Friday, October 17, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያናችን አንዱ ችግር እንጂ ሁሉንም አይደለም“እስመ ኵሉ ዘእኩይ ምግባሩ ይጸልዕ ብርሃነ ወኢይመጽእ ኀበ ብርሃን ከመ ኢይትከሠቶ ምግባሩ እስመ እኩይ ውእቱ፡፡” “ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፡፡ እውነት የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደሆነ ይገለለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል፡፡” (ዮሐ. 3፥20)፡፡
ይህንን ጥቅስ መሪ ለማድረግ የመረጥንበት ምክንያት በደኅንነት፣ በሕጋዊነትና በኢሕጋዊነት የሚጓዙ ሰዎች ልዩነትና በሁለት ወገን ያለውን አካሄድ አስመልክቶ ቁልጭ ያለ መልእክት ስለያዘ ነው፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሕግ ዕውቀቱ የታወቀ የሕግ መምህር ለሆነው ኒቆዲሞስ በሚገባውና በሚያውቀው የሕግ አካሄድ ግልጽ የሆነ መልእክት ነገረው፡፡ ክፋት የሚሰሩ ሰዎች፣ ማጅራት መቺዎች፣ ሌቦች፣ ነፍሰ ገዳዮች በአጠቃላይ በሕግ ቁጥጥር ሥር ላለመዋል ጨለማንና አሳቻ ሰዓትን በመጠቀም ወንጀል ይፈጽማሉ፡፡ በሕግ ላለመጠየቅ ጨለማን ይመርጣሉ፡፡ እውነት ነው፣ ሕግ የማይገዛቸው ስለሆኑ ሕግ ሲመጣ ሲቃወሙና ሲያምፁ ይታያሉ፣ ታይተዋልም፡፡ ለምሳሌ በአገራችን በቅርቡ የታክሲ ሾፌሮች ለሕግ ተገዙ በሕግ ሥሩ ሲባሉ ምን ያህል እንዳስቸገሩ ይታወቃል፡፡ ውሎ አድሮ ግን የሕግ ልዕልና ተከብሮ በሕግና በደንብ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡
በአንጻሩ በሕግ ልዕልና የሚያምኑ፣ ለሃይማኖታቸውና ለኅሊናቸው የሚገዙ ትክክለኛ ሰዎች ግን ሕግ በወጣ ቁጥር ከመጨነቅና ከመሸበር ይልቅ ሕጉን በማክበር ሃይማኖታቸውን የሚያከብሩበትና ለሕጉም መከበር አዎንታዊ የሚሉትን ነገር ሁሉ እንደ ግብአት በመጠቀም የእምነታቸውን እና የኅሊናቸውን ነጻነት በንጽሕና ጠብቀው ይኖራሉ፡


በዚሁ ወደ ርእሰ ጉዳያችን ስንገባ ሰሞኑን በማኅበረ ቅዱሳንና በቅዱስ ፓትርያርኩ መካከል የተፈጠረው ልዩነት ቅዱስነታቸው በቤተክርስቲያን ስም መነገድ ይቁም፣ ሁሉም ሰው በሕግ ማዕቀፍ መግባት አለበት በማለታቸው ሲሆን በሕግ ልዕልና ፈጽሞ የማያምኑ እና ዓመፅን የተለማመዱ ሰዎች የበግ ለምድ ለብሰው በቤተክርስቲያንዋ ዙሪያና ውስጥ ወንጀል ፈጽመው ከተጠያቂነት ለማምለጥ ሲሉ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ለዚህም የሕግ የበላይነት ይስፈን የሚል የቅዱስነታቸውን ሐሳብ ሸክምና ቀንበር አድርገው ሲወስዱት ታይቷል፡፡
እነዚህ ቡድኖች የቅዱስ ሲኖዶስ አባቶችን በመከፋፈል የግል ጥቅማቸውን ብቻ በማስቀደም፣ አባቶችን በማስፈራራት በሕዝበ ክርስቲያኑም ውስጥ ውጅንብር በመፍጠር ከ20 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያን መራመድ የሚገባትን ያህል ርቀት እንዳትጓዝ ወደኋላ የመጎተት ኢክርስቲያናዊ የሆነ አፍራሽ ሚና በመጫወት በትውልድና በቤተክርስቲያን በአጠቃላይም በሀገር ትልቅ ጉዳት አድርሰዋል፡፡ እያደረሱም ይገኛሉ፡፡ የዚህም ዋና ዋና ማሳያዎች ሰሞኑን በተፈጠረው የቡድኑን ከሕግ አፈንጋጭነት ለቅዱስ ሲኖዶስም ይሁን ለፓትርያርኩ አንታዘዝም ማለት በአንዳንድ አባቶች አይዞህ ባይነትና አበጃችሁ በሚል ስሜት ሲደገፍ ታይቷል፡፡ ለምሳሌ አቡነ ማቴዎስ ከሕገ ቤተክርስቲያንና ከቅዱስነታቸው ትእዛዝ ይልቅ ለዚህ በሕግ የበላይነት የማያምን ቡድን ተላላኪ በመሆን ፓትርያርኩንም ለግድያ እስከ መዛት አልፎ ተርፎም የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አሟሟት ይደርስቦታል በማለት ቅዱስነታቸውን በአደባባይ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ሲያስፈራሩ ተሰምተዋል፡፡
እዚህ ጋ ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ግን የብፁዕ አቡነ ጳውሎስ አሟሟት በድንገት ከመሆኑ የተነሣ ብዙ መላምት እንደነበረ ይታወቃል፡፡ አሁን ወቅቱና ሰዓቱ ደርሶ ግን አቡነ ማቴዎስ የአቡነ ጳውሎስ አሟሟት ላይ ለምን እንደሞቱ፣ በምን እንደሞቱ፣ እንዴት እንደሞቱ፣ በጥንቆላም ይሁን በመርዝ በተጨባጭ የሚያውቁትን መረጃ እንዳለ በግልጽ አስቀምጠዋል፡፡ ይህ መረጃ የብዙ ምእመናንና የሕዝብ ጥያቄም ጭምር በመሆኑ የሕግ ሰዎችና የሚመለከታቸው ሁሉ ብዙ ርቀት ሊሄዱበት እንደሚገባ በአንክሮ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
አቡነ ማቴዎስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያውቁትን መረጃ ብቻ በመጥቀስ አላቆሙም፡፡ ይልቁንም ይህ ተግባር በቅዱስነታቸውም ሊደገም እንደሚችል ዝተዋል፡፡ ስለዚህ እኛ ማለት የምንችለው ይህ ማኅበር 3ኛ አማራጩን ትቶ አንድም በተመዘገበበት ደንብና ሥርዓት የቤተክርስቲያኗን አደረጃጀት ጠብቆ በሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ሁኖ ቁጥጥር ቢደረግበት አሊያም በጨለማ የሚሰራውን የፖለቲካ አካሄድ የአገሪቱን ሕግ ተጠቅሞ በብርሃን ፖለቲካውን ቢያራምድ ይሻለዋል እንላለን፡፡ አለበለዚያ ግን በአገራችን እንደሚነገረው ተረት ይሆናል ነገሩ፡፡ ተረቱ ይህ ነው፥ አንድ ካህን ናቸው አሉ፣ ባለቤታቸው አርብ ማታ ለቅዳሜ ዋዜማ እህል ይፈጫሉ፡፡ ቄሱም በሚስታቸው ሥራ ተቆጥተው የተፈጨውን እህል ከአፈር ይቀላቅሉታል፡፡ ሚስታቸው ለምን ብለው ቢጠይቁ ቅዳሜ ገብቷል በበዓል አይፈጭም ይላሉ፡፡ ሚስታቸውም የዋዛ አልነበሩምና አንድ መላ ይፈጥራሉ፡፡ ዶሮ አሳርደው ጣፋጭ የሆነ የዶሮ ወጥ ሰርተው አርብ ማታ እራት ያቀርቡላቸዋል፡፡ ቄሱም ለመብላት ሲሰናዱ ሥጋ መቅረቡን አይተው ይቆጣሉ፡፡ ሚስትየውም ይብሉ እንጂ ጌታዬ ለምን ይቆጣሉ? ቢሏቸው፣ በቁጣ ዛሬ አርብ ነው በማለት ይበልጥ ያፈጣሉ፡፡ ሴትየዋም እህል ሲፈጩ ቅዳሜ ነው በማለታቸው፣ ሥጋ ሲያቀርቡላቸው ደግሞ አርብ ነው በማለታቸው ግራ ተጋብተው እንዲህ ሲሉ ባላቸውን ተናገሩ፡፡ “አርብ ነው ይበሉ እንፍጭበት፣ ቅዳሜ ነው ይበሉ እንብላበት” አሉ፡፡ ምን ለማለት እንደፈለግን ግልጽ ይመስለናል፡፡
ማቅም ከላይ እንደገለጽነው ሃይማኖታዊ ነኝ እያለ ዓላማው ቤተክርስቲያንን መቆጣጠርና ፖለቲካዊ ጉዞውን ማጠናከር ነው፡፡ በቅድሚያ ማንም እንዲረዳልን የምንፈልገው ማቅ ይፍረስ ሳይሆን ይስተካከል የሚል አቋም ነው ያለን፡፡ ምክንያቱም በማቅ ውስጥ ድብቅ አጀንዳ ያላቸው ጥቂቶች ብቻ ሳይሆኑ ብዙዎቹ ለቤተክርስቲያኒቱ ቅናት ያላቸው ገንዘባቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ሳይሰስቱ በመስጠት የሚያገለግሉ ናቸውና፡፡ ማቅ ለቤተክርስቲያን የችግሩ አንድ አካል እንጂ ሁሉንም አይደለም፡፡ ቤተክርስቲያን የምታተርፈው ደግሞ ማቅ በመፍረሱ ሳይሆን ማቅ ወደ ትክክለኛው መሥመር በመግባቱ ነው፡፡ ማቅ ወደ መሥመር እንዳይገባ ግን የእርሱ ተላላኪ የሆኑ ጳጳሳት አይዞህ ባይነት የልብ ልብ ሰጥቶታል፡፡ በአሁኑ ወቅት በተለይ አቡነ ማቴዎስ ያላቸውን ሥልጣን ተጠቅመው ለማቅ ያልተመቹትን ሰዎች ከሥራ በማባረርና በማንሳፈፍ፣ ለማቅ የሚጠቅሙ ሰዎችን ደግሞ በየቦታው በመሰግሰግ ከፍተኛ ድጋፍ እያደረጉለት እንደሚገኙ የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ስለዚህ ሥልጣናቸውን ለማቅ ዐላማ ማስፈጸሚያነት እየተጠቀሙበት ያሉትን አቡነ ማቴዎስን አንድ ማለት ተገቢ ነው፡፡ አሁን እየተካሄደ ባለው የሰበካ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ አባ ማቴዎስ ፓትርያርኩ ይህ ጉባኤ ሳይበተን በማቅ ላይ አንድ ውሳኔ ማሳለፍ አለብን በማለት ያስተላለፉትን መመሪያ ተግባራዊ ላለማድረግ ጉባኤው በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ እንዳያተኩር አቅጣጫ የማሳት ሥራ እየሰሩ እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነው፡፡
ከላይ እንደገለጽነው የቤተክርስቲያኒቱ ችግር ማቅ ብቻ አይደለም፡፡ ማቅ አንዱ ችግር ነው፡፡ ከማቅ በተጨማሪ ትልቅ ችግር የሆነባትና የቤተክርስቲያኒቱን አገልጋዮች ያማረረው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የምክትላቸው ብልሹና በሙስና የተዘፈቀ አስተዳደር ነው፡፡ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የጥቂቶች መክበሪያ የብዙኃን አገልጋዮች መሰቃያ ስፍራ ከሆነ ውሎ አድሯል፡፡ ከዘበኞች ጀምሮ በጉቦ ነው የሚሠራው፡፡ ጉቦ የሰጠ ባለጉዳይ ሰተት ብሎ ሲገባ ጉቦ አንሰጥን ያሉ ግን በሩ ላይ ተኮልኩለው ፀሐይ ሲቀቅላቸው ይውላሉ፡፡ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን ለተመለከተ በአገሪቱ ላይ መንግሥት አለ ወይ የሚያሰኝ ነው፡፡ ሥራ አስኪያጁ ቀሲስ በላይ መኮንንና ምክትላቸው ኃይለማርያም ቤተክርስቲያኒቱን በሊዝ እየቸበቸቧት ነው፡፡ እነዚህ እስካሁን ጠያቂ አካል ያልተነሳባቸው ሙሰኞች ጩኸቱ ሲበዛ በቅርቡ መነሳታቸው አይቀርም፡፡ ነገር ግን እንደከዚህ ቀደሞቹ ሙሰኞች ሥራ አስኪያጆች እንደነአባ ገብረሚካኤል (አሁን አቡነ እስጢፋኖስ) እንደነፋንታሁን ሙጬ እና ንቡረእድ ኤልያስ ወዘተርፈ ስላደረሱት የአስተዳደር በደልና ስለመዘበሩት የቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት ሳይጠየቁ ወደ ጵጵስናና ጠቅላይ ቤተክህነት አንድ ቢሮ ተዛውረው እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡ እነርሱ ያፈናቀሉትና ያንሳፈፉት ሰራተኛ ግን ከነቤተሰቦቹ ለብዙ ችግርና እንግልት ተጋልጦ ዓመታትን በሰቆቃ ያሳልፋል፡፡
የጥቅምትና የግንቦት ሲኖዶስ በመጣ ቁጥር ሕገወጥ ዝውውርና ማንሳፈፍ የተለመደ ስለሆነ አንዳንድ ጸሐፊዎች ከሥራ አስኪያጆች ጋር ተመሳጥረው ጉቦ ክፈል አሊያ ትዛወራህ እያሉ ብዙዎችን የሚያስፈራሩበትና የሚያፈናቅሉበት ወቅት ነው፡፡ አንድ ሰው የቅያሬ ደብዳቤ ከተጻፈበት አለቀለት፡፡ በምን ምክንያት፣ በምን የሕግ አግባብ እንደተቀየረ ሳያውቅ ወደሌላ ደሞዙ አነስተኛ ወደሆነና ከመኖሪያው እጅግ ወደራቀ ቤተክርስቲያን ይዛወራል፡፡ በዝውውሩ መካከል በሙስናው ሰንሰለት ውስጥ የሚገኙ ሹሞችና ደላሎች ግን ዳጎስ ያለ ገንዘብ ያጋብሳሉ፡፡ አሁን አሁንማ የወር ደሞዛችሁን አዋጡና መኪና ሸልሙኝ አሊያ አስቀይራችሀለሁ ማለት ፋሽን ሆኗል፡፡ ለምሳሌ የማቅ አጨብጫቢ አባ ነአኩቶ ለአብ ወደተቀየረበት ደብር ከመጣ ሁለት ወር ሳይሞላው ካህናቱን አስፈራርቶ መኪና አስገዝቷል፡፡ ለቤተክርስያን ቆሜያለሁ የሚለው ማቅ እንደነአኩቶ ለአብ ያሉ ወዳጆቹ እየፈጸሙ ያለውን ሙስናና የጠራራ ፀሐይ ዝርፊያ ጆሮ ዳባ ብሎ ሲቃወምም ሆነ ሲያወግዝ አይሰማም፡፡ ይህም የሚያሳየው ማቅ ለግል ጥቅሙ እንጂ ለቤተክርስቲያን ጥቅም እንዳልቆመና የሙስናውና የዥርፊያው ተባባሪ መሆኑን ነው፡፡ ለማቅ ሙሰኞች የሚባሉት ለእርሱ ያልተመቹት እንጂ ሙስና የፈጸሙ ሁሉ አይደሉም፡፡ እንዳሻቸው ቤተ ክርስቲያንን እየመዘበሩ ያሉና አይዞህ ከአንተ ጋር ነን ያሉት ግን ለማቅ እውነተኞች ናቸው፡፡ ግን እስከመቼ?     
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና ምክትሉ ጥፋት በደል መቼ በዚህ ያቆምና፡፡ ግንዘብ አለአግባብ አናስበላም ያሏቸውን ደብሮች የሰበካ ጉባኤ አባላትን በሕገወጥ መንገድ እስከመለወጥ ይደርሳሉ፡፡ ከዚያም ከእነርሱ ጋር የጥቅም ትስስር የሚፈጥሩ ሙሰኞችን እንዲመረጡ በማድረግ የቤተክርስቲያንን ጥቅም ረግጠው የግል ጥቅማቸውን ያሳድዳሉ፡፡ ስለዚህ የቤተክርስቲያናችን ችግር ማቅ ብቻ ሳይሆን እነዚህ ሙሰኞችም ናቸውና አንድ እንዲባሉ እንጠይቃለን፡፡
በአዲስ አበባ ሀገረስብከት አድባራትና ገዳማት የምንገኝ ግፉዓን  


17 comments:

 1. It think it is time to say goodbye to MK. The church will be better of without MK. The church has 1900+ history without MK and she should be free of it until the LORD comes back. The church has survived so many hardship in the past because her protector is a living God. MK was conceived in the desert of BLATEN military training camp by the students who went there to train how to kill members of the current regime. There was no any calling from heaven to those people to save the church. The energy to save the derg regime was transformed to saving the church without any calling from above heaven. I was there and witnessed there was no holy or spiritual thing in Blaten. I was one of them in the 6th brigade. Those MK members don't obey any authority either the church or the government. They want to do what they wish. If they are touched they don't hesitate to retaliate with their maximum ability. What is so scary is they can use their well networked members from north to south, east to west to start revolution on the church and the government. This is well conceived and it will be a matter of time. May God protect the church from such MK's evil.

  ReplyDelete
  Replies
  1. You think its a time to say goodbye. Do you think Jesus judge like human being; never ever that can happen. They have the truth and the sprit of God. You guys need to find life and truth instead of attack and against the church of Jesus and people of God.
   God bless you.

   Delete
  2. I think you should make distinction between the holy church that was formed 2000 years ago by the lord Jesus and MK just a mahber that was formed 23 years ago. Members of MK are still part of the holy church if they want to. If they think that they need to be members of MK to be part of the holy church, that is totally wrong. They need to be preached again. MK is just an association not a church. It can be dissolved and the church still will continue to live. But if we think that the existence of the church is based on the existence of MK, that is heresy and a sin against almighty GOD. May God give you wisdom.

   Delete
 2. God bless you guys for you have told us the truth.

  ReplyDelete
 3. Enante yefugnit lijoch, begidachu mahibere kidusanin bbelogachu tastewawekalachu!!!!!!!!

  ReplyDelete
 4. የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች በሪፖርታቸው፣ ማኅበረ ቅዱሳን÷ በተለይ በጠረፋማ አህጉረ ስብከት አዲስ አማንያንን አስጠምቆ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ባደረገበትና የምእመናንን ቁጥር በጨመረበት፤ በተለያዩ ቋንቋዎች የተተኪ መምህራንና ካህናት ሥልጠና ባካሔደበት፤ የአብነት የአዳሪ ት/ቤቶችን እንዲኹም የዘመናዊ ት/ቤቶችን ግንባታ በጀት መድቦ የዲዛይንና ክትትል ሥራ በሠራበትና የግንባታቸውን ጠቅላላ ወጪ በሸፈነበት፤ በቅዱሳት መካናት የልማት ፕሮጀክቶች ቀረፃና በሕግ የማማከር አገልግሎት በሰጠበት፤ በ341 የመንግሥትና የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባደራጃቸው ግቢ ጉባኤያት 200,000 ኦርቶዶክሳውያን ተማሪዎችን በትምህርተ ሃይማኖት ባሠለጠነበት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከፍተኛ ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡

  ReplyDelete
 5. ካሕናቱና ማኅበሩ…እንዴት ተጃመሩ(ተጀማመሩ)???… http://www.dejebirhan.org

  ReplyDelete
 6. We heard the annual percent from AA diocess to bete kehnet for the budget year 2006 is more than 64 million birr which is a record amount. So if the current AA diocess administration is currupt as u mentioned how come they manage to acheive this figure. And we all know zat whatever good mk does u are against it. What annoys me is zat u are against zem for the sake of it.

  ReplyDelete
 7. What joins the devils sprit missions Abay Selma group and the people who are bite the breast of mom orthodox. Machinery Kidusan is the truth son of the orthodox church. As you said and you use ase the leading word the bible word that belongs for Mahibere kidusan.Because they are doing everything in the light in the name of God. But you guys living in the dark, and your activity and your faith is dark.

  ReplyDelete
 8. ማኅበረ ቅዱሳን ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተገንጥሎ ሌላ ቤተ ክርስቲያን ለመመሥረት እየሠራ እንደሆነ ማስረጃ እንዳላቸው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አስታወቁ፡፡ http://www.tehadeso.com/2014/10/blog-post_19.html#more

  ReplyDelete
 9. Mk its time to go where you belong. To the he'll y'all.

  ReplyDelete
 10. MK is the truth son of the orthodox church yes They are but They are not Childern of GOD. MK has nothing to do with God or true Christ follower they just a group of nothing.

  ReplyDelete
 11. May God protect the church from such MK's

  ReplyDelete
 12. 'Abaselemawoch' bemawekim balemawekim yeseytan meliktegnoch nachu.Lenisiha mot yabkachu!!!!!

  ReplyDelete
 13. 'Abaselemawoch' bemawekim balemawekim yeseytan meliktegnoch nachu.Lenisiha mot yabkachu!!!!!

  ReplyDelete
 14. 'Abaselemawoch' bemawekim balemawekim yeseytan meliktegnoch nachu.Lenisiha mot yabkachu!!!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. kikikikikik...........belay, almot bay tegaday timeslaleh........

   Delete