Wednesday, October 15, 2014

ሰበር ዜና፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያን ቅኝ ገዥ መሆኑን አስታወቁ፡፡“ቤተ ክርስቲያን በማኅበረ ቅዱሳን ቅኝ ግዛት ሥር ወድቃለች!”
(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ) 


ስለ ማኅበሩ ለመናገር ሲጀምሩ “ስለ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ መናገር እፈልጋሉ፤ ይህ ጉባኤ በዓመት አንድ ጊዜ የሚገኝ ነው፤ እድሉ ሊያልፈኝ አልፈልግም” ብለዋል ቅዱስ ፓትርያርኩ፡፡ “ሁሉንም ማወቅ አለባችሁ፤ ስለቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ሁኔታ ያለኝን ልገልጽላችሁ እፈልጋለሁ” ያሉት አቡነ ማትያስ “ቤተ ክርስቲያን በቅኝ ገዥዎች ተይዛለች፤ ማነው ቅኝ ገዥው? አንድ ማኅበር ነው! በምንድን ነው ቤተ ክርስቲያን ቅኝ ግዛት የተያዘቺው? በገንዘብ! ከራስዋ በራስዋ ስም በሚሰበሰብ ገንዘብ ነው!” ሲሉ ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለጉባኤው ገልጸዋል፡፡ አቡነ ማትያስ “ንግር ወኢታርምም” ማለትም ዝም አትበል ንገር፤ አስተምር ተብሏልና እናገራለሁ፤ የቤተ ክርስቲያን ክብርና ልዕልና ተወስዷል፤ ባለፈው ዓመት ማኅበሩ በቁጥጥር ሥር ይግባ ተብሎ ተወስኖ ነበር፤ ነገር ግን እንቢ አሉ፤ ማንስ ጤየቋቸው! እነርሱስ መቼ እሺ አሉና ሲሉ ከአቡነ ጳውሎስ ጊዜ ጀምሮ በየጊዜው እየተወሰነ የሚተላለፍ መመሪያ ሁሉ በግብረ-በላ አባቶችና የቤተ ክህነት ሠራተኞች ሳይፈጸም መቅረቱን ገልጸዋል፡፡
“ቤተ ክርስቲያን ከቅኝ ግዛት ትውጣ፤ ካህናት ከሰቀቀንና ከመከራ ነጻ ይውጡ” ያሉት ፓትርያርኩ ቤተ ክርስቲያን የነጻነትና የሉዓላዊነት ክብሯን አሳልፋ ለማኅበር እንደሰጠችና ነገሮች ወደ አስቸጋሪ ሁኔታ እያመሩ እንደሆነ አመላካቺ የሆነ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ “እኔ ሁለት ቤተ ክርስቲያን አላስተዳድርም፤ የተመረጥሁት አንዲትን ቤተ ክርስቲን ለማስተዳደር ነው፤ ቤተ ክርስቲያንን ለመክፈል አልተቀመጥሁም” ያሉት ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያንን እንደከፈላትና ራሱንም እንደቤተ ክርስቲያን ቆጥሮ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ይህንንም ፓትርያርኩ በዘመናቸው እንዲሆን በፍጹም የማይፈልጉ ነገር መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ነገሩ ሲታይ ከባድ ይመስላል፤ ብዙዎች አቡነ ማትያስ ማኅበረ ቅዱሳንን መነቅነቅ የጀመሩት አብደው ነው እንዴ? በማለት ለማኅበሩ ፕሮፖጋንዳ እየነዙ እርሳቸውንም እያስፈራሩ መሆኑን የተገነዘቡት ፓትርያርኩ “አባ ማትያስ አላበደም፤ እኔ መልእክቴን እያስተላለፍሁ ነው፤ መልእክቴን በጸጋ እንድትቀበሉልኝ ነው የምማጸነው፤ የቤተ ክርስቲያን ችግር ስለሆነብኝ ነው የምናገረው፤ ብታገሠውም ምንም መፍትሔ አላገኘሁም፤ ስለዚህ እናንተ (ጉባኤው) መፍትሔ ፈልጉ” ሲሉ የሚያሳስባቸው የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ 


እንደተጠበቀው የማቅ አጀንዳ መጦዝ ጀምሯል፤ ማኅበረ ቅዱሳን በቤተ ክርስቲያን ስም ገንዘብ ማግበስበስና በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር ሆኖ ያረጀ ያፈጀ የአጼዎችን ፖለቲካ ለማራመድ  ያለው ፍላጎትና ተግባር ፈተና አጋጥሞታል፡፡ ይህን የማቅ ስውር አጀንዳ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ከተረዱትና መታገል ከጀመሩ ብዙ ጊዜው ቢሆንም አባቶች በቅንነትና በገንዘብ በመደለል እስካሁን ድረስ ሲሸፋፍኑለት ቆይተዋል፤ አሁንም በዚህ ቤተ ክርስቲያንን የሚጎዳ ተግባር ውስጥ የቀጠሉ አባቶች ብዙ ናቸው፡፡   
ቅዱስ ፓትርያርኩ በተለይ የማኅበሩን ችግር በተመለከተ ያስተላለፉትን መልእክት በንግግራቸው መጨረሻና ትኩረትን በሚስብ መልኩ ማቅረባቸው የጉባኤው ዋና ነጥብ እንዲሆን አድርጎታል፤ ሁሉም የጉባኤው ተሳታፊዎች በጉዳዩ ላይ በምሳ ሰዓት ከፍተኛ አጀንዳ ያደረጉት መሆኑን በየቦታው ይደረግ ከነበረው ውይይት መረዳት ይቻላል፡፡
አንዳንድ የፓትርያርኩን አሳብ የሚደግፉ ወገኖች ጉዳዩ አሁን ካለበት ደረጃም ጠንከር ብሎ መያዝ አለበት፤ የማኅበሩ ሕግ የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና ጠብቆ በቤተ ክርስቲያን ሥር ሊያሠራ የሚችል ሆኖ መቀረጽ አለበት፤ ማኅበሩን ያዝ ለቀቅ ማድረግ ተገቢ አይደለም፤ አባቶች ችግሩን ሊረዱና ከማኅበር ይልቅ ቤተ ክርስቲያንን ሊደግፉ ይገባል፤ ብዙ አባቶች ማኅበሩን የሚደግፉት የማኅበሩን ስውር ተልእኮና ተንኮል ባለመረዳት ስለሆነ ሊሠራበት ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ቅዱስ ፓትርያርኩ በመልእክታቸው ያተኮሩባቸው ነጥቦች፡- አዲሱ ዓመት ስብከተ ወንጌልን የምናስፋፋበት፣ ልማትንና መልካም አስተዳደርን የምናረጋግጥበት፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሀብትና ንብረት በአግባቡ የምንይዝበት፣ በዓለም ላይ በተለይም አፍሪካውያን ወገኖቻችንን እየጎዳ ያለውን በሽታ በተመለከተ ጸሎትና ምህላ የምንይዝበት እንዲሁም ወደ ሀገራችን እንዳይገባ መንግሥት እያደረገ ያለውን ጥረት የምንደግፍበትና ሀገራችንን ከአደጋ የምንጠብቅበት ሊሆን ይገባል የሚሉት ናቸው፡፡
ከፓትርያርኩ መልእክት በፊት መዝሙር ያቀረቡት የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል ሰ/ት/ቤት ወጣቶች በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ማካተት የማንፈልገውን ስለ አቦና ስለ ጽጌ የሚያወሳ የተረት መዝሙር ዘምረው ወርደዋል፤ ከጉባኤው ታላቅነትና ከተነበበው ወንጌል ጋር የማይሄድ ተረት ያዘለ መዝሙር ነው፡፡ ነገሩ ዛሬ ጥቅምት አምስት ቀን የአቦ በዓል ስለሆነ ጉባኤውን የአቦ ጉባኤ ለማድረግ ስለፈለጉ ነው፡፡ ጉባኤው የቤተ ክርስቲያን እንጂ ሰው ይሁን ሌላ ፍጡር ያልታወቀ አቦ የተባለ ፍጡር በዓል አይደለም፡፡ ነጻ ያልወጣች ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ በማኅበር ብቻ ሳይሆን በተረት ቅኝ ግዛት ሥር የወደቀች ናት፡፡ ስለዚህ ፓትርያርኩ እንዳሉት ቤተ ክርስቲያን ከማኅበር ቅኝ ግዛት ብቻ ሳይሆን ከተረትም ነጻ ልትወታ ይገባል እንላለን፡፡  
ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ አቡነ ማቴዎስ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር ያሉ መምሪያዎችና ድርጅቶች፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተከናወኑትን ተግባራት በተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በተለመደው መርሐ ግብር መሠረት ለዕለቱ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ጊዜ የተያዘላቸው አህጉረ ስብከት የበጀት ዓመቱን የሥራ ክንውን ዘገባዎች አቅርበዋል፡፡  
33ተኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዛሬ ጥቅምት 5 ቀን 2007 ዓ/ም ተጀምሯል፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ 50 አህጉረ ስብከትና ከውጭ የሚመጡ ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያናችን ተወካዮች የሚገኙበት ይህ አጠቃላይ ስብሰባ የሚወስናቸው ውሳኔዎችና የሚያቀርባቸው አሳቦች በቅዱስ ሲኖዶስ ካልጸደቁ በቀር በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያመጣው ለውጥ ባይኖርም የቤተ ክርስቲያናችን ታላቅ ጉባኤ ነው፡፡ ጉባኤው በሁሉም አህጉረ ስብከትና ድርጅቶች የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት የሚቀርቡበት  ነው፤ በዚህ ጉባኤ አህጉረ ስብከት ሪፖርት ከማቅረብ በተጨማሪ በዓመቱ ውስጥ ከሰበሰቡት የልማትና የሰበካ ጉባኤ አባልነት ክፍያ፣ እንዲሁም ከስዕለትና ከልዩ ልዩ ገቢዎች የሚያገኘውን ገቢ ፐርሰንት የሚያቀርቡበት ስብሰባ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያንን ነጻ የሚወጡ የቤተ ክርስቲያን ውሳኔዎችን የምወስንበትን ጊዜ ፈጣሪ ያምጣልን!  የቤተ ክርስቲን አምላክ ቤተ ክርስቲያንን ከማኅበረ ቅዱሳንም ከተረትም  ቅኝ ግዛት ነጻ ያውጣልን! አሜን፡፡43 comments:

 1. ቀኑ ቀርቧል

  ReplyDelete
 2. enante keristeyanoche idelacuhem selezehe afacuhen zegulen

  ReplyDelete
 3. you are all liars. First of all everyone knows how you are strongly working to divide our beloved church, but the truth is different from this. We Ethiopian Orthodox Tewahido believers protect our loyalty even if we are not Mahibere Kidusan members. MAY GOD SHIELD OUR MOTHER ETHIOPIAN ORTHODOX CHURCH FOR EVER

  ReplyDelete
 4. በለው በለው በለው አለቀላት ማቅ

  ReplyDelete
  Replies
  1. አደጋ አለው አለች የዘሩ ሚስት

   Delete
 5. that is great BRAVO His Holiness

  ReplyDelete
 6. the only way to save the church is to stop the trader MK

  ReplyDelete
 7. ከ400 በላይ ቅጥረኛ ሠራተኛ ይዞ በጎ ፈቃደኛ በነፃ አገልጋይ ማለት፣
  ከ65 በላይ የንግድ ድርጅት ከፍቶ ቅን፣ አሳቢ ተቆርቋሪ አገልገጋይ፣
  ከሚሊየኖች ገንዘብ በነጭ ወረቀት እየተቀበለ እና እየነገደ ሕግ አክባሪ በሲኖዶስ ሕግ ተዳዳሪ የሑሳብ ስሌት አዋቂ መሳይ
  ሊቃውንትንና እና አባቶችን እያሳደደ ተሳዳጅ መሳይ
  ስንቱን ሊቀጳጳስ ሲዘልፍ፣ ስንቱ አገልጋይ ሲሰድብ ቆይቶ ተሰደብኩ ማለት
  የምን ቀልድ

  የተሳደዱት፣ የተሰደቡት፣ የተነገደባቸው፣ እነማን እንደሆኑ አላወቀም

  ReplyDelete
 8. ከ400 በላይ ቅጥረኛ ሠራተኛ ይዞ በጎ ፈቃደኛ በነፃ አገልጋይ ማለት፣
  ከ65 በላይ የንግድ ድርጅት ከፍቶ ቅን፣ አሳቢ ተቆርቋሪ አገልገጋይ፣
  ከሚሊየኖች ገንዘብ በነጭ ወረቀት እየተቀበለ እና እየነገደ ሕግ አክባሪ በሲኖዶስ ሕግ ተዳዳሪ የሑሳብ ስሌት አዋቂ መሳይ
  ሊቃውንትንና እና አባቶችን እያሳደደ ተሳዳጅ መሳይ
  ስንቱን ሊቀጳጳስ ሲዘልፍ፣ ስንቱ አገልጋይ ሲሰድብ ቆይቶ ተሰደብኩ ማለት
  የምን ቀልድ  የተሳደዱት፣ የተሰደቡት፣ የተነገደባቸው፣ እነማን እንደሆኑ አላወቀም

  ReplyDelete
 9. wengel yisebekal...seyitan yiwaredal..yebetekeristian tinsae keribual...yihn degimo endiyasayen enitseliyalen. Bertu abaselamawoch!!

  ReplyDelete
 10. Enate Ethiopians malet MK Abaselama(thahadsowoch)edihum asteyayet sechiwoch endiy yemiyanakurachu sitetu yenate adelem ye aganint new yememihir Girma Wondimun Timirt tketatelu.Egziyabher Ethiopianna hizibochuan yibark ye embetachin yedingil amalajinet ayileyen Amen Amen Amen.

  ReplyDelete
 11. What is going on? is mk this much a treat ? if it is who is responsible to correct the org? why it is always a talking point in the church. this should be resolved.

  ReplyDelete
 12. Ye egziabher fird kerebech.yerkusanu mahber kenu derese kabawo liwelk.yemiyafrubet geta liyasaferachewo new.alwokehm endalut alawokachum libalu .mekemke le mk (mahbere keberowoch) kalu new yemiferdebachu ashebari menal siyansachu new.

  ReplyDelete
 13. ከ400 በላይ ቅጥረኛ ሠራተኛ ይዞ በጎ ፈቃደኛ በነፃ አገልጋይ ማለት፣ ከ65 በላይ የንግድ ድርጅት ከፍቶ ቅን፣ አሳቢ ተቆርቋሪ አገልገጋይ፣ ከሚሊየኖች ገንዘብ በነጭ ወረቀት እየተቀበለ እና እየነገደ ሕግ አክባሪ በሲኖዶስ ሕግ ተዳዳሪ የሑሳብ ስሌት አዋቂ መሳይ ሊቃውንትንና እና አባቶችን እያሳደደ ተሳዳጅ መሳይ ስንቱን ሊቀጳጳስ ሲዘልፍ፣ ስንቱ አገልጋይ ሲሰድብ ቆይቶ ተሰደብኩ ማለት የምን ቀልድ የተሳደዱት፣ የተሰደቡት፣ የተነገደባቸው፣ እነማን እንደሆኑ አላወቀም

  ReplyDelete
 14. Yemimeka beigziabiher yimeka

  ReplyDelete
 15. ante new yemiyalkilih zebaraki

  ReplyDelete
 16. እስከነ ስሙ ማቅ!!! ማቅ ማለት የሀዘን ልብስ ማለት ነው። ይህ ማቅ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን የሀዘን ልብስ ሊገፈፍልን ነው። ነጋዴ፤ ከፋፋይ፤ ሰላይ፤ ነፍሰ ገዳይ፤ ሽፍታና ዘረኛ ማኅበር 2007 የመጨረሻው ዘመን ነው።

  ReplyDelete
 17. Mk called demonstrate to against of Church, Ethiopian gov.and the pateriarc on October9, 2007 at Holy trinity Cathedral in Addis Ababa , Ethiopia. SOURCE Ecadforum.com

  ReplyDelete
 18. ኧረ ጉድ ነው አዬ ጉድ አዬ ጉድ !!!!!!!

  ReplyDelete
 19. ይህን ለፃፍከው ጻድቁ አቦ! ልቡና ይስጡህ ደፋር ቢጤ ነህ, ሌላው ዘገባ ጥሩ ነው።

  ReplyDelete
 20. Mk and Ebola are the same. Time to act for quarantine terror mk. Bravo aba!!!! Yetem tewolde America edeg

  ReplyDelete
 21. Mahebere Kidusan is no less than EPRP. Bad apple in the society. the power struggle with in its leaders has brought its dooms day. Alas for those who follow them blindly. The shining moments for Haimanot Abew has started.

  ReplyDelete
 22. እውነት ነው። ሕግና ሥርዓተ ቤተ ክርስትያን ግድ መከበርና መፈጸም አለበት።የእምነት ጉዳይ ነው።ሊቃ ጳጳሳትም ብሆኑ ለእግዚአብሔር ህግና ስርዓት ለግዙ መንፈሳዊ ግዳታ አለባቸው። ጥቁር ልብስና ቆቡ ብቻ ማድረጉ በእዚአብሔር ሆነ በሰው ዘንድ አያስመሰግንም አያስከብርም። ለእዉነትና ለእግዚአብሔር ቃል መገዛት መታዘዝ አለባቸው። አንድ ቀን አፈር መልበስ አይቀርምና። ገንዘቡም ማህበሩም ሁሉም ኮተታኮተቱ አብሮ አይቀበረም። እንደ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ እውነትን መስክሮ ማለተፈ ደስ ያሰኛል። ለማህበር ገንዘብና ጥቅም መቆም ከጌታቸን ከኢየሱስ ክርስቶም ደም አይበጥም። ክቡር ደም ዛሬም ይፈርዳል። የቀንና የግዜ ጉዳይ ብቻ ነው።አሁንም ደግመን ዳጋግመን እንመሰክራለን የማህበረ ቅዱሳን በቅድስት ቤተ ከርስትያን መወረስና ማስረከብ አለበት። ሁለት የአስራት ካዝና (ሳጥን) ማኖር የቁም ይበቃል። እዉነተኛች አባቶችና ወንድሞች እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ለክርስቶስ መስቀል በአንድ ልብ ከቅዱስ ፓትራያርኩ ጋር ልቆም ያስፈልጋል። ይህች ቀን ታልፋለች። የማያልፈው የእግዝአብሔር ቃል ብቻ ነው። በዉጭ ሀገር እነሆ ቤተ ከርስትያናችን በሦስት ቦታ ለመክፈል እየተዳራጁና እየተቋቋሙ ናቸው። በሰሞኑ በላስቨጋስ የተከፈተው የማህበረ ቅዱሳን ቤተ ከርስትያን ያለ ሀገረስብከቱ ቡራከ ተመርቆ ተከፈቶዋል።የዚህ ዋና አመጸኛው መሪ በሆኑ አባ ገ/ኪዳን ሥርዓተ ቤተ ከርስትያን ሳይጠብቁ በጉልበት አድርገውታል። እዉነት ይህ ነው።

  ReplyDelete
 23. Wonderful article go for it AbaSelama.

  ReplyDelete
 24. በርባን ተፈቶ ኢየሱስ ይሰቀል”???

  የቤተክርስቲያናችንን ክብር የነካው ማነው? የቤተክርስቲያናችንንስ አጥር ሳይገባው የሚነቅል ፡ የሚነቀንቅ ማነው? የቤተክርስቲያናችንንስ ምእመናንን እየነጠቀ ያለ ማነው? ኦርቶዶክሳዊውንስ ጥንታዊ አስተምህሮ በአዲስ የምንፍቅና ትምህርት ሊቀይር ላይ ታች የሚል ማነው? በተሃድሶ ስም የተሰባሰበ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ህብረት አይደለምን?

  ከክርስቶስ ትምህርት ውጭ የሆኑ ለክርስትናም ሃይማኖት ስድብ የሆኑ ከትእቢትና ከንቀት ውጭ ሌላ ፍሬ ያልታየባቸው ፡ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ላይ የክፋት ጦራቸውን የወረወሩ እኒሁ አይደሉምን?
  በስብከታቸው ፡ በመፅሄታቸው በአደባባይ ኦርቶዶክሳዊ ቤተክርስቲያንን እናጠፋት ዘንድ ከውስጧ እንሰግሰግ በማለት በስጋዊ በመንፈሳዊም ህግ የሚያስፀይፍ ስራ የሚሰሩ እኒሁ አይደሉምን?

  የማይገባቸውን ፡ የእነሱ ያልሆነውን ፡ የማያምኑበትን እምነት ፡ ያልለፉባቸውን ምእመናን ለመንጠቅ በግልፅና በስውር የሚለፉ ቅኝ ገዢወች እኒሁ አይደሉምን?

  እንግዲህ እኒህን የሚቃወም አርበኛ ፡ እውነተኛ ፡ የቤተክርስቲያን ወዳጅ መባል ሲገባው በምን መስፈርት “ቅኝ ገዢ” ሊባል ይችላል? ለቤተክርስቲያንስ ከዚህ የበለጠ ምን አንገብጋቢ ስራ ኖሮባት ይሆን ወዳጆቿን ልትገፋ የምትፋጠነው?

  በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን የሚመራው የተሃድሶ ክንፍ ገዳማት ይዘጉ ይላል ፡ ቅዳሴ ይቅር ይላል ፡ ቅዱሳን ስማቸው አይጠራ ፡ መታሰቢያቸው አይደረግ ይላል ፡ ቀሳውስት ዳግመኛ ይጠመቁ ይላል ፡ ጳጳሳት ፈሪሳውያን ናቸው ይላል ፤ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሚመራው ማህበረ ቅዱሳን ደግሞ ገዳማት ይከፈቱ ፡ ይበርቱ ይላል ፤ ቅዳሴ አይታጎል ፡ ቀሳውስት አይጎዱ ፡ መነኮሳት ከባእታቸው አይሰደዱ
  ይላል ፡ ጳጳሳት ክብራቸው ይጠበቅ ፡ የቤተክርስቲያናችንም ልእልና ዝቅ አይበል ይላል፡፡

  እንግዲህ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በማን ላይ ፈረደች? የአትናቴወስ የዲዮስቆሮስ ቤት በማን ላይ ፈረደች? የሊቃነ አይሁድ ህብረት ወንበዴውን ፈቶ መድሃኒቱን እንዳሰቀለ እንዲሁ ፍርድ ተጓደለባት? ወይንስ በርባን ተፈትቶ ኢየሱስ ተሰቀለባት?

  ሊሆን ያለው ከመሆን አይቀርም ፡ ነገር ግን ለክፋትና ለአድርባይነት ለተባበረ ግን ወዮ ወዮታ አለበት፡፡

  ReplyDelete
 25. በርባን ተፈቶ ኢየሱስ ይሰቀል”???

  የቤተክርስቲያናችንን ክብር የነካው ማነው? የቤተክርስቲያናችንንስ አጥር ሳይገባው የሚነቅል ፡ የሚነቀንቅ ማነው? የቤተክርስቲያናችንንስ ምእመናንን እየነጠቀ ያለ ማነው? ኦርቶዶክሳዊውንስ ጥንታዊ አስተምህሮ በአዲስ የምንፍቅና ትምህርት ሊቀይር ላይ ታች የሚል ማነው? በተሃድሶ ስም የተሰባሰበ የፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን ህብረት አይደለምን?

  ከክርስቶስ ትምህርት ውጭ የሆኑ ለክርስትናም ሃይማኖት ስድብ የሆኑ ከትእቢትና ከንቀት ውጭ ሌላ ፍሬ ያልታየባቸው ፡ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ላይ የክፋት ጦራቸውን የወረወሩ እኒሁ አይደሉምን?
  በስብከታቸው ፡ በመፅሄታቸው በአደባባይ ኦርቶዶክሳዊ ቤተክርስቲያንን እናጠፋት ዘንድ ከውስጧ እንሰግሰግ በማለት በስጋዊ በመንፈሳዊም ህግ የሚያስፀይፍ ስራ የሚሰሩ እኒሁ አይደሉምን?

  የማይገባቸውን ፡ የእነሱ ያልሆነውን ፡ የማያምኑበትን እምነት ፡ ያልለፉባቸውን ምእመናን ለመንጠቅ በግልፅና በስውር የሚለፉ ቅኝ ገዢወች እኒሁ አይደሉምን?

  እንግዲህ እኒህን የሚቃወም አርበኛ ፡ እውነተኛ ፡ የቤተክርስቲያን ወዳጅ መባል ሲገባው በምን መስፈርት “ቅኝ ገዢ” ሊባል ይችላል? ለቤተክርስቲያንስ ከዚህ የበለጠ ምን አንገብጋቢ ስራ ኖሮባት ይሆን ወዳጆቿን ልትገፋ የምትፋጠነው?

  በፕሮቴስታንት ቤተክርስቲያን የሚመራው የተሃድሶ ክንፍ ገዳማት ይዘጉ ይላል ፡ ቅዳሴ ይቅር ይላል ፡ ቅዱሳን ስማቸው አይጠራ ፡ መታሰቢያቸው አይደረግ ይላል ፡ ቀሳውስት ዳግመኛ ይጠመቁ ይላል ፡ ጳጳሳት ፈሪሳውያን ናቸው ይላል ፤ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሚመራው ማህበረ ቅዱሳን ደግሞ ገዳማት ይከፈቱ ፡ ይበርቱ ይላል ፤ ቅዳሴ አይታጎል ፡ ቀሳውስት አይጎዱ ፡ መነኮሳት ከባእታቸው አይሰደዱ
  ይላል ፡ ጳጳሳት ክብራቸው ይጠበቅ ፡ የቤተክርስቲያናችንም ልእልና ዝቅ አይበል ይላል፡፡

  እንግዲህ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን በማን ላይ ፈረደች? የአትናቴወስ የዲዮስቆሮስ ቤት በማን ላይ ፈረደች? የሊቃነ አይሁድ ህብረት ወንበዴውን ፈቶ መድሃኒቱን እንዳሰቀለ እንዲሁ ፍርድ ተጓደለባት? ወይንስ በርባን ተፈትቶ ኢየሱስ ተሰቀለባት?

  ሊሆን ያለው ከመሆን አይቀርም ፡ ነገር ግን ለክፋትና ለአድርባይነት ለተባበረ ግን ወዮ ወዮታ አለበት፡፡

  ReplyDelete
 26. ቅኝ ገዠ ሰለፌ

  ReplyDelete
 27. ማህበረ ቅዱሳን ማለት የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስትያን የጀርባ አጥንት ነው፡፡ማህበሩ ከሊቃውንቱ ጋር በመመካከር
   የተዋህዶ ልጆች የሆኑ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በግቢ ጉባኤ ውስጥ ታቅፈው ኃይማኖታዊ ስርአቱ የጠበቀ የቤተክርስትያን ት/ት በኮርስ መልክ እያስተማረ ኃይማኖታቸው እንድያጸኑና ከመናፍቃን ት/ት ራሳቸው እንዲጠብቁ የምያደርግ
   ኃይማኖታዊ ስርአቱ የጠበቀ የወንጌል ት/ት በጋዜጣ፤በመፅሔት በድምፅወምስል የምያስተምርና የምሰራጭ
   ገዳማትና አብነት ት/ት ቤ/ት የምያጠናክር
   በአጠቀላይ ተዋሕዶ ኃይማኖታችን ስርአቷና ትውፊቷ የምያስጠብቅ ማህበር ነው፡፡
  ታድያ ይህን ሁሉ ውንጀላ ለምን ይሆን?ድንግል ማርያም እውነቱን ትግለጥልን?!አፅራረ ቤተክርስትያን ታስታግስልን?! አሜን!!!!

  ReplyDelete
 28. Ke haha ametat befit beneberut ametat betekrestiyanua yejerba atent alneberatem malet new????mk abalat bemulu mk yejerba atent minamen malet yewedalhu.atntwam demewam estenfaswam medahniyalem new.

  ReplyDelete
  Replies
  1. Ante senef astawl be 30 ametat wist min yakil miemenochoan endatach bitekrstiyan tawqaleh mahiberu geter legeter terf leterf tezwawro wongel silsebekenew woyis beye universityw wotatu haymanotun endiawq wengel endimar hagerun endiwod silarege new yemitikesut kesash diablos new esum yegibr abatih new

   Delete
 29. የምስራች ለመላው የተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እፁብ ድንቅ የእግዚአብሔር ሥራ የአባቶች ትንቢት ቀኑ ደርሶና ተፈጽሞ ለማየት ያበቃን አምላከ ቅዱስ ኤልያስ የተመሰገነ ይሁን አንዱ በመጨረሻው ዘመን በቅዱስ ኤልያስ መምጣት ከሚጠረጉት አንዱና ዋነኛው ማኅበረ አጋንንት ዛሬ ደርሶ ለምን እንደደነቀን አላውቅም በቅዱሳን አባቶቻችን ጥሪ ማኅበረ አጋንንት እራሱን (ማኅበረ ቅዱሳን ) ብሎ የሚመጻደቀው ከፈረሰ ሰነበተ መለመላውን የቆሞ መስሎን የነበረ ዛሬ በአባታችን አንደበት መነገሩ ካልሆነ በቀር ከፈረሰ ውሎ አድሯል፡፡ አሁን ሁላችንም ወደ ልቦናችን ልንመለስ ይገባል ሕግና ነብያት ሠንበት ተዋሕዶን የቅዱስ ኤልያስን መውረድ ይዘን ቅድስት ምድር ኢትዮጵያ በተዋህዶ ዓለምን አንድ አድርጋ እገዛች ነው፡፡ቅድስት ምድር ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛና መዳኛ ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር ወልድ ዋህድ ኢትዮጵያ ሀገረ ማርያም እመፍጥረት፡፡

  ReplyDelete
 30. የምስራች ለመላው የተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እፁብ ድንቅ የእግዚአብሔር ሥራ የአባቶች ትንቢት ቀኑ ደርሶና ተፈጽሞ ለማየት ያበቃን አምላከ ቅዱስ ኤልያስ የተመሰገነ ይሁን::በመጨረሻው ዘመን በቅዱስ ኤልያስ መምጣት ከሚጠረጉት አንዱና ዋነኛው ማኅበረ አጋንንት ነው፡፡ዛሬ ደርሶ ለምን እንደደነቀን አላውቅም በቅዱሳን አባቶቻችን ጥሪ ማኅበረ አጋንንት እራሱን (ማኅበረ ቅዱሳን ) ብሎ የሚመጻደቀው ከፈረሰ ሰነበተ፡፡መለመላውን የቆሞ መስሎን የነበረ ዛሬ በአባታችን አንደበት መነገሩ ካልሆነ በቀር ከፈረሰ ውሎ አድሯል፡፡ አሁን ሁላችንም ወደ ልቦናችን ልንመለስ ይገባል ይህም ቅዱስ ኤልያስ ይዞት የመጣው ሕግና ነብያት ሠንበት ተዋሕዶን እንዲሁም የቅዱስ ኤልያስን መውረድ አምነን ቅድስት ምድር ኢትዮጵያ በተዋህዶ ዓለምን አንድ አድርጋ እገዛች መሆኑን አውቀን፡፡ቅድስት ምድር ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛና መዳኛ መሆንዋን እና ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር ወልድ ዋህድ ኢትዮጵያ ሀገረ ማርያም እመፍጥረት መሆንዋን አምነን ለቅድስት ምድር ኢትዮጵያ ትንሣኤ እንዲያበቃን በጸሎታች ልንበረታ ይገባል፡፡

  ReplyDelete
 31. በኹሉም የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ሪፖርት፣ ለማኅበረ ቅዱሳን ኹለንተናዊ የድጋፍ አገልግሎት ከፍተኛ ዕውቅና በተሰጠበትና ይህም በጉባኤተኞች ደማቅ ድጋፍ በተረጋገጠበት እንዲኹም በማኅበሩ ላይ አንዳችም ተቃውሞ ባልተሰማበት ኹኔታ፣ አጠቃላይ ጉባኤው ፀረ – ማኅበረ ቅዱሳን አቋም እንዲይዝና በጋራ መግለጫው እንዲያካትት ጥቂት አማሳኞች የሚያደርጉት ጫና ፓትርያርኩን የበለጠ ከማዋረድ ያለፈ ፋይዳ እንደማይኖረው ታምኖበታል፡፡

  ReplyDelete
  Replies
  1. geta yibarkih edime mastewalin kalsete shibetma enche

   Delete
 32. hulunim heta begizew aderegew.

  ReplyDelete
 33. Ye haymanotachin merin enesma weyese ...ye lebochun mahbere erkusan yealtazezem amba genenenet??? Mk yalesedebna sew mawared mawgeez sira yelachum?? Enante amogash enantew awgaze.egziabheren yemamesegenew yemengeste semaet kulf benante ejje alemehonu.zemawi y alhone leba yalhone gubogna yalhone atasgebum neber.yezemawiyan mahber betelut yismamachwal.

  ReplyDelete