Tuesday, October 14, 2014

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የውይይት ሐሣብና አንድምታው

Read in PDF

ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በቅርቡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ባሉ ገዳማትና አድባራት ከሚገኙ አስተዳዳሪዎችና ጸሀፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ ወይይቱ ከሌሎችም የቤተክርስቲያኒቱ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ጋር እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ በውይይት ሐሳቡ ላይ እንደተናገሩት ውይይቱ በቤተክርስቲያኑቱ አሰራር፣ በምእመናን አያያዝና በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የቅዱስነታቸው ዘመነ ፕትርክና “ተሐድሶ” የሚለውና ከጥንት ጀምሮ ሲሰራበት የነበረው ቃል የቤተክርስቲያንን ትምህርት በራሱ መንገድ እየነዳ ባለውና እውነትንና ተረትን አደበላልቆ ለብዙ ምእመናን ወደሌሎች አብያተ ክርስቲያናት መፍለስ ዋና ተጠያቂ በሆነው በማኅበረ ቅዱሳን በተከፈተበት የሥም ማጥፋት ዘመቻ ምክንያት “ለውጥ” በሚል አጠራር ቢተካም ዞሮ ዞሮ ቤተክርስታየኒቱ ተሐድሶ የሚያስፈልጋት መሆኑን የጠቆመ የውይይት ሐሣብ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡
“ዘመኑን ሳንዋጅ ቀርተን እንዲሁ እያዘገምን፤ አሠራራችን ለሀገርና ለወገን በሚጠቅም ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መንገድ በሳል የሆነ አመራር የማንሰጥ ከሆነ ሳናስበው ራሳችንንና የምንመራውን ሕዝብ አደጋ ላይ ልንጥል እንችላለን” የሚለው የፓትርያርኩ ንግግር ተሐድሶ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ላይ ተሐድሶ ሳናደርግና ዘመኑን ሳንዋጅ ብንቀር ትልቅ አደጋ እንደሚፈጠር የሚጠቁም ነው፡፡  ፓትርያርኩ “ራሳችንን ለመፈተሽ አንዳንድ ተጨባጭ ጥናቶችንና ኩነቶችን” አንስተዋል፡፡ ከእነዚህም አንዱ የምእመናን ቁጥር መቀነስ ነው፡፡ እንደ ፓትርያርኩ ገለጻ “ባለፉት አስር ዓመታት ብቻ በአዲስ አበባ 7 በመቶ ቀንሷል፣ በኦሮምያ 10% ቀንሷል፤ በደቡብ ክልል 7.8 በመቶ ቀንሷል፡፡ ይህ አኃዝ አሁንም እየቀጠለ እንጂ እየቀነሰ አይደለም፡፡

ችግርን መለየት ለመፍትሄው የመጀመሪያ እርምጃ ነው፡፡ ቤተክርስቲያናችን የምእምናኗ ቁጥር መቀነሱን እያመነች ከመጣች የሠነበተች ቢሆንም ምክንያቱን በተጨባጭ አላስቀመጠችም፤ “ሌሎች ወሰዱብኝ፣ ወይም ወደሌሎች ሄዱ” ከሚልና ራስን ከተጠያቂነት ከሚያሸሽ ምላሽ በቀር ትክክለኛውን መፍትሄም አልወሰደችም፡፡ የፓትርያርኩም የውይይት ሐሣብ የምእመናን ቁጥር መቀነስ የሚያስከትለውን የከፋ ውጤት ብቻ የጠቆመ እንጂ የችግሩ ምንጭ ምን እንደሆነ በሚገባ ያስተነተነ አይደለም፡፡ እንደእኔ እምነት የዚህ ችግር ዋናው ምንጭ ራሷ ቤተክርስቲያናችን ናት፡፡
ቤተክርስቲያናችን የስብከተ ወንጌል መምሪያ ቢኖራትም፣ ወንጌልን እሰብካለሁ ብላ ብትናገርም፣ በተግባር ሲታይ ግን የሠውን ልብ የሚያሳርፍና ምን ማድረግ አለብኝ የሚያሰኝ ወንጌል ተሰብኳል ማለት አያስደፍርም፡፡ ለብዙዎች ወንጌልን መስበክ ስለአዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መስበክ አይመስላቸውምና በወንጌል እንሰብካለን ስም ወንጌል ያልሆኑ ለሰው የነፍስ ጥያቄ ምላሽ የማይሰጡ እንዲያውም ጥያቄ የሚፈጥሩ ሌሎች ጉዳዮች ናቸው በስፋት የሚሰበኩት፡፡ አንድ ሰባኪ አዘውትሮ ስለአዳኙ ኢየሡስ ከሰበከ ከመበረታታት ይልቅ መናፍቅ ነው ተሐድሶ ነው የሚል ስም ይሰጠዋል፡፡ ከቤተክርስቲያን በህገወጥ መንገድ ጭምር ይታገዳል፣ ይሰደዳል፣ ይሰደባል፣ ይደበደባል፤ ለሕይወቱ አስጊ ሁኔታዎች ሁሉ ይደቀናሉ፡፡ ስለዚህ ይህን የሚያዩ አንዳንዶች በወንጌል ምክንያት የሚመጣባቸውን ስደት በመፍራት ከሁኔታው ጋር መመሳሰልን ይመርጣሉ፡፡ የተሰቀለውን ክርስቶስን ብቻ ሳይሆን ሌሎችንም ይሰብካሉ፡፡
ከምእመናን ወገን የሆኑ ጭምር መምህራንን ክርስቶስን ብቻ ነወይ የምትሰብከው? ማርያምንም ስበክ እንጂ እያሉ ልዩ ወንጌል እንዲሰብኩ ያስገድዳሉ፡፡ እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች ቤተክርስቲያናችን በስብከተ ወንጌል ዙሪያ ያሉባትን ክፍተቶች የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ስለእኛ ተሰቅሎ የሚተውና በሞቱ ያዳነን ኢየሡስ ክርስቶስ ብቻ ስለሆነ በወንጌል ሊሰበክ የሚገባው እርሱ ብቻ መሆን አለበት፡፡ ይህ የምእመናንን ፍልሰት የሚገታና የፈለሱትንም እንኳን ሊመልሳቸው የሚችል አንዱ መፍትሄ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ ምክንያቱም ወደሌላ የፈለሱት አብዛኞቹ የሚፈልጉት እውነትንና ለነፍሳቸው ጥያቄ ምላሽ የሆነውን ኢየሡስ ክርስቶስን ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም የእርሱን አዳኝነትና አሳራፊነት ሳትቆጥብ፣ ሳትሸራርፍና ሳትደበላለቅ ልትሰብክላቸው ይገባል፡፡
ስለክርስቶስ መሰደድ የሚገባት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ መሰበክ ምክንያት ማሳደድን ሠራዬ ብላ መያዟ እጅግ አስነዋሪና ለቤተክርስቲያን የማይገባ ክፉ ድርጊት ነው፡፡
ሌላው ለምእመናን ፍልሰት መንስኤ የሆነው ማኅበረ ቅዱሳን የተባለው ስብስብ ነው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን መከራዎችና ችግሮች ወንጌልን በሚሰብኩ የቤተክርስቲያን ሰባኪዎች ላይ የሚያመጣው በዋናነት ማኅበረ ቅዱሳንና የእርሱ ግርፎች ናቸው፡፡ ማኅበሩ ከእኔ በቀር ሌላው ሁሉ የተሳሳተ ነው ብሎ የሚያምን የግብዞች ጥርቅም ነው፡፡ ለቤተክርስቲያን ከእኔ በቀር ጠበቃ የለም፣ እኔ ባልኖር ቤተክርስቲያን አትኖርም በሚል ፕሮፓጋንዳ ለእርሱ አስተሳሰብ ያልተገዛውን ወገን ሁሉ መናፍቅ እያለ ሲያሳድድ ነው የኖረው፡፡ ብዙዎችን ያሳደደውም ማርያምን አልሰበኩም ኢየሡስን ብቻ ነው የሰበኩት ብሎ ነው፡፡ የእርሱ ተቀናቃኝ መስለው ከታዩትም መናፍቅ የሚለውን ስም ይለጥፍባቸውና በልዩ ልዩ መንገድ ያሳድዳቸዋል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን እንደትናንትናው ዛሬም በዚህ ክፉ ሥራው እንደቀጠለ ነው፡፡ ማኅበሩ ይህን ማድረጉን እንደ ድልና ቤተክርስቲያንን እንደመጠበቅ ቢቆጥረውም ቤተክርስቲያን ብዙ የደከመችባቸውን ልጆቿን የሚያሳጣና የሚጎዳ ተግባር ነው፡፡ በየስፍራው ማህበሩና ግርፎቹ ያሳደዷቸው አገልጋዮችና ምእመናን አጅግ ብዙ ናቸው፡፡ ስለዚህ በእርሱ መቋቋም ከሰበሰበው ይልቅ የበተነው ይበልጣል፡፡ ታዲያ ለምእመናን ቁጥር መቀነስ ማቅስ ተጠያቂ አይደለምን? ግጥም አድርጎ!!! ስለዚህ ቤተክርስቲያን ምእመናኔ ቀነሱብኝ ብቻ ሳይሆን ለመቀነሳቸው ምክንያቱ ምንድነው? ብላ መፍትሄ መፈለግ አለባት፡፡
ወደሌላው ጉዳይ ሳልፍ በአቡነ ማትያስ የውይይት ሐሣብ ላይ የተነሣው ሌላው ነጥብ በቤተክርስቲያን ውስጥ የተስፋፋውን ሙስናና ብልሹ አሰራር የተመለከተው ነው፡፡ ይህን በዝርዝር ሲያቀርቡ “ፍትህ ማጉደል፣ ፍትህንም ለማጉደል መደለያ (ጉቦ) መቀበል፣ በአካባቢ በመደራጀት ንጹሁን ሰው መበደል፣ ያልደከሙበትን የህዝብን ሀብት ያለአግባብ ማባከን” አንዱ የአደጋው መገለጫ ነው ብለዋል፡፡ በማስረጃ ሲገልጹትም “ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ከአምስት በላይ ከሚሆኑ አድባራትና ገዳማት የተወጣጡ ምእመናንና ካህናት መልካም አስተዳደር አጥተናል በሚል በሰልፍ መጥተዋል፡፡” የአቤቱታው ጥቅል ይዘት ሲቀርብም “በቤተክርስቲያን የተሰጠው ኃለፊነት ተጠቅመው ለራሳቸው ጥቅም የሚሯሯጡ አንዳንድ ሰዎች መኖራቸው በአንዳንድ ቦታዎች ብቻ ሳይሆን በመዋቅር ውስጥ እንደሰንሰለት ተያይዘው ለራሳቸው ጥቅም የሚሰሩ ግለሰዎች መኖራቸው” ተብሏል፡፡ ይህም ለቤተክርስቲያን ቀጣይ ህልውና አደጋና በምእመናን ላይም የልብ ስብራት እያደረሰ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
እንደተባለውም ይህ የቤተክርስቲያናችን አንዱና ትልቁ ችግር ነው፡፡  የቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ጀምሮ የጥቂቶች መክበሪያ ሆኗል፡፡ ከላይ ፓትርያርኩ የገለጹት ችግር የኖረና ከአቡነ ጳውሎስ ዘመን የዞረ ድምር ነው፤ ዛሬም ብሶበታል እንጂ የተስተካከለ ነገር የለም፡፡ ሥራ አስኪያጆችና በየደረጃው በሙስና ሰንሰለቱ ውስጥ የተያያዙ ተወራጅ ሃላፊዎችና ጉቦ አቀባባዮች የችግሩ ፈጣሪዎችና ዋና ተዋናዮች ናቸው፡፡ ይህ በግልጽ እየታወቀ የሚወሰድ እርምጃ ግን የለም፡፡ ክፉዎች እየበረቱና እንዳሻቸው እየሆኑ እውነተኞች ግን የሚገፉባትና መከራቸውን የሚያዩባት ሆናለች ቤተክርስቲያን፡፡ ጩኸት ሲበዛም የጠገበውን ሥራ አስኪያጅ አንስቶ የተራበውን በቦታው መተካት ነው የተያዘው፡፡ እርሱም የድርሻውን አንስቶ ሲጠግብ (ጠግቤያለሁ ባይልም) ይነሳና ሌላው ተረኛ በላተኛ ሥራ አስኪያጅ ይመደባል፡፡ ሙስናና ዝርፊያው የሚፈጸምበት አንዱና የብዙዎችን ሕይወት እየጎዳ ያለው ያለአንዳች ምክንያት ጉቦ በመብላት ብቻ የህገወጥ የሠራተኛ ዝውውር መፈጸም ነው፡፡ ምንም ያላደረገውን ሰራተኛ ያለአንዳች ምክንያት ከሚያገለግልበት ደብር አንስቶ በጀቱ አናሳ ወደሆነ ደብር መቀየርና ዳጎስ ያለ ጉቦ ለከፈለው ሌላ ሰራተኛ ቦታውን መስጠት እነቀሲስ በላይ መኮንን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሚሊየነር የሆኑበት አትራፊ ስራ ሆኗል፡፡ ፓትርያርኩ ይህን አያውቁ ይሆን? በፍጹም ያውቃሉ፡፡ ግን ምንም የመፍትሄ እርምጃ እየወሰዱ አይደለም፡፡ ታዲያ ስለሙስናና ስለፍትህ መጓደል በማውራት ብቻ ፍትሐዊነትን ማስፈን ይቻላል ወይ? ኧረ በፍጹም አይቻልም፡፡
ስለዚህ ፓትርያርኩ በአሁኑ ሰዓት ለፍትህ መጓደል ትልቅ ምክንያት የሆነውን የህገወጥ የሰራተኛ ዝውውር ማገድ፣ አላግባብ የተቀየሩትንም ወደቦታቸው መመለስ፣ ዝውውርን የተመለከተ ሕጋዊ መመሪያ ማዘጋጀትና በዚያ መሰረት መስራት አማራጭ የለውም፡፡ ከምንም በላይ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በር ላይ ተሰልፎና ሰሚ አጥቶ ወደቤቱ የሚመለሰውን ፍትህ እየተጓደለበት ያለውን ሰራተኛና ቦታው በሕገወጥ ደላሎችና ሙሰኞች አየር ባየር የሚሸጥብትን ሰራተኛ ብሶት መስማት ጊዜ የማይሰጠው አሳሳቢ ችግር ነው፡፡ አስፈላጊ ከሆነ የሠው ሃይል ጨምሮ አቤቱታዎችን ማቃለልና ከዚያ በኋላ በሌሎች የመንግስት መሥሪያ ቤቶች እየተደረገ እንዳለው በጥቂት ደቂቃዎችና ሰዓታት ውስጥ ባለጉዳዮችንን ማስተናገድ የሚቻልበትን አሰራር መዘርጋት ነው፡፡ ጉቦ የለመዱትና በሙስና ሰንሰለቱ ውስጥ የሚገኙት ከላይ እስከታች ያሉት ሰራተኞችና ሃላፊዎች ግን እንደዚህ ያለው ስርአት እንዲሰፍን ሳይሆን አሁን ባለው ሁኔታ እንዲቀጥልና በብዙሃኑ ጉዳት እነርሱ መክበር ነው የሚፈልጉት፡፡ ፓትርያርኩ በዚህ ረገድ እርምጃ ካልወሰዱና ፍትህ እንዲሰፍን ካልሰሩ ትልቅ አደጋ ይሆናል፡፡ ከንግግር ወደ ተግባር ቢሸጋገሩ ይመሰገናሉ፡፡
ሌላው ፓትርያርኩ በውይይት ሐሣባቸው ያነሱት የማኅበረ ቅዱሳን ጉዳይ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንን እያወከ የሚገኘው አንድ ማኅበር እርሱም ማህበረ ቅዱሳን መሆኑ እየታወቀ ግን “ማኅበራት” በማለት በብዙ ቁጥር መጥቀሳቸው ከምን የመነጨ እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ እንደተዘረዘረው ማኅበረ ቅዱሳን የኢኮኖሚ ክንዱን ማፈርጠሙና ለቤተክርስቲያን አለመታዘዙ የሚታይ እውነት ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በአጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የተወሰነውና ሀብቱና ንብረቱን እንዲያሳውቅ፣ ኦዲት እንዲያስደርግና በቀጣይ በቤተክርስቲያን ሞዴላሞዴሎች እንዲጠቀም ወዘተ የተላለፈውን ውሳኔ እስካሁን ድረስ አላከበረም፡፡ ለምንድነው የማታከብረው ብሎ የጠየቀውም ሆነ ውሳኔውን ያስፈጸም አካል የለም፡፡ ይህ ለምን ሆነ? ያለፈውን ውሳኔ ማስፈጸም ያልቻለ አስተዳደር ሌላ ውሳኔ ቢወስን ለተፈጻሚነቱ እርገጠኛ መሆን ይቻላል ወይ?
ማቅ በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁከት ፈጣሪ ማኅበር እንደሆነ መናገር ይቻላል፡፡ ሆኖም አሸባሪ የሚለው ስም ለማቅ ይበዛል ባይ ነኝ፡፡ አሸባሪነት የሚለው ስያሜ ያዘለው ፅንሰ ሀሳብና ማቅ ይገናኛሉ የሚል እምነት የለኝም፡፡ በክርስትና ውስጥ አሸባሪነት ሊኖር የሚችልበት እድል የለምና፡፡ ማቅም እያደረገ ያለው ቤተክርስቲያንን የማወክ ተግባር ነውና አዋኪ ድርጊቱ ሊወገዝና አንድ መላ ሊበጅለት ይገባል፡፡ በማቅ ላይ አሁን የሚያስፈልገው ሌላ ውይይት አይመስለኝም፡፡  ከዚህ ቀደም የተላለፉ ውሳኔዎችን ማስፈጸም ነው፡፡ አሊያ የሲኖዶስ ስብሰባ በመጣ ቁጥር የወሬ ዘመቻ መክፈት ለማቅ የልብ ልብ ከሚሰጠው በቀር ምንም የሚፈይደው ነገር የለም፡፡ ማቅም ቢሆን ለቤተክርስቲያን ውሳኔ ራሱን ማስገዛትና መታዘዝ አለበት፡፡ በማን አለብኝነቱ ከጸናና ቤተክርስቲያንን ማወኩን ከቀጠለ ግን ውጤቱ የከፋ የሚሆን ይመስለኛል፡፡
መ/ር አብርሃም

16 comments:

 1. ጐበዝ ይህን ዳንኤል ክብረትን አደብ አይገዛብ እንዴ ተከሳሹ በሌለበት ሲካሄድ የነበረው ለተባለው ማቅ በሐስት ከሶ ስንቱቹን ካህናት በሌሉበት አስወገዛችው ? እንሱጋ ሲሆን ነው እንዴ የፍርድ ሂደቱ ትክክል ኣይደለም የሚባለው ? እንደ አጋግ ስንቱችን ከማህጸነ ቤተክርስቲያን ጨፍጭፋችዋል ? ሞት መሪር ነው ቢሆንም የ ግፍ ጽዋችሁ አሁን ሞልቷል

  ReplyDelete
 2. Mahibere kidusan is equal to Egypt's Muslim brotherhood. The end of mahibere kidusan is coming soon. I can assure you the government will do its next move soon. Just watch. By the way, all the main leaders of mahibere kidusan are from Shewa. This organization is trying to bring back the old days of monarchy.

  ReplyDelete
 3. Mahibere kidusan is equal to Egypt's Muslim brotherhood. The end of mahibere kidusan is coming soon. I can assure you the government will do its next move soon. Just watch. By the way, all the main leaders of mahibere kidusan are from Shewa. This organization is trying to bring back the old days of monarchy.

  ReplyDelete
 4. ማን ይሆን ዕርማት ሊሰጥ የሚችል? ሕዝብ በመምራት ላይ ያለን ሰዎች መንገዱ ሲሠወርብን፤
  ቸልተኞች፤ ዋዘኞች፤ ዘረኞችና ጉበኞች በመሆናችን፤ እንዲሁም ለፈጣሪና ለፍጡር የተመቸን ባለመሆናችን ዕርማት ሰጮቹ
  እነሀብታም አያከብሬ እነድኃ አይምሬ በሽታና ሞት ይሆናሉ።አያድርስ አይጣል አያምጣ አይበል! ካለስ?

  ReplyDelete
 5. ማን ይሆን ዕርማት ሊሰጥ የሚችል? ሕዝብ በመምራት ላይ ያለን ሰዎች መንገዱ ሲሠወርብን፤
  ቸልተኞች፤ ዋዘኞች፤ ዘረኞችና ጉበኞች በመሆናችን፤ እንዲሁም ለፈጣሪና ለፍጡር የተመቸን ባለመሆናችን ዕርማት ሰጮቹ
  እነሀብታም አያከብሬ እነድኃ አይምሬ በሽታና ሞት ይሆናሉ።አያድርስ አይጣል አያምጣ አይበል! ካለስ?

  ReplyDelete
 6. ራሱ ጠይቆ ራሱ የሚመሰክር እርሱ ከሁሉ ያነሰ አስተሳሰብ ያለው ነው የዚህ ጽሑፍ ፀሐፊም እንደዚሁ ነህ፡፡

  ReplyDelete
 7. ማኅበረ ቅዱሳን ለሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ 90 ሺሕ ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

  ReplyDelete
 8. Most of the leader from shewa. They have two wife and 28 girl friend each leader. They have paid church money for sex. They have had contact with terrors. Mk and Ebola is the same.

  ReplyDelete
  Replies
  1. koshasha Balege Mk Betihremit yeminoru ye kidusan Mahber new

   Delete
 9. How killed His Holiness Abune Paoulos. I read Abune Atewos said that abbune make shorten ten years because of his evil advisers. In case some one killed maybe mk?

  ReplyDelete
 10. Papassatu hulu bezemut yetelkefu yemilu abat yehone nacheo .abune matiyas enzihn bemaserejja eyataru bileyuachew tiru neber.ye mk degafiwochum enzihu wenjjelgna yehonut papasat nachew.yenesum neger yetssebebet .

  ReplyDelete
 11. የድኃ ነገር እንዲያው መግደርደር ትንሽ ብትኖረው በዚያች መምቦጥረር ዋናው ጽሑፍ እያለ ባስተያየት ሰጩ ላይ ትችት ማቅረብ ትንሽ ያላት ረፍት የላት ወይም ፍየለ በላ እንደትን ያክላላ ሆኖበት ነው እንጅ
  አስተያየት ሰጩኮ (In the present days,corruptions are any were) ባገር ውስጥና ባለም አቀፍ ደረጃ እየሆነ ያለውንና አሉታ ሊጭኑበት የማይቻል እውነታ ነው ያስቀመጠው ዳሩ ግን (የልቡን ሲነግሩት የኰረኰሩትን ያህል ይስቃል)ነውና ሁሉም በላተኛ ስለሆነ ምን ይደረግ?

  ReplyDelete
 12. የድኃ ነገር እንዲያው መግደርደር ትንሽ ብትኖረው በዚያች መምቦጥረር ዋናው ጽሑፍ እያለ ባስተያየት ሰጩ ላይ ትችት ማቅረብ ትንሽ ያላት ረፍት የላት ወይም ፍየለ በላ እንደትን ያክላላ ሆኖበት ነው እንጅ
  አስተያየት ሰጩኮ (In the present days,corruptions are any were) ባገር ውስጥና ባለም አቀፍ ደረጃ እየሆነ ያለውንና አሉታ ሊጭኑበት የማይቻል እውነታ ነው ያስቀመጠው ዳሩ ግን (የልቡን ሲነግሩት የኰረኰሩትን ያህል ይስቃል)ነውና ሁሉም በላተኛ ስለሆነ ምን ይደረግ?

  ReplyDelete
 13. ያባ ሰላማ ጽሑፍ አቅራቢዎች ይመሰገናሉ ምክንያቱም ወደ ዕውነት ጠጋ ያለውን አመለካከት ያቀርባሉ።
  ሌላው ግን እንደ ሌት ወፍ (እነደ ብልዝ ዓይን) አንዱን መንታ አድርጎ ያቀርባል። የሌት ወፍ እንደዕሥሥት
  ክንፍ ላላቸው ማኅበረ አዕዋፍ ከእናተ ጋር ነኝ ስትል፤ ክንፍ ለሌላቸው ዐይጦች ደግሞ የእናተ ወገን ነኝ አታርቁኝ ትላለች እናም የሰው ልጆች እውነተኞች ሊሆኑ ይገባቸው ነበር ያም ባሆን ወደ ዚያው ጠጋ ያሉ
  ጨርሰው ግን ሸረኞች መሆን አይገባቸውም ነበር፤ ዳሩ ግን ሆነና ምን ይደረግ ባለቤቱ እስቲመልሰው እንዲሁ እንመልከተው።

  ReplyDelete
 14. ያባ ሰላማ ጽሑፍ አቅራቢዎች ይመሰገናሉ ምክንያቱም ወደ ዕውነት ጠጋ ያለውን አመለካከት ያቀርባሉ።
  ሌላው ግን እንደ ሌት ወፍ (እነደ ብልዝ ዓይን) አንዱን መንታ አድርጎ ያቀርባል። የሌት ወፍ እንደዕሥሥት
  ክንፍ ላላቸው ማኅበረ አዕዋፍ ከእናተ ጋር ነኝ ስትል፤ ክንፍ ለሌላቸው ዐይጦች ደግሞ የእናተ ወገን ነኝ አታርቁኝ ትላለች እናም የሰው ልጆች እውነተኞች ሊሆኑ ይገባቸው ነበር ያም ባሆን ወደ ዚያው ጠጋ ያሉ
  ጨርሰው ግን ሸረኞች መሆን አይገባቸውም ነበር፤ ዳሩ ግን ሆነና ምን ይደረግ ባለቤቱ እስቲመልሰው እንዲሁ እንመልከተው።

  ReplyDelete
 15. LEMEHONU YEKEREW KERITO DEGIMO EMINETACHININ LEMEBEREZ METACHIHU ENDE YIKIRIBACHIHU EGIZIABIHER YAYACHIHUAL ENANTE LE EMINET TEKORKUARI MESILACHIHU YELIBACHIHUN LEMEGILETS ATIMOKIRU ENANTE MENAFIKAN EREFU KE EGIZIABIHER KUTA ATAMELITUMNA !!!!!!!!!!!!!!

  ReplyDelete