemereja ewunet new yetsafut...bechifin mekawem agibab ayidelem.mereja akiribo meweyayet woyim masamen new mihurinet.lela kerito ketenesaw rees gar minm yemayigenagn sidib manisat...tekawumo masemat yalemaweq wutet new.eyeteqawemachihu yalachihut abaselamawochn sayihon ewunetin new.yikir yibelachihu..abaselamawoch beritu kegonachihu nen!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. ክፍል 1
   ስለ ጽጌ ጾም በደንብ ይነበብ

   • "እኔ የምድረ በዳ አበባ ነኝ … በሾህ መካከል ያለ የሱፍ አበባ ያማረ የተወደደ እንደሆነ አንችም በቈነጃጅት መካከል በእኔ ዘንድ እንደዚያ የተወደድሽ ነሽ፡፡" (መኃልይ. ፪፥፩)

   ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ "አይንህን አንስተህ ፍጥረታትን ተመልከት፤ስለ እግዚአብሔር የሚናገሩ አሻራዎቹን በየቦታው ታገኛለህ፤ አይንህን ዝቅ አድርገህ ቅዱሳት መጻሕፍትን አንብብ፤ ስለ እርሱ የሚናገሩ ምሳሌዎችን ታገኛለህ" ይላል (Hymns Against Heresies)፡፡ ለኑሮ ፍጆታ ከሚጠቅመን በተጨማሪ ሥነ ፍጥረት የረቀቀውን ለመመሰል፣ ለአንክሮ ለተዘክሮ (እግዚአብሔርን በፍጥረቱ ለማመስገን) ይጠቅመናል፡፡

   ለዐይናችን ደስታ፣ ለልቡናችን መደነቂያ ይሆኑ ዘንድ ምድርን በአበቦች ሰማይን በከዋክብት ያስጌጠ ሰውን ወዳጁ አምላክ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ከዓመት እስከ ዓመት እግዚአብሔርን ስለመግቦቱ እና ስለ ድንቅ የእጆቹ ሥራዎች ማመስገንን አታስታጉልም፡፡ በዚህ የአበባ ወቅትም እንዲህ እያለች ትዘምራለች፦
   “ነአኲተከ እግዚኦ አምላክነ
   አሠርጎካ ለምድር በሥነ ጽጌያት
   እኩት ወስቡሕ ስመ ዚአከ እግዚኦ” (ዝማሬ ዘዘመነ ጽጌ)

   ትርጉሙም "ምድርን በአበቦች ውበት ያስጌጥካት አምላካችን አቤቱ እናመሰግንሃለን፤ አቤቱ ስምህ የተመሰገነ ፣የከበረ ነው" ማለት ነው፡፡ በሌላም ምስጋና፦
   "ወጻእኩ ውስተ ገዳም እንዘ እሴብሖ ለእግዚአብሔር
   ወበህየ ርኢኩ ኃይለ እግዚአብሔር
   አዳም ግብሩ ዘኢኮነ ኃይሉ ከመ ኃይለ ሰብእ
   አሠርገዎ ለሰማይ በከዋክብት ወለምድርኒ አሠርገዋ በሥነ ጽጌያት
   አዳም ግብሩ አዳም ግብሩ ለወልደ እግዚአብሔር"(እስመ ለዓለም ዘዘመነ ጽጌ)

   ትርጉሙ "እግዚአብሔርን አመሰግን ዘንድ ወደ ምድረ በዳ ወጥቼ በዚያ የእግዚአብሔርን ኃይል አየሁ፤ ሥራው መልካም ነው፤ ኃይሉም እንደ ሰው ኃይል አይደለም፤ ሰማይን በከዋክብት ምድርንም በአበቦች ውበት አስጌጣት፤ የእግዚአብሔር ልጅ ሥራዉ ያማረ ነው" ማለት ነው፡፡
   ይቀጥላል

   Delete
  2. ክፍል 4

   እመቤታችንን ‹አበባ› ካልን ደግሞ ጌታን ‹ፍሬ› እንላለን፤ ቅዱስ ያሬድ በአንቀጸ ብርሃን ድርሰቱ ‹‹አንቲ ውእቱ ዕፅ ቡሩክ ዕፀ ሕይወት ወዕፀ መድኀኒት…ፍሬኪኒ ፍሬ ሕይወት ውእቱ ወዘበልዐ እምኔሁ ሕይወተ ዘለዓለም የሐዩ፤ የተባረክሽ የሕይወትና የመድኀኒት ዕፅ አንቺ ነሺ…ፍሬሽም የሕይወት ፍሬ ነው፤ ከእርሱ የበላ ለዘላለም በሕይወት ይኖራል›› እንዳለ፡፡ በተጨማሪም አባ ጽጌ ድንግል በዚሁ በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ ደግሞ እንዲህ ይላል፦
   ተፈሥሓት ምድር ወሰማይ አንፈርዓፀ
   በዕለተ ጸገዩኪ አብላስ ወአውፅኡ ሠርፀ

   ትርጉሙም ‹‹በለሶች(ኢያቄምና ሃና) አበባ አንቺን በወለዱ ጊዜ፣ ቡቃያ አንቺን ባስገኙ ጊዜ፣ ምድር ደስ ተሰኘች፤ ሰማይም በደስታ ዘለለ›› ማለት ነው፡፡

   ሌላዋ ‹‹በሾህ መካከል ያለ የሱፍ አበባ›› የተባለች እመቤታችንንም የምታጠቃልለው ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ በዚህ ትርጉም ‹ቤተ ክርስቲያን› የሚለው ማኅበረ ምእመናንንም እያንዳንዳቸውን ቅዱሳንንም ያጠቃልላል፡፡ሙሽራዋ ወልደ እግዚአብሔር ሙሽሪት ቤተ ክርስቲያንን ‹እሾህ› በተባለ ክፉ ዓለም መካከል የምትኖሪ ‹የሱፍ አበባ› ነሽ ሲላት ነው፡፡

   በዚህም ምክንያት የሁለተኛው የጽጌ እሁድ ምንባባት ስለ ክርስቶስ እና ቤተክርስቲያን በሙሽሮች የተመሰለ ፍቅር የሚያትቱ ናቸው፡፡ የዚህ እሁድ ምስባክ ‹‹የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፤ ምስጉን ነህ መልካምም ይሆንልሃል። ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።›› የሚል ነው(መዝ. ፻፳፯፥፪)፡፡ የእለቱ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክትም ‹‹ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ። ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው፥ እኔ ግን ይህን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ። ሆኖም ከእናንተ ደግሞ እያንዳንዱ የገዛ ሚስቱን እንዲህ እንደ ራሱ አድርጎ ይውደዳት፥ ሚስቱም ባልዋን ትፍራ” የሚል ነው (ኤፌ. ፭፥፳፰-፴፫)፡፡ ወንጌሉ ደግሞ ‹‹ዮሐንስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ … ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ። እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል”ይላል (ዮሐ. ፫፥፳፯-፴)፡፡

   ድንግል ማርያም ከፍጥረታት ሁሉ በላይ በቅድስና የከበረች መዓዛዋ የመላ (ምልዕተ ጸጋ የሆነች) አበባ ነች፡፡ ቤተክርያቲያንም የክርስቶስን የቅድስና መዓዛ ይዛ ለዓለም የምታሰርጭ ንጽህት አበባ ናት፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ነገር ግን በክርስቶስ

   ይቀጥላል

   Delete
  3. ክፍል 5
   ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን፤ በሚድኑቱና በሚጠፉቱ ዘንድ ለእግዚአብሔር የክርስቶስ መዓዛ ነንና፤ ለእነዚህ ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ለእነዚያም ለሕይወት የሚሆን የሕይወት ሽታ ነን። ለዚህም ነገር የሚበቃ ማን ነው?›› እንዲል(፪ኛ ቆሮ. ፪፥፲፬)፡፡

   በዚህ የትርጓሜ መስመር ቤተክርስቲያን ልዩ ልዩ አበቦች የሞሉባት ገነት (የአትክልት ቦታ)፣ ሙሽራዋ ክርስቶስ የአትክልት ቦታው ባለቤት፣ የአበቦቹ ውበትና መዓዛ የምእመናን ሃይማኖትና ምግባር ናቸው፡፡ በዘመነ ጽጌ ሊቃውንት በማኅሌት እንዲህ እያሉ ያመሰግናሉ፦
   "ወልድ እኁየ ወረደ ውስተ ገነት ከመ ይርዓይ ስነ ጽጌያት
   ትብሎ መርዓት ለመርዓዊሃ ነዓ ወልድ እኁየ ንፃዕ ሐቅለ
   ወናንሶሱ አእፃዳተ ወይን ኀበ ጸገየ ወይን ወፈርየ ሮማን
   ዬ ዬ ዬ ውስተ ገነት ብሒል ውስተ ርስቶሙ ለኲሎሙ ሐዋርያት ብሒል" (ዚቅ ዘዘመነ ጽጌ)

   ትርጉሙም "ልጅ ወንድሜ የአበቦቹን ውበት ያይ ዘንድ ወደ ገነቱ ወረደ፤ ሙሽራይቱ ሙሽራውን፦ልጅ ወንድሜ ሆይ ና ወደ በረሐ እንውጣ፤ወይን ወደአበበባቸው፣ ሮማን ወደአፈራባቸው የወይን ቦታዎች እንዘዋወር፤ዬ ዬ ዬ ወደ ገነት ማለት ወደ ሐዋርያት ሁሉ ርስቶች (ሐዋርያት በእጣ ተከፋፍለው ወደ አስተማሩባቸው አብያተ ክርስቲያናት) ማለት ነው" የሚል ይሆናል፡፡

   ቅዱሳንንም "በእሾህ መካከል እንዳሉ የሱፍ አበቦች እናንተ ለእኔ እንደነዚያ ያማራችሁ ናችሁ" ይላቸዋል፡፡ ያማረ ውበታቸው እና መዓዛቸው የቀና ሃይማኖታቸው እና ምግባራቸው ነው፡፡
   "መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ጽጌ ደንጎላት ወከመ ሮማን ዘውስተ ገነት
   ይትፌሥሑ ጻድቃን የዋሃን ውሉደ ብርሃን
   በትፍሥሕት ዔሉ ውስተ አድባር"(ዚቅ ዘዘመነ ጽጌ)

   ትርጉሙ "የቅዱሳን መዓዛቸው እንደ ሱፍ አበባ፣ በአትክልት ቦታ ውስጥ እንዳለ ሮማን ነው፤ የብርሃን ልጆች የሆኑ የዋሃን ጻድቃን ደስ ይበላቸው፤ በተራሮች ላይ ደስ እየተሰኙ ዞሩ" ማለት ነው፡፡

   ምንም እንኳ ቤተ እስራኤል፣ እመቤታችን፣ ቤተክርስቲያን እና ቅዱሳን ብለን ከፋፍለን ብናያቸውም ፍሬ ነገሩ ግን የተከፋፈለ አይደለም፡፡ ልምላሜ፣ አበባ እና ፍሬ የሃይማኖት፣ የቅድስና እና የምግባር ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ቤተ እስራኤልንም ሆነ
   ቤተክርስቲያንን፣ እመቤታችንንም ሆነ ቅዱሳንን በእግዚአብሔር ዘንድ ያስወደዷቸው የቀና ሃይማኖታቸው እና የተቀደሰ ሥራቸው ነውና፡፡
   ይቀጥላል

   Delete
  4. ክፍል 6

   ከብዙ በጥቂቱ ስለ አበባና ምሳሌነቶቹ ለመናገር ሞክረናል፡፡ አበባ በቅዱሳት መጻሕፍት የያዛቸው ምሳሌያዊ ትርጎሞች እነዚህ ብቻ አይደሉም፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሊቃውንት ‹‹ምሳሌ ዘሐጽጽ፤ ምሳሌ ከተመሳዩ ያንሳል›› እንዲሉ ከእኛ ጋር ለመነጋገር ራሱን ዝቅ በማድረግ ራሱን በአበባ መስሎ ተናገረ እንጂ ምሳሌዎች ስለእርሱ ሊናገሩት የሚችሉት በጣም ጥቂት ነገር ብቻ ነው፤ ስለሌሎቹም እንደዚሁ፡፡

   "ንጉሥ ውእቱ ዘለዓለም ክርስቶስ ፤አሠርገወ ሰማየ በድዱ ወጽጌያት ዘበበዘመዱ…መርዓዊሃ ለቤተ ክርስቲያን መዓዛሆሙ ለቅዱሳን፤ ንጉሥ ውእቱ ዘለዓለም ክርስቶስ ንጉሥ ውእቱ ኢይሠዓር መንግሥቱ፤ ክርስቶስ የዘላለም ንጉሥ ነው፤ የሰማይን መሠረት አሳመረ፤ አበቦችንም በልዩ ልዩ ኅብር አስጌጠ… የቤተ ክርስቲያን ሙሽራዋ፣ የቅዱሳን መዓዛቸው ነው፤ ክርስቶስ መንግሥቱ የማይሻር የዘላለም ንጉሥ ነው" አሜን፡፡
   ወስብሐት ለእግዚአብሔር

   Delete
  5. belew......belew...... mamtatat!!!!!!! minun keminu? bemedhanialem eref, meneshahm medreshahm gira new.......zim bileh ewnetun lemekebel rashen azegaj enji ........endih yale aynen ginbar yargew min yemilut new?

   Delete
 7. አባ ሰላማዎች በት/ታችሁ ደስ ብሎኛል፤ ህዝቡ ስለ መጽሐፉና ትርጉሙ ምንም ሳያውቅና ሳያስታውል በጥቂት መሪጌታዎች ትምህርት ሲነዳ እንደነበር ግልጽ ነው። ለብዙ ሺህ ዓመታትም የኢትዮፕያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በግዕዝ ብቻ ስትሰብክ ስለነበር እነሱ የሚደግሙትን መርገም ይሁን ቡራኬ ትርጉሙ ሳይገባን አሜን እያልን ነበር፤ በወቅቱ ግዕዝ የቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ሰማያዊ ቋንቋም ጭምር እንደሆነ የሚያምኑ ነበሩ። አሁን ቋንቋውን በመተርጎም ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል የሚቃረኑ ተቀጽላ ሐሳቦችን በማጋለጥና አማኙ ትክክለኛውን ግንዛቤ እንድይዝ እያደረጋችሁ ስለሆነ እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርካችሁ።

  ReplyDelete
 8. zelaleme lemekawem setetegu yegeremale yehen hulu zemen teshagera yemetathe betekereseteyane letaremuna sehetete setelu yemataferu lebuna setuthu ke abatuthe egere ser lememare yabekathu

  ReplyDelete
 9. Yekdus Yared Dorset enken yemaywetalet fetsum masthaf kidusawi new sihtet yefetsemew debteraw new

  ReplyDelete
 10. Mergemt yemetama inante menafikan hagerachinin keweresachihu behwala newu.Iski benegestat gize Ethyopian zor bilachihu iyu.Italiyanin yanberekekech,kedemt siltane yeneberat,bread basket of east Africa sitbal yeneberech,gizatwa iske yemen yemiderse,Istaeln betorinet yewegach,Germenin sinde yeredach......Sile geta mekakelnet degmo yersun keab manes yemiyasay aydelem.Bebiluy zemen Ab yebelete metaweku-bewengel zemen weld myebelete metawekunina-kegeta irget behwala degmo menfes kidus metawekun yemiyasay newu inji inante menafikan indemitergumut andu yebelay andu degmo yebetach aydelum.Iski besewu medan wust Iyesus bicha newu dirsha yalewu?abs yelewum?menfes kidusis yelewum? chifin amlakiwoch lezih mels situgn.Iyesus bicha bilo yet lay newu yetesafewu Irsu Irasu Andandochin Kesiol menchikachihu awutu bilwal.Irsu,abna menfes kidus yebhiriy adagn sihonu Imebetachinina kidusan yesitota/yetsega adagnoch nachewu.Beinante bet Bale raiyu yohannis lemelaku yesegedewu iwuket bematatu newu weym tesasitwal.Igna ga gin tirgumu lela newu.Begna betekirstyan Yohannis alawaki newu atilm.Irsun alawaki malet yetsfewu wengel sihitet newu Raiyum haset newu-menfes kidus aladerebetim yasbilal.Silazih yenante tirgum ayaskedim.Beachiru metshaf kidus kebetekirstyan behwala yemeta newu.Kidmiya betekirstiyan yemitlewun bitsemu baltesenakelachihu neber

  ReplyDelete
  Replies
  1. Orthodoxawi hoy Wededum telum ewnet ewnet new wegen......... Anbibu enji, ende abatochachihu endaltemarut enantem begegemaw mekawem bich? enesu enkuan balemawek new mikniyatum manbeb aychilum neber. yenante gin min yemilut chifininet new? manbeb aykelim? lenegeru endatanebut tedegmobachihu yele? eyandandesh gin manbeb yejemersh let gudesh yifelal. bemejemeriya gin ye BIBLE kutrun bebeteseb biyans wede hulet kef enditadergu tiriyachinin enastelalefalen........

   Delete
 11. Abaselama needs to close down for poisoning others with the false information.

  ReplyDelete
 12. Awrew ye sidib af tesetew biloal silezih be Emebetachin lay afachihun kemekifet tekotebu witetun ray yohanesin muluwin miraf anbibu.

  ReplyDelete
 13. ነገር ግን አምላኮአችን ቅይጥ፣ ምስጋናችን ውሸት፣ ጩኸታችን ከንቱ ጩኸት፣ዝማርያችን አድራሻ የሌለውና ጸሎታችን ድጋም ሆኖብን በበረከት ፈንታ መርገምን ለልጅ ልጆቻችን እያወረሰን እንገኛለን እግዚአብሔር ወደ እውነት ይምራን

  ReplyDelete
 14. ተባረኩ እንዲህ ህዝብን ወደ እውነት መምራት ያስደስታል

  ReplyDelete
 15. To Anonymous October 16, 2014 at 7:31 AM
  Which one should come first?The Bible or the church?As to me the church is more truthful than the Bible.B/c the Bible. My brother if you have no bible what do you follow. you said the church who is the church you mean the building or the people? where are the people now?
  if you have no bible you are lost. that why you are lost any ways. Let the Lore open your eyes

  ReplyDelete
 16. ከጨለማዉ አጋንንት ጋር ተባብረዉ በጨሌማ መንገድ ሰመሩን የነበሩን ዘረያሀቆባዊያን ማሀበረ እርኩሳኑ ዛሬም ለባሀድ አምልኮያቸዉ ሂዝቡን ግራ እያጋቡ ሰለሆነ ጠንቅቀን ለሰሂተታቸዉ መሰመር ማዘጋጀት አለብን። እዉነት ትቀጥናለች እንጅ አትበጠሰም

  ReplyDelete